Wednesday, May 25, 2011

ያልታረሙ ድርሰቶች ባልታረሙ ሰዎች - - - READ PDF

ማህበረ ቅዱሳን የቀኝ ዐይን ድንግል ማርያም በሚል ርዕስ በድረ ገጹ ላይ ባስቀመጠው ድርሰቱ የሚከተለውን ድርሰት መሰረት በማድረግ ጽሑፍ አስቀምጦአል። ሙሉውን የማሕበረ ቅዱሳን ጽሑፍ (በዲያቆን ብርሃኑ አድማስ የተደረሰ) ከዚህ በታች ባለው ሊንክ በመሄድ ማንበብ የሚችሉ ሲሆን የዲያቆን ሉሌን መልስ ከዚህ በታች ያንብቡ።

አንቲ ውእቱ ረዳኢተ ያዕቆብ በቤተ ላባ

ትርጉም፦ በላባ ቤት ያዕቆብን የረዳሽው አንቺ ነሽ ማለት ነው


http://www.eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_content&task=view&id=641&Itemid=1


ማህበረ ቅዱሳን በአጋንንት የሚመራ ማህበር ነው። የጥንቱን የመናፍቃን ድርሰት ዛሬም እንደ አዲስ እያስተማረ ቤተ ክርስቲያንን እያዋረደ ነው የሚለው ጩኸታችን ከእውነት የራቀ አይደለም። ያልታረሙ ድርሰቶችን ገና ለገና ረጅም እድሜ አስቆጥረዋል በሚል ሚዛን ብድግ እያደረጉ ማስተማር ትልቅ ውድቀት ያመጣል ለዚህ ነው ስሕተቶቻችን ይታረሙ እያልን የምንጮኸው።

ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ ማን ዲያቆን እንዳረገው እና ማን የሃይማኖት አስተማሪ አድርጎ እንደሾመው አይታወቅም ነገር ግን የጌታን ቃል በጌታ መንፈስ ሳያጣራ የመካከለኛው ምሥራቅ መናፍቃን በቤተ ክርስቲያናችን የጣሉትን ክህደት እንደ ትልቅ ነገር ሲያሰራጭ ይኖራል።

ሰውየው በጭፍን የሚጽፍ የህሊና እውር መሆኑን በዚህ ጽሑፉ ለመረዳት አያዳግትም ‚ያዕቆብን በላባ ቤት የረዳሽው አንች ነሽ‚ የሚለው የካሃድያን ድርሰት እንደ ቁም ነገር አድርጎ ጽፎታል።

ለመሆኑ ያዕቆብን በላባ ቤት የረዳው ማን ነው?

ያዕቆብ ከወንድሙ ከኤሳው ጋር በነበረው ግጭት በናቱ ምክር ተነሣሥቶ የተወለደበትን እና ያደገበት ሀገር ትቶ ወደ አጎቱ አገር ወደ ላባ መሰደዱን እና በዚያም በላባ ቤት 14 ዓመት ሲያገለግል ኖሮ መመለሱን መጽሐፍ ቅዱስ ይተርካል ዘፍ 28፥6-22።

መጀመሪያም ያዕቆብ ስደቱን ሲጀምር እግዚአብሔር እንዲረዳው ስለት በመሳል ነበር

ያዕቆብም ማልዶ ተነሣ፥ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፥ በላዩም ዘይትን አፈሰሰበት።
ያዕቆብም ያንን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው አስቀድሞ ግን የዚያች ከተማ ስም ሎዛ ነበረ።
ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ። እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥
ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ፥ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል
ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ‚ ይላል ዘፍ 28፥20-22።

ያዕቆብ እንደ ብርሃኑ አድማሱ መናፍቅ አልነበረም። ለማን መሳል እንዳለበት ማንን ማምለክ እንደሚገባው፤ ማንስ ሊረዳው እንደሚችል ያውቃል፤ ስለዚህ ስለቱን ለግዚአብሔር ተሳለ፤ እውነትም የለመኑትን የማይነሳ የነገሩትን የማይረሳ ጌታ ለያዕቆብ በሄደበት ሁሉ መልካም አደረገለት እግዚአብሔር ከርሱ ጋር ሆኖ ረዳው።

ላባ ደሞዙን ብዙ ጊዜ ሊያታልለው ሞክሮ ነበር እግዚአብሔር ግን ያላባን ማታለል ለያዕቆብ በረከት አደረገለት። ያዕቆብ እግዚአብሔር የረዳው መሆኑን እንዲህ ሲል መስክሯል


ያዕቆብም ልኮ ራሔልንና ልያን ወደ በጎቹ ስፍራ ወደ ሜዳ ጠራቸው፥
እንዲህም አላቸው፦ የአባታችሁ ፊት ከእኔ ጋር እንደ ዱሮ እንዳልሆነ አያለሁ ነገር ግን የአባቴ አምላክ ከእኔ ጋር ነው።
እኔ ባለኝ ጕልበቴ ሁሉ አባታችሁን እንዳገለገልሁ ታውቃላችሁ።
አባታችሁ ግን አታለለኝ፥ ደመወዜንም አሥር ጊዜ ለወጠ እግዚአብሔር ግን ክፉ ያደርግብኝ ዘንድ አልፈቀደለትም።
ደመወዝህ ዝንጕርጕሮች ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ዝንጕርጕሮችን ወለዱ ሽመልመሌ መሳዮቹ ደመወዝህ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መሳዮችን ወለዱ።
እግዚአብሔርም የአባታችሁን በጎች ሁሉ ነሥቶ ለእኔ ሰጠኝ።
እንዲህም ሆነ በጎቹ በጎመጁ ጊዜ ዓይኔን አንሥቼ በሕልም አየሁ እነሆም፥ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ሽመልመሌ መሳዮችና ዝንጕርጕሮች ነቁጣ ያለባቸውም ነበሩ።
የእግዚአብሔርም መልአክ በሕልም። ያዕቆብ ሆይ አለኝ እኔም። እነሆኝ አልሁት።
እንዲህም አለኝ፦ ዓይንህን አቅንተህ እይ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ሽመልመሌ መሳዮችና ዝንጕርጕሮች ነቁጣ ያለባቸውም ናቸው ላባ በአንተ ላይ የሚያደርገውን ሁሉ አይቼአለሁና።
ሐውልት የቀባህበት በዚያም ለእኔ ስእለት የተሳልህበት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ አሁንም ተነሥተህ ከዚህ አገር ውጣ፥ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመለስ‚ ዘፍ 31፥4-14። 

እንግዲህ እግዚአብሔር ምንም በያሻማ መልኩ ያዕቆብን የረዳው እግዚአብሔር እንደነበረ ይናገራል ‚ስእለት የተሳልህባት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ‚ ብሎ ያናጋረው ድንግል ማርያም ናትን ወይስ እግዚአብሔር? ያዕቆብ በስደት በነበረበት ጊዜ ድንግል ማርያም ነበረችን? ድንግል ማርያም በኋላ ከኢያቄምና ከሃና የተወለደች አይደለምን እርሷ በሌለችበት ዘመን እንዴት አድርጋ ያዕቆብን ረዳችው?

በነገራችን ላይ ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ የጠቀሰው የክህደት ድርሰት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተባለው የዘራ ያዕቆብ የቅርብ ሰው ከመካከለኛው ምሥራቅ መናፍቃን ያመጣው ነውር ነው። ልብ ቢኖረውማ ያዕቆብን በላባ ቤት የረዳሽው አንቺ ነሽ በማለት የጌታን ለማርያም በመስጠት አይዘባበትም ነበር። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የ እውነተኛ ሊቃውንትን ድርሰት እርሱ ለማርያም እየቀየረ የነአባ እስጢፋኖስ ዘጉንዳጉዴ ንጹሕ የምስጋና ድርሰትን ከራሱ ድርሰት ጋር እየቀላቀለ አጼ ዘራ ያዕቆብን ያስደሰተ ግለሰብ ነበር።

ሰውየው ሰይጣንን ይዞ የቤተ ክርስቲያን የድንጋይ ደወል እንዲያመጣና ያን የድንጋይ ደወል እየመታ እንዲያገለግል ያደረገ ባለሙያ ነበር [ታሪኩ እንደሚናገረው]ቅዱሳን ሰይጣንን በኢየሱስ ስም ያባርሩታል እንጂ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ሊያደርጉት አይችሉም ምክንያቱም ሐሳቡን አይስቱትምና፤ ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ እንጂ በርኩስ መንፈስ አትገለገልም። ክርስቶስ ከሰይጣን ጋር ምን ሕብረት አለው? ተብሎ ተጽፏል 2ቆሮ 6፥15። ሰይጣንን እየጎተቱ አገልጋይ ማድረግ የደብተራዎች ስራ ነው ይህም የባቢሎናውያንና የከናናውያን ልምምድ ነው።

ገድለ ተክለ ሃይማኖት ም 48 ላይ ተክለዬ ሰይጣንን ገርዘው አጥምቀው፤ አመንኩሰው ስሙን ክርስቶስ ሐረዮ ብለው ሰይመው የደብረ ሊባኖስ አገላጋይ አድርገውት እንደነበር ይተርካል፤ ሲሞትም ፍታት ተፈቶለት ተዝካር ተበልቶለት ወደ መንግሥተ ሰማያት ገባ በማለት ይደመድማል። ወደ የትኛው መንግሥተ ሰማያት እንደገባ ግን ሰይጣንና የገድሉ ጸሐፊ ያውቁታል። ይህ የደብተራዎች ልምምድ መሆኑን በርካታ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይናገራሉ። ይህን ታሪክ በሰፊው እንመለስበታለን። ይህን ሃሳብ ለማንሳት የተገደድነው ዛሬም ማህብረ ቅዱሳን ይህን ነውረኛ ታሪኮችን የቤተ ክርስቲያናችን ብቸኛ እውነት አድርጎ እያስተማረና ትውልድ እየበከለ በመገኙቱ የቤተ ክርስቲያናችን እውነት አይደለም በማህበረ ቅዱሳን የስሕተት ትምህርት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መነቀፍ የለባትም የሚል አቋም ስላለን ነው።   
  
 አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ተብሎ የሚታወቀው የቤ/ክርስቲያናችን ሊቅ የቀለደውን ቀልድ እንመልከት-አንድ ቀን ውዳሴ ማርያም እየደገመ ባለበት ሰዓት ዓይነ ምድር መጣበት፤ ነገር ግን እንዴት አይነ ምድር እየወጣሁ የመቤቴን ስም እጠራለሁ ? የሚል ጭንቀት አደረበት ምክንያቱም ሰውየው ለሰከንድ እንኳ ውዳሴ ማርያም ከመድገም ስለማያቆም ነው ይላል ገድሉ። በኋላ ግን ለመቤቴ እንዲህ በማለት ነገራት፦ እመቤቴ ምስጋናሽን ማቋረጥ አልችልም  ባይነ ምድር ጊዜ ግን ስምሽን ለመጥራት ተቸግሬያለሁ እባክሽ መቀመጫየን ድፈኝልኝ አለ ይላል ገድሉ። ከዚያም እመቤቴ ለዘላለሙ መቀመጫየን ደፈነችለኝ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዓይነ ምድር ተቀምጨ አላውቅም፤ በማለት በጌታችን እናት በቅድስተ ቅዱሳን ወላዲተ አምላክ ክብርት እና ልዩ እናታችን ላይ የቀለደ ሰው ነው።

እንዲህ ዓይነቱ ድፍረትና ቀልድን በወላዲተ አምላክ የሚናገር ሰው ምን መንፈሳዊ ነገር ይገኝበታል? ያዕቆብን በላባ ቤት የረዳሽው አንቺ በማለት ከንቱ ውዳሴ ለማርያም ሲያቀርብ ቅድስት እናታችን አዎ አሜን ብላ ትቀበለኛለች ብሎ አስቦ ይሆን? በውነቱ እናታችን ይህን ያላደረገችውን ሲናገሩላት እጅግ የምትጸየፈው አይደለምን? እርሷ ያልነበረችበትን ታሪክ አንቺ ነሽ ያደረግሽው እያሉ ሲዘባበቱባት እግዚአብሔርስ እንዴት ዝም ይላል?

የማህበረ ቅዱሳን አባላት አእምሯቸው በአጋንንት መንፈስ ታውሯል። እንክርዳዱን እና ስንዴውን መለየት ሳይችሉ አስተማሪ በመሆን የሰሜን አፍሪካና የመካከለኛው ምሥራቅ መናፍቃንን ድርሰት ለትውልዱ እያስተማሩ እየበከሉ ነው፤ ይታረሙ የምንለው ዝም ብለን በጥላቻ አይደለም።

ይህን በመሳሰሉ ድርሰቶች እርማት ካልተደረገ እነዚህን ድርሰቶች ተከትሎም የመጣውን የባዕድ አምልኮ ልምምድ ከቤተ ክርስቲያናችን ካላስወገድን ሁልጊዜ ለምን በሐፍረት እንኖራለን?፤ ማህበረ ቅዱሳንም የመናፍቃቃንን ትምህርት ማስተማሩን ትቶ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ዘወር ይል ዘንድ ለምን እምቢ አለ?

ዲያቆን ሉሌ ነኝ

26 comments:

 1. Of all the critics who posted on this site, Deacon Lule has done a good job on this piece. Your points are genuine concerns and questions. Whoever can answer the questions should respond.

  I also don't agree that Satan has any form of salvation. I agree our church is infested with lots of deftera writings and tinkola type practices. Unfortunately, the Synod/ the Leqawint Gubae is lame and completely incompetent.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ያዕቆብ እግዚአብሔርን በትግል አሸነፈ እንዴት፤ በልዓም ኢአማኒ ሆኖ ሳለ የእግዚአብሔርን ሕዝብ መባረክና መርገም ይችል ነበር እንዴት ። መላዕክት ከሰዎች ጋር ተጋብተው ተዋለዱ በምን ተኣምር ።እግዚአብሔር አብርሃም ጋር ምግብ በላ እንዴት ይበላል እንዴ ። የኤለሳ አጥንት ሙት አስነሳ እንዴት ። ሶምሶም የአንበሳ ደቦልን እንደፍየል ጠቦት ቆራረጠ። የእግዚአብሔር መንፈስ ወርዶበት ምንም ያላደረጉ ሰዎችን ለልብስ ሲል ገደለ በእግዚአብሔር መንፈስ መግደል ይቻላል ። ሳሙኤል አጋግን በእግዚአብሔር ፊት ቆራርጦ ገደለው ያ ከልጅነት የተመረጠው ሳሙኤል ነፍሰገዳይ ነው ለካ ። ዳዊት የአንበሳና ድብ ማጅራት መቶ ይገድል ነበር። አረ ስንቱይነገራል በእምነት ካልሆነ የማንቀበላቸው ብዙነገሮችን መጽሀፍ ቅዱስ ይዟል። ከላይ የሰፈሩትሁሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ የ ተገኙ ናቸው። አቶ ሉሌ የሩቅ ምስራቅ እምነት የምትለው የምዕራቡ ይሻላል ለማለት እና ወደ ፕሮቴስታንት ለመጠጋት ካለሆነ ማመን ካለማመን ይሻላል። እመቤታችን አለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በአምላክ ልቦና ታስባ ትኖር ነበር ማለት ኣምላክ ቀጥሎ ምን እንደሚመጣ ያውቃል ለማለት ነው። ተሀድሶ ነህና እንከን ትፈልጋለህ ፤ አባቶችን ለማዋረድና የቤተክርስቲያንን ልጆች ጥርጥር ውስጥ ለመክተት ። ከላይ የጻፍከውን ከመጠራጥርህ በፊት በመጽሀፍ ቅዱስ የተጻፉ በእምነት ካልሆነ ልንቀበላቸው የማንችላቸው ብዙነገሮች ኣሉና ለእነሱ መልስ ስጥ። እባብ ሄዋንን አታለለቻት እንዴት በምን ቋንቋ አረ ስንቱ በል ሉሌ ከላይ ላሉት ከእምነት ውጭ ሆነህ ኣሳምነኝ። እኛ ተዋህዶዎች በእምነት እንኖራለን ። ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሔር ይቻላልና።

   Delete
 2. ኦርቶዶክስMay 26, 2011 at 8:01 PM

  ዲያቆን ሉሌ፥ አሁን ጉዱን አወጣኸው እኮ። እውነት ተናጋሪ አያሳጣን። ይህችን ጥንታዊት እና መጽሐፍ ቅዱሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንን ሰይጣን ሲታገላት ይኖራል። በብዙ በኩል ስናየው በጣም ስኬታማ ሆኖ እናስተውለዋለን። አሁን ሰይጣንን ድል መንሳትና ወደ ቀደመ ወንጌላዊነታችን መመለስ ይኖርብናል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ዝባዝንኬዎች የሰይጣን ስራዎች ስለሆኑ እግዚአብሔር እንዲያስወግድልንና ህዝባችን ዓይኑን ወደ ክርስቶስ መስቀል ብቻ እንዲያዞር ይርዳን።

  ReplyDelete
 3. ለዲያቆን ብርሃኑ አድማስ
  አሳፈርኸን ለምን አጣርተህ አትጽፍም ?ያዕቆብን በላባ ቤት የረዳሽው አንቺ ነሽ የሚለው በድንግል ማርያም ላይ መዘባበት ነውኮ ምን ዓይነት ችግር ውስጥ ነው ያለነው ጎበዝ? አሁን ጊዜው ገና ነው ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ መልስ ስጥበት እባክህ እኛ ራሳችን እርማት ሳናደርግ ተሐድሶ ተሐድሶ እያልን ብንጮህ ነገሩን ባሰበት እንጂ ለውጥ አላመጣንም ተሃድሶዎችን የምናጠፋ ስሕተቶቻችንን በማጥፋት ነው የሚል እምነት አለኝ
  ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ አንተስ ምን ትላለህ?

  ReplyDelete
 4. Menafik Yeweladite Amlak Sim sinesa yibesachal. Miknyatum seitan siladerebet. Beantsaru Menfes Kidus yaderebet sew Emebetachinin Yiwedal. Silezih wanaw Menafik lule new.

  ReplyDelete
 5. Selam all,
  I knew both of you. I also read the link you gave us. There is no issue about what you are menthioning. It seems you want to blame MK and Dn.Birehanu. There is no concert points in your writing. It is not a character of christian to mislead people.

  ReplyDelete
 6. ዲያቆን ሉሌ እግዚብሔር ይስጥልኝ። እንደምታውቀቅ ብዙዎቻችን እውነት ትመረናለች በተለይ ሲነገረን ከኖረው ውሸት ጋር የሚጋጭ ከሆነ። ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምን እንወዳለን እናከብራለን እግዚአብሔር ሰውን ሊያድን ወደ ምድር ሲመጣ ዙፋኑ አድርጎ መርጦአታልና። ለእመቤታችን የምንሰጠው ክብር ግን ያልሆነውን ነገር በመቀባጠር አይደለም። በላባ ቤት ያዕቆብን የረዳሽው? ጉደኛ ነህ! ምን አይነት ውሸት ነው ይሄ ደግሞ። የድንግል ማርያም እናት እና አባት እንኳ ከመወለዳቸው በፊት የሆነውን ታሪክ እንደዚህ ብሎ መናገር ምን አይነት ስካር ነው?

  ReplyDelete
 7. Can anyone tell me the paragraph and line numbers in Deacon Birhanu's article where he says the alleged words regarding St. Mary? I skimmed through the paper, but I did not see the alleged statements.

  ReplyDelete
 8. Yared,

  Right below the icon (picture) in red/orange color. It is in Geez. አንቲ ውእቱ ረዳኢተ ያዕቆብ በቤተ ላባ

  Maybe Dn. Birhanu doesn't really understand Geez, so he probably doesn't know what he wrote

  ReplyDelete
 9. Thanks Anonymous. Do you have any idea where these words are used in the church? Is it among the melka-melks? I assume Dn Birhanu adopted it from some source. Or did he just created it himself? Unfortunately, lots of dirset/wrtitings have been adopted by EOTC without proper review for consistency with the bible. I believe some of the ethiopian emperors have contributed for this problem. Why adopt a dirset that does not reflect the proper doctrine of the church? I think "kemen aneshe" bemil felit yetelaeyau defteras wrote bad dirsets that are not disturbing the church.

  For example, Mk at one point sang a song as follows:

  " Yeamilk chinkaruma amist bicha neber:-
  Yeamilk chinkaruma amist bicha neber:-
  Yeantema Giorgis ejig girum neger::"

  Any one who has basic understaning of Christianity cannot compare the sufferings of Christ with those of the saints/martyrs, leave alone decalring the latter to be superior to that of the former. By singing the above, MK has shown how ignorant it is. Future generations may quarrel about this song like we are not exchanging fires over the writings the old time defteras.

  In conclusion, the statement used by Dn. Birhanu is not clear to me even if I understand some of the comparisons used in the Liturgy of St Mary, such as Yeyaecob Meselal, Yeaberham Dinkuan/Engidinet, Yedawit Mesenko, etc..., . Nor does it sound right. Dn Birhanu needs to explain and answer all the questions raised.

  ReplyDelete
 10. Yared, you just nailed it. Agree with everything you said.

  ReplyDelete
 11. You guys, I hate Tehadisos since they insult our church and they are pro protestants but today I agree with them. As a chuch servant I see so many problems in some of our books. Specially in books "Sehatat" sorry to say many people including me like it but it has problems as mentioned above.

  My recommendation is if the church can correct them. They might have some "Mister" but they are not easily acceptable by people. How can Marry be called "Helper of Jackob"? Now way to accept it as an orthodox Christian.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Before you want decide why he said this. try to understand contextually. ኦሪት ለወንጌል ጥላ መሆኗን ረሳችሁኮ።

   Delete
 12. I think dn. birahanu does not know about Bible . come on deacon do not teach and prech this kind of heretics teaching. Donot preach gidil or dersan they are aganist the Holy Bible.

  ReplyDelete
 13. ወንጌልን አስዎጥተን የራሳችን የሆነውን ወንጌል አስገባን ነገር ግን ኦርቶዶክስ የሚለውን የደርጅት ስም ሙሉውን እንዳለ ወስድን መቀየሩ አስፈላጊ ስላልሆነ። ስለዚህ የፈለግነውን ብንሰብክ በራሳችን ቤት ስለሆነ ማነው ከልካዩ የራሳችሁን የድሮውን ወንጌል መስበክ ከፈለጋችሁ የራሳችሁን ድርጅት ማቋቋም ወይንም ከቻላችሁ የኛኑን በግድ መውረስ ይኖርባችኋል እኛ እንዳደረግነው ማለቴ ነው። ያቆብን የረዳሽው ዘጋስጫን የደፈንሽው ጊዎርጊስ የተፈጨው ተክለሃይማኖት የቀዘነው የያቆብ መሰላል የኦርቶዶክስ ብርሃን ለአንች ብቻ ሳይሆን ለስእልሽ ምስጋና ይገባል ብንል ማነው ከልካዩ? ማንም ቄስ የያዘውን የእንጨት ሆነ የብረት መስቀል ተሳለሙትም አመስውግኑትም( ስብሃት ለመስቀለ…..) ማነው ከልካዮ? እባካችሁ ጥንታዊቷ ኦርቶዶክስ እያላችሁ አታድክሙን ዘረዓ ያቆብ ያጸናውን ደብተራዎች የደገሙትን አሁንም የቤተክርስቲያን ቀሳውስት ጳጳሳትና ሲኖዶሱ ሊቀይረው ያልፈለገውን ምእመናኑም ቢቀየርም ባይቀየርም ሊገባው ያልቻለዉን በማህበረቅዱሳንም የዘወትር ስብከታቸው የሆነውን መቀየር እንዴት ሆኖ!!! ትገርማላችሁ የጥንቷ ኦርቶዶክሳውያን

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንድ ፊቱኑ አንተው ትሻላለህ ። ከውጭ ሆኖ መሳደብ ሰ ስጥ ሆኖ ከመሳደብ ይሻላል። በርግጥ ስድብን የወረሳችሁት ከአባታችሁ ከዲያቢሎስ ነው ። ይቅር ይበላችሁ።

   Delete
 14. ጸሀፊው ከጨዋነት የወጣ አነጋገር መጠቀምዎትን አልወደድኩልዎትም ማን ዲያቆን እዳደረገው አይታወቅም የሚለው የጥላቻዎን ዳራ የሚያሳይብዎት ከመሆን ውጭ በእርስዎ ያልታወቀ ክህነት ተቀባይነት እንደሌለው አድርገው ያስቀመጡ ያስመስልብዎታል ሌላው የእርስዎን የጽሁፍ መነሻ መሰረት አድርጌ የዲ.ብርሃኑን ጽሁፍ ደጋግሜ ባነበው እርስዎ ያጣጣሉትን አባባል በእርሱ ጽሁፍ ውስጥ ላገኘው አልቻልኩም ስለዚህ ያላለውን እንዳለ አድርገው በማቅረብዎ ከእርሱ ጋር የግል ጸብ ይኖረዎታል ብዬ ከድምዳሜላይ ደረስኩ ለጽሁፍዎት መነሻ ያደረጉት ቃል በመጽሐፈ ሰዓታት ላይ የሚገኝ መሆኑን እኔም አውቃለሁ ዲ.ብርሃኑ ግን በጽሁፉ ውስጥ ስለ አርሱ ያነሳው ነገር የለም የድረ ገጹ አዘጋጆች ለጽሁፉ መግቢያ ባደረጉት ስዕለ ማርያም ላይ አባባሉን አስፍረውት ከማየት ውጭ እርስዎ በዲያቆኑ ላይ እንዲዎርዱበት ምክንያ የሆነ ነገር ባለማየቴ ግራ ገብቶኛል ይህ አስተያየቴ በበጎ ይታይ

  ReplyDelete
 15. i know Dn brehanu and i know where and how he gets his maereg. It seems u went out of line when speaking abt someone u donot know well.i really wast my time reading this scam. i feel sorry for u. a word of advice; pls read well before you write.

  ReplyDelete
 16. i know and i understand your starategy
  all the persons wh give comment are almost one person
  unfortunately i am a professional of web based architecture
  u seem to show that u have so many readers and followes
  u need to show blaming the church

  let me tell u what i understand from all your articles and tehadso movement :-

  1- your enemy isnot mahibere kidusan ,but the church
  2- when u want to blame the church u make mahibere kidusan a reason

  3- u are simply an ethiopian missionary sent from europeans and others

  So what ever u do , what ever u move , what ever u write .... u can do nothing without the will Of God
  But what happens now is expected
  as the church passed so many wars

  Libona Yistachihu

  ReplyDelete
 17. Anonymous above: if are you so smart that you can tell who commented etc, the topic discussed in this article should not have been so difficult for you. YOur 3 point conclusions are kind of weak. If you don't already know Mahberekidusan is the enemy of our church, you must be a member and brainwashed to not be able to see reality.

  ReplyDelete
 18. i am the one who gave u the 3 comments
  u answered for me
  good
  but why don't u give a reply to the above comments who give u a negative comment
  do u know why ? it is given by your self

  u write the blog
  u write the comment
  u write the answer
  and u act as if u have so many reader
  i am not a fan of Mk but i am an orthodox christian
  simply when a person writes a negative comment u will say Mahibere kidusan
  why not directly u say we have our own belief , teaching which is different from the Orthodox church
  why don't u clearly state your self ?
  what so ever the case it may be by the blessing of God and will Of God u can do nothing
  Our Lord and our Holy savior is always with us

  i always pray for those persons like u to get Libona even though i am a sinner.
  but i strongly tell u that what u are doing now will be be rewarded by God with a good punishment
  May God Bless U
  May Gd Be with U
  MAy God Libona Yistachihu
  i wish after u confess we will be in one church to praise our Lord
  this is my always wish

  ReplyDelete
 19. it's really funny when u insult our church u don't have any idea. about what religion means.

  ReplyDelete
 20. he's name is luley he was in prison b/c of reaped 13 years old girl so haw do u think he know ab religion

  ReplyDelete
 21. enantem bete yetemekerew egham bet temekroal.GOD BLESS MKIDUSAN.

  ReplyDelete
 22. the problem is you run for criticism, be responsible to serve your holy nation [the church] at least be good example, for me redaete Yacob be bete Laba has no problem if you think in symbolic theology, not in systematic theology, because it is for the motherhood of Jesus Mariam was chosen, and Yacob to be her ancestor, and the most important thing when you write you will be valued as you are valuing where did you find the Jock about Abba Giorgies

  Take care brothers or sisters

  ReplyDelete