Wednesday, February 16, 2011

የቃል ኪዳኑ ታቦት እና ሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት

ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል እየተባለ የሚነገርለት የቃል ኪዳኑ ታቦት ብዙ ጥያቄዎችን እየፈጠረ ያለ ነገር ነው። በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ሰዓት ታቦት ተብሎ የሚጠራው እግዚአብሔር ለሙሴ ከሰጠው ታቦት ጋር በይዘትም ሆነ በአሠራር ተመሳሳይ ባለመሆኑ የሁለቱንም ልዩነት ይዘት እና አሠራር በማቅረብ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ጉባኤ ወይም እኔ አውቃለሁ የሚል መምህር ሁሉ መልስ እንዲሰጥበት ትክክለኛውን መልስ የማይሰጥ ከሆነ ሕዝብን ከማደናገር እንድንቆጠብ ይህን ለመጻፍ ወደድን።

ቃል ኪዳን የሚባለው አሰርቱ ትእዛዛትን መሠረት አድርጎ በእሥራኤል ሕዝብና በእግዚአብሔር መካከል የተደረገው ውል ነው ዘጸ342728
የቃል ኪዳኑ ቃላት የተጻፉበት ድንጋይ ደግሞ ጽላት እና  ምስክር በመባል ይታወቃል። ዘጸ 32 15 2516 እነዚህ አሥር ቃላት  የተጻፉባቸው ሁለት ድንጋዮች የሚቀመጡበት ሳጥን ታቦት ይባላል።  ታቦት ማለት ማስቀመጫ ፤ ማደሪያ  ማለት ነው። ስለዚህ የቃል ኪዳኑ [የውሉ] ማስቀመጫ ስለሆነ የቃል ኪዳኑ ታቦትተብሎ ይጠራል። ስለታቦት አሠራር ለሙሴ የታዘዘበትን ክፍል ከዘጸአት ም 25 ቁ 10-22 ያለውን ቃል በሙሉ ጠንቅቀን እናንብ፦
ከግራር እንጨትም ታቦትን ይሥሩ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን።
11፤ በውስጥና በውጭም በጥሩ ወርቅ ለብጠው፤ በእርሱም ላይ በዙሪያው የወርቅ አክሊል አድርግለት።
12፤ አራት የወርቅ ቀለበቶችም አድርግለት፥ እነርሱንም በአራቱ እግሮቹ ላይ አኑር፤ በአንድ ወገን ሁለት ቀለበቶች፥ በሌላው ወገን ሁለት ቀለበቶች ይሁኑ።
13፤ መሎጊያዎችንም ከግራር እንጨት ሥራ፥ በወርቅም ለብጣቸው።
14፤ ለታቦቱ መሸከሚያ በታቦቱ ጐን ባሉት ቀለበቶች መሎጊያዎቹን አግባ።
15፤ መሎጊያዎቹም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ ይኑሩ፥ ከቶም አይውጡ።
16፤ በታቦቱም ውስጥ እኔ የምሰጥህን ምስክር ታስቀምጣለህ።
17፤ ከጥሩ ወርቅም ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ሥራ።
18፤ ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፥ በስርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ።
19፤ ከስርየት መክደኛውም ጋር አንዱን ኪሩብ በአንድ ወገን፥ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው ወገን አድርገህ በአንድ ላይ ትሠራዋለህ።
20፤ ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘረጋሉ፥ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፥ ፊታቸውም እርስ በርሱ ይተያያል፤ የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ ስርየት መክደኛው ይመለከታሉ።
21፤ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ፤ እኔም የምሰጥህን ምስክር በታቦቱ ውስጥ ታኖረዋለህ።
22፤ በዚያም ከአንተ ጋር እገናኛለሁ፤ የእስራኤልንም ልጆች ታዝዝ ዘንድ የምሰጥህን ነገር ሁሉ፥ በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለት ኪሩቤል መካከል፥ በስርየት መክደኛውም ላይ ሆኜ እነጋገርሃለሁ።

የታቦት አሠራር

ስለ ታቦት አሠራር ምን መምሰል እንዳለበት እግዚአብሐር ለሙሴ አዝዞታል  ሙሴም እግዚአብሐር እንዳዘዘው  አድርጎ ሳይቀንስ ሳይጨምር ሰርቶታል ዘጸ ም 402. የእግዚአብሐር ትዛዝ አይመችም አይባልም።


ስለዚህ ዘጸ 25 ቁ 10-22 ላይ በተጻፈው መሠረት ታቦት ምን እንደሚመስል እንመልከት (ከላይ ያሉ ምስሎችም ይገልጹታል)።አሁን በኢትዮጵያ ከሚገኘው ታቦት ጋር ፈጽሞ እንደማይመሳሰልም እናስተውላለን።1 ከግራር እንጨት ይሠራል
2 ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል ነው
3 ቁመቱ አንድ ክንድ ተኩል
4 ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል
5 በውስጥና በውጭ በወርቅ  የተለበጠ  ነው
6 ዙሪያውን የወርቅ አክሊል  አለው
7 በአራቱ እግሮቹ ላይ የወርቅ ቀለበቶች አሉበት
8 በወርቅ የተለበጡ ሁለት መሎጊያዎች በቀለበቶች ውስጥ ይገባሉ።
9 መሸከሚያወቹ ከታቦቱ ጎን ምንጊዜም አይወጡም
10 የታቦቱ ግጥም የሥርየት መክደኛ ይባላል በርዝመት፤ በቁመት፤ በወርድ ከታቦቱ ጋር እኩል ነው 
11 በሥርየት መክደኛው ላይ ሁለት ኪሩቤል ይቀመጣሉ የነርሱ አሠራር እና አቀማመጥም እንደሚከተለው ነው
12 ከወርቅ የተሠሩ ናቸው
13 በጎንና በጎን ሆነው  ፊት ለፊት ይተያያሉ
14 ክንፎቻቸው ወደላይ የተዘረጉ ናቸው
15 በክንፎቻቸው  የሥርየት መክደኛውን ይሸፍናሉ

16 አይኖቻቸው ወደ  ሥርየት መክደኛው ይመለከታል
17 ታቦቱን መሸከም የሚቻለው በትክሻ ብቻ ነው
18 ታቦቱ ትልቅ እና ሰፊ በመሆኑ አራት ሰዎች ይሸከሙታል 2ዜና ም 15 15

19 ታቦቱ የሚቀመጠው ሦስት ክፍል በነበረው ድንኳን ወይም ቤተመቅደስ ባንደኛው ክፍል ውስጥ ነበር ዕብ 94
20 በጦርነት ጊዜ ወደ ጦር ሜዳ ይወሰድ ነበር 1ሳሙ 44
21 ሙሴ የሠራው  ታቦት አንድ ብቻ  ነበር

አሁን በኢትዮጵያ የሚገኙ ታቦቶች አሠራር

በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ስለሚገኘው ታቦት ስለ አሠራሩ የታዘዘና በመጽሐፍ የታጸፈ ነገር ለማግኘት ሞክረን አላገኘንም ከድርሳናትም ሆነ ከሌላ መጽሐፍ አሁን ስላለው ታቦት አሠራር የታዘዘ ነገር የለም።

ከድንጋይ ከእብነ በረድ፣ ከወርቅ፣ ከእንጨት ከዋንዛ ከዝግባ ከወይራ ወዘተ... ይሠራል። ምስሉን ከላይ ይመልከቱ


1 ቁመቱ- ልክ የለውም [እንደ እንጨቱ ሁኔታ የሚሠራ ነው]
2 ወርዱ- ልክ የለውም
3 ርዝመቱ - ልክ የለውም
4 በውስጥ እና በውጭ በወርቅ የተለበጠ አይደለም ለነዚህ ሁሉ ታቦቶች የሚበቃ ወርቅ አይገኝም።
 5 ዘሪያውን አክሊል የለውም
6 የታቦቱ መሸከሚያ ቀለበትና መሎጊያ የለውም
7 የሥርየት መክደኛ የለውም
8 የኪሩቤል ቅርጽ የለውም።
9 ብዛቱ ልክ የለውም በየቤተ ክርስቲያኑ ከአራት በላይ ታቦት ይገኛል።
10 የሥላሴ ስእልና የባለ ታቦቱ ስእል ማለትም የጊዮርጊስ፣ የአቡየ፣የተክልየ፣ የሚካኤል ወዘተ ስእል አለበት አንዳዱ ታቦት የመስቀል ቅርጽ ብቻ ይገኝበታል።
11 ዙሪያውን የሐረግ ጥልፍ ይደረግለታል።
12 የቀበሌው[ያገሩ] እና የቄሰ ገበዙ ስም እንዲሁም ያገረ ገዡ ስም ተጽፎበታል።
13 በጨርቅ የተሸፈነ ነው ከቄስ በቀር ማንም አያየውም

የኢትዮጵያው ታቦት ለሙሴ ከተሰጠው ታቦት ጋር ፈጽሞ አይመሳሰልም


14 የባለ ታቦቱ በአል ወይም ጥምቀት ሲሆን ካህናቱ በራሳቸው ተሸክመውት ቤተ ክርስቲያኑን ሦስት ጊዜ ይዞሩታል።
15 ባለሙያ የሆነ ሁሉ ሊሠራው ይችላል።
16 ብዙ ጊዜ ሌባ እየወሰደው በአውሮፓ ሙዝየሞች ይገኛል። 

ይህ የኢትዮጵያው ታቦት በእግዚአብሔር ያልታዘዘ ከሆነ ከየት የመጣ ነው? ለሚለው ጥያቄ ነገሩን ከማድበስበስ በቀር ትክክለኛ መልስ መስጠት አልተቻለም።  አንዳድ ሰባኪዎች በጭፍን የሚያስተምሩት ትምህርት እግር እና እጅ የሌለው ባዶ ማደናገሪያ ነው። የቃል ኪዳኑ ታቦት እየወጣ ነው እልል በሉ ሲሉ ሕዝብ ሁሉ ይስገዳል ግን የየትኛው ቃል ኪዳን ታቦት ነው? ለሚለው ጥያቄ መልስ የለም? የብሉይ ኪዳን ነው ብለን እንዳንመልስ ከብሉይ ኪዳኑ ታቦት ጋር በምንም አይገናኝም፤ የሐዲስ ኪዳን ነው ብለን እንዳንመልስ ስለ አሠራሩ ስለብዛቱ በማን ስም መሆን እንዳለበት በየኛውም መጽሐፍ ላይ ተጽፎ አናገኝም። የሐዲስ ኪዳኑ መካከለኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን እግዚአብሔርም በዚያ በኩል ተናግሯል ምንም መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ የለም ነገሩ እንቆቅልሽ ነው።


ታቦት በየአይነቱ


 
  
ትክክለኛው ታቦት የትኛው ነው?

ሁሉም ታቦቶች እኩል አይደሉም ለምን? እግዚአብሔር እንዲህ እንዲሠራ አዟል? የት ይገኛል? በየትኛው መጽሐፍ? ምራፉና ቁጥሩ ይነገረን።

አንዳዶች ቄሶች አሁን ታቦት ብለው የሚሸከሙት ጽላት እንጂ ታቦት አይደለም።

የጽላቱን አሠራር ደግሞ ከዘጸ ም 32 ቁ 15-16 እንመልከት
ሙሴም ተመለሰ፥ ሁለቱንም የምስክር ጽላቶች በእጁ ይዞ ከተራራው ወረደ፤ ጽላቶቹም በዚህና በዚያ በሁለት ወገን ተጽፎባቸው ነበር።
16፤ ጽላቶቹም የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ፤ ጽሕፈቱም በጽላቶች ላይ የተቀረጸባቸው የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበረ
1 ጽላቶቹ የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ
2 ጽላቶቹ ሁለት ብቻ ነበሩ
3 ጽላቶቹ በዚህ እና በዚያ የተጻፈባቸው ነበሩ
4 ጽሕፈቱ የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበረ
ሆኖም እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ጽላቶች እስራኤል ጣኦት ሲያመልኩ በመገኘታቸው ሙሴ ተቆጥቶ ወርውሮ ሰበረው። በኋላ ግን እንደፊተኞቹ አድርጎ እንዲጠርብ ታዘዘና ጠረበ እግዚአብሔርም አሠርቱ ትእዛዛትን ጻፈለት።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው። ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እንደ ፊተኞች አድርገህ ጥረብ፤ በሰበርኻቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ ዘጸ ም 34 ቁ 1
1 ጽላቶቹ የድንጋይ ነበሩ
2 ልክ እንደፊቶኞች ነበሩ
3 የፊተኞቹ ቃላት ተጽፈውባቸው ነበር
4 እነዚህ ቃላት አሠርቱ ትእዛዛት ናቸው ዘጸ ም 34 ቁ 27
5 የሰውም ሆነ የቀበሌ ስም የሰው ምስልም የለባቸውም
6 በማንኛውም ቅዱስ ስም አልተሰየሙም
7 በታቦቱ ውስጥ ይቀመጣሉ።
8 ከታቦቱ ውስጥ ፈጽሞ አይወጡም

አሁን በኢትዮጵያ የሚገኘው ጽላት አሠራር

1 ከማንኛውም እንጨት የተሠራ ነው፤ አንዳዱ ከድንጋይ ተሠርቷል
2 አሠርቱ ትእዛዛት አልተጻፈባቸውም፤ የቄሰ ገበዙ እና የባላባቶች ስም ተጽፎበታል።
3 ብዛታቸው ሁለት ብቻ አይደለም በመቶ ሺህ የሚቆጠር ነው።
4 የሰው ወይም የመላእክ እንዲሁም የሥላሴ ምስል አለበት
5 ጽላቱን የሚሸከሙት በታቦቱ ውስጥ ሳይሆን በጭንቅላታቸው ነው
6 ዙሪያውን ሐረግ አለው ብዙ ሌላም ነገር አለው

ስለዚህ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲቀርጽ ካዘዘው ጋር ፈጽሞ አይመሳሰልም። በብዛት በዓይነት በአሠራር አይገናኝም። የሙሴ ጽላት ሁለት ብቻ ከነበሩ ይህ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ጽላት ከምን የተገኘ ነው? ሕግም አልተጻፈበትም ቢጻፍበትም እንኳ ጌታ ሕጌን በልባቸው እጽፈዋለሁ ስላለ የጌታን ቃል አይቃወምም? ኤር ም 31 ቁ 31-35። ይህ ነገር እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ከሆነ ጽላትም አይደለም ታቦትም አይደለም። ታዲያ ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ አንዳድ አባቶች ሲመልሱ በአንድ አካባቢ ቤተ ክርስቲያን ለመትከል የተፈቀደ መሆኑን ለማረጋገጥ ለአካባቢው የተሰጠ የምስክር ወረቀት ነው ታቦት ወይም ጽላት መባሉ ግን ለኛም ግልጽ አይደለም ይላሉ። እናም በሁኔታው እያዘኑ እየተከዙ የሚኖሩ አባቶች እጅግ ብዙ ናቸው።
  
ዛሬ የቃል ኪዳኑ ታቦት የት ይገኛል?

ይህ የቃል ኪዳኑ ታቦት በቀዳማዊ ምኒልክ በሰሎሞን ዘመነ መንግሥት ተሰርቆ ወደ ኢትዮጵያ ምጥቶ በአክሱም ይገኛል ይባላል።
ይህን ታሪክ ተጽፎ የምናገኘው
    1 በክብረ ነገሥት መጽሐፍ
    2 በገድለ ተክለ ሃይማኖት
   3  በድርሳነ ኡራኤል ነው።
በመጽሐፍ ቅዱስ የምናገኘው ታሪክ ግን ወደ ባቢሎን ተወሰደ የሚል ነው
 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሃስቦች በግዚአብሔር ቃል ያጢኑ።
ቅዱሱን ታቦት የእሥራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን  ባሠራው  ቤት ውስጥ አኑሩት ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም2ዜና ም353 ኢዮስያስ ለሰሎሞን አሥራ ስድስተኛ ንጉስ ነበር ። ከኢዮስያስ በፊት ነግሶ የነበረው ምናሴ  የቤተ መቅደሱን ዕቃ አውጥቶ  በውስጡ ጣኦት አስቀምጦበት ነበር  2ዜና ም 338 በዚህ ምክንያት ካህናቱ ታቦቱን ተሸክመው በየቤታቸው  ይዞሩ ነበር። ኢዮስያስ ምናሴ የተከለውን የጣኦት ምስል ያፈራረሰና ታቦቱ ወደ ቤተ መቅደስ እንዲመለስ ያደረገ ንጉሥ ነው። ከንግዲህ ወዲህ በትክሻችሁ ሸክም አይሁንባችሁ ያለው በዚህ ምክንያት ነው። የባቢሎን ምርኮ ከኢዮስያስ ዘመን በኃላ ተጀምሮ በሴዴቅያስ ዘመን ተፈጽሟል። በባቢሎን የምርኮ ዘመን የነበረው ነቢይ ኤርምያስ ነበር። ኤር ም 1 ቁ 1-5። 2ዜና ም 3611-23 በራሱ መጽሐፍም እንዲህ ብሎአል የግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ብለው ከንግዲህ ወዲህ አይጠሩም ልብ አያደርጉትም አያስቡትምም አይሹትምም ከንግዲህ ወዲህም አይደረግምም ኤር ም 316። ኤርምያስ ከኢዮስያስ ጀምሮ እስከ ባቢቢሎን ምርኮ እስከ ሴዴቅያስ የነበረ ነቢይ ነው  ኤር ም 11-3 ያንቡ።
      ታቦቱ በሴዲቅያስ ዘመን ወደ ባቢሎን እንደተወሰደ የሚናገረው  የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሚከተለው ነው።

እግዚአብሔርን የሚያገለግሉበትን ንዋየ ቅድሳቱን ጥቃቅኑን እና ታላቁን ዕቃ ሁሉ የግዚአብሔር ማደሪያ ታቦትንም ከቤተ መንግሥት እቃ ቤትም ያለውን ሳጥኑንም ሁሉ ማርከው ወደ ባቢሎን ወሰዱ እዝራ ካልእ ም 154

ቤተ መቅደሳችን እንደፈረሰ አታይምን ግናይቱ እንደጠፋ ምስጋናችን እንደቀረ ዘመራ ዘውዳችን እንደወደቀ ተድላ ደስታችን እንደጠፋ የሕጋችን ማደሪያ ታቦተ ጽዮን እንደተማረከች አታይምን? እዝራ ሱቱ ም 923

ከዚህ ሁሉ የሚበልጥ ታቦተ ጽዮን እንደጠፋች ቀረች ከሳ ጋርም ንዋየ ቅድሳቱ ተማርኮ ሄደ በጠላቶቻችን በባቢሎናውያን እጅ ወደቅን እዝራ ሱቱ ም 923

ከዚህ ትምህርት እንደምንረዳው  መጽሐፍ ቅዱሱና ክብረ ነገሥቱ፣ ገ/ተክለ ሃይማኖት፣ ድርሳነ ኡራኤል አለመስማማታቸውን ነው።  ምክንያቱም  ሦስቱ መጻህፍት በሰሎሞን ጊዜ ታቦቱ ተሰርቆ መጥቷል ሲሉ  መጽሐፍ ቅዱስ ግን ወደባቢሎን ተማርኳል ይላል። ሶሎሞን ለእስራኤል ሦስተኛ ንጉስ ሲሆን ሴዴቅያስ ግን 21ኛ ንጉስ ነው። በሶሎሞን ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ተሠርቆ የመጣው ታቦት በሴዴቅያስ ጊዜ እንዴት ወደ ባቢሎን ሊሄድ ቻለ? ከኢትዮጵያ ነው የሄደው ወይስ ከኢየሩሳሌም ? ከሶሎሞን እስከ ሴዴቅያስ የ350 ዓመት ልዩነት መኖሩን ስናስተውል ደግሞ የክብረ ነገሥትን ውሸት በጣም ያጋልጠዋል በጣም ያሳፍራል።
ለምን እንዋሻለን? ማፈሪያችን ብዛቱ? መጽሐፍ ቅዱሱ ነው ትክክለኛው ወይስ ክብረ ነገሥት?
የክብረ ነገሥት ደራሲ ይህን ልብ ወለድ ታሪክ ለምን መጻፍ እንዳስፈለገው ብናጠና ሰሎሞናዊ ነው የሚባለውን ስርወ መንግሥት ለማስፋፋት የታለመ ፖለቲካ መሆኑን በሰፊው አሳያችኋለሁ። ታቦቱ በአገራችን ቢኖር እሰየው፤ የታላቅ ቅርስ ባለቤቶች ያደርገናል ባይኖር ግን የሐዲስ ኪዳንን መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስን ተቀብለናልና የብሉይ ኪዳኑ ታቦት አስፈላጊያችን አይደለም። እንኳንስ ለእኛ ለእሥራኤልም አስፈላጊያቸው እንዳልሆነ ኤርምያስ ተናግሯል ኤር ም 3 ቁ 16። ታዲያ በሌላ ሕዝብ ታሪክ ይህን ያህል መታበይ ከትዝብት ላይ የሚጥል ነው።  

ማህበረ ቅዱሳን ያሳተመው ታቦተ ጽዮንን ፍለጋየሚለው መጽሐፍ ግን ታቦቱ በሰሎሞን ጊዜ ሳይሆን  በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ወደ ግብጽ በተሰደዱ ካህናተ ኦሪት  ለዘመናት ግብጽ ቆይቷል ከዚያም ስደት ሲበዛባቸው ወደ ሱዳን ይዘውት እንደ መጡ ከሱዳን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ይዘውት እንደገቡ ይተርካል። በጣና ቂርቆስ 800 መቶ አመት ያህል ቆይቶ  የአክሱም ነገሥታት  ከአይሁድ ቀምተው  እንደወሰዱትና በአክሱም እንዳስቀመጡት እንዲሁም  በዮዲት ጦርነት ጊዜ ወደ ዝዋይ ተወስዶ ቆይቶ ዮዲት ከተሸነፈች በኋላ ወደ አክሱም ተመልሶ  አሁንም በዚያ እንደሚገኝ መጽሐፉ ይተርካል።
ይህ ትረካ ትንሽ እውነት ይመስላል። ሆኖም በሥራ ላይ እስካልዋለ ድረስ  የሚያኮራና የሚያስታብይ ነገር አይደለም። አሁን በኢትዮጵያ አለ ብንል እንኳ እስከ እለተ ምጽአት ድረስ ቆይቶ ከሰማይ እና ከምድር ጋር በዚያው ሳናየው ይወገዳል እንጅ ምንም አይጠቅመንም።

Mekonen Abera, Addis Ababa

27 comments:

 1. gud fela! I think most eotc members have a wrong view of "tabot". we can't blame the members because that's how the priests want us to view it. well, we might as well call the current tabot something else because there are no similarities at all. The Catholics use a table, the Copts use something else for the communion during liturgy. So our tabot tradition is kind of uneccessary. Very interesting stuff.

  ReplyDelete
 2. No one cares how it came to the country. What we believe is we have it in our custody. The world has confirmed it; the church has confirmed it; and the priests guardig it has confirmed it.

  I don't have any reason to doubt it. Doing so does not add any value either.

  The writer needs to understand the difference bewteen Tabot and Tselat:

  1. Tabot is the case used for carrying the Tselat. The ones you showed a being the true taot are the tabots; When you open the tabot, you get the tselat.
  2. The one you have shown with the cross is the Tselat.

  Over the years, the Tselat has taken on the name of the Tabot, vice versa. Nothing wrong with that.

  You are wrong when you say the Tsion Tabot has no value. We go there and get blessed.

  Don't forget that our fathers won the battle of Adwa carrying the Tabot with them and praying, in addition to fierce fighting.

  Unfortunately, some people tend to despise their own tradition and aspire that of the white people or outsiders.

  When are we going to appreciate ours? What proble the Tabot created other than blessing us and serving as plate to sacrfice the blood and flesh of Christ.

  Yes, the new testament Tabot is different. We put the cross and His Holy Name on it.

  Will continue.

  ReplyDelete
 3. John, እየቀለድህ ነው? ጽሑፉን አንብበኸዋል ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው? Who and where does it say the new testament tabot should be this way or that way? ከየት እንደመጣብን የማይታወቅ አጉል ባህል ነው። ታቦት ሲወጣ (ለጥምቀት etc_) ካልደመቀ አይንቀሳቀስም ሲባል ሰምተህ አታውቅም። ድራማ እኮ ነው እየተሰራ ያለው። ለምንድን ነው ተሸክመነው የምንወጣው? ከየት ያመጣነው ልማድ ነው? ለስጋና ደሙ ማዘጋጃ ተብሎ መቅደስ ቢቀመጥ ጥሩ፤ የምናየው ነገር ግን ከዛ ያለፈ ነው። ተሸክመነው እንወጣለን፤ አትጠጉት ይባላል፤ ይሰገድለታል፤ "አስርቱ ትዕዛዛት የተፃፉት ጽላት ዘሙሴ ጽላት" እያልን እንዘምርለታለን። አሁን አስርቱ ትዕዛዛት አይጻፍበትም፤ የሙሴም ጽላት አይደለም እያልን የምናካሂደው ስርዓት ግን የብሉይ ኪዳኑን ነው። ብቻ መላ ቅጡ ጠፍቶብናል።

  ReplyDelete
 4. Orthdox,

  Yes, we are different from all the rest of Christians in that we accepted christianity not from paganism, but from Judaism. Therefore, we have kept some elements of the old testament that don't contradict Christianity.

  Did not the Israelis sing and bow for the Tselat/Tabot according to the Bible? They did...
  The new testament Tabot/Tselat does not deserve a lesser respect. Guys, we should even value and apprecaite our unique Christian tradition...

  Our forefathers followed the instruction God gave to Moses to inscribe a tabot/tselat and modifed it to reflect the Christian faith. I think the source is the Bible itself, nothing else. I think it is not wise to wage war against our own history and tradition (assuming you are one of us), which in this case is a good one.

  We should rather fight ignorance, rebellion on the word of God, poverty, backwardness, superstition etc... For example, local Ethiopia is so ignorant and supersitious, but I am not seeing any one proposing an idea to fight this. Also, the Gospel has not reached well in Ethiopia even in the stronghold of EOTC, but no one is working on that. The local Amhara and Tigre peasantry are taken for granted, and EOTC has not made any effort to spread the Gospel in those areas.

  If you are genuine Orthodox Chrisitians, we have a lot more serious problems. We hould focus on those than engaging on hair spliting and questioning good traditions. We should be proud of this unique tradition, and work hard to revive christianity in our country like it was in those good old days.

  God bless.

  ReplyDelete
 5. yene geta, I think you should invest some time trying to understand the two testaments (Old and New). Based on your comments above, you don't seem to understand those distinctions. The point the writter is trying to make is that we are mixing it up. While the tabot in the new and old testament are completely different, the church treats it almost the same. This is confusing. If it is just a tradition, the church needs to make that clear. But it is usually presented as a Dogma that can not be changed etc. As I have said it above, we even sing as if it is the tabot from the old testament.

  ReplyDelete
 6. Orthodox,

  Are you an orthodox christian? Did you read what I wrote? It appears you did not.

  Why do we need to change the tradition? As far as we believe that it is from God, what is wrong with respecting the Tabot? Afterall, it is His name that is written on the tabot/tselat. We are singing for His name or the name of saint for whose name the tabot has been dedicated (just for rememberance).

  Of course, the tabot is not a means to reach God. That has been replaced by Christ. Of course, we are all His Tabot. However, he never removed the Holy things from the temple when He was chasing the business people and removing their stuff when He visited the temple.

  Again, we have come from a Judaic tradition and should not be expected to be like the ones who came from paganism. It is a privilege for us to have that tradition. We are not worshiping the tabot! The tabot is not a dogma either! It is a good Judaic tradition that we happen to have because of our background.

  It is better to focus on more value-adding issues than attacking a tradition that we inheirted from God Himself. All those things that are not in line with the Christian faith were removed 2000 thousand years ago.

  ReplyDelete
 7. Yes, I am an orthodox christian and my question is also the question the writter raised. The tabot in the old testament has clear specifications as to how it should be built and handled. But the tabot we use in our church has no specifications. Does anyone know where those specifications are located?

  የታቦት ሥርዓት አልተሻረም አሁንም እግዚአብሔር በታቦቱ ላይ እየተገለጠ ብቻ ነው የሚገኛኘን የሚል እምነት እንደሌለን ግልጽ ነው። የብሉይ ኪዳን የታቦት አገልግሎት ተሽሮአል። በብሉይ ኪዳን የበግ፤ የላም፣ መስዋእት በክርስቶስ ተተክቶ እንደቀረ ሁሉ የታቦቱም አገልግሎት እንዲሁ ቀርቶአል። አሁን የበግ የላም መስዋእት አናቀርብም። ለምን? አንድ ጊዜ በቀራንዮ የተሰዋልን የዘለዓለም መስዋዕት ኢየሱስ ክርስቶስ አለንና። የታቦትም አገልግሎት ተሽሮአል። ለምን? በዛች በአንዲትዋ ቤተ መቅደስ በታቦቱ ላይ ብቻ እየተገለጠ የሚገኛኘን አምላክ አሁን በውስጣችን አደረ፤ መጋረጃው ተቀደደ። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችን ታቦት ብላ የምትጠራው ነገር ያ የብሉይ ኪዳኑን ታቦት አይደለም። ጸሐፊው እንዳለው አሁን ታቦት የምንለው በየትኛውም መስፈርት ተመሳሳይነት የለውም።

  1) አይሁዶች ታቦታትን እያባዙ በየ ምኩራባቸው አላስቀመጡም። የነበራቸው ታቦት አንድ ብቻ ነው። እኛ ግን በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ታቦታትን አባዝተን እንጠቀማለን። ታዲያ ይህ ባህል ከየት መጣ?

  2) የአይሁድ ታቦት እንዴት መሰራት እንዳለበት ታዘው ቁመቱ፤ ርዝመቱ፤ የተሰራበት ቁስ፤ ታውቆ ያንን ተከትለው ሰርተው ተጠቅመዋል። የኛ ታቦታት ግን ምንም መስፈርት የላቸውም። በዘፈቀደ ይሰራሉ። ይህ ከየት መጣ? የተጻፈ ነገር አለ?

  3) የብሉይ ኪዳን የታቦት አገልግሎት የተሻረ ከሆነ ለምንድን ነው አሁን ተሸክመነው የምንወጣው፤ ቤተ ክርስቲያን የምንዞረው? ምን ለማድረግ ነው? ምን ማለት ነው? ግራው የተጋባ ነገር ነው። ባህል የመጥላት ሳይሆን አልገባኝም! መቼስ አልገባኝም ግልጽ ይደረግልኝ ማለት ኃጢዓት እየሆነ መጥቶአል።

  4) አሁን በአዲስ ኪዳን የታቦት አገልግሎት ምንድን ነው? ስጋና ደሙን ማቅረቢያ/መፈተቻ ነው? እንደዚያ ከሆነ ለምንድን ነው ሌላ ሌላ ነገር የምናደርገው? የብሉይ ኪዳን የሆኑ ነገሮችን ስናደርግ እንስተዋላለን። ለምሳሌ ታቦት ሲወጣ ጽላት ዘሙሴ ጽላት እያልን እንዘምራለን። እያችሁ እንዴት እንደምናደበላልቀው? አልገባኝም።

  ReplyDelete
 8. Orthodox,

  I am not the right person to answer all those questions; I am an ordinary bleiever. However, I don't have problem respecting the Tabot, which bears the name of Christ, as much as I respect the Cross and the Icons. In addition, it is a special plate on whihc the Priest sacrifices the blood and flesh of Christ.

  I have been to Coptic and Catholic churches, and have seen the priests kissing and respecting the sheet/table that they use for same purpose mentioned above.

  My answers to some of your questions are:

  1. I think the Church Canoon (kenona)suggests that we use the tabot for the liturgy and as a eat for the acrifice. You cannot find ome of the kenona laws/rules in the bible. For example, similar to the fasting kenona. Every ancient church has its own kenona.

  2. The source is the bible primarily; the TWIFTAWI tradition secondly. The kenona may have something to say.

  3. It is good to ask; I don't condemn people when they ask. Otherwise, we cannot learn. My anwer to the question is - because it bears the name of Christ and the old testament tabot has been modified to serve the new testament. The procesion is a tradition of celebrating certian holidays. Moreover, the spiritual root is the old testament wherebuy the Isrealis did a procession of the Jarico wall, which fell apart when they finished the procession. We hope our enemy falls apart when we praise God and celebrate the holiday in the procesion. I want to remind you that it is only some of the old testament traditions that have been altered in the new testament. There are a lot of traditions that you can keep even it it is not mandatory to do so. Basically, the new testament has done the following: (a) completely changed or replaced some aspect of it (ex the sacrifice), (b) kept or tightened some others (example the ten commandments), and (c) left still some others optional (ex the circumcission - spiritually replaced by baptim, but you can still continue to be circumcised), etc...

  4) We are singing for the spiritual tselat and the name Christ Jesus. That song is simply mentioning the root source of the tselat. Well, coming from a judaic background, some reflection of that tradition should be expected. At the end of the day, it is not an offence against God; all the singing and praising is for the Holy name of Jesus Christ. Even when we praise the saints, we are prising Christ as the saints bear the name of Jesus Christ. We do that with that spirit and belief.

  Sorry if my answer is not comprehensive enough. I refer you to Aba WoldeTensae of the LA(original) if you live in the US or Australia. He can better explain it... If I get hold of him, I will ask and get back to you. Appreciate your interest to learn.

  ReplyDelete
 9. Thanks John,

  I agree that 'Kenonas" don't have to be in the Bible, but they have to be documented somewhere. As you have mentioned, "Kenona" related to fasting has been written in several of our church books, but I have yet to find any book that describes how the new testament tabot should be built and should be used. That is the point the writter is trying to make too. Since there aren't clear directions, we are now trying to describe what we think it is. I think I have heard a recording where Aba Woldetensae explain it. I think the explanation was reasonable, but he never explains where the specifications of the current tabot came from. I am sure a lot of people have problems with Aba's explanation too. Because most of our people understand tabot as being the same as the old testament tabot.

  God bless you!

  ReplyDelete
 10. Orthodox,

  Hope you have read the article on Tabot and Tselat. I believe it answers some of your questions.

  ReplyDelete
 11. John, I actually liked the article. Who ever wrote it (It sounds like it was extracted from Aba Woldetensae's sermons)at least tries to make sense out of it. It defends the church in a smart way. ህግና ነብያትን ልሽር አልመጣሁም ስላለ አሁንም ታቦት አለ ብለው ከሚከራከሩት ጭፍኖች ይሄ በ 1000 እጥፍ ይሻላል። Not entirely satisfied, but I can live with the explanation provided. What will surprise you is that most of our members (including people who serve in the church) wouldn't agree the article. The way the article expains it, we might as well call it something else. Because it has no similarities with the old testament tabot. Not even a single commonality. What is interesting is that our forefathers could have decided to use something else for communion preparation instead of the "tabot".

  ReplyDelete
 12. John, I actually liked the article. It makes more sense than what most people try to explain. Whoever wrote it (sounds like it was extracted from Aba Woldetensae's sermons) defends the church in a smart way. ሕግን እና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ስላለ በቃ ታቦትም አልተሻረም ለዚህ ነው ብለክ ከሚከራከሩ አላዋቂዎች በ 1000 እጥር ይሻላል። I am not completely satisfied with the answers presented in the article, but it is something I can live with. To your surprise, mose people (including church and sunday school leaders) wouldn't agree with the concept in the article. The reason is that the widely accepted understanding of the new testament tabot is that is is the same as the old testament's. According to the article, we might as well call it someting else because it has no similarities with the old testament tabot. not even a single commonality! Sounds like the people who established the new testament tabot "konona" had a choice to use something else instead. Do you think everyone is in agreement that the new testament "tabot" we use is simply a "kenona" that we use and the Synod can make changees to it if neccessary? My position is that the "tabot" created more confusion and wrong perceptions among our members than the intended benefit.

  ReplyDelete
 13. Ezra 2 goes like this:

  And they took all the holy vessels of the Lord, both great and small, with the vessels of the ark of God, and the king's treasures, and carried them away into Babylon [1:54]

  The vessels of the Ark of God is not the same as the Ark of God. Ezra is not only consistent with the Kibre Negest and other holy books, but also instructive of the fact that it was absent in the temple of Solomon prior to the Babylonian conquest.

  The New Covenant Tabotat that are in every Tewahdo Church are new testament Tabotat and has a lot to do with Getachin Medahnitachin Eyesus Kristos and the Blessed Virgin Mary. Ill intentioned questions why the new covenant Tabot does not have the physical dimensions of Tslate Mussie are not appropriate, because they lack the humility for the Menfesawi Mistir the Tabot bears. Question is, is divulging the Menfesawi mistir to reproachful, rebellious provocations appropriate?

  ReplyDelete
 14. I think the EOTC better come up with a clear explanation about how the tabots we have came to use and Why it is revered. Otherwise, the church is in danger of losing members. Times have changed and the young generation needs explanation. I am sure there is a reason for using tabot in every church. It is just that the Church should put it in the kenona and make it offical

  ReplyDelete
 15. Dear Writer,

  1- It be clearly seen from you distortion that you didn't have a clear understanding of the issue including the aim and effect as well as respect of the ark of the convenient both in the old and the new testament

  2- an lets give you an example - First read the following verse from the new testament

  "THEN THE TEMPLE OF GOD IS OPENED IN HEAVEN , AND THE ARC OF HIS COVENANT WAS SEEN IN HIS TEMPLE. AND THERE WERE LIGHTNINGS ,NOISES , THUNDERING ,AN EARTHQUAKE AND GREAT HAIL" REV 11;19

  2-1=where is this arc of the covenant came from, is it from Babylon?

  2-2=why do you think st John with the will and power of God wanted him to write it on the new testament?

  3- Do you accept the ark of he covenant if it is done in t he way Moses was Told to do?

  4-why do you believe is that the covenant is broken in Moses hand ?

  ReplyDelete
 16. you guys you don't want to publish ideas if they are not in favor of your idea or if they are challenging to you , It means you lied when you said you tolerate different ideas. You are just writing but not willing to listen. It seems that The whole purpose of this site as i understand it is to inject poison into those who doesn't have adequate understanding of the Holy bible, not to have clear discussion on concrete issues.

  Good for you , sooner or later you realize that you are possessed.

  ReplyDelete
 17. you are saying that small cross and big cross are not the same. Yes u are right if u consider only size. But the purpose and function of them are one and the same.

  ReplyDelete
 18. በሐዲስ ኪዳንም ‹‹ድል ለነሣው ስውር መናን እሰጠዋለሁ፤ የብርሃን መጽሐፍንም እሰጠዋለሁ፤ በዚያ መጽሐፍ ውስጥ ላይ ከተቀበለው በቀር ማንም የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎበታል›› ራእ 217፡፡ ለዚህ ስም ደግሞ ጉልበት ሁሉ መንበርከክ እንደሚገባ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፤

  ‹‹ይህም በሰማይና በምድር በቀላያትና ከምድርም በታች ያለ ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሰግድ ዘንድ ነው። አንደበትም ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር አብ ክብር ጌታ እንደሆነ ያምን ዘንድ ነው›› ፊልጵ 2፥10-11፡፡ በዚህ መሠረት ቅዱስ ስሙ በተጻፈበት ከነጭ ድንጋይ (ከዕምነ በረድ፣ከእንጨት) በተሠራው በጽላቱ ፊት ለቅዱስ ስሙ መስገድ ታላቅ የመንፈስ ጥበብ እንጂ ሞኝነት አይደለም፡፡ ምናልባት ስለታቦት፣ ስለጽላት ባለማወቅ ባጠቃቀሙ በኩል የሚሳሳቱ አባቶችን፤ እናቶችን ወንድሞችንና እህቶችን በተገቢው መንገድ ማስተማር ተገቢ ነው፡፡
  http://www.eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_content&view=article&id=443%3A&catid=5%3A-&Itemid=42

  ReplyDelete
 19. Which one is appropriate to believe?The Church or The Bible.Was there a Bible before Church?Or church before the Bible? First identify that.We consider the Bible written by protestants because it does not oppose us at all.If you really in need of knowing the truth, you have to believe the Ethiopian orthodox is so long older than the Bible.Then you give priority to assets of The Church and get rest in your mind.What transferred through history has much power to be believed than those writen,subjected to distortion.God blesses us .

  ReplyDelete
 20. The ethiopian orthodox is the most evil religious empire next to chatolics, infact it is the embassy of the devil here on earth, filled with demonic practicis and lie. Totally against Gods word, idol worshippers.
  This two religions are called in the bible as the "modern day babylon,the prostitute, the harlots,and he will destroy them(revelation,17&18) and they are catagorized with islam as an anti christ (1john,2:18-22)

  ReplyDelete
 21. 1ኛ፡- ታቦት እንደሙሴ ሕግ የሚዘጋጀው ከግራር እንጨት ሆኖ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፤ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ቁመቱም አንድ ተኩል ይሁን ይልና በውስጥና በውጭም በጥሩ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ አክሊል አድርግለት ይላል፡፡ ደግሞም ታቦቱን የሚሸከሙት ከወርቅ በተሠሩ መሎጊያዎች አራት ሰዎች እንደሆኑ እንረዳለን፡፡ በአጠቃላይ የብሉይ ኪዳን የታቦት አሠራር እጅግ ከባድ በመሆኑ በሁሉም ዘንድ አይቻልም ነበር፡፡ ምናልባት አንዳንድ የቤተክርስቲያን ፍቅር የነበራቸው ነገሥታትና ዛሬም ፍቅረ ቤተክርስቲያን ያላቸው አንዳንድ ምዕመናን ይችሉት እንደሆነ ነው እንጂ፡፡

  2ኛ፡- ጽላት፤ ጽላትም እንደሙሴ ሕግ ከሆነ መዘጋጀትና መጠረብ ያለበት ከከበረ ድንጋይ ነው፡፡ በአንድ ታቦት ውስጥም መቀመጥ ያለባቸው ሁለት ጽላቶች ናቸው፡፡ ዘዳ 34፥1፡፡ በአጠቃላይ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሕግና ሥርዐት ከባድ ነው፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ሥርዐትም ለሐዲስ ኪዳኑ ሥርዓት ጥላ ሆኖ አልፏል፡፡ 2ኛ ቆሮ 3፥7-11 ፤ ቆላ 2፥17፤ ዕብ 10፥1፡፡

  እንግዲህ እዚህ ላይ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦትና ጽላት የብሉይ ኪዳኑን የታቦት አሰራርና ሥርዐት ጠንቅቆና ተከትሎ የማይሄድ ከሆነ፤ ይህ የብሉይ ኪዳኑን የታቦትና የጽላት አቀራረጽ ሥርዐት ጠንቅቆ ያልሄደ የሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ከየት መጣ የሚል ጥያቄም ሳይነሳ አይቀርም፡፡

  አንባብያን ሆይ በቀጥታ ወደ ጥያቄው ከመግባታችን በፊት በዚህ ጽሑፍ ዶግማ ላይ ስለዶግማና ቀኖና ማብራሪያ የሰጠነው ይህን ለመሰለው ጥያቄ እንዲጠቅም ነው፡፡ አሁን ወደ ሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ስንሄድ ቁም ነገሩ እንደሚከተለው ነው፡፡

  የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽም ሆነ አጠቃቀሙ የተወሰነውና የሚወሰነው በቀኖና ነው፡፡ ቀኖና ደግሞ እንደ ሁኔታው የሚሻሻል ነው፡፡ ሲቻል ይጨመርበታል ሳይቻል ደግሞ ይቀነስለታል፡፡ እንግዲህ በቤተክርስቲያናችን ቀኖና ካበረከታቸው ነገሮች አንዱ የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽንና አጠቃቀምን ነው፡፡

  ስለዚህ በሐዲስ ኪዳን ታቦትን ለመቅረጽ የግራር እንጨት ባይገኝ በዘፍ 1፥31 ላይ ‹‹ እግዚአብሔርም የፈጠረውን (ያደረገውን) ሁሉ እጅግ መልካም እንደሆነ አየ›› ስለሚልና እግዚአብሔር የፈጠረውን ስለማይንቅ ከግራር ሌላ ከማይነቅዝ እንጨት መቅረጽ እንችላለን፡፡ ቁመቱ ወርዱና ዙሪያውም እንደችሎታችን ይሆናል፡፡ በውስጥና በውጭ ስለሚሆነው የወርቅ ክብርም እንደችሎታችን ይወሰናል፡፡ ከሌለንም ወርቁ ይቀራል ቀኖና ነውና፡፡

  ስለጽላቱም እንደዚሁ ነው ከቻልን ከከበረ ድንጋይ፣ ከዕብነ በረድ መቅረጽ እንችላለን፤ ካልቻልን ጽላቱን ከማይነቅዝ እንጨት መቅረጽ እንችላለን፡፡ በሌላ በኩልም ከቻልን እንደ ብሉይ ኪዳኑ በአንድ ታቦት ሁለት ጽላት ማስቀመጥ እንችላለን፤ ካልቻን በአንድ ታቦት አንድ ጽላት ብቻ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የጽላቱን ማስቀመጫ ታቦት ባይኖረን ጽላቱን ታቦት ብለን በመጥራት በጽላቱ ብቻ መጠቀም እችላለን ቀኖና ነውና፡፡

  በተጨማሪም በኤር 31፥31፤ 2ኛ ቆሮ 3፥1-3፤ በዕብ 8፥8-13፡፡ የእኛ አካልና ልቡና የእርሱ ታቦትና ጽላት አልሆነም ወይ? በሐዲስ ኪዳን ለምን ታቦትና ጽላት አስፈለገ? ለምንስ ይህ ሁሉ ተፈጠረ የሚሉ አሉ፡፡ የክርስቲያኖች አካልና ልቡና በክርስቶስ ደም ታቦት፤ ጽላት፤ ቤተ መቅደስ መሆኑን እናምናለን፡፡ ቢሆንም በሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ያስፈለገበት ምክንያት ስለአምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነትና ክብር ሲባል ነው፡፡ ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ክብሩን የገለጠበት፤ ቃሉን ያሰማበት፣ ሙሴን እንደባልጀራ ያነጋገረበት፣ የክብሩ ዙፋን ሆኖ ጽላቱ በውስጡ ለታቦቱ ማደሪያ በመሆኑ፤ በሐዲስ ኪዳንም የሥጋውና የደሙ የክብር ዙፋን እንዲሆን ሲሆን ስለእኛ በዚህ ዓለም መከራ የተቀበለውን መድኅኔዓለም ክርስቶስን ለማክበር ሲባል ነው፡፡

  ReplyDelete
 22. 1ኛ፡- ታቦት እንደሙሴ ሕግ የሚዘጋጀው ከግራር እንጨት ሆኖ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፤ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ቁመቱም አንድ ተኩል ይሁን ይልና በውስጥና በውጭም በጥሩ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ አክሊል አድርግለት ይላል፡፡ ደግሞም ታቦቱን የሚሸከሙት ከወርቅ በተሠሩ መሎጊያዎች አራት ሰዎች እንደሆኑ እንረዳለን፡፡ በአጠቃላይ የብሉይ ኪዳን የታቦት አሠራር እጅግ ከባድ በመሆኑ በሁሉም ዘንድ አይቻልም ነበር፡፡ ምናልባት አንዳንድ የቤተክርስቲያን ፍቅር የነበራቸው ነገሥታትና ዛሬም ፍቅረ ቤተክርስቲያን ያላቸው አንዳንድ ምዕመናን ይችሉት እንደሆነ ነው እንጂ፡፡

  2ኛ፡- ጽላት፤ ጽላትም እንደሙሴ ሕግ ከሆነ መዘጋጀትና መጠረብ ያለበት ከከበረ ድንጋይ ነው፡፡ በአንድ ታቦት ውስጥም መቀመጥ ያለባቸው ሁለት ጽላቶች ናቸው፡፡ ዘዳ 34፥1፡፡ በአጠቃላይ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሕግና ሥርዐት ከባድ ነው፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ሥርዐትም ለሐዲስ ኪዳኑ ሥርዓት ጥላ ሆኖ አልፏል፡፡ 2ኛ ቆሮ 3፥7-11 ፤ ቆላ 2፥17፤ ዕብ 10፥1፡፡

  እንግዲህ እዚህ ላይ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦትና ጽላት የብሉይ ኪዳኑን የታቦት አሰራርና ሥርዐት ጠንቅቆና ተከትሎ የማይሄድ ከሆነ፤ ይህ የብሉይ ኪዳኑን የታቦትና የሚል ጥያቄም ሳይነሳ@የጽላት አቀራረጽ ሥርዐት ጠንቅቆ ያልሄደ የሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ከየት መጣ አይቀርም፡፡

  አንባብያን ሆይ በቀጥታ ወደ ጥያቄው ከመግባታችን በፊት በዚህ ጽሑፍ ዶግማ ላይ ስለዶግማና ቀኖና ማብራሪያ የሰጠነው ይህን ለመሰለው ጥያቄ እንዲጠቅም ነው፡፡ አሁን ወደ ሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ስንሄድ ቁም ነገሩ እንደሚከተለው ነው፡፡

  የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽም ሆነ አጠቃቀሙ የተወሰነውና የሚወሰነው በቀኖና ነው፡፡ ቀኖና ደግሞ እንደ ሁኔታው የሚሻሻል ነው፡፡ ሲቻል ይጨመርበታል ሳይቻል ደግሞ ይቀነስለታል፡፡ እንግዲህ በቤተክርስቲያናችን ቀኖና ካበረከታቸው ነገሮች አንዱ የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽንና አጠቃቀምን ነው፡፡

  ስለዚህ በሐዲስ ኪዳን ታቦትን ለመቅረጽ የግራር እንጨት ባይገኝ በዘፍ 1፥31 ላይ ‹‹ እግዚአብሔርም የፈጠረውን (ያደረገውን) ሁሉ እጅግ መልካም እንደሆነ አየ›› ስለሚልና እግዚአብሔር የፈጠረውን ስለማይንቅ ከግራር ሌላ ከማይነቅዝ እንጨት መቅረጽ እንችላለን፡፡ ቁመቱ ወርዱና ዙሪያውም እንደችሎታችን ይሆናል፡፡ በውስጥና በውጭ ስለሚሆነው የወርቅ ክብርም እንደችሎታችን ይወሰናል፡፡ ከሌለንም ወርቁ ይቀራል ቀኖና ነውና፡፡

  ReplyDelete
 23. 1ኛ፡- ታቦት እንደሙሴ ሕግ የሚዘጋጀው ከግራር እንጨት ሆኖ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፤ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ቁመቱም አንድ ተኩል ይሁን ይልና በውስጥና በውጭም በጥሩ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ አክሊል አድርግለት ይላል፡፡ ደግሞም ታቦቱን የሚሸከሙት ከወርቅ በተሠሩ መሎጊያዎች አራት ሰዎች እንደሆኑ እንረዳለን፡፡ በአጠቃላይ የብሉይ ኪዳን የታቦት አሠራር እጅግ ከባድ በመሆኑ በሁሉም ዘንድ አይቻልም ነበር፡፡ ምናልባት አንዳንድ የቤተክርስቲያን ፍቅር የነበራቸው ነገሥታትና ዛሬም ፍቅረ ቤተክርስቲያን ያላቸው አንዳንድ ምዕመናን ይችሉት እንደሆነ ነው እንጂ፡፡

  2ኛ፡- ጽላት፤ ጽላትም እንደሙሴ ሕግ ከሆነ መዘጋጀትና መጠረብ ያለበት ከከበረ ድንጋይ ነው፡፡ በአንድ ታቦት ውስጥም መቀመጥ ያለባቸው ሁለት ጽላቶች ናቸው፡፡ ዘዳ 34፥1፡፡ በአጠቃላይ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሕግና ሥርዐት ከባድ ነው፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ሥርዐትም ለሐዲስ ኪዳኑ ሥርዓት ጥላ ሆኖ አልፏል፡፡ 2ኛ ቆሮ 3፥7-11 ፤ ቆላ 2፥17፤ ዕብ 10፥1፡፡

  እንግዲህ እዚህ ላይ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦትና ጽላት የብሉይ ኪዳኑን የታቦት አሰራርና ሥርዐት ጠንቅቆና ተከትሎ የማይሄድ ከሆነ፤ ይህ የብሉይ ኪዳኑን የታቦትና የሚል ጥያቄም ሳይነሳ@የጽላት አቀራረጽ ሥርዐት ጠንቅቆ ያልሄደ የሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ከየት መጣ አይቀርም፡፡

  አንባብያን ሆይ በቀጥታ ወደ ጥያቄው ከመግባታችን በፊት በዚህ ጽሑፍ ዶግማ ላይ ስለዶግማና ቀኖና ማብራሪያ የሰጠነው ይህን ለመሰለው ጥያቄ እንዲጠቅም ነው፡፡ አሁን ወደ ሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ስንሄድ ቁም ነገሩ እንደሚከተለው ነው፡፡

  የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽም ሆነ አጠቃቀሙ የተወሰነውና የሚወሰነው በቀኖና ነው፡፡ ቀኖና ደግሞ እንደ ሁኔታው የሚሻሻል ነው፡፡ ሲቻል ይጨመርበታል ሳይቻል ደግሞ ይቀነስለታል፡፡ እንግዲህ በቤተክርስቲያናችን ቀኖና ካበረከታቸው ነገሮች አንዱ የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽንና አጠቃቀምን ነው፡፡

  ስለዚህ በሐዲስ ኪዳን ታቦትን ለመቅረጽ የግራር እንጨት ባይገኝ በዘፍ 1፥31 ላይ ‹‹ እግዚአብሔርም የፈጠረውን (ያደረገውን) ሁሉ እጅግ መልካም እንደሆነ አየ›› ስለሚልና እግዚአብሔር የፈጠረውን ስለማይንቅ ከግራር ሌላ ከማይነቅዝ እንጨት መቅረጽ እንችላለን፡፡ ቁመቱ ወርዱና ዙሪያውም እንደችሎታችን ይሆናል፡፡ በውስጥና በውጭ ስለሚሆነው የወርቅ ክብርም እንደችሎታችን ይወሰናል፡፡ ከሌለንም ወርቁ ይቀራል ቀኖና ነውና፡፡

  ReplyDelete
 24. 1ኛ፡- ታቦት እንደሙሴ ሕግ የሚዘጋጀው ከግራር እንጨት ሆኖ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፤ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ቁመቱም አንድ ተኩል ይሁን ይልና በውስጥና በውጭም በጥሩ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ አክሊል አድርግለት ይላል፡፡ ደግሞም ታቦቱን የሚሸከሙት ከወርቅ በተሠሩ መሎጊያዎች አራት ሰዎች እንደሆኑ እንረዳለን፡፡ በአጠቃላይ የብሉይ ኪዳን የታቦት አሠራር እጅግ ከባድ በመሆኑ በሁሉም ዘንድ አይቻልም ነበር፡፡ ምናልባት አንዳንድ የቤተክርስቲያን ፍቅር የነበራቸው ነገሥታትና ዛሬም ፍቅረ ቤተክርስቲያን ያላቸው አንዳንድ ምዕመናን ይችሉት እንደሆነ ነው እንጂ፡፡

  2ኛ፡- ጽላት፤ ጽላትም እንደሙሴ ሕግ ከሆነ መዘጋጀትና መጠረብ ያለበት ከከበረ ድንጋይ ነው፡፡ በአንድ ታቦት ውስጥም መቀመጥ ያለባቸው ሁለት ጽላቶች ናቸው፡፡ ዘዳ 34፥1፡፡ በአጠቃላይ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሕግና ሥርዐት ከባድ ነው፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ሥርዐትም ለሐዲስ ኪዳኑ ሥርዓት ጥላ ሆኖ አልፏል፡፡ 2ኛ ቆሮ 3፥7-11 ፤ ቆላ 2፥17፤ ዕብ 10፥1፡፡

  እንግዲህ እዚህ ላይ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦትና ጽላት የብሉይ ኪዳኑን የታቦት አሰራርና ሥርዐት ጠንቅቆና ተከትሎ የማይሄድ ከሆነ፤ ይህ የብሉይ ኪዳኑን የታቦትና የሚል ጥያቄም ሳይነሳ@የጽላት አቀራረጽ ሥርዐት ጠንቅቆ ያልሄደ የሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ከየት መጣ አይቀርም፡፡

  አንባብያን ሆይ በቀጥታ ወደ ጥያቄው ከመግባታችን በፊት በዚህ ጽሑፍ ዶግማ ላይ ስለዶግማና ቀኖና ማብራሪያ የሰጠነው ይህን ለመሰለው ጥያቄ እንዲጠቅም ነው፡፡ አሁን ወደ ሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ስንሄድ ቁም ነገሩ እንደሚከተለው ነው፡፡

  የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽም ሆነ አጠቃቀሙ የተወሰነውና የሚወሰነው በቀኖና ነው፡፡ ቀኖና ደግሞ እንደ ሁኔታው የሚሻሻል ነው፡፡ ሲቻል ይጨመርበታል ሳይቻል ደግሞ ይቀነስለታል፡፡ እንግዲህ በቤተክርስቲያናችን ቀኖና ካበረከታቸው ነገሮች አንዱ የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽንና አጠቃቀምን ነው፡፡

  ReplyDelete
 25. ስለጽላቱም እንደዚሁ ነው ከቻልን ከከበረ ድንጋይ፣ ከዕብነ በረድ መቅረጽ እንችላለን፤ ካልቻልን ጽላቱን ከማይነቅዝ እንጨት መቅረጽ እንችላለን፡፡ በሌላ በኩልም ከቻልን እንደ ብሉይ ኪዳኑ በአንድ ታቦት ሁለት ጽላት ማስቀመጥ እንችላለን፤ ካልቻን በአንድ ታቦት አንድ ጽላት ብቻ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የጽላቱን ማስቀመጫ ታቦት ባይኖረን ጽላቱን ታቦት ብለን በመጥራት በጽላቱ ብቻ መጠቀም እችላለን ቀኖና ነውና፡፡

  በተጨማሪም በኤር 31፥31፤ 2ኛ ቆሮ 3፥1-3፤ በዕብ 8፥8-13፡፡ የእኛ አካልና ልቡና የእርሱ ታቦትና ጽላት አልሆነም ወይ? በሐዲስ ኪዳን ለምን ታቦትና ጽላት አስፈለገ? ለምንስ ይህ ሁሉ ተፈጠረ የሚሉ አሉ፡፡ የክርስቲያኖች አካልና ልቡና በክርስቶስ ደም ታቦት፤ ጽላት፤ ቤተ መቅደስ መሆኑን እናምናለን፡፡ ቢሆንም በሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ያስፈለገበት ምክንያት ስለአምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነትና ክብር ሲባል ነው፡፡ ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ክብሩን የገለጠበት፤ ቃሉን ያሰማበት፣ ሙሴን እንደባልጀራ ያነጋገረበት፣ የክብሩ ዙፋን ሆኖ ጽላቱ በውስጡ ለታቦቱ ማደሪያ በመሆኑ፤ በሐዲስ ኪዳንም የሥጋውና የደሙ የክብር ዙፋን እንዲሆን ሲሆን ስለእኛ በዚህ ዓለም መከራ የተቀበለውን መድኅኔዓለም ክርስቶስን ለማክበር ሲባል ነው፡፡

  ReplyDelete
 26. 1ኛ፡- ታቦት እንደሙሴ ሕግ የሚዘጋጀው ከግራር እንጨት ሆኖ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፤ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ቁመቱም አንድ ተኩል ይሁን ይልና በውስጥና በውጭም በጥሩ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ አክሊል አድርግለት ይላል፡፡ ደግሞም ታቦቱን የሚሸከሙት ከወርቅ በተሠሩ መሎጊያዎች አራት ሰዎች እንደሆኑ እንረዳለን፡፡ በአጠቃላይ የብሉይ ኪዳን የታቦት አሠራር እጅግ ከባድ በመሆኑ በሁሉም ዘንድ አይቻልም ነበር፡፡ ምናልባት አንዳንድ የቤተክርስቲያን ፍቅር የነበራቸው ነገሥታትና ዛሬም ፍቅረ ቤተክርስቲያን ያላቸው አንዳንድ ምዕመናን ይችሉት እንደሆነ ነው እንጂ፡፡

  2ኛ፡- ጽላት፤ ጽላትም እንደሙሴ ሕግ ከሆነ መዘጋጀትና መጠረብ ያለበት ከከበረ ድንጋይ ነው፡፡ በአንድ ታቦት ውስጥም መቀመጥ ያለባቸው ሁለት ጽላቶች ናቸው፡፡ ዘዳ 34፥1፡፡ በአጠቃላይ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሕግና ሥርዐት ከባድ ነው፡፡ የብሉይ ኪዳኑ ሥርዐትም ለሐዲስ ኪዳኑ ሥርዓት ጥላ ሆኖ አልፏል፡፡ 2ኛ ቆሮ 3፥7-11 ፤ ቆላ 2፥17፤ ዕብ 10፥1፡፡

  እንግዲህ እዚህ ላይ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦትና ጽላት የብሉይ ኪዳኑን የታቦት አሰራርና ሥርዐት ጠንቅቆና ተከትሎ የማይሄድ ከሆነ፤ ይህ የብሉይ ኪዳኑን የታቦትና የሚል ጥያቄም ሳይነሳ@የጽላት አቀራረጽ ሥርዐት ጠንቅቆ ያልሄደ የሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ከየት መጣ አይቀርም፡፡

  አንባብያን ሆይ በቀጥታ ወደ ጥያቄው ከመግባታችን በፊት በዚህ ጽሑፍ ዶግማ ላይ ስለዶግማና ቀኖና ማብራሪያ የሰጠነው ይህን ለመሰለው ጥያቄ እንዲጠቅም ነው፡፡ አሁን ወደ ሐዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ስንሄድ ቁም ነገሩ እንደሚከተለው ነው፡፡

  የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽም ሆነ አጠቃቀሙ የተወሰነውና የሚወሰነው በቀኖና ነው፡፡ ቀኖና ደግሞ እንደ ሁኔታው የሚሻሻል ነው፡፡ ሲቻል ይጨመርበታል ሳይቻል ደግሞ ይቀነስለታል፡፡ እንግዲህ በቤተክርስቲያናችን ቀኖና ካበረከታቸው ነገሮች አንዱ የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽንና አጠቃቀምን ነው፡፡

  ReplyDelete