Thursday, April 7, 2011

መናፍቃን ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ያስገቡት የባዕድ አምልኮ ልምምድ - Read PDF

ቤተ ክርስቲያናችን ፊልጶስ ባጠመቀው ጃንድረባ አማካኝነት በኢትዮጵያ ከተመሠረተች በኋላ በአባ ሰላማ መሪነት እያደገች እየተስፋፋች መሄዷን፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን የሰሜን አፍሪካ መናፍቃን ወደ ኢትዮጵያ እየተሰደዱ መጥተው ልዩ ልዩ ባዕድ ነገሮችን ተክለውባት እንዳለፉ ታሪክ ይናገራል አሁን እያየን ያለነውም ይህንን እውነት ነው።

ለምሳሌ የጥንቆላ ሥራዎች በቤተ ክርስቲያን ሰዎች በስፋት ሲሰራባቸው ይታያል። ጥንቆላው የሰሎሞን ጥበብ እየተባለ ስለሚነገር ብዙ ሊቃውንት ተብለው የሚጠሩ ሰዎች የሚጠቀሙበት ነገር ነው። አቃቤ ርእስ፤ ግርማ ሞገስ፤ መስተፋቅር፤ መድፍነ ጸር፤ ወዘተ እየተባሉ የሚጠሩ ድግማቶች በቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት የሚዘወተሩ ናቸው። አሁን አሁን ደግሞ የገብያ፤ የፍቅር ተብለው ተሰይመው በዘመናዊ መሣሪያ እየታተሙ ለምእመናኑ እየተሰራጩ ነው።
በተጨማሪም ሕልመ ዮሴፍ፤ ምሕሳበ ቅዱሳን፤ ምህሳበ መላእክት የሚባሉ ድግማቶች አሉ እነዚህ ድግማቶች በስፋት የሚዘወተሩት በባሕታውያኑ ነው። 
ሕልመ ዮሴፍ የሚደገመው አንድ ሰው እጣ ፋንታውን ለማወቅ በሚፈልግበት ጊዜ ባሕታዊ ወይም መነኩሴ ወይም መናኝ ወደ ተባለው ሰው ሄዶ ጸልይልኝ ሲለው ባሕታዊው ሕልመ ዮሴፍን በጠያቂው ስም ደግሞ ሲተኛ ስለ ሰውየው ሕልም ይታየዋል ይባላል። ይህ በብሕትውና ስም የተሸፈነ ጥንቆላ መሆኑ ነው።
ምሕሳበ ቅዱሳን የሚባለው ድጋም ደግሞ የሞቱ ቅዱሳንን ለማናገር የሚደገም ነው። ይህን ድግማት ለመድገም ብዙ ውጣ ውረድ አለው። በመጀመሪያ ውርሻ መዋረስ አለበት፤ ከሴት መራቅ አለበት፤ ሁልጊዜ ሽቶ አይለየውም፤ ሥጋም መብላት የለበትም። ይህ ሙታንን የማናገር ሥራ በባሕታውያን የሚዘወተር ነው። እግዚአብሔር ግን ሙታንን መሳብ ርኩሰት መሆኑን አስቀድሞ ተናግሯል።


"አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ"  ዘዳ 18፥11።

በቤተ ክርስቲያናችን ሥር የታቀፈው ምእመን በነዚህ ደጋሚዎች ምክንያት ከመጣበት የመንፈስ እሥራት ላማላቀቅ ከባድ መስዋዕትነት ይጠይቃል።
ብዙ የመናፍስትን ሥራ የተለማመዱ ወገኖች መርጌታ፤ ደብተራ፤ ሊቅ፤ የሚለውን ስም በመያዝ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ስለሆኑ አምልኮተ እግዚአብሔር ከአምልኮተ ባዕድ ጋር ተቀላቅሏል። ዝማሬው፤ ማህሌቱ፤
ጸሎቱ፤ ስግደቱ፤ ስእለቱ ባዕድ ነገር የተቀላቀለበት ስለሆነ መጥራት አለበት።

ለምሳሌ ጸሎቱን ብንመረምረው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ሆኖ እናገኘዋለን።
ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ማለት ነው፤ ከመላእክት፤ ካረፉ ቅዱሳን፤ ከማርያም ጋር መነጋገር ማለት ግን አይደለም።  እግዚአብሔርን የምናመልከው በጸሎት አማካኝነት ነው። በአምልኳችን ጊዜ ወደ መላእክትም ወደ ማርያምም የምንጸልይ ከሆነ እነርሱንም እያመለክን ነው። ጸሎት እራሱ አምልኮ ነው።

ጌታ ስለጸሎት ሲያስተምር "በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ ስምህ ይቀደስ መንግስትህ ትምጣ..." በሉ ብሎ የጸሎታችንን አቅጣጫ አሳይቶናል። በማቴ 6፥6 ላይ በሥውር ላለው አባትህ ጸልይ በሥውር የሚያይ አባትሕ በግልጥ ይከፍለሃል። በማለት  በሥውር ላለው አባታችን እንድንጸልይ በግልጥ አስተምሮናል።

ሐዋርያትም "በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምሥጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ" ሲሉ አስተምረዋል ፊልጵ 4፥6። ልመናችንን ማስታወቅ ያለብን፤ ጸሎትና ምልጃ ፤ ምሥጋና የሚቀርበው ለእግዚአብሔር ነው፤ የሚያስጨንቀንንም የምናስታውቀው ለጌታ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ የምናውቃቸው ቅዱሳን ነቢያት አባቶች ሁሉ ጸሎታቸው ወደ እግዚአብሔር ነበር፤ ኃጢተኞች እንኳ ሲጸልዩ የኖሩት ወደ እግዚአብሔር ነው። ምክንያቱም ጸሎትን ሊሰማ የሚችለው በሁሉ ሥፍራ የሚገኝ ሁሉን የሚችል ሁሉንም የሚሰማ እግዚአብሔር ብቻ ስለሆነ ነው።

በኛ ቤተ ክርስቲያን ግን ወደ መላእክት፤ ወደ ማርያም ፤ ወደ አረፉ ቅዱሳን ይጸለያል። ድርሳነ ሚካኤል፤ ድርሳነ ገብርኤል፤ ወደ መላእክት የሚጸለዩ ጸሎቶች ናቸው፤ የሰኔ ጎልጎታ፤ መልካ ማርያም፤ የህሊና ጸሎት፤ መጽሐፈ ሰዓታት ወዘተ ወደ ማርያም የሚጸለዩ ጸሎቶች ናቸው። በጠቅላላው መልካ ጉባኤ የሚባለውን ትንሣኤ ዘጉባኤ እና ተስፋ ገብረ ሥላሴ የሚያሳትሟቸውን እየተጠረዙ የጸሎት መጽሐፍ ተብለው ለሕዝብ የሚከፋፈሉትን ድርሰቶች ሁሉ ብናስተውላቸው ባዕድ አምልኮ የተሞላባቸው፤ ነውር የበዛባቸው፤ በመናፍስት ጠሪዎችና በሙታን ሳቢዎች የተደረሱ ናቸው።

 ሕዝቡ እነዚህን ጸሎቶች ጀምሮ መተው ወይም ማቋረጥ፤ መቅሰፍትን ያመጣል ተብሎ ስለሚነገረው በመንቀጥቀጥና ብዙ ሰዓት በመቆም ቢደክመው እያዛጋ በግድ ሳይወድ ይጨርስዋል። በትራስህ ስር አርገው፤ ባንገትህ አንጠልጥለው ስለሚባል ብዙ የጸሎት መጽሐፎች በምመናን አንገትና በየግድግዳው ተንጠልጥለው ይገኛሉ።

ወደ ማርያም የሚጸለዩ ጸሎቶች

"እግዝእትነ ማርያም አዕርጊ ጸሎተነ ወአስተስርዒ ኃጢአተነ ቅድመ መንበሩ ለ እግዚእነ" ትርጉም፦ "እመቤታችን ማርያም ሆይ ጸሎታችንን አሳርጊልን፤  በጌታችን መንበር ፊት ኃጢአታችንን አስተስርይልን"

እመቤታችንን ጸሎታችንን አሳርጊልን ስንል ምን ማለታችን ነው? እግዚአብሔር ጸሎታችንን አልተቀበለውም ማለት ነው? በእምነት የምንጸልየውን ሁሉ እግዚአብሔር በቀጥታ እንደሚቀበለው መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል። እመቤታችን ተቀብላ እንደምታሳርገው የሚናገር የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ግን የለም። በሌላ ጊዜ ደግሞ "መላከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰዓል ወጸሊ በእንቲያነ አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ አቢይ" ትርጉም "የሰላማችን መላክ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ሆይ ስለኛ ጸልይ ለምን ጸሎታችንንም በጌታችን መንበር ፊት አሳርግልን" በማለት እንቀባጥራለን።

ማርያምን አሳርጊልን ስንል መቆየታችንን እረስተን እንደገና ሚካኤልን አሳርግልን እንላለን አንዱን ሥራ ለሁለት መስጣችን ይሆን? አብሾ ባሳበዳቸው ደብተራዎች የተደረሰ በመሆኑ ግራ የሚያገባ ባዶ ቃላት ነው።   

ኃጢአታችንን አስተስርይልን የሚለውም የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት የሚቃወም ነው። ኃጢአት የሚሰረየው ንስሐ ስንገባ እና በጌታ ፊት ወድቀን ይቅርታ ስንጠይቅ ብቻ ነው፤ ማርያም ግን ኃጢአትን እንደምታስተሠርይ የሚናገር የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፈጽሞ የለም። እኛ ማርያምን እንድታማልደን እንጠይቃታለን እንጂ ወደ እሷ አንጸልይም እያሉ የሚከራከሩ የቤተ ክርስቲያናችን መናፍቃን "ከአዳኝ አውሬ ታድኝን ዘንድ ተማጽነንበሻል ስለ አባታሽ ስለ ሃና ብለሽ ስለ እናትሽ ስለ ኢያቄም ብለሽ" የሚለው የማን ጸሎት ነው? እዚህ ላይ እመቤታችንን "አድኚን" በማለት ደብተራዎቹ አዳኝ አድርገዋታል፤ መዳንም በሌላ በማንም የለም የሚለውን ቃል ፈጽመው ክደውታል

በታሕሳስ ገብሬል ዚቅ ላይ ደግሞ "አድህነኒ ዘአድሃንኮሙ ሊቀ መላእክት" እያልን ስንጸልይ እናድራለን። አዳኝ እግዚአብሔር ነው ነገር ግን ራሱ እግዚአብሔር  በመላእክ ወይም በሌላ ሊያድነን ይችላል፤ እግዚአብሔርን ትቶ ገብሬልን አድነኝ ሲሉ ማደር ግን ትልቅ ክህደት ነው።

ይቀጥላል

ዲያቆን ሉሌ   

16 comments:

 1. "Deacon" Lule,

  You started well, but you went south into hell after a while. You don't have to claim to be a deacon to be credible... it did not take me long to know you who you are... what does the following mean?

  "በኛ ቤተ ክርስቲያን ግን ወደ መላእክት፤ ወደ ማርያም ፤ ወደ አረፉ ቅዱሳን ይጸለያል።"

  Yes, we pray to St Mary adn all the other saints. So do all the rest of the Christians in the world, except Protestants. Please don labor much hoping you could separate us from our most beloved Mother and the saints. Yes, our chuch has numerous problems, but praying to St. Mary has never been our problem and will never be. St. Mary is so close to our heart and nothing can separate us from Her... We, all Orthodox Christians, pray day and night to Her seeking Her intercession and motherly love...

  You will not succeed to destroy our church in the name of reform and clean up... You would have done a great job if you had continued like you started condemning the tinkola and satanic degimt...

  I love this prayer. In fact, i pray it every time and all the time..

  "እመቤታችን ማርያም ሆይ ጸሎታችንን አሳርጊልን፤ በጌታችን መንበር ፊት ኃጢአታችንን አስተስርይልን"

  love it...love it...love it.

  ReplyDelete
 2. yaltadele tiwlid Tinte Telatun seyTanen tito keqidist dingile mariam gar yitagelal! St. Mary is our mother; she is given to us on Qeranyo through ‘Yohannes’. We know she is our mother those of you who do not believe in that just leave her; you are losers she do not loss anything she is the mother of Jesus Christ. Can you please try to struggle with devil ‘Tinte Telat Diablos’ if you are true Christian, you do not need to struggle with ‘ye-amlak enat’. Your father gave you good assignment that can never been done so you will n ever have time to straggle with him. Yemtazazinu fitretoch.

  ReplyDelete
 3. The above two folks: You guys are expressing only empty frustrations based on what you were told growing up. The writter is claiming specific things and he is agruing based on the Bible. Why don't you instead provide Biblical references to what you are talking about? It is very clear that you both don't even read the Bible that much. Just empty rethoric! come on! let's grow up. Instead of just exprressing your empty emotions, ask the scholars, read your Bible, take some time to think, and provide evidence based answers to the claims the writter is providing. I don't neccessarily agree with everything the writter is saying, but hey he makes good points, so I need to read and ask to be able to confirm his claims. Let's be good thinkers. God gave us all beautiful brains to ask and think.... God bless

  ReplyDelete
 4. the above anonymous ,who are the scholars that you and me should ask? are they pastors like Dniel,TOLOSSA OR DAWIT?
  KEMIDIR BELAY LELA HIWOT ENDALE AMNALEHU EYALE KIDUSAN GIN KEMOTU BEHUALA(SOME ALSO SAY BEFORE) MUTAN NACHEW BILO KEMINAGER TIWILD BEWNET AMLAK YISEWREN!
  I like view of the writer on Tinkola,Digmt and other odd worishepings but later the bad failure follows.what makes me amazed is the source of this tinkola and digmt you mentioned? is it the Copt church(North Africa?)?

  ReplyDelete
 5. ''ማርያምን አሳርጊልን ስንል መቆየታችንን እረስተን እንደገና ሚካኤልን አሳርግልን እንላለን አንዱን ሥራ ለሁለት መስጣችን ይሆን? አብሾ ባሳበዳቸው ደብተራዎች የተደረሰ በመሆኑ ግራ የሚያገባ ባዶ ቃላት ነው። '' were you really an active member of our church ?if so ,you could at least know what is needed to mean by this 2 ideas whether you believe on the content(praying to saints) or not.you are asking the question that Lutherans always ask in the streets,LEMEHONU GIN ''BETECHRISTANACHIN''YETGNAWN NEW?

  ReplyDelete
 6. Guys, don't get all emotional. Even though we try to make this a sensitive issue, it is really not. እኔ ለምሳሌ እመቤታችንን እና ሌሎችንም ቅዱሳን አከብራለሁ እወዳለሁ ግን እነሱን በቀጥታ እንዲህ አድርጉልኝ ብየ ጠይቄ አላውቅም። ለምን? እግዚአብሔር በነሱ በኩል ካልመጣህ አልቀበልህም አላለማ። እንዲያውም ልጆች ናችሁ ተብለናል እኮ። ልጆችም ስለሆናችሁ ወራሾችም ናችሁ ይላል ሐዋርያው። ስለዚህ እኔ አባቴን አነጋግረዋለሁ እስካሁን የከለከለኝ ነገር የለም፤ የሚያስፈልገኝን ሁሉ እያደረገልኝ እኖራለሁ። በዚህ አመቤታችንም ሆነች ቅዱሳን ቅር ይሰኛሉ ብዬ አላምነም። አይ እኔ በእመቤታችንና በቅዱሳን በኩል ካልሆነ አምላኬ ሊሰማኝ አይችልም የምትሉ ሰዎች ከአምላካችሁ ጋር የተዛባ ግንኙነት ነው ያላችሁ ብየ ነው የማምነው። ከአምላካችን ጋር ያለን ግንኙነት እኮ የልጅ እና የአባት እንጂ፥ የጌታና የባሪያ አይነት አይደለም።

  ለምሳሌ ከላይ እንደተባለው በሰኔ ጎልጎታ ጸሎት መጽሐፍ ላይ፦ ሰለ እናትሽ ስለ ሐና ብለሽ ስለ አባትሽ ስለ ኢያቄም ብለሽ ከአዳኝ አውሬ አድኝኝ ብለን እንድንጸልይ ተጋብዘናል። እግዚአብሔር ጋር ለመድረስ፥ ክርስቲያኖች - ሐና እና ኢያቄም - አመቤታችን - እግዚአብሔር። Of course the most efficient ways is Christian - God. So if it works for you to go through all those steps to get to God, go for it. For me, that's not how it works. I have a very close relationship with my God!!! He loved me to the corss, I love him back. He said I am his son, and I gladly accept his fatherhood. So I say let's not fight with this topic. Not worthit.

  God bless,

  ReplyDelete
 7. Dear Owner of the blog, here is my reply to your question የተሰማዎትን እንዲገልጹ እንጋብዛለን

  When I read the articles in this blog, It reminded me of the former protestants of 1978 - 1985 around Addis and more over it has given me a very good introduction as to
  1. who you are
  2. what you thought process is
  3. what you believe in
  4. what your strategy is
  5. what your plans are for the Orthodox Tewahido Church

  To all who view this website, to the owner and all bloggers or commenters.
  Just 1 question.
  We are keeping the teachings and beliefs of all the Golden fathers on top of this website. Except His Grase Abune Melketsedik most of them have passed and they are in the truth place by now.
  The Only remainig , alive and active is His Grace Abune Melketsedik - I wish him all the best. We will keep what they have thought us and no problem so far.
  Shall we conclude he also accepts and believes in what you are writting on this blog ?

  ReplyDelete
 8. Please get educated before you speak on issues like your raise here. Well it is not your fault. Dinkurena negesual in our beloved country. kenferachewin besemaye liye anoru, milasachewinim be midir lie awelebelebu lilal. Kidusan kal didan alachew. Enkuwan kidusan, kesoch bemidir yaserachehut besimaye tetasere yihun yalew siltan alachew....which means hatiyat mastesereye yechilalu. Gin anegebabam....first you have to get educated. mastewalun yestih

  ReplyDelete
 9. በትላልቅ ሰዎች ስም ብሎግ ከፍቶ ከሃይማኖታችን ውጭ የሆነ አስተምህሮ ፖስት ማድረግ እጅግ አሳፋሪ ነው።
  እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ።

  ReplyDelete
 10. አባ ሰላማን ታውቁአቸዋላችሁ? እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ ያላቸው አልነበሩም።
  የበግ ለምድ ለብሰው ... የተባለ ለእናንተ መሆኑን ልብ በሉ።
  ከመቼ ወዲህ ነው ቤተ ክርስቲያናችን እንደዚህ አይነት ትምህርት ማስተማር የጀመረችው?
  ታሳዝናላችሁ።
  በዮሐንስ ራእይ ላይ የተገለጸውን ልብ በሉት።
  ዘንዶው ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።
  ዘንዶው ማን ነው? እናንተ አይደላችሁምን?
  ______________የዮሐንስ፡ራእይ፥ምዕራፍ፡12።______________
  ምዕራፍ፡12፤
  1፤ታላቅ፡ምልክትም፡በሰማይ፡ታየ፡ፀሓይን፡ተጐናጽፋ፡ጨረቃ፡ከእግሮቿ፡በታች፡ያላት፡በራሷም፡ላይ፡የዐሥራ፡
  ኹለት፡ከዋክብት፡አክሊል፡የኾነላት፡አንዲት፡ሴት፡ነበረች።
  2፤ርሷም፡ፀንሳ፡ነበር፥ምጥም፡ተይዛ፡ልትወልድ፡ተጨንቃ፡ጮኸች።
  3፤ሌላም፡ምልክት፡በሰማይ፡ታየ፤እንሆም፡ታላቅ፡ቀይ፡ዘንዶ፤ሰባት፡ራሶችና፡ዐሥር፡ቀንዶችም፡ነበሩት፡በራሶ
  ቹም፡ላይ፡ሰባት፡ዘውዶች፡ነበሩ፥
  4፤ዥራቱም፡የሰማይን፡ከዋክብት፡ሢሶ፡እየሳበ፡ወደ፡ምድር፡ጣላቸው።ዘንዶውም፡ሴቲቱ፡በወለደች፡ጊዜ፡ሕፃኗን
  ፡እንዲበላ፡ልትወልድ፡ባላት፡ሴት፡ፊት፡ቆመ።
  5፤አሕዛብንም፡ዅሉ፡በብረት፡በትር፡ይገዛቸው፡ዘንድ፡ያለውን፡ልጅ፡ወንድ፡ልጅ፡ወለደች፤ልጇም፡ወደ፡እግዚአ
  ብሔርና፡ወደ፡ዙፋኑ፡ተነጠቀ።
  6፤ሴቲቱም፡ሺሕ፡ከኹለት፡መቶ፡ስድሳ፡ቀን፡በዚያ፡እንዲመግቧት፡በእግዚአብሔር፡ተዘጋጅቶላት፡ወደነበረው፡ስ ፍራ፡ወደ፡በረሓ፡ሸሸች።
  7፤በሰማይም፡ሰልፍ፡ኾነ፤ሚካኤልና፡መላእክቱ፡ዘንዶውን፡ተዋጉ።ዘንዶውም፡ከመላእክቱ፡ጋራ፡ተዋጋ፥አልቻላቸ ውምም፥
  8፤ከዚያም፡ወዲያ፡በሰማይ፡ስፍራ፡አልተገኘላቸውም።
  9፤ዓለሙንም፡ዅሉ፡የሚያስተው፥ዲያብሎስና፡ሰይጣን፡የሚባለው፡ታላቁ፡ዘንዶ፡ርሱም፡የቀደመው፡እባብ፡ተጣለ፤
  ወደ፡ምድር፡ተጣለ፡መላእክቱም፡ከርሱ፡ጋራ፡ተጣሉ።
  10፤ታላቅም፡ድምፅ፡በሰማይ፡ሰማኹ፡እንዲህ፡ሲል፦አኹን፡የአምላካችን፡ማዳንና፡ኀይል፡መንግሥትም፡የክርስቶ
  ስም፡ሥልጣን፡ኾነ፥ቀንና፡ሌሊትም፡በአምላካችን፡ፊት፡የሚከሳቸው፡የወንድሞቻችን፡ከሳሽ፡ተጥሏልና።
  11፤እነርሱም፡ከበጉ፡ደም፡የተነሣ፡ከምስክራቸውም፡ቃል፡የተነሣ፡ድል፡ነሡት፥ነፍሳቸውንም፡እስከ፡ሞት፡ድረ ስ፡አልወደዱም።
  12፤ስለዚህ፥ሰማይና፡በውስጡ፡የምታድሩ፡ሆይ፥ደስ፡ይበላችኹ፤ለምድርና፡ለባሕር፡ወዮላቸው፥ዲያብሎስ፡ጥቂት
  ፡ዘመን፡እንዳለው፡ዐውቆ፡በታላቅ፡ቍጣ፡ወደ፡እናንተ፡ወርዷልና።
  13፤ዘንዶውም፡ወደ፡ምድር፡እንደ፡ተጣለ፡ባየ፡ጊዜ፡ወንድ፡ልጅ፡የወለደችውን፡ሴት፡አሳደዳት።
  14፤ከእባቡም፡ፊት፡ርቃ፡አንድ፡ዘመን፥ዘመናትም፥የዘመንም፡እኩሌታ፡ወደምትመገብበት፡ወደ፡ስፍራዋ፡ወደ፡በ
  ረሓ፡እንድትበር፡ለሴቲቱ፡ኹለት፡የታላቁ፡ንስር፡ክንፎች፡ተሰጣት።
  15፤እባቡም፡ሴቲቱ፡በወንዝ፡እንድትወሰድ፡ሊያደርግ፡ወንዝ፡የሚያኽልን፡ውሃ፡ከአፉ፡በስተዃላዋ፡አፈሰሰ።
  16፤ምድሪቱም፡ሴቲቱን፡ረዳቻት፥ምድሪቱም፡አፏን፡ከፍታ፡ዘንዶው፡ከአፉ፡ያፈሰሰውን፡ወንዝ፡ዋጠችው።
  17፤ዘንዶውም፡በሴቲቱ፡ላይ፡ተቈጥቶ፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዛት፡የሚጠብቁትን፡የኢየሱስም፡ምስክር፡ያላቸው
  ን፡ከዘሯ፡የቀሩትን፡ሊዋጋ፡ኼደ፤
  18፤በባሕርም፡አሸዋ፡ላይ፡ቆመ።

  ReplyDelete
 11. Realy, you are correct Mihretab
  Thank you

  ReplyDelete
 12. Weshetamoche menefeqan enanete setesadbu rasacehuneme attbequ swenme atasetbequ doketre erswo manot lgdamu mthfe sche yraswa siyarbate yswe tamaselalche alu ymnafesete mchfriya honwe ymmeenedy ytotbytwo adamtu bytblu ymilflefutene ganel wdaortodox ytmlsutene memnane ereswome 1-7 yaseflegewotale telu ewntu enedigltelwo

  ReplyDelete
 13. First of all may God help us all.I don't have deep knowledge but I know this I believe in God.I know saint Mary is my Mom.I don't worship Saint Mary but I adore and love her.She belongs to God.
  correct me if I am wrong

  14፥12 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥

  So she can do what ever you ask her to do but ከእርሱዋ የተነሳ ሳይሆን ከእግዚያብሄር የተነሳ ነው.I think you got that wrong.

  It is a very simple logic.simple example,lets say u want something from ur dad u can ask him directly or u can ask him through ur mom what is wrong
  with it? please it is better የኑፋቄ ትምህርት ባታስፋፋ.
  There are peoples who make it like they worship Saint Mary or other saints apart from God.That is individual problem.That is nothing to do with our church's teaching about saint Mary.I think You should work on that.

  Generally,either you are not from our church or you didn't understand it well.u almost got me.

  የሉቃስ ወንጌል 17፥2 ከእነዚህ ከታናናሾች አንዱን ከማሰናከል ይልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይጠቅመው ነበር። ይህ ለናንተ እንዳይሆን ተጠንቀቁ።

  ReplyDelete
 14. ከአክሱም ስርወ መንግስት ጀምሮ ክርስትና( ኦርቶዶክስ) የሃገሪቱ ዕምነት የነበረ ሲሆን ደርግ የዚህን ሃይማኖተ-ስርወ መንግስት አንኮታኩቶ ወደመቃብር ከትቶታል፡፡ ይህ የሆነው የደርግ ፍቃድ ስለሆነ ሳይን የእግዚአብሄር መልካም ፍቃድ ስለሆነ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የክርስትያን ደሴተ ነች እየተባለ ሲለፈፍ ለዘመናት የኖረ ታሪክ ቢሆንም ዘሬ ግን የሁሉም ሃይማኖት ደሴት ነች፡፡ የሃገራች ቅድመ ክርስትና ቤተ- ዕምነቶች የነበሩ - አምልኮተ-በአደ (pagans)፤ አምልኮ-ኦሪት (Judaism) ስፍራቸውን ለወንጌልና ለክርስትና ከመልቀቃቸው በፊት ኢትዮጵያ ደሴታቸው ነበረች፡፡ ለዘመናት (theocratic state) የነበረችና ንጉሶቿ ካህን የነበሩ ይቀድሱም ደም ያፈሱም የነበሩ በሁለት ቢላ የሚበሉ ፍጥረታት ነበሩ፡፡ በርግጥ የማይታበል ሃቅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ለዚህች ሃገር ክርስትና ማበብና ማንሰራራት ትልቁን ሚና ብትጫወትም፡፡ ብዙ የዚህች ቤተ-ክርስቲያን ሊቃውንት በዕምነት ደረጃ አንቱ የተባሉ ስራዎችን እንደቅርስ ጥለውልን ያለፉ ሲሆን፡፡ የኑፋቄና የተረት አባት የሆነው አጼ ዘረያቆብ በቤተክርስቲያኒቱና በወንጌል ላያ የዘራው የፀረወንጌል ዘር ዛሬ ፍሬው ተራብቶ አንክርዳድ ሆኖ በየደብሩና በየገዳሙ እንደ ቫይረስ ተሰራጭቶ ሰውን ሁላ ወንጌልን ሳይሆን ገድልና ድርሳናት በኑትን ተረቶች እያጠመቁ ሁሉን ቻይ ከሆነው ጌታ እየሱስ አቆራረጡት፡፡ በባህል እና በትውፉት ታውረው ወደእውነት ላለመቅረብ ራሳቸውን በክህደት ሰንሰለት አስረው በርካታየጠፉ ትውልዶች ሆነው ሌሎችንና አሳውረው የጋህነም ፍርደኞች የሰይጣን ምርኮኛችና እስረኞች አድርገዋቸል፡፡ እስኪ እውነት እንነጋገር ዛሬም በሰለጠነ ዘመን የሰው ልጅ ማንበብና ማፃፍ በሚችበትና ነገሮችን በቅጡ ማገናዘብ በሚችልበት ሂደት መፅሃፍ ቅዱስን ማንበብ ሲችል ደበተራዎች የሚሉትን እየሰማ ራሱን ወደ አዘቅጥ እየከተተ ይገኛል፡፡ አባቶቻችን መስማት እንጅ ማንበብ ሳይችሉ በሌሎች ተነድተውና ተገፍተው የገሃነም እራት ሆነዋል፡፡ ዛሬም ሰው መፅሃፍ ቅዱስ ሲያነብ ሲታይ መናፍቅ ይባላል፡፡ ትልልቅ የዳውት፡ የአዋልድ፡ የድግምት መፅሃፍትን ባደገደጉት ነጠላ ስር ይዞ ሲሄድ ያወቀና የፀደቀ ይመስለዋል፡፡ ይህ የፈሪሳው ተገረባር ወደ ሞት እንጂ ወደ እግዚአብር መንግሰተ ያማይወስድ ሰፊውና የአጋንንት መንገድ ነው፡፡ ይህ ህዝብ የጌታ እየሱሰ ጠላት እሰከመቼ እነደሚሆን አይገባኝም፡፡ ግንብ በመሳምና በየገዳሙ በመዞር የዳነና እውነትን ያገኘ እየመሰለው የሚኮፈስ እየጠፋ ፤ ጠባቂ የሌለው መንጋ ነው፡፡ መዳን በማንም የለም እነድንበት ከሰማይ በታች የተሰጠን ስም ጌታ እየሱስ ስለመሆኑ ተገለፃ ሳለ ዛሬ ግን በየታክሲውና በየመንገዱ ላይ ‹‹ያለማሪያ አማላጅነት ዓለም አይድንም›› ተብሎ ይለፈፋል፡፡ ይህ እርኩሰት ነው፡፡ ያለማወቅና የመታወር ምልክት ነው፡፡ ይህን ክፋትና እርኩሰት ያመጣውን ሰው ጌታ ይቅር ይበለው፡፡ ለሌሎች እግዚአብሄር አይናቸውን ያብራላቸው፡፡ የአምካችንን የጌታችንን የእየሱሱን ስምና ዝና ዝቅ የሚያደርግ ራስንም ለጥፋትና የሚያጋልጥ ተግናር ነው፡፡ ቅድሰት ድንግል ማሪያምም ያለችው ‹‹እርሱን ስሙት›› አለች እንጂ ስለሷ ክብርም ምምን አልተናገረችም፡፡ ለቅድሰት ድንግል ማሪያምም ክብር መስጠት እናዳለብን ብናውቅም የአምላክ ያህል ክብር ሊሰጣት ግን ተገቢ አይደለም፡፡ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላካችን እግዚአብሄር አይናቸው ለታወረው ወገኖች ልቦና ይሰጣቸው አንድ እፀልያለሁኝ፡፡
  መፅሃፍ ሲናገር ልእግዚአብሄር አምላክህ ብቻ ስገድ ተብሎ ተፅፎ ሳለ የሚሰገድላቸው አማልክት ብዛታቸው ለቁጥር ይታክታሉ፡፡ ዛሬ ገንዘብ አነፍናፉዎች በየማስታወቂያውና፤ በየታክሲው አውቶቢስ ውስጥ ወደዚህ ገዳም እንወስዳን እያሉ እነሱ ኪሳቸውን እያደለቡ ሌሎችንን ወደሞት ቀጠሮና እውነት ወደማይገኘበት ቦታ እየወሰዱ ህይወታቸውን ይቀጥፋሉ፡፡ እስቲ እውነት እንነጋገር በየቤታችንን ስንቶቻችን ነን መፅሃፍ ቅዱስን ታራስ አድርገንና ሸፍነን እሰቀምጠን ስንታመምም እና የተለከፍን ሲመስለን እያወጣን የንምሳለመው፡፡ ይህ ነው እንዴ እምነት?! ይገርማል! ምናለ እውነትን በቃሉ ውስጥ መርምረው በደረሱበት!
  ህዝቡን በባእትና በእመነት ስም የፊጥኝ ይዘውት ወይ አይሰሩ ወይ አያሰሩት፡፡ መንግስት ልማት በሎ ኢነሳ ገዳም ተደፈር በሎ እሪ ጠንቧ ማለት ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው፡፡ ህዝቡን በመተትን በድግምት በደብተራዎች አስማት ይዘውት ወደኋላ እየጎተቱት እዳይራመድና ከሌላው አለም እኩል እናዳይድ በማድረግ ወደሃላ አስቀርተውናል ጌታ እግዚአብሄር ይቅር ይበላቸው፡፡ አእምሮ እንዲሰጣቸው እንፅልይ፡፡

  ReplyDelete
 15. ደብተራ ው ዲያቆን ሉሌና AnonymousOctober 5, 2012 at 3:27 AM የኛ ካድሬዎች የኑፋቄና ገንዘብ አነፍናፉዎች የተረት አባቶችበዮሐንስ ራእይ ላይ የተገለጸውን ልብ በሉት።
  ዘንዶው ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።
  ዘንዶው ማን ነው? እናንተ አይደላችሁምን?:-
  ታሳዝናለህ የሰው ልጅ ማንበብና መፃፍ በሚችበትና ነገሮችን በቅጡ ማገናዘብ በሚችልበት በሰለጠነ ዘመን ምነው

  እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥ አንበብ

  ከእነዚህ ከታናናሾች አንዱን ከማሰናከል ይልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይጠቅመው ነበር::
  ፤ዘንዶውም፡በሴቲቱ፡ላይ፡ተቈጥቶ፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዛት፡የሚጠብቁትን፡የኢየሱስም፡ምስክር፡ያላቸውን፡ከዘሯ፡የቀሩትን፡ሊዋጋ፡ኼደ፤፤በባሕርም፡አሸዋ፡ላይ፡ቆመ።

  ReplyDelete
 16. Aye mhiret Ab ye'ab mihret endesemih yehunleh enji adagn geta becha yemesema geta becha. esti anet yewnet ye'bitkiresetiyan leg kehon yen'yohanes aforken mesehaf aneben ye'haymanot abwen mesehaf anebeb ahun le'birr blew geta eyshefenu degemet yemisterutn metetegna debetera yemeseretat eko adelechem ortodox yewent yemet kireteyan leg kehon geta yalewen adereg geta memechaw deresal ayekrem ened pawoles balmawek getan eyasadedachu new anetena mesleachu mahebere kesusan. "geta gen lezelalem yaw new" masetwal testen

  ReplyDelete