Saturday, April 30, 2011

የባቢሎን ርኩሰት በኢትዮጵያ - Read PDF

                                            
ግድያን፣ ዝሙትን፣ የበላይ ለመሆን የሚደረግ ጥረትን፣ ስግብግብነትን ወዘተ ከመሰሉ የርኩሰት ዓይነቶች ሌላ በባቢሎኖች የነበረ ርኩሰት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተዘርዝሯል።

1. ኮከብ ቆጠራ (ኢሳ 4፥13)፦ የኮከብ ቆጣሪነት ትምህርት በአብዛኛው የከለዳውያን ጥበብ ስለ ነበረ ኮከብ ቆጣሪነት ከለዳዊነት ተብሎ ተጠርቷል። ዳን 2፥2-10። በኮከብ አቆጣጠር ትምህርት የሰውን ጠባይ ዕድልና የሚያጋጥመውን አስቀድሞ ለመተንበይ ይሞከራል ይህን በሀገራችን ያሉ ደብተራዎች ይሠሩበታል።

2.መተት፦ ጠላትን ለማፍዘዝ፤ ጠላትን ጉዳት እንዳያደርስ ለመከላከል የሚደረግ ሲሆን በሀገራችን "አፍዝ አደንግዝ መድፈነ ጸር፣አቃቤ ርእስ" እያሉ ደብተራዎች ይሠሩበታል ኢሳ 4፥9-12። ይህ ርኩሰት ከኩሽ ልጆች የከነአናውያን መኖሪያ በነበረችው በመካከላኛው ምሥራቅ በአሦር በግብፅ፣ ከባቢሎን አስቀድሞም  ሆነ በኋላ ሲሠራበት ነበረ ዘዳ 1፥9-10 ናሆም 3፥1-9። አሁን በኢትዮጵያ በተስፋ ገ.ሥላሴ ማተሚያ ቤት እየታተመ ለሕዝብ ይሰራጫል።

3.አስማት፦ ርኩሳን ስሞችን በመጥራት መድገምና መማጸን ሲሆን በጣኦታት የሚያድሩትን መፍስት ወይም የሙታን ነፍሳት ነን የሚሉትን አጋንንት በስሞቹ መጥራት ማምለክና እርዳታ መጠየቅ ነው። በኢትዮጵያ ኅቡዕ ስም ተብሎ የሚታወቀውና በየድርሳናቱ የሚገኘው ነው።
. በጠላት ላይ ጉዳት እንዲያደርሱ መነፍስቱን መጠየቅም አለ፤
. ይህ ርኩሰት የኩሽ ልጆች መኖሪያ በነበረችው ምድረ ከነዓን የታወቀ ልምምድ  ነበረና እግዚአብሔር ሕዝበ እሥራኤልን ወደ ዚያ በሚገቡበት ጊዜ ይህን ልምምድ ከከነዓናያን እንዳይወርሱ ጠንካራ ማስጠንቀቂያዎችን አስተላልፎ ነበር። ዘሌ 19፥31፣ 20፥6 ዘዳ 18፥10-13።
. በዚህ ክፍል ውስጥ ሌሎች ርኩሰቶች በአባሪነት ተዘርዝረዋል።
. ሟርት
. ጥንቆላ
. መተት
. መናፍስትን መጥራት
. የሙታን መናፍስትን መሳብ እየተባለ ተገልጧል።

በምድረ ግብጽ አስማተኝነት ሥር የሰደደ ርኩስት ነበርና ግብጻውያን አስማተኞች በአስማታቸው የእግዚአብሔርን ክንድ ለመቋቋም ሞክረው ሳይሳካላችው ቀረ ዘጸ 11፥22፤ 8፥2፤ 18-19።

እስራኤላውያን ምንም ቢከለከሉ ይህን ሁሉ በሚገባ ወርሰው ነበር 1 ሳሙ 28፥7-14፤ ኢሳ 8፥19፤ 2ዜና 38፥5-6።
.በሀገራችን እንደ ድርሳነ ሚካኤል ያሉ በግልጽ አስማት ተጽፎባቸዋል። በሚካኤል በቀኝና በግራ ክንፉ የተጻፉ ናቸው ተብሎ ማብራሪያ ተስጥቶታል[ድርሳን ዘህዳርን ያንቡ] በመሠረቱ በቅዱሳን ስም የሚጠሩ ሁሉ የሙታን መናፍስት ናቸው።

ከጥንቆላው ዓለም ከነኮተታቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ዘው ብለው የገቡ ደራስያን እመቤታችንን ምን ብለው እንደሚጠይቋት እንመልከት

     "ለጸባኢነ ጽብኢ፣ ወለገፋኢነ ግፍኢ፤
     ማርያም ድንግል ወለተ መዋኢ፤"

ትርጉም፦ የአሸናፊው ልጅ ድንግል ማርያም ሆይ
      ጠላታችንን ተጣይ የሚገፋንንም ግፊ፤ [መጽሐፈ ሰዓታት]

    "አጽራርየ እለ ተንሥኡ በነገረ ከንቱ ወበክ፤
    ሐመደ ለይኩኑ በጽባሕ ወሠርክ፤"

ትርጉም፦ ባልሆነ ነገር የተነሱ ጠላቶቼ፤
       በጥዋትና በማታ ዐመድ ይሁኑ[መልካ ጊዮርጊስ]

4. አስማተኝነት እንዴት ወደ ኢትዮጵያ ገባ?

4.1. ከግብፅ ጀምሮ ወደ ደቡብ በተንጣለለው ሰፊ በርሃማና ወይና ደጋ መሬት አባይን ተከትለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡትና የሠፈሩት ከነገደ ካም "ኩሻውያን" መሆናቸው በክብረ ነገሥትም በተጠና ታሪክም ተረጋግጧል። እነዚህ ሠፋሪዎች በነነዌና በባቢሎን በከነዓንም እንዲሁም በግብጽ ኩሻውያን በሆኑ ዘመዶቻቸው ይሠራበት የነበረውን አምልኮ፣ አስማት፣ ጥንቆላ፣ ሟርት፣ መተት፣ ኮከብ ቆጠራ፣ መናፍስት መጥራትን፣ የሙታን መናፍስትን መጥራትን የመሳሰለውን ሁሉ ይዘው እንደገቡ ይገመታል።

በትንቢተ ናሆም ምዕራፍ ሦስት እግዚአብሔር ነነዌን በዚሁ በተጠቀሰው ርኩሰቷ ሊያጠፋት መወሰኑን ገልጧል። ከዚያ ቀደም ብሎ በኢትዮጵያ በግብጽ፣ በፉጥና፣ በሊቢያ፣ ትደገፍ የነበረችው የኖእ አሞን [ካሶራውያን በፊት በ663] እንድትመለስ ማድረጉን በማስረጃነት ጠቅሷል።

4.2 ከኩሻውያን ቀጥሎ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ከነገደ ሤም ሳባውያን በየመን በኩል ቀይ ባሕርን በማቋረጥ እንደሆነ ይተረካል። የነዚህ ነገዶች አምልኮ አብሮ መግባቱን ታሪክና ቅርሶች ይገልጻሉና እነዚሁ ሁለተኛ ሰፋሪዎች በዐረብ፤ በፋርስና በሕንድ የተለመዱ የአስማት ዓይነቶችን እንደ አምልኳቸው ይዘው ሳይገቡ አልቀሩም።

4.3 በሦስተኛ ደረጃ በግብጽ በኩል አባይን ተከትለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ከነገደ ሴም እሥራኤላውያን ናቸው። እነርሱም በሀገራቸው በጊዜው ከእግዚአብሔር ተግሣጽና ማስጠንቀቂያ ይደርሳችው የነበረው ከአስማት ከጥንቆላና ከባዕድ አምልኮ በተያያዘ ልምምዳቸው ምክንያት ስለነበረ 2ነገ 17፥16-20፤21፥3-6 እሥራኤላውያን ይህንኑ ልምምዳቸውን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ እንደ ገቡ ይገመታል። ጠቋሚ ማስረጃዎችም አሉ  ኤር 7፥18-19፤ 44፥1።

4.4 በዓመተ ምሕረት ውስጥ ከ7ኛው ምእት ዓመት ጀምሮ ሙስሊም አረቦች  ወደ ኢትዮጵያ በገፍ እየገቡ መስፈራቸው ተለምዶ ነበር ። እነርሱም አዳዲስ የአስማት መጻሕፍትን ይዘው ሳይገቡ አልቀረም ተብሎ ይታሰባል።

4.5 በኢየሩሳሌምና በአካባቢው በመስቀል ጦርነት በግብጽም በእስክንድራያም ቤተ ክርስቲያን ላይ ስደት በደረሰበት ጊዜ 12000 ያህል ስደተኞች ከመኖሪያቸው ፈልሰው በዛጐየ ዘመነ መንግሥት መግባታቸው በታሪክ ተረጋግጧል። አፄ ላሊበላም ብዙዎችን በግዛቱ ውስጥ በመደልደል መኖሪያ ስለ ሰጣቸው እነርሱም ብዙ የአዋልድና የአስማት መጻሕፍትን ይዘው እንደገቡ ይገመታል።
4.6 ከዚህ በላይ የተገለጹት ሁሉ በክርስትናችን ውስጥ ሥር እየሰደዱ ውስጥ ለውስጥ ሲሠራባቸው እንደቆየ ሲገመት በአፄ አምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት [1304-1331] በቤተ መንግሥቱ ውስጥ  በካህናተ ደብተራ ሲሰራበት የነበረ "እገሊት እጣ ክፍልህ ናት" የሚል ከኮከብ ቆጠራ የተያያዘ  የአስማት ሥራ ነበር። ይህን ንጉሥ "የአባትህን ሚሥት ብታገባ ጠላትህ ይጠፋል  መንግሥትህ ይሰፋል፣ ዕድሜህም ይረዝማል" ብለው አጋብተውት ነበር። አቡነ ፊልጶስ እጨጌ ዘደብረ ሊባኖስ ንጉሡን ገሠጹት "እንደርስዎ ያሉ መምህራን ይህንን እንዳደርግ በመከሩኝ መሠረት የፈጸምኩት ስለ ሆነ ያገባኋትን ሴት አልፈታም" ከማለቱ ሌላ ዕጨጌውን ደም እስኪፈሳቸው ድረስ ገረፋቸው፤ በኋላ ከመንበራቸው አሳደዳቸው።

በዚህ ንጉሥ ዘመን ጠቃሚ የሆኑ ያልሆኑም መጻሕፍት ከዐረበኛ ወድ ግእዝ የመተርጎም ሥራ እንዲቀጥል በማድረግ በቅዱሳን ስም ለተሰየሙ መናፍስት ግጥም በመግጠም ሰላምታ በማድረስ የታወቀው አፄ ዘርዓ ያዕቆብ [1426-1460] ዓ.ም ነው።

5. የአስማት ሥራ አይነቶች

ጥንትም ሆነ ዛሬ የአስማት ሥራዎች ከካህናቱ ጋር ተያይዘው ይገኛሉ። ሥራውም በድጋምና በጽሕፈት ስለሚከናወን አስመተኛነት ምንጊዜም የተማረው ክፍል ንብረት ሆኖ ቆይቷል። ተራው ሰው ገንዘቡን ቋጥሮና ደጅ ጠንቶ የሚያገኘው ከካህናቱ ክፍል ነው።

የአስማት ዓይነቶችን በዝርዝር ለመጻፍ ሳያስቸግር አይቀርም አንዱ የሚያውቀውን ሌላው ስለማያውቀው በዝርዝር ለመጻፍ ጊዜን ይወስዳል። ነገር ግን በዐጭሩ ዋና ዋናዎቹን እንደሚከተለው መጠቆም ይቻላል።

5.1 እራስን ለመጠበቂያ [አቃቤ ርእስ] እና መፍትሔ ሥራይ።

5.2 ጠላትን ለመጉጃ
   1. መድፍነ ፀር
   2.ጥላ ወጊ
   3.አንደርቢ
   4. የተለያዩ ማዕሠሮች [እንዳያገቡ፣ ሀብት እንዳያገኙ፤ እንዳይማሩ፤ ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን ለማሠር የሚጠቀሙበት።
  5. መስተአብድ [የሚያሳብድ]

5.3 ለዝሙት ማስፋፊያ

  1. መስተፋቅር
  2.አምጽኦ ብእሲት[ሴትን አክነፍንፎ የሚያመጣ]
  3.አካልን ለዝሙት ሥራ ለማነሣሳት

5.4 ለትምህርት

  1. አእምሮን የሚከፍት
  2. አፍልሆ [እውቀት ወይም ትምህርት በውስጡ እንዲፈልቅ የሚያደርግ]
  3. ዘኢያገድፍ[እንዳይረሳ የሚያደርግ]

5.5 ለንብረት ጥበቃ
 
  1.መስተኃድር[የአውሬና የሌባ ማሠሪያ]
  2.እግረ መልስ [ሌባ ወይም አሽከር ተመልሶ እንዲመጣ የሚያደግርግ]
  3.አቃቤ ንዋይ[ በጠቅላላው ንብረት የሚጠብቅ]

5.6 የሰውን ሀብት ለመውሰጃ

  1.መስሕበ ንዋይ
  2.ሟርት

5.7 ታምራት መሠል ሥራ

  1.ዕፀ መሠውር [ከሰው ለመሰወር]
  2.መስተጽእነ ደመና[ በደመና ተጭኖ ለመሄድ የሚረዳ]
  3.መስተጽእነ አራዊት [በአራዊት ተጭኖ ለመሄድ የሚረዳ]
  4.ምስሐበ ጋኔን [ጋኔን የሚስብ]

እነዚህ ሁሉ አስማቶች በሦስት መንገድ ይሠራባቸዋል።

1 በድግምት
2 በድግምትና በእጽ
3 ያለ ድግምትና ያለ እጽ[አንድ ጊዜ በሰይጣን በመዋረስና በደም ቃል ኪዳን በመግባት]

6. መዋረስ ምንድን ነው?

ሰው ለተሸነፈለት ለርሱ [ለሰውም ይሁን ለመንፈስ ወይም ለዓመጽ]ባሪያ መሆን  በመጽሐፍ ተገልጧል።
በዚህ መሠረትም ሰው ከሰይጣን በቀረበለት የተንኮል ምክር ተሸንፎ ኃጢአትን ሲሠራ የኃጢአት ባሪያ ሆኖአል፤ የኃጢአትም ምንጭ ሰይጣን ስለሆነ በተዛዋዋሪ ለሰይጣን ባሪያ መሆኑ እርግጥ ነው። ዮሐ 8፥34። ሮሜ 6፥16። ይህም ሁኔታ አንዳድ ጊዜ ለሰይጣን እንደ ግብር ልጅነት ይቆጠራል፤ በዚህም መሠረት የአዳም ልጅ የሆነውን ሁሉ ያ በአዳም በኩል ከሰይጣን ወደ ሰው የገባው ኃጢአት ከሰይጣን ጋር አቆራኝቶታል። ስለሆነም

·        ጌታ እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ ብሏል ዮሐ 8፥44።
·        መጥምቁ የሐንስ "እናንተ የእፉኝት ልጆች" ብሏል። እፉኝት ከእባብ ዘር አንዱ ዓይነት ነው፤ የቀደመውን እባብ ሰይጣንን ያመለክታል። ማቴ 3፥19፤ ራእ 12፥9። በዚህ ዓይነት በልደት የአዳምና የሔዋን ልጆች በመሆናችን ይህ ዓይነት ጠባያዊ ትሥሥር መኖር ሳያንስ ሰው ደግሞ በፈቃዱ ከሰይጣን ጋር በቃል ኪዳን ይወራረሳል፤ ሰውየው ሰይጣኑን ሊሆን ሰይጣኑም ሰውየውን ሊሆን ቃል ኪዳን ይገባሉ።

ቀደም ሲል ከሰይጣን ጋር የተወራረሰው ሰው የሰይጣኑን ስም በመጥራት እንዲገለጥ ያደርገዋል፤ አብዛኛውን ጊዜ ዶሮ ታርዶ ደሙ ለሁለት ይከፈላል ለሰይጣኑ ድርሻው ይሰጠዋል  የሰውየው ድርሻ በምላጭ በተበጣው በሰውየው አካል ውስጥ ይቀበራል። አንዳድ ጊዜ የተረፈውን ደም ሰውየው እንዲጠጣው ይደረጋል፤ ተወራረሱ ማለት ይህ ነው።

አብዛኛውን ጊዜ ከሰይጣን ጋር የተዋረሰ ደብተራ  ሰይጣኑን የሚጠራበት እንደ ኮድ ያለ ቃል [ኅቡዕ ስም] ብቻ ይጠቀማል። ሰይጣኑ ሲመጣ አድርግልኝ የሚለውን ሰውየው ይነግረዋል፤ ሰይጣኑም ለሰውየው ያደርግለታል። ግደልልኝ፣ አሳምምልኝ፤ ቤቱን አቃጥልልኝ  ወዘተ ቢለው ይፈጸማል። ታዲያ ሰይጣኑም ደብተራውን አድርግልኝ የሚለውን ሁሉ ደብተራውም በበኩሉ ያደርግለታል።

ይህ ሁሉ ተረት ሊመስል ይችላል ነገሩ እውነት ነው። በጣም ደስ የሚለው ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ባመኑት፣ ስሙን በሚጠሩትና ዘወትር በሚጸልዩ ክርስቲያኖች ላይ ፈጽሞ የማይሠራ መሆኑ ነው። ከዚህ ሰይጣናዊ ሥራ ነጻ የሆኑ አባቶችም ስላሉን እነሱን አይጨምርም።

በነገራችን ላይ በቅዱሳን ስም ለተሰየሙ መናፍስት የተደረሱትን ድርሳናትን መልካ መልኮችን ሰላምታዎችን ወዘተ  በተመስጦ ሰዎች መላልሰውና አዘውትረው ሲደግሙ በስማቸው የተጠሩ ጠበሎችን ሲጠጡ  ሳያውቁት ከመናፍስቱ ጋር ሊወራረሱ ይችላሉ።

7. በመናፍስት የመያዝ ምልክቶች

መናፍስት ብዙ ጊዜ ራሳቸውን አይገልጹም በመንፈሳዊ ሥራ እና አገልግሎት ውስጥ ሠርጎ የመግባት ችሎታ አላቸው  አገልጋዮች ሊመረምሯቸው ይገባል። በግልጽ የሚታወቁት እንደ ተጠበቁ ሆነው ግን ድብቅ ለሆኑ መናፍስት ቀጥሎ የተመለከቱት ሁኔታዎች እንደ ምልክት ሊሆኑ ይችላሉ።

. ሥጋዊ ጥቅምን አብዝቶ መፈለግ
. መንፈሳዊ ነገር ሳይገባቸው እንደ ገባቸው ሆኖ ከሌሎች ቀድሞ መታየት
. ለጸሎትና ለእግዚአብሔር ቃል ጥናት የሚውለውን ጊዜ እንደባከነ መቁጠር፤
. የመንፈስ ቅዱስን የጸጋ ስጦታዎች ማናናቅና እንቅሥቃሤውንም ማጥላላት፤
. በመንፈስ ቅዱስ የጸጋ ስጦታዎች መዘባበት የአገልጋዮችን ድክመት ለመንፈስ ቅዱስ ስጥቶ መሳደብ፤
. በአገልጋዮችና በተገልጋዮች መካከል ሐሜትን በመንዛት ዐድማ ማነሣሣት፤
. ለአገልግሎት ዳተኛ መሆን
. ለእግዚአብሔር ነገር ግድ የሌሽ መሆን
. ለነፍሳት የፍቅር ሸክም አልመኖር
. በዋዛ ፈዛዛ መሞላት፤
. በቅድስና ጉድለት ማገልገል፤
.መዋሸት፤
. በገንዘብ ታማኝ አለመሆንና በሌሎቹም የሥጋ ሥራዎች መያዝ፤
. በቂም በበቀልና በእልህ ማገልገል

8. መንፈሱ የሚወጣበት መንገድ

ነጻ የወጣና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የተሞላ ሰው ከሰይጣን ጋር ለተወራረሰው ሰው ሲጸልይለት በሰውየው ራስ ላይ ወይም የተቀበረው ነገር ባለበት የአካሉ ክፍል ላይ እጁን ጭኖ መጸለይን  አገልጋዩ መርሳት የለበትም፤ ክታብ በአንገቱ ፤ በክንዱ፤ በወገቡ፤ ላይ ቢኖር መበጠስንና ከዚያ በኋላ እንዳይሠራ በኃይለኛው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ማዘዝና ቃል ማስገባትን ከዚያም ክታቡን ማቃጠልን አለመርሳት ነው።

ከሰይጣን የተወራረሱ ሰዎች ነጻ እንዲወጡ በሚጸለይበት ጊዜ

. አንዳዶች መናፍስት ቶሎ ጮኸው ይወጣሉ፤
. በአንዳዶች አካል ላይ የተቀበረው ነገር ፈንድቶ ከደም ጋር ይፈሳል፤
. አንዳዶች በመጠጥ ወስደውት የነበረው በትውከት ይወጣላቸዋል፤
. ከንዳዶች ግን ለማስወጣት ረጅም የጾምና የጸሎት ጊዜ ይጠይቃል።

እንደዚህ ያሉ ሰዎች ነጻ ከወጡ በኋላ በእጃቸው ያለው የአስማት መጽሐፍና ሥራ ሥር ሁሉ ቀርቦ ከተጸለየበት በኋላ መቃጠል አለበት የሐዋ 19፥19-20።

ሰውየው ነጻ ከወጣ በኋላ እውነተኛ ንስሐ ሊገባ እና ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ ነጻ አውጭ መሆኑን በጠላቶቹ ላይ ማወጅ አለበት፤ ጠላቶቹ ሁሉ የእግሩ መረገጫ ይሆናሉ ፤ በኢየሱስ ስም ካልሆነ ግን በሌላ ስም ወይም በዱላ አጋንንትን አወጣለሁ ብሎ መሞከር ድራማ ነው። ሰይጣን የወጣ ለመምሰል አውቆ ይጮሃል እንጂ ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ አይሸነፍም።

በእንጦጦ፤ በሽንቁሩ ሚካኤል፤ በጻድቃኔ ማርያም፤ በአቃቂ፤ በዱከም የሚደረጉትን የጥንቆላ ጥምቀቶችን አደራረጋችውንና አሠራራቸውን የአጥማቂዎችን ታሪክ ጨምረን ከነአስማታቸው ወደ ፊት እናቀርባለን

ተስፋ ነኝ

8 comments:

 1. ይሄ ይሄ ጉዳችን ይሆን ቤተ ክርስቲያናችንን ምስቅልቅልዋን ያወጣው? በጣም የሚያሳዝነው ብዙ የጥንቆላና የሙዋርት ስራዎች በክርስትና ስም እና በቅዱሳን ስም መከናወኑ ነው። በየጸበል ቤታችን ሰይጣንን ለማውጣት የምንሞክረው በዱላ እና በሌላ ስም እንጅ ሀይለኛው የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ብዙም አንጠቀምበትም። በየውቃቤ ቤቱ የሚካኤልና የገብርኤል ስእል ተሰቅሎ ይስተዋላል? ምን ማለት ነው? አይናችንን ከክርስቶስ ላይ እንድናነሳ የሰይጣን ተንኮል አይደለምን?

  ReplyDelete
 2. Yes, our church is infested with tenkwayoch and tinkola. However, St. Mary, the angels and the holy saints have nothing to do with that. By relating the satanic tinkola some defteras do to the holy saints of God, you are insulting God Himself. This is because the saints are the servants of God; they bear His holy name; God is always with them.

  Please don't try to use the tinkola to defame the saints and belittle their value to the human race. Again, tinkola is from satan while veneration of the saints is from God. Let's attack the tinkola and tenkwayoch, not the saints.

  ReplyDelete
 3. እናንተ እነማናችሁ?

  ReplyDelete
 4. በሃገራችን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ የቄስ ክብሩ ድግምቱ መሆኑን ሁላችንም የምናዉቀዉ ሃቅ ነዉ ፡፡ ለዚህም ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ከፍተኛ ክብር የሚሰጠዉ የትምህረት ዓይነት የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት ሳይሆን ጥንቆላና አስማት ነዉ ፡፡ ይህንንም ትምህርት የሰይጣን ስራ ዉጤት መሆኑን ለመደበቅ “ጥበብ” ብለዉ ይጠሩታል ፡፡ ለዚህ እኩይ ስራ በማስተማሪያነት የሚዉሉ እጅግ በርካታ የአስማትና የጥንቆላ መጽሃፍት ከዉጭ ሃገር ተተርጉመዉ በግዕዝ እና በአማርኛ በየቤተክርስቲያኑ እና በየአድባራቱ ይገኛሉ ፡፡ ዓዉደ ነገስት፤ዐቃቤ ርዕስ፤መድፍነ ጸር ፤ልሳነ ሰብዕ እና የመሳሰሉት ለዓብነት ያህል የሚጠቀሱ የአስማትና የጥንቆላ መጽሃፍት ናቸዉ ፡፡ እነዚህን መጽሃፍት በመጠቀም በየአድባራቱ እና በየቤተስኪያኑ ድግምት ይተበተባል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንዲህ ያለ በሳል አስተያየት የመጀመሪያዬ ነዉ ፡፡

   Delete
  2. ከፍ ሲል የሚታየዉን አስተያየት የሰጠሁት እዉነተኛዉን እምነት ፍለጋ ባደረኩት ጥረት የደረስኩበት ሲሆን ፤፤ ትክክለኛዉን እምነት ለመረዳት አእምረዊ እና መንፈሳዊ ምርምሮችን አድርጌያለሁ ፡፡ በመጨረሻም ወደ እዉነቱ እግዚያብሄር መራኝ ፡፡በዚህ ዙሪያ ሰፊ እዉቀት ስላለኝ ብዙ ማለት እችላለሁ

   Delete
 5. አስተማሪ ጽሁፍ ነው አንዳንድ ነገሮች ለማነጻር አማራጭ አልተቀመጡም ለምሳሌ በድርሳናት ላይ
  ያሉ ኅቡዕ ስሞች እንደ ድርሳነ ሚካኤል የእግዚአብሔር ስም አለመሆናቸውን በማስረጃ አልተደገፉም በደፈናው እመኑኝ ናቸው ማለት ይከብዳል።የሰሎሞን ጥበብ አይሁዶች በሰፊው የሚጠቀሙባቸው ድግምቶች ለምርምር ክፉንና ደጉን ለመለየት ለማስረጃ ኢንተርኔት ላይ አሉ።
  በሐገራችን ብዙ ነገሮችን ከማስተማር ምስጢር አድርጎ መያዝ የተለመደ ነው።ጸሀፊው ተስፋ ሕዝቡ
  እንዲነቃ የክፉውን ሴራ በማጋለጥህ አመሰግንሀለሁ።

  ReplyDelete
 6. u ppl didnt get it at all yetu new asmat yemetelanen tetay malet negus dawit said also that yemeyasadedugne be huwalachew yemelesu it isnot asemat u pente are really idiots u have no clue about the bible at all very jugmental and work for european and american protestants who want to renew ethiopian orthdox church jil neger nachu betam hula ker ....pls close these page enanten belo orothdox adash kkkkkkkkkkkkkkkkkk

  ReplyDelete