Thursday, April 14, 2011

የማህበረ ቅዱሳን አባላት ወደ መቂት ወረዳ የተንቀሳቀሱት ለስብከተ ወንጌል አልነበረም Read PDF

የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ መላከ ብርሃን ፈንታው አማረ፤ የማህበረ ቅዱሳን ጸሐፊ አቶ አወቀ አዱኛ፤ መምህር ተክለ ወልድ እና የሀገረ ስብከቱ  ሹፌር ቄስ ሞላ የመኪና አደጋ ደርሶባቸው ከዚህ ዓለም በሞት መሰናበታቸውን ሰምተን አዝነናል እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር። ነገር ግን ማህበረ ቅዱሳን በዜናው ገጽ ለስብከተ ወንጌል ተንቀሳቅሰው ባለበት ሕይወታቸው አለፈ ብሎ የዘገበው ዘገባ ከእውነት የራቀ ነው።
ሰዎቹ የተንቀሳቀሱት ወንጌል ለመቃወም እንጂ ወንጌልን ለመስበክ አልነበረም። በተለይም ስራ አስኪአጁ ፈንታው አማረ ዋና የወንጌል ተቃዋሚ ነበሩ።
ነገሩ እንዲህ ነው፤ በመቂት ወረዳ ተሃድሶዎች ተስፋፍተዋል የሚለውን ወሬ ተከትለው ለወንጌል ታጥቀው የተነሱ ወንድሞችን ለማሳጣት እና በሕዝብ ፊት ለመክሰስ ብሎም ከሥራ ለማባረር ነበር ይሄዱት። እነ ዳንኤል ክብረት እና ዘመንድኩን በጀመሩት ወንጌልን የመቃወም ፕሮግራም ውስጥ የታቀፈ እንቅሥቃሴ ነበር። በመቂት ወረዳ ሄደው ሲያደርጉ የዋሉትም በአካባቢው የሚገኙ ካህናትን ስም በመጥራት በቪዲዮ የተደገፉ የወንጌል እንቅሥቃሴዎችን ለሕዝብ በማሳየት ወንድሞችን ሲከሱ እና ኢየሱስ ክርስቶስን ሲቃወሙ ወንጌልን ሲያጣምሙ ነበር የሰነበቱት። በሕዝቡ ላይ ሽብር እና ፍርሐት ዘሩ እንጂ ሕይወቱን የሚያንጽ እውነተኛውን የእግዚአብሔር ቃል አላሰሙትም ነበር። በዚህ የማህብረ ቅዱሳን ድርጊት ወንድሞችና አባቶች እጅግ የመረረ ኃዘን እና ጸሎት ላይ እንደነበሩ ምንጮች አስረድተዋል። እነዚህ ተቃዋሚዎች ወንድሞቻችን ነበሩ ነገር ግን እግዚብሔርን የሚያገለግሉ መስሎአቸው ወንድሞችን ሲያዋርዱ እና ወንጌልን ሲቃወሙ ሰነበቱ፤ ይህ ባለማወቃቸው የሚያደርጉት ስለሆነ "አባት ይቅር እንዲላቸው እንለምናል"
ነገር ግን የማህበረ ቅዱሳን አባላት ይህ ተግጻጽ እና ትምህርት ሆኗቸው ንስሐ ሊገቡና ኢየሱስ ክርስቶስን ከመቃወም ሊታቀቡ ይገባል "የመውጊያውን ብረት ብታቀወመው ባንተ ይብስብሓል" ተብሏልና። ሐዋርያው ጳውሎስ ወንጌልን ሲሰብክ በርያሱስ የተባለው ጠንቅዋይ በተቃወመ ጊዜ የወደቀበትን ጨለማ ከሐዋርያት ሥራ እናነባለን፤ ሄሮድስም ለጌታ ክብርን ስላልሰጠ የጌታ መልአክ መጥቶት በትል ተበልቶ ሞቷል። ይህ የእግዚአብሔር ታምር መደበቅ የለበትም። ለትምህርት እና ለተግሣጽ ይሆነን ዘንድ ሰዎች የተገሠጹበት እውነተኛ ታሪክ መውጣት አለበት።
እግዚአብሔርን ልንፈራ ይገባናል ያገለገልነው እየመሰለን እየተቃወምነው እንገኛለንና እንጠንቀቅ።
ማህበረ ቅዱሳን ስለሞቱ ወንድሞቻችን የዘገበውን ከድረ ገጹ ያንቡ

ከታዛቢው

7 comments:

 1. enante tehadiso mehonachiun hulum yawkal bekentu atidikemu

  ReplyDelete
 2. ምንም እንኳን ወንጌልን ለማዳፈን ሲንቀሳቀሱ ሕይዎታቸው ቢያልፍም ለዘላለም ሕይዎት ሳይዘጋጁ በመሄዳቸው እንደ ሰው ማዘን ቢኖርብንም 'ነፍሳቸውን ይማር' ማለታችሁ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስላልሆነ ቢታረም እወዳለሁ:: ይልቅስ የቀሩት የማህበሩ አባላት እንደዚህ ሳይመሽ ንስሃ እንዲገቡ እንጸልይ:: ጌታ ሁላችንንም ይርዳን አሜን::

  ሰላም ይብዛላችሁ

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
 3. ማህበረ ቅዱሳን የሰውን ደም ሲመጥና የወንጌል እንቅፋት በመሆን እድሜውን ጨረሰ

  ReplyDelete
 4. ''ማህበረ ቅዱሳን የሰውን ደም ሲመጥ''see how much ''christian you are?'',even you don't know best words to express your emotion.By saying this I am not at the side of MK.They may have their own problem to the church.what is important is giving hands to the church to solve variety of problems it faced today.you and some other groups rather prefer protestatism as a solution to the current problem .this is not the right track as our Faith is our live and we know what protestantism really is.so,what I think you should do is,organize a group and ask the holly synod all problems you think there are in the church and have a discussion with MK (I know this will happen if you really want a change having a full orthodoxy faith).Otherwise ,you ,me and some other man can't say ''lets bring reformation to the orthodox church'' by our own.

  ReplyDelete
 5. I grew up at the heart of MK.we always try to protect our religion hence our people. so just take sides don't stand in the middle.rest to one side.If you get closer to Ethiopian orthodox church scholars, they will teach you the right testament. not the western.

  you can't modify dogma.if you do you are on another religion so please stay put to yours'.
  millions may not follow what you believe but who cares as far as you believe what you stand for. you die with it. BUT DO NOT SPREAD IT TO PEOPLE WHO HAVE VALUES OF THEIR OWN FOR THOUSANDS YRS BEFORE SOME HAPPEN TO START OUT THE NEW STYLE OF BELIEF YESTERDAY.It's so western to think like that.

  I wish that God open our eyes.

  ReplyDelete
 6. what are you joking? kikikikiki

  ReplyDelete
 7. ENNTE MENAFEKANE YEHE YETAHEDESO ENKESEKASE NEW AFE ZEME TEBELO AYKEFETEME

  ReplyDelete