Wednesday, February 9, 2011

ገለባ ውስጥ የተደበቁትን ሁሉ ትንሽ እሳት ያስፈራቸዋል

ከፍርሐት፣ ከሥጋትና ከጭንቀት ነጻ ሆነው የሰላም እንቅልፍ ተኝተው ማደር የሚችሉት እውነትን የያዙና የሰው ደም የሌለባቸው ንጹሐን ብቻ ናቸው። ቃኤል ወንድሙን አቤልን ያለምንም ምክንያት ከገደለ ጀምሮ ፈሪና ተቅበዝባዥ ሆኖ ትንሽ ኮሽታ ሲያስደነግጠው የኖረ ሰው ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት የአቤል ደም ወደ እግዚአብሔር በመጮኹ ነበር። ዘፍ 3፡10። የጻድቅ ደም እንቅልፍ አያስተኛም።
ዳንኤልን ያለምንም በደል በተራቡ የአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ያስጣለው የጥንቷ የባቢሎን የዛሬዋ ኢራቅ ገዢ የነበረው ሜዶናዊው ዳርዮስ እንቅልፍ አጥቶ ምግብም አልበላ ብሎት ሰላሙን አጥቶ አልጋው አልመቸው ብሎ ሲሰቃይ እንዳደረ ት/ዳን 6 ቁ 18 ላይ ይናገራል። ነቢዩ ኢሳይያስ ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል ኢሳ 57 ቁ 21። የሰው ደም እንደ ውሃ ሲያፈሱ፣ ጻድቁን ሲኮንኑ፣ ኃጥኡን ሲያጸድቁ በፕሮፓጋንዳቸው ተሰውረው ትንሽ እድሜ ያገኙ ሁሉ ሰላም የላቸውም።
በአሁኑ ሰዓት ይህን መጻፍ የፈለግሁት አንዳድ ቡድኖች በተለኮሰባቸው የነጻነት እሳት የሚይዝቱን እና የሚጨብጡትን አጥተው እየተወራጩ ስለሆነ ወገኖቼ የፕሮፓጋንዳቸው ሰለባ እንዳይሆኑ ለመከላከል ነው። እነዚህን ገለባ ውስጥ የተደበቁትን የደም ሰዎች እንደሚከተለው አቅርቢያቸዋለሁ።
1ኛ ኢሕአዴግ
ይህ ፓርቲ ከተመሠረተ ጀምሮ ያፈሰሰው ደም ወደ ላይ እየፈሰሰ አንገቱ ደርሶ እያነቀው በሞት ፍርሐት ውስጥ የሚኖር ተስፋ የሌለው ፓርቲ ነው። ነገር ግን ጽዋው ገና ስላልሞላ በሕይወት ያለ ግዙፍ ፓርቲ ይመስላል። ኢሐዴግ የሕጻናት፣ የወጣቶች፣ የሽማግሌዎች፣ የምሑራን፣ የመሐይምናን፣ የባልቴቶች፣ የወታደሮች ወዘተ ደም ወደ እግዚብሔር እየጮኸበት እንቅልፍ ያጣ ድርጅት ነው። እውነተኛ ሰዎች ያስደነግጡታል በራሱ አይተማመንም፣ የቃየልን መንፈስ ተዋርሶ ስለሚጠንቁል ያገኘኝ ሁሉ የሚገለኝ ይመስለዋል።
ቃኤል አቤልን ከገደለ በኋላ ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል አመለከተ በምድር ኮብላይ እና ተቅበዝባዥ እሆናለሁ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል አለው እግዚአብሔር ግን ይህ ፍርሐቱ የፈራውን ሁሉ ሰው በተደጋጋሚ እንዲገል ስለሚያደርገው ቃየልን ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት አደረገለት ይላል ዘፍ 3 ቁ 14-15። እግዚአብሔር ቃየልን ማንም እንዳይገድለው የሚጠብቀው ምልክት ባያደርግለትና ትንሽ እረፍት ባይሰጠው ኖሮ ቃየል የፈራውን ሁሉ በመግደል ሰዎችን በጨረሰ ነበር።
ኢሕዴግን ከአራት ኪሎ እንዳይወጣ በሩን ዘግቶ ባለፈ ባገደመው ላይ እየተኮሰ እንዲቆይ ያደረገው ያፈሰሰው የደም ብዛት ስለሚጮኽበትና ያገኘኝ ሁሉ ይገለኛል ከሚለው ፍርሐቱ የተነሣ ነው። ይህ የቃየል መንፈስ እንዴት ይወገድለታል?
ኢሕአዴግ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ነኝ እያለ ቢያወራም አስተማማኝ የሆነ መኖሪያ ቤት የሌለው ገለባ ውስጥ የሚኖር መሆኑን እራሱ ያውቀዋል። ስለዚህ ትንሽ እሳት እጅግ ያስፈራዋል። ለምሳሌ አረና የተባለውን የትግራይ ፓርቲ እጅግ ስለሚያስፈራው ፎርጅድ አረና ሰርቶ ዋናውን እውነተኛ ፓርቲ ለማፍረስ እየሠራ ነው። አረናን ለምን ፈራው? ሕውሐት በትግራይ ሕዝብ ስም ዘግናኝ በደሎችን የፈጸመ ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ያደረገ፣ ባድሜን ፈርሞ የሰጠ፣ የትግራይን ምርጥ ልጆች [እነሐየሎምን]ያለምንም ምክንያት የገደለ፣ የትግራይን ሕዝብ ከጎረቤቶቹ ከኤርትራ፣ ከወገኖቹ ከአማራ፣ ከኦረሞ፣ ከሱማሌ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ብሔረሰቦች ጋር ያጋጨ ጠላት የፈጠረ ግፈኛ በመሆኑ ትግራይን ከሌሎች ብሔረሰቦች ጋር ሊያስታርቅና በጋራ በኩልነት በነጻነት እንድትኖር ሊያደርግ የሚችል ፓርቲ የወያኔን ግፍ ሊያጋልጥ የሚችል በመሆኑ ይፈራዋል። አረና ከኢትዮጵያውያን ጋር እንዴት መኖር እንደሚገባ የተረዳ ቀና ፓርቲ፣ ብሐራዊ እርቅን የሚደግፍ፣ አብሮ መኖር የሚፈልግ ይመስለኛል።
ወያኔ ግን በጠባዩ ነፍሰ ገዳይ ነው። እንደ አቤል ያለ ቀና ፓርቲን ስለሚመቀኝ መግደል አለብኝ ብሎ ያስባል። ኢሕአዴግ ማንም እንደማይገድለው እንደ ቃኤል ምልክት ካልተደረገለት ገና ብዙ ይገላል ባይ ነኝ። እናም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕውሃትን ፍርሃት ሊያስወግድ የሚችል ፖለቲካዊ መተማመኛ እንዲሰጡት ስል እማጸናለሁ። አጥፍቶን ከመጥፋቱ በፊት ያገኘው ሁሉ እንደማይገድለው ማረጋገጫ ያስፈልገዋል። በዚህ ወቅት ግብጽ ላይ የተለኮሰው እሳት ገለባ ቤት ውስጥ የሚኖሩትን የአፍሪካ አምባገነኖች እያስደነገጠ ነው። የኛው ሕዋሐትም ኑሮው በታላቅ ፍርሐትና በጭንቀት ነው። ከዚህ ሁሉ ለምን ከገለባ ቤት ወጥቶ እሳት ወደማያስፈራው ዲሞክራሲያዊ ጽኑ ቤት ሽግግር አያደርግም? እሳት በተነሳ ቁጥር ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ ለምን ግራ ያጋባናል? ነፋሱ ወደ ኢትዮጵያ ከነፈሰ እሳቱ ፊቱን ማዞሩና ገለባውም መበላቱ የማይቀር ነው። ስለዚህ ገላባው ውስጥ ያላችሁ ሁሉ ከገለባው ውጡ።
2ኛ የሃይማኖት መሪዎች
የሃይማኖት መሪዎች የእግዚብሔርን ድምጽ ለሕዝብ ለማሰማት በእግዚአብሔር ወንበር ላይ የተቀመጡ የከበሩ ሰዎች ናቸው። ነገር ግን አቀማመጣቸው ለአደጋ አጋልጧቸዋል። መንግሥት መገሠጽ እግዚአብሔር ልብ ለሰጣቸው መሆኑን አውቃለሁ ስለዚህ ለምን አይገሥጹትም የሚል ፍርድ ለመናገር አልደፍርም። እኔም ከዚያ ቦታ ላይ ብቀመጥ ምን ላደርግ እንደምችል አላውቅምና በሰው ግፊት ሰማትነት እንዲቀበሉ አልመክርም። ነገር ግን መገጸሥ ባይችሉም ከኢሐዴግ ጋር መተባበራቸው ከተጠያቂነት አያድናቸውም። በልማት በመልካም አስተዳደር ቢተባበሩ ተገቢ ነው። እንደ ኢሕአዴግ ሆነው የኢሐዴግን ተቃዋሚዎች ንጹሐንን አሳልፈው መስጠታቸው ግን ከቃኤል ማህበር ውስጥ መገኘታቸውን ያመለክታል።
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በአሜሪካ የሚገኙት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ምርቆርዮስ 13 ጳጳሳትን በሾሙ ጊዜ የአዲስ አባባን አገልጋዮች በማዋከብ ሰላም ነስተዋቸው እንደነበር እናስታውሳለን። ዛሬም የዉጩ ሲኖዶስ ሲነሣ እንቅልፍ እንደማይወስዳቸው ብዙ ጊዜ ታዝበናል። ይህ ሁኔታ ቃኤል እና አቤልን እንድናስታውስ ያደርገናል ቃኤል ሰላም አልነበረውም አቤል ግን እረፍት ላይ ነበር። በውጭ ያለው ሲኖዶስ በውጩ ዓለም ያሉ ኢትዮጵያውያንን በማስተማር በመሰብሰብ አንድነቱን አጠናክሮ እሳት በሚተፉ ስባኪዎቹ ታጅቦ ወደ ኢትዮጵያ የመግባት ተስፋ ያለው ነው ይባላል። የአቡነ ጳውሎስ ሲኖዶስ ግን በ2009 ዓ.ም በተነሣው የውስጥ ክፍፍል ታላላቅ አባቶችን በሌሊት እንደ ወንበዴ ሲደባደብ ተስተውሏል። ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከገለባው ውስጥ ሊወጡ ይገባቸዋል። በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ታላላቅ ቦታዎች ላይ ተሹመው የሚገኙት የኢሕአዴግ አባላት የሆኑት ስለሆኑ ሕዝቡ የሐይማኖት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ እስራትም እንዲኖርበት እንዳይንቀሳቀስና ሃማኖታዊ ንቃት እንዳይኖረው እመቤቴ ታውቅላሃለች በሚል አጉል ተስፋ እንዲደነዝዝ ተደርጓል። ይህ ገለባ እሳት የበላው ቀን ወዮ!
3ኛ ማህበረ ቅዱሳን
ማህበረ ቅዱሳንን በየጽሑፋችን የምናነሳው ጥላቻ ስላለብን አይደልም። ኢትዮጵያን ወደ ኋላ እየጎተተ ያለ ለኢትዮጵያ የማይጠቅም አስተሳሰብ ይዞ ስለሚራመድ እንዲያስብብበት ለማድረግ ነው። አባላቱ ወንድሞቻችን ናቸው ነገር ግን አሳባቸው እጅግ በጣም የተባለሸ ነው። መንፈሳዊ ነገር የተማሩ ቢመስሉም ምንም የሚያውቁት አንዳች ነገር የለም። አባላቱ የማህበረ ቅዱሳን አባላት የሆኑት መንፈሳዊ ነገር ተረድተው ሳይሆን የፕሮፓጋንዳ ሰላባ በመሆናቸው ነው። የሚማሩት ሃይማኖታዊ ፖለቲካ እንጂ የእግዚአብሔርን ፈቃድ አይደለም። የሳይኮሎጂ ችግር ውስጥ ገብተዋል። ይህን ለማረጋገጥ አንድ ነገር እንድታስተውሉ ልጠቁማችሁ።
እነርሱ ባሉበት ሁሉ ሰላም የለም። ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ ለራሳቸው ማምለክ ሳይሆን የሚፈልጉት የሌሎችን አለባበስ፣ አዘማመር፣ ካህናቱ ቅዳሴ ገብተው እስኪወጡ ድረስ እንቅስቃሴያቸውን መከታተል፣ ቃጭሉ ምን ያህል ጊዜ እንደተመታ፤ መጋረጃው መቸ እንደተዘጋ እና እንዳልተዘጋ ማየት፤ የሁሉንም ምእመናን የአምልኮ ሁኔታ መቆጣጠር፤ ትክክል አይደለም ያሉትን ለማስተካከል በመከራከር የሃይማኖት ፖሊስ መሆን ይፈልጋሉ። በዚህ አሰልቺ ክርክራቸው ስንቱ ክርስቲያን እቤቱ ቀርቷል?። ሰርግ ላይ ሲገኙ ማን ምን እንደለበሰ የሚቆጣጠሩት ማህበረ ቅዱሳኖች ናቸው። በሰርጋቸው ላይ ከውሃ በቀር ሌላ እንዲጠጣ አይፈልጉም። በቬሎ የተጋቡ ሙሽሮችን አጥብቀው ያወግዟቸዋል።
በሰዎች ላይ መከፋፈልንና የሳይኮሎጂ ችግር ሊያመጣባቸው የሚችለውና ዋናው የማህበረ ቅዱሳን የፍርኃት ትምህርት ተሃድሶዎች እትዮጵያን ሊያጠፉ የመጡ ናቸው የሚለው ነው። ይህ ፕሮፓጋንዳ በኦርቶዶክሳውያን መካከል መተማመን እንዳይኖር ከሳሽ እና ተካሽ ሆነን እንድንከፋፈል አድርጎናል። ፍርሐትን እንጂ እምነትን አይማሩም፤ በዚህ ምክንያት በአብያተ ክርስቲያናት ሰላም ጠፍቷል እስከ አሁን ያልበረደው የአዋሳ ገብርኤል ብጥብጥ በማህበረ ቅዱሳን የሚመራ ነው። በአሜሪካ በዳላስ ሚካኤል ዱላ እስከመማዘዝ ደርሰዋል። የውጭው ሲኖዶስ ጨርሶ ስላባረራቸው በሰላም እየኖረ ነው ከዚያ በፊት ግን በነዳንኤል ክብረት አዝማችነት ከፍተኛ ሁከት ነበር።
ዛሬ በነሱ ላይ ለመጻፍ የተነሳሳሁበት ምክንያት ደጀ ሰላም በተባለው ጸረ ሰላም ድረ ገጻቸው ላይ የተሃድሶ ወጥመድ” የሚል ሐሳብ ያለው ጽሑፍ ካነበብሁ በኋላ ነው። ይህ ፕሮፓጋንዳ ኦርቶዶክሳውያን እርስ በርሳቸው እንዳይተማመኑ የሚያደርግ ተንኮል ስለሆነ ወገኖቼን ተተንቀቁ ለማለት ነው።
ኢሕዴግን ዲሞክራሲ የሚያስፈራውን ያህል ማህብረ ቅዱሳንንም ወንጌል ያስፈራዋል። ኢየሱስ የሚል ስም ያስደነግጠዋል፤ ወንጌል የኃጢአትን ቆሻሻ የሚያቃጥል እሳት መሆኑ የታወቀ ነው። ማህበረ ቅዱሳን ወንጌልን የሚፈራው ገለባ ውስጥ ተደብቆ ስለሚገኝ ነው። ገድላት እና ድርሳናት በሚል ጭፍን ፕሮፓጋንዳ ይዘታቸውን የማያስተውለውን ሕዝብ በማሰለፍ የገንዘብ ምንጫቸው ስላደርጉት ወንጌል ሲሰበክ አይወዱም ኢየሱስ ጌታ አዳኝ የሚሉ ሰዎች ሁሉ ተሃድሶዎች ስለሆኑ አትስሟቸው ብለው አባላቱቹን አሳውረዋቸዋል።
እውነቱን የተረዱ ወጣቶች የቤተ ክርስቲያናቸውን ችግር ለይተው ያስተዋሉና ቤተ ክርስቲያናችንን አንለቅም ብለው የቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን እውነቱን አውቀው ወደ ሌላ ሃይማኖት እንዳይፈልሱ በቅንነት እየተጉ ያሉትን ወገኖች ስማቸውን በመበከል መከራ ሊያመጡባቸው ይፈልጋሉ። ከሣቴ ብርሃን የተባለውን ኮሌጅ እና ቅድስት ሥላሴን መጥፎ ጥላሸት እየቀቡ ናቸው። እነዚህ የቤተ ክርስቲያናችንን ተስፋዎች ድርሳን እና ገድል ካላነበባችሁ ተብለው እንደዚህ የሚወገዙት ለምን ይሆን? እስልምና አገር እየወረረ ባለበት በዚህ አሳዛኝ ወቅት ሰባኪዎቻችንን ተቀባይነት እንዲያጡ የሚድረገው ሥራ ሰይጣናዊ ሥራ እንጂ ሌላ ፋይዳ አይገኝበትም።
እነዚህ ወንድሞቻችን ትምህርት ቤት የገቡት ከሕዝቡ የተሻለ አስተሳሰብ እንዲያገኙና ሕዝብን ካለበት ችግር እንዲያላቅቁ ታስቦ እንጂ ባሉበት ላይ እየረገጡ ጎታች ቡድኖች እንዲሆኑ አይደለም። የመንፈሳዊ ኮሌጆቻችን ተማሪዎች መለወጥ ለቤተ ክርስቲያናችን ተስፋ ነው። ዘኬ በመብላት ጊዜያቸውን ከሚያባክኑ 500000 [አምስት መቶ ሺህ] ካህናት ውስጥ የለውጥ ሰዎች ማግኘታችን እድሎኞች ያደርገናል እንጂ የሚጎዳን አይደለም። እነርሱ ቤተ ክርስቲያን በጥራት መጓዝ እንዲኖርባት ለማስተካከል የሚታገሉ እንጂ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት እንዳልሆነ ለማንም ግልጽ ነው።
ማህበረ ቅዱሳን እውነት መስሎት ልጄ ልጄ እየተባለ ሲቆላመጥ በነበረበት ወቅት በትውልዱ ላይ ያን ሁሉ ቆሻሻ ትምህርት ዘርቶ አሁን እውነቱ እየወጣ ሲጋለጥ ስም በማጥፋት ጊዜውን ለማራዘም ይታገላል። ካፈርሁ አይመልሰኝ እንደሚባለው መረጃ አገኘሁ ሊያጠፉን ነው በማለት ይጮኻል።
በመሠረቱ ማህበረ ቅዱሳን ለተሰጡት አስተያየቶች መልስ መስጠት አለበት።  በ abaselama.org ላይ የቀረቡት ትችቶች መልስ አልተሰጠባቸውም።  የዶሮ ጭንቅላት መብላት እንደ ቅባ መንግሥት ሆኖ በገድለ ተክለሃይማኖት ላይ መገለጡ ከምን የተቀዳ ልምምድ ነው? ለሚለው ጠንካራና ግልጽ ጥያቄ መልስ መስጠት ያስፈልጋል ወይም መጽሐፉን አንቀበለውም የኛ አይደለም ማለትም አንድ መልስ ነው። ከዚህ አልፎ ግን ባዶ ፕሮፓጋንዳ መንዛት ያልበላውን ማከክ ነው። እውነቱን መደበቅ አይቻልም። ማህበረ ቅዱሳን እውነቱን በመሸሽ በፕሮፓጋንዳው እቀጥላለሁ ካለ ግን በተጨባጭ አሁን እየተደረጉ ያሉ አስከፊ የሚባሉ ሃይማኖታዊ ሽፋን ተሰጥቷቸው የሚፈጸሙትን ምሥጢራዊ ወንጀሎችን ወደ አደባባይ እንዲወጡ ያደርጋቸዋል። ይልቁንስ ተሃድሶ እያለ ከሚከሳቸው ወንድሞቹ ጋር በመወያየት ክርስትናው በኢትዮጵያ የሚስፋፋበትን መንገድ በጋራ መፈለግ፣ መታረም ያለባቸው እንዲታረሙ መርዳት፣ አጉል ኩራት አይሆንም እራት እንደተባለው የሁለት ሺህ ዓመት ታሪክ አለኝ የሚለውን ትምክህት ትቶ ዛሬ የጌታን ፈቃድ ቢፈጽም ይሻለዋል።
አንዳድ አስተያየት ሰጭዎች ተሃድሶዎች ኦርቶዶክስን ትተው ፕሮቴስታንቱን ለምን አያድሱም ይላሉ። እነርሱ ስለቤታቸው እንጂ ስለጎረቤታቸው የሚያገባቸው ነገር የለም የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች እንደተባለው መሆን አይፈልጉም።
ማህበረ ቅዱሳን እንደሚያወራው ተሃድሶዎች ቤተ ከርስቲያኒቱን ለማፈረስ ሳይሆን ከወደቀችበት ለማንሳት ትልቅ ሸክም ያለባቸውና ወደ ጥንታዊ ማንነቷ እንድትመለስ የሚደክሙ ናቸው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!
በተስፋ አዲስ

11 comments:

 1. Well said here "...ይልቁንስ ተሃድሶ እያለ ከሚከሳቸው ወንድሞቹ ጋር በመወያየት ክርስትናው በኢትዮጵያ የሚስፋፋበትን መንገድ በጋራ መፈለግ፣ መታረም ያለባቸው እንዲታረሙ መርዳት፣ አጉል ኩራት አይሆንም እራት እንደተባለው የሁለት ሺህ ዓመት ታሪክ አለኝ የሚለውን ትምክህት ትቶ ዛሬ የጌታን ፈቃድ ቢፈጽም ይሻለዋል።"

  However, why do you attack our most beloved Mother? It is sad that you guys believe that you cannot make your point without attacking St. Mary. The following statement is very offensive;

  "...ሃማኖታዊ ንቃት እንዳይኖረው እመቤቴ ታውቅላሃለች በሚል አጉል ተስፋ እንዲደነዝዝ ተደርጓል። ይህ ገለባ እሳት የበላው ቀን ወዮ!"

  It may be okay for unbelievers perhaps like you, but it is offensive for most of us who have St. Mary deep in our heart.

  It crearly shows where you are heading. Faith in the intercession of our Mother is core to all genuine EOTC christians although it may be "geleba" for you guys. It is one thing to demand genuine and well deserved reform, but it is another thing to attack our Mother and belittle Her love and intercesion for us. You seem to have an ulterior motive as most accuse you. Don't bother man - we will not cooperate to lose and/or defame our most beloved Mother. We are better off bearing the arrogance of MK and carrying ome books that may need "correction." With our patience, we will buy salvatiion. God will send us genuine reformers who truely care for the Gospel and love our church and our most beloved Mother. Short of that, all your effort is misplaced and is in vain.

  ReplyDelete
 2. Come on! the above commenter. I think you have misunderstood the writter. I am sure he loves our mother St. Mary more than you do. This article is not about St. Mary. You ignore the most important and the obvious issue, but you pull a sentence in the article and give it a spin. come on! Read the context, the general idea. You already assumed the wirtter is your enemy. That's not where you should start. When you do that your analysis will be out of touch with what the writter intends to do.

  ReplyDelete
 3. እውነትም ማህበረ ሰይጣን
  ከተፃፈው ስንት ቁም ነገር መካከል ላንተ የታየህ ቁም ነገር ያልሆነው ነው። አላዋቂ ሳሚ ምን ይለቀልቃል አሉ አሁንም ያልተጠየከውን ከምትመልስ የተጠየከውን ብትመለስ ይሄ ህይወት ያለው ሬሳ ለሆነው ባዶ የጨዋዎች ጥርቅም ማህበረ ሰይጣን( የአክራሪ እስላምች የውስጥ ለውስጥ ደርጅት)ታላቅ የሆነ መጥፋት ምክንያት ትሆናለህ የተጠየከውን መልስ ድንግልን ያከበርክ እያስመሰልክ አታዋርዳት እሷ አንተ አከበርካት አላከበርካት የጌታ እናት ናት እንዲሁ የከበረች ናት እናንተ ልምትቀቧት የሃሰት ክበር እሷም ጊዜ የላት አትልፉ እናቱ ማንነቷን ከማንም የበለጠ ታውቃለች እውነተኛ የተዋህዶም ልጆች የድንግልን ክብር ከማህጸን ሳይወለዱ ያውቁታል። ያልተጠየከወን አታውራ። ይግረምህና ጸሃፊው ማርያምን አንተ ከምታስበው በላይ አክብሮ እንደሚወዳት እርግጠኛ ነኝ ደሞም ባየፈልጋትመ እሱ ቀረበት እነጂ አንተ ምንም የተጎዳኸው ነገር የለም ስለዚህ ስለራስህ አስብ። አሁንም ህዝቡን በአባታችሁ በዲያቢሎስ አስማት አታደንዝዙት ወንጌል ይሰበክለት የድንግል አማላጅነት በስነስርዓት የነገረው ገድላት ደርሳናት ይታረሙ የማንም መጤ ሃይማኖት መሳቂያ እንዳንሆን በተለይ በተለይ መህበረ ቅዱሳን የሚባል ውሸታም ክርስቲያን መሰል ከሃዲ ግሩም እራሱን ለቤተ ክርስቲያን ያስገዛ እንደው በዚህስ ዘመን ጸበል ለናንተ ነበር የሚያሰፈልገው። የያዛችሁ ሰይጠን እስኪወጣ እናስጠምቃችሁ ነበር ለማንኛውም የሄንን ጽሁፍ ያዘጋጅህልን በርታ አሁንም የድንግል ልጅ ጌታ ኢየሱስ እንደ ጳውሎስ የኦሪትን ቅርፊት በብረሃኑ ገልጾልህ ለትውልድ መዳን ምክንያት ትሆን ዘንድ ጸሎቴ ነው
  እግዚአብሔር ሃገራችንን እና ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን።

  ReplyDelete
 4. . . . ወንድሞች ሆይ ጊዜው ሳይደርስ በማንም ላይ አትፍረዱ የሚል የመጽሀፍ ቃል አለ። የሁላችንም ቅናት የሁላችንም ጩኸት የቤተ ክርስቲያናችንን ትንሳኤና እድገት ለማየት ነው፤ እርስ በርስ መወጋገዛችን የሚያተርፍልን ነገር የለም የጠላት መጠቀሚያ ከመሆን በስተቀር። ማኅበረ ቅዱሳንም ሆኑ ሌሎች ቤተ ክርስቲያን ህጋዊ እውቅና የሰጣቻቸው ማኅበራት እንደሚገባኝ ከሆነ እየሰሩ ያሉት ለቤተ ክርስቲያን እድገት ይመስለኛል። ስለዚህም ስህተቶቻችንና ጉድለቶቻችንን በመነጋገር ለማረም መሞከር እንጂ ጎራ ለይቶ በቃላት መጠዛጠዝ ጥቅሙ ለማን እንደሆነ አልገባኝም፤ እንደው ዘንግ በተወረወረ ወፍ በበረረ ቁጥር መግለጫ ማውጣትና አካኪ ዘራፍ እያሉ የስም ማጥፋት ዘመቻ ማካሄድ ክርስቲያናዊ አካሄድ አይመስለኝም፤ ሁሉም በፍሬው ይታወቃል፤ ሁሉንም እግዝብሔር ወደ ብርሃን ያመጣዋል።

  ዛሬ ማኅበረ ቅዱሳንን የዲያቢሎስ ቁራጭ አድርገው የሚናገሩ ግለሰቦችም ሆኑ ማኅበራት በትክክል ስለ ማኅበሩ ለመናገር ቢያንስ እንቅስቃሴያቸውንና ስራቸውን መገምገም ያስፈልጋል፤ እንዲሁ በስማ በለው በሆነ አካሄድ ማኅበሩን ጥላሸት መቀባት ደግ አካሄድ አይደለም በእርግጥ ማኅበረ ቅዱሳን እንደ እኔ እና እንደ እናንተ ያሉ ሰዎች ስብስብ እንጂ የመላእክት ማኅበር አይደለም ሊሳሳት ሊደክም ይችላል። ማኅበሩም ለእስከዛሬው ጉዞውና ስኬቱ የእግዝብሔርን ጸጋና ኃይል፣ የቅዱሳንን ጸሎትና አማላጅነት በመተማመን ያከናወነው እንጂ በራሴ ብርታትና ጥረት ነው እዚህ የደረስኩት የሚል ትምክህት ተናግሮ የሚያውቅ አይመስለኝም፤ በዩኒቨርስቲ ቆይታዬም ሆነ በስራ ዓለም እንደታዘብኩት ለቤተ ክርስቲያን እድገት፣ ለቤተ ክርስቲያኒቷዋ ቅርስና ታሪክ ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጥ፤ በክብር ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ የሚጥር መሆኑን በተደጋጋሚ በቃል ብቻ ሳይሆን በሥራም ጭምር አሳይቷል፤ ለዚህም በተለያዩ ገዳማትና ታሪካዊ ቅርሶች ባሉበት ሁሉ አቅም በፈቀደ መጠን እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ለቤተ ክርስቲያንን ብቻ ሳይሆን ለሀገሪቱ የቱሪዝም እንዱስትሪ ፋይዳ ያለው ጭምር መሆኑን ለታሪኩ ለማንነቱና ለክብሩ የሚቆረቆር ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚመሰክረው ነው።

  ቤተ ክርስቲያኒቱ በሀገራችን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ታሪካዊ ተቋማት ላይ ካላት መጠነ ሰፊ ድርሻ አንጻር ማኅበረ ቅዱሳን በእነዚህ ዘርፎች ላይ ሀገር አቀፍ የሆኑ ጥናቶችንና ዓውደ ርእዮችን በማዘጋጀት እየተጫወተ ያለው ሚና ልናደንቀው የሚገባ ነው፤ በስራ ዓለም ያሉ የማኅበራቱ አባላትም በተለያየ አጋጣሚ ለመታዘብ እንደሞከርኩት ለቤተ ክርስቲያናቸው ለታሪካቸውና ለቅርሳቸው ያላቸው መቆርቆርና ክብር ይሄ ነው የሚባል አይደለም፤ ለአባቶች፣ ለቤተ ክርስቲያን ትውፊትና ሥርዓት ያላቸው ክብርና ትህትና እንዲሁም ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ ነው።

  በእርግጥ ይሄ አስተያየቴ ሁሉንም ያጠቃልላል ማለት ባይቻልም እንደ መልካም ግጽታ ልንወስደው የሚገባ ነው፤ በተቃራኒው ተሃድሶን እናራምዳለን ከሚሉት የሚበዙት የወረቀት ነብር ከመሆን የዘለለ ሥራ ሲሰሩ አላየንም፤ ሀገራችን በብዙ የውጭ ጠላቶችና በእስልምና እምነት አራማጆች የመወረር አደጋ ደጋግማ በወደቀችበት ዘመን ለክርስትና እምነት መቀጠል ነፍሳችውን ጭምር ሳይሳሱ የሰጡ አባቶችን ያፈሩ ገዳማትን ለመርዳትና ለማገዝ አይደለም በእግራቸው ለመርገጥ እንኳ እንደ ኃላ ቀርነትና የወንጌል እንቅፋት እንደሆነ አድርግው በመገመት እየሄዱበት ያለው አካሄድ ከራሳቸው ጋር የሚያጋጫቸው ይመስለኛል፤ ነገሮችን በጥልቀት እንፈትሻቸው ከተባለ ተሃድሶን እናራምዳለን በሚሉትና በሚቃወሙት ማኅበራትም ሆነ ግለሰቦች ዙሪያ በግልጽ መነጋገር ያለብን ብዙ ጉዳዮች ይኖራሉ፤ አነሳሴ ይሄን መጠነ ሰፊ ርእሰ ጉዳይ በዚህ ጹሁፌ ለማንሳት አይደለም ምናልባት በሌላ ጊዜ እመልስበት ይሆናል ነገር ግን አንድ ነገር ለማለት እወዳለሁ ይኽውም እንዲሁ በጭፍን በሆነ አካሄድ ተሃድሶ ተሃድሶ የሚለው ጩኽት ከጥቅሙ ይልቅ አደጋው ሊያመዝን ይችላል የሚል ፍርሃት አለኝ፤ ተሃድሶ ያስፈልገናል የሚለው ምንም ጥያቄ የለውም ለምን፤ እንዴትና በምን አኳኃን የሚለው ግን በጥልቀት መታየት ያለበት ጉዳይ ነው። የቤተ ክርስቲያን አባቶችም ሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ጉዳይ ላይ መእመኑን ለመታደግ ሲባል አፋጣኝ መልስና መፍትኄ ሊሰጡን ይገባል።

  በመጨረሻም ተሃድሶን እናራምዳለን በሚሉት ማኅበራትም ሆነ ግለሰቦች ዙሪያ የሚነሳው በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ስላሉት መጽሀፍት ዙሪያ ብዙ ማለት ይቻላል፤ በእኛ ዘመን እንኳ ባህታዊ ገ/መስቀል የተባሉ ባህታዊ የደረሷቸው ናቸው በሚል በየቤተ ክርስቲያኑ ሲሸጡ የነበሩ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሲኖዶስና የሊቃውንት ጉባኤ ያላርሟቸው መጻህፍት ነበሩ ዛሬም አሉ፤ ከበሽታና ከክፉ መንፈስ ይከላከላሉ በማለት በጊዜው በርከት ያሉ ሰዎች እንዚያን መጻህፍት በኪሳቸው በአንገታቸውና በራስጌያቸው ያደርጉ እንደነበር ትዝ ይለኛል። መጽሀፍን በተመለከተ ሥልጣኑም ኃላፊነቱም ያለው ቅዱስ ሲኖዶስና የሊቃውንት ጉባኤ እንጂ ማኅበራት አይመስሉኝም፤ በርግጥ የቤተ ክርስቲያን ልጆች እንደ መሆናችን መጠን አስተያየትና ጥቆማ መስጠት እንችላለን። ያለመታደል ሆኖ በሂደት እንደተገነዘብነው የቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶስ በብዙ እያሳሰበው ያለው የገንዘብ፤ የስልጣንና የራስ ክብር እንጂ የክርስቶስ ወንጌልና የአብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ አይደለም፤ መንጋዎቹን ያሰማራሉ በጎቹን ይጠብቃሉ ጠቦቶቹንም ይሸከማሉ ተብለው በተሾሙት የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች ዙሪያ እንነጋገር ከተባለ ብዙ ጭንቅላትን አሲይዞ ኡ ኡ ኡ... የሚያሰኙ ጉዶች አሉ።

  ነገር ግን እርስ በርሳችን ነውራችንን መገላለጥ ለማን ይጠቅማል፤ መሳለቂያና መዘባበቻ ከመሆን በቀር። ብንችል ፍቅር የኃጢያትን ብዛት ይሸፍናል እንደሚል ቃሉ እርስ በራሳችን ብንሸካከም እንዴት ባማረብን የእግዘብሔር ጸጋም በበዛልን ያም ባይሆንልን፤ የምንሸካከምበትና የሌላውን ድካም ለመሸፈን የሚያስችል መንፈሳዊ ጉልበት ባይኖረን እንኳ ዝም የምንልበት ትግስት አጥተን በዘመናችን በየአደባባዩ የአባቶቻችንንና የወንድሞቻችንን ኃጢያትና ድካም በመግለጽ ወደር የሌለው ፈሪሳዊነታችንን በማሳየት ላይ ነን። ያለ ፍቅር የሆነ ምክርና መገሳሰጽ አንዳች የሚያተርፍልን ነገር የለም፤ እውነተኛ ተሃድሶ ይመጣልን ዘንድ በእንባ በፆምና በጸሎት እግዘብሔርን ልንማጸነው ያስፈልገናል፤ መጽሀፍ እንደሚል የሰው ቁጣ የእግዘብሔርን ጽድቅ አይሰራምና። እርስ በርሳችን በፍቅር እንተያይ፤ ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት፣ ቅድስት ናት፤ የክርስቶስ አካል ናት፤ ቤተ ክርስቲያን ዘላለማዊ ናት፣ የገሃነም ደጆች ያናውጧት ዘንድ አይችሉም!!!
  ሠላም! ሻሎም!

  ReplyDelete
 5. ፍቅር፦ ጥሩ ሚዛናዊ የሆነ አስተያየት ነው። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደዚህ አይነቱ መዝረክረክ በቤተ ክርስቲያናችን አባቶች የሚፈታ ቢሆን እጅግ የተመረጠ ነበር። ነገር ግን ሁላችንም እንደምናውቀው ለብዙ ሞቶ አመታት ቋንቋችንን በማይረዱ የግብጽ ጳጳሳት ስንመራ ቆይተን የራሳችን የአባቶች ጉባኤ (ሲኖዶስ) ከመሰረትን እነሆ ወደ 50 ዓመት ያህል ነው። በርግጥ 50 ዓመት ብዙ ነው ግን ሲኖዶሳችን በአስተዳደርና በመንፈሳዊ ርቀት ብዙም አላደገም ስለዚህ የቤተክርስቲያን ልጆችን እያባሉ ያሉ ችግሮችን የመፍታት አቅም አለው ብየ አላምንም። የማህበረ ቅዱሳንም በማያገባው ውስጥ ገብቶ ምርጥ የቤተ ክርስቲያን ልጆችን በመጽሔቱና በጋዜጣው ስም እያጠፋ ሲቻልም እያስደበደበ ከቤተ ክርስቲያን የሚያባርረው በሲኖዶሳችን ድክመት ምክንያት ነው። ጠንካራ መሪ በሌለበት አገር የጎበዝ አለቆች በየሰፈራቸው የራሳቸውን መንግስት እንደሚያቋቁሙ (ለራሳቸው ህልውና እና ስልጣን ሲሉ) በቤተ ክርስቲያናችንም እንዲሁ እየሆነ ነው ያለው። አባቶች ስራቸውን እየሰሩ ስላይደለ ሁሉም ለቤተ ክርስቲያን ይበጃል የሚለውን ሲሞክር ይሰተዋላል። ውጤቱ ግን እንደሚታየው ብዙም አመርቂ አይደለም። ለማንኛውም አባቶቻችን ጉልበት እና ማስተዋልን አግኝተው ቤተ ክርስቲያናችንን እስኪያስተካክሉ ድረስ በተለያዩ የቤተክርስቲያናችን ጉዳዮች ላይ መወያየቱ መልካም ይመስለኛል። የማህበረ ቅዱሳን አባል ነን በሚሉ ዱርየዎች የቤተክርስቲያናችን ልጆች ሲደበደቡ/ስማቸው ሲጠፋ/ ሲባረሩ ማየትም እጅግ ከባድ ነው። የቤተክርስቲያናችን ገድላት እና ድርሳናት ሁሉ ምንም እንደን የላቸውም ብሎ የሚፎክረው ማህበረ ቅዱሳን ብዙ የቤተክርስቲያን ልጆችን/ማህበሮችን እየበደለና ከባድ ጥፋት እያደረሰ ስለሆነ መከላከል/መምከር ግን የግድ አስፈላጊ ነው። ስንቶች ወንድሞቻችን ተደበደቡ፥ ስንቶችን አጣን፥ ይህ ኢ-ክርስቲያናዊ ድርጊት በውሸት ፕሮፓጋንዳ ሲሆን ዝም ማለት ግን እጅግ ይከብዳል። ለጊዜው እንወያይ፤ ውይይት ጥሩ ልምምድ ነው። በተለይ በቤተክርስቲያናችን ውይይት ብዙም አልተለመደምና እንለማመደው። ጥሩ አስተዳደር እግዚያብሔር ሲያመጣለን ለቤተክርስቲያናችን አስተዳዳሪዎች አመቺ እንሆናለን።

  ReplyDelete
 6. ፍቅር ተዋህዶ
  ደስ ትላላችሁ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካችሁ
  ነገር ግን ፍቅር የወረቀት ነበር ያልሻቸው ተሃድሶዎች ስራ መሰራት የጀመሩት በ14 ክፍለ ዘመን ነበር ነገር ግን በግልጽ መንቀሳቀስ ካቆሙ 10 አመት አልሞላም ስራ አላሰራ ያሏቸው "ማህበረ ቅዱሳን ነን የሚሉት የቅዱሳን መሰረት የተለያቸው ናቸው ሲባል ሰምቻለሁ"። ይሄንንም ያደረጉበት ምክንያት የኤሳወነአ የያዕቆብ እርግጫ እንዳይሆን እንጂ በፍርሃት በይም በመሸነፍ አይደለም ስለ መነጋወ ግድ ስለሚላቸው ጌታ ይፍረደን ብለው ነው ስለዚህ ምንም እነካን ካንቺ የተሻለ ስለ "ማሀበረ ቅዱሳን" እያለ እራሱን ስለሚጠራው ቡድን ባላውቅም ተዋህዶ እንደተናገረው ሰውን በመግደል በማሳደድ በጸረ ወንጌላዊነታቸው አለም ያወቃቸው ናቸው ሰሊዘህ ለሁላችንም ማስተዋል ይስጠን ወንጌል ልባችን ወስጥ ይግባ የተሰቀለውን ኢየሱን እንመልከት።
  ሰላማችን ይብዛ

  ReplyDelete
 7. mr editor,

  Per your editorial policy, insults and name callings are not allowed. However, the guy who posted at "February 9, 2011 9:46 PM" is engaged in name calling. It would be make your blog truely credible if you enofrce your policy. Overall, you attempt to accommodate opposing views in the blog is admirable.

  ReplyDelete
 8. what name did he engaged? please get a life if you have something against the comment say something beside that he have the right to express his feeling or idea and you can do the same beside that ጸጉር መሰንጠቅ ይብቃህ lastAnonymous
  February 10, 23011 2:49pm ምድረ ጨዋ የልባችንን እንዳንናገር በፀረ ሰላም ድህረ ገጻችሁ ላይ ታወናብዳላችሁ አሁን ደሞ እዚህ ሰው መቶ የልቡን ሲናገር ለምን ተናገረ ትላላችሁ በል በነጻነት እንድንኖር ከርስቶስ ነጻ አወጣን ስለዚህ የአባ ሰላማን ድረ ገጽ አምላክ የጠብቅልን ይልባችንን እንደንናገርና እውነትን እንድናነብ።

  ReplyDelete
 9. penten silhok new selamawoch leboch nachihu.seytanoch.bushti.

  ReplyDelete
 10. SORRY ! ALWAYS CRITISISME.YOU HAVE NOT ANY ADVISE ,TEACHING...........

  ReplyDelete
 11. Wow! to the points. outstanding piece of work. I have this mix feeling about Mahebere Kidusan too. There are some good things they do as restoring the Gedamats, taking initiatives to help Abenet Schools yet they think they have the mandate to police churchs. They are the Taliban virsion of ETOC. I will never forget what they did @ Amere Nohe Kidane Mehiret Houston, St. Mary Church, Irving TX. and St. Michael Church Dallas. All these places they made me sick. Should there be any discussion about any issue It should not be MK or Daniel to censor it.

  ReplyDelete