Wednesday, June 8, 2011

ማቅ - ስመ ቅዱሳንን የያዘው ማህበር - Read PDF

ስለዚህ ማኅበር አወላለድ በመምህር ጽጌ ስጦታው(ይነጋል) እና በዲያቆን ሙሉጌታ /ገብርኤል (ማኅበረ ቅዱሳን ወይስ ማኅበረ ሰይጣን) መጽሐፍ  ብዙ ብዙ ስለተገለጠ ለጊዜው ከዚያ የምጨምረው የለኝም ከተወለደበት የዝሙት ህይወቱ ባሻገር አሁን ባለው የገንዘብ አፍቅሮቱና ያልበላውን የሚያክበት የቤተክርስቲያንን ታዛ የተጠለለበትን መሰሪ አካሄዱን በተመለከተ ጥቂት ለማለት እወዳለሁ።
ማቅ መሰሪ የሚባልበት ዋናው ምክንያት በምሁራን እውቀትና ያለእውቀት ጭፍን የክርስትና አፍቅሮት ባላቸው አላዋቂዎች መጠቀም መቻሉ ነው። የቅዱሳንን ስያሜ በለበሰው ማቅ ተሸፋፍኖ እውቀት ባላቸው እና  በፍቅረ ክርስትና በሰከሩ ማይማን እንዴት እንደሚጠቀም አንድ ባንድ እንመልከት።
በምሁራን እውቀት መጠቀም ይህ ኃይል ማዕከላዊ የበላይነትንና አንድ ወጥ ተዓዝዞትን ለማስፈን ከአዲስ አበባው ማቅ ማዕከላዊ ቢሮ ጀምሮ በክልል ፤በዞን፤ በወረዳና በአጥቢያ የእስትንፋስ ሴሎችን የሚያዋቅር፤ የሚያደራጅና የሚመራ የኅልውናው አንቀሳቃሽ  ዋና ሞተር  ነው። ከላይ ወደታች ይተነፍሳል፤ ከታች ወደላይ እስትንፋስ ይቀበላል። የደም መልስና የደም ቅዳ(circulation) ዓይነት ሥራ የሚከውን ማቅ ማዕከላዊ ልብ ነው። ይህ አካል ማዕከላዊ የበላይነትን ሳይሸራርፍ ሌሎች አመላላሽ የደም ሥሮችን ገጥሞ በቤተክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ሕይወቱን ያመላልሳል። ይኸውም፣
1/ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ህግ በድንግልና ሳይኖሩ በድብቅ ልጅ የወለዱ፤ የእህቴ ልጅና የአክስቴ ልጅ እያሉ በቤታቸው ቅምጥ ያላቸው፤ በልጅነት ጊዜያቸው አግብተው የፈቱ፤ ከጊዜ በኋላም አዳማዊ ተፈጥሮ አሸንፎአቸው የጭናቸውን እሳት ለመተንፈስ የተገደዱ፤የቤተክርስቲያን ሙዳየ ምጽዋት በመገልበጥ የታወቁ፤ ከዜሮ ተነስተው ሃብታም የሆኑ ጳጳሳትንና መነኮሳትን ከገቡበት ገብቶ ማቅ አባል ማድረግ ዋና ስልቱ ነው። ይህ የሚጠቅመው የቤተክርስቲያን አመራርን የመቆጣጠርንና ላዩ ላይ ተጠምጥሞ የመተንፈሻውን ሳንባ ወደ ማቅ ማዕከላዊ ቢሮ ሳንባ ለመቀየር ሲባል ነው።
እነዚህ ልዩ ልዩ ችግር ያለባቸውን ሰዎች ለመያዝ መፈለጉ በግብር ከመመሳሰላቸውም በላይ ትርጉሙ ቀላል አይደለም። ይህ ማቅ በቅድሚያ የሰዎቹን የግል ማኅደር አገላብጦና በርብሮ በቂ መረጃ ከያዘ በኋላ ለአባልነት ሲመለምላቸው ግለሰቦቹ ይህ ከሳሽ ድርጅት መሆኑንና ገመናቸውን ጸሓይ ላይ ከማስጣት እንደማይመለስ አሳምረው ስለሚያውቁ አንድም ከባቴ አበሳ ከሆነው ከእግዚአብሔር ይልቅ ይህ ድርጅት እንዲሸሽግላቸው አለያም ከሌሎች ኃይሎች ጋሻ መከታ እንዲሆንላቸው በነዚህ ሁለት ምክንያት አገልጋይ ለመሆን ይገደዳሉ። ብዙዎቹ የዚህ ቡድን ደጋፊ ጳጳሳት በዚህ ጉዳይ የሚታሙ ብቻ ሳይሆን የሚታወቁ፤ ከፊሎቹም በቤተክርስቲያኒቱ ስም ከሚያንቀሳቅሰው የንግድና የልመና  ሼር ተቋሙ በጥቅም ያንበረከካቸው አንዳንዶቹም ፓትርያርክ ጳውሎስን ፈንግለን እናንተን ፓትርያርክ እናደርጋችኋለን በሚል የህልም የሹመት ፈረስ ያሰከራቸውን ታማኝ አገልጋዮቹም የአባሎቹ መነሻ ነጥብ ነው።በሶስተኛ ምክንያት ሊጠቀስ የሚችለው ደግሞ ከዚህ ከሳሽ ድርጅት ጋር መጋጨት ለቤተክርስቲያን የመሪነት ዕድገትና ለጵጵስና ሹመት ከመድረስ በአጭሩ እንዳይቀሩ ይህን ቡድን ወደመጠጋት ይሄዳሉ። ቡድኑም ገመናቸው የቱንም ያህል አስቀያሚ ሆኖ ለሹመት የማያበቃቸው ቢሆንም እንኳን የእርሱ ታማኝ አገልጋይ እስከሆኑ ድረስ የክስና የማሳሳቻ እስትንፋሱ በሆነው «ስምዓ ጽድቅ» እና «ሐመር» መጽሔቱ ላይ ቃለ መጠይቅ በማብዛት፤ የልማት አባት በማለት ዲስኩር በመርጨት፤ ተከታዮቹንና አገልጋዮቹን ሁሉ በማንቀሳቀስ እንዲሾሙለት ያስደርጋል። በተቃራኒው ደግሞ የሚታገሉትንና የክፋት አፉን ለመዝጋት ሌት ከቀን የሚደክሙትን ደግሞ ጥላት በመቀባት፤ የሃሰት ስም በማውጣት፤ ከመኮነንና ከመማስኮነን አልፎ ተርፎም ከድብደባ እስከግድያ የዘለቀ ሰይጣናዊ አገልግሎቱን ለመፈጸም የማይመለስ ለመሆኑ ድብደባውን የቀመሱ፤ ዛቻውን ፈርተው የተሰደዱ፤ የሞት ዕቅድ የተደገሰላቸው ከማንም በላይ ያውቁታል፤ እኛም ህያው ምስክሮች ነን።
2/ ሌላው በምሁራን የመጠቀም ብቃቱ የዓላማና የዕቅዱን መዳረሻ ማስፋት ሲሆን ይህም አባላትን አብዝቶ በመመልመል መጠመድ ነው። ይህም በዩኒቨርሲቲዎችና በኮሌጆች ነጠላ ለባሽ ተማሪዎችን ማደራጀት ነው። ከሃሺሽ የከፋ አለማወቅን በልባቸው ዘርቶ ዘሩን እንዲያባዙ የታማኝ አገልጋይነትን ባርኮት በላያቸው መተንፈስ ነው።
3/የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ልብ በመስረቅ የአጥቢያ ቤተክርስቲያንን የልብ ትርታ ማዳመጥ ሲሆን የካህናቱን ማንነትና ምንነት፤ የሰበካ ጉባዔ አባላትንና የአስተዳዳሪውን ተግባር በነዚህ ወጣቶች በኩል በመቆጣጠር የማይመስለው ነገር ከተገኘ ማሳደም፤ ስም ማስጠፋት፤ ማስከሰስ የመሳሰለውን ሁሉ መጠቀም መቻል ነው።
4/ከላይ እንደተመለከትነው የቤተክርስቲያን መሪዎችን (ሲኖዶስ) የተባለውን አካል ጭምር ከመቆጣጠር አልፎ፤ የልዩ ልዩ ክፍል ተማሪዎችን በአባልነት ከመመልመልና የአጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን በእጁ  ከማስገባት ቀጥሎ ሌላው ጥበባዊ የመሄጃ መንገዱ በስጋዊ አስተዳደር ያሉትን ክፍሎች መቆጣጠር ነው። ይህም ፖሊሶችን፤ዳኞችን፤ መንግስታዊ ባለሥልጣናትንና ሹማምንትን በአባልነትም ይሁን በደጋፊነት ዙሪያውን ማሰለፍ መቻሉ ነው። ይህም እሱ የሚፈልገውን ለማስፈጸም፤ በእሱ ላይ የሚመጣውን ለማወቅና ለመከላከል፤ እሱ የማይፈልገውን ለማስወገድና ለማስመታት፤ ተከላካይ መንግስታዊ ኃይልን ከጀርባው ከማሰለፍም በላይ ጊዜ፤ ሁኔታና አጋጣሚ ከተመቸውም መንግስታዊ ስልጣኑን ከክህነታዊ ሲመት ጋር ተስፈንጥሮ ለመቅለብ ጥርጊያውን እያዘጋጀ ለመሆኑ የማይጠረጥር ሰው ከመጋረጃው ጀርባ ያለውን የዚህን ቡድን ማንነት ያለማወቅ ችግር አለ ማለት ይቻላል። በጭፍን ክርስትና ለዚህ ማኅበር የሚሟገቱ(የድርጅቱን ማይማንእንዴትነት ለሌላ ጊዜ ላቆየውና ለዚህ ድርጅት አልያዝ ያሉትን የጋለ ብረት ክፍሎች ጠቅሼ ጽሁፌን ልቋጭ።
በየትኛውም አጥቢያ ያሉት አብዛኛዎቹ ቀሳውስት፤ ዲያቆናትና አገልጋይ መነኮሳት ይህን ድርጅት የሚጠሉት እንደጠላት ነው። ምክንያቱ ምን ይሆን?

ስሙን ካልገለጸ አንባቢ የተላከ

8 comments:

 1. It is an accurate desciption of Mahibere Kidusan. The author, I think, knows them well. MK has been a big negative element in the church for so many years now. It is lead by hooligans who care less for christianity and the church; instead, they care most for their hegemony and worldy gains. If they don't like you, they give you the TEHADOS label and chase you wherever you go.

  There is a lot of blood in their hands. They will account for it when Ethiopians get their freedom and the rule of law prevails.

  ReplyDelete
 2. KKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKKK............
  Jiloch

  MK is called by God
  You all are of the servants of the King of this World.
  You are always loosers.
  Why don't you mention your name if u have evidence ???
  I am
  Dn. G/Mikael
  From

  The Holly town Axum

  ReplyDelete
 3. በእውነት ይህ ጽሁፍ የዚያን የመሰሪ ድርጅት አሰራር ያጋለጠ፤ ስለማንነቱ የበለጠ እንድናውቅ ያደረገ ስለሆነ ይቀጥል እላለሁ። የተግባሩ መገለጫ ደብረ አሚን ተ/ሃይማኖት ቤ/ክ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶችን ጥሩ አድርጎ መቀጥቀጡን ደጀ ሰላም በተባለው ብሎግ እንደዝና ሲናገር በማየቴ ከዚያ በላይ ለነፍሰ ገዳይነቱ ማረጋገጫ የለም። ከሳሽና ደም አፍሳሽ ድርጅትን በጋራ እንታገለው።

  ReplyDelete
 4. እንዲህ ያለ የጅልና የቂል አስተሳሰብ እንኳን ባናስብ መልካም ነው፡፡ አሁን እኮ ዘመኑ የመረጃ ዘመን ነው፡፡ ማን ምን እንደሆነ በተጨባጭ በረጃ ሁሉም ሰው ያውቃል፡፡ ስለዚህ ዝም ብላችሁ ባልተጨበጠ ልፍለፋ ስም ከማጥፋት ወደ እውነቱ በቅረቡ እጅግ ማትረፊያ ስለሆነ በስጋ ምኞት ከመቋመጥና በፈቃደ እግዚአብሔርና በሕግ ቤተክርስቲያን የሚመራውን ማኅበር ከመክሰስና ከመኮነን መጀመሪያ ከሳሾቹ የሆናችሁ ማኅበረ ቅዱሳን ከሠራው መልካምና አገራዊ ፋይዳ ካለው ሥራ ውስጥ 1/1000000000ኛውን እስኪ ለመጀመር ጸልዩ፡፡
  እግዚአብሔር ልብ ይስጣችሁ፤ ከዚህ የድንቁርና አስተሳሰብ ያውጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 5. የክህደት ግንባር በአንድነት በማ/ቅ ላይ ዘምቷል:: የአሁኑስ ለመናፍቃኑ የተከፈለው ክፍያ በጣም ላቅ ያለ ሳይሆን አልቀረም:: ለምን ራሳችሁን ችላችሁ ጴንጤ አትሆኑም የናንተ ችግር እኮ ማ/ቅ ሳይሆን ሲከፈላችሁ የገባችሁት ውል ላይ ያሉት ግደታወች ናቸው:: ማስተዋሉን ይስጣችሁ:: ማ/ቅ እናንተ እንዲዳከሙ የምትፈልጓቸውን ገዳማት እና የአብነት ትምህርት ቤቶች በአሉበት እንዲቀጥኩ የበኩሉን ጥረት እያደረገ ነው:: እናንተ ግን ክህደት ከማስፋት በስተቀር ይህ ነው ተብሎ የሚገለጽ ለቤተ ክርስቲያናችን ያደረጋችሁት ነገር የለም የጥርጥር ኃይማኖትን ብቻ ዝሩልን:: የአውሮጳን ሕዝብ ወደአለማመን ወደአደረሱት ስፖንሰሮቻችሁ እኛን በስጦታ ለማቅረብ የምታደርጉት ድካም ይገርመኛል:: ክፉዎች ናችሁ እግዚአብሔር ይቅርታውን ያድርግላችሁ::

  ReplyDelete
 6. ከንቱ ልፋት!!!! የዘመኑ ትውልድ እንደ እናንተ እይነቱ ተህድሶ መናፍቅ እና የዘመኑ የተዋሀዶ አርብኞች በደንብ ለይታል!!!!!
  ዬትም አትደርሱም!!! እግዚአብሔር በንሰሐ ይመልሳቹ!!!

  ReplyDelete
 7. in politics u can reform the party or gov.if u came to religion it's impossible look catholics protestants etc all are reformist but they can't reform the orthodox except separation so why don't u leave orthodox and teach your own doctrine

  ReplyDelete
 8. Is it what you observed or is is what you think in your God forsken mind. Support youn thoughts with evidence if you want to be heard. You don't have one!

  ReplyDelete