Saturday, January 15, 2011

ለሁለቱ ሲኖዶሶች የእርቅ እንቅፋት ሊሆኑ ከሚችሉ ነገሮች - ታምረ ማርያም?

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ እና በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ከተወጋገዙ ዓመታት አልፈዋል። አሁን ለመታረቅ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ስንሰማ እጅግ ደስ ብሎን በጉጉት እየጠበቅነው ነው
ነገር ግን አንዳድ እንቅፋቶች ይኖራሉ ብለን ስለምናምን እነዚህን ጉዳዮች ለውይይት ልንቃርባቸው ወደድን።
እንደሚታወቀው ሁለቱም ሲኖዶሶች በተወጋገዙበት ቃለ ውግዘት ውስጥ የኢትዮጵያው ሲኖዶስ በጻፈው ላይ መልክአ ሥእል እና ታምረ ማርያም አያነቡም የሚል ውግዘት እንዳለበት ተመልክተናል። ነገር ግን በአሜሪካው ሲኖዶስ ሥር ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ታምረ ማርያም ከቅዳሴ በፊት እንደሚያነቡ ሰምተናል።
ይሁን እንጂ የታምረ ማርያም ነገር በዚህ እርቅ መፍትሔ ካልተሰጠበት የሰው ስም ማጥፊያ፤ የፖለቲካ መጠቀሚያ እየሆነ ትውልድ ሲያወጋግዝ ሊኖር ይችልላና አብሮ ቢታሰብበት ለትውልድ የሚሆን መፍትሔ ያመጣል ብለን እናምናለን።
መጽሐፉን ለግምገማ ይመች ዘንድ በውስጡ ያለውን ይዘት ጥቂት ለማቅረብ ሞክረናል።
ታምረ ማርያም የሚባለው መጽሐፍ በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን[በ1530 ዓ.ም.] ተጽፎ በየገዳሙ እንደተላከና ደቂቀ እስጢፋኖስ እንደተቃወሙት በዚህም ምክንያት በእሳት ተቃጥለው እንደሞቱ የታወቀ ታሪክ ነው።
ይህ ከጊዜ በሁዋላ ሰርጎ የገባ መጽሐፍ እስከ አሁን ድረስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ልጆች ቀሳውስትን፤ ዲያቆናትን ምእመናንን እየከፋፈለ የሚገኝ አንዳዶችንም ያስደበደበ ከዚያም አልፎ ደም ሲያፋስስ የኖረ መጽሐፍ ነው።
 በመቅድሙ መጀመርያ ላይ ም 1 ቁ 35 ላይ በእሑድ ሰንበት የማርያምን ታምር ለመስማት የማይሄድ ክርስቲያን ቢኖር አባ ገብርኤል እና አባ ሚካኤል በሚባሉ ጳጳሳት ተወግዟል ይላል ስለዚህ ክርስቲያን ነኝ ያለ ሁሉ ከውግዘቱ ለመዳን እሑድ ተገኝቶ ታምረ ማርያም መስማት ግዴታው ነው።
ምእመኑ ታምረ ማርያም ሲባል እንዲሁ በደፈናው ለመስማት እና ለመሳለም ይጣደፋል እንጂ ደም ሲያፋስስ የኖረ መሆኑን በውስጡም ያለውን ይዘት አስተውሎት አያውቅም። ነገር ግን የማርያምን ስም ስለሚጠራ ብቻ ከፍተኛውን ቦታ ይዞ የኖረ መጽሐፍ ነው።
ዛሬም ከቅዳሴ በኋላ በቀሳውስቱ የሚነበብ ሲሆን አንዳድ የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርት የተረዱ ካህናት ግን እየተሸማቀቁ ሲያነቡት ይታያሉ። አብዛኛዎቹ ቀሳውስት በታምረ ማርያም ማንበብ ደስተኛ አይደሉም ነገር ግን ሕዝብ የለመደው ስለሆነ ሕዝቡን ላለማስቆጣት ስለሚጠነቀቁ በግእዝ ሸፋፍነውት ያልፋሉ።  
ለመሆኑ ታምረ ማርያም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ያለው ግጭት ምንድን ነው?
ከዚህ ቀጥለን በመጽሐፉ ውስጥ የሚገኙ አንዳድ ሐሳቦችን በማቅረብ ለፍርድ አቅርበነዋል።
በእንተ እግዝእትነ ማርያም ተገብረ ኩሉ ዓለም በእንተ እግዝእትነ ማርያም ተፈጥሩ አዳም ወሄዋን ትርጉም ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ፤ አዳም እና ሄዋንም ስለ እመቤታችን ተፈጠሩ የዘወትር መቅድም ም 1 ቁ 7
ይህ አባባል መጽሐፍ ቅዱስን ፈጽሞ የሚቃረን ነው። ፍጥረት የተፈጠረው እግዚአብሔርን ለማመስገን ነው። ሰማይና ምድር በሙሉ እንኳ የእግዚብሔርን ክብር እንደሚገልጡ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል መዝሙር 18 ቁ 1። ሰማይና ምድር ለሰው ልጆች ሁሉ የተፈጠሩ የእግዚአብሔር የክብሩ መግለጫ ናቸው እንጂ ለእመቤታችን ተፈጠሩ የሚለው የተጋነነ ውሸት ነው የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንም ጥንታውያን አባቶችም ትምህርት አይደለም።
አዳም እና ሄዋን ለማርያም ተፈጠሩ ማለትስ ምን ማለት ነው? ያን ያህል ዘመን በሲኦል ሲማቅቁ የኖሩት ለማርያም ተብሎ ነውን? ነገሩ ግልጽ አይደለም። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም  የጌታችን እናት በመሆኗ ክብር ይገባታል። ከዚህ ውጭ ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ በምንወዳት በድንግል ማርያም ስም ማጣመም ተገቢ አይደለም።
ወቅድመ ሥእላ ስግዱ ዘኢሰገደ ላቲ ይደምሰስ እምቅዋሙ ወኢይት አወቅ ዝክረ ስሙ ትርጉም፥ በሥእሏ ፊት ስገዱ ለሥእሏ ያልሰገደ ከቆመበት ቦታ ይጥፋ ስም አጠራሩም አይታወቅ የዘውትር መቅድም ም 1 ቁ 35።
ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ካመነ ስሙ በሕይወት መጽሐፍ እንደሚጻፍ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል ሉቃ ም 10 ቁ 20። በዘዳ ም 4 ቁ 15-19 ላይ እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክ ከቶ አላያችሁምና እጅግ ተጠንቀቁ፤ እንዳትረክሱ፥ ተቀረጸውን ምስል የማናቸውንም ነገር ምሳሌ፥ በወንድ ወይም በሴት መልክ የተሠራውን፥  በምድር ላይ ያለውን የእንስሳን ሁሉ ምሳሌ፥ በሰማይም በታች የሚበረውን የወፍን ሁሉ ምሳሌ፥  በምድርም ላይ የሚሽከረከረውን ሁሉ ምሳሌ፥ ከምድርም በታች በውኃ ውስጥ የሚኖረውን የዓሣን ሁሉ ምሳሌ እንዳታደርጉ፥  ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አንሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር ከሰማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕዛብ ሁሉ የሰጣቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንና የሰማይን ሠራዊት ሁሉ ባየህ ጊዜ፥ ሰግደህላቸው አምልከሃቸውም እንዳትስት ተጠንቀቅ ይላል። ታዲያ ለሥእል መስገድን ምን አመጣው?
በተለይም የወንድ ወይም የሴት ምስል የሚለውን ቃል ማስተዋልና መጠንቀቅ ተገቢ ነው ለማርያም ስእል  ግን መስገድ የተፈቀደበትን ስፍራ አናገኝም። አጼ ዘርዓ ያዕቆብ የእግዚአብሔርን ቃል ከመተላለፉም በላይ ከቆመበት ይጥፋ ስም አጠራሩ አይታወቅ የሚሉትን የእርግማን ቃላት ያለቦታቸው አስቀምጧቸዋል ሥእል ትምህርት ሰጪ ታሪክን የሚገልጥ ሊሆን ይገባል እንጂ ስግደት ጸሎት  አምልኮ ሊቀርብለት እና ሰውን ለማጥፋት መራገሚያ ሊሆን አይገባም።
መልክአ ስእል የሚባለው ድርሰት ሁልጊዜ በየጠዋቱ የሚጸለይ ሲሆን የሚናገረው ስለ ስእል ቁንጅና ፤ ለሥእል  ስግደት እንደሚገባ የሚናገር ነው ሁልጊዜ ካህናቱ ከኪዳን በፊት የሚጸልዩት የጸሎት ክፍል ነው። በዚህ መጽሐፍ ላይ እንዲህ የሚል አለ።
ዘኢሰገደ ለስእልኪ አሥሪጾ ምማኤ በሥጋሁ ወበነፍሱ ኢይርከብ ትንሣኤ ትርጉም፦  እራሱን ዝቅ አደሮጎ ለሥእልሽ ያልሰገደ ቢኖር በነፍሱ እና በሥጋው ትንሣኤ አያገኝም
ይህ ድርሰት አባ ስጢፋኖስን ለመራገም የተደረሰ ሲሆን በሐግሪቱ ላይም ሥጋዊ እና ማሕበራዊ ውድቀት ሊያመጣ የሚችል ስለሆነ ባስቸኳይ ሊቆም ይገባል ። ጸልዩልን ብሎ የሚማጸንን ሕዝብ ለሥእል ካልስገደ ተብሎ በሥጋው[በኑሮው] እና በነፍሱ ትንሣኤ አያግኝም ተብሎ ለዚያውም ጠዋት ጠዋት ሊረገም አይገባውም።
ወዘኢተክህሎ ነሢአ ቍርባነ ሰሚኦ ይሑር ውስተ ቤቱ ወይከውኖ ከመ ቁርባን ለእመ ሰማዐ በአሚን  ትርጉም፦ ሥጋውን ደሙን መቀበል ያልቻለ ታምሯን ሰምቶ ይሂድ ሥጋውና ደሙን እንደተቀበለ ይሆንለታል መቅድም ም 1ቁ 45
ይህ ደግሞ ጌታ ሥጋዬን ያልበላ ደሜንም ያልጠጣ የዘለዓለም ሕይወት የለውም ብሎ ያስተማረውን ትምህርት ፈጽሞ ያላገናዘበ ነው ። ሥጋውን ደሙንም ምንም ዓይነት ታምር ሊወክለው አይችልም። ብዙ ሰዎች ብዙ ታምር ሰምተዋል አይተዋልም ነገር ግን በክርስቶስ ማመን እንዲሁም ሥጋውን ደሙን መቀበል ስላልቻሉ ወደ ሕይወት አልመጡም።  በጣም የሚያሳፍር አባባል ነው። ዛሬ ታምር በመስማት የሚንከራተተው ሕዝባችን ከዚህ እርግማን ጋር ተያይዞ የመጣበት ይሆንን?
ዋናው የጠብ ምንጭ በታምረ ማርያም ውስጥ
 ኦ ኃጥአን አኃውየ እለ ከማየ እምይእዜሰ ኢንሕሥስ ከዊነ አግብርተ እግዚአብሔር ለፈጽሞ ሕግጋት አሠርቱ ወሰደስቱ እስመ ውእቱ መጠወነ ኪያሃ እግዝእተ ኪዳን ጊዜ ቀትር አመ ሀሎ ዲበ ዕፀ መስቀል እንዘ ይብል ነያ እምክሙ ወእግዝእትክሙ ወበእንተዝ እብለክሙ ንቅድም ወንትባደር ከዊነ አግብርት ለማርያም እምነ ወእግዝእትነ
ትርጉም እንደ እኔ ያላችሁ ኃጥአን ወንድሞቼ ሆይ እንግዲህ አሠርቱ ትእዛዛትን እና ስድስቱ ቃላተ ወንጌልን በመጠበቅ የእግዚአብሔር ባሪያ ለመሆን ማሰብ የለብንም እርሱ በቀትር ጊዜ በመስቀል ላይ ሆኖ እመቤታችንን እናት አድርጎ ሰጥቶናልና፤ ይልቁንስ የእመቤታችን እና የእናታችን የማርያም ባሪያ ለመሆን እንሽቀዳደም ይላል። ታምረ ማርያም ምዕራፍ 12፡52-53።
እንግዲህ ይህ አባባል በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ተጽፎ ወደየገዳማቱ በተላከ ጊዜ ከፍተኛ ውዝግብ አስነሥቶ አባ እስጢፋኖስ እና ደቀ መዛሙርቱ እንዲገደሉ ምክንያት የሆነው እና እስከ ዛሬ ድረስ መፍትሔ ያላገኘ እንቆቅልሽ ነው።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብትወዱኝ ትዛዜን ጠብቁ ብሎ አስተምሯል። ስድስቱ ቃላተ ወንጌል የሚባሉት በ ማቴ 25 ቁ 35-44 ላይ ይገኛሉ። ታዲያ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ምን አይነት መጻሕፍትን ቢያነብ ነው የእግዚአብሔርን ትእዛዛት መጠበቅ አያስፈልገንም ያለው? ይህን መጽሐፍ በቤተ ክርስቲያናችን ሰይጣን አስርጎ ያስገባው የጠላት ተንኮል እንጂ ልናነበው እና ልንሳለመው የሚገባ መጽሐፍ አይደለም አሁንም ከቤተ ክርስቲያናችን ተጠርጎ መውጣት ያለበት ቆሻሻ ነው። ጥንታውያን የወንጌል አርበኞች ኦርቶዶክሳውያን አባቶች ይህንን ጉድ ቢያዩ እንዴት ያዝኑ?  ወንጌሉን ከማንበብ ይልቅ ሕዝቡ በዚህ መጽሐፍ ተሸፍኖ ሕይወት ያለበትን የወንጌል ቃል እንዳይሰማ ተደርጓል። ወንድሞቻችንንም እያጣንበት ያለ መጽሐፍ ነው።
የኢትዮጵያው ሲኖዶስ አባላት ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት ታምረ ማርያምን አይቀበሉም አያምኑበትም፤ ሕዝቡን በመፍራት ብቻ ተሸክመውት ይኖራሉ። ነገር ግን እውነቱን እያወቁ ጠላቴ የሚሉአቸውን ማጥቂያ እና የፖለቲካ መሳሪያ ማድረጋቸው አልቀረም። የማሕበረ ቅዱሳንም የመጀመሪያዎቹ አመራሮች ታምረ ማርያምን እንደማያምኑበት ብዙ ጊዜ ባደረግናቸው ውይይቶች ተገንዝበናል። የማህበሩ ተራ አባላት ግን ይህን አይረዱም። የማህበሩ መሪዎች ይህ መጽሐፍ በ እናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም የገባ የሲይጣን ስራ መሆኑን ልባቸው እያወቀው ጠላቴ የሚሏቸውን የቤተ ልርስቲያኒቱን ውድ ልጆች ለማጥቃት ሲሉ የፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ ማድረጋቸው እጅግ የሚያሳዝን ነው። ለማንኛውም ሕዝባችንን ማሳወቅ የምንፈልገው ሁለቱ በማያምኑበት ነገር የፕሮፓጋንዳ ሰለባ ሆኖ ኃጢአት እንዳይሠራ ነው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቀኖና የተቀበለቻቸው መጻሕፍት ሰማኒያ አንድ ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ታምረ ማርያም እና መልክአ ሥእል አይገኙበትም። አንድ የቤተ ክርስቲያን ልጅ እምነቱ መፈተሽ ያለበት በሰማኒያ አሐዱ መጻሕፍት መሆን ሲኖርበት በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝነው ባልተጣሩ እና እርስ በርሳቸው በማይስማሙ የደብተራ ድርሰቶች የቤተ ክርስቲያን ልጆች ጥቃት ሊፈጸምባቸው አይገባም።
ስለዚህ የኢትዮጵያው ሲኖዶስ እርሱ በማያምንበት እና ከሰማኒያ አሐዱ መጻሕፍት ውጭ በሆኑ መጻሕፍት አማካኝነት ስም አጥፍቷልና ይቅርታ መጠየቅ አለበት። ቤተ ክርስቲያኒቱ ለዚህ መጽሐፍ መፍትሔ በመስጠት ወደ ፊት ሊፈጠር የሚችለውን የመከፋፈል አደጋ ከወዲሁ ማስወገድ አለባት። የእርቅ ኮሚቴው እውነተኛ እርቅ ማምጣት ከፈለገ ይህን ጉዳይም ቢመለከተው መልካም ነው፤ የሁለት ግለሰቦች መስማማት ብቻ የቤተ ክርስቲያኒቱን መሠረታዊ ችግር ሊፈታው አይችልም የሚል ሥጋት አለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን 
ከሙሉ ሰው  

4 comments:

 1. Good Point.God Bless You!

  ReplyDelete
 2. I am an ardent believer of the Tewahido Orthodox Faith and will continue to be so God willing, I have read the above article thoroughly and in my opinion, I think the problem is entirely on the Introduction of the book (Mekdim), other than that, I don't see problems in it, as to genuflecting towards the image of the Virgin Mary, as long as its done not for the hanged image but for Her in mind in no way of worshiping but in glorifying her, I think its ok. But the overall definition of the Mekdim is completely out of touch with our Orthodox Faith, our Blessed Church clearly teaches the vast charity of God that can never be compromised for the mere reason of not bowing for an image. That is not the Christ our Church preaches. In the actual book (Miracles of Mary, or Te'amire Mariam) it tells of a story how a murderer was saved just by the mention of Virgin Mary's name, if that can be done, it would be very wise to believe that God never condemns people over insignificant acts. If one says the Virgin Mary doesn't deserve veneration, that would be an issue, if one says She doesn't deserve praise, that would be something, if one says we can't bow for Her not by worshiping but for the very fact that She is the Mother of One God the Son, that would be an act of evil but the way it was described in the Mekdim and how the world is created to praise Her would be something I find hard to take it as a teaching of my Church, I pray Wudase Mariam everyday and our Mother the Virgin Mary deserves more than that. If we see the great Liturgy of Aba Hiryakos called Kidase Mariam, we can never get the kind of mistakes we encountered at the Mekdim, in fact Kidase Mariam can be noted as one of the best liturgies ever, it glorifies the Virgin Mary in every possible and appropriate ways as well as glorify and worship our God the Holy Trinity in a way that can get deep in our bones. Anyways, our Church Orthodox Tewahido, in my point of view is immaculate Church and doesn't need excessive "tehadiso", the Church only needs to expel some writing that may have been added by laymen overtime. This action must only be taken by Church officials without any help from the outside, specifically the Tehadiso group with different agendas.
  As for Emperor Zera Yacob, I honestly believe he was a saintly man who would not be ignorant enough to officially approve the Mekdim, he was an Emperor determined to the service of the Holy Trinity, Ethiopia has passed through great ordeals after he passed away including Grangn Ahmed's conquest against our nation, through this gaps of our history many unauthorized modifications must have taken place, i would sincerely not expect mistakes like this from an Emperor who has authored great works like Mahsafa Milad ("The Book of Nativity") and Mahsafa Selassie ("The Book of the Trinity" as well as Melka Mariam which dignifies our Lod Jesus Christ more than it dignifies the Virgin Mary for whom the book is named after. Anyhow, May the aTrinity Unite us and protect our beloved Church forever and ever, Amen

  ReplyDelete
 3. ተረት ተረት ከመጻፍህ በፊት ለምታወራው ተረት ትንሽ ተአማኒነት እንዲኖረው ለተረትህ ምንጭ መጥቀስ አትርሳ:: የምንጭ አጠቃቀም የማትችል ከሆነ በመጀመሪያ ተማር:: በተለያዩ የአለማችን ቋንቋዎች ተጽፎ የሚገኝውን የእመቤታችን መጽሐፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ተደረሰ ማለትህ እራሱ ምን ያለ ታሪክ የማታውቅ ባዶ መሆንህን ያስረዳል:: ለወደፊቱ ትንሽ በቀላሉ የማያስነቃ ተረት ይዘህ ለመቅረብ ሞክር::

  በኢትዮጵያም ሆነ በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ አባቶች መአል አንዳቸውም ስለ ታምረ ማርያው እንዳንተ የተወላገደ አመለካከት የላቸውም:: አንዳንድ የተአድሶ አቀንቃኞች በሰሜን አሜሪካው ሲኖዶስ ስር በሚተዳደሩ አንዳንድ ደብራት ተደብቀው እንደሚገኙ እና እነማን እንደሆኑ የት እንደሚኖሩ በደንብ ስለሚታወቅ ግርግር ለሌባ ያመቻል እንደሚባለው በቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል ባለው ልዩነት ተጠቅመን ምኞታችንተ እንፈትጽማለን ብላችሁ ታድሶዎች(መናፍቃን) አትድከሙ::

  ReplyDelete
 4. egziabher yebarkachu

  ReplyDelete