Friday, December 30, 2011

ተጠንቀቁ - ክፍል ሁለት - - - Read PDF

 
ፈሪሳውያን በጥቃቅን ነገሮች ሁሉ ሌሎችን መተቸት ይወዳሉ

ፈሪሳውያንም አይተው እነሆ፥ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ማድረግ ያልተፈቀደውን ያደርጋሉ አሉት። (ማቴ 12:2)
ፈሪሳውያን በአይሁድ ሕግ ከሰው መሬት ላይ ተክል ነቅሎ መብላት ክልክል እንደሆነ ያውቁ ነበር። እዚህ ላይ ጌታን የሚጠይቁት ግን ደቀ መዛሙርቱ ለምን እንደዚህ አይነቱን ነገር በሰንበት ያደርጋሉ ብለው ነው። ፈሪሳውያን በጥቃቅን ነገሮች ሁሉ ሌሎችን መተቸት ይወዳሉ። ማቴዎስ 15:2 ላይ ጌታን "ደቀ መዛሙርትህ ስለ ምን የሽማግሎችን ወግ ይተላለፋሉ? እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና" ብለው ጠየቁት። ሁልጊዜም ሌሎች አማኞችን ተከታትለው ትንሽም እንኳ ቢሆን ጥፋትን ለማግኘት ይሞክራሉ። ሐሰተኛ ወንድሞቻችንም ዛሬ እያደረጉ ያሉት ይህንን ነው።

   ማንም ሰው ታላቅ መሪ ሆኖ እንደዚህ የሚያደርግ ከሆነ በሚያገለግልበት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ፈሪሳውያንን ሊያፈራ ይችላል። ምክንያቱም ብዙውን ጊዜ ሰዎች የመሪያቸውን ባህርይ ነው የሚወርሱት። ይሄንንም በዮሐንስ ራዕይ 2 እና 3 ላይ እናያለን። መሪ የሆነ ሰው ግን ከፈሪሳዊነት የራቀ ከሆነ ተከታዩም ከዚህ ባህሪ የራቀ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ክርስቲያኖች እንደዚህ ካሉ የቤተክርስቲያን መሪዎች መራቅ አለባቸው። ጌታን እራሱን መከተል ነው እንጂ እንደነዚህ ያሉትን የሀይማኖት መሪዎች መከተል የለብንም።

Wednesday, December 28, 2011

የስምአ ጽድቅ ጋዜጣ ሪፖርተር የነበረው ዲያቆን ኅሩይ ባየ ከጋዜጣ ሪፖርተርነቱ ተነሣ፤ ወደ ድረገጽ ሪፖርተርነት ተዛውሯል።

የመለሰ ወጉን ጽሑፎች ቃል በቃል እየገለበጠ፣ እያሳጠረና አንዳንድ የቃላት ለውጥ እያደረገ የእርሱ ሥራ አስመስሎ «የተለወጠ ሕይወት» በሚል ርእስ መጽሐፍ አሳትሞ የነበረውና በሕገ ሥነጽሑፍ ተጠያቂ መሆኑ «ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክህነት ዕዳ» በተሰኘው መጽሐፍ ላይ የተጋለጠውማኅበረ ቅዱሳንን ትልቅ ትዝብት ላይ የጣለው ዲያቆን ኅሩይ ባየ ከስምአ ጽድቅ ሪፖርተርነቱ መነሣቱንና ድረገጽ ላይ እንዲሠራ መመደቡን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ ከህዳር ወር እትም ጀምሮ የህሩይ ስም ከስምአ ጽድቅ ጋዜጣ ላይ መነሳቱንና ስም ወደማይጠቅሱ የወሬ ድረገጾች ላይ እንዲሰራ መመደቡን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሰው መጽሐፍ ሰርቆ በራሱ ስም ካሳተመና ሥራው ከተጋለጠ ወዲህም በቅድስት ስላሴ ኮሌጅ በማታው ክፍለ ጊዜ ይከታተል የነበረውን ትምህርት እንዳቆመና ወደክፍል ገብቶ እንደማያውቅ ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

ጸሎት ወደ ማን ይጸለያል? - - - Read PDF

ጸሎት ማለት «መነጋገር» ማለት ነው። መነጋገር ማለትም «መናገርና ማዳመጥ» ማለት ነው። መናገር ብቻ ጸሎት አይሆንም። ካላዳመጥን መልሱን ላንሰማ እንችላለን። ከማን ጋር ነው የምንነጋገረው? ለሚለው ጥያቄ መልሱ አጭር ነው፤ ሰምቶ መልስ መስጠት ከሚችለው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር ብቻ ነው። እግዚአብሔር ይሰማል ይናገራልም። አባቶቻችን ይህን ሁኔታ ሲገልጡ "ጸሎት ብሂል ተናግሮ ምስለ እግዚአብሔር [ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ማለት ነው] ብለዋል።

 ጸሎት «መናገር እና ማዳመጥ» መሆኑን ከሃና እመ ሳሙኤል እንማራለን «እርስዋም በልብዋ ትመረር ነበር በእግዚአብሔርም ፊት ጸለየች፥ ጽኑ ለቅሶም አለቀሰች እርስዋም አቤቱ የሠራዊት ጌታ ሆይ፤ የባሪያህን መዋረድ ተመክልከተህ ብታስበኝ፤ እኔንም ባትረሳ ለባሪያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም ብላ ስለት ተሳለች» ይላል 1ሳሙ 110-11 ይህ የሃና መናገር ሲሆን መልሱን ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ያዳመጠች መሆኗን ደግሞ፣ ቃሉ እንዲህ በማለት ይመሰክራል «ሴቲቱም መንገዷን ሄደች በላችም ፊትዋም ከንግዲህ ወዲያ አዘንተኛ መስሎ አልታየም» 1ሳሙ 118
 ሃና የራሷን ንግግር ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር በመንፈሱ ለመንፈሷ የተናገረውንም ስላዳመጠች፤ ከዚያን ቀን ጀምሮ ልመናዋን እንደተቀበላት አምና በደስታ መኖር ጀመረች። ከጸሎታችን በኋላ የሸክም መቅለል፣ የመንፈስ እረፍትና የልብ ደስታ ካገኘን እግዚአብሔር ተናግሯል ማለት ነው። ሐዋርያው ዮሐንስ በመልእክቱ «በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደተቀበልን እናውቃለን» ብሏል 1ዮሐ 514-15