Saturday, January 29, 2011

ገድላት እና ድርሳናት በሃገራችን ላይ ያመጡት ችግርና ማለቂያ የሌለው ውሸታችን

ማህበረ ቅዱሳን ደጀ ሰላም በሚባለው ድረ ገጹ ላይ ባስነበበን ጽሑፍ ነጻ ሚዲያዎችን ለማስፈራራት ሞክሯል ዘምስለ ጠዋይ ትጠዊ ከጠማማ ጋር ጠማማ ትሆናለህ እንደተባለው ከወያኔ ጋር መዋል እንዲህ ያለውን ባሕርይ ያስይዛል።

ማሕበረ ቅዱሳን

Monday, January 24, 2011

ሃይማኖት የምንቀበለውና የምንጠብቀው እንጂ የምንሠራውና የምናሻሽለው አይደለም

በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
 
ከታኅሣሥ 29 ቀን ጀምሮ እስከ ዐቢይ ጾም መግቢያ ድረስ ያለው ወቅት /ጊዜ/ ዘመነ አስተርእዮ /የመገለጥ ወራት/ እየተባለ ይጠራል፡፡ በታኅሣሥ 29 ቀን የጌታችን ልደት ስለሆነ በዚህ አምላክ በሥጋ የተገለጠበት በዓል ይከበራል፡፡

Wednesday, January 19, 2011

የታቦት መባዛት ምስጢር

እግዚአብሔርም ሙሴን አለው። ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እንደፊተኞቹ አድርገህ ጥረብ። በሰበርኻቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ። (ዘጸ 34፥1)

Saturday, January 15, 2011

ለሁለቱ ሲኖዶሶች የእርቅ እንቅፋት ሊሆኑ ከሚችሉ ነገሮች - ታምረ ማርያም?

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ እና በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ከተወጋገዙ ዓመታት አልፈዋል። አሁን ለመታረቅ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ስንሰማ እጅግ ደስ ብሎን በጉጉት እየጠበቅነው ነው
ነገር ግን አንዳድ እንቅፋቶች ይኖራሉ ብለን ስለምናምን እነዚህን ጉዳዮች ለውይይት ልንቃርባቸው ወደድን።

Thursday, January 13, 2011

ታቦት - በማህበረ ቅዱሳን እይታ/ትምህርት

ትምህርት ሃይማኖት (የሃይማኖት ትምህርት) በሁለት ይከፈላል፡፡ ይኸውም፦
1ኛ፡- ዶግማ   2ኛ፡- ቀኖና በሚል ነው፡፡
ዶግማ- ቃሉ የግሪክ ሲሆን ፍችውም እምነት ማለት ነው፡፡
ቀኖና- ደግሞ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ሥርዓት ማለት ነው፡፡ ከእነዚህ ከሁለቱ ዶግማ ወይም እምነት አይጨመርበትም፤ አይቀነስበትም፤ አይሻሻልም፤ ችግርና ፈተናም ቢመጣ እስከ ሞት ድረስ አጥብቀን የምንይዘው ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረ፤ ቢመረምር እንጂ የማይመረመር ሁሉን ቻይ አምላክ፤ የሚሳነው ነገር የሌለ ፈጣሪ፤ የሰማይና የምድር ባለቤት የሠራዊት ጌታ ሕያው እግዚአብሔር ነው፡፡

Monday, January 10, 2011

የተደፈነ የውሃ ጉድጓድ (ዘፍ 26፥15-22)

ቤተ ክርስቲያን ወደ ቀደመ ክብሯ መመለስ ይኖርባታል የሚሉ ወገኖች (ተሃድሶዎች) ራዕይ በቀላል ቋንቋ ሲገለጽ፦

ሕይወት ላለው የፍጥረት ወገን እጅግ በጣም ጠቃሚና አስፈላጊ ከሆኑት ነገሮች መካከል ውሃ ግንባር ቀደሙ ነው። ሕይወት ያላቸው ፍጥረቶች ያለ ውሃ ህልውና አይኖራቸውም። በመሆኑም በአርአያ ሥላሴ የተፈጠሩ የሰው ልጆች ኑሮአቸውን ሁሉ የሚመሠርቱት ከውሃ ማግኘት ጋር በተያያዘ መንገድ ነው።

Saturday, January 8, 2011

የኢትዮጵያ ኦርቶስዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያን ታሪክ በአጭሩ - በተሃድሶዎች እይታ።

የቤተ ክትስሪያኒቱን ታሪክ ማወቅ አሁን ያለባትን ችግሮች ከምንጩ  ለመረዳት እና መፍትሔውን ለመሻት ያስችላል።
ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ስትመሠረት የነበረውን የሐገሪቱን ሁኔታ የሕዝቧን ባሕል ወደ ኋላ መለስ ብሎ መቃኘት ተገቢ ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶስዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያን ታሪክ ከማህበረ ቅዱሳን ድረ-ገጽ

በማህበረ ቅዱሳን የተዘጋጀ ዘርዘር ያለ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ

እዚህ ላይ ይጫኑ

Friday, January 7, 2011

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሥር ተመሥርተው እያገለግሉ ያሉ እና የነበሩ ጥንታዊ ማህበራት

በቤተ ክርስቲያን ማህበር ማቋቋም አሁን የመጣ ዕንግዳ ነገር አይደለም የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በማህበር ነበር የተመሠረተችው። አሁንም ማህበር ወይም ጉባኤ ናት  ማህበር ማለት የወንድሞች ኅብረት ማለት ነው። <<ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን>> እንዲል [ጸሎተ ሃይማኖት]

ማህበረ ቅዱሳንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሻሻል አለባት የሚሉ ተሐድሶዎች-ክፍል ሦስት


በክፍል ሦስት የምናያቸው ደግሞ መሃል ሰፋሪ አገልጋዮችን ነው። እነዚህ መሃል ሰፋሪ አገልጋዮች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ እውቅና ያላቸው መድረኩን ተቆጣጥረው የሚኖሩ፤ ዋና ዋና የገንዘብ ቦታዎች ላይ የተቀመጡ ጸሐፊዎች ሒሳብ ሹም ገንዘብ ያዥ፤ አስተዳዳሪዎች ናቸው። ማህበረ ቅዱሳንንም ሆነ ተሃድሶዎችን ይቃወማሉ  የሚቃወሙትም ከጥቅማቸው የተነሣ እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ስለተቆረቆሩ አይደለም።

Wednesday, January 5, 2011

ማህበረ ቅዱሳንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሻሻል አለባት የሚሉ ተሐድሶዎች-ክፍል ሁለት

ክፍል ሁለት
ማህበረ ቅዱሳን
ማህበረ ቅዱሳን በደርግ ዘመን ለውትድርና እንዲሰለጥኑ በተመለመሉ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ብላቴን ላይ የተመሰረተ ማህበር ነው ይላሉ። ማህበሩ በተለያዩ የጻድቃን እና የቅዱሳን ስም በየአካባቢው የጽዋ ማህበር ሆኖ የቆየ ሲሆን ሁሉም ማህበራት ዝዋይ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ዘንድ እየተሰበሰቡ ይማሩ ነበር። ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በሞቱ በዓመቱ የተለያዩ የጽዋዕ ማህበራት አባላት ሙት ዐመት ለማሰብ ተሰበሰቡ ከተሰበሰቡት አንዱ የስማቸው መታሰቢያ የሚሆን ማህበር እናቋቁም የሚል ሐሳብ ሲያመጣ ሁሉም የማህበራት አባላት በነገሩ ይስማማሉ።

Tuesday, January 4, 2011

ማህበረ ቅዱሳንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሻሻል አለባት የሚሉ ተሐድሶዎች።

ክፍል አንድ
ተሐድሶዎች እነማን ናቸው?
ብዙ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ስሄድ የስብከት ካሴት ሳዳምጥ፤ የተለያዩ ሥነ ጽሑፎችን ሳነብ ፡ተሐድሶዎች ተሐድስዎች፡ የሚል ጩኸት እሰማለሁ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሥር የተቋቋመው ማህበረ ቅዱሳን የሚባለው ድርጅት አባላቱም ሆኑ አመራሮቹ ስለተሐድሶዎች  በስብከታቸው እና በጽሑፋቸው ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ ሳያነሱ አያልፉም።

Monday, January 3, 2011

የአባ ሰላማ ብሎግ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
አባ ሰላማ ወይም ፍሬ ምናጦስ፤ ከሳቴ ብርሃን እየተባሉ የሚጠሩት ሰው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ቤተ ክርስቲያንን ወደ ታላቅ ዕድገት ያደረሱ ባለውለታ አባታችን ናቸው ይህች ብሎግ የእርሳቸው መታሰቢያ ትሁንልን።
  ይህች ብሎግ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የተነሡ ሁለት ኃያላን እነርሱም ማህበረ ቅዱሳን እና ቤተ ክርስቲያናችን ተሃድሶ[መሻሻል] ያስፈልጋታል የሚሉ ወገኖች የሚወያዩባት ነጻ መድረክ ናት። በዚህች መድረግ የሰውን ስም ከማጥፋት እና ከስድብ ነጻ በሆነ ሥነ ጽሑፋዊ ጨዋነት መሳተፍ እና አስተያየት መስጠት ይቻላል። የግለሰብን ስም በመጥፎ የሚያነሱ ሥነ ጽሑፍም ሆነ አስተያየት ብሎጓ ፈጽሞ አትቀበልም።
ብሎጓ የሁለቱን ሐሳቦች እና አመለካከቶች ከመጽሔቶቻቸው፤ ከመጻሕፍቶቻቸው እና ከስብከቶቻቸው ያለምንም አድልዎ ታቀርባለች። እንዲሁም ወቅታዊ እና ትኩስ የሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ዜናዎችንም ትዘግባለች።
ይህን የውይይት መድረክ የከፍትንበት ምክንያት የቤተ ክርስቲያናችን ምእመን በተባራሪ ወሬዎች ግራ ሳይጋባ ሁለቱንም በውል ተረድቶ የሚጠቅመውን እንዲይዝ ለመርዳት ነው። እግዚአብሔር አይለየን!