Friday, April 15, 2011

በቤተ ክርስቲያናችን የሚዘወተሩ የባዕድ አምልኮ ልምምዶች - Read PDF


ካለፈው የቀጠለ
ባለፈው ጽሑፌ ጸሎታችን በመናፍቃን ድግምት እንደተበከለ እና ወደ መላእክት፤ ወደ አረፉ ቅዱሳን እንድንጸልይ፤ በመደረጋችን እስከ አሁን ድረስ በችግር ላይ እንደምንገኝ፤ እንቆቅልሻችንም ከመፈታት ይልቅ እንደገና ውስብስብ እየሆነ መምጣቱን በጥቂቱ ለመጠቆም ሞክሬያለሁ።
ዛሬም ትንሽ ብርሃን ልፈነጥቅ አሰብሁ....

ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እንጂ ከመላእክት ወይም ከቅዱሳን ጋር መነጋገር ማለት አለመሆኑን ማንም የሚያውቀው ጉዳይ ነው። ነገር ግን ይህ እውቀት ተግባራዊ ሆኖ ስለማናየው እራሳችንን ልንመርምር ይገባል። የጥንታዊት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ መንፈሳውያን አባቶቻችን በነዘርዓ ያዕቆብ ከመገደላቸው በፊት ይጸልዩት የነበረውን ጸሎትና አምልኳቸውን ጥቂት እንመልከት
"የአኩተከ ልብነ እግዚኦ አንተ ኃይሉ ለአብ ወጸጋ ለአሕዛብ፤ አእምሮ ርትዕ ጥበበ ስሑታን መፈውሰ ነፍስ፤ እበየ ትሑታን ሀገሪትነ አንተ ውእቱ ምርጉዘ ጻድቃን ተስፋሆሙ ለስዱዳን መርሶሙ ለእለ ይትሐወኩ። ብርሃነ ፍጹማን ወልደ አምላክ ሕያው አብርህ ላእሌነ እምዘኢይትአተት ጽጋከ ትክለተ ውጽንአተ ተአምኖ ወጥበበ ወኃይለ ሃይማኖት ዘኢይጸነን ወዘኢይትመየጥ ተስፋ። አእምሮ መንፈስ ሐብ ለትሕትናነ ከመ ዘልፈ በርቱዕ ንጹሐነ ንኩን አግብርቲከ እግዚኦ"
ትርጉም "አቤቱ ልባችን ያመሰግንሃል የአብ ኃይሉ የአሕዛብም ጸጋ አንተ ነህ የቅን እውቀት የስሑታን ጥበብ ነፍስን የምታድን ለተዋረዱት ክብር አገራችን፡የጻድቃን ምርኩዝ ለተሰደዱት ተስፋቸው፤ ለሚታወኩት ጸጥታቸው አንተ ነህ። የፍጹማን ብርሃን የሕያው አምላክ ልጅ ከማይለይ ጸጋህ አብራልን፤ መተከልን መጽናትንም መታመንንና ጥበብን፤ የማያዘነብል የኃይማኖትን ኃይል የማይለወጥ ተስፋንም።የነፍስ እውቀትን ለትሕትናችን ስጥ አቤቱ እኛ ባሮችህ በሚገባ ዘወትር ንጹሐን እንሆን ዘንድ" የጌታ ቅዳሴ ቁ 19-21። አባቶቻችን ጌታን እንዲህ ከፍ እያደረጉ በደስታ ያመልኩት ነበር፤ መንፈስን የሚያረካ እውነተኛ አምልኮ ይህ ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ደግሞ "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ ዘበአማን ኢይሱስ ክርስቶስ ዘትትቄደስ በአፈ ኩሉ"
ትርጉም "በሁሉ አፍ የምትመሰገን እውነተኛ የሆንህ ኢየሱስ ክርስቶስ አንተ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ ትመሰገናለህ" ሲል ጌታን አምልኳል። ዮሐንስ አፈ ወርቅ ቅዳሴ ቁ 35።
"ዘአውጻእከነ እምዕቅፍተ ጽልመት ወብርሃነ ዘኢይትረከብ ጸጎከነ። ዘእማዕሠር ለእለ የአምኑ ብከ ፈቲሐከ በሃይማኖት ከለልከነ፤ ዘኢይርሕቅ እማግብርቲሁ ወትረ ዘምስሌሆሙ ይሄሉ ዘኢይጸመም ለዘበፍርሐት ወበረአድ ትስእሎ ነፍስ እምቅድመ ሕሊና ኩሎ የአምር ወእምቅድመ ሕሊና ይፈትን ወዘእንበለ ንስአሎ ይሁብ ፍትወተነ ዘእምፈቃዱ፤ ወይሰማአነ እለ እንበለ ኑፋቄ ንጼውዖ ዘኢይትነገር ብርሃን ንጉሠ ሠራዊተ ሰማያት ሰማዒ ስብሐተ ማኅሌት ዘሊቃነ መላእክት ዘዲቤሆሙ የአርፍ"
ትርጉም "ከጨለማ መሰናክል አውጥተህ የማይገኝ ብርሃንን የሰጠኸን፤ ያመንብህ እኛን ከማእሠረ ክህደት አውጥተህ በሃይማኖት ያከበርኸን። ከአገልጋዮቹ የማይርቅ የማይለይ፤ ዘወትር ከነርሱ ጋራ የሚኖር፤ በፍርሐት በረዓድ የምትለምነውን ነፍስ ቸል የማይል፤ ከሕሊና አስቀድሞ የሚመረምር፤ ሳንለምነው የምንሻውን ዐውቆ የሚሠጠን፤ ሳንጠራጠር የምንለምነውን የሚሰማን፤ የማይመረመር ብርሃን፤ በሰማያት ያሉ የመላእክት ንጉሥ አድሮባቸው የሚኖር ሊቃነ መላእክት ያቀረቡለትን ምስጋና የሚቀበል አቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ቁርጥ ልመናችንን ስማን" ጸሎተ ኪዳን
እባቶቻችን እውነተኛውን ጌታ አግኝተው አምልከውት አልፈዋል፤ የጌታን ምስጋና ለማንም ሳይሰጡ አክብረውታል፤ እምነታቸው የማይወላውል የነጻ ባዕድ ነገር ያልተቀላቀለበት ልዩ ኃይልን የሚሰጥ መንፈስን የሚያረካና ወደ እግዚአብሔር የሚያደርስ ነበር።
ቅዱስ ያሬድም "ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖሕ ኪዳነ ዘአቀምከ፤ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ፡"
ትርጉም "እንዳተ ያለ መሐሪ ማን ነው? ከኖሕ ጋር ኪዳንን ያቆምህ፤ ለ እስራኤል ልጆች መናን የሰጠህ እንዳንተ ይቅር ባይ ማን ነው?" በማለት አመስግኗል።
ያሬድ በሌላ መዝሙሩም "አምላክ ፍጹም በሕላዌሁ ዘሀሎ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም ዘበመንግሥቱ ይኴንን ዓለመ ሰማየ ገብረ ለስብሐቲሁ ዓለመ ፈጠረ ወምድረ ሣረረ"
ትርጉም "ጌታ በአኗኗሩ ፍጹም ነው ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ነው በመንግሥቱም ዓለምን ይገዛል ሰማይን ለክብሩ ሠራ ዓለምን የፈጠረ ምድርንም የሠራ እርሱ ነው" በማለት ለጌታ ዘምሯል። {የኖላዊ መዝሙር}
እውነተኛዎቹ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች በምድሪቱ ላይ እግዚአብሔርን በማክበር ባዕድ ነገር ሳይቀላቅሉ የመላእክትን ዝማሬ በመንፈስ ቅዱስ እየተሳተፉ ምድሪቱ በኃይልና በበረከት እስክትሞላ ድረስ በእምነታቸው እግዚአብሔርን ደስ አሰኝተዋል።
በ15ኛው ክፍለ ዘመን የተነሳው ዘርዓ ያዕቆብ በጠጅ እና በጠላ ያሠከራቸው ደብተራዎች ከመናፍስት ጋር ባለቸው ዝምድና እየተደገፉ እውነተኛ አባቶቻችንን ካስገደሉ በኋላ በቤተ ክርስቲያናችን ስፍራ በመያዝ እውነተኛውን አምልኮ በባእድ ነገር ቀይረው ሃይማኖቱንም አምልኮውንም ዝብርቅርቁን በማውጣት ከፍተኛውን ሚና ተጫውተዋል። ይኸው ዛሬ እነርሱ የተበተቡት የጠላት ድርሰት ለምድሪቱ እና ልትውልዱ እዳ ሆኖ ደም ሲያፈስ ይኖራል።
በተለይም ይህን የጠንቋዮችን ድርሰት የባቶቻችን ነው በማለት መሠረት አድርገው ቤተ ክርስቲያንን እያፈረሱ ያሉት የዘመናችን ደብተራዎች ማህበረ ቅዱሳን የጌታን አምልኮ ለሌላ አንሰጥም ባሉ ወንድሞች ላይ ያባታቸውን የዘርዓ ያዕቆብን ታሪክ ባደባባይ እየደገሙት ነው።
የእውነተኛ አባቶችን ጸሎት ከላይ እንዳየነው ሁሉ እስኪ ደግሞ በቤተ ክርስቲያናችን ስፍራ የተሰጣቸው ደብተራዎች እንጸልያለን እያሉ ዘኬ የሚበሉበትን ጸሎት ከዚህ ቀጥለን እንመልከተው---
ወደ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የሚጸለይ ጸሎት
"ሰላም ለአእዛኒከ እለ ያጸምዓ በቅጽበት፤ ጸሎተ ብእሲ ኅዙን ወቃለ ብእሲት ትክዝት፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መሐሪ ገባሬ መንክራት አበይት፤ ዘአንተ ርዳኤ ኩሉ ወጸጋዌ ኩሉ ሐብታት፤ ሕሊናከ በኀቤየ ይጸንእ ለምንት።"
ትርጉሙ
"ያዘነ ሰውን ጸሎትና ያዘነች ሴትን ቃል በቅጽበት ለሚሰሙ ለጆሮችህ ሰላምታ አቀርባለሁ።ታላላቅ ታምራትን የምታደርግ ይቅርባይ የሆንህ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ አንተ እኮ ሁሉን የምትረዳ ሀብታትን ሁሉ የምትሰጥ ነህ፤ ለምን ልብህ በኔ ጸና?" ማለት ነው።[መልካ ገ.መንፈስ ቅዱስ]
በመጀመሪያ ለጆሮ የሚቀርብ ሰላምታ መኖሩን ከምን ዓይነት ልምምድ የተቀዳ እንደሆነ አልታወቀም። ጆሮህን ሰላም እላለሁ ማለት ምን ማለት ነው?
"ያዘነ ሰውን ጸሎት በቅጽበት የምትሰማ"
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሰው መሆናቸው የታወቀ ነው ነገር ግን ጸሎትን በቅጽበት እንደሚሰሙ ተነግሮላቸዋል እኒህ ሰው አምላክ ናቸው ወይስ ምን? ገብረ መንፈስ ቅዱስ እንደ ፈጣሪ በሁሉም ስፍራ የመገኘት ሁሉንም የማዳመጥ፤ ብቃት ሊኖራቸው ይችላል ? በየቤተ ክርስቲያኑ በወር በወር ወደ እርሳቸው የሚቀርበውን ጸሎት የመስማት ችሎታ ካላቸው አምላክ እንጂ ፍጡር ሊሆኑ አይችሉም። እውነቱ ግን ቅዱሳን በምድር ላይ የነበራቸውን የሥራ ጊዜ አጠናቀው አሁን በእረፍት ላይ የሚገኙ እንጂ ስለ ዓለም ሁኔታ የሚያውቁ አይደሉም እግዚአብሔር ካልገለጠላቸው በቀር። በውዳሴ ማርያም አንድምታ ላይ እንዲህ የሚል ትርጉም አለ
"ልመናስ ስንኳን በርሷ በሌሎች ቅዱሳንም የለባቸውም በቀደመ ልመናዋ የምታሥምር ስለሆነ እንዲህ አለ እንጂ" ሰዓሊ ለነ ቅድስት የሚለውን ቃል እውነተኛ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት ሲተረጎሙ የተናገሩት ነው።
ስለዚህ ይህ ጸሎት ከመናፍስት ጠሪዎች አንዱ የደረሰው ስሕተት ነው ብለን እንደመድማለን።
"ታላቅ ታምራትን የምታደርግ ይቅርባይ የሆንህ" መጽሐፍ ቅዱስ ታላላቅ ታምራትን የሚያደርግ እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ይመስክራል። በቅዱሳኑ የሚያደርጋቸው ታምራትም ከራሱ በራሱ የተደረጉ እንጂ በሰዎች ልዩ ችሎታ የሚደረጉ አይደሉም። መዝ 135 ቁ 4። ቅዱሳን ታምራት ቢያደርጉም ክብሩ ለእግዚአብሔር እንዲሆን እንጂ ከሞቱ በኋላ ወደ እነርሱ እያንጋጠጥን ምሥጋና እና አምልኮ እንድናቀርብላቸው አይደለም። ስለዚህ በገብረ መንፈስ ቅዱስም ይሁን በሙሴ ታላላቅ ታምራትን ያደረገ እግዚአብሔር ነውና ምስጋናው ለእግዚአብሔር ይገባል እንላለን።
"ይቅርባይ የሆንህ"? ይቅርባይ ማን ነው? ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወይስ እግዚአብሔር? ገብረ መንፈስ ቅዱስ መሐሪ ይቅርባይ ከሆነ ለምን አማላጅ ሆነ? እናስተውል ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይቅር የተባለ እንጂ ይቅርባይ አይደለም የእግዚአብሔርን ምስጋና ለፍጡር እየሰጡ መጸለይ እብደት ነው።
"አንተ እኮ ሁሉን የምትረዳ ሀብታትን ሁሉ የምትሰጥ ነህ?" አቤት ጣኦት! ጉድ ነው!
ሁሉን የሚረዳ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሀብታትን የሚሰጥም መንፈስ ቅዱስ ነው 1ቆሮ ም 12 ቁ 4-13 ማንበብ ይቻላል። የሰውን ልብ እና አቅም የሚያውቅ መንፈስ ቅዱስ ነው ለማን ምን እንደሚያስፈልገው የሚያውቅ እርሱ ብቻ ነው። ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሀብታትን የሚያድሉት እንዴት ነው? ጠንቋዮች ጨካኞች ናቸው፤ ክህደታቸው ጠንቅ ነው የመንፈስ ቅዱስን ሥራ ለአንድ ሰው ሰጥተው "ሁሉን የምትረዳ ሀብታትን የምታድል" ብለው አንድ ፍጡር እንድናመልክ አድርገውናል። አቤቱ ይቅር በለን!
ማህበረ ቅዱሳን የተባለው አፍቃሬ መናፍስት ግን እኛ ቅዱሳንን እናከብራቸዋለን እንጂ አናመልካቸውም እያለ በተደጋጋሚ ይጽፋል። ግን "ሁሉን የምትረዳ ሀብታትን የምታድል፤ይቅር ባይ፤ ሁሉን የምትሰማ" የሚለው ጸሎት አክብሮት ነው ወይስ አምልኮ? ከዚህ ሌላ እግዚአብሔርንስ ምንድን ነው የምንለው?
"እዎ እግዚኦ ረዳኤ ኩሉ እዎ እግዚኦ ጸጋዌ ኩሉ" እያልን በቅዳሴ ጊዜ እናመሰግነው የለምን? መቼ ነው የእግዚብሔርን ምስጋና ከመናፍስቱ የምትለዩት? እናከብራቸዋለን እንጂ አናመልካቸውም የሚለው አባባል የክህደቱን ዘመን ለማራዘም የሚነገር ማጭበርበሪያ እንጂ እውነት አይደለም።
እንዲያውም ገብረ መንፈስ ቅዱስ የተባሉት ሰው በኢትዮጵያ ይኑሩ አይኑሩ ማረጋገጥ አልተቻለም። አንዳድ ሊቃውንት ልብ ወለድ ናቸው ሲሉ አንዳዶች ደግሞ በመስቀል ጦርነት ጊዜ ተሰደው የመጡ ፈረንጅ ናቸው ይላሉ።
ገድሉ የግብጽ ሰው እንደሆኑ ይናገራል። ነገር ግን የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ገብረ መንፈስ ቅዱስን አታውቃቸውም። በኢትዮጵያም የሚያውቃቸው ሰው አልተገኘም በገድሉ ምራፍ 20 ቁ 1-3 ላይ ገብረ መንፈስ ቅዱስን በኢትዮጵያ ማንም እንዳላያቸው ይናገራል ። ሰውየው ምግብ አይበሉም ነበር፤ መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው ጸልየዋል፤ ለቁራ አሞራ ከዓይናቸው ውሃ አጠጥተዋል፤ ዝናብ አይመታቸውም ነበር፤ ጸሐይም አያቃጥላቸውም፤ የዛፍ ጥላም አያስፈልጋቸውም ጸጉራቸው በምድር ላይ እስኪጎተት ድረስ ረጅም ነበር፤ አምስት መቶ ስልሣ ዓመት ያህል እድሜ አላቸው፤ ኑሯቸው እንደመላእክት ነው። ይህን ሁሉ ገጸ ባሕርይ ገድሉን በማንበብ መረዳት ይቻላል። ሰው ናቸው እንዳይባል ከሰው ልማድ ወጣ ያሉ ናቸው አይበሉም አይጠጡም። ዮሐንስ መጥምቅ እንኳ የበርሃ አንበጣ እና የጣዝማ ማር ይመገብ ነበር፤ ለሰውም ይታይ ነበር፤ ኤልያስም ምግብ ይበላ ነበር፤ ጌታችን እንኳ ምግብ በልቷል። ገብረ መንፈስ ቅዱስ ግን አምስት መቶ አመት ሲኖሩ ምንም አልበሉም። ግን እኒህ ሰው በፍጥረት ታሪክ የመጀመሪያው ናቸው። የመጀመሪያው ምግብም የማይበላው ውሃ የማይጠጣው ሰው ገብረ መንፈስ ቅዱስ ነው። መላክ ናቸው እንዳንል ከሰው እንደተወለዱ ተጽፏል ከአንበሳ እና ከነምር ጋርም ልዩ ቅርበት ነበራቸው። ግን ለሰው አይታዩም ነበር፤ ገድሉም ሊጻፍ የበቃው ይፋት በሚባል አገር [ሰሜን ሽዋ] ዋሻ ውስጥ ይኖር ለነበረ ባሕታዊ ተገልጠውለት ስለነገሩት ነው ይላል ገድሉ። ይህች ጥያቄ ታመጣለች "ዋሻ ውስጥ የሚኖር ባሕታዊ?"
 ባህታዊው እራሱ ያልታወቀ ሰው በመሆኑ እውነተኛ ምስክርነት ነው ብለን ልንቀበለው ይከብደናል። ሁለቱም በኢትዮጵያ አልታዩም  ታዲያ በኢትዮጵያ ካልታዩ በግብጽም ካልታወቁ እኒህ ሰው ምን ይሆኑ ይሆን? ሌላው ቀርቶ መቃብራቸው እንኳ የት እንደሆነ አይታወቅም። ገድሉ እና መልኩ መላእክት ቀበሩት ይላል። "በኢየሩሳሌም ወይም በምድረ ከብድ ተቀብሯል ይባላል" በማለት ጥርጣሬውን ከመናገር በቀር ምንም ማረጋገጫ አልሰጠም።  እንግዲህ ይህን እንቆቅልሽ  ለጌታ እንተወውና እኛ ግን ወደ እርሳቸው የመጸለይ የመዘመር ግዴታ የለብንም፤ ሲሆን ሲሆን ቤተ ክርስቲያናችን ይህን ጉዳይ አጣርታ ትክክለኛውን ታሪክ እንድታቀርብልን ስንል እንማጸናለን። ወደ ፊት በገብረ መንፈስ ቅዱስ ላይ ጥናት ለማድረግ እንሞክርና ለኢትዮጵያ ሕዝብ እናሳውቃለን።
በዲያቆን ሉሌ

11 comments:

 1. ''የጥንታዊት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ መንፈሳውያን አባቶቻችን በነዘርዓ ያዕቆብ ከመገደላቸው በፊት ይጸልዩት የነበረውን ጸሎትና አምልኳቸውን ጥቂት ...'' asmesay hulu,arfeh bitkemet yishalhal

  ReplyDelete
  Replies
  1. Anonymous thank you for pointing out that his writer is 100% a liar. I bet this person is not Orthodox. Deginetu metshaf kidus min yilal, Betachristianin yimifetaten ke kristina wed ahizabinet yigebal. yih sew Ahizab honewal.Matios 18:17If he refuses to listen to them, tell it to the church.And if he refuses to listen even to the church, regard him as you would a pagan

   Delete
 2. ''በበገብረ መንፈስ ቅዱስም ይሁን በሙሴ ታላላቅ ታምራትን ያደረገ እግዚአብሔር ነውና ምስጋናው ለእግዚአብሔር ይገባል እንላለን።በገብረ መንፈስ ቅዱስም ይሁን በሙሴ ታላላቅ ታምራትን ያደረገ እግዚአብሔር ነውና ምስጋናው ለእግዚአብሔር ይገባል እንላለን። ።''do you believe that God has done a miracle through ገብረ መንፈስ?can I get this on the bible?

  ReplyDelete
 3. ዲያቆን ሉሌ,while you were studying ''WUDASIE MARIAM'' to be Deacon (if you really were a deacon),don't you study ANKETSE BIRHAN? DERASIW MAN YILAL? he is kiduse yared! so if you believe that Yared is our true father ,why don't you do the same ? have u a better kidsna than yared to accept some of his books and to neglect the others?

  ReplyDelete
 4. I would like to hear the results of your research. Please talk to Pope Shenuda and the other authorities at the Coptic church. Gebre MenfesKidus may not have been crowned as a saint without the support of the Coptic church as they were the head of the church during that time. How did they support it without knowing it?

  Any way, I really doubt its authenticity if he was not seen to people. How did he preach the bible if he was not seen to people? I guess he came to Ethiopia to preach the bible. Otherwise, why would God send him to Ethiopia?

  I agree there are millions of myths that the Ethiopian church needs to explain. Unfortunately, the church is as defunct and disorderly as an army without a leader. Everybody shoots randomly without any clear purpose... No one knows where we are heading to.


  Regarding prayer, you are not obligatd to pray to any saint. Nor are you expected to believe in it either. That is not a requirement for your salvation. However, it is not a sin to pray through the saints either. Yes, prayer is a conversation with God. What we need to know is we are members, including the saints, of the family of God. Prayin to the saints is like asking your brother or sister in faith to pray for you. However, i fully agree that it has been stretched above the limit in our church. Sometimes the veneration is elevated to the extent of worship. I agree that needs to be changed. Most of the deftera-written books are full of heretics. After some frustrations, I have stopped reading such books to protect myself from unnecessary contamination. Except few awalid books, most seem to be out of touch from the core faith.

  Thus, it will be good to put some pressure and resist the establishment to bring some positive changes. What will be wrong is to seek protestant flavored changes in our church. For some uneducated and immature people, adopting the protestant faith is the answer for the problem that we are in. Our church is Orthodox; so, we need an orthodox solution for the serious problems we are in. The protestant churches have even more serious problems; some have even embraced satanic spirits knowingly or unknowingly.

  Coming back to our church, I seriously worry why we have removed God from our lives and almost replaced Him by the saints. I like the saints and believe in the power of their prayers, but again what we see in our church does not look healthy. We need a reform to clean up all the junks thrown at the church over the years. That reform needs to be led by the Holy Spirit. Teach the untainted truth and the believers will throw away the bad practice with the help of the Holy Spirit.

  ReplyDelete
 5. Kechin Ewnet, You raised an interesting question, but the problem is that over the last many years St. Yared's original books have been contaminated with lots and lots of garbage. Even on his 'Diguwas', many bad things have been added many hears after his death. So just because a book has Yared's name on it, it doesn't mean it is trully Yared's writtings. It is really sad. we are in a mess.

  ReplyDelete
 6. I AM LIVING US . I GOT A CHANCE TO TALK TO THE EGYPTIAN ORTHDOX CHURCH PRIEST ABOUT GEBREMEN FESE KIDUS. HE SAID TO ME WE DONOT KN OW HIM. SO WHY THE ETHIPOIA ORTHODOX CHURCH SAID AND TALK ABOUT GEBRE MENFEKIDUS WITHOUT GET INFORMATION ?. WHAT EVER IT IT OUR LORD JESUS CHRIST IS THE ONLY SAVIOUR FOR US. ONLY HIM , ONLY HIM . AMEN

  ReplyDelete
 7. ገብረመንፈስ ቅዱስ (ገብሬ) ትክለሃይማኖት (ተክሌ) ቅ.አርሴማ (አርሲ) ጊ. ዘጋስጫ (ዘጨ) እና የመሳሰሉት የተፈጠሩት በ 8ኛው ቀን( ማለት ጌታ ፍጥረቱን ፈጥሮ ከጨረሰ በኋላ) ስለሆነ ይመስለኛል ቦታ ሊሰጣቸው ያልተቻለና ውድቅ ሆነው የቀሩት

  ReplyDelete
 8. There are many saints that are not known in the bible.I am baffled by your morality to question others religion.why is every religion against Ethiopian orthodox?it's amazing.0_0.
  I don't believe this blog is neutral. You are allowing posts as huge as insulting one's religion.

  why don't you go to other religions and do your post or blogging.we are all at least Christians for God's sake.It just doesn't make sense.

  peace.

  ReplyDelete
 9. read mehalye mehaly ze solomon

  ReplyDelete
 10. ere fentakiwe ewenetm birehan fenetek jilajil. bechelema menorehnemane mane benegereh? mutcha yalawekinih meseleh Yetehdiso site mehonun

  ReplyDelete