Wednesday, January 5, 2011

ማህበረ ቅዱሳንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሻሻል አለባት የሚሉ ተሐድሶዎች-ክፍል ሁለት

ክፍል ሁለት
ማህበረ ቅዱሳን
ማህበረ ቅዱሳን በደርግ ዘመን ለውትድርና እንዲሰለጥኑ በተመለመሉ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ብላቴን ላይ የተመሰረተ ማህበር ነው ይላሉ። ማህበሩ በተለያዩ የጻድቃን እና የቅዱሳን ስም በየአካባቢው የጽዋ ማህበር ሆኖ የቆየ ሲሆን ሁሉም ማህበራት ዝዋይ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ዘንድ እየተሰበሰቡ ይማሩ ነበር። ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በሞቱ በዓመቱ የተለያዩ የጽዋዕ ማህበራት አባላት ሙት ዐመት ለማሰብ ተሰበሰቡ ከተሰበሰቡት አንዱ የስማቸው መታሰቢያ የሚሆን ማህበር እናቋቁም የሚል ሐሳብ ሲያመጣ ሁሉም የማህበራት አባላት በነገሩ ይስማማሉ።
 ነገር ግን ስም አወጣጡ ላይ አልተስማሙም ነበር አንዱ ማህበረ ማርያም፤ አንዱ ማህበረ ተክለ ሃይማኖት፤ አንዱ ማህበረ ጊዮርጊስ፤ ሌላው ማህበረ ሚካኤል ወዘተ በማለት ሲከራከሩ፤ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ሁላችሁም በቅዱሳን ስም ነው የተመሰረታችሁት ለምን ሁሉንም ትተን ማህበረ ቅዱሳን አንለውም አሉ። ሁሉም ማህበራት በዚህ ተስማምተው ጸሐፊ እና ሊቀ መንበር መርጠው መሥራት ጀመሩ።

አባላቱ በብዛት የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ሲሆኑ በዘመናዊ ሙያ የበለጸጉ ዶክቶሮች፤ ሎዌሮች፤ ኢንጅነሮች፤ የተሰበሰቡበት ማህበር ነው። ከቤተ ክርስቲያን ባለሙያዎችም ጳጳሳት፤ ቀሳውስት፤ መምህራን፤ ዲያቆናት፤ በአባልነት አሉበት።በአባላት ብዛት፤ በአደረጃጀት፤ በኢኮኖሚ አቅም፤ የሚወዳደራቸው የለም።
ማህበሩ በተለያዩ ሀገሮች እና ከተማዎች ታላላቅ የንግድ ማዕከላት አሉት እያንዳዱ አባል አሥራቱን ለማህበረ ቅዱሳን ዋና ማዕከል ይክፍላል፤ የራሱ ሊቃውንት ጉባኤ፤ የልማት ክፍል፤ የትምህርት ክፍል፤ የራሱ ጽሕፈት ቤት፤ በየሀገረ ስብከቱ የራሱ ማዕከል አለው።
የማህብረ ቅዱሳን አባላት በዘመናዊ ትምህርት እንጂ በመንፈሳዊ እውቀት ብዙ የሚመሰገኑ አይደሉም። ነገር ግን ከማንኛውም የቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን በብዙ ይሻላሉ። በቤተ ክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ እውቀት በኩል ከተሃድሶዎች ጋር ሲወዳደሩ የሰማይና እና የምድር ያክል ይራራቃሉ። ነገር ግን ለባህል ፤ ለቅርስ፤ እንዲሁም ለሀገራቸው እና ለአባቶች ወግ ያላቸው ቅናት ከፍተኛ ነው። ማንኛውም የማህበረ ቅዱሳን አባል ሥልጠናውን ከጨረሰ በኋላ ሦስት ዓይነት ከለር ያለው ክር ባንገቱ እንዲያደርግ ይሰጠዋል የማህበረ ቅዱሳን አባል መሆኑ የሚታወቀው በዚህ ነው። ይህን ሁኔታ የተመለከቱ ሰዎች ወደፊት ማህበረ ቅዱሳን የራሱን ቤተ ክርስቲያን መመሥረቱ የማይቀር ነው ይላሉ።

 በአምልኮ ወደ ነፍሳት፤ ወደ መላእክት፤ መጸለይን፤ ለቅዱሳን እና ለመላእክት ሥእል መስገድን አጥብቀው ያስተምራሉ፤ ይጽፋሉ።
በመጻሕፍተ አዋልድ አንዳድ ስሕተቶች እንዳሉባቸው ቢያምኑም ይህን ማሻሻል ያለበት ሲኖዶስ እንጂ እኛ አይደለንም ይላሉ። ይህን የሚሉት ጥቂት የማህበረ ቅዱሳን መሪዎች እንጂ ሌሎች ተራ አባላቶች ምንም ስሕተት የለባቸውም ብለው የሚያምኑ ናቸው።


የማህበሩ ዓላማ
ቤተ ክርስቲያንን በሙያቸው በነጻ ማገልገል፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን ታሪክ በተለያዩ መንገዶች ለምሳሌ በኢግዚብሽን ማስተዋወቅ፤ ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋት ወጣቱ በቤተ ክርስቲያን እንዲታቀፍ ሥልጠና መስጠት የሚል ነው። በመንግሥት ውስጥ ታላቅ ቦታ አላቸው እስከ አምባሳደር የደረሱ የማህበረ ቅዱሳን አባላት አሉ። በሥራቸው ትጉህ ናቸው፤ በገዳማት እና በተለያዩ ያሉ መምህራንን የገንዘብ እርዳታ ለመስጠት ጥረት ያደርጋሉ የአብነት ትምህርት ቤቶችን እንደገና በዘመናዊ መልክ ለማደራጀት ይታገላሉ፤ 
 ሌላም ከዚህ ያለፈ ዓላማ እንዳለው ይታማል።
ማህበሩ የሚታማባቸው ዋና ዋና ነገሮች
 የማህበሩ መሪ የነበረው --- አንዱ ሰው ናዝሬት ላይ በሰይጣናዊ አሠራር ሰው ሊገድል ሲል በፖሊስ ተይዞ በመታሠሩ በማህበሩ ላይ ጥላ አጥልቶበት ነበር። ይህ ሁኔታ እስከ አሁን ድረስ ማህበሩን ጥያቄ ላይ የጣለው ነገር ነው። የማህበሩ መሪ ማርያም መሥዋዕት አቅርቡልኝ ስላለች አንድ ሰው ታንቆ መሞት አለበት በማለት  አንዲትን ሴት አሳምኖ ኖሯል በገመድ ተንጠልጥላ በመንፈራገጥ ላይ እያለች ፖሊስ ደርሶ ከሞት አትርፏታል።
ይህ ድርጊት በፖሊስ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ተሌቭዥን በተከታታይ ሲቀርብ ነበር። ታሪኩ በመጽሐፍም ተጽፎ ይገኛል።
በኋላ ግን ማህበሩ እንደምንም ብሎ ስሙን አደሰ መንፈሳዊ ዝግጅት እያዘጋጀ መንፈሳዊ ጉዞዎችን እያደረገ አባላትን መስብሰብ ጀመረ። ይህን እንቅሥቃሴ በትኩረት የተመለከቱ አቡነ ቴዎፍሎስን ያስገደለው የታላቁ ጉባኤ አባላት ትኩረታቸውን ማህበረ ቅዱሳን አባላት ላይ በማድረግ ስድስት ኪሎ በሚገኘው ምስካየ ሕዙናን መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ግቢ እየነጠሉ በመሰብሰብ አላማቸውን አስቀይረዋቸዋል ይባላል። ማህበሩ የታላቁ ጉባኤ አባላት ከገቡበት ጀምሮ አቡነ ጎርጎርዮስን ለማሰብና ቤተ ክርስቲያንን ለመርዳት የነበረውን አላማውን ትቶታል የሚሉ አሉ።
 ከተመሠረተ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ለምሳሌ ሃይማኖተ አበውን ለማፍርስ ያደረገው እንቅሳቃሴ እና ለአባላቱም የሚሰጠው ስልጠና በዋናነት <<የመናፍቃን ምላሽ>> የሚል ሆነ። በጽሑፉም ሃይማኖተ አበውን የሚያጥላላ ጽሑፍ እያሠራጨ ቆይቶ በደንብ ከተዘጋጀ እና እውቅና ካገኘ በኋላ በየአብያተ ክርስቲያናቱ ቡድን በማደራጀት የሃይማኖተ አበውን አባላት እና ተሃድሶ ናቸው ያላቸውን ሁሉ በመደባደብ በማሳደዱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከ60 ሺህ በላይ አባላቷን አጥታለች እየተባለ ይተቻል።
ሌላው ማህበሩ የሚታማበት ነገር ብዙ የሚያጠራጥር ነው በመጀምሪያ ቤተ ክህነቱን መቆጣጠር ሲሆን ቤተ መንግሥቱንም ማለፍ አይፈልግም ይባላል። የታላቁ ጉባኤ አባላት እንደ የበላይ ጠባቂ ሁነው  የማህበሩ አማካሪ ናቸው፤ ማህበሩ አካሄዱን እንዲያሳምር ያደረጉት እኒህ የታላቁ ጉባኤ አባላት ናቸው  አንዳዶች የሞቱ ሲሆን የተወሰኑት አሉ።[በጠቅላይ ቤተ ክህነት የሚዘጋጀው ጋዜጣ ዜና ቤተ ክርስቲያን እንደዘገበው]።
ማህበረ ቅዱሳን ምሥጢራዊ የሆነ የሥለላ ቡድን አለው ይህ የስለላ ቡድን በዋነኛነት የሚሰልለው ተሃድሶ እና ተቃዋሚዎቼ የሚላቸውን ነው ተቃዋሚዎቹን ሁሉ ተሃድሶ ይላቸዋል ነገር ግን ብዙዎቹ በከንቱ ነው ስማቸው የጠፋው ይባላል። ከዚህ በተረፈ ጳጳሳትን፣ ካህናትን፣ መነኮሳትን፣ ዲያቆናትን ኑሮአቸውን ሕይወታቸውን ይሰልላል የእያንዳዱ ጳጳስና መነኩሴ የሕይወት ታሪክ፤ በቴፕ እና በቪዲዮ የተደገፈ መረጃ ይሰበስባል። ባማህበረ ቅዱሳን ላይ ያመጸ አገልጋይ ቢኖር ይህ መረጃ ይሰጠውና አፉን እንዲይዝ ይደረጋል።
እያንዳዱ የደብር ጸሐፊ እና አስተዳዳሪ ሒሳብ ሹም፣ ቁጥጥር፣ ገንዘብ ያዥ፤ ሰባኪ፤ ወዘተ በሙሉ በማህበረ ቅዱሳን የመረጃ መረብ ውስጥ የገባ ነው። ከማህበረ ቅዱሳን ማምለጥ የማይቻል ነው። ሆኖም ተሃድሶዎችን ግን አልቻሏቸውም ከማህበረ ቅዱሳን አቅም በላይ የሆኑ ቢኖሩ ተሃድሶዎች ብቻ ናቸው። ምክንያቱም ተሃድሶዎች እጅግ በጣም ቁጥብ  በሙስና የማይገኙ ከመሆኑም በላይ ሥራቸውንም በዝግታ ስለሚያካሂዱት ውስጥ ለውስጥ የሚቀጣጠሉ እና የተዳፈኑ እሳቶች ናቸው። አሁን አሁን ማህበረ ቅዱሳን እንደተሃድሶዎች ሆኖ ተሃድሶውችን እየሰለለ ቢሆንም ተሀድሶዎችም በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ በስፋት ገብተው አንዳድ ማዕከላትን ተቆጣጥረው ይገኛሉ። በአሁኑ ሰዓት  የተሃድሶዎች እና የማህበረ ቅዱሳን ሁኔታ አሳሳቢ ነው ነገሩ እየከረረ መጥቷል። ይህ ሁኔታ በቶሎ በሲኖዶሱ ሊፈታ ይገባል በማለት አስተያየታቸውን የሚሰጡ ብዙዎች ናቸው። ይቀጥላል....

4 comments:

 1. ደግሞ እናንተ እነማን ናችሁ? ርእሶቹ ኢንተረስቲንግ ናቸው

  ReplyDelete
 2. ይህ ጽሑፍ በአቡጌዳ ድረ-ገጽ ላይ በመቅረቡ ምክናያት ከተሰጡ አስተያየቶች መካከል ይህንን ሳይት አንዱ አቅራቢ ስለጠቆሙ ነው ያገኘሁትና በመረጃ ላይ የተመሰረቱ አስተማሪ ጽሑፎች የሚቀርቡ ከሆነ ደንበኛችሁ እሆናለሁ::

  ሰላም ይብዛላችሁ

  ሰላም ነኝ
  ከአዲስትዋ ኢየሩሳሌም

  ReplyDelete
 3. እናንተ እነማን ናችሁ ተሀድሶ

  ReplyDelete
 4. slmahber kdusan dkmt kmawrt mahberu lhagrm lbetkrstian ymitkm slhon dkmtun bmassal enditnakr madrg nw. thadso malt protestnant malt nw ythadso guday dgmo ymahbr kdusn aydlm yhulacn ortodox lgoch nw

  ReplyDelete