Tuesday, March 29, 2011

ስለ ሰዎች ልጆች ፍቅር የተሰቀለው መርቆሬዎስ ነው - Read PDF

ዚቅን ጽፈውታል የሚባሉት ሰዎች ሲያነቡ የተሳሳቱ አልያም የትምህርት ማነስ ምክንያት ሆኖ መንፈሳዊ ነገር ያልገባቸው ሳይሆኑ ሆን ተብሎ የእግዚአብሔርን ክብር፤ የእግዚአብሔርን ምስጋናና የእግዚአብሔርን ሥራ በመለወጥ እንዲያገለግሉት ሰይጣን የሾማቸውና ራሳቸውም ለሰይጣን ያለጸጸት ለመገዛትና ለማገልገል የወሰኑ በርኩስ መንፈስ የተነዱ ናቸው።


በየዘመናቱ ተነሱ የተባሉት በርካታ መናፍቃን እንኳ ሰለ ሰው ልጆች ኃጢአት የተሰቀለውና የሞተው እርሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ አልካዱም። በባህርዩ ላይ ሕጸጽ ይገኝባቸው እንጂ። አንዳንዶች ፍጡር ነው፤ አንዳንዶችም ሁለት ባህርይ ነው ሌሎች ደግሞ አንድ ባህርይ ነው ቢሉም ስለሁላችን መከራን የተቀበለ የሞተና የተነሣው ክርስቶስ እንደሆነ ያምናሉ።

አገር በቀሎቹ የእኛዎች ከሐድያን ግን ሚያዚያ 25 ቀን በሚዜመው መዝሙራቸው ገጽ 170 ላይ እንዲህ በማለት ከእነቀያፋና ሐና የባሰውን ክሕደት ጽፈዋል።

"ንዜኑ መርቆሬዎስ ሂሩተ ትኅትና
ወየውሐተ ዘተአገሰ በእንተ አፍቅሮተ
ስብእ ዘሰቀሎ ለሰማይ ከመ ቀመር ዲበ
ዕፅ ተሰቅለ። ዘከለሎ ለሰማይ በከዋክብት አክሊለ ዘሦክ ተቀጸለ"

ትርጉም፦
"ስለ ሰው ልጆች ፍቅር በመታገስ
መከራን የተቀበለ በእንጨት ላይ
የተሰቀለ ሰማይን እንደዋልታ የዘረጋና
በከዋክብት የሸፈነ መርቆሬዎስ የሾክ
አክሊልን በራሱ ላይ ደፋ ስለዚህ
ቸርነቱና ትኅትናው ደግነቱን እንናገራለን"

ኃጢአት ያስከተለውን በሥጋ ለባሽም ያልተቻለውን የኃጢአት ደመወዝ ይኸውም ሞት ነው፤ መጽሐፍ እንደሚል እግዚአብሔር የገዛ ልጁን ልኮ አድርጎታል ይላል (ሮሜ 8፥3-4) ኃጢአት ያስከተለውን ሞትና ከእግዚአብሔርም ክብር መጉደል እግዚአብሔር በራሱ ለመመለስ በመፍቀዱ ዓለም ሳይፈጠር በታቀደው መሠረት ርግማንን ያጠፋ ዘንድ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ተከቦ ይኖር የነበረው ኃያል አምላክ የሰላም አለቃ የዘላለም አባት ተብሎ የተጠራው ወልድ በተለየ አካሉ በሥጋ ሰብእ ተገልጦ ስለ ሁላችን በውክልና ለሞት ያውም ለመስቀል ሞት ተላልፎ እንደተሰጠ ራሱ ሰይጣን በግዱ ያመነው እውነት ነው።

ይህም በአብ ፈቃድ ስለመተላለፋችን እደቆሰለ በደላችንንም እንደተሸከመ (ኢሳ 53፥1-12) ነቢያት ተንብየውታል። አምላክ በሥጋ ተገልጦ በፈጠራቸው ሰዎች እጆች መከራን በመቀበል የሾኽን ጉንጉን አክሊል እያሉ ዓይኖቹን እየሸፈኑ ማን እንደመታህ ትንቢት ተናገር በማለት ሲቀልዱበት የሰው ልጆች ፍቅር ለዚህ እንዳደረሰው ደጋግ አበው ተናግረዋል። መጻህፍትም ገልጠዋል። "ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት" ትርጉም፥ "ፍቅር የአምላክን ልጅ ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አበቃው"። እንዲሉ።

ጸሐፍተ ዚቅ ወመዝሙር የሆኑት መናፍቃን ግን ከክርስቶስ ዕርገት በኋላ 300 ዓመታትን ቆይቶ ነበረ የተባለውን ፍጡር እንዲህ ብለውታል።

"ስለ ሰው ልጆች ፍቅር በመታገስ መከራን የተቀበለ በእንጨት ላይ የተሰቀለ ሰማይን እንደዋልታ የዘረጋና በከዋክብት የሸፈነ መርቆሬዎስ የሾኽ አክሊልን በራሱ ላይ ደፋ ሰለዚህ ቸርነቱና ትህትናው ደግነቱን እንናገራለን።" በማለት በድፍረት ጽፈዋል።
ወገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ የሚለውን የኦሪት ዘልደት የመጀመሪያ ክፍል በመፋቅ "ሰማይን እንደዋልታ የዘረጋና በከዋክብት ያስጌጠ መርቆሬዎስ ነው" እያሉ በንባብም በዜማም እየደገሙ ከአንድ ኃይል አለ ባዩ ፍልስፍና በክህደት የላቀውን ደረጃ አስመዝግበዋል።

ሰዎቹ መርቆሬዎስ እያሉ የሚጠሩትን ባዕድ መንፈስ አንዴ ፈጣሬ ዓለማት ሲሉት ሌላ ጊዜ ለሰው ልጆች ሲል የተሰቀለ ይሉታል። የሚገርመው ፍጡር ሰው መሆኑን በድርሳናቸው መገለጣቸውን ረስተው ስግደትንና አምልኮን የሚቀበል አምላክ አድርገውም ስለውታል። ዕድሜው ያልዘለቀውን ዕሩቅ ብዕሲ እንዲህ እያሉ በቤተ ክርስቲያን ሥፍራ ቢሰጡትም እኛ እግዚአብሔር ባቀደልን መሠረት ከድንግል ማርያም በእውነት በሥጋ በተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በክርስቶስ ከዛሬ 2003 ዓመታት በፊት በእንጨት ላይ ተሰቅሎ ባፈሰሰው ደሙ የኃጢአት ሥርዬትን እንዳገኘን የሲኦል መሠረቶች እስኪናዱ ድረስ እናውጃለን።

ጸሐፊዎቹ ክሕደታቸውን በዜማም ሆነ በስብከት ሀገር ያደረስ ሥራ ክርስቶስን ተቀብያለው በማለት በስሙ ለተቋቋመችው ቤተ ክርስቲያናችን ዛሬ ለምትገኝበት ዝብርቅርቅ ሕይወት እንድትወድቅ ዳርጓታል። ህዝባችንም "አዕይንተ እግዚአብሔር" እያለ ካህናቱን ታምኖ የሚኖር በመሆኑ ሳይመረምርና ጥያቄ ሳያቀርብ ሁሉን ሰለሚቀበላቸው ሳያውቀው እግዚአብሔርን እየተቃወመ ወደ ሶኦል እንዲነጉድ አድርገውታል።

ሌላው ቀርቶ በፍታታችን እናጸድቅሃለን የሚሉት እነኚሁ መናፍቃን በክርስቶስ ይሁን ወይም አይሁን የማይታወቅ አስከሬን በፊታቸው አጋድመው ምዕመኑ በማያውቀው ቋንቋ ከሚጸልዩት መዝሙር አንዱ "ሚስቱን ሌላ ይውሰዳት ልጆቹም ይበተኑ ሥልጣኑም ለሌላ ትስጥ" የሚለውን በይሁዳ ላይ የተተነበየውን መርገም ነው። ምን አንደተባለ የማያውቀው ሕዝብ አሜን በማለት ሲተባበራቸው ይታያል።

በእነዚህ የመናፍስት ቁርኝት አገልጋዮች ሤራ አብዛኛው የቤተ ክርስቲያናችን አገልጋዮች ሳይቀሩ እንዳይቃወሙ ታሥረው በክፉዎች ትምህርት እየተነዱ ይገኛሉ። የሚያሳዝነው በዓለ ስቅለት ዘክርስቶስ በደረሰ ጊዜ "ዘበእንቲአሃ ለቤተ ክርስቲያን ተጸፋእከ በውስተ ዐውድ ከመ ትቀድሳ በደምከ ክቡር ዘበእንቲአሃ ዝግሐታተ መዋቅሕት ፆረ ወተዐገሠ ምራቀ ርኩሰ እንዘ አልቦ ዘአበሰ አምላክ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሰቀለ" ትርጉም፥ "ለቤተክርስቲያን (ለማህበረ ምዕመናን) ስትል በአደባባይ በጥፊ የተመታክ አቤቱ ይህን ማድረግህ እርሷን በከበረ ደምህ ትቀድሳት ዘንድ ነው ለእርሷ ሲል ታሥሮ መጎተትን የቻለ የበደለውም በደል ሳይኖር ርኩስ ምራቅን ሲተፉበት የታገሠ አምላክ በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ" (የያሬድ ጸሎት) እያለች የምትዘምር ቤተ ክርስቲያን ክፉዎች መርቆሬዎስ ሆይ ለሰው ልጆች ስትል በእንጨት ላይ ተሰቀልህ የእሾህም አክሊል ተሸከምህ የሚለውን ውሉደ አጋንንት ለማገድ ተሸንፋ በክፉዎች ተወርሳ መታየቷ ነው።

አድማስ - ገድል ወይስ ገደል የተባለውን መጽሐፍ አብነት በማድረግ

13 comments:

 1. Do you have proof that this is written in an EOTC book? If yes, please post the copy of the page containing this and the cover page of the book.

  If it exists, this must have been written by the spirit of Satan as alleged. One of the problems in our church is the language that has remained Ge'ez despite the transformation of the Ethiopian society.

  If the people hear the debteras sing this in Amharic, they will problably challenge it. Personally, I renounce any writing of that sort that is clearly anti-Christ..

  ReplyDelete
 2. who is merkorios??

  ReplyDelete
 3. ኦርቶዶክስMarch 30, 2011 at 7:34 AM

  You will find the book of Zeek (ዚቅ) in every church. All churchs have one to use it as part of the daily prayer etc. If you ask one of the priests of the church you go to, they should be able to show you the book. Anyway, it would be nice to see a scanned copy here too.

  Thanks Abaselama for for attempting to create such an awareness of the realities in our church. As one of your articles indicated a while ago, our church has great foundations, but a lot of things have gone wrong overtime. We need a major cleanup.

  ReplyDelete
 4. personally i don't believe what u have said .'' semayatin yezerega '' ,who ? is he the person that u mentioned? does our church teach like that? no! no!no! I think the word merkorios may have some other meaning in Ge'ez .Surely ,no membere of EOTC accepts ''ስለ ሰው ልጆች ፍቅር በመታገስ
  መከራን የተቀበለ በእንጨት ላይ
  የተሰቀለ ሰማይን እንደዋልታ የዘረጋና
  በከዋክብት የሸፈነ መርቆሬዎስ የሾክ
  አክሊልን በራሱ ላይ ደፋ ስለዚህ
  ቸርነቱና ትኅትናው ደግነቱን እንናገራለን'' .becose it completely replaces Jesus's salvation service with one person.Oh ,sirs u might be searching ways to confuse members of EOTC by such foolish and totally unbelievable notices.I guess this after observing yr source ,it is a book by one Pastor ''gedil woys gedel''.what is yr link with such groups having the name orthodox still with u?

  ReplyDelete
 5. ኦርቶዶክስMarch 31, 2011 at 1:14 PM

  Anonymous above, I suggest that you go and ask one of the church fathers you know and ask them to show you the book. The page numbers are referenced. what else do you want?

  ReplyDelete
 6. I asked a priest about this book, which he confirmed that it has been with the church for many years now. However, he said the book has never been approved by any theolegian of the church and is not taught among religious circles. He said the book was written by the debteras who use it while singing in the church. As you may know, the debteras are known for embarassing the church with many un-christian behaviors.

  The gist of my investigaion is two fold: (1) yes the book does exist in the EOTC churches; (2) however, it is not officially sanctioned by any theoloigian (I mean the well learned fathers excluding the Zebenes who are known for fabricating stuff to apparently defend whatever they find in the church) of the church and in fact most well-learned fathers of the church oppose the book. The EOTC priest whom I tlaked to despises that book and says it is the work of yemender debteras (neighborhood debteras) who know nothing about the doctrine of the church. He also gave examples of similar people who still write to this date wrong pieces and books, which the next generation could wrongly consider as the voice of the church.

  The conclusion that I have been able to reach after talking to the priest is that the EOTC is a church without any leader and true owner where anyone or group can insert some alien thing and claim to be that of the church. Very sad, right? The present generation has a lot to clean in order to save the coming generation from heretic things and assure the church's continued existence. It is important to note also that the church has golden pillars of faith despite some tainted writings and beliefs here and there. It only needs some clean up, not complete deconstruction. God help the true fathers who care for His words.

  ReplyDelete
 7. ኦርቶዶክስApril 1, 2011 at 7:17 AM

  Yared, you just nailed it. I agree with all of your findings and your assessment/conclusions. Indeed, we do have a beautiful church foundation with rich culture, but we definetely need the leadership to step up and clean up this kind of garbage from the church. Even though most theologians don't neccessarily accept the book of "Zeek", it is still used (on a daily basis) in all of our churchs. By the way the book of "Zeek" is just an example. The church needs to review all the books in the church and clean up as neccessary. Lots of garbage the enemy dumped in our beloved church.

  One important note: The theologians who speak up and say this book should be corrected or removed from the church are usually removed from their post, given a bad name, called Tehadeso etc or even tortured/beaten by some "Akrari" groups such as Mahbere Kidusan. This is the current fact on the ground. ያሳዝናል!

  ReplyDelete
 8. That is correct Ortodox. Mahbere kidusan would defend this kind of things to death. Bechfin! I have always wanted the mahbere to learn and shape its path, but now I just want it dissapear from this earh (for the sake of our church). MK members need to be rescured and freed from this 'tibtib'.

  ReplyDelete
 9. I see so much darkness in this blog.I feel so so sad when I read this blog. I don't know what to say. who ever has posted the blog should really really look at his/her self. at least guards give their lives and soldiers also do give their lives. that would have been enough common sense for the blog poster to dig more about the story of "Merkorewos" rather than such a far sighted and misleading post.

  well wot am I doing here.
  ciao

  ReplyDelete
 10. the real zik is not like that he purposely changed it to merkorios the real zik is like this
  "ንዜኑ አምላክነ ሂሩተ ትኅትና
  ወየውሐተ ዘተአገሰ በእንተ አፍቅሮተ
  ስብእ ዘሰቀሎ ለሰማይ ከመ ቀመር ዲበ
  ዕፅ ተሰቅለ።
  እናም እሱ ያደረገው አምላክነ በሚለው ፋንታ መርቆሬዎስ የሚለውን በመተካት በድፍረት ሰው አያውቅብኝም በማለት መሆኑ ግልጽ ነው። ዚቅ ማለት ለአውደ አመታትና በአላት ለየበአሉ የሚባል የዜማ አይነት ነው። በማህሌት ጊዜ ከሌሎች ጋር አብሮ የሚባል ዜማ ነው። እናም ይህን ዚቅ ሰው አያውቅብኝም ብሎ በተሳሳተ ሁኔታ ለመተርጎም በመሞከሩ በጣም ነው የሚያሳዝነው። ሰዉ የተሃድሶ መናፍቃንን መንገድ ሲገነዘብባቸው የኑፋቄ ስብከታቸውን አልቀበል ሲል አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ ኦርቶዶክስን ተመሳስሎ በመግባትና በውሸት ሰዉን ለመውሰድ ይሞክራሉ። እግዚአብሔር ደግሞ ለእነዚህ አይነት ሰዎች ያዘጋጀው ቅጣት እስኪመጣ ድረስ በቀናች ሀይማኖት ጸንተን ለመኖር ያብቃን። በሌላ አዲስ ትምህርት አትወሰድ ብሏልና ቅዱስ ጳውሎስ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሌላ ማንም ክርስቲያን ነኝ ባይ መጥቶ ሊያስተምር ሲሞክር በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስም የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡት ተጥንቀቁ እንዳለ ጌታ ውሸትን በማስተማር ከቀኖናና ከዶግማችን ሊያወጡን የሚሞክሩትን አሁንም ቢሆን እግዚአብሔር ልቦናን ይስጣቸው። ከንቱ ድካምን እየደከሙ ነው ያሉት ለምን ቢባል ጌታ እንዳለው የገሃነም ደጆች እንኳን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አይችሏትም ሊያፈርሷትም አይችሉም እንኳን አይደለም አንድ ተራ አጭበርባሪ ሰው ሊያፈርሳት ቀርቶ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

  ReplyDelete
 11. The zik says "amlakne" but he relpaced it "merkorios". It was suppost to be amlakne but he changed it to merkorios. May god pay your price for all the things you are doing. If it wasn't for his mercy you wouldn't live to write another falsley claimed orthodox teaching.

  ReplyDelete
 12. Ay egziabher behaymanotachin lay sichawetu Stet alk. Chernetih bezu new.

  ReplyDelete
 13. IT is suppost to be amlakne why did you change it to merkorios. you thought you could get away with it. Please why the false teaching. Why dont you try to explain truthfully why do you have to make up stuff. May god forgive you and call you back to the holy church of Orthodox Tewahedo.

  ReplyDelete