Tuesday, June 28, 2011

"ንጉሱን ውጋና ግደለው" - Read PDF

 «ንጉሱን ውጋና ግደለው...» ሚለው ርእስ የተመረጠው ከአንድ ፃድቅ እንደሆነ ከተነገረለት ሰው የተሰጠ መመሪያና ይህም ትዕዛዝ ተግባራዊ ሆኖ ንጉሱ የተገደለበት ታሪክ እጅጉን ቢገርመኝ እውነት ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውን? የጻድቅስ ቃል ይህን ይናገራልን? የሚለውን ለመመልከት ስሞክር የተመረጡት ሕዝቦችም በአንድ ወቅት ስህተት ሰርተው እንደነበር ዛሬም እኛ ልዩና ምርጥ ሃይማኖተኞች እንደሆንን ብንቆጥር በሰው ልጆች ህይወት ውስጥ ሊያልፉ የቻሉ ስህተቶች እኛን እንደማይነኩን ከሚያስብ ትምክህት ወጥተን እምነታችንንና ልባችን የሚመካበትን መጽሐፍቶቻችንን በእግዚአብሔር ቃል አንጻር ልንመረምራቸው ይገባል እንጂ የራሳችን የሲና በረሃ የምንጭ ውኃ ያለን፤ የሚያጠግብ የምንቸት ቅቅል ያዘጋጀን፤ መናን ጋግረን ያዘነብን ያህል ቆጥረን ከኛ ወዲያ ላሳር ማለት ምርጥ ከተባሉት ከእስራኤላውያን እኛ በተለየ ስህተት አልባዎች ነን እንደማለት ይቆጠራልና የምንመካበትን ነገር እውነታ በሚመዝን የእግዚአብሔር ቃል ልንፈትሽ ግድ ሆኖ «ንጉሱን ግደለው» መጽሐፍ እንመዝነው፤ አብረን እንለካው፤ እውነታውን አስረግጣችሁ ለልባችሁ ንገሩ - ቀሪውን ለማንበብ የጽሁፉ ርዕስ ላይ ይጫኑ

Monday, June 27, 2011

ANNOUNCEMENT/ ማሳሰቢያ

Dear readers:
 As we have promised when we first launched this blog, we will continue to encourage you to express your opinion on any of the contents presented on this blog.  We acknowledge that most people within our church do not have a good habit of openly discussing opposing/controversial views.  Instead of trying to understand what the other party is trying to say, we usually find it easier to demonize people who do not share our views.  We believe that this lack of respect and lack of tolerance we have towards one another compromises growth of our church in the right direction. We hope that this blog will allow us to practice openness, respect and objectively discussing the various visions we all have for our church. To this end, we would like to announce that we will introduce minimal review of your comments before making them available for readers. The intent is only to filter out non-value added and emotional comments such as “ እናንተ ሌቦች ገሀነም ትገባላችሁ ….”.  This is an example of comments we would like to filter out because they are empty and do not add value to our discussions. However, we would like to assure you that as long as your comment is on the relevant article, it will not be rejected based on content.
God bless our union!
Abaselama blog

ውድ አንባብያን፦
እዚህ ብሎግ ላይ የሚሰጡ አስተያየቶች ኦርቶዶክሳዊ ጨዋነት የሚታይባቸውና በተጻፉት ጽሑፎች ዙሪያ ያተኮሩ እንዲሆኑ ስለምንፈልግ ስድቦችንና በውስጣቸው  ቁም ነገር የሌላቸውን አስተያየቶች ለአንባቢያን ለማቀረብ እንደማንወድ ከወዲሁ ልናስገነዝብ እንወዳለን። አስተያየቱ ከጭፍን ስድብ ያለፈና በተጻፈው ነገር ላይ ያተኮረ ማንኛውንም ሀሳብ ግን ለአንባብያን እናቀርባለን። የዚህ ብሎግ አንደኛው አላማ የአንዲት ቤተ ክርስቲያን ልጆች በሀሳቦች ልዩነት መጠላላት እና መገዳደል ሳይሆን በመከባበር፥በክርስቲያናዊ ፍቅር እንዲሁም በመቻቻል የመወያየት ልምድ እንዲያዳብሩ ነው። አእምሮን ሰፋ አድርጎ የተለያዩ ሀሳቦችን ለመረዳት መሞከርና ክርስቲያናዊ ጨዋነት የተሞላበት ውይይት ማካሄድ ለቤተክርስቲያናችንም ሆነ ለህብረተሰባችን መልካም ልምድ እንደሆነ እናምናለን።
አግዚአብሔር አንድነታችንን ይጠብቅ። አሜን
አባሰላማ ብሎግ

Sunday, June 26, 2011

በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ላይ መዋሸት ይቁም! - Read PDF

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጸጋን የተሞላች፣ በትሕትናዋ፣ በእምነቷ በቅድስናዋ ተወዳዳሪ የሌላት፣ አስደነቂውን መለኮታዊ ምሥጢር በልቧ በመጠበቅ እስከ መስቀል ድረስ የተገኘች ብቸኛዋ እናታችን ናት።

Thursday, June 16, 2011

የመጽሐፍ ቅዱስና የመልክአ ሚካኤል አለመግባባት - - - Read PDF

መጻሕፍት በመንፈስ ቅዱስ አሳሳቢነት በቅዱሳን አባቶች የተጻፉ የእግዚአብሔር መልእክት ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ  የታቀፉ እና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተወስነው የሃይማኖት ማስተማሪያ ሆነው የኖሩት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስድሳ ስድስት ሲሆኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተወስነው የቤተ ክርስቲያኒቱ የሃይማኖት መመሪያዎች ግን ሰማኒያ አንድ መጻሕፍት ናቸው። አንድ ሰው ሃይማኖቱ ትክክለኛነት ተመዝኖ ሊወገዝም ሆነ ሊመሰገን የሚችለው በነዚህ መጻሕፍት መሠረት ነው።

ጦቢያና ሰንበላጥ --- Read PDF

"ሐሮናዊውም ሰንበላጥና ባርያው አሞናዊ ጦቢያ ለእስራኤል ልጆች መልካምን ነገር የሚሻ ሰው እንደ መጣ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተበሳጩ፡፡ ሐሮናዊውም ሰንበላጥ ባሪያውም አሞናዊው ጦቢያ ዓረባዊውም ጌሳም በሰሙ ጊዜ በንቀት ሳቁብን (አፌዙብን) ቀላል አድርገውም ይህ የምታደርጉት ነገር ምንድነው? በውኑ በንጉሡ ላይ ልትሸፍቱ ዘንድ ትወዳላችሁን? አሉ፡፡" (ነህ. 210, 19) በመቀጠልም በምዕ 3 እና 4 "ሰንበላጥም ቅጥሩን እንደሰራን በሰማን ጊዜ እጅግ ተቆጣ ተበሳጨም በአይሁድም አላገጠ በወንድሞቹና በሰማርያ ሠራዊት ፊት እነዚህ ደካሞች አይሁድ የሚሰሩት ምንድነው? ይተዉላቸዋልን? ይሰዋሉን? ብሎ ተናገረ አሞናዊውም ጦቢያ በአጠገቡ ቆሞ በድንጋይ የሚሠሩትን ቅጥራቸው ላይ ቀበሮ ቢመጣበት (ቢተኛበት) ይፈርሳል አለ፡፡ እንዲሁም በእግዚአብሔር ቤት በመቅደሱ ውስጥ እንገናኝ የመቅደሱንም ደጆች እንዝጋ እነርሱ መጥተው ይገድሉሃልና በሌሊትም ይገድሉህ ዘንድ ይመጣሉና አለ፡፡ እኔም እግዚአብሔር ልኮት እንዳልነበረ በእኔ ላይ ግን ትንቢት እንደተናገረ እንሆ አወቅሁ ጦቢያና ሰንበላጥም ገዝተውት ነበር" እንዲል (ነህ፡610-13)

 ቀሪውን ጽሑፉ ለማንበብ የጽሑፉ ርዕስ ላይ ይጫኑ

Tuesday, June 14, 2011

ለውጥ ያስፈልጋል - - - Read PDF

ብዙ ጊዜ በሃይማኖት ላይ የሚካሄድ መንፈሳዊ ለውጥ እግዚአብሔር በቃሉ የገለጠውንና ለዘለዓለም ጸንቶ የሚኖረውን እውነት የማስጠበቅ ጉዳይ እንጂ አዲስ ነገር የመፍጠር፣ ወይም አዲስ ነገር የመፈልሰፍ ሂደት አለመሆኑን በተደጋጋሚ ለማሳየት ተሞክሯል። በመሆኑም በእግዚአብሔር እውነት ላይ የተጨመረና ከቃሉ ጋር የሚቃረነውን ባዕድ ነገር ማስወገድ፣ ከእግዚአብሔር እውነት ላይ የተቀነሰውንና የተሸራረፈውን ነገር እንደ ገና መመለስ የመንፈሳዊ  ለውጥ ዋና ተግባር ነው።

Wednesday, June 8, 2011

ማህበረ ቅዱሳን ከስም ማጥፋት ደም ወደ ማፍሰስ ተሻገረ ለዘማርያኑም የወንጌል ወግ ደረሳቸው - READ PDF

ባለፈው ጽሑፋችን ሰይጣን የኢትዮጵያውያንን ደም ለማፍሰስ ገና እያሰበ መሆኑን እና ባማህበረ ቅዱሳን አማካኝነት ቅሥቀሳ እያደረገ እንደሚገኝ፣  አስታውቀን ነበር። ይኸው ከተናገርን ገና ሁለት ሳምንት ሳይሞላን በተክለ ሃይማኖት ምክንያት በተክለ ሃይማኖት ደጀ ስላም [መርካቶ] ድብደባ ተጀምሯል።  
ዲያቆን ሙሉጌታ ወልደ ገብርኤል "ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን‚ በሚል እርስ ያሳተመው መጽሐፍ በጣም ተጋነነ ተብሎ ሲተች ሰምቼ ነበር መጽሐፉ ግን ዛሬ በተግባር የተረጋገጠ እውነተኛ ምስክርነት መሆኑን ከማህበረ ቅዱሳን ተግባር መረዳት እንችላለን። በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ ያለው መንፈስ ደም የማፍሰስ ጥማት ያለው መሆኑን በማጋለጥ ደጋግመን ብንጮህም የተገነዘበን ግን እጅግ ጥቂት ሰው ነው የሚል ስጋት አለን። እኛ ስም ለማጥፋት የተንሳን ሰዎች አይደለንም፣ በማህበረ ቅዱሳን ምክንያት የሚመጣው የርስ በርስ ጦርነትና የቤተ ክርስቲያን ለሁለት መከፈል ከወዲሁ የታየን አገር ወዳድና የቤተ ክርስቲያናችን ቅናት የሚበላን ኢትዮጵያውያን ነን እንጂ።

ማቅ - ስመ ቅዱሳንን የያዘው ማህበር - Read PDF

ስለዚህ ማኅበር አወላለድ በመምህር ጽጌ ስጦታው(ይነጋል) እና በዲያቆን ሙሉጌታ /ገብርኤል (ማኅበረ ቅዱሳን ወይስ ማኅበረ ሰይጣን) መጽሐፍ  ብዙ ብዙ ስለተገለጠ ለጊዜው ከዚያ የምጨምረው የለኝም ከተወለደበት የዝሙት ህይወቱ ባሻገር አሁን ባለው የገንዘብ አፍቅሮቱና ያልበላውን የሚያክበት የቤተክርስቲያንን ታዛ የተጠለለበትን መሰሪ አካሄዱን በተመለከተ ጥቂት ለማለት እወዳለሁ።

Friday, June 3, 2011

የማይሞተው ሞተ - Read PDF

መላከ ገነት ጽጌ የሚባሉ ሊቅ መሐለ እግዚአብሔር ለዳዊት በጽድቅ ወኢይኔስሕ ማለት እግዚአብሔር በእውነት ለዳዊት ማለ አይጸጸትም  የሚለውን ንባብ ሲተረጉሙ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አቋረጧቸውና እግዚአብሔር ከርሱ በላይ ያለ በማን ሊምል ነው ? አሏቸው። መላከ ገነትም ፈጥነው እኔ ልሙት ብሎ ማለለታ ጃንሆይ  ብለው መለሱ።  ጃንሆይም መማር እንደ ጽጌ ነው  አሉ ይባላል።