Wednesday, March 2, 2011

በትርጉም የተቀበሩ እውነቶችና ቦታ ያገኙ ውሸቶች

በመጽሐፍ ለተገለጹት እውነቶች የተሳሳተ ትርጉም ከተሰጣቸው ምክንያቶች መካከል ዋናው ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ ሰርገው ለገቡት የስሕተት ትምህርቶች ሕጋዊነት ለመስጠት ሲባል መሆኑ ምስክር አያሻውም። ብዙ የስሕተት ትምህርቶች በማስመሰል መንገድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፍ እንዲኖራቸው የሚደረገው መጽሐፍ ቅዱስን ሁሉም የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ስለ ሚስማማበት ነገሩ ተቀባይነት እንዲኖረው ነው። መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ እንዲሉ አበው።


የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል ተብሎ የተጻፈውን ቃል በማስተዋልና ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ በሚለው ቃል መሠረት ማንኛውም ምእመን የሃይማኖቱን ትምህርት በእግዚአብሔር ቃለ መሠረት ሊመረምርና መልካሙን ከመጥፎው ለይቶ ሊይዝ ተገቢ ነው። (ምሳ 14፥15፤ 1ተሰ 5፥20)

የቤርያ አይሁድ አመለካከት ከተቀበልነው ውጪ ሌላ መስማት አንፈልግም በሚል ጠባብነት ያልተሞላና ከላይ ባየነው የእግዚአብሔር ቃል ላይ የተደገፈ በመሆኑ እውነትን ከሐሰት፥ ትክክለኛን ነገር ከተሳሳተው ለይቶ ለመረዳት ቀና መንገድ ሆኖላቸዋል። (የሐዋ ሥራ 17፥11)

ስንቶቻችን የሃይማኖታችንን ትምህርት በእግዚአብሔር ቃል መርምረናላ? መመራመር መጥፎ ነው የሚለው የሰነፎች ብሂል አስሮ የያዘንስ ስንቶች ነን? በተገለጠው ነገር ላይ መልካሙን ከመጥፎው ለመለየት የሚደረገው ምርምር ምንም መጥፎ ጎን የለውም። እንግዲያውም ወደ እውነት ያደርሳል። ከተገለጠልን ውጪ እግዚአብሔር ራሱ ምስጢር ያደረገውን ነገር ለመግለጥ መፍጨርጨሩ ግን ወደ አልተፈለገ ስሕተት ይመራናል። ብዙዎች ከሃይማኖት ወጥተው በትዕቢት ተነፍተው የወደቁት ከዚህ የተነሣ ነው። ለሁሉም ግን ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ የተባለው በተገለጠው እውነት ላይ ሁሉን በእግዚአብሔር ቃል መሠረት መርምረን እንደ ቤርያ አይሁድ ወደ እውነት እንድንደርስ መሆኑን አንዘንጋ።

አንዳንዱን በትክክል ሳንረዳ እኛ እናውቅላችሁአለን በሚሉን ሰዎች ስንመራ ኖረናል። የእግዚአብሔርን እውነት አግኝተን ግን አላረፍንም። ለነገሩማ መጽሐፍ ቅዱስን አንብቡ፥ ተማሩ፥ አስተምሩ ብለው ሰጥተውን ነበር። እኛም ገልጠን ማንበብ፥ መማር፥ ማስተማር ጀመርን። በዚህ ጊዜ የተረዳነው እውነት ከእነርሱ አስተምህሮ ጋር ሳይስማማ ቀረ። ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ብልጭ ብሎልን ጥያቄ ስናቀርብ እንኳን ዘመናትን ካስቆጠረው ስሕተት ጋር ጥያቄአችን ስለሚጋጭ ይህ የመናፍቃን ጥያቄ ነው። ተብለን እንነቀፋለን። መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ የሚሆኑ ቢገኙም ለህልውናቸው ሲሉ በማቻቻልና አገም ጠቀም በሆነ መንገድ የማያረካ መልስ ይሰጣሉ። እግዚአብሔር ይመስገን! አሁን ግን የእግዚአብሔርም ልጅ እንደመጣ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደሰጠን ተረድተናል። (1ዮሐ 5፥20)

እውነት እንዲዛባ ያደረገው በአተረጓጎም ላይ የተፈጠረው ስሕተት ነው። ከዚህ ቀጥሎ በቤተ ክርስቲያናችን የተሳሳተ ትርጓሜ ከተሰጣቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች መካከል አንዱን ብቻ እንቃኛለን።

ያዕቆብ በሕልሙ ያየው መሰላል

ያዕቆብ ከቤርሳቤት ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ። ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ። ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ። በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሳ። ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ ሕልምም አለመ። እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር። እነሆም እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር። (ዘፍ 28፥10-13)

ያዕቆብ ከወንድሙ ከኤሳው ፊት ሸሽቶ በጉዞ ላይ ሳለ ካደረበት ቦታ ሌሊት ተኝቶ በሕልሙ ያየው ይህ መሰላል ድንግል ማርያም ናት ብለው ብዙዎች ያምናሉ፥ ያስተምራሉም። በድርሰቶቻቸውም ውስጥ አስረግጠው በስፋት ጽፈዋል። ይህም የክርስቶስን ስፍራ ለእርሷ ለመስጠት ብለው ያደረጉት ነው።

ያዕቆብ በምድር ተተክሎ፥ ራሱን ወደ ሰማይ ደርሶ ያየው መሰላል በምድር የሚኖሩ ሰዎች በሰማይ ካለው አምላክ ጋር የተገናኙበት ሰው የሆነው አምላክ የክርስቶስ ምሳሌ ነው። ለያዕቆብ በምሳሌነት የታየው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ሲመጣ መላእክት በመሰላል ላይ ሳይሆን የሰው ልጅ በተባለው በክርስቶስ ላይ እንደሚወጡና እንደሚወርዱ ራሱ ጌታችን ተናግሯል፦ እውነት እውነት እላችሁአለሁ። ሰማይ ሲከፈት የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ። (ዮሐ 1፥52)

ያዕቆብ ስለመሰላሉ ያየው ራእይ በክርስቶስ መፈጸሙን ሊቃውንተ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በየድርሳኖቻቸው አስቀምጠውልናል።

ወሶበሂ ርእይዎ ዓዲ እንዘ የዓርግ ሰማየ ተፈሥሑ ወተሐሠዩ ጥቀ ወዐርጉ ምስሌሁ ውስተ ሰማይ ወበእንተዝ እምአመ ዕለተ ዐርገ እግዚአነ ኢየሱስ ክርስቶስ ኮነ ራእይ ዘነጸሮ ያዕቆብ እሙነ እንዘ መላእክት የዐርጉ ወይወርዱ ኃበ አብ ወዝ ውእቱ ርእይ ሐዲስ ዘኮኑ ይትሜነዩ ይርአይዎ እምቅድመ ዮም ወናሁ ይእዜ ርእይዎ

ትርጓሜ፦ ዳግመኛ ወደ ሰማይ ሲያርግ ባዩት ጊዜ ፈጽሞ ደስ አላቸው። ወደ ሰማይም ተከትለውት ወጡ ስለዚህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገበት ቀን ጀምሮ መላእክት ወደ አብ ሲወጡ ሲወርዱ ያዕቆብ ያየው ራእይ ደረሰ ተፈጸመ። ከዛሬ አስቀድሞ ሊያዩት ይመኙት የነበረ እንግዳ ማየት ይህ ነው። እነሆ አሁንም ዛሬ አዩት። (ሃይ። አበ ዘዮሐ አፈ ም 68 ክፍል 25 ቁ 34)

ያዕቆብኒ ይቤ ርኢኩ ሰዋስወ ዘሰማይ፤ ወመላእክተ እግዚአብሔር የዐርጉ ወይወርዱ፤ እንተ ይእቲ ሰዋስወ ኢየሱስ ይነብር በየማነ አቡሁ አእላፍ መላእክት ይትለአክዎ።

ትርጓሜ፦ ያዕቆብም ወደ ሰማይ የደረሰ መሰላልን አየሁ አለ። የእግዚአብሔር መላእክትም የወጡበታል ይወርዱበታል። ይህችም በአባቱ ቀኝ የተቀመጠ አእላፍ መላእክት የሚያገለግሉት የኢየሱስ መሰላልነት ናት። (የዮሐንስ ድጓ ገጽ 88 3ኛ ዓምድ)


አብይ - የተቀበረ መክሊት ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።

9 comments:

 1. Okay. That verse is primarily for Jesus Christ of course, but it can be for St. Mary secondarily. Don't over stretch facts. I think Aba Heriakos also calls St. Mary as the "Ladder of Jacob." All is secondary... What is wrong for the Mother to be called with some of the qualities of Her most beloved Son, who is the fruit of Her Womb? Again, it is not that helpful to fight on this. Better to focus on other areas of improvement. Let's get the debteras and some other followers out of tinkola and other bad beliefs. The mainly Pente West has approved gays and lesbians to be bishops of the church of Christ; it may not be long before we see similar demands by ethiopian pentes. At least, no orthodox is accused of that... Better fight the evil; St. Mary is the Mother of Christ and has no parllel for Her. Even if your verse applies solely for Jesus Christ, it won't affect Her and nor our love for Her. Again, it is better to focus on other value-adding areas if you are a genuine christian.

  ReplyDelete
 2. Anonymous, እየቀለድህ ነው አይደል? What do you mean by primary and secondary? Come on! let's stop confusing ourselves and others. A given word of God in the Bible has one and only one message for all of us. Primary, Secondary የሚለው ዝባዝንኬ ጸሐፊው እንዳለው የስህተት ትምህርቶችን እውቅና ለመስጠት የተደረገ ነው። እመቤታችንን ለማክበር የግድ ለክርስቶስ የተነገረውን ለእርሷ ማድረግ የለብንም። ይሄ የእግዚአብሔርን ቃል ማጣመም ነው። ክብር ለሚገባው ክብርን እንሰጣለን ግን ያለቦታው እና የመጽሐፍን ትርጉም በማዛባት አይደለም። YOur argument regarding some protestant's views on gays and lesbians is confusing. Are you saying we should stop discussing all other issues because of this? I think the witter has a valid point and has done a good job of pointing out a dangerous trend in our church to use the Bible in the wrong way to justify or exagerate some things. I don't understand your view of "value adding areas" Should we just talk about Pentes, Gays, Lesbians? please make yourself clear. ለክርርስቶስ የተነገረው ክብር, ማንነት ለሌላ መሰጠቱ፥ ላንተ ምንም ላይሆን ይችላል። ለአንዳንዶቻችን ደግሞ እጅግ ያሳዝናል። ጥያቄው እኮ እግዚአብሔር ለያዕቆብ ያንን ህልም ሲያሳየው ሊያስተላልፍ የውደደው መልዕክት ምንድን ነው? ነው። መልዕክቱ አንድ እና አንድ ነው። እንደዚህም ነው እንደዛም ነው የሚለው ማወናበድ ስህተት ነው!

  ReplyDelete
 3. Ewinet,

  If you knew the bible and the church well, you would not say that. Do you know "ANDIMINTA Tirgum" in our church? What that means is detailed one-by-one interpretation of each and every verse in the bible. Andem this; andem that; lelam this... Thus, one verse can have three, four or more meanings depending on the case. I suggest that you talk to people who studied the Bible (old & new testaments) in our church. I can give hundreds of examples to highlight my point - I mean verses having multiple interpretaions. thanks.

  ReplyDelete
 4. Ewinet,

  See below additional comments/answers:

  1) The reason I mentioned about the Pente gays and lesbians is to highlight the fact that other so-called churches have used the bible to legalize and defend their sinful life, such as same sex marriage. However, our church has not done damages of that magnitude. We have some problems which we can solve with a concerted effort. I am not saying we should not talk or write about those; I am just saying the alleged problem is not as such a big problem. As I said, that verse may definitely apply to St. Mary as a second derivative while it fully applies to Christ first and foremost.

  2) By value-adding I mean things that can address the major problems that have entangled the church, such as -
  a) ways to reach out to rural Ethiopia where the bible has not been preached for years;
  b) ways to weaken and eventually remove Tenkway members of the clergy, including most of debteras, from the church;
  c) ways of furhter revititalizing the bible in urban centers;
  d) ways of helping the saints who live in the monasteries;
  e) ways of correcting some of the bad books that some bad folks have written;
  f) ways of translating some of the ancient books that are avilable in Ge'ez only;
  g) ways of reaching other people that EOTC does not have a strong presence;
  h) ways of reconciling the church that has been split along ethnic and political lines;
  i) ways of de-politicing the church, except on national matters that deal with sovereignty and justice;
  j) on and on and on...

  Otherwise, if we don't write and discuss, how can we learn about our own church and the outside world? I thank the writer for his courage to publish this. As far as the writing is not be elements of our enemy, I always welcome it even if I may diagree with some of the contents.

  ReplyDelete
 5. Are you saying the ladder of jacob is ANDIM emebetachin ANDIM getachin? It doesn't make sense. It has to be only one of them. I am aware of the ANDIMTA TIRGUAME, but I don't neccessarily agree with it. At least not all the time. I don't know how much you read it, but I do read it. Sometimees it is helpful, but confusing most of the time. One thing should only have one meaning. There are some cases where you may use a verse to communicate two messages, but we overdue it. In fact, I have seen contradicting interpretations for a single verse.

  ReplyDelete
 6. one thing you have to know is, Jesus said all the holy books tells about me not others

  please my brothers and sisters don't be confused

  Jesus said I am the only way

  Tsega

  ReplyDelete
 7. Ewinet,

  I found the following on STG site and felt it could highlight my point on tirguame. I undertand you are aware of that tirgume book; nothing i perfect, except God. I hope you will like this piece...

  ‹‹ ከእኔ አብ ይበልጣል ›› ዮሐ፡- 14፡27 የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ሀይለ ቃል ስለምን እንደተናገረው ሳይረዱ አንዳንድ ወንድሞች ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ያንሳል ስለዚህ የባሕርይ አምላክ አይደለም ይላሉ ፤ ግን የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችን በመዋዕለ ስብከቱ / ሥጋዌው/ ወቅት ሰዱቃውያን አንድ ወቅት ስለ ትንሣኤ ሙታን አንስተው በጠየቁት ጊዜ እንዲህ ብሎ ነው የመለሰላቸው ‹‹መጽሐፍትንና የእግዚአብሔርን ሀይል አታውቁመና ትስታላችሁ ›› ማቴ፡- 22፡29 ነበር ያላቸው ዛሬ ዛሬም ብዙ ሰዎች ይህን ካለመረዳት በራሳቸው ፊቺ እየፈቱ ሲሰናከሉ መጽሐፍት /ነቢያትም ፣ ሐዋርያትም/ ስለ እርሱ ያልተናገሩትን ሲናገሩ ይሰማሉ ፤ የመጻሕፍትን ትርጓሜ ለመረዳት መጀመሪያ ትህትና ፣ የዋህነት ሊኖረን ያስፈልጋል ያን ጊዜ ነው እንደ ሐዋርያት ‹‹ መጻሕፍትን እንዲያስተውሉ አይምሯቸውን ከፈተላቸው ›› እንደተባለ ለእኛም ማስተዋሉን ያድለን ፡፡ ሉቃ፡- 24፡45 ማስተዋል ለሰው ልጅ አስፈላጊ ነገር ነው ታዲያ ማስተዋልን የሚያድል ቢኖር አንድና አንድ ነው ፤ እርሱም ጌታ እግዚአብሔር ነው ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈስ ልጁ ለጢሞቲዎስ በላከው መልዕክት እንዲህ ነበር እያለ የሚመርቀው ‹‹ ጌታ በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ ›› 2ጢሞ፡- 2፡7 ነበር የሚለው ፡፡ ማስተዋል በጣም ጠቃሚ ነገር ስለሆነ ከምንፍቅና ፣ ከክህደት፣ ከመጠራጠር፣ ከመገልበጥ ያድናልና፡፡ እግዚአብሔር አስቀድሞ በነቢዩ ሆሴዕ አድሮ እንደተናገረ እስራኤላውያን ከምን የተነሣ እንደጠፉ ሲናገር ሆሴ፡- 4፡14 ‹‹የማያስተውልም ሕዝብ ይገለበጣል›› ይል ነበር፡፡ ስለዚህ ለሁላችን ማስተዋሉን ያድለንና ከላይ ያነሳነውን ጥያቄ እንደ ቤተክርስቲያ አስተምህሮ በጥቂቱ እናያለን ፤ የምሥጢር ባለቤት ምሥጢሩን ይግለጥልን ፤ ጌታችን ከእኔ አብ ይበልጣል ሲል ከአብ አንሶ አይደለም ፤ ይህማ ከተባለ ወንጌል እርስ በርሷ ትጋጫለች ልንል ነው / ሎቱ ስብሐት/ ወንጌል ምንም እንኳን የተሰወረች ፍቺ የሚያስፈልጋት ቢሆንም ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው ‹‹ወንጌላችን የተከደነ ቢሆንም እንኳ የተከደነባቸው ለሚጠፉ ነው ›› እንዳለ 2ኛቆሮ፡- 4፡3 ስለዚህ ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን የወንጌል ፊቺ ትርጓሜን እግዚአብሔር በየዘመኑ ለተነሱ አባቶቻችን ገላልጦላቸው አንድም እያሉ በብዙ ትርጉም ተርጉመውልናል ፡፡ እነሆ ጌታችን አብ ከእኔ ይበልጣል ብሏልና ፤ በድፍረት ወልድ ከአብ ያንሳል ማለት አለማስተዋል ነው፡፡ ፍቺው አንደኛ ይህን በለበሰው ሥጋ ነው በለበሰው ሥጋ እንኳን ከአብ ፣ ከመላእክት አንሷል ፤ በለበሰው ሥጋ መከራን በመቀበሉ እንዲህ አለ ‹‹ አብና መንፈስ ቅዱስ ሥጋን አልተዋሐዱም ፤ መከራ አልተቀበሉምና ስለዚህ መላእክትም መከራ እንደ ጌታ አልተቀበሉምና ›› መዝ፡- 8፡5 ‹‹ከመላእክቱ እጅግ ጥቂት አሳነስኸው ብሎ ከክርስቶስ ልደት ከ1000 ዓመት በፊት የተናገረው ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን መልእክቱ ዕብ፡-2፡9 ‹‹ አሁን ግን ሁሉ እንደ ተገዛለት ገና አናይም ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ የክብርና የምሥጋናን ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን›› ይላል ታዲያ ጌታችን እኮ ከእኔ ይበልጣል ማለቱ አንሶ አይደለም፤ ምሥጢረ ሥጋዌን በደንብ ከተረዳን አምላክ ለምን ሰው ሆነ የሚለው መልስ ካገኘን እንደገናም እንኳን ከአብ ፤ ከመላእክት እንዲል ተብሏል ፡፡ ታዲያ በእውነት ማነው ኢየሱስ ክርስቶስ ከመላእክት ያንሳል ተብሎ ሲጠየቅ በድፍረት አዎ የሚለው ፤ ጌታ ሰው የሆነው አንደኛው ምክንያት ለእኛ ትህትናን ሲያስተምረን ራስን ዝቅ ማድረግን ሲያስተምረን ነው፡፡ ማቴ፡- 11፡19 ‹‹ ከእኔ ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት ነኝ ›› ብሎናል ሌላም እንጨምር ጌታ ሲያስተምር ራሱን ከመንፈስ ቅዱስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ተናግሯል፤ ማቴ፡- 12፡32 ባጠቃላይ ይህን ሁሉ የመሰለ ሀይለ ቃል ጌታ የተናገረው በለበሰው ሥጋ ነው፤ ፊሊ፡- 2፡7 ባሕርየ ሰብእ በመዋሐዱ ፍጹም ሰው የሆነና በሰውነቱም /በለበሰው ሥጋ/ መከራ መቀበሉን ለማጠየቅ ነው፡፡

  አንድም፡- ይህን ሀይለ ቃል የተናገረው አብ ከእኔ ይበልጣል ያለበት ምክንያት ለጊዜው አባቶቻችን ሐዋርያት መከራ መስቀል እንደሚቀበል ከእነሱ በዕርገት እንደሚለይ እሞታለሁ፣ እቀበራለሁ ፣ እነሳለው ወደ አባቴ ዐርጋለው እያለ ሲያስተምራቸው በጣም ፈርተው በልባቸው አዝነው ነበርና ‹‹ ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሔር እመኑ በእኔም ደግሞ እመኑ ›› እያለ የሚያስፈልጋቸው እምነት ብቻ እንደሆነና ፍርሐትን ከውስጣቸው አውጥተው መጣል እንዳለባቸው ሲነገራቸው ያለንን ነገር ሁሉ ትተን ተከትለን እንዲህ ያደረገን እያሉ በልባቸው ያስቡ ነበርና ወላጆች እንደሌላቸው አልፅናና ሲሉት ሰው መቼም ከዚህ የበለጠ አለ ሲሉት ሁል ጊዜ የበለጠውን የማየት ጉጉት አለበትና በመጨረሻም በዚህ ቢፅናኑ ብሎ ‹‹ የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር ›› አላቸው ፡፡ ስለዚህ ይህ ሀይለ ቃል የተናገረው ጌታ ከአብ አንሶ ሳይሆን ሐዋርያትን ለማፅናናት ነው፡፡

  አንድም፡- ምሥጢረ ሥላሴን /የአካል ሦስትነት/ የሚቃወሙ አሉና ለእነሱ መልስ ይሆን ዘንድ ነው ፡፡

  አንድም፡- ለትሕትና ነው ፤ ወንድሜ ከእኔ ይበልጣል እንድንል ትምህርት ይሆነን ዘንድ ‹‹የተጠራችሁ ለዚህ ነውና ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና ›› 1ኛጴጥ፡- 2፡21.

  ReplyDelete
 8. andimta malet if the first one is not right ,the second one is right malet new. kesemay eskemdr mezergat yemichel eyesus enji maryam aydelecm. miknyatum
  1 sewuna egziabehier megenagnet slalebachew eyesus mekakelegna (meselal)hone.
  2 mariyam degmo yaqobin honech hilmin sayhon ewnetin ayech

  ReplyDelete
  Replies
  1. On the name of the FATHER, the SON and the SPIRIT one GOD amen.
   It's realy better to know our spiritual status before evaluating those who are above our level. It's true to say that a man who only learnt Grade 2 can not evaluate that of a university lecturer. your writings are like this... Who're you first to forcefully tell others about the mother of Jesus??? Is it not better to first do a single word of GOD practically, evaluate yourself...If you deny a truth, you better deny alone, don't let others to go on your way, you'll also be asked by GOD regarding others sin too. I see you'ren't spiritually sufficient enough to evaluate mother of GOD...I advise you not to further tell others regarding any idea that you're not sure. Don't play with fire. We as human beings are only required to keep and do practically words of GOD, that's all.Let's do it. That's the difficulty part. Spliting words, ideas, truths... will not be asked. Please, please, please let's evaluate ourself and improve our spiritual level!!!

   Delete