Saturday, January 8, 2011

የኢትዮጵያ ኦርቶስዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያን ታሪክ በአጭሩ - በተሃድሶዎች እይታ።

የቤተ ክትስሪያኒቱን ታሪክ ማወቅ አሁን ያለባትን ችግሮች ከምንጩ  ለመረዳት እና መፍትሔውን ለመሻት ያስችላል።
ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ስትመሠረት የነበረውን የሐገሪቱን ሁኔታ የሕዝቧን ባሕል ወደ ኋላ መለስ ብሎ መቃኘት ተገቢ ነው።
ኢትዮጵያ ቅድመ ክርስትና
1.0   ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ ከሄት መጣ?
1.1 ኢትዮጵያ የሚለው ስም በሰባ ሊቃናት ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ እና ከእርሱ በተቀዳው የ1952 ዓ.ም. እትም የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ከ40 ጊዜ በላይ ተጽፎ ይገኛል። በዕብራይስጥ የተገለጹትን የሁለት ቃላት ሐሳቦችን ሊተረጉም እንደ ገባ ሊቃውንት ይገልጣሉ።
1.2 ኵሽ የሚለው ቃል የካምን ልጅ ስም በአንዳድ ቦታ ተክቷል በዚህም መሠረት የኵሽ ምድር  ኢትዮጵያ ተብላለች ዘፍ 2፡13 ኢዮ 28፡19 ኢሳ 11፡11።
ኵሻውያን ኢትዮጵያውያን ተብለዋል 2ዜና 14፡13
1.3 ጸይም [በርሃ] የሚለውን ተክቶ <<ኢትዮጵያ>> ተብሏል መዝ 72፡9፡72፡14።
1.4 ኢትዮጵያ በግሪክ ትርጉም፦ <<ኢትዮ>> ማለት ጥቁር <<ጵያ>> ማለት ሐገር ማለት ሲሆን ሁለቱ ሲገናኙ የጥቁሮች አገር የሚለውን ትርጉም ይሰጣል።
2.0 ኢትዮጵያ ከየት እስከ የት?
በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ <<ኢትዮጵያ>> የምትባለው ከግብጽና ከሊብያ በስተደቡብ ያለች በደቡብ እና በምእራብ ወሰኗ ያልተገለጸ ሰፊ የዓለም ክፍል ናት።
2.2 ኢትዮጵያ፤ ግብፅ እና ሊብያ ወሰንተኞች እርስበርስ የተገዛዙ ናቸው የሚያሰኛቸው ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ጦር ማዝመታቸው፤ መሪዎችም አንዳድ ጊዜ ኢትዮጵያዊ ሌላ ጊዜ ግብጻዊ መባላቸው ነው። 2ነገ 19፡9፤ 2ዜና 12፡2-9፤14፡9-13፤16፡8 ኢሳ 37፡9።
3.0 የኢትዮጵያ ሕዝብ እና አምልኮታቸው
በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ነገዶች ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል ተብሎ ይተረካል።ይህንንም የምንጠቅሰው መሠረተ አምልኮውን ለመገንዘብ ነው።
3.1 ከነገደ ካም ኩሻውያን
የአባይን ወንዝ በመከተል በሰሜን፣ በምራብና በደቡብ በኩል ዘልቀው ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ሠፈሩ።
አምልኮታቸው
በወንዝ፣ በኩሬ፣ በሐይቅ፣ በተራራ፣ በእንሥሳት፣ በአራዊት፣ በአዕዋፍ፤ በዛፎች፤ እንደነበር ይተረካል ምልክቱም እስከዛሬ ድረስ ይታያል።
3.2 ከነገደ ሴም ሳባውያን
በምሥራቅ እና በሰሜናዊ ምሥራቅ በኩል ገብተው ሠፈሩ።
አምልኮታቸው በጸሐይ በጨረቃና በከዋክብት ነበር።
በኋላ ከኩሻውያን ጋር ተዋግተው እራሳቸውን ነጻ ካወጡ በኋላ <<አጋዝያን>> ተባሉ። ቋንቋቸውም ግእዝ ነበር። እየተደራጁ ሲሄዱም የኩሻውያንን መንግሥት ደምሥሰው የራሳቸውን መንግሥት የሳባውያንን መንግሥት አቋቋሙ።
3.3 ከነገደ ሴም እሥራኤላውያን
+ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ722 የዐሥሩ ነገደ እሥራኤል መንግሥት ሲፈርስ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ586-539 የይሁዳ መንግሥት ሲደመሰስ።
+ ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከ67-70 ዓ.ም. በሮም መንግሥት ኢየሩሳሌም ስትወረር፤ እስራኤላውያን  ወደ ኢትዮጵያ በአክሱም፣ በሽሬ፤ በላስታ፤ በሰሜን፤ በወገራ፣ በቋራ፤ ወዘተ ሠፈሩ።
አምልኮታቸው በኦሪቱ ሕግ መሠረት ሲሆን ምኩራቦችም ነበሯቸው።
የክርስትና ወደ ኢትዮጵያ መምጣት
1.0 ከሊብያና ከግብጽ በስተደቡብ የተንጣለለው ሰፊ በርሃ ተጨምሮ ተራራማዋ የአገራችን ክፍል ሁሉ በንድነት <<ኢትዮጵያ>> እየተባሉ ሲጠሩ የነበሩ ሲሆን መቼ እንደተለያዩ በትክክል ሳይታወቅ <<የኑብያ ኢትዮጵያ እና የሳባ ኢትዮጵያ>> መባል ጀምረው በነዚህ ስሞች እየተጠሩ ባለበት ጊዜ ክርስትና ተሰበከ።
1.1 ኑብያ ኢትዮጵያ
በቋንቋ፣ በባህል፣ በታሪክና በመልካአ ምድር ከግብጽ ጋር ተቆራኝታ ለተገኘችው ለኑብያ ኢትዮጵያ ወንጌልን የሰበከላት ወንጌላዊው ፊልጶስ ነበር። ይህችውም የአሁንዋ ኢትዮጵያ ግዛት ስለነበረች ክርስትና ከዚያb ወደዚህም ተሻግሮ ነበር። በዚህች አገር ወንጌል በ34 ዓ.ም. ተሰበከ ቤተ ክርስቲያንም በ56 ዓ.ም.ተቋቋመች። በ1100 ዓ.ም. በሙስሊም ወራሪዎች ተደመሰሰች። በአሁንዋ ኢትዮጵያ የነበረች ቤተ ክርስቲያን ግን አልተደመሰሰችም።
1.2 ሳባ ኢትዮጵያ የኛይቱ
የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን ያስፋፋትና ወንጌልን የሰበከላት ግሪካዊው አባ ሰላማ ነው ዘመኑ ከ318-330 ዓ.ም.ባለው ጊዜ ውስጥ ነው። በእርሱ አገልግሎት፦
= ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት የተባለች ቤተ ክርስቲያን ተመሠረተች
= የጸሎት ቤተ ተሠራ
= መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ግእዝ ተተረጎመ
= ቤ/ ክር በኢትዮጵያ መስፋፋት ጀመረች
የክርስትና መበረዝ እና መዳከም
ሥር በሰደደው የአረማውያን አምልኮ እና በአክራሪ የአይሁድ ዕምነት ተከታዮች መካከል በዚህ ሁኔታ የተሰበከው ክርስትና ገና የሚገባውን ያህል ሳይስፋፋ የሚረግጡት እና የሚያዳክሙ ችግሮች መጡበት። የሚከተሉት ነገሮች ክርስትናውን አዳክመውታል
1.0 ምንኩስና በተሳቱ ቅዱሳን[ከ460-600 ዓ.ም.]
ከሮም ግዛት ተሰደው የመጡ ዘጠኝ መነኮሳት <<በምንኩስና  ጽድቅ ይገኛል>> የሚለውን ፍልስፍና ይዘው ገቡ። ከዚህ በኋላ <<እጽድቅ ያለ መንኩሶ፤ እካስ ያለ ታግሦ>> የሚለው አባባል በሕዝባችን ውስጥ ጠልቆ ገባ።
2.0 እስልምና በመሐመድ አጎት በጃፋር መሪነት[600-800 ዓ.ም.]
ከመሐመድ ዘመዶች 85 ያህሉ ሙስሊሞች በጥገኝነት ወደ ኢትዮጵያ ገቡ[በአርማህ ዘመን] እስልምናን በብልጠት ሰበኩ። በተከታታይ ዓመታት የሀገራችንን ምሥራቃዊ የባህር ጠረፎች ወረሱ።
3.0 የዮዲት እና እስራኤል አመፅ[600-800 ዓ.ም.]
በዮዲት አዝማችነት የተመራው የቤተ እሥራኤል አመፅ በከባድ ሁኔታ ተቀስቅሶ
= የአክሱም ከተማ ወደመ
= የሳባውያን መንግሥት ተደመሰሰ
= አባያተ ክርስቲያና ተቃተሉ
= መጻሕፍት ተቃጠሉ
= መምህራን ቀሳውስት ዲያቆናት ተገደሉ።
4.0 የውስጥ ለውጥና የሥልጣን ሽኩቻ[900-1200 ዓ.ም.]
በነገደ ሳባ እና በነገደ ዛጕየ መካከል ለ300 ዓመታት ሽኩቻዎች ስለቀጠሉ ክርስትናን አስቀድሞ በነበረበት ሁኔታ እንኳ መልሶ በእግሩ ለማቆም አልቻለም።
5.0 የቤተ ክህነት እና የቤተ መንግሥት መጣመር[1300 ዓ.ም.]
በአቡነ ተክለሃማኖት ዘደብረ ሊንባኖስ የፖለቲካ እና የሃይማኖት መሪ መሆን የመንግሥት ሥልጣን ከነገደ ዛጕዬ ወደ ነገደ ሳባ ተዛወረ።
ቤተ መንግሥት እና ቤተ ክህነት በቃል ኪዳን ተሳሰሩ ቃል ኪዳኑም 1262- ደርግ እስከ ተነሳበት እስከ 1966 ዓ.ም. ድረስ ጸንቶ ቆየ።
6.0 አስማት እና ኮከብ ቆጠራ
ወደ ኢትዮጵያ በተለያየ ጊዜ የገቡት ሁሉ በሀገራቸው ይሠራበት የነበረውን አስማት እና ከእርሱ ጋር ተያይዞ የሚገኘውን ለሙታን ነፍሳትና ለተለያዩ መናፍስት ስም እየሰጡ የመጥራት ልምድን ይዘው ሳይገቡ አልቀሩም። በተለይ ከአጼ አምደ ጽዮን 13ኛው ምእት ዓመት ጀምሮ በቤተ መንግሥቱ እና በቤተ ክህነቱ በግልጽ ይሠራበት ነበር።
7.0 አምልኮ ባእድ በአዋጅ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገባ[15ኛው ዓ.ም.
አፄ ዘራዓ ያዕቆብ ባወጣው አዋጅ እራሱን የቤተ ክርስቲያን መሪ በማድረግ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የሚከተሉትን እዳዎች አመጣ።
= ማርያም እና መስቀል ከፈጣሪ እኩል ይሰገድላቸው የሚል አዋጅ [አወጀ መስተብቁ ዘመስቀል ይመልከቱ]  ከምግብ በኋላ የሚባለው ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ከሚለው የሥላሴ ምስጋና ጋር ስብሐት ለእግዝትነ ማርያም ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ የሚለው ተጨመረበት። እሰግድ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በሚለው የአምልኮ ጸሎት ላይ እሰግድ ለእግዝትነ ማርያም እና እሰግድ ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ[ለመስቀል እሰግዳለሁ] የሚለው ተጨመረ።
= በእግዚአብሔር የማያምን ሰው ቢኖር በቅዱሳን አማላጅነት ይድናል የሚሉ ድርሰቶች በስፋት ተሰራጩ ለምሳሌ የበላኤሰብን ታሪክ የመሳሰሉ ድርሰቶች ወደ ቤተ ክርስቲያን ገቡ።
= እውነተኛውን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ያስተምሩ የነበሩ ሊቃውንት በእሳት ተቃጠሉ ተገደሉ ተሰደዱ በዚህ ምክንያት ሐሰተኛ ትምህርቶች ቦታ ሊይዙ ቻሉ።
መ. ለቤተ ክርስቲያን የተላከ የንሥሐ ጥሪ ወይም የመጀመሪያው ተሃድሶ [ከ1400-1500] ዓ.ም.]
= አባ እስጢፋኖስ በመንፈስ ቅዱስ አብርሖት በቅዱሳት መጻሕፍት መሳሪያነት የተቀበረውን ጥንታዊውን መሠረተ እምነታችንን ቆፍሮ አወጣ።
= <<የሰው መዳን በእግዚአብሔር ጸጋ የተጠናቀቀ ስለሆነ የክርስቶስ ሞት የኃጢአትን ዕዳ ለመክፈል እንደ ሆነ የሚያምን ሰው ከመሞቱ በፊት ድኛለሁ ብሎ መመስከር ይችላል>> አለ።
= የጥንቶችን እውነተኛ አማኞች እንደገና እደራጀ
= ገዳማትን መሠረተ
= በዘርዓ ያዕቆብ ፍርድ ተደብድቦ ሞተ።
= ተከታዮቹ በዐፄ ዘራአ ያዕቆብ፤ በአፄ በእደ ማርያም፤ በአፄ እስክንድር፤ በአፄ አምደ ጽዮን፤ በዐፄ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግሥት እየታደኑ ሲገደሉ ሲሰደዱ ኖሩ።
በዚህም ቤተ ክርስቲያኒቱ ከእግዚአብሔር የተላከውን የንሥሐ ጥሪ አሻፈረኝ አለች።
ሠ ከእግዚአብሔር የተላከ ተግሣፅ[ከ1527=1542 ዓ.ም.]
ነገሥታት እና የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በደቂቀ እስጢፋኖስ አማካኝነት ከእግዚአብሔር የተላከላቸውን የንሥሐ ጥሪ በመቃወማቸው መለኮታዊውን ትምህርት በመጋፋታቸው ከባድ ቅጣት ተላከ
= 1.0 ግራኝ መሐመድ በጭካኔ ተነሥቶ አብያተ ክርስቲያናትን አቃጠለ፤ ንዋዬ ቅድሳትን ዘረፈ፤ አንሰልምም ያሉ ቀሳውስት ዲያቆናት ምመናን ተገደሉ።
2.0 በካቶሊካውያን እና በኦርቶዶክሳውያን ጦርነት[ከ1607-1632 ዓ.ም.] ብዙ ደም ፈሰሰ።
3.0 <<ቅባት>> እና <<ጸጋ>> የሚባሉ ሁለት የእምነት ቡድኖች ተነሥተው ሲከራከሩ እና ሲዋጉ ብዙ ሰው አለቀ።[1632-1846 ዓ.ም.]
4.0 በመጨረሻ <<ካራ>> የተባለው ቡድን ተነሥቶ ምንም የአውጣኪን እምነት ያየዘ ቢሆንም <<ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እኔ ነኝ>> በማለት ሥልጣን ይዞ ቅባት እና ጸጋ የተባሉትን አስፈጀ[1847-1909 ዓ.ም.]
5.0 ድርቅ ረሃብ በሽታ ጦርነት የተለያዩ መቅሰፍቶች እስከ አሁን እንደ ቀጠሉ ናቸው። እነዚህ ሁሉ ሌላ ምክንያት ስለሚሰጣቸው የእግዚአብሔርን የንስሐ[ የተሐድሶ] ጥሪ ባለመቀበላችን እንደሆነ አልተገነዘብንም።
 ረ.  የአሁኑ የንስሐ ጥሪ [ተሐድሶ]
በአሁኗ ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ አቅጣጫውን የሳተ የምንኩስና መንፈስ ። በተለያዩ ቅዱሳን ስም ተሸፍኖ መናፍስትን የመማጸን ባዕድ ነገር፤ አስማቶች እና ጥንቆላዎች በአስፈሪ ሁኔታ አገሪቱን ማዳረሳቸው፤ ቀሳውስትና ምእመናን ወደ ተለያዩ እምነቶች መፍለስ፤ የትውሉዱ የሥነ ምግባር ውድቀት፤ ባዕድ ባሕሎች ርኩሰቶች እያደረሱ ያሉት ጥፋት እጅግ በጣም ያሳስበናል። ለዚህም ተሃድሶ ያስፈልገናል ይህ ማለት ሥራአት እና ሃይማኖትን መለወጥ ሳይሆን እውነተኛ የልብ ለውጥ ማድረግ እና ብቸኛ አምላክ ለሆነው ለዑል እግዚአብሔር መገዛት ማለት ነው።
ከሁሉም አስቀድሞ በቤተ ክርስቲያናችን ወንጌልን በመስበክ ወደ ጥንታዊት የአባ ሰላማ እመነት ለመመለስ ልብ የሠጠንን አምላካችችን እናመሰግናለን። ወገኖቻችን ይህን ታላቅ መለኮታዊ ሥራ ለመሥራት ጾምና ጸሎት ያስፈልገናል።  አረማዊ ልማዶችን እና በኋላ በጉልበት የተጨመሩብንን አረሞች ለመንቀል በትክክል ስዴውን ከእንክርዳዱ መለየት እንዳለብን እንክርዳዱ የትኛው ነው ስንዴውስ የትኛው ነው የሚለውን እግዚአብሔር ገልጦ አሳይቶናል። ይህን የንሥሐ ጥሪ የምንቀበል ከሆነ መከራችን ሊያጥር እና በሰማያዊ እና በምድራዊ በረከት ልንባረክ እንችላለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!
ከኆኅተ ብርሃን መጽሔት የተወሰደ መጋቢት 2002 ዓ.ም.

10 comments:

 1. Sir,

  Okay, do you know segdet is divided into two - yeamlikot and yeakibrot? We kneel down beofre God worshiping Him, but we kneel down before St. Mary just venerating Her. Also, we only kneel down one or two/three times for St, Mary, not more, but multiple times for God. In the Bible, we read in many places people kneeling down for the Angels and other people respected for their position in society. That is exactly what we are doing when we kneel dowm for St Mary and other Saints.

  However, I agree many dirts have been introduced in the church over the years that are not consistent with the true teaching of the Bible. Those need to be studied and erased from our books. Unfortunately, there is no interest to do so among the Sinodos members, who theoretically command the highest power of the church.

  ReplyDelete
 2. Ante Dirsan Ena Gedile yitfu Tilaleh gin ayitefum Enji bitefu Endante yalew Alawaki min Anbbo yalawakinet kihidet Ena alubalta yawarel?Geta Yemiwodew Dirsan weyiom gedile yisafiletal Endante Yalew hod amlaku Degmo Banda hono yikawemel negeru bemeshemakek Bihonm.mesihaf kidus talks About gedile lemisale ye Eyob tarikn eye ante mehayim.Balegediloch hulem yiregtuhal antem Ayinhin Chefineh Alkis

  ReplyDelete
 3. do you tell me who pritch kibat w

  ReplyDelete
 4. where do you get the history about dekike estifanos if it was not written as gedle estifanos? so we need gedel

  ReplyDelete
 5. እግዚአብሔር ይርዳን! እግዚአብሔር ያድሰን!

  ReplyDelete
 6. God bless you for this important information. May be it will open our eyes.Help us God to open our eyes. Now we can read the bible and follow through.

  ReplyDelete
 7. Thank you so much for this article! Please continue to write in detail about all the highlights you've mentioned. I really am interested in Dekike Estiphanos' history.

  ReplyDelete
 8. ቤተ ክርስትያን በኢትዮጵያ officially የተመሰረተችበት ግዜ በታሪክ ሲጠቀስ የሚነሱት ታሪኮች ተመሳሳይ ስላልሆኑ ሁልግዜም ይገርመኛል፡፡ አንዳንድ የታሪክ ምንጮች ኢትዮጵያን ለክርስትና Origin አድርገው ያያሉ ምክንያተቸውም በመጽሀፍ እንደተጠቀሰው ኢትዮጵያዊው ጃነደራባ ክርስትናን አስተምሩዋል የሚል ነው፡፡ ይብሱንም በትግራይ አንዳንድ ቅዱስ ቦታዎችም (አክሱም ማህበረ ድጓ ) ኢየሱስ ክርስቶስ በአካል እየመጣ ያስተምር እንደነበርና ብሎም ማህበርተኛ ሆኖ የማህበር ፅዋ ይጠጣ እንደነበረና ይጠጣበት የነበረው አንኮላ (መጠጫ)አሁንም በቦታው እንዳለ የሚገልጽ አፈ ታሪክ ይነገራል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታም ይህ ድህረ ገጽ ቤተ ክርስቲያን በ56 ዓ.ም.ተቋቋመች የሚለውን ሃሳብ ይዞ ይተነትናል፡፡
  ሌሎች የኦርቶዶክስ የታሪክ ምንጮችና Encyclopedia Britannica እንዲሁም Wikipedia የመሳሰሉት ደግሞ ክርስትና በኢትዮጵያ officially ገበቱዋል ብለው የሚጠቅሱት በ4ኛው ከ/ዘመን (330 ) በንጉስ ኢዛና ዘመን በፍሬምናጦስ መሆኑን ይታወቃል (According to traditional sources, paganism as well as Judaism were practiced side by side in Ethiopia before the introduction of Christianity. Both were the result of contact with Middle Eastern countries through commercial channels) http://www.ethiopianorthodox.org/english/ethiopian/prechristian.html

  "Before its conversion to Christianity, the Aksumites practiced a polytheistic religion related to the religion practiced in southern Arabia. This included the use of the crescent-and-disc symbol used in southern Arabia and the northern horn. In the UNESCOsponsored General History of Africa French archaeologist Francis Anfray suggests that the pagan Aksumites worshipped Astar, his son, Mahrem, and Beher. Before converting to Christianity King Ezana II's coins and inscriptions show that he might have worshiped the gods Astar, Beher, Meder/Medr, and Mahrem..."

  https://www.quora.com/Before-Christian-Islam-what-religion-is-Ethiopian

  መቸም ዘመኑ የአብርሆት(Enlightenment) ዘመን ነውና ሁሉንም የታሪክ ትንታኔዎች Google እያደረግን እናነባላን እንመረምራለን፡፡ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ አፈ ታሪክን በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንፈትሻለን፡፡ ምንም እንኩዋን የተለያዩ ሰዎች እንዲሁም የሀይማኖት ተቁዋማት እንደ አመቺነቱ የፈለጉትን ትንታኔ ቢከተሉም እኔ እንደሚመስላንኝ ግን ሁለተኛው ትንታኔ የተሻለ ይመስላኛል፡፡ ምክንያቱም የክርስትና ባለቤት ክርስቶስ እስራኤላዊ በመሆኑ ክርስትናም Originኑ ከዛው ከሀገረ እስራኤል መሆን ስላለበት ነው፡፡ ክርስትና Originኑ እስራኤል ከሆነ ደግሞ ሌሎች ሀገራት (ኢትዮጵያን ጨምሮ) Origin ሊሆኑ አየችሉም፡፡ ምን ትላላችሁ?

  ReplyDelete