Tuesday, June 14, 2011

ለውጥ ያስፈልጋል - - - Read PDF

ብዙ ጊዜ በሃይማኖት ላይ የሚካሄድ መንፈሳዊ ለውጥ እግዚአብሔር በቃሉ የገለጠውንና ለዘለዓለም ጸንቶ የሚኖረውን እውነት የማስጠበቅ ጉዳይ እንጂ አዲስ ነገር የመፍጠር፣ ወይም አዲስ ነገር የመፈልሰፍ ሂደት አለመሆኑን በተደጋጋሚ ለማሳየት ተሞክሯል። በመሆኑም በእግዚአብሔር እውነት ላይ የተጨመረና ከቃሉ ጋር የሚቃረነውን ባዕድ ነገር ማስወገድ፣ ከእግዚአብሔር እውነት ላይ የተቀነሰውንና የተሸራረፈውን ነገር እንደ ገና መመለስ የመንፈሳዊ  ለውጥ ዋና ተግባር ነው።
  መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ የሆነው መንፈሳዊ ለውጥ ሲከናወን የኖረው በዚህ መንገድ እንደ ሆነ እንረዳለን። ለምሳሌ እግዚአብሔር ነቢዩ ኤርምያስን ሲጠራው ዐላማው በእርሱ አማካኝነት ሁለት ተግባራትን በማከናወን በሕዝቡ ሕይወት ላይ መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት ነበር። እግዚአብሔር ነቢዩን ገና ለአገልግሎት ሲለየው "እነሆ ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ፣ እነሆ ትነቅልና ታፈርስ ዘንድ ታጠፋና ትገለብጥ ዘንድ፣ ትሠራና ትተክል ዘንድ በአሕዛብና በመንግሥት ላይ ዛሬ አድርጌያለሁ‚ ኤር 1፥9-10። በማለት ተናግሮታል።
  ነቢዩ በተቀበለው በዚህ ኃላፊነት ውስጥ እንዲያከውናቸው የተሰጡት ሁለት ተግባራት ናቸው። የመጀመሪያው መንቀል፣ ማፍረስ፣ ማጥፋትና መገልበጥ ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ መሥራትና መትከል ናቸው። በሌላ አነጋገር ከሕዝቡ ሕይወት መወገድ የሚገባቸውን የእግዚአብሔር ያልሆኑ ነገሮች ማስወገድና  በጊዜው ከሕዝቡ ሕይወት የታጡና ሊኖሩ የሚገባቸውን የእግዚአብሔር እውነቶች መመለስ ናቸው።መንፈሳዊ ለውጥ ከዚህ ውጪ ሲሆን አይችልም። በእግዚአብሔር እውነት ላይ በልዩ ልዩ መንገድ የተጨመሩ ስሕተቶች የሚነቀሉበት፣ የሚፈርሱበት፣ የሚጠፉበትና የሚገለጡበት፣ ከእግዚአብሔር እውነት ላይም የተቀነሰና የተጣለ ነገር ተመልሶ የሚተከልበትና የሚሠራበት ሂደት ነው።
 ስለ መንፈሳዊ ለውጥ ሲታሰብ ልብ ሊባል የሚገባው ቁም ነገር ያለው የሚነቀለውንና የሚተከለውን፣ የሚፈርሰውንና የሚሠራውን ነገር በውል ለይቶ ማወቁ ላይ ነው። በተወሰኑ ስሕተቶች ምክንያት ሁሉንም ኮንኖ በጅምላ ሃይማኖታዊና አገራዊ እሴቶችን ለማስወገድ የሚደረገው እንቅሥቃሴ በሰው ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ዘንድም ተቀባይነት አለው ብሎ ማሰብ ይከብዳል። በሃይማኖት ላይ የሚካሄድ መንፈሳዊ ለውጥን ትክክለኛ ገጽታ ከእግዚአብሔር ቃል ሳያስተውሉ እንዲሁ በጭፍን ሃይማኖት አይሻሻልም የሚለው አዝማሚያም ትክክለኛ አይደለም።
 መቼም ቢሆን የእግዚአብሔር እውነት ለድርድር አይቀርብም። የሕዝቡ አኗኗር መገለጫ የሆኑ ልዩ ልዩ ሥርዓቶች፣ አገራዊ ልማዶችና ባህሎችም ለእግዚአብሔር ሐሳብ ተቃራኒ ሆነው እስካልተገኙ ድረስ እንዲፈርሱና በሌሎች ሥርዓቶች፣ ባህሎችና ልማዶች እንዲተኩም የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ብሎ ማሰብ ያስቸግራል። ሰዎችን ሁሉ ከአንድ ወገን ፈጥሮ የተወሰኑ ዘመናትንንና የሚኖሩበትን ሥፍራ የወሰነላቸው እርሱ ነው። የሐዋ 17፥26-27።በመደበላቸው አካባቢ ሊኖሩም እንደየሚኖሩበት ሥፍራ የራሳቸው የሆነ ባህልና ልማድ ይኖራቸዋል። እግዚአብሔር ሰዎች በየሚኖሩበት ሥፋራ ባህልና ልማድ ውስጥ ሆነው ቃሉ በሚናገረው መሠረት እርሱን እንዲያውቁት እንዲያመልኩትና ለእርሱም እንዲኖሩለት ይፈልጋል። ከዚህ ውጪ ግን እግዚአብሔር በተለያየ ሥፍራ የሚኖሩ ሰዎች ከያዟቸው ባህሎች መካከል መርጦና ለይቶ በአንደኛ ደረጃ ያስቀመጠው ምርጥ ባህል የለም። ከአንዱ ባህል  ወደ ሌላው ባህል፣ከአንዱ ሥርዓት ወደሌላው ሥርዓት የማፍለስን ተልእኮ የሰጠው አገልጋይ ሊኖር አይችልም። ከዚህ አንጻር ያንዱን ባህልና ልማድ ንቆና አጣጥሎ በሌላው ለመተካት የሚደረገው እንቅሥቃሴ የባህል ወረራ እንጂ በሃይማኖት ላይ የሚካሄድ የመንፈሳዊ ሕይወት ለውጥ አካል ተደርጎ ሊወሰድ ፈጽሞ አይችልም። ስለዚህ ከባህል ጋር በተገናኘ፣ ሐዋርያት እንዳደረጉት [የሐዋ 15፥28-29]። ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ፍጹም ተቃራኒ እግዚአብሔርን ለማምለክም ዕንቅፋት በሆኑና ምንም ችግር በሌላቸው ሥርዓቶች ባህሎችና ልማዶች መካከል ያለውን ልዩነት ማጤን ተገቢ ነው።
  ለውጥ በሰላማዊ መንገድ ቢሆን ይመረጣል
ሃይማኖት ለሰዎች ስሜት ቅርብ ነውና በሃይማኖት ውስጥ እንደ እግዚአብሔር ቃል የሆነ መንፈሳዊ ለውጥ ለማምጣት ሰላማዊ መንገድን መከተል ይገባል። ከዚህ ውጭ የሚደረግ ማንኛውም የለውጥ እንቅሥቃሴ ተቀባይነት ማጣት ብቻ ሳይሆን በራስ ላይም በቀላሉ ሊበርድ የማይችል ተቃውሞን ያስነሣል።
ከሚያግባቡና የጋራ ከሆኑ እውነቶች በመነሳት፣ ሌሎች ስሕተቶችን በሂደት ማስተካከል የሚቻልበትን ብዙ እድል መፍጠር ሲቻል ከሚያጋጩና ከሚያለያዩ ነገሮች መጀመር ሰላማዊ እልባት አያመጣም።
በእርግጥ ወንጌል ያለተቃውሞ ሊሰበክ አለመቻሉ እውነት ነው፣ አንዳድ ጊዜ ግን ተቃውሞን ያሰነሳው የተሰበከው ወንጌል ነው? ወይስ አሰባበኩ? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። በእግዚአብሔር መንግሥት ታሪክ ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እየተሰራ ያለ የወንጌል ሥራ በተቃውሞና በስደት ብዛት ወደ ፊት ሲገፋ እንጂ ወደ ኋላ ሲቀር፣ አድማሱ ሲሰፋ እንጂ ሲጠብ አልታየም። በክርስትና የመጀመሪያ ዘመናት ከኢየሩሳሌም ተነሥስቶ በይሁዳ፣ በሠማርያና እስከ ምድር ዳርቻ የወጣው ወንጌል ብዙ የተደራጀ ተቃውሞ ገጥሞታል። በዚያው ልክ ግን በመክሰም ፈንታ እያደገና እየሰፋ እየበረታና እያሸነፈ ተቃዋሚዎቹንም ጭምር እየማረከ ይሄድ ነበር። የሐዋ 2፥41፣ 6፥7፣ 9፥1-6. 12፥24፣ 19፥20። በዘመናችን በወንጌል አገልግሎት ዙሪያ የሚነሱ ተቃውሞዎችና የሚያስከትሉአቸው አሉታዊ ውጤቶች ከዚህ አንጻር መታየት፣ መገምገምና ስሕተቶች ካሉም መስተካከል እንዳለባቸው ሁሉም ሊረዳው ይገባል ለሁሉም ግን ለፍሬያማ ፤ ለውጥ ሰላማዊ መንገድን መከተሉ አማራጭ የለውም።
ለውጡ ደግሞ መንፈሳዊ ሕይወት ላይ እንጂ ሥርዓትና ባህል ላይ መሆን የለበትም ይህ ጊዜን የሚፈጅ አሰልቺ ነገር ነው።
ለማነኛውም ግን እንለወጥ
የለውጥ ያለህ ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ
ተስፋ ነኝ

20 comments:

 1. You don't have anything to say except post from Tehadiso books.
  Which apostle teach you Lie? Paulos? I don't think so. He was Jew. When he got call start to preach Jesus out of Jews temple not in their temple. He didn't try
  to reform it. So, if you feel a need to reform why don't you open you hall somewhere? Then if you have a truth people follow you if not still you will have a few followers anyway. But your objective isn't Jesus though. You try to dismantle the church and then allow Guy marrige and make many that's your single and only reason.

  ReplyDelete
 2. this article is quoted from Tehadso book
  simply we are knowing who u are

  Thankyou

  ReplyDelete
 3. eferu enji enanite protestant

  ReplyDelete
 4. በቃ ኡ ኡ ማለት ብቻ ነው? መልክ ያለው መልስ መስጠት ሲቻል ዝም ብሎ ማጉረምረም አይጠቅምም። በኔ አስተያየት አውነተኛው የተሃሕዶ ልጅ የዚህ ጽሁፍ ቀማሪ ነው። ወገን ዝም ብሎ አካኬ ዘራፍ ማለት አይጠቅምም። በዚህ ብሎግ ላይ የሚጽፉ ሰዎች ተራ ሰዎች አይደሉም ስለዚህ የማትስማሙበት ነገር ካለ ጥቅስ ጠቅሳችሁ አሳማኝ ነገር ተናገሩ። ዝም ብሎ እሪ ማለት የበለጠ እናንተን ትዝብት ውስጥ ይጥላል

  ReplyDelete
 5. Chachata, Please read and contemplate. Zerefa aytekemem. There is a need for real tehadeso for EOTC. With the grace of God, it will happen soon. First Anonymous, I don't think you read your bible, Paul always go first to the temple and mukrab until people like you pushed him out. Our Lord Jesus (Sweet his name) preached in the temple but Pharises like MK pushed him out. This will continue to the end. Begeze tekete bro.

  ReplyDelete
 6. Anonymous 6:57 said...
  Hey man oh you knew the bible well? don't you know the bile said don't lie? you deceive to be tewahedo since you are tehadeso. That's lie don't you think? By the way in the temple of Jews, still they preached God, their own.And your bible don't even tell you where paulos dead?(you didn't read it) what I'm saying is respect peoples wish. Go establish your whatever

  ReplyDelete
 7. i have read the post; it seems good but it has its own measion. which practices of church need reformation , what does it mean reformation of church. please do not be hurt it

  ReplyDelete
 8. I have read the post it seems good, but what is reformation, what is the bad habit or activity that is performed in church. For me i do no if there any practices which perform in it; why we do not you discuss with face to face. Is reformation mean does not accept Virgin saint Mariam, does it mean avoid fasting, segedeit and other

  ReplyDelete
 9. I think the proper term that describes what is written in this article is Renewal, not reformation. We absolutely need renewal. There is a lot of garbage in our church that needs to get cleaned up. Want to know what garbage? read the rest of the articles in this blog. I can also provide you with other sources. If you are open minded that is. our church is beautiful, but ሰይጣን በጥንቆላ ፣ ከመፅሐፍ ቅዱስ ጋር በሚጋጩ ነገሮችና በመሳሰሉት ብርዝርዝ አድርጎብናል። ጉዳችንን ቶሎ ቶሎ ካላስተካከልን የቤተክርስቲያንዋ የወደፊት እጣ ፈንታ ጥሩ አይሆንም።

  ReplyDelete
 10. It has nothing to do with our beloved mother St Mary except some unbiblical teachings that we found in Gedlat about her. Fasting, praying and Segdet are part of our religious activities that we use to worship our God, offcourse not to get saved or to get acceptance in the eyes of God by our deeds.

  "በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል። በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ" mat 9:16-17

  Please first be open mind and read these books. Then yarege amelekaketehen aswegedeh accept and live the pure word of God, otherwise you will not benefit. You will know the truth, and the truth will set you free.

  http://good-amharic-books.com/onebook.php?bookID=179 (yetekebere Meklit)

  http://good-amharic-books.com/onebook.php?bookID=513 (Yelewet yaleh)


  http://good-amharic-books.com/onebook.php?bookID=72 (Gedel weys Gedel)


  http://good-amharic-books.com/onebook.php?bookID=540 (Bahtawi Seytan)


  http://good-amharic-books.com/onebook.php?bookID=256 (Yenegal)

  http://good-amharic-books.com/onebook.php?bookID=257 (Nufake)


  http://good-amharic-books.com/onebook.php?bookID=303 (mekedes yegebu menafekan)

  There are lots of books out there and many more are coming which we can't stop them from coming out. These will get you started.

  May God help you.

  ReplyDelete
 11. "በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል። በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ" mat 9:16-17

  you qoute this but didn't know what it said!
  Our church is OLD for you! So Go and establish new one because በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም፤ መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና:: Do you undersatnd?

  ReplyDelete
 12. ይድረስ ለአባ ሰላማ ብሎግ አዘጋጆች እና የብሎጉን አብይ ተልዕኮ ለምትደግፉ ሰዎች በሙሉ፡፡

  እናንተ ያነሳችሁት የመለወጥ አስፈላጊነት በእዉነቱ በዚህች ቤተ ክርስትያን ያለ እንኳን ቢሆን፤ እጅግ ክርስትያናዊ ካልሆነዉ አቀራረባችሁ የተነሳ እንዴት ልንቀበለዉ እንችላለን? በክርስቶስ አምኛለሁ የሚል ሰዉ፤ ክርስቲያናዊ ስነ ምግባር ሊኖረዉ አይገባም ወይ?

  እንኳን የክርስቶስ ፍቅር ልቡን ከሰበረዉ ክርስትያን ይቅርና ከአንድ ሀይማኖት የለሽ የመንደር ዱርየ እንዲህ ያለ ጸያፍ ንግግር፤ ስድብ እና እርግማን እንዴት ይጠበቃል? ይህስ የክርስትና ፍሬ ነዉ?

  በእዉነት የሚከተሏቸዉ ኦርቶዶክሳዊያን ፈጽመዉ ተሳስተዋል ብንል እንኳ፤ በእዉነት እነርሱ ራሳቸዉ ይህንን የሚሰጣቸዉን ክብር አይፈልጉትም ብንል እንኳ፤ እንዴት አርገን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱሳን እንዲህ እንዘልፋቸዋለን? እንዴትስ እንዲህ እናቃልላቸዋለን? በዚህስ ለጌታችን ክብርን እንጨምርለታለን? እርሱን አምነዉ፤ እርሱን ተከትለዉ ህይወታቸዉን የሰጡ ቅዱሳን ሲዘለፉ የሚደሰት አምላክስ እንዴት ያለዉ ነዉ?

  ይልቁንስ ጸያፉን ስድብ ወደጎን ተዉትና የሚከተሉትን ጥያቂዎች መልሱልኝ፡፡

  1. ከላይ የጠቀሳችኌቸዉ የቅዱሳን ገድላትን እዉነተኝነት የተጠራጠራችሁት ከምን መነሻ ነዉ? ፈጽመዉ ለአእምሮ የሚከብዱ፤ ለማመን የሚያዳግቱ ለሰዉ ልጅ አቅም የሚከብዱ ስለሆኑ ነዉን? እንዲያ ከሆነ የገድላቱን ትተን በመጸሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ለማመን የሚከብዱ ለጆሮ የሚቆረቁሩ ታሪኮች የሉም? አህያ ሰዉን አናገረች ተብሎ አልተጻፈምን? ሰዉ በአሳ አንበሪ ሆድ ተጓጉዞ፤ ተተፍቶ፤ ንስሀን ሰበከ ተብሎ አምተጸፈምን? ሰዉ ወደ ጨዉ ዲንጊያነት ተቀየረ የሚል አልተጸፈምን? ታዲያ ገድላቱ ላይ የተጻፉት የቅዱሳን ስራዎችን ማመን ከሌለብን የመጽሀፍ ቅዱሶቹን ታሪኮች እንደምን ባለ አገባብ ልንቀበላቸዉ እንችላለን?

  2. ብዙዉን ግዜ እንደምንሰማዉ ስለ ገድላቱ እና ድርሳናቱ የምታነሱት እንዲሁ የሰዉን ቀልብ ለመግዛት ነዉ እንጂ በመሰረታዊ የሀይማኖት ጥቂዎች ላይ ፈጽሞ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ያፈነገጣችሁ እና ለትሮቴስታንት ዶክትሪን የቀረባችሁ ናችሁ ይባላል፡፡ እንደምትባሉት መሆን አለመሆናችሁን ከእናንተ መስማቱ ሀሳቦቻችሁን በትክክል ለመረዳት ጠቃሚ ነዉና እስኪ ለሚከተሉት ቀጥተኛ ጥያቄዎች የእናንተን ቀጥተኛ መልስ ብትሰጡኝ፤


  2.1 ኢየሱስ ክርስቶስ ያማልዳል ወይስ አያማልድም? አምላክነቱስ እንዴት የለ ነዉ? (ከምስጢረ ስላሴ አንጸር)
  2.2 ቅዱሳን ያማልዳሉ ወይስ አያማልዱም? የምልጃ አስፈላጊነትስ ምንድን ነዉ፡፡ ይህንንም በህይወተ ስጋ እያሉ እና በአጸደ ነፍስ ሆነዉ በሚል በሁለቱም ግዜያት ብትመልሱልኝ
  2.3 እምነት ብቻዉን (ያለስራ) ያጸድቃልን?
  2.4 ስርአት ለክርስትያኖች ስፈልጋልን? የጾም፤ የጸሎት፡ የስግደት፤ የአለባበስ እና የመሳሰሉት
  2.5 ታቦት ለቤተክርስትያን ያስፈልጋልን?
  2.6 መስቀል ለክርስትያኖች ያለዉ ፋይዳ ምንድን ነዉ?
  2.7 ቅዱሳን ስእላት ያስፈልጋሉን? እነርሱን መሳለም እና በእነርሱ አንጻር መጸለይ ይገባልን?
  2.8 ለቅዱሳን የጸጋ ስግደት መስገድ ይገባልን? እነርሱን ማመስገንስ?
  2.9 ጸበል አስፈላጊ ነዉን? ያድናልስ?
  2.10 የንስሀ ስርአት እንዴት ያለ ነዉ? ለንስሀ አባት ሀጢያትን መናዘዝ የግድ ነዉን? ካህናትስ ሀጢያትን ይቅር ማለት፤ ማስተስረይ ይችላሉን?

  ለእኒህ ጥያቂዎች የሚኖራችሁ መልስ ለእናንተ የሚኖረንን አመለካከት እና አቀባበል ይወስነዋል፡፤ ይህን ጥያቄ የብሎጉ አዘጋጆችም ሆናችሁ የእንቅስቃሴዉ ደጋፊዎች ጥርት አርጋችሁ እንድመልሱልኝ በእግዚአብሄር ስም እለምናችዃለሁ፡፡

  ፍቅረ ዮሀንስ

  ReplyDelete
 13. Thank you Fekere Yohannes,
  Note: Christianity is a choice we make!!! I will try to answer your first question first.

  First of all let us not forget that Jesus Christ is Fully God and Fully Man.(ከምስጢረ ስላሴ አንጸር).


  2.1 ኢየሱስ ክርስቶስ ያማልዳል ወይስ አያማልድም? አምላክነቱስ እንዴት የለ ነዉ? (ከምስጢረ ስላሴ አንጸር).

  Answer. Yes
  Reason - because the bible says so, to many verses but here are few, in fact a whole book is dedicated for the high priesthood of our lord Jesus, with the sacrifice he already made. Read the book of HEBREW. You can check all verses from the greek version.

  “የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” romans 8:34

  “ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል” Heb 7:25

  “ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።” 1 john 2:1

  “እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል” Heb 7:22

  “ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ፥ የተጠሩት የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው።” Heb 9:15

  “አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” 1 tim 2:5

  “ሕልምም አለመ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር።” Gen 28:12

  “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይ ሲከፈት የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ አለው።” John 1:52

  “በእግዚአብሔርም ቤት ላይ የሆነ ታላቅ ካህን ስላለን” Heb 10:21

  “በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም” John 14:6

  “በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ” Heb 9:24


  Now my turn to ask you

  1 - What does it mean when we say Jesus is the high priest now (as the priesthood of Melchizedek)?

  We will come to your next question:

  2.2 ቅዱሳን ያማልዳሉ ወይስ አያማልዱም? የምልጃ አስፈላጊነትስ ምንድን ነዉ፡፡ ይህንንም በህይወተ ስጋ እያሉ እና በአጸደ ነፍስ ሆነዉ በሚል በሁለቱም ግዜያት ብትመልሱልኝ

  Answer : Yes yemaledalu but how is that? will be our next discussion. We will start like by me asking you some questions like

  -Other than the general prayer we see in revelation, tell me bible verses that teaches us about the prayer of the departed for individuals? Abraham referred to the not departed as we see in Luke 16.

  ReplyDelete
 14. 1 - Awo Eyesus Yamaledal
  2 - Kidusan anten yet yawekuhal?
  3 - Betsegaw-beemenet neew, endechereneteh
  4 - sereAt yasfelegal biblical eskehone deres
  5 - tabot ayasfelegem
  6 - Meliket becha
  7 - seEl menem ayasfelegem God is Spirit
  8 - Kayehachew seged
  9 - BeEyesus sim tetseleyobet kehone
  10 - Kahen Hatiyat Yekere ayelem sorry hatiayt bedem neew yeminetsaw.

  Opps - You got 1.5/10

  Very serious, read your bible.

  ReplyDelete
 15. Dear my Ethiopian Orthodox brothers & sisters, pls read revelation 2 & 3. Our lord instructs St John to write letters to churchs at that time ( 1st century churchs).
  If he were to send a message to EOTC our church (after 2000 years) what things he might commend? Rebuke us for? Well done, pure, blameless?

  Hint: See the fruit.

  ReplyDelete
 16. Hello Fikre Yohanes,

  I felt obligated to answer some of the questions that you raised to the extent I can.

  2.1 ኢየሱስ ክርስቶስ ያማልዳል ወይስ አያማልድም? አምላክነቱስ እንዴት የለ ነዉ? (ከምስጢረ ስላሴ አንጸር)

  Yes, Christ intercedes with God on behalf of all who believe in Him. He is the eternal High Priest who offers sacrifice for our salvation. However, the orthodox definition of the intercession of Christ and that of the Pentes are quite different. According to the pentes, they believe that Christ still does another intercession in heaven until the end of the world. However, this definition is completely wrong. Christ completed His intercession on the cross, but that work that He did on the cross is still live and fresh and is eternal so that it intercedes between God and the human race eternally. Moreover, the blood and flesh of Christ that we sacrifice in our churches every day intercedes for the salvation of the faithful. If it was not for the blood and flesh of Christ, God would not give mercy to anyone. Christ has assumed the position of the Intercessor or Intermediator of His own will, the will of the Father and the will of the Holy Spirit. He plays multiple roles for the sake of our salvation. He is God or the Recipient of the Sacrifice, High Priest or Intercessor, and the Sacrifice that the High Priest offers to God. The mystery is so amazing. It does not contradict with the Holy Trinity as Christ is perfect God and perfect Man.

  2.2 ቅዱሳን ያማልዳሉ ወይስ አያማልዱም? የምልጃ አስፈላጊነትስ ምንድን ነዉ፡፡ ይህንንም በህይወተ ስጋ እያሉ እና በአጸደ ነፍስ ሆነዉ በሚል በሁለቱም ግዜያት ብትመልሱልኝ

  Yes, the saints can intercede both in flesh and in heaven. However, the intercession of the saints is quite different from that of Christ. You can visualize the intercession of the saints as prayer for one another.

  2.3 እምነት ብቻዉን (ያለስራ) ያጸድቃልን?
  Yes, faith is enough. The guy on the right hand of Christ, I mean yemanay, got salvation just by faith. The Bible says that we are justified by faith. This does not mean good deeds are not relevant. Good deeds are in fact very important and we need to do them. However, whatever amount of good deeds we do, we cannot be justified by good deeds. We got God's mercy because of Christ. The millions of deeds we may do can not be compared to what God gives us in the coming Kingdom and to the blood of Christ that He shed on the cross. Our deeds are tokens or indications of our faith. If we don't do them, it means that we don't have faith and cannot get salvation.

  2.4 ስርአት ለክርስትያኖች ስፈልጋልን? የጾም፤ የጸሎት፡ የስግደት፤ የአለባበስ እና የመሳሰሉት

  Yes, we need sereat or cannon laws to guide the practice of our faith. We are like an army of a nation. The army can be weak and in disarray if it does not follow some form of military codes. Likewise, Christians need sereat. However, that sereat can be reformed depending on the time and level of development of the the society following the faith.

  ReplyDelete
 17. Contin'd

  2.5 ታቦት ለቤተክርስትያን ያስፈልጋልን?

  No, we are the true tabots of the new testament. Moreover, the work of the tabot has been replaced by Christ. However, EOTC has tabots because of our jewish background. At EOTC, the tabot/tselat is used to sacrifice the blood and flesh of our Lord. Moreover, we use it as a way to remember the saints. The bible says the remembrance of the saints is for eternity. In a nutshell, the tabot we haveat EOTC is more of a tradition than a Christian practice. However, we need to respect our tradition - it is a holy tradition. Having said that, we are not expected to follow the old testament practice regarding tabot. Also, the new testament tabot we are usning at EOTC is different from the old testament tabot in form, shape and spiritual significance.

  2.6 መስቀል ለክርስትያኖች ያለዉ ፋይዳ ምንድን ነዉ?

  A lot. The Cross is our life. We got our salvation from the crucifixion of Christ on the Cross.

  2.7 ቅዱሳን ስእላት ያስፈልጋሉን? እነርሱን መሳለም እና በእነርሱ አንጻር መጸለይ ይገባልን?

  Yes, we need them. an icon speaks volumes compared to words. Also, we practice our worship using them. When we see Christ crucified on the Cross, we can easily elevate our spirit to God and connect with Him very easily.

  2.8 ለቅዱሳን የጸጋ ስግደት መስገድ ይገባልን? እነርሱን ማመስገንስ?

  Yes, they deserve both segdet and praise. However, it should be very limited to avoid mixing up the veneration with the worship. You cannot kneel down for the saints all day long, Otherwise, it amounts to worship. However, you can kneel down once or twice to show respect to the saints of God.

  2.9 ጸበል አስፈላጊ ነዉን? ያድናልስ?

  Holy water has been in use since the old testament era. We are allowed to use them. Christ gave us the holy water while on the cross - water came out of His body when one jew hit His body with an arrow. Holy water has a healing power. I can tell you that I got healed with holy water given in the name of St. Mary.

  2.10 የንስሀ ስርአት እንዴት ያለ ነዉ? ለንስሀ አባት ሀጢያትን መናዘዝ የግድ ነዉን? ካህናትስ ሀጢያትን ይቅር ማለት፤ ማስተስረይ ይችላሉን?

  Yes, Christ has given the power of the remission of sins to the true priests. They say the word, but Christ cleans you from sins based on their word. However, the key in the confession and sin remission process repentance of the sinner. The rest is procedure we have been ordered to follow. Moreover, this process is like visiting a doctor to seek medicine. The true healer is the medicine (Christ in our case) and the the doctor is the priest who prescribes the medicine and gives some counsel to the patient.

  Hope the above helps somehow.

  ReplyDelete
 18. Great. Thank you for addressing my questions.
  The core purpose of raising those questions, as I explained it earlier, was only to know, in precise terms, where you stand.

  All of your answers are, with no error margin, similar to the responses I get from my protestants all the time.

  I will, in fact address your answers, with my counter answers, in detail and one by one.

  But I am still surprised why you are calling yourself Orthodox Christians?? because you are clearly protestants. What else does a protestant do that you didn't and what else does a protestant preach that you didn't?

  So, now I know why all those curses has been thrown against Mahibere Kidusan. They must have know you very very well, at hand.
  I used to pay attention to some of your criticism of MK thinking they emanate from a true child of the church. But now, everything is revealed. MK is right and it justifies the unique kind of insult you commit on it.

  So protestants, I will be getting back to you with the Orthodox teaching of all the questions I raised. But, do not pretend as if u r an Orthodox. How is that gonna make u even close to some one who honestly thinks he follows GOD?

  This is Fraud and Sin.

  Fikre Youhanes

  ReplyDelete
 19. Hi Fikre Youhanes,

  Teregaga brother, It's your choice/right to be MK. What is important for you is to know the truth. It will see you free from the bandage. Jesus will set you free, and you will start to enjoy the fruit of the Spirit - Peace, joy ... BTW, how offen do you read your bible? I know a lot of MK leaders, I also know their personal life, they are still under slavery. You don't see the fruit of the spirit in them. You need to Abide in the true Vine our lodr Jesus.Check your self wether you have "the fruit of the Spirit is love, joy, peace, patience, kindness, goodness, faithfulness ..." Gal 522 Do you have these in your life? if not that will be your homework.

  They way of Mahbere "kidusan" is the way of slavery and bandage. Do you want to turn your face away from the lord Jesus, ok be MK and live the dry life and spent eternity in ...


  Fikre Eyesus negn.

  ReplyDelete
 20. Yemitanebu Agenazbu Yebetekiristiyanin timihirt eweku atnawetu. I think most of the writers are Protestant. No dout

  ReplyDelete