Saturday, January 29, 2011

ገድላት እና ድርሳናት በሃገራችን ላይ ያመጡት ችግርና ማለቂያ የሌለው ውሸታችን

ማህበረ ቅዱሳን ደጀ ሰላም በሚባለው ድረ ገጹ ላይ ባስነበበን ጽሑፍ ነጻ ሚዲያዎችን ለማስፈራራት ሞክሯል ዘምስለ ጠዋይ ትጠዊ ከጠማማ ጋር ጠማማ ትሆናለህ እንደተባለው ከወያኔ ጋር መዋል እንዲህ ያለውን ባሕርይ ያስይዛል።

ማሕበረ ቅዱሳን
ለተሰዘነዘሩት ግልጽ የሆኑ አስተያየቶች መልስ መስጠት ሲችል በቤተ ክርስቲያን ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ነው በማለት ሊያደናግር ይሞክራል። ማህበረ ቅዱሳን እንዲህ የተበሳጨበት ምክንያት ግን የተደበቀበት ጫካ እሳት እየበላው መሆኑን በመገንዘቡ ነው። ቤተ ክርስቲያናችንን ያጠቃት እና እንዳትራመድ እግሯን ተብትቦ የያዛትስ የእግዚአብሔር ቃል ያልሆኑ ተረቶች እንዲሁም በሕዝባችን ላይ የተጫኑ ባዕድ ሸክሞች እንጂ እውነትን ወደ አደባባይ ያወጡ ልጆቿ አይደሉም። አሁንም በዚህ ውሸት ላይ ርህራሔ የለንም ገና ለሕዝባችን የምናስተምረው ብዙ ነገር አለ ።
  በኢትዮጵያ ሰዎች ሕዝብን በሃይማኖት እያስፈራሩ እና እያታለሉ መግዛት ጥንታዊ አሠራር መሆኑን  በማስተዋል ማየት ከምንችልበት ወቅት ላይ ነን። ጥንታውያን አባቶቻችን ለእምነታቸው የሚሞቱ ሐቀኛ እና ሰራቶኞች ነበሩ። በአንጻሩ ደግሞ የፖለቲካው ጥገኛ ሆነው እውነተኛ አባቶቻችንን ሲያሳድዱ ሲገድሉ እና የውሸት እና የምንፍቅና ድርሳናትን ሲጽፉ የነበሩ ደብተራዎችም ነበሩ። የነዚህ ደብተራዎች ሥራ፤ ጥንቆላ እና የፈጠራ ታሪክ ዛሬ ለደርሰብን ኪሳራ ዋና ምክንያት ናቸው፤ ይህን ማንሳት የፈለግሁት ወደ አለፈው ታሪክ በመጎተት ጊዜን ለማጥፋት አይደለም። ዛሬም እነዚህ የደብተራ መናፍቃን ሥራዎች በፖለቲካችን በመንፈሳዊ ሕይወታችን እንዲሁም በኢኮኖሚያችን መሻሻል እንዳይኖረን መንገዳችችን አጥረው ሰለያዙት ጥርጊያውን እንዲለቁ ለመጠቆም ነው።እነዚህ ውሸቶች ከእግዚአብሔር የተገባልንን ተስፋ እንዳናገኝ ዛሬም በማሕበረ ቅዱሳን እና በመናፍቃን እንደ አዲስ ሆነው እየተቀነባበሩ ወጣቱ ስለሚማራቸው ወደተሳሳተ አቅጣጫ እየነጎደ ነውና ተመለስ እንላለን።


የይኮኖ አምላክ መንግሥት በዶሮ ጭንቅላት
ይኮኖ አማላክ የተባለው ሰው የላስታን መንግሥት ወደ ሶሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት ሲገለብጥ የዶሮ ጭንቅላት በመብላት እንደነበረ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ይተርካል ም 25 ቁ 4፤ ም 27 ቁ 6_13 ይመለከቱ። የዚህ የዶሮ ጭንቅላት ታሪክ የሚከተለው ነው
አንድ ዶሮ የኔን ጭንቅላት የበላ የዳዊትን መንግሥት ይወርሳል በዓለም  ነግሦ ይኖራል መንግሥቱም ወደ ሌላ አይሄድም እያለ ሦስት ወር ያህል ጮኸ ይላል ይህን ሕልም ያየው እና የሰማው የላስታው እልመክኑን ወይም ይትባረክ የተባለው የነአኩቶ ለአብ ልጅ ነው። ይህን ሕልሙን ለማስተርጎም በወቅቱ የደብረ ሊባኖስ እጨጌ ወደ ነበሩት ወደ ተክለ ሃይማኖት በመምጣት ይነግራቸዋል። እርሳቸውም ፈጥነህ ዶሮውን አርደህ ብላው አሉት ይላል ገድለ ተክለ ሃይማኖት ም 25 ቁ 13። እዚህ ላይ ቆም እንበልና እናስተውል አንድ የወንጌል ሰባኪ ሁሉም ግልጥ በሆነበት በሐዲስ ኪዳን ይህን ሕልም ከወዴት እንደሆነ ሳይመረምር ዶሮውን አርደህ ብላው ማለቱ አጠያያቂ ነው።
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሚገኘው  የእጅ ጽሑፋቸው እና በመዝገበ ቃላታቸው ሐፄጌ በሚለው ሥር ስለ ተክለሃይማኖት ሲጽፉ ሰውየው ብልጥ፤ ከሰው ጋር የመግባባት ችሎታ ያለው እና ሥልጡን ሰው ነበር መንፈሳዊ ሰው ግን አልነበረም፤ ከእግዚአብሔር መንግሥት ይልቅ የዚህ ዓለም መንግሥት አገላጋይ ነበር ብለዋል። የዶሮን ጭንቅላት በመብላት ንግሥና ይገኛል የሚለው ንግርት የነገሩን ጥልቅነት እና ምሥጢራዊነት ያስገነዝባል።
ታሪኩ ይቀጥልና በተክለ ሃይማኖት እንደተነገረው ዶሮውን አሳርዶ ሠራተኛይቱ ቀቅላ እንድትሰጠው አደረገ ይላል። ሆኖም ሠራተኛይቱ የዶሮውን እራስ ቆርጣ ጥላ ሌላውን ሥጋ አቀረበችለት ይትባረክም የዶሮውን እራስ ባላገኘው ጊዜ  እጅግ አዝኖ ወደ ተክለ ሃይማኖት እንደሄደ ይተርካል።
ሠራተኛዋ የጣለችውን የዶሮ እራስ በልጅነቱ ከሽዋ ተማርኮ ወደ ላስታ የሄደው ወጣት ይኩኖ አምላክ አገኘውና አንሥቶ በላው ይላል። ይኩኖ አምላክ ይህን የወደቀ የዶሮ እራስ ለመብላት ምን አነሣሣው? ወይስ ወድቆ የተገኘ የዶሮ እራስ ይበላ ነበር ወይ? ነገሩ እንቆቅልሽ  እና አሳሳቢ ነው። ይኩኖ አምላክ ይህን የዶሮ እራስ በበላ ጊዜ ኃይል ተሰማው መልኩም እንደጸሐይ አበራ የንጉሡ ባለሟሎች ሁሉ ግርማውን አይተው ፈሩት ይላል ገድሉ። ም 26 ቁ 1-5። ግርማ ሞገስ በዶሮ ጭንቅላት ይልሃል ይህ ነው ሀብተ እግዚአብሔር አደረበት ተብሎ ተጽፎለታል በገድሉ ላይ።በመጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስናነብ በመንፈሳዊ ቅባት ተቀብተው ሀብተ እግዚአብሔር ያደርባቸው ሳዖል እና ዳዊትን የመሳሰሉ ነገስታትን እናገኛለን፤ የወደቀ የዶሮ እራስ በመብላት ሀብተ እግዚአብሔርን ማግኘት እንደሚቻል የሚያስረዳ መንፈሳዊ ልምምድ የለም። ይህ ዓይነቱ አሠራር ከየት የተቀዳ ይሆን? ቤተ ክህነታችንም ሆነ ቤተ መንግሥታችን በጠንቋዮች እጅ ወድቆ የኖረ እስከ አሁንም ያልጸዳ መሆኑን በዚህ ጉዳይ ሲሠሩ የኖሩ ደብተራዎች ዛሬ ንስሐ ግብተው እየተናዘዙት ያለ ነገር ነው።
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተክለ ሃይማኖት የተባሉት ሰው ይትባረክን ገልብጥው ይኩኖ አምላክን በማንገሥ የዛጐየን መንግሥት ወደ ሽዋ ሰሎሞናዊ መንግሥት ለማዛወር ሃይማኖታዊ፤ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ዘዴዎችን የተጠቀሙ ሰው ነበሩ።
ይህ ሁሉ ከሆነ ባኋላ ከጌታ የተላከ መልአክ ለተክለ ሃይማኖት ተገልጦ ለዳዊት ልጅ ለይኩኖ አምላክ የጌታውን መንግሥት መልሸለታለሁ ቀብተህ አንግሠው አለው ይላል።
የዳዊት መንግሥት በኢየሩሳሌም የነበረ መንግሥት ከዚያም በተነገረው ትንቢት መሠረት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተወረሰ መንግሥት ነው ሉቃ 1 ቁ 33። ይኩኖ አምላክ ከመወለዱ አስቀድሞ ከ1000 ዓመት በፊት ተፈጽሞ እያለ እንደገና ጌታ በደብረ ሊባኖስ ተገልጦ በኢትዮጵያ አዲስ የዳዊት መንግሥት እንዴት ሊያቋቁም ቻለ? ለስሙ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታስ ይህን አልተናገረም የዳዊት መንግሥት በክርስቶስ ተወርሷልና።
ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል ለተንኮላቸው አጣመው በመተርጎም አዲስ ታሪክ በመፍጠር ክብረ ነገሥት የሚባል የተረት መጽሐፍ አዘጋጅተው ሕዝባችንን ቀንበር አሸክመው የኖሩ እና ዛሬም ያን ጥንታዊ ተንኮል በመከተል በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ስም በማህበር ተደራጅተው ሌላ ቀንበር በሕዝባችን ላይ ለመጫን የሚያሞጠሙጡትን እናውቃቸዋለን። ይህን ምሥጢራቸውን አግኝቶብናል ብለው የገመቱትን ደግሞ ጴንጤ እያሉ ስም በማጥፋት ከሕዝቡ ለመለየት የሚደረገውን ተንኮል ዝም ብለን አናልፈውም ሕዝባችን እውነቱን ይወቀውና ምርጫውን ይወስን።
ወደ ቀደመው ነገራችን እንመለስና ተክለሃይማኖት በተነገራቸው መሠረት በሚከተሉት እፀዋት፦ ስሒን፣ እንጎታት፣ የሎሚ ውሃ፣ጵስጥቂስ፣ ኮል፣ የወይን ፍሬ፣ ሚዓ፣ ቀንሞስ፣ ቀናንሞስ፣ ወይን ወዘተ በሚባሉ እጸዋት በተቀመመ ቅባት ከመዝሙረ ዳዊት በተመረጡ ጸሎቶች እና ሌሎች ጸሎቶች እየተደገመበት እጣን እየታጠነ 21  ቀን [3 ሱባዔ] ታቦቱን ካዞሩት በኋላ ቅባቱ ፈላ ያን ጊዜ ይኩኖ አምላክን ቀቡት በማለት ይተርካል። ነገሩን እንቆቅልሽ የሚያደርገው ግን ጌታ ለተክለሃይማኖት ተገልጦ ይህን ቅባ መንግሥት ከይኩኖ አምላክ በኋላ የሚነሱ ነገሥታት የሚቀቡት አይደለም ዘራዓ ያዕቆብ ብቻ ነው እንጂ የሚለው ነው። ም 27 ቁ 14። ከ1278 ዓ.ም ጀምሮ ከ200 መቶ አመት በኋላ ለሚነሳው ዘራ ያዕቆብ የሚቀባ ቅባት ለዚያን ያህል ዘመን መቀመጡ አስደናቂ ነው።
ይህን ቅባት ዘርዓ ያዕቆብ ከተቀባው በኋላ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያደርሰውን ውድመት በፕሮፌሰር ጌታቸው ከተተረጎመው ደቂቀ እስጢፋኖስ መጽሐፍ መገንዘብ ይቻላል። ምን ዓይነት ቅባት ይሆን?
ለ34 ዓመታት የነገሠው ዘርዓ ያዕቆብ የገደላቸው እና ያሳደዳቸው የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት እጅግ ብዙ ናቸው ይህ ታሪክ በራሱ መጽሐፍም ተጽፎ ይገኛል።
ተክለ ሃይማኖት ለይኩኖ አምላክ ለዋሉት ውለታ ሲሶ መንግሥት  አግኝተዋል። ሲሶ መንግሥት ብቻ ሳይሆን ባለ ስድስት ክንፍ እና 25ኛ ኪሩብ ሆነዋል። ይህ ሁሉ ስጦታ ከይኩኖ አምላክ ስለ ውለታቸው የተበረከተ መሆኑ ነው። ያለ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን በመልአክ የተሾሙ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ጳጳስም ናቸው እንደ ገድላቸው ትረካ። እንደ ገድሉ አባባል ከተክለሃይማኖት ወገኖች በቀር በተክለ ሃይማኖት ወንበር ላይ ማንም መቀመጥ አይችልም፡ ይህን ክፍል ደጋግመው ያነበቡ ሰዎች ዛሬም እረፍት እያሳጡን ነው። በዚህ አደገኛ ታሪክ ምክንያት የኢትዮጵያ ፖለቲካም ስኬት እርቆት በመዋዠቅ ላይ ይገኛል። ወያኔም ይህን ታሪክ የአማራውን ብሔር ለመከፋፈል ብዙ ጊዜ ተጠቅሞበታል። ፓትርያርክ ቴዎፍሎስን ለሞት ፓትርያርክ መርቆርዮስን ከሥልጣን ለመውረድ ያበቃቸው ይኸው ገድለ ተክለ ሃይማኖት ነው። ስለ ገድሉ ይዘት በሰፊው እመለስበታለሁ።
ለምሳሌ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ሆነው ሲሾሙ በአባታችን መንበር ላይ ባዕድ ሰው ሲቀመጥበት ዝም ብለን አናይም በሚል ምቀኝነት ታላቅ ጉባኤ የሚባል ማህበር መሥርተው የተቃወሙ ነበሩ[ ዜና ቤተ ክርስቲያን እንደዘገበው] ይህ ማህበር ቴዎፍሎስን ካቶሊክ፣ ጴንጤ፤ ጾም የሻረ፣ የተክለ ሃይማኖት መንበር የማይገባው ነው እያለ ስም ሲያጠፋ እና ሲከስ እንደኖረ ታሪክ ያስረዳል። የጃንሆይ እና የእግዚአብሔር ድጋፍ ያልተለያቸው ቴዎፍሎስ የነዚህን ተንኮለኛ ሰዎች ክስ እስከ ደርግ ዘመነ መንግሥት ድረስ ማለፍ ችለው ነበር። በኋላ ይህ ታላቅ ጉባኤ የተሃድሶ ጉባኤ በሚለው እውቅና ባለው ማህበር ውስጥ ገብቶ ቴዎፍሎስን መወንጀል ጀመረ በመጨረሻም ወንጀላቸውን አብዝቶ እርምጃ ይወሰድባቸው ዘንድ እንደግፋለን በማለት ተፈራርሞ ደብዳቤ ለደርግ በመላክ ለፍጻሜ አበቃቸው። አሁን ይህ ነፍሰ ገዳይ ቡድን የማህበረ ቅዱሳን ምሥጢራዊ አማካሪ ሆኖ እውነተኛ ኦርቶዶክሳዊ ሊቃውንትን እያስፈጀ ነው።
ማህበረ ቅዱሳን ከወያኔ ጋር እንዲሠራ የመከሩት እነዚህ ሰዎች ሲሆኑ ለአባላቱ የሚነገረው ምክንያት ግን ቤተ ክርስቲያንን ከመናፍቃን ለመጠበቅና ማህበራችንን ከመፍረስ ለማዳን ከወያኔ ጋር መሥራት የግድ ነው የሚል ነው።
የዚህን ቡድን እውነተኛ ፍላጎት ጠንቅቆ ያጠናው ወያኔ እንዴት እንደተጠቀመበት ትንሽ ላወሳ እወዳለሁ። ወያኔ እንደገባ ብዙም ሳይቆይ ከፓትርያርክ መርቆርዮስ ጋር መሥራት አልችልም እያለ መናገር ጀመረ፤ በኃይል ለማውረድ ሲያስብ በኃይማኖት ጣልቃ አልገባም የሚለው አባባሉ ውሸት ሊሆንብኝ ነው ብሎ አሰበ። ይህን በሚያስብብበት ወቅት ለፓትርያርክነት አጭቶ ያስቀማጣቸው አቡነ ጳውሎስ ነበሩ። ግን እንዴት አድርጎ ፓትርያርክ መርቆርዮስን አውርዶ አቡነ ጳውሎስን ይተካ? ይህን በማውጣት በማውረድ ላይ እያለ በተክለ ሃይማኖት መንበር ምክንያት አቡነ ቴዎፍሎስን ያስገደለውን ቡድን አገኘ፤ በተላላኪዎቹ ለየብቻ እየነጠለ መንግሥቱ የኛ ነው ክህነቱን ግን ለናንተ ሰጥተናችኋል አቡነ መርቆርዮስን አውርዳችሁ የወደዳችሁትን ፓትርያርክ ሹሙ የሚል የተቀመመ ተንኮል መከራቸው፤ በዚህ ጊዜ በለስ የቀናን የመሰላቸው ቡድኖች እየተመካከሩ በአቡነ መርቆርዮስ ላይ ማሴር እና ስም ማጥፋት ጀመሩ። የአቡነ መርቆርዮስን ጉዳይ ለመመልከት እና እጩ ፓትርያርክ ለመምረጥ በሚል ከወያኔ ጋር ሆነው ኮሚቴ አቋቋሙ። ኮሚቴው ከነዚህ ቡድኖች እንዲሁም ከመካከለኛ ወገኖች እና ከወያኔ የተዋቀረ ነበረ። መካከለኞቹ የሁለቱን ውስጠ ወይራ ሳያውቁ በመርቆርዮስ ላይ አብረው ይመክሩ ነበር። ሁለቱ ግን የራሳቸው እጩ ፓትርያርክ፤  ወያኔ ደግሞ አባ ጳውሎስን፤ የታላቁ ጉባኤ አባላት በበኩላቸው አቡነ...ን አዘጋጅተው እየተደባቡ ነበር። በመጨረሻ የኮሚቴው ቡድን እጩዎችን በሚጠቁምበት ጊዜ አቡነ ጳውሎስ ከጥቆማው ውስጥ አልነበሩበትም ወያኔ ግን ከእጩዎች ውስጥ አቡነ ጳውሎስ ካልገቡ ሞቼ እገኛለሁ አለ። የታላቁ ጉባኤ አባላት ተስፋ መቁረጥ የጀመሩት በዚህ ጊዜ ነበር። ድራማው አባ ጳውሎስን ፓትርያርክ በማድረግ ተጠናቀቀ።ቤተ ክርስቲያንም ለሁለት የተከፈለችው በዚህ ጊዜ ነው። እነዚያ ቡድኖች ግን የተክለ ሃይማኖትን መንበር ያገኘን መስሏቸው የወያኔ ዱላ በመሆን አቡነ መርቆርዮስን መቱ በመጨረሻ እራሳቸው ተመቱ እባብን ግደል ከነበትሩ ገደል ይሉሃል ይህ ነው።
እነዚህ ተንኮለኞች በተንኮል በወያኔ ሲበለጡ ባሕታዊ ገብረ ሥላሴ በሚባል ሰው አቡነ ጳውሎስን ለማስመታት እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ሙከራ አድርገው የአቡነ ጳውሎስ ዘመዶች በሽጉጥ ቀደሟቸው፤ ምስኪኑም ባማያውቁት ተንኮል ገብተው ተጎዱ። በባሕታዊ ገብረ መስቀልም በኩል ሕዝብን ለማሳመጽ ተሞከረ ይህም ሳይስካ ቀረ። [በጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ይሠራ የነበረውን ድራማ ይነጋል ከሚባለው መጽሐፍ ያንቡ።] በመጨረሻ ያማህበረ ቅዱሳን አማካሪ ሆነው አሁን ቤተ ክርስቲያንን እየበጠበጡ ይገኛሉ። አስፈላጊ ሆኖ ካገኘነውና ማህበረ ቅዱሳን እውነቱን የሚክድ ከሆነ ስማቸውንና ያሉበትን ሁኔታ የሚሰበሰቡበትን ቤት ወደ ፊት እናቀርባለን ሰዎቹ የቤተ ክህነት ሰዎች ብቻ አይደሉም ነጋዴዎችና ጡረተኞችም አሉበት። ንስሐ ሊገቡ ይገባቸዋል፣ እምቢ ካሉ ግን ቤተ ክርስቲያናችንን ይልቀቁ።
የተደራጀ ቡድን ሲያገኙ እንደ ወተት ዝንብ ወደዚያ ድርጅት ጥልቅ ይሉና የበላይነት ለመያዝ ሲታገሉ ድርጅቱን እና ትግሉን ይበትኑታል። እነዚህ ሰዎች የሚያልሙት ስለጠቅላላ የኢትዮጵያ ለውጥ ሳይሆን ስልጣን ስለማያዝ ነው። ራእያቸው ለውጥ ሳይሆን ሥልጣን ነው። ለዚህም ነው የነርሱ ደብተራዎች በከተቧቸው ተንኮለኛ ገድላት እና ድርሳናት ውስጥ መደበቅ የሚፈልጉት። ድርሳናችን ገድላችን እያሉ የሚሰብኩት የቅዱሳን ክብር ገብቷቸው አምልኮተ እግዚአብሔር አስቀንቷቸው ሳይሆን ያችን የሚያስቧትን ሥጋዊ ሥልጣን ለማግኘት የሕዝብ ማደንዘዣ ይሆነናል ብለው ስለሚያስቡ ነው።  ዛሬ የፖለቲካ ድርጅቶችን የሚያፈርሳቸው ወያኔ ብቻ አይደለም፤ ሥልጣን ለመያዝ በድብቅ የተሳሳተ ሥልጠና የሚወስዱ ወገኖች ጥንብ እንዳየ አሞራ ሲራኮቱ እራሳቸውን ያፈርሳሉ እንጂ። ለሥልጣን እንጂ ለለውጥ ስለማያስቡ ለወያኔ ተመችተውታል።
ሀገራችን ሁለንተናዊ ለውጥ ያስፈልጋታል። በተለይም ቤተ ክህነታችን በሥልጣን ሽሚያ መራኮቱን ትቶ በመንፈሳዊ ተሃድሶ በጥሩ ሥነ ምግባር ላይ እንዲያኩር እንፈልጋለን። ሀገራችን ፈውስ ያስፈልጋታል እውነት በሀገራችን በቅሎ ሲያፈራ ማየት እንፈላጋለን።   
በእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ስም የዓለማውያንን ርእዮተ ዓለም እያካሄዱ ያሉ ሰዎች እግዚአብሔርን እንዴት እንደናቁት ? ዋ!ያስፈራል።
በቤተ ክርስቲያናችን ስም፤ በቅዱሳን ስም፤ በሰማዕታት ስም የሚካሄደው የጥንታውያን መናፍቃን ትምህርት ይቁም እንላለን።
ስለለውጥ እናስብ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
በሙሉ ሰው            

27 comments:

 1. "እናንተ ዝመ በሉ እግዚአብሔር በዘመኑ ስራውን የሚሰራ ሰው ያስነሳል" የዚህን ጽሁፍ አዘጋጅ የሰማይ አምላክ ይባርክህ እውነት በቦታው ማለት እንዲህ ነው። እንግዲህ ይህንን እውነት ሰምቶ የማይነቃ ያው የሃሰት/የዲያቢሎስ ወገን ነውና አትፍረዱበት ለኔ ግን ጠቅሞኛል እግዚአብሔር ይስጥልኝ በምችለው መንገድ አባዝቼ ለወገኔ አስተላልፋለሁ በጣም ደስ የሚል እውነት ሲጻፍ እንጂ ሃሰት ሲለፈፍ አይደለም በርቱ።

  ReplyDelete
 2. እኔ ለዚች ሀገር እና ቤተ ክርስቲያን ተጠያቂዎች 1. መለስ 2.አቡነ ጳውሎሰወ 3.ዳንኤል ክብረት መስፍን ወልደ ማርያም ናቸው ሰለሁሉም እያንዳንዳቸው ልጽፍ እችላለሁ ምን እንዳደረጉ

  ReplyDelete
 3. ኦርቶዶክሳዊJanuary 31, 2011 at 1:46 PM

  ጉድ ፈላ! አንተ ጸሐፊው ሲነገረን የኖርነውን ነገር ሁሉ እኮ አፈር አበላኸው። እንዴ! እንዴ! እንዴ። ግን ጥሩ ነው። አእምሮአችንን ሰፋ አድርገን መወያየቱ ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም።

  ReplyDelete
 4. kikiki Yedoro chinkilat? This is really funny. I don't know how people believed this story. Tinkola yimeslal.

  ReplyDelete
 5. Minalbat tikit yewuahochin tagegnu yihonal .Ene ena meseleche gin bedemb inawkachualen atilfu.Ine yemlew gin mk satanesu zimblachu beresachihu ewnet new yalachihutn neger ataworum ?kezia behuala anbabi yerasun wusane yiwosnal.new weys mkann yemeyawkewn hizb silemahberu masawok new alamachihu?

  ReplyDelete
 6. ማቅ በቃ መልስ ሲያጣ ዝም ብሎ ማጉረምረም። ባክህ የዋሃን ብሎ ነገር የለም። በእናንተ አባባል የዋህ ማለት ማህይም ማለት ነው። አሁን ሁሉም የሚያነብበት እና መረጃ በቀላሉ የሚያገኝበት ዘመን ላይ ነው ያለነው። የዋህ ማለት የማያውቅ፤ ጅል ማለት ነው? አይደለም። ሁላችንም የዋሃን እንድንሆን ተጠርተናል (ገላ 5፥16) የዋህ እያላችሁ ሰውን በጭፍን ማጭበርበር ነው ስራችሁ። ጀግንነት ማለት የዶሮውን ጭንቅላት ጉዳይና ሌሎችንም እንዴት መፅሐፍ ቅዱሳዊ እንደሆኑ ማብራራት ነው። ዝም ብሎ ማጉረምረም ግን በዚህ ዘመን ውጤት የለውም።

  ReplyDelete
 7. ብርቱካን ...
  መጀመሪያ ነገር እንደው ከምንም ተነስቶ ውስጥ አዋቂ ነኝ ማለት እግዜሩን ተወውና ለሠው ህሊናም ይከብዳል፡፡ አንተ ማነህ? ዝም ብለህ እንድትቀባጥር ያዘዘህ የትኛው ሰይጣንህ ነው? በእውነት እኛ የራሳችንን ሳይሆን የሠው ናፋቂ ነን፤ በህንድ ለአቅመ ሄዋን ባልደረሰች ህፃን ወይስ በቻይናዎቹ... እንድናመልክ የምትፈልግ ግብዝ ነህ? እኛ የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እመነት ተከታዮች እንዳተ ባሉ የከንቱ ከንቱዎች ባልተፈጠሩበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ለሚወዳቸው በሚገለፅበት ወቅት በነበሩ ቅዱስ አባቶቻችን የተፃፉትን ትተን እንዳንተ ሃይማኖታቸው በማይፈቅደዉና ለሆዳቸው ባደሩ ሰዎች የሚፃፉትን ልቦለድና ተረት ተረት እንመን? በበኩሌ ሰው ነኝ ብለህ በዚህ ድረገጽ ሁለተኛ እንዳትቀርብ እመክርሃለሁ፡፡ እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 8. ሳራ ነኝ ...
  ጥያቄዬ በምን የተነሳ ተጣልታችሁ ምንስ አይነት አደጋ ቢያደርሱባችሁ ነው??? ዛሬ ማህበረ ቅዱሳንን ለመስደብ የቅድስት ቤተክርስቲያናችንን እውነተኛውን ትክክለኛውን ንጹሑን ሀይማኖታችንን እንደዚህ ከቀላል ሰው በወጣ ቀላል ቃላት በቻላችሁት ሁሉ የምታንቋሽሹት??? እንዴ ፀባችሁ ወይም ችግራችሁ እንደ ሀገራችን ደንብ መሰረት ሽማግሌ ጥሩና ታረቁ:: እኛም የተወደደች ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን እንደዚህ ስታቃልሉ ዝም ብለን ማየታችን ለሁል ጊዜ እንዳይመስላችሁ:: ተዋሕዶ ትዕግስት አለው በብዛት ያለቀ ዕለት ግን እናንተን አያድርገኝ::
  እመ አምላክ ከልቦናችሁ ታስታርቃችሁ!!!
  ሁላችንንም ከልጇ ከወዳጇ ታስታርቀን!!!
  ያለ ድንግል ማርያም አለም አትድንም! እኛ የአስራት ልጆቿ ነን እና ከጎናችን አትለይ!!!
  አሜን!!!

  ReplyDelete
 9. አሁንም ሳራ ነኝ ...
  ..."እምቢ ካሉ ግን ቤተ ክርስቲያናችንን ይልቀቁ።
  " የቱን ቤተክርስቲያን? ሲፈጠር ጀምሮ ትክክል አይደለም እያላችሁ የምትተቹትን??? ... እንዴ! እንዴት ብሎ የእናንተ ሆነ??? ጥሩ አይደለም ስትሉ የሰማሁ መስሎኝ። በዚህ አባባላችሁ እኮ ቀማኞች በጉን ከየዋሁ ሰው ለመንጠቅ ሳይመቻቸው ቢቀር ተመካክረው በመንገዱ ላይ ምነው ወዳጄ ቆዳ ተሸክመህ ትሄዳለህ? በማለት ደጋግመው ቢጠይቁት የዋሁ ሰው እውነት ቆዳ ይሆን እንዴ? በሚል ጥርጣሬ በግ መሆኑን እያወቀ አውርዶ እንደጣለው ሰው አይነት ሞኝ እየፈለጋችሁ እንደሆነ በግልጽ ይናገራል።

  ReplyDelete
 10. በሙሉ ሰው ... አንተ ይሄን የምትጽፍ ስም የለህም አይደል?? እንዴት ብሎ ይኖርሃል????? በል ስለ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ከመጨነቅህ በፊት እራስህን እወቅ:: የቀረብህ ጥቅም ምን እንደሆነ ተናገር:: አብረህ ተምረህ ዛሬ እነሱ በሃይማኖት ታንፀው በልጠውህ ከሆነ አንተም በሃይማኖት ጽና ተሃድሶን ጣል የተጠመቅበትን ሃይማኖት ተከተል::
  በነገራችን ላይ እኔ ስም አለኝ ሳራ የተዋሕዶ ኦርቶዶክስ ልጅ ነኝ!!
  አየህ ተዋሕዶ አይታፈርባትም ይመኩባታል እንጂ

  ReplyDelete
 11. እረ ጉድ ነው የቱን ቤተክርስቲያንነ ነው ሲጀመር ጀምሮ ትክክል አይደለም የምትሉት ለመሆኑ በእነዚህ በታላላቅ የተዋሕዶ ሐይማኖት ሊቃውንት ስመ ብሎግ ከፍታችሁ የምትቀባዥሩት በጣም ይገርማል የእውነት እኮ የተዋህዶ ልጆች ብትሆኑ አጠፉ የምትሉትን ሰብሰብ አድርጋችሁ ማስተማማ፣ መገሰፅና ካልሆነም ማውገዝ እኮ ይቻላላ የሚሰራ ሰው ሁሌም ይሳሳታል ያጠፋል ያበላሻል የታወቀ ነው የማይሰራ ግን ቁጭ ብሎ የሚሰራውን ሲተች ተው የሚውለው በእውነት ይህ ከእናንተ አይጠበቅም እና እስቲ ቆም ብላችሁ አስቡ በእውነት እኛ ለዚህች ሐይማኖት ምን እየሠራን ነው በማለት እራሳችሀን ጠይቁ፡፡ በተረፈ ግን ልዑል እግዚአብሔር በደሙ የመሠረታትን ቤተክርስቲያን ማንም ምንም ሊያደርጋት አይችልም አመናችሁም አላመናችሁም፡፡ ልዑል እግዚአብሔር ልቦና ይስጣችሁ:: አሜን!!!

  ReplyDelete
 12. abet abet ante maneh bel? yebete krstiyan tekorkuwari? mannm atatallm!

  ReplyDelete
 13. yematerbu agsesesoche nacche betame yemetegermu yenat tete necashe nache tegermalche abo endeywem helachem gedel gebu asemesaye atalye koye entye eneyemelwe yehechen betekerstyan yemesertant m.k weys eysus lemen kehedetachen be m.k asttakache tengerlche..........enta yematerbu ewneten yemelache tehadiso kemehon pagant henne yeesat mekerawen bekebel yekelae yehen sehofe wende aftete atwetem

  belu gedel gebu ke adama universty

  ReplyDelete
 14. አለመታደል ሆኖ የምዕመናን ችግር ኦርቶዶክስነት ወይም ክርስትና ማለት በገድላት ማመን ስለሚመስላቸው ነው፡፡ኦርቶዶክስነት ግን በድንግል ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ማለት ነው፡፡አብዛኛው ምዕመናን ተክልዬ ከሚነኩ ኢየሱስ ቢነካ ምንም አይመስላቸውም ምክንያቱም ሁሉም በልማድ ስለሚመላለስ እውነት ሲነገር ሁሉም ያመዋል በእርግጥ የኖሩበትን ስህተት በአንዴ መተው አይቻልም ፡፡እባካችሁ ክርስቲያኖች መጽሀፍ ቅዱሳችሁን ብቻ ገልጣችሁ አንብቡ ያኔ ወደ እውነት ትመጣላችሁ ፡፡በተሰቀለው ጌታ ብቻ ማመንና መኖር መናፍቅነት ከሆነ መናፍቅነት እውነት ነው፡፡ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ ደም አለም አይድንም!!!

  ReplyDelete
 15. kirakimbo zemenafik yale gedilatna dirsanat endet bete kiristiyan litikom tichilalech metsihaf kidusm ikkoo tiliku gedil new yalemawkachihu new enji.gedil malet ikkoo yemayitamenu negeroch beigziabiher hayil bekidusan yetederegutn yemiyastemr new.yemitamen kehne weyim bezemenawi logic yemideresbet kehone minun gedil hone?yematanebu deddebooch silehonachihu new inji geta iyesusm ikko lemiyamin kezih belay madireg yichalewal new yalew.libona yistachihu

  ReplyDelete
 16. Betekiliye ma atimitubitge kidusan iko beigizeabihair yetemeretu nachew. sadikun besadik sime yemikebel yesadikun waga yagengal.

  ReplyDelete
 17. ንጋት/ወለተጊዮርጊስ
  ረ ጉድ ነው የቱን ቤተክርስቲያንነ ነው ሲጀመር ጀምሮ ትክክል አይደለም የምትሉት ለመሆኑ በእነዚህ በታላላቅ የተዋሕዶ ሐይማኖት ሊቃውንት ስመ ብሎግ ከፍታችሁ የምትቀባዥሩት በጣም ይገርማል የእውነት እኮ የተዋህዶ ልጆች ብትሆኑ አጠፉ የምትሉትን ሰብሰብ አድርጋችሁ ማስተማማ፣ መገሰፅና ካልሆነም ማውገዝ እኮ ይቻላላ የሚሰራ ሰው ሁሌም ይሳሳታል ያጠፋል ያበላሻል የታወቀ ነው የማይሰራ ግን ቁጭ ብሎ የሚሰራውን ሲተች ተው የሚውለው በእውነት ይህ ከእናንተ አይጠበቅም እና እስቲ ቆም ብላችሁ አስቡ በእውነት እኛ ለዚህች ሐይማኖት ምን እየሠራን ነው በማለት እራሳችሀን ጠይቁ፡፡ በተረፈ ግን ልዑል እግዚአብሔር በደሙ የመሠረታትን ቤተክርስቲያን ማንም ምንም ሊያደርጋት አይችልም አመናችሁም አላመናችሁም፡፡ ልዑል እግዚአብሔር ልቦና ይስጣችሁ:: አሜን!

  ReplyDelete
 18. JESUS IS LORD! HE SAVES U BELIEVE IN HIM. DON'T WORRY ABOUT UR WORSHIPING STYLE, BUT FOR ETERNAL LIFE OR ETERNAL PUNISHMENT.

  ReplyDelete
 19. God bless this blog,
  The book called GEDIL or DIRSAN are the curst of this country, which are covering the people from bible light and opening the door of hell, but the bible is always true, because it was written by the holly sprit, not by debtera like gedil and dirsan, which are lead by Satan
  Let me give you one example
  In the book of gedle tekilehymanot chapter 48 it is mentioned that
  1.Satan was caught by hand physically
  2.Satan was vasectomize (megerez)
  3.Stan was monk and serve Teklehymanot
  4.Satan was serving the monks and loving God
  5.Satan was died
  6.Satan was given a chance of salivation to go heaven as righteousness people
  But according to the bible,
  1.Satan wills not caught by hand physically
  2.Satan has no human flesh to vasectomize (megerez)
  3.Satan has no gender or sex organ
  4.Satan can serve for the people who following him like debtera people but not people like paul and other man of god, I have no idea why teklehymanot allow this?????
  5.Satan never die
  6.Satan never go to heaven but he will go to hell for ever.
  So this is the book we gave the same position with holly sprit, please my brothers and sisters don’t be TIFIZO just follow the bible,
  But one day the master of shepherd will appear and will give the right judgment

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yih yeseytan timihirt new, seytan bemenem menged aymotim degimom ayitsedikim!!!

   Delete
  2. Zinabu Lelam indezih aynet gud kale bitakerbew melkam new!

   Delete
 20. ለመጋቢ ሐዲስ ዲያቆን በጋሻው እስከሞት ድረስ የታመንክ ሁን ይላል ምን ማለት ይሆን ማንም ቢሆን ሳይገባው ቢሆን ሰይገባው የክርሰቶስን ስም መድረክ ላይ ቆሞ መስበክ የለበት ብዮ አምናሁ እኔ ስብከት እፀፀ አለው ማለቴ አይደለም እውቀቱ ስለሌለኝ፤፤ እሱን ለሊቃውንቱ ትቼዋለሁ ግን በዘመናችን አዲስ ሐዋርያ ስላየሁ ድንቅ ሆኖብኝ ነው በፊትም የለም ወደኋላም የሚኖርም አይመስለኝም፤፤ ሰደበኝ ብሎ ከሕዝብ ልቦና አወጣኝ ብሎ የአለም ፍርድ ቤት የቆመ ሐዋርያ የመጀመሪያ ሰው አንተ እንደሆን ታውቅ ይሆን ለዚህ እኮ ነው የምንሰብከው ሌላ ተግባራችን ሌላ በሰበከው ሰብከት እንዃ ቢሰድቡህ ቢመቱህም ምንም እንደማትል ጣትህን ፈትፍቼ አበላሐለው ሲለኝ ናና አብረን እንበላለን አልኩት ብለህ አንዳውም አየሰቅ ነበር የተናገርከው ያኔ ለካ
  ተረተረት ነበር የነገርከን ምክንያቱም እውቀቱ ባይኖረኝም እንድ ሰበኪ መከሰስ እንጂ መክሰስ የለበትም ስለ ክርስቶሰ ብሎ መገረፍም አለበትና ጌታ ፍርድ ቤት ቆመ በሀሰት ተፈረደበት ነው አይደል የሚለው ግራ
  ገባህ መሰለኘ ለአንተ እኮ ትልቅ በረከት ነበረህ የተባልክወን ሆነህ ካልተገኘህ አባቶች አኮ በዓለም ሲሰደቡ
  እንዴት ደስ እንደሚላቸው አታውቅ ይሆን አንዴ ክርስቶስን አውቀዋለው ብሎ ውንጌል ከያዙ በኋላ እንኳን መሰደብ መሞትም አለው ሰለዚህ በምድር በረከት የሚቀበል ሰባኪ በሰማይ በረከት እንደሌለው ታውቃለህ
  ስለዚህ ስበከትህ ሁሎ ያለ ሰማያዊ ዋጋ ነበር ለከንቱ ውደሴ በከንቱ ሮጠህ ነብር ሰማያዊ ዋጋ አጣህበት
  ምክንያቱም ከዚሀ አለም ፍርድ ተቀብለሀልና፤፤ ተዋህዶ አፍራብሀለች የዘማሪ ይልማን መዝሙር አላደመጥክም በደንብ አዳምጥ ይህን የምልህ በጣም አዝኜ ነው ያሁሉ ስድብ ሲወርድበህ እንደአባቶችህ ተመስገን የምትል መስሎኝ ነበር ግን አልሆነም ስለዚህ ሰባኪ ማለት ምን ማለት ነው መልሱን ከአንተ እጠብቃለሁ እግዚአብሔር ኃይማኖታችንን ይጠብቅ፤፤

  ReplyDelete
 21. አንተ መናፍቅ ለምን ስለ ሰምሶም ጸጉር የተጻፈውን አላስተዋልህም? ሙሴ ታምር ይሰራባት የነበረችውን ዘንግስ እንዴት አየሀት? መናፍቅ ማለት ይሔ ነው የተጻፈውን የማያስተውል። እግዚአብሄር አምላክ ነፍሥህን ከአስቆሮቱ ይሁዳ ጋር ያኑራት። የሰይጣን አገልጋይ

  ReplyDelete
 22. እንኩዋን የቅዱሳን የራሳችሁንም ገድል እያስነበባችሁንም አይደል

  ReplyDelete
 23. ሃይሌ እባላለሁ ..... እኛ ኢትዮጽያዊያን ከባድ ድንቁርና አለብን... ያልተገባንን ዕውቀት አለን ብለን የምናወራ ... ሙሉ ቁና ሰፌድ የሚያክል ኩራት ተሸክመን እስከመቼ???? በመጀመሪያ ማንም ኢትዮጽያዊ በዘርም በሃይማኖትም በብሄርም በጎሳም በቋንቋም ይሁን በሌላ ልዩነት ቢኖረንም ኢትዮጽያዊ ነን ስለዚህ እኛ ኢትዮጽያዊያኖች ደግሞ ትክክለኛውን የኢትዮጽያ ታሪክ የምናገኘው ወይም የምንወርሰው አሁን ካሉት አባቶች ሳይሆን ከቀደሙ አባቶቻችን ነው....... ያሁኖቹ በስልጣን ጥማት በየቤተ እምነቱ የተሰገሰጉት በሙሉ የሰውን ልጅ ነፍስ አምላካቸው ጋር ሊያስታርቁ ሊያስተምሩ ሳይሆን ምዕመናኑን ለራሳቸው የገንዘብ ምንጭ ለማድረግ እንደሆነ ግልጽ ነው .... ሲፈልጉ ከላይ ወንድሜ እንዳለው የተፃፈውን ሁሉ ሲፈልጉ እየጨመሩ ውሸት ሲቀላቅሉ ሲፈልጉ ቀንሰው ምዕመናኑን ወደ ሌላ እንዲሄድና ለሌሎች የእምነት ባለ ስልጣናት የገንዘብ ምንጭ ሲሆኑ ለኛ እሄንን ማወቅ ዕድሜ አይወስንም .... በኔ እድሜ ይህ መሆኑን ለማወቅ በቂ ምክንያቶችን አይቻለሁ .... አንዳንዴ ከቤተ እምነቶች ይልቅ ሳይንስ ይሻለኛል .... ሳይንስ ፈጣሪን አውቆ ለሰው ልጆች በሰላም መኖር እና ምቾት ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ አድርጓል ... ሳይንስ ፈጣሪን ለማወቅ ገና ከራሳቸው የእጅ ጥፍር እንዴት እንደተፈጠረ እና ለምን አላማ እንደተፈጠረ ተመራምረው ይገረማሉም የበለጠ ፈጣሪያአቸውንም እጅግ ያደንቃሉ ይገዙማል .... ቀጥሎም በተሰጣቸው አዕምሮ ለሰው ልጆች መገልገያ የሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ ሰርተው ያቀርባሉ ... መኪናውን ሞባይሉን ኮምፒዩተሩን እረ ስንቱን .... እነዚህ ሁሉ ደግሞ ሳይንስን በእጅጉ በሚነቅፉ የእምነት ቤቶች ጭምር ሲገለገሉባቸው ይታያሉ .... ስለዚህ ዛሬ ቤተ እምነቶች የእውነት የነፍስ መዳኛ ሳይሆኑ የንግድ የግለሰቦች የገንዘብ ማግኛ ሲሆኑ እንዴት የማይባንን ትውልድ ሊፈጠር ይችላል??? እኛ ኢትዮጽያዊያን በማይሆን ነገር ላይ ወግ ማጥበቅ ማክረር እንወዳለን ግን ለብዙ ሚሊዮን ኢትዮጽያዊያን እህትና ወንድሞቻችን በብዙ ችግርና ፈተና ሲወድቁ ልክ ወጋችን ነው ብለን ክርርርርርርር ብለን ሳንደርስላቸው ስንቶች ከስጋም ከነፍስም ሳይሆኑ ተለዩን???? እንደ እኔ እውነት ነው ዛሬ በማይሆኑ እጆች የተፃፉ የእምነት መፃፎች ሁሉ ሊፈተሹ ይገባል ይህንን ስል ትውልዱ ካለበት ኋላ ቀርነት አስተሳሰብ ሊላቀቅ እንደሚገባው እያሳሰብኩ .... በጣም አሳዛኝ ስብከት በሁሉም እምነቶች እኛ ኢትዮጽያዊያን ከእስራኤል ልጆች የበለጠ ለእግዚአብሄር ቅርብ ነን ... ስለዚህ እኛ ብቻ ከሁሉም ዓለም በተለየ ልዩ ስፍራ እንዳለን የሚሰበክ ተራ ስብከት መቆም አለበት .... ሁሉም ቆም ብሎ ማሰብ ይኖርበታል .... ዛሬ በምድራችን ወደ 8 ቢሊዮን ህዝቦች አሉ ... ከነዚህ ሁሉ ህዝቦች እኛን ለይቶ ፈጣሪ ይየን ቢባል እንኳን ... ስለተቀሩት ህዝቦች ፈጣሪ ምን ያደርጋቸዋል ? እነሱስ ልክ እንደኛ የቤተ እምነት ስርዓት ሲፈፅሙ ይድናሉ? ወይስ ያው እንደተለመደው አይድኑም ተብሎ የተለመደ ስብከት ለቀጣዩም ትውልድ ይተላለፍ?/ይህ ነው ድንቁርናን ማውረስ/? ትውልዱ ይንቃ .... ለሰው ልጅ በሙሉ የነፍስ ድህነትን እንሰብካለን ከተባለ በዕውቀት ይሁን....

  ReplyDelete
 24. ለውጥ የምትለዋን ሃሳብ ያመጣሃት ከየት ነው? በውስጧ የተቀመመ ነገር እንዳይኖራት!

  ReplyDelete
 25. ወንድም ሃይሌ እውነት ብለሃል፡፡ እንደሃይማኖተኛ መዋደድ መተጋገዝ ሲገባን በጥቃቅን ነገሮች እየተለያንና እየተከፋፈልን መጣላታችን ጥሩ አይደለም፡፡ እደኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት አስተሳሰብ ፈጣሪ ሊያድን የመጣው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ማህበረ ቅዱሳን አባላትን ብቻ ነው፡፡ ሌላው ሊድን የማይችል ብቻ ሳይሆን ሊድን የማይገባው ነው፡፡ ከ8 ቢሊየን የአላም ህዝብ የኢትዮጵያ ኦረቶዶክስ ማህበረ ቅዱሳን አባላትን ብቻ!! ሌላው መናፍቅ አህዛብና categorically የማረባ ነው፡ ይህን የመሰለ ድንቁርና በየትም ሀገር የለም፡፡
  ዘመኑ የአብርሆት (Enlightenment) በመሆኑ ሁሉም ያነባል ያስተውላል፡፡ሀይማኖትን ይፈትሻል በተገቢው መንገድ ካልተገበረና ለሰው ልጅ ፋይዳ የሚሰጥ ካልሆነ ለጥለቻ እና ጥል ዋነኛ ድልድይ መሆኑን ይስማማል፡፡ በዚህም ምክንያት የአለም ኢአማንያን ቁጥር ከቀንወደቀን እየጨመረ ይገኛል፡፡ እኛ ኢቲዮጵያውያን ግን አሁንም በውሸት ታሪክና ትውፊት ራሳችንን አጥረን እርስ በርስ እንባላለን፡፡ በውሸት ታሪካችንም ከአለም ህዝብ ተነጥለናል፡፡ እኛ ኢትዮጽያዊያን ከእስራኤል ልጆች የበለጠ ለእግዚአብሄር ቅርብ ነን ... ስለዚህ እኛ ብቻ ከሁሉም ዓለም በተለየ ልዩ ስፍራ እንዳለን ይሰበካል፡፡ ዲያቆን ፅጌ ሥጦታው ስለዚህ ውሸት ይህንን ብለው ነበር፡ “አሁንም እንዋሻለን፡፡መዋሸታችንን ልባችን እያወቀው ወደ እውነት ለመመለስ ሐፍረት እየተሰማን እስከ አሁን እንዋሻለን፡፡በብዙ ውሸት ሀገራችን እውቅና አግኝታለች፡፡ ታቦተ ፅዮን በኢትዮጵያ፣ ግማደ መስቀሉ በኢትዮጵያ፣ ድንግል ማርያም ተሰዳ የኖረችው በኢትዮጵያ፣ ፃድቃን የተባሉ ሁሉ የተፈጠሩት በኢትዮጵያ፣መላእክት የሚዘምሩት በግዕዝ ቋንቋ፣ አዳም ንግበረ ተብሎ የተፈጠረበት በግዕዝ ቋንቋ፣ ለማርያምም፣ ለጊዮርጊስም ለአቡዩም፣ለተክልዬም አሥራት የተሰጠች ኢትዮጵያ፣ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው፡፡” (ይነጋል፣1997፣ገፅ 133)
  እባካችሁ ይህ ሁሉ ጥልና ውሸት ማብቂያ ይኑረው፡፡

  ReplyDelete