Wednesday, June 8, 2011

ማህበረ ቅዱሳን ከስም ማጥፋት ደም ወደ ማፍሰስ ተሻገረ ለዘማርያኑም የወንጌል ወግ ደረሳቸው - READ PDF

ባለፈው ጽሑፋችን ሰይጣን የኢትዮጵያውያንን ደም ለማፍሰስ ገና እያሰበ መሆኑን እና ባማህበረ ቅዱሳን አማካኝነት ቅሥቀሳ እያደረገ እንደሚገኝ፣  አስታውቀን ነበር። ይኸው ከተናገርን ገና ሁለት ሳምንት ሳይሞላን በተክለ ሃይማኖት ምክንያት በተክለ ሃይማኖት ደጀ ስላም [መርካቶ] ድብደባ ተጀምሯል።  
ዲያቆን ሙሉጌታ ወልደ ገብርኤል "ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን‚ በሚል እርስ ያሳተመው መጽሐፍ በጣም ተጋነነ ተብሎ ሲተች ሰምቼ ነበር መጽሐፉ ግን ዛሬ በተግባር የተረጋገጠ እውነተኛ ምስክርነት መሆኑን ከማህበረ ቅዱሳን ተግባር መረዳት እንችላለን። በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ ያለው መንፈስ ደም የማፍሰስ ጥማት ያለው መሆኑን በማጋለጥ ደጋግመን ብንጮህም የተገነዘበን ግን እጅግ ጥቂት ሰው ነው የሚል ስጋት አለን። እኛ ስም ለማጥፋት የተንሳን ሰዎች አይደለንም፣ በማህበረ ቅዱሳን ምክንያት የሚመጣው የርስ በርስ ጦርነትና የቤተ ክርስቲያን ለሁለት መከፈል ከወዲሁ የታየን አገር ወዳድና የቤተ ክርስቲያናችን ቅናት የሚበላን ኢትዮጵያውያን ነን እንጂ።
ማህበረ ቅዱሳን መንፈሳዊ ድርጅት ቢሆን አብረነው ለመስራት ዝግጁ ነበርን መንፈሳዊ አይደለም የምትሉበት ምክንያት ምንድን ነው? ለሚል ጠያቂ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ያለውን ጥላቻ በማየት የማህበሩን መንፈስ መገምገም ይቻላል እንላለን። ኢየሱስን ለድርጅታቸው ክርስቲያናዊ ሽፋን ለመስጠት ይጠሩታል እንጂ እጅግ የሚደነግጡበት ስም ነው።"ጌታ ኢየሱስ‚ ብለው ለመጥራት እጅግ ይከብዳቸዋል አንዳዴ ለመስበክ ስሙን ይጠራሉ ግን የርሱን ሐሳብ ሳይሆን ራሳቸው የተቋቋሙበትን አላማ በመስበክ ያጭበረብራሉ። ሰው ምን ይለናል በሚልም ይሉኝታ ስሙን የሚጠሩትም አሉ።
ይህን ጽሑፍ የምታነቡ ሁሉ እኛንም ለመታዘብ ከፈለጋችሁ በአካባቢያችሁ የሚገኝን የማህበረ ቅዱሳን አባል "ጌታ ኢየሱስ‚ "የናዝሬቱ ኢየሱስ‚ "ኢየሱስ አዳኝ ነው‚ የሚሉትን የከበረና ምሥጢራዊ ስም በማንሳት መንፈሱ ምን ያህል እንደሚረበሽና እንደሚቆጣ መመልከት ትችላላችሁ የማህበረ ቅዱሳን አባል መሆኑንና አለመሆኑን እንኳ በዚህ ስም አጠራር ለይቶ ማወቅ ይችላል። ሆኖም ግን መንፈሱ ጌታችን መድኃኒታችን የሚለውን አጠራር በመዘርዘር ለማጭበርበር ይሞክራል። መንፈሱ ጋታችን መድሃኒታችን ማለት ከቻለ የናዝሬቱ ኢየሱስ ሲባል ለምን ይደነግጣል? ይህ ነው እንቆቅልሹ!
ታዲያ ማህብረ ቅዱሳን የናዝሬቱ ኢየሱስ ሲባል የሚደነግጥ ከሆነ የተቋቋመበት ዋና አላማ ምንድን ነው?
የመጀመሪያው የማህብረ ቅዱሳን አላማ የሥጋ ዘመዶቹ የሆኑትን የተክለሃይማኖት ተከታዮችና የዘራ ያዕቆብን የተበላሸ ታሪክ ለመሸፋፈን ነው። ወንጌል እንዲሰበክና እውነቱ እንዲወጣ አይፈልጉም፤ ተክለሃይማኖት ተከታዮችና ዘራያዕቆብ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እና ሕዝብ ላይ የፈጸሙት ተንኮል እንዲገለጥባቸው አይፈልጉም። ለዚህም አላማቸው ወንጌል እንሰብካለን እያሉ በወንጌል ስም የተክለሃይማኖትን ገድልና ተረት በመስበክ ሕዝቡ የተሳሳተ ወንጌል እየሰማ እንዲደነዝዝ ያደርጋሉ።
ሁለተኛው ደግሞ በተክለ ሃይማኖት ስም የተሰወረውን አላማቸውን ማሥፈጸምና መንበሩን መውረስ ነው። ለዚህም የተለያዩ መነኮሳትን በመመልመል ለጵጵስና እያቀረቡ የሲኖዶሱን አባላት በማብዛት መንበረ ፓትርያርኩን መቆጣጠር ነው። ይህን የማህበረ ቅዱሳን ፍላጎት ያወቁ መነኮሳትም የተክለ ሃይማኖትን ሥእል ከትራሳቸው በማድረግ፣ ደብረ ሊባኖስ ሄዶ በመመንኮስ፣ ስለ ተክለ ሃይማኖት በማስተማር፣ የተክለዬ ታማኝ ወዳጅ መሆናቸውን በማሳየት ጵጵስናን ለመሾም ደጅ እየጠኑ ነው።
ለምሳሌ፦ በተክለ ሃይማኖት ስም የሥጋ ሥራ እየሠሩ ያሉትን ወገኖች ለማስደስትና የማህበረ ቅዱሳን ታማኝ ወዳጅ ለመሆን ጥረት ከሚያደርጉት አባት መካከል አንዱ ተክለ ሃይማኖትን እና ገብረ መንፈስ ቅዱስን ወደ አሜሬካ በመውሰድ የዲሲ እና የአትላንታ ታቦቶች አድርገው ወዳጅነትን አትርፈዋል።
የትግሬዎችንና የቡልጋዎችን ወዳጅነት ለማትረፍ ያሰቡት የዳላሱ ቄስ---- ደግሞ አቡነ አረጋዊንና ተክለ ሃይማኖትን ደራርበው ታቦት አድርገዋል። ሁሉም የሰውን ወዳጅ ለማብዛት እንጂ የሃይማኖት ሥራ ለመሥራት የሚፈልግ የለም። በአዲስ አበባ ከተመሠረቱት ወደ መቶ ሃምሳ ከሚጠጉት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በኢየሱስ ስም የተሰሩት ሁለት ብቻ ሲሆኑ በአሜሪካ ግን አንድ ብቻ የኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን አለ [በውጩ ሲኖዶስ ሥር]። ኢየሱስ የሚለውን የተጸውዖ [ዋና መጠሪያ] ስም የፈሩ አንዳድ ምእመናን ግን መድኃኔ ዓለም የሚለውን የግብር ስም [የሥራ ስም] በማንሳት ቤተ ክርስቲያን መሥርተዋል። ይህም ተመስገን ነው። የማህበረ ቅዱሳን መንፈስ ያለባቸው አቡነ ... ወደ አሜሪካ ከሄዱ ጀምሮ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን የከፈቱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ ተክለ ሃይማኖት [ዲሲ]፣ ገ/መንፈስ ቅዱስ [አትላንታ]፣ ራጉኤል [ዲሲ]፣ ገብርኤል [ኬንታኪ] ወዘተ ናቸው። ኢየሱስን ግን ረስተውታል ከዘላለሙ ፍርድ በመስቀል ሞቶ ያዳናቸው እውነተኛ ወዳጅ ግን እርሱ ነበር። እነሱ ግን አንድ ቤተ ክርስቲያን እንኳ በስሙ ለመትከል ፈቃደኛ አይደሉም "ለወፎች መጠለያ ለቀበሮዎች ጉድጓድ አላቸው የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት እንኳ የለውም‚ በማለት ጌታ አስቀድሞ ባይናገር እጅግ ይገርመን ነበር።  ዛሬ ኢየሱስ የሚለውን ስም ደፍሮ ለማንሳት ትልቅ እምነትን ይጠይቃል፤ ኢየሱስ የሚለውን ስም ከቤተ ክርስቲያን እያስወጡ ወደ አሜሪካ እንኳ የዘው የሚሮጡት አቡዬን እና ተክልዬን ነው ድሮስ ወደ አሜሪካ እየተሄደ ያለው በዘመድ አይደል! ኢየሱስማ ምን ዘመድ አለው? እንኳንስ ወደ አሜሪካ የሚወስደው በኢትዮጵያም እነዳንኤል ክብረትና ዘመድኩን እያሳደዱት ነው።
ወደ ተነሳንበት ርእስ እንመለስና የተክለ ሃይማኖት ጠበቃ ነን ያሉ በማህበረ ቅዱሳን አሰልጣኝነት በሥውር የተደራጁ ወንበዴዎች አገልጋዮችን መደብደብ ጀምረዋል። ቀሲስ አሸናፊ ገብረ ማርያምን፣ ዘማሪ ዳግማዊን፣ ዘማሪ ምርትነሽን የድንጋይ ናዳ በማውረድ በመርካቶ ተክለ ሃይማኖት ደብድበዋቸዋል። ይህ ቡድን የማህበረ ቅዱሳን "አማራጭ ኃይል‚ ተብሎ በሥውር የተደራጀው ጉዳት ለማድረስ የተዘጋጀው ቡድን አካል ነው።
ባሁኑ የኢትዮጵያ ትውልድ ከሃያ አምስተኛ ኪሩብነት እየወረዱ የመጡትን አባት ተክለሃይማኖትን በዚያው በኪሩብነታቸው ለማቆየት ሲባል በቡድን ተደራጅቶ መደባደብ ዋና የማህበረ ቅዱሳን አማራጭ ሆኗል። ታዋቂው ደራሲ በውቀቱ ስዩም "እግር የሌለው ባለ ክንፍ‚ በሚል ያቀረበው ጽሑፍ ተክለ ሃይማኖትን ጥያቄ ላይ የጣላቸው ሲሆን ትንሽ ዱላ መቅመሱ ተሰምቷል። "አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ‚ እንደተባለው ሃያ አምስተኛ ኪሩብ ብናደርጋችውም፤ ስድስት ክንፍ ብናወጣላቸውም፣ ቃል ኪዳናቸውን ብናበዛውም፣ ቤተ ክርስቲያን እየሰራን ብንሰብክላቸውም፣ ብንዘምርላቸውም፣ ከትውልዱ እንደማዕበል እየፈሰሱ ያሉ ጥያቄዎችን ማቆም ግን አልተቻለም። ምክንያቱም ጻድቁን "ሰይጣንን ገርዘው የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ አድርገውታል‚ የሚለው ትምህርት ጥያቄ ላይ ጥሏቸዋል። ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ 5፥ 6 ላይ "መገረዝም ሆነ አለመገረዝ አይጠቅምም‚ ብሎ አስተምሮ እያለ ሰይጣንን መግረዝ ለምን አስፈለገ? በውነቱ ይህ የሐዋርያትን እምነት ከሚከተል ሰው ይጠበቃልን? እንዲህ ዓይነቱን ማፈሪያ ታሪክ በማረም ፈንታ በርሳቸው ምክንያት ባልተገረዙ የቤተ ክርስቲያን ወንበዴዎች ተጠግቶ፣ ደም ለማፍሰስ መጣደፉ ግን አግባብ አይደለም።
እኛን የሚያስፈራን ግን ማህበረ ቅዱሳን እነምርትነሽን መደብደብ እንዳማራጭ የሚወስደው ከሆነ ዱላው ነገ ወደ ማህበረ ቅዱሳን አባላት ፊቱን ማዞሩ የማይቀር መሆኑ ነው። እናም የቤተ ክርስቲያን የርስ በርስ ጦርነት ከመነሳቱ በፊት የመጨረሻ እልባት ይደረግለት ስንል እንማጸናለን። መንግሥትም ቢሆን እንዲህ ዓይነቱ መከፋፈል ለፖለቲካ ይጥቅመኛል ብሎ እንዳያስብ፤ ይህ ከሁሉም የከፋ ኋላ ቀርነት ነው ድህነትን እየተዋጋን እንዳለን ሁሉ ኋላ ቀርነትንም መዋጋት አለብን እምነት በሕሊና እንጂ በጉልበት አይሆንም፤ በጉልበት እንዲያምን የተደረገ ሰው እስላም እንጂ ክርስቲያን ሊሆን አይችልምና ማህበረ ቅዱሳን ወንበዴዎችን በማደራጀት የከፈተውን ጦርነት እንደገና ቁጭ ብሎ ያስብበት።
ዘማርያኑም ማስተዋልና ትግሥት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል በደም ፍላት መንፈሳዊ ሥራ አይሰራም በእግዚአብሔር ፊት በጾምና በጸሎት በመውደቅ እንጂ።አንዳዶቻችሁ ግን ወዘሮ እጅጋየሁን መጠጋታችሁን አልወደድነውም። እርሷን ተዋትና እግአዚአብሔርን ተጠጉ፤ በፖሊስና በዘመድ ኃይል ፍርድን ለማግኘት አትሞክሩ። ይህ የወንጌል ሕይወት ነው ብለን አናምንም። በናንተ ላይም ጥያቄ አለን ወንጌል ሰላማዊ ስለሆነ እየወደቅን ብዙዎችን ከወደቁበት እናነሳለን እንጂ ደካማዎችን በጉልበት እየጣልን ለመቆም አንሞክር። ይህን ከናንተ ያርቀው አሜን!   
ይቆየን ተስፋ ነኝ   

56 comments:

 1. Gud bel MK

  Thank God like you said, Eyesus (Maryland - Baltimor) is under the exile syond, I would have been changed to others if it were under abune abereham.

  ReplyDelete
  Replies
  1. የዚህ ድረ ገጽ አዘጋጆች በጣም ተራ የሆነና አንባቢያችሁን የሚያሰለች ጽሁፍ ባታወጡ አንዳንድ መጣጥፎችችሁ እጅግ አስተማሪና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶን የሚሰብኩ ሲሆኑ ለምሳሌ “የማይሞተው ሞተ” ዓይነት ግሩም አርቲክል ነው አዘጋጁ እግዚአብሄር ይባርከው ሌሎቹ አብዛኛዎቹ መጣጥፎቻችሁ ግን አልወደድኩዋቸውም በተለይ ማሕበረ ቅዱሳን የሚባለውን ድርጅት የሚኮንኑ ብቻ ናቸው ዘገባዎቹም ከጭፍን ጥላቻ የመነጩ ይመስላሉ በቤተ ከልርስቲያናችን እየተደረጉ ያሉትን ሁሉ ለአንድ አካል ብቻ ተሰጥቶ በሚነገርበት ግዜ ለምሳሌ የተክለሓማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ያደረጉትን ለማሕበረ ቅዱሳን ሲኖዶሰ የወሰነውን ለማሕበረ ቅዱሳን ውንጀላው ሲበዛብኝ ይህን ማሕበር ይህ ድረ ገጽ ለምንድር ነው ባልሆነው በሆነው የሚወነጅለው በማለት መጠየቅ ጀምሪያለሁ አካሄዳችሁ የብስለት ይሁን

   Delete
  2. BETAM YEMIGERM TSEHUF NEW BENBA NEW YANEBEBKUT YEMOTELN GETA DEMUN AFSESO YADANNEN GETACHEN MEDHANITACHEN ADAGNACHENNEN EYSUS GETA BELO METRAT KALCHALEN YETGANEW EMNETACHEN ADGALAYNEW YALENEW BETAM EUUUUUUUUUUUUUUUUUUUUUUUUUUUUUUUUUBELN MECHOH ALEBN TABOTU HULU LEFETARIW SAYHON LEFITURU HON GETA YERARALEN WEDELEBONACHEN YEMELESEN.

   Delete
 2. የዚህ ድረ ገጽ አዘጋጆች በጣም ተራ የሆነና አንባቢያችሁን የሚያሰለች ጽሁፍ ባታወጡ አንዳንድ መጣጥፎችችሁ እጅግ አስተማሪና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶን የሚሰብኩ ሲሆኑ ለምሳሌ “የማይሞተው ሞተ” ዓይነት ግሩም አርቲክል ነው አዘጋጁ እግዚአብሄር ይባርከው ሌሎቹ አብዛኛዎቹ መጣጥፎቻችሁ ግን አልወደድኩዋቸውም በተለይ ማሕበረ ቅዱሳን የሚባለውን ድርጅት የሚኮንኑ ብቻ ናቸው ዘገባዎቹም ከጭፍን ጥላቻ የመነጩ ይመስላሉ በቤተ ከልርስቲያናችን እየተደረጉ ያሉትን ሁሉ ለአንድ አካል ብቻ ተሰጥቶ በሚነገርበት ግዜ ለምሳሌ የተክለሓማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ያደረጉትን ለማሕበረ ቅዱሳን ሲኖዶሰ የወሰነውን ለማሕበረ ቅዱሳን ውንጀላው ሲበዛብኝ ይህን ማሕበር ይህ ድረ ገጽ ለምንድር ነው ባልሆነው በሆነው የሚወነጅለው በማለት መጠየቅ ጀምሪያለሁ አካሄዳችሁ የብስለት ይሁን

  ReplyDelete
 3. i have the same comment

  ReplyDelete
  Replies
  1. I have the same comment, too. Why so much time to blame M.K. There may some huge secret behind your deeds, that make you focus on M.K.
   If you realy care for the words of God there are a lot of Crops on the field. Just feel releif by leaving M.K, otherwise you folks in sheeps figure.The word "Geta..." is better used Getachin Medihanitachin iyesus..." that have great meaning in our church. May God bless you come to the Exact road!!!!!

   Delete
 4. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መሪ አልባ ሆነች .... የማህበረ ቅሱጣን ወደል ማሃይሞች ከአስመሳይ ሃይማኖተኝነት ወደማጅራት መቺነት ተቀየሩ ይገርማል!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አየ የሰይጣን ፍልስፍና! እኔ በራሱ በስንቃጣ (ፍረወይኒ ) በ2001 ማህበረ ሰላማ ነበርኩኝ በጣም የሚያሳዝነው ግን የግለ ሰው ቤት ጫማችሁን ኣውልቃችሁ ግቡበት የሚለው ኑፋቄ ነው ከዛ ቤቱ ይሰገድ እና ቆይቶው ስግደት ለቅዱሳን ኣይገባም ትላላችሁ ስለዚ እኔ ግዜ የለኝም ሁሉ አሉባልታችሁ ለመፃፍ ግን ባቀረባችሁት ፅሑፋችሁ ሃይላይት ልጥቀስላችሁ 1.አቡነ ተክለሃይማኖት ፃድቅ ገባሪ ተኣምር ኣባት ናቸው ስለዚ ለምን ከኣባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ትሉዩዋችሃላችሁ ምክንያቱ በርግጥ አባ ሰላማ ለኑፋቄኣችሁ የሚመች መስራተችሁ እንጂ እውነተኛው ቅድስት ቤተ ክርስትያናችንም ይሁን ማህበረ ቅዱሳን ይዘክራሉ 2.ታቦት የሚጠራው በእግዚአብሔር ፍቃድ እንጂ ልክ እናንተ እና እንደ እኔ የመሰሉ ሰዎች ለልጆቻችን እንደ ምንሰጠው ስመ ኣይደለም ስለዚህ የኢየሱስ ቢባል የማርያም ቢባል የገብርኤል ባወቃችሁስ ታቦቱ የስሉስ ቅዱስ የክርስቶስ ኢየሱስ ታቦት ነው የሚቀረፀው በተለያዩ ቅዱሳን ቢጠራም 3.ኢየሱስ ክብር ምስጋና ለስም ኣጠራሩ ይሁንነና የሚል ክቡር ስም ልክ እንደ ጓደኛችሁ ኢየሱስ ወዳጄ ወንድሜ ስትሉት የጌታችን ስም ሲዘነጠል ኣወ እውነተኛው ክርስትያን ከኣህዛብ በሚለየው መልኩ እውንተኛ ልጅነቱ የሚያረጋግጥበት የፈጣሪው ስም ሲዛነፍ የናድደዋል ማናደድም ብቻ ሳይሆን ልክ ቅዱስ ሚካኤል ከ ሰይጣን በሙሴ ሰውነት ላይ ሲከራከሩ እንደ ተናገረው ጌታ ይገስፃችሁ እንላለን 4.ዘማርያኑንና ሰባካያኑ ልክ እንደ እናንተው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ኢየሱስየ ሲሉ በእውነተኛው አማኝ ስሜት ይንሳበታል ለምን ቢባል በእነሱ ምክንያት ፈጣርያቸው በኣሕዛብ ስለ ሚሰደብ፣ የሚዘምሩት መዝሙርም ኣምላክነቱ ኣይገልፁምና ፡፡ ብዙ መፃፍ ይቻላል ይሁን እንጂ የምትመለሱ ከሆናቹ የኔ የደካማው መልስ ሳይሆን የኣባቶች ውግዘት ባረማችሁ ነበርና

   Delete
 5. i don't think this blog doesn't go by it's law.
  it looks like going to the opposite . i read your blog every day , but it has negative impact on one side . i didn't see when MK blogers are participated.

  ReplyDelete
 6. Don't you people have anything else except demonizing Mahibere Kidusan? Why don't you look at their website and take some ideas how to run a christian site? Shame on you!!!

  ReplyDelete
 7. +++
  Aba Selama Blog: Teru newu, rashachehun ortodox lemasmesel yaderegachehut mukera, gen yikebedal yastawukebachuhal. Eseti tetachehu wede betekerstian Temelesu. Alzegeyem Eyesus Kerstos hulem lenesseha Ejun zergeto Yitebekachuhal. Wusete Gebeto Mamtatatu yibekachu eseti. Ke ande Enjera belay aybel yehen yahel letekem(Mechem Lehayamanot Alelem). Yimegermewu Beyetegnewu Aba Selama newu Blogun Yeseyemachehut? Bemetesedebut Kidasan weis kenante yandachehu sem newu? Legizehu yebetekerstiann fetena betebezum mashenefe Endematchelu Eweku(Yeganem Dejoch Aycheluwatema).Lemangnewum Eyesus kirstos, Bekeraniyo demun selegna yafesesewu, segawun yekoresewu Amanuel, Yealemu Medehanit Medehanialem(Atsasatu Hulum Yesu semoche nachewu)Lebonachehun meleso leneseha mot yabekachehu zend Kedus fekadu yihunlene.Amen

  ReplyDelete
 8. Dear Aba Selama Blog. If You have confidence on what you have written, why not post your phone, address, photo....etc, like D/n Daniel Blog, Mahibere Kidusan website,.....
  May the help of God Be with us.

  ReplyDelete
 9. You - group of protestants: why don't you leave our Church? Your backups from Europe have already left their so called religion but እናንተ አዲስ ሁናችሁ ቤተክርስቲያናችንን ትበጠብጧት አላችሁ። ለነገሩ ለእምነቱ ሳይሆን ለምታገኙት ገንዘብ ነው የምትሰሩት።እኛን ለማስተው ይህን ሁሉ ምን አደከማችሁ። ሰው ለማጥፋት ይህን ያህል ሩጫ ይገርማል። የእኛን ቤተክርስቲያን ነው እናንተ የምታድሷት መጀመሪያ መሰረቱን እስቲ መለስብላችሁ አስተውሉ። በመጨረሻ ይህ እንደሚሆን መጽሐፍ ይናገራል። መቸም የእኛ ቤተክርስቲያን በኋላ የመጣች ትምቢት መፈፀሚያ እንዳልሆነች ልነግራችሁ አልፈልግም። ማን በማን ላይ በጥፋት እንደሚነሳ ስለሚታወቅ እግዚአብሔር አምላክ ልቦና ይስጣችሁ።

  ReplyDelete
 10. Ethiopian yemekefafel eked kalachehu zeregnenetun tewutna beglts tenageru hezbun bekedusanu yemtkefaflut neger altemechegnem. Sele mk degmo tenesh weshetu menamen beza ewnet ewnet eyalachehu quntal weshet mederder yekebdal. Bemecheresham tsadiku teklehaymanot enante legenzeb mesbsebiayanet yanegebchehuten wongel le ethiopia yaberu talak sew nachew.

  ReplyDelete
 11. Wow do you guys pray, fast or confess at all? You have no religion. Who in the world say this kind of bad words when he says he is christian. I will never read this blog

  ReplyDelete
 12. Makoch Ayzoachihu! The world knows you guys are good followers of the church. The issue is your mahber. Your mahber Blinded you and paralized your brains so that you don't think. Not sure if they used drugs to do that to you. ወይም ደግመውባችሁ ይሆናል። የድግምት መጻህፍት እንደሆን በየጓዳችን ተርፈዋል። ለዚህም ይሆናል አንዳቸውም እንዳይነኩ ማቅ ሽንጡን ገትሮ የሚከራከረው። It is my wish that you all get out of that 'Merzegna' mahber and just stick to your beautiful tewahedo church.

  ReplyDelete
 13. 14 በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤

  የዮሐንስ ወንጌል 2-15 የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥

  16 ርግብ ሻጪዎችንም። ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው።በንስሀ፡ብትመለሱ፡ይሻላችዋል፡፡ቤተክርስቲያንን፡መዋጋት፡ክርስቶስ፡መዋጋት፡መሆኑን፡እወቁ፡፡

  17 ደቀ መዛሙርቱም። የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ።

  ReplyDelete
 14. ይድረስ ለአባ ሰላማ ብሎግ አዘጋጆች እና የብሎጉን አብይ ተልዕኮ ለምትደግፉ ሰዎች በሙሉ፡፡

  እናንተ ያነሳችሁት የመለወጥ አስፈላጊነት በእዉነቱ በዚህች ቤተ ክርስትያን ያለ እንኳን ቢሆን፤ እጅግ ክርስትያናዊ ካልሆነዉ አቀራረባችሁ የተነሳ እንዴት ልንቀበለዉ እንችላለን? በክርስቶስ አምኛለሁ የሚል ሰዉ፤ ክርስቲያናዊ ስነ ምግባር ሊኖረዉ አይገባም ወይ?

  እንኳን የክርስቶስ ፍቅር ልቡን ከሰበረዉ ክርስትያን ይቅርና ከአንድ ሀይማኖት የለሽ የመንደር ዱርየ እንዲህ ያለ ጸያፍ ንግግር፤ ስድብ እና እርግማን እንዴት ይጠበቃል? ይህስ የክርስትና ፍሬ ነዉ?

  በእዉነት የሚከተሏቸዉ ኦርቶዶክሳዊያን ፈጽመዉ ተሳስተዋል ብንል እንኳ፤ በእዉነት እነርሱ ራሳቸዉ ይህንን የሚሰጣቸዉን ክብር አይፈልጉትም ብንል እንኳ፤ እንዴት አርገን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱሳን እንዲህ እንዘልፋቸዋለን? እንዴትስ እንዲህ እናቃልላቸዋለን? በዚህስ ለጌታችን ክብርን እንጨምርለታለን? እርሱን አምነዉ፤ እርሱን ተከትለዉ ህይወታቸዉን የሰጡ ቅዱሳን ሲዘለፉ የሚደሰት አምላክስ እንዴት ያለዉ ነዉ?

  ይልቁንስ ጸያፉን ስድብ ወደጎን ተዉትና የሚከተሉትን ጥያቂዎች መልሱልኝ፡፡

  1. ከላይ የጠቀሳችኌቸዉ የቅዱሳን ገድላትን እዉነተኝነት የተጠራጠራችሁት ከምን መነሻ ነዉ? ፈጽመዉ ለአእምሮ የሚከብዱ፤ ለማመን የሚያዳግቱ ለሰዉ ልጅ አቅም የሚከብዱ ስለሆኑ ነዉን? እንዲያ ከሆነ የገድላቱን ትተን በመጸሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ለማመን የሚከብዱ ለጆሮ የሚቆረቁሩ ታሪኮች የሉም? አህያ ሰዉን አናገረች ተብሎ አልተጻፈምን? ሰዉ በአሳ አንበሪ ሆድ ተጓጉዞ፤ ተተፍቶ፤ ንስሀን ሰበከ ተብሎ አምተጸፈምን? ሰዉ ወደ ጨዉ ዲንጊያነት ተቀየረ የሚል አልተጸፈምን? ታዲያ ገድላቱ ላይ የተጻፉት የቅዱሳን ስራዎችን ማመን ከሌለብን የመጽሀፍ ቅዱሶቹን ታሪኮች እንደምን ባለ አገባብ ልንቀበላቸዉ እንችላለን?

  2. ብዙዉን ግዜ እንደምንሰማዉ ስለ ገድላቱ እና ድርሳናቱ የምታነሱት እንዲሁ የሰዉን ቀልብ ለመግዛት ነዉ እንጂ በመሰረታዊ የሀይማኖት ጥቂዎች ላይ ፈጽሞ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ያፈነገጣችሁ እና ለትሮቴስታንት ዶክትሪን የቀረባችሁ ናችሁ ይባላል፡፡ እንደምትባሉት መሆን አለመሆናችሁን ከእናንተ መስማቱ ሀሳቦቻችሁን በትክክል ለመረዳት ጠቃሚ ነዉና እስኪ ለሚከተሉት ቀጥተኛ ጥያቄዎች የእናንተን ቀጥተኛ መልስ ብትሰጡኝ፤


   ኢየሱስ ክርስቶስ ያማልዳል ወይስ አያማልድም? አምላክነቱስ እንዴት የለ ነዉ? (ከምስጢረ ስላሴ አንጸር)
   ቅዱሳን ያማልዳሉ ወይስ አያማልዱም? የምልጃ አስፈላጊነትስ ምንድን ነዉ፡፡ ይህንንም በህይወተ ስጋ እያሉ እና በአጸደ ነፍስ ሆነዉ በሚል በሁለቱም ግዜያት ብትመልሱልኝ
   እምነት ብቻዉን (ያለስራ) ያጸድቃልን?
   ስርአት ለክርስትያኖች ስፈልጋልን? የጾም፤ የጸሎት፡ የስግደት፤ የአለባበስ እና የመሳሰሉት
   ታቦት ለቤተክርስትያን ያስፈልጋልን?
   መስቀል ለክርስትያኖች ያለዉ ፋይዳ ምንድን ነዉ?
   ቅዱሳን ስእላት ያስፈልጋሉን? እነርሱን መሳለም እና በእነርሱ አንጻር መጸለይ ይገባልን?
   ለቅዱሳን የጸጋ ስግደት መስገድ ይገባልን? እነርሱን ማመስገንስ?
   ጸበል አስፈላጊ ነዉን? ያድናልስ?
   የንስሀ ስርአት እንዴት ያለ ነዉ? ለንስሀ አባት ሀጢያትን መናዘዝ የግድ ነዉን? ካህናትስ ሀጢያትን ይቅር ማለት፤ ማስተስረይ ይችላሉን?

  ለእኒህ ጥያቂዎች የሚኖራችሁ መልስ ለእናንተ የሚኖረንን አመለካከት እና አቀባበል ይወስነዋል፡፤ ይህን ጥያቄ የብሎጉ አዘጋጆችም ሆናችሁ የእንቅስቃሴዉ ደጋፊዎች ጥርት አርጋችሁ እንድመልሱልኝ በእግዚአብሄር ስም እለምናችዃለሁ፡፡

  ፍቅረ ዮሀንስ
  ይድረስ ለአባ ሰላማ ብሎግ አዘጋጆች እና የብሎጉን አብይ ተልዕኮ ለምትደግፉ ሰዎች በሙሉ፡፡

  እናንተ ያነሳችሁት የመለወጥ አስፈላጊነት በእዉነቱ በዚህች ቤተ ክርስትያን ያለ እንኳን ቢሆን፤ እጅግ ክርስትያናዊ ካልሆነዉ አቀራረባችሁ የተነሳ እንዴት ልንቀበለዉ እንችላለን? በክርስቶስ አምኛለሁ የሚል ሰዉ፤ ክርስቲያናዊ ስነ ምግባር ሊኖረዉ አይገባም ወይ?

  እንኳን የክርስቶስ ፍቅር ልቡን ከሰበረዉ ክርስትያን ይቅርና ከአንድ ሀይማኖት የለሽ የመንደር ዱርየ እንዲህ ያለ ጸያፍ ንግግር፤ ስድብ እና እርግማን እንዴት ይጠበቃል? ይህስ የክርስትና ፍሬ ነዉ?

  በእዉነት የሚከተሏቸዉ ኦርቶዶክሳዊያን ፈጽመዉ ተሳስተዋል ብንል እንኳ፤ በእዉነት እነርሱ ራሳቸዉ ይህንን የሚሰጣቸዉን ክብር አይፈልጉትም ብንል እንኳ፤ እንዴት አርገን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱሳን እንዲህ እንዘልፋቸዋለን? እንዴትስ እንዲህ እናቃልላቸዋለን? በዚህስ ለጌታችን ክብርን እንጨምርለታለን? እርሱን አምነዉ፤ እርሱን ተከትለዉ ህይወታቸዉን የሰጡ ቅዱሳን ሲዘለፉ የሚደሰት አምላክስ እንዴት ያለዉ ነዉ?

  ይልቁንስ ጸያፉን ስድብ ወደጎን ተዉትና የሚከተሉትን ጥያቂዎች መልሱልኝ፡፡

  1. ከላይ የጠቀሳችኌቸዉ የቅዱሳን ገድላትን እዉነተኝነት የተጠራጠራችሁት ከምን መነሻ ነዉ? ፈጽመዉ ለአእምሮ የሚከብዱ፤ ለማመን የሚያዳግቱ ለሰዉ ልጅ አቅም የሚከብዱ ስለሆኑ ነዉን? እንዲያ ከሆነ የገድላቱን ትተን በመጸሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ለማመን የሚከብዱ ለጆሮ የሚቆረቁሩ ታሪኮች የሉም? አህያ ሰዉን አናገረች ተብሎ አልተጻፈምን? ሰዉ በአሳ አንበሪ ሆድ ተጓጉዞ፤ ተተፍቶ፤ ንስሀን ሰበከ ተብሎ አምተጸፈምን? ሰዉ ወደ ጨዉ ዲንጊያነት ተቀየረ የሚል አልተጸፈምን? ታዲያ ገድላቱ ላይ የተጻፉት የቅዱሳን ስራዎችን ማመን ከሌለብን የመጽሀፍ ቅዱሶቹን ታሪኮች እንደምን ባለ አገባብ ልንቀበላቸዉ እንችላለን?

  2. ብዙዉን ግዜ እንደምንሰማዉ ስለ ገድላቱ እና ድርሳናቱ የምታነሱት እንዲሁ የሰዉን ቀልብ ለመግዛት ነዉ እንጂ በመሰረታዊ የሀይማኖት ጥቂዎች ላይ ፈጽሞ ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ያፈነገጣችሁ እና ለትሮቴስታንት ዶክትሪን የቀረባችሁ ናችሁ ይባላል፡፡ እንደምትባሉት መሆን አለመሆናችሁን ከእናንተ መስማቱ ሀሳቦቻችሁን በትክክል ለመረዳት ጠቃሚ ነዉና እስኪ ለሚከተሉት ቀጥተኛ ጥያቄዎች የእናንተን ቀጥተኛ መልስ ብትሰጡኝ፤


   ኢየሱስ ክርስቶስ ያማልዳል ወይስ አያማልድም? አምላክነቱስ እንዴት የለ ነዉ? (ከምስጢረ ስላሴ አንጸር)
   ቅዱሳን ያማልዳሉ ወይስ አያማልዱም? የምልጃ አስፈላጊነትስ ምንድን ነዉ፡፡ ይህንንም በህይወተ ስጋ እያሉ እና በአጸደ ነፍስ ሆነዉ በሚል በሁለቱም ግዜያት ብትመልሱልኝ
   እምነት ብቻዉን (ያለስራ) ያጸድቃልን?
   ስርአት ለክርስትያኖች ስፈልጋልን? የጾም፤ የጸሎት፡ የስግደት፤ የአለባበስ እና የመሳሰሉት
   ታቦት ለቤተክርስትያን ያስፈልጋልን?
   መስቀል ለክርስትያኖች ያለዉ ፋይዳ ምንድን ነዉ?
   ቅዱሳን ስእላት ያስፈልጋሉን? እነርሱን መሳለም እና በእነርሱ አንጻር መጸለይ ይገባልን?
   ለቅዱሳን የጸጋ ስግደት መስገድ ይገባልን? እነርሱን ማመስገንስ?
   ጸበል አስፈላጊ ነዉን? ያድናልስ?
   የንስሀ ስርአት እንዴት ያለ ነዉ? ለንስሀ አባት ሀጢያትን መናዘዝ የግድ ነዉን? ካህናትስ ሀጢያትን ይቅር ማለት፤ ማስተስረይ ይችላሉን?

  ለእኒህ ጥያቂዎች የሚኖራችሁ መልስ ለእናንተ የሚኖረንን አመለካከት እና አቀባበል ይወስነዋል፡፤ ይህን ጥያቄ የብሎጉ አዘጋጆችም ሆናችሁ የእንቅስቃሴዉ ደጋፊዎች ጥርት አርጋችሁ እንድመልሱልኝ በእግዚአብሄር ስም እለምናችዃለሁ፡፡

  ፍቅረ ዮሀንስ

  ReplyDelete
 15. ተዋህዶን ታድሷት ዘንድ የተዘጋጃችሁ እናንት እንማን ናችሁ ?

  1.እናንተ ግን ተዋህዶን ልታድሱ የተነሳችሁ አዳሾች ፦ ተዋህዶን ታድሱ ዘንድ ምን ህፀፅ ጉድለት አገኛችሁባት? የትኛውንስ
  የሃይማኖት ዶግማ ልታሻሽሉት ሃሳብ ገባችሁ? እስኪ መልሱልኝ ቃል ስጋ ስለመሆኑ ምስጢር ነውን ? ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ፣
  ከእውነተኛ አምላክ የተገኝ እውነተኛ አምላክ ፣ የተወለደ እንጂ የተፈጠረ ያይደለ ፣ በባህርይው ከአብ ጋር የሚስተካከል ፣ ሁሉ በእርሱ
  የሆነ የሚለውን ህፀፅ አገኛችሁበት? ወይንስ ከሁሉ በላይ በምትሆን ሃዋርያት በሰሯት በአንዲት ቤተ-ክርስቲያን እናምናለን የሚለው
  ጎረበጣችሁ? አለዚያስ ሃጢአት በሚሰረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን የሚለውን የክርስቶስ ትእዛዝ አይደለም ትላላችሁ? ስለ ክቡር
  መስቀሉ ሃይል የተነገረውንስ ልትክዱስ ትዳዳላችሁ? ወይንስ የዘላለም መጥፊያ የሚሆናችሁን የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና፣
  አማላጅነትና የአምላክ እናትነት አለማመንን ገንዘብ አደረጋችሁ? አለዚያስ ፃድቃን ቅዱሳንን ንቃችሁ ራሳችሁን ፃድቃን አደረጋችሁ?
  እንዲህስ ከሆነ እንግዳ የሆነውን ትምህርታችሁን ከወዴት አመጣችሁት? እስኪ መልሱልኝ መሬት ወድቃችሁ አመድ ነስንሳችሁ ፆምን
  ፆማችሁን? ይህንስ እንዳልል አላማውን በዘነጋው አገልግሎታችሁ ብዛት በመድከማችሁ ፆምን መፆም ትታችኅል፡፡ ፆምስ ካልሆነ ታዲያ
  ሱባኤ ገብታችሁ ሌቱን በትጋት በፀሎት በመቆም ፣ ቀኑን ሙሉ ቅዱሳን መፃህፍትን በመመልከት ተጠመዳችሁን? ይህንንም እንዳልል
  ውሏችሁ ፣ አዳራችሁና ተግባራችሁ በአለም ከተቆራኝነው ከእኛ ጋር ነው፡፡ ታዲያ ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነት በተለየው አንደበታችሁ
  መንፈስ ቅዱስ ፀጋውን አበዛልን ፣ ኢየሱስ ገለጠልን ትሉ ይሆንን? ነገር ግን የእግዚአብሄር ፀጋ ለዚያውም አዲስ ጥበብ ያለ ፆም ያለ
  ፀሎት እንዳይገኝ እናውቃለን፡፡ ታዲያ እናንተ የሃይማኖት መሰረትን ትቀይሩ ዘንድ የተነሳችሁ ከ318ቱ የኒቂያ ጉባኤ ሊቃውንት ትበልጡ
  ዘንድ ከእነ ቅዱስ ቄርሎስ የተሻለ ሃይማኖታዊ ግብር ታየባችሁን? እነዚያ የተወደዱ ሊቃውንት ግን “ ከአባቶች ከሃዋርያት ስትያያዝ
  የመጣች ከዚህ አትለፍ ፣ ከዚህ አትትረፍ ብለው የወሰኑዋት ፤ ሰውን ሁሉ ከአራት መአዘን የሰበሰበች ሃይማኖትን” አፅንተው፤
  ከተመሰረተው መሰረት ሌላ መሰረት እንዳይመሰረት አዘዙ፡፡

  ReplyDelete
 16. ተዋህዶን ታድሷት ዘንድ የተዘጋጃችሁ እናንት እንማን ናችሁ ?
  2.እናንተ ተዋህዶን ልታድሱ የተነሳችሁ ፦ የተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ስርአቷ አሪታዊ የሃዲስ ኪዳንም የፍቅር ብርሃን ያልበራባት
  መሰላችሁ ይሆን? ወይንስ ስርአቷ ክርስቲያናዊ እንዳልሆነ ሃሳብ ገባችሁ? እንደዚያ ካሰባችሁ የወንጌሉ ብርሃን ቤተ-ክርስቲያን ላይ
  በሙላት እንዴት እንደበራ የቤተ-ክርስቲያንን ስርአት ከየትኛው ጀምሬ ልናገር? መሰረቷም ጉልላቷም ክርስቶስ እንደሆነ አምና
  ስለምትሰራው ህንፃ ቤተ-ክርስቲያን ልናገር? ወይንስ ስለ የትኛው ልናገር? ስለ ሰጎኑ እንቁላል? ከሰገነቱ በታች ስላለው መሶበ-ወርቅ?
  በክርስቶስ ልደት ወቅት ሄሮድስ ያስጨፈጨፋቸውን ሰማእት ህፃናትን ጩኅት ስለሚያዘክረው በጣርያው ዙሪያ ስላሉት ትናንሽ ቃጭሎች
  ባወራ ይሻል ይሆን? ስለ በሩና ስለ መስኮቱ ? ስለ ቤተልሄም? ስለ ቅድስተ ቅዱሳን? ወይንስ ስጋወ ደሙ ስለሚከብርበት ታቦቱ
  ልናገርን? እንዲህ ስርአቷ በሙሉ ባለሙያ ሴት በጥንቃቄ እንዳሰናዳችው ማእድ በአግባቡ ተሰናድቶ አንዱ ካንዱ ጋር ሳይጋጭ ፣ አንዱ
  አንዱን ሳያጠፋው ፤ ከመሰረቷ እስከ ጉልላቷ በወንጌል ባሽበረቀችው ቤተ-ክርስቲያን ላይ ክርስቶስንና የክርስቶስን መለኮታዊ ፈቃድ
  የሚቃወም ምን ነገር አገኛችሁና እናድስ ብላችሁ ተነሳችሁ? ይህስ የቤተ-ክርስቲያን ውበት ምእመናን እንደ ቤተ-ክርስቲያናቸው ስጋቸው
  ነፍሳቸውና ልቦናቸው እንዲሁ በወንጌል እያሽበረቀ ለአለም ሁሉ ክርስቶስን በህይወት እንዲሰብኩ የሚያነሳሳ መሆኑን ልብ አላላችሁም?
  ወይንስ እናንተ ዲያቢሎስን ያስከፋውን ይህን እፁብ ድንቅ የቤተ-ክርስቲያን ጌጥ ታፈርሱ ዘንድ ሰልፋችሁን ከሚጠፉት ጋር አደረጋችሁ?
  እንዲህስ ካልሆነ የትኛውን ታድሱ ዘንድ ፈለጋችሁ? በቅዱሳን ስም በየወሩ የሚዘከረውን ዝክር ከወንጌል ውጭ ነው ትላላችሁን?
  ምእመናንስ የሰንበቴውን በረከት ሊካፈሉ ሲሰባሰቡ ስትመለከቱ ትናደዳላችሁ? ወይንስ በክርስቲያኖች ቤት ዘወትር በልደታ የሚቀቀለውን
  ንፍሮ ትርጉሙ ቢጠፋባችሁ መሳለቅ ወደዳችሁን? እናንተ ለፀሎት ለፆምና ለምስጋና መንፈሳዊነታችሁ ቢደክም ፣ አለማዊ ደስታና ጥጋብ
  በእናንተ ላይ ቢሰለጥን ፣ የስጋዊ ሃብት ምቾት ከተጋድሎ ቢያስቀራችሁ ፤ ቅዳሴ ያጥር ዘንድ እንደ አዋቂ ትማከራላችሁን? ወይንስ ከ7ቱ
  አፅዋማት እየመረጣችሁ ይህንን ፁሙ ፣ ይህ እንኳን አይጠቅምም ለማለት እንዴት ትደፍራላችሁ?

  ReplyDelete
 17. ተዋህዶን ታድሷት ዘንድ የተዘጋጃችሁ እናንት እንማን ናችሁ ?

  3.እናንተ ተዋህዶን ልታድሱ የተነሳችሁ ፦የሆነ ሆኖ ከቀደሙት ቅዱሳን አባቶቻችን አብልጠን እናንተን እንሰማ ዘንድ የተገባ ይመስላችኅል?
  ቅዱስ ያሬድ ያከበራትን ፣ የኖረባትን ፣ ያፀናትን እምነት ትተን አላፊ ጠፊ በሆነው በዚህ አለም ወሬያችሁ ተታለን የምንወጣ እንደሆን
  ታስባላችሁ? ወይንስ አባታችን አቡነ ትክለሃይማኖት ህይወታቸውን በሙሉ በስርአቷ የተመላለሱባትን ፣ ቅዳሴዋን አስቀድሰው
  የቀደሱባትን ፣ የእጣኑን ሽታ አሽትተው እጣን ያጠኑባትን ፣ ጥምቀቷን ተጠምቀው ያጠመቁባትን ፣ ትምህርቷን ተምረው ያስተማሩባትን
  ፣ ከአለማዊ ግብር ተለይተው እንደ ተዋህዶ ስርአት በገዳም ራሳቸውን ወስነው በፆም በፀሎትና በተጋድሎ ከክርስቶስ ጋር የተገናኙባትን
  መሰላል ትተን በገንዘብ ፍቅር የወደቃችሁትን ፣ በአለም ወዳሴ ያበዳችሁትን ፣ ከፆም ከፀሎት የተለያችሁትን እናንተን እንሰማ ዘንድ
  የምንፋጠን ሞኞች መሰልናችሁን? እናንተስ በየትኛው መልካም መንፈሳዊ ፍሬያችሁ ከአባቶቻችን ጋር ትደመሩ ዘንድ አዲስንም ትምህርት
  ታመጡ ዘንድ ቻላችሁ? ከመጀመሪያወቹ የክርስትና መናንያን ቀዳሚ የሆኑት የተወደዱት አባ ጳውሊ ፦ ከ90 አመታት በላይ አንድን ሰው
  እንኳን ሳያዩ በፆም በፀሎት ተወስነው በሚኖሩ ጊዜ ፤ አባታችን አባ እንጦንስ በእግዚአብሄር ተመርተው አባ ጳውሊን ሊጎበኙ ቢመጡ
  ምስጉን የሆኑ አባ ጳውሊ አባ እንጦንስን አንድን ነገር እንዲያመጡላቸው ግድ አሏቸው ፤ ይሔውም አቡነ አትናቴዮስ የኦርቶዶክስ
  እምነትን በ318ቱ ሊቃውንት ህግ ካፀና በኅላ ለመነኮሳት ልብስ የሚሆን ስለአዘጋጀ ከዚህ የመነኮሳት ልብስ አንድ እንዲያመጡላቸው
  ነበር ፤ ይህንም የሚያደርጉት አትናትዮስ ያፀናትን የኦርቶዶክስ እምነትን ህይወታቸውን ሙሉ እንደያዙ መኖራቸውን ህዝቡ ሁሉ
  እንዲያውቅ ለምስክርነትም እንዲሆን ተናገሩ፡፡ ታዲያ እናንተ ኦርቶዶክስን ታድሱና ትቀይሩ ዘንድ የተነሳችሁ ከእነኘህ ፅኑ ፣ ቅዱስ ፣
  ክርስቶስን የመሰሉ የምድር መላእክት ከሆኑ ስለ ወንጌልም ሁሉን ትተው ክርስቶስን ከተከተሉት አባቶች ትበልጡ ዘንድ ተገባችሁን?
  እንግዲህስ እወቁት እኛስ እናንተ በምትነግሩን ነፍስንም ደስ የማያሰኝ አዲስ እውቀት በመንግስተ ሰማያት ከምንኖር ይልቅ እነ አባ
  ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ፣ እነ ቅዱስ ያሬድ ፣ እነ ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ ፣ እነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ እነ አቡነ ተክለሃይማኖት የነገሩንን ይዘን ፣
  የኖሩበትን ህይወት ኖረን ሲኦል እንድንገባ እንመርጣለን፡፡ ነገር ግን መንግስተ ሰማያት ለእንደዚህ ያሉ ቅዱሳን አባቶች የተዘጋጀች
  እንደሆነች የክርስቶስ ወንጌል ይመሰክራል ፤ ይህችም ቅድስት ቦታ አለምን ንቀው ፣ ርቀው ፣ ጠልተው በእግዚአብሄር ትእዛዝ ለሚፀኑት
  እንደተሰጠች ፣ የመንፈስ ቅዱስ ፀጋም በፀሎት ፣ በፆም ፣ ትሩፋትን አብዝቶ በመስራትና በመሳሰሉት መንፈሳዊ ተግባራት የሚገኝ እንደሆነ
  እናውቃለን፡፡

  ReplyDelete
 18. ተዋህዶን ታድሷት ዘንድ የተዘጋጃችሁ እናንት እንማን ናችሁ ?
  እኛም ክብር የሚገባው ኢየሱስ ክርስቶስ የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡ በውስጣቸው ግን ነጣቂወች ተኩላወች ከሆኑ
  ተጠበቁ ፤ እንዚህንም ከፍሬያቸው ትለዩዋቸዋላችሁ እንዳለን ፤ ወንጌል በሚያበራልን ብርሃን ተኩላወችን ነቅሰን እናወጣ ዘንድ ይገባናል፡፡
  እናንተም ተዋህዶን ታድሱ ዘንድ የተነሳችሁ ለሰው ሁሉ የሚታየው ፍሬያችሁ መልካም አይደለምና አስቀድማችሁ ራሳችሁን በንስሃ
  ታድሱ ዘንድ አይሻላችሁምን? ስለ ገንዘብም ያላችሁን መገዛትና መመካት ትተው ዘንድ የተገባ ነው፡፡እናንተ ግን መንፈሳዊ ሰው የመንፈስን
  ስራ በገንዘብ እንዳይለውጥ አባቶቻችን ሃዋርያት መንፈስ ቅዱስን የማሳደር ፀጋን በፈቀደው ሰው ላይ ለማውረድ እንዲችል ከሃዋርያት ጋር
  ፀጋውን በገንዘብ ሊደራደር የሞከረውን ከንቱ ሰው የዘለፉበትን ነገር እረሳችሁት፡፡”የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰሩት” የሚለውን
  የአምላክ ትእዛዝ እንደገዛ ፈቃዳችሁ ለሆዳችሁ እንዲስማማ አድርጋችሁ ተረጎማችሁት፡፡የክርስቶስን ወንጌልና የመንፈሳዊውን ስራ በገንዘብ
  የመሽጣችሁን ነገር “ለሰራተኛ ደመወዙ ይገባዋል” በሚለው እድሜያችሁን ሙሉ የማትጨርሱትን ምድራዊ ሃብትን ማከማቻ
  አደረጋችሁት፡፡ የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ አባቶቻችን ግን እጅግ ውድ የሆነውን መንፈሳዊውን ፀጋ እጅግ ርካሽ ለሆነው አለማዊ ንዋይ
  እንዳይለውጡትና ከንቱ በሆነው ግብር እንዳይተባበሩ ከህሊናቸውና ከዚህ አለም አምሮት ጋር እድሜያቸውን ሙሉ ታገሉ ፤ ስላሽነፉትም
  ለክርስቲያን ወገኖች ሁሉ ትምክህትና አርአያ ተባሉ፡፡እናንተ ግን ከዚህ አለም ናችሁና የአለም ምኞቷና አምሮቷ ጠልፎ ጣላችሁ፡፡
  መንፈሳዊ ከመባልም የለየለት አለማዊ ነጋዴ ወጣችሁ፡፡ ስለነጋዴነታችሁም መንፈሳዊውን ስብከትም ሆነ መዝሙር ስታዘጋጁ
  የመንፈሳዊው ጌታ እግዚአብሄር ምን ብናገር ይወዳል(what God want or what the people need) ከማለት ይልቅ የዚህ
  ስብከትና መዝሙር ገዥ ምን ባዘጋጅለት ብሩን ደስ ብሎት ያወጣል ( what the people want) በሚል ለወጣችሁ፡፡በዚህም
  እግዚአብሄርን ማገልገል ትታችሁ ስለ ገንዘብ ጥማት የሰይጣንና የሰው ባርያ ሆናችሁ፡፡ በአለማዊውም ምቾትና መንደላቀቅ በሚገኝ
  በሚስረቀረቅና በሚያስገመግም ድምፅ ፣ ስለ ሃጢአት ሰውን ከመገሰፅ ይልቅ ፃድቅ በማድረግ ፣ በትህትና ራስን ዝቅ ከማድረግ ፈንታ
  በትእቢት ከሁሉ በላይ ራስን መስበክና ማስወደድን በማብዛት መልካም የነበረውን ሰው አለማዊ በሆነው ተግባራችሁ ከመንፈሳዊ
  ስነምግባር ይወጣ ዘንድ ታፋጥኑታላችሁ፡፡እንግዲህ እኔ ደግሞ የእናንተን ሃጢአት ስዘረዝር ራሴን ፃድቅ ማድረጌ ነውን?አይደለም ፤የእናቴን ቤት አጥር ልታፈርሱ ስትነቀንቁ ስላየኅችሁ እንጂ ፡፡ታዲያ እስኪ ንገሩን ፦ የትኛው መልካም ስራችሁ ተዋህዶን ልታድሷት አደረሳችሁ?
  ለመሆኑ ተዋህዶን ታድሷት ዘንድ የተነሳችሁ እናንተ እነማን ናችሁ? የክርስቶስን ወንጌል ለመስበክ ቤተ-ክርስቲያን ከምትችለው በላይ
  ለዚያውም የታወቀ አለማዊ መምህር ከሚጠይቀው ገንዘብ የሚበልጥ ካልተከፈለን ወንጌልን አንሰብክም የምትሉ ብኩኖች ፤ እኛም
  ካልሰበክን ጉባኤው ይፈታል የምትሉ ትእቢተኞች ስትሆኑ ፦ ከአለም ኑሮ ፣ መንፈሳዊ ኑሮ እንዲበልጥ ፤ ከገንዘብ ፍቅር የእግዚአብሄር
  ፍቅር እንዲሻል እንዴት መናገር ትችላላችሁ? ወይንስ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ባከማቻችሁት የደሃ ገንዘብ ፤ እናንተ እያማረባችሁ ፣
  እየወዛችሁ ፣ እየወፈራችሁ ና ትካሻችሁ እያበጠ ስትታዩ የምትሰብኩት ምእመናን ደግሞ እየጎሰቆሉ ፣ እየገረጡና እየከሱ መምጣታቸው
  መልካም እረኛ የሚያደርጋችሁ ይመስላችኅል? የተዋህዶ እውነተኛ እረኞች ግን ክርስቶስ እንዳደረገ በጎቹ እንዳይባዝኑበት ራሱን
  መስዋእት ያደርጋል፡፡ ዛሬ ዛሬ የተዋህዶ እውነተኛ እረኞች ከአንዱ ሃገር ወደ ሌላው ፣ ካንዱ መምህር ወደ እዚያኛው እየተንከራተቱ
  የክርስቶስን ወንጌል አምልተው ፣ አመስጥረው ቅኔን ፣ ዜማን ፣ ትርጓሜን ፣ አቋቋምን እድሜ ልክ ተምረው ሊቀ ሊቃውንት ቢባሉ ፦
  ተራራ ለተራራ ፣ ዋሻ ለዋሻ ፣ ገጠር ለገጠር እየዞሩ ገዳማቱ እንዳይፈቱ ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶች እንዳይበተኑ ፣ ምእመናን ከምግባር
  ከሃይማኖት እንዳይርቁ በ 40 ና በ 80 ብር ቤተ-ክርስቲያናቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሲያገለግሉ ፤ እናንተ ግን ምን ፣ መቼና የት
  እንደተማራችሁ እንኳን በቅጡ የማይታወቅ በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብን በቤተ - ክርስቲያን ስም ስታስገቡ ከእግዚአብሄር ይልቅ
  ለገንዘብ መገዛታችሁ እንደሆነ አታውቁምን? ወይንስ የገንዘብ ፍቅር መልካም ስራን ሁሉ እንደሚያጠፋ አልተማራችሁም? ወይንስ
  ደመወዛችሁ ይብቃችሁ የተባሉትን እውነተኛ የተዋህዶ ሊቃውንት የክርስቶስን ወንጌል በገንዘብ እንዲቀይሩ ፈተና እንደሆናችሁባቸው
  አልተረዳችሁምን?

  ReplyDelete
 19. ተዋህዶን ታድሷት ዘንድ የተዘጋጃችሁ እናንት እንማን ናችሁ ?

  ፕሮቴስታንታዊ በሆነው ስብከታችሁና መዝሙራችሁ ደግሞ የቅዱሳንን በትህትና ዝቅ ማድረግ እንደ ውርደት ቆጥራችሁ
  ራሳችሁን በሰውና በአምላክ ፊት ከፍ ከፍ ስታደርጉና ራሳችሁን ስታፀድቁ ፤ ተዋህዶ ግን ስለቅዱሳን መናገር አንድም ህይወታቸው
  ትምህርት ስለሆነ አንድም በረከታቸውን ለመካፈል እንደሚረዳ ስታስተምር ፣ እናንተ ግን የቀደሙ ቅዱሳን አባቶችን ማስረሳትን አንድም
  ምእመናንን ከበረታቸው ለማስወጣት አንድም በቀደሙት አባቶች መልካም ተጋድሎ የእናንተ ስራ እንዳይጋለጥ ስራየ ብላችሁ
  ተያያዛችሁት፡፡እናንተ ሌባ ሌባነቱ ቢታወቅ ፈቃዱን ይፈፅም ዘንድ ስለማይችል ፣ አመቺ ጊዜ እስኪያገኝ መልካም ሰው መስሎ ለመታየት
  ጥረት እንደሚያደርግ ፤ እናንተም አላማችሁን ሳታሳኩ ተሃድሶነታችሁ እንዳይጋለጥ በመዝሙራችሁና በስብከታችሁ ውስጥ በጥቂቱ ስለ
  አምላክ እናት ከመናገር ያለፈ እስኪ ስለ ሰማእቱ ጊዮርጊስ ፣ ሰማእቱ እስጢፋኖስ ፣ አቡነ ዘርአ ብሩክ ፣ አቡነ አረጋዊ ፣ አቡነ ሃብተ
  ማርያም ፣ ቅድስት አርሴማ ፣ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ፣ስለ ቅዱሳን መላእክት ፣ ስለ ሌሎችም ቅዱሳን ሁሉ በስህተት እንኳን የት ቦታ
  አስተማራችሁ? ነገር ግን ተዋህዶ እግዚአብሄር በቅዱሳኑ ድንቅ ነው የሚለውን ታምናለች ታስተምራለችም፡፡ ይህንንም የየወሩን እለታት
  በስማቸው ለመታሰቢያቸው ሰጥታ ትዘክራቸዋለች፡፡ እናንተ ግን ልጆቿ አይደላችሁምና ከእርሷ ያልሆነ አዲስን ዘር ትዘራላችሁ፡፡ እስኪ
  ንገሩን ፦ ቅዱስ ጳውሎስ እኔ ክርስቶስን እንደመሰልኩ እኔን ምሰሉ እንዳለ እነዚህን ቅዱሳን እንደታዘዝን የኑሯቸውን ፍሬ እያየን በእምነት
  እንመስላቸው ዘንድ ካልቻልን መንፈሳዊነትን ከማን እንማር ዘንድ ትወድዳላችሁ? ከእናንተ እንማር ዘንድ ፈቃድ ካላችሁስ ህይወታችሁን
  አይተን እንማርበት ዘንድ መልካሙ ፍሬያችሁ የት አለ? ወይንስ እውር እውርን ይመራው ዘንድ ይችላልን? እንደዚያስ ከሆነ መንፈሳዊ
  አይን በተለየው ህይወታችሁ የተዋህዶን ህፀፅ እንዴት ልትመለከቱ ቻላችሁ? ወይንስ ስለ ፆም ስለ ፀሎት መስማታችንን ትተን የእናንተ
  ችሎታ ስለሆነው በክርስቶስ ወንጌል እንዴት ገንዘብ መስራት ይቻላል? የሚለውን እናጥና ይሆን? ወይንስ ራስን በማክበድና በማስወደድ
  እንዴት የሰውን ከበሬታ ማገኘት እንደሚቻል እንማር? እኛስ ይህንን የሰይጣን ስራ እንዳንሰራ ፣ ሲጀመርም እናንተን እንዳንሰማ ፣
  ከተኩላወችም ጋር እንዳንተባበር ክርስቶስ አስቀድሞ አዘዘን፡፡
  ፕሮቴስታንታዊ በሆነው ስብከታችሁና መዝሙራችሁ ነፍስ የተለየው ስጋ ምውት እንደሆነ ከስራም የተለየ እምነት ባዶ ነው
  የሚለውን የተዋህዶ አስተምሮ ትታችሁ ለአለማዊ አኗኗር የሚስማማውን ስራ ስለተለየው እምነት አብዝታችሁ ታስተምሩ ዘንድ
  ደከማችሁ፡፡ነገር ግን ተዋህዶ ወርቅ ወርቅነቱ በእሳት ተፈትኖ እንዲታወቅ እምነትም ከዚህ አብልጦ በስራ እንዲፈተን ለልጆቿ
  ታስተምራለች፡፡ይህን የሚያውቁ ልጆቿም ዘወትር ለትሩፋት ይፋጠናሉ፡፡ነገር ግን እናንተ ፍሬ የማያፈራ ፣ ክብር የሚገባው አብም
  ያልተከለው የሚነቀል ዘርን በአሽዋ ላይ ትዘሩ ዘንድ ሮጣችሁ፡፡ፕሮቴስታንታዊ በሆነው እምነታችሁ በገዳም ተወስኖ እድሜን መጨረስ
  የሰነፎች ስራ ነው በማለት የአባ እንጦንስንና የአባ መቃርስን ትምህርት ሻራችሁ፡፡ነገር ግን በሰው ተከቦ ለአለም ሁሉ ወንጌልን ከመስበክ ፣
  ተአምራትንም እያደረጉ ዋጋን ከሰው ከመቀበል ፤ ራስን ስለ ክርስቶስ ከሰው ለይቶ ፣ ከምቾት ርቆ ፣ ስጋን ለነፍስ አስገዝቶ ፣ አብዝቶ
  በመፆም ፣ አብዝቶ በመፀለይ ፣ የሌሊቱን ድምፀ አራዊት ታግሶ ፣ የሰይጣንን ድብቅና ግልፅ ፈተና ታግሎ ድል ማድረግ ምን ያክል
  አድካሚና ዋጋውም የቱን ያክል የበዛ እንደሆነ ዘነጋችሁ፡፡ እናንተ ግን ለስጋችሁ አምሮት ከዚህ ግርግር ከበዛበት አለም የተሻለ አታገኙምና
  ለገዛ ምቾታችሁ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ትቃወማላችሁ፡፡ ታዲያ እስኪ ንገሩን ፦ በሁሉ ስህተት ሆናችሁ እያየን እናንተን እንሰማ ዘንድ
  የሚገባ ይመስላችኅል?
  እንግዲህ የተወደደው አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ኖሮበት ያለፈውን የቤተ-ክርስቲያናችን ዶግማና ቀኖና ይታደስ ዘንድ
  የምትሮጡ እናንተ እነማን ናችሁ? ወይንስ ማደስ (renew) የሚለውን ቃል መቀየር (change) ወይም ማሻሻል (upgrade)
  አድርጋችሁ ወሰዳችሁን? ማደስ ማለት ወደ ድሮው ወይም ወደቀደመው ነገር መመለስ (back to the Origional) እንደሆነ
  አላስተዋላችሁምን? ኦርቶዶክስን እናድሳት ስትሉስ ወደቀደመው ስርአቷ እንመልሳት ማለት እንደሆነ ካወቃችሁ ከቀደሙት ቅዱሳን
  አባቶች የተሻለ የቀደመችውን ሃይማኖት ታውቁ ዘንድ እንዴት ቻላችሁ? ነገር ግን የሰይጣን ምክር እንዳይዘነጋ የእናንተም ሃሳብ መልካም
  ስራን መስራት ሳይሆን አውሮፓውያንና አሜሪካውያን የራሳቸውን ህዝብ ከሃይማኖተኛነት አውጥተው አለማዊ አድርገውት ሲያበቁ
  ፦አሁን ደግሞ በሃይማኖት የፀኑትን የኦርቶዶክስ አማኝ ክርስቲያኖች ወደ አለማዊነት ወደሚያንደረድረው የፕሮቴስታንታዊ ምንፍቅና
  ማሰደድ ነው፡፡ ነገር ግን ቤተ-ክርስቲያን በክርስቶስ አለትነት ላይ የተመሰረተች ናትና የገሃነም ደጆች እንኳን አይችሏትም፡፡ እኛም
  ከቀደሙት ቅዱሳን አባቶች ይልቅ እናንተን ፤ ከመልካሙ መንፈሳዊ የህይወት ፍሬ ይልቅ የከረፋውን አለማዊ ህይወታችሁን አይተን
  እንታለል ዘንድ እንዳንችል እናንተ የናቃችኅቸው የቅዱሳን ፀሎት ዘወትር ይጠብቀናል ፡፡
  እንግዲህ ምን እንላለን ፦ እንዚያ አምነው የነበሩ የካዱትንም ትመልሷቸው ዘንድ አትድከሙ የሚለውን የተወደደ የሃዋርያ
  መልእክት እንሰማ ዘንድ ይገባናል፡፡ እናንተ ግን መልካችሁን እንደ ዲያቢሎስ እየቀያየራችሁ መኖሩ ልብንና ኩላሊትን በሚመረምር
  በእግዚአብሄር ዘንድ የተጠላ መሆኑን አስተውሉና ለነፍሳችሁ እዘኑላት፡፡ እኛ ልክ ነን ካላችሁ ግን ውጡ ፤ እምነታችሁን ይዛችሁ
  እምነታችንን ልቀቁልን፡፡ ስለ እምነታችሁም በአደባባይ ስበኩ ፣ አውሩ ፣ አስተምሩ ፤ ነገር ግን የተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አውደ ምህረት
  የእናንተ አይደለምና ውረዱ ፡፡ እግዚአብሄርም በውሽት ፣ በማጭበርበርና በማስመሰል እንደማይከብር ፣ በዚህም ሰወች ወደእርሱ
  ይመጡለት ዘንድ እንደማይፈልግ እወቁ፡፡ እናንተም ከእኛ ወገን የሆናችሁ ባለማወቅም ፣ በስንፍናም ከእነዚህ ጋር የምትተባበሩ የተዋህዶ
  ልጆች ስለ እናታችን ስለ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ብላችሁ ከፀረ-ተዋህዶ የዲያቢሎስ ተላላኪወች ተለዩ፡፡እናንተ ግን ተዋህዶን
  ልታድሱ የተነሳችሁ ፦ ከቀደሙት ቅዱሳን አባቶቻችን አብልጠን እናንተን እንሰማ ዘንድ የተገባ ይመስላችኅል? ወይንስ ቅዱስ ያሬድ
  ያከበራትን ፣ የኖረባትን ፣ ያፀናትን እምነት ትተን አላፊ ጠፊ በሆነው በዚህ አለም ወሬያችሁ ተታለን የምንወጣ እንደሆን ታስባላችሁ?
  ወስብሃት ለእግዚአብሄር ፣ ወ ለወላዲቱ ድንግል ፣ ወ ለመስቀሉ ክቡር፡፡

  ታምራት ፍስሃ
  ግንቦት 21/2003

  Come forward don't go under the shadows if you have some truth on you.

  ReplyDelete
 20. ኦርቶዶክስJune 16, 2011 at 1:38 PM

  T/Haymanot, You need to read more. I encourage you to read the book "Gedil Woyis Gedel" and get back to me with good responses. Read the whole thing, be open minded. When you are done, let me know and I will give you another book. Don't just judge the change agents without doing enough research.

  ReplyDelete
  Replies
  1. "ኦርቶዶክስ" your book Gedil woyis gedel is from anti Church source we all know it no need of other books,you better read the book "Gedil lemnafik Gedel" or better if you read the Gedil of St paul from his 14 messages from Holy Bible. Never use Ortohodox as your cover name as Orthodox fellows are known for their respect and honor of ALL SAINTS who are honored by GOd!! May God bless u. and come back to your previous home!!!!!!!!

   Delete
 21. አይ T/Haymanot, አንተ ጥሩ ቀናተና ሃይማኖተኛ ነህ። ዝም ብለህ አካኬ ዘራፍ ከማለት ቀስ ብለህ ሰውጥ ፈላጊ ወገኖቻችን ምን እንደተረዱ ብታስተውል ጥሩ ነው። ከላይ አንደተተቀሰው ገድል ወይስ ገደል እንዲሁም የተቀበረ መክሊት የተሰኙ መጻህፍትን አንብብና ፍርድ ስጥበት። ራስህን የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ሌላውን ጠላት አድርጎ መናገር አሳዛኝ ነው። መጀመሪያ አንብብ። ፕሮፓጋንዳ ብዙም ውጤት የለውም

  ReplyDelete
  Replies
  1. Wegenoche mejemeria be Kirstos rasenet yetemeseretechew tewahido betekrestian ye emnet a'emaduwa men endehone tereduna keza behuala wede gedlu ena awald metsehafu gemgema tegebalachu. Mewalehisanat saycheresu college merget eko hone negerachu. Egna man nenena new derso kidusan tesadabi yehonew?? Baykedesu enquan egna eneman nen enesun lemanquasheshena sim lemeletef?? Kirstos gen fikeren enji, lemitelun ena lemiyasadedun metseleyen enji mekefafelen alastemarenem. Ere sewoch enastewel... eski westachenen enemermer ena be ewnet ena bemenet Egziabheren enfeleg keza behuala ersu hulun yegeltelenal

   Be lewt felagi sem mafres gen ye kifu sira new wendemalem ante demo "Amde Haimanoten" Anbeb kehulu belay demo Kirstosen teketayoch enji sewochen teketayoch anehun!

   Delete
  2. You are not normal. why you open your WIDE mouth St tekehaymanot is the real church father you are messenger of other religious groups ,remember this word and send me your answer / alee lon le kenafr ele yineba ameta laele tadik be tiebit webe menino /it is giez language !!am M.W.N

   Delete
 22. ወልደ ገብርኤልJune 19, 2011 at 11:14 PM

  መፅሀፍ ቅዱስን በተለያየ መንገድ ሰድበን ለሰዳቢ ባንሰጥ መልካም ነው እውነትን እንናገራለን ካልን እውነትን እንፃፍ: ካልሆነ ግን አንኮነን የቤተ ክርስትያን ሁሉ ራስ እየሱስ ክርስቶስ ነው ብላ ቤ/ክርስትያን ታስተምራለች ቤቱ በቅዱሳን ስም መጠራቱ የጌታን ክብር ዝቅ አያደርገውም ይልቅ በቅድሣኑ መከበር እርሱም ደስ እንደሚለው እኛም ደስ ሊለን ይገባል እንጂ ልንቀናም አይገባም:: ራሳችንን ማክበር ትተን አምላካችንን እና ቅዱሳኑን እናክብር እራሳችንን ከፍ ማድረግ ጌታ አላስተማረንንም::

  ReplyDelete
  Replies
  1. መልካም ብለሃል ወንድም ወልደገብርኤል በኦርቶዶክስ ቤ/ክ ሥር ያሉ አድባራትና ገዳማት ሁሉ ተሚጠራው የሚቀደሰው የሚቆረሰው የህያው ክርስቶስ ስምና ቅዱስ ሥጋና ደም መሆኑን የዘነጉት ይመስላል፡፡ እባካችሁ እያስታወቀባቺሁ ነው፡፡ መመለስ ካልፈለጋችሁ ሌላውን ባትበጠብጡ ጥሩ ነው፡፡ ደግሞ እስቲ ክርስቲያናዊ ቃላት ተጠቀሙ ፡ ጀማሪ መናፍቃን መሆናችሁ ያስታውቃል ! ለቤተክርስቲያን አዲስ አይደለም፤ በውስጥም እንደ አላችሁ ይታወቃል ሆኖም እግዚአብሔር የሥራ ጊዜ አለው… ከቅዱሳን ክብር ጋር አትገዳደሩ ያከበሩህን አክብራለሁ እንዳለ ....

   Delete
  2. If you uncderstand He has already given everlasting life(New everyday).
   Churchs named by saints are not to mean Jesus Christ is left, he has given the stength to be saints. In that specific church you can hear AHADU AB KIDUS, AHADU WOLD KIDUS,AHADU WI'ITU MENFES KIDUS.... You may get the idea that this word has been said for more than 20 centuries. Reform is for Busness organisation not for GOD's church.

   Delete
 23. Well, there is serious problem on both sides. The tehadso wing does not have a clea agenda and is highly fragmented with the majority of its proponents being pente leaning or purely pente. On the other hand, the reform opponents led by mk tell us that every book and tradition that we find in our church is perfect. While I disagree with both pente reformists and mk, I want to share with the readers that this is the best time to reform ourselves by focusing on the core teachings of the bible instead of continuing the proxy christianity that we have had for years. The excessive focus on the saints in our church need to be balanced, and people need to start focusing on the bible and the bible and Christ.

  The way I see the excessive focus on the saints is as a proxy christianity. We need to come to the cross and cleanse ourselves with the blood of Christ. However, it is very important to mention here the imporance and great value of the saints, particulalry St. Mary. They are our models; they help us with their prayers etc... It is very helpful to have a saint as our intercessor; however, what I don't like to see is the excessive worship like devotion that almost takes out Christ out of the pitcture. I think that needs to be changed....

  Orthodox theologian Sergei Bulgakov wrote: "Love and veneration of the Blessed Virgin Mary is the soul of Orthodox piety. A faith in Christ which does not include his mother is another faith, another Christianity different from that of the Orthodox church."

  I agree with Sergei Bulgakov. How about you???

  ReplyDelete
 24. I have a lot to say but i don't think you will get it! though i will ask you a simple question. Why do you like the name of Orthodox Tewahedo so badly? clearly, what you wrote is not Ethiopian Orthodox Tewadedo's dogma. You even don't know what your religion is. Have your own first before opening your devil's mouth. For the record, you are not the kind of person who can point a finger on others bro. A piece of advice, if you want to be a better person, quit insulting others for it won't make you any better. Have you taken any psychology class? Jealousy makes people desperate like YOU. But you know what? Everything will be right when you face the truth
  which is bitter for you. Face the truth and leave our church!!!

  ReplyDelete
 25. Ayeee sew tefa, genzeb endih yadrigachihu esti lelaw yikir Gibtsawiyanu yazegajutin sile St. Takla Haymanout yetezegaje web site temelketuna http://st-takla.org/ egna yet lay nen bilachihu teyiku, Kedifret hatiyate yawitachihu.

  ReplyDelete
 26. ወንድማችን ነገረ ሃይመኖትን ከነገረ ብሔር ከነገረ ፖለቲካ እያዳቀልክ ስለጻፍክ ትክክለኛ ነኝ ለማለት እየሞከርክ መሆንህን ማንኛውም ተራ የቤተከርስቲያን ምአመን ሊያውቀው የሚችል ሐቅ ነው፡፡
  ይልቅ የቅዱሳንን ስም ከማጥፋት ራስህን ጠይቅ…በሌላ አነጋገርህ የኢትዮያ ሕዝብ እግዚአበሔርን ሲያመልክ እለኖረም ለማለት ዳር ዳር እያልክ ለመሆኑ ይታወቅሃል….ስለጾም አንስተሃል የምትፆም ከሆነ ቅዱሳንን የሚያዋርድ መንፈስ ባንተ ላይ ስለማደሩ አትጠራጠር…አብዘተህ ስለእግዚአብሔር ስም ለመቆርቆር የተጨነክ ይመስለኛል…እኔ ተራ ምዕመኑ እነኳ ልንገርህ የመናፍቃን ዋናው ሴራ እግዚአብሔርን የወደዱ እየመሰሉ ኢየሱስ…የናዝሬቱ እየሱስ…..ጌታ…የሚለውን ቃል እብዝተው እንደሚጠቀሙ አልተገነዘብክም….ለኛ ኦርቶክሳውያን የእግዚአብሔርን ስም መጥራት አዲስ አይደለም…..የበግ ለምድ መልበስ ግን አዲስ እንደሆነ አልተረዳህም ወይ….በስመ ክርስትና ለምን ይብሔር ስም ታነሳለህ ጌታችን ብሔር ከብሔር ለመለየት አልመጣም የተከተሉት ቅዱሳን አባትም እንዳንተ የአንድን ብሔር ልዕልና ለማጉላት የኖሩ አይደለም…..እስኪ ረጋ በልና የዘህችን ቤተክርስቲያን ነገር በጾም በጸሎት ጠይቅ…..አባታችን ተክለሃይማኖተ፣አባታችን ገብረመንፈስ ቅዱስ ሌሎች ቅዱሳን አባቶች እንዲሁም ቅዱሳት መላዕክት አንተ እንደምትላቸው እንደኛ በምግባር የወረዱ አይደሉም…እትጠራጠር በጊዜአቸው በምግባር የጸኑ አባቶች እንደነበሩ እመንና በአማላጅነታቸው እመን…..ምንም የሚጎልብህ ነገር ውይም ከአምላክህ የሚያርቅህ ነገር አይኖርም…..እስኪ ትክክለዓ ክርስቲያን ለመሆን ሞክር……ነገሮችህ በሙሉ በጸሎት በምልጃ እግዚአብሔርን በማሳወቅ ይሁን….በትዕቢትና በጉራ አይሁን……እትጠራጠር….አንተ ስላልደረስክበት ሚስጥር ሌሎችን አታሳስት…..ሰይጣንም ከመላዕክቶች አንዱ እንደነበረ አትዘንጋ ነገ አንተና እኔ ምን እንነደምንሆን ሰለማናውቅ ስለሁሉም ነገር ስለሚያውቀው አምላክ አብዝተን ልንለምነው ያስፈልጋል…..የዕምነት አባቶቻችንን እንምሰል….በእንግዳ ትምህርት አንወሰድ……የመናፍቃንን አጠራር እወቅ እንጂ ሌሎች እነዳላወቁ አታድርግ እኘም አስቀድመን እናውቃለን…..የበግ ለምድ ግን መልበስ አንፈልግም እወነተኛ በጎች ግን መሆንን አጥብቀን እንፈልጋለን…..የክርስትና ጉዞ ተጀመረ ገና ብዙ ጊዜ ይቀረናል……
  እግዘኢአብሔር ወደ ቀናው እምነትህ ይመልስህ፡፡

  ReplyDelete
 27. Menfesin Hulu Atimenu, ewenet ahun enante orthdox tewahedo nen bitilu endew ene tinishu, dekamaw, mahiyimu enkuwan alamenkuwachihum wey Anchi Mariyam yelalu enatoch.

  ReplyDelete
 28. MAy God give u new life to live, new brain to think with, new eyes to watch and new heart to pray. Because you are Enemies of Jesus that make the church to cry on your doings. May God help ypu to be good christians. If There any "tsilat" that do not have the name of the God? lets stop about others and let our self be persons for God.

  ReplyDelete
 29. "የተክለሃይማኖትን ገድልና ተረት..." እውነት ይህ ይኦርቶዶክ ተዋህደ ልጆች ድምጽ ነው? አያቹ ወንድሞቼ ለምን ማህበሩ ተሀድሶ አለ እንደሚል? አያቹ ወንድሞቼ ለምን ማህበሩ አሳዳጅ እንደበዛበት?

  ReplyDelete
 30. betam yemiyasazenew neger enante le mk betam telacha endlalachew eyansebarkachew new eyesus yemilewn sem enante endemetelute sheshete sayhone sitera enkwan lesem ateraru keber mesgana yegbawna amlakachen medhanitachen eyesuse kerestose belo new enje endegwadegn eyesus aylem lelaw betam tehadsio mehonachew eyetawek erasachehune magalete alebachew andem ken ke mahebere kedusan tefatew wechi lela neger atawekum Iam sorry.

  ReplyDelete
 31. hey sewoch me'emen yemilew kal silemaymethinachihu neew sititsifu eyastewalachihu kemereja ga bihon thiru neew seythan enkua yalemereja sewin hathiyategna neew bilo aykesim enante gin tinish agurazelel alhonachihum ? any ways ende ensesa sayhon ende seew asibu

  ReplyDelete
 32. ነገረ ሃይመኖትን ከነገረ ብሔር ከነገረ ፖለቲካ እያዳቀሉ ፣ እያሳከሩ መጻፍ የዲያቢሎስ አላማ ነዉ እንጅ የማን አላማ ሊሆን ይችላል?ተዋህዶ እምነትን ሳታዉቅና ስለቅዱሳን ሳትረዳ በጎሳ መደብካቸዉ። የጌታችን የመደሃኒታችን የኢዬሱስ ክርስቶስ ወዳጅ ለመምሰል ደግሞ ቅዱሳን የጌታችንን ክብር በተዋህዶ እምነት ፍልስፍና የተነሳ እንደነጠቁት ተናገርክ። ለምሆኑ በአሁኑ ሰአት በመላዉ ምዕራብ አለም ቤተክርስቲያን ወደ ሲኒማ ቤትነት፣ ወደ ዲያቢሎስ ቤትነት ሲለወጡ እና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምልኮ ከህዝቡ ልብ ዲያቢሉስ ሲያስጥል ለምን አንድ ቃል አትተነፍሱም። ነገረ ሃይማኖትን ከነገረ ብሔር ከነገረ ፖለቲካ እያዳቀልክ ይሄና ያ ብሄር ካልጠፋ የምትል ሰዉ በእዉነቱ የክርስቶስ ኢየሱስ ወዳጅ ነኝ ብትለኝ እንዴት አምንሃለሁ? ይሁን ይመችህ ፤ አንተ እንደተመኘህልን ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ መንፈስና ሀይል ለዘለዓለም በምድሪቱ እነመላለሳለ። እስካሁን ማንም እንዳላጠፋን ወደፊትም ምንም አይነት የደባና የጥላቻ መንፈስ አያጠፋንም።

  ReplyDelete
 33. "የተክለሃይማኖትን ገድልና ተረት..." እውነት ይህ ይኦርቶዶክ ተዋህደ ልጆች ድምጽ ነው? አያቹ ወንድሞቼ ለምን ማህበሩ ተሀድሶ አለ እንደሚል? አያቹ ወንድሞቼ ለምን ማህበሩ አሳዳጅ እንደበዛበት?

  ReplyDelete
 34. "የተክለሃይማኖትን ገድልና ተረት..." እውነት ይህ ይኦርቶዶክ ተዋህደ ልጆች ድምጽ ነው? አያቹ ወንድሞቼ ለምን ማህበሩ ተሀድሶ አለ እንደሚል? አያቹ ወንድሞቼ ለምን ማህበሩ አሳዳጅ እንደበዛበት?

  ReplyDelete
 35. "የተክለሃይማኖትን ገድልና ተረት..." እውነት ይህ ይኦርቶዶክ ተዋህደ ልጆች ድምጽ ነው? አያቹ ወንድሞቼ ለምን ማህበሩ ተሀድሶ አለ እንደሚል? አያቹ ወንድሞቼ ለምን ማህበሩ አሳዳጅ እንደበዛበት?

  ReplyDelete
 36. እለማወቄን ይቅር በለው!

  ReplyDelete
 37. Dear aba selama blogger don't be a floosh we know you .you were from us but now you are not with us. you were spent a lot of years in the church but b/c the church enable to fulfill your negative interest you have join the anther church groups for money. but you are training to seem an orthodox followers no one believe you .pleas back to your home EOTC is better from the religious you run. god help you!!

  ReplyDelete
 38. How is your witness as you are EOTC sons .no one .my be you sons, of aba melketsedek how divorce or divided the holly synod in to two parts and live in America hotels not in monastery as his parents .we know he was TEREMARYAM we know you from your message as you are not ours send your photo and real address then we believe you!!M.N.S

  ReplyDelete
 39. jiboch betekristiyan atbezebezim mechem mahberun egziabher yiredawal. tera weregnoch nachu

  ReplyDelete
 40. "የአስመሳዮች blog"


  እኔ በሕይወቴ ሳነብ በሙሉ ልብና ተመሰቶ ነበር.የናንተን ሳነብ ግን በመጠራጠር ና በአለማመን ሆነብኝ.ምን ነው ምክንያቱ? አስመሳዮች ናችሁአ.እንደዝህ ማስመሰል ምን ያደርጋል? ሌቦች ናችሁ.
  እባካችሁ የዚህ blog አንባብያን "የበግ ለምድ ለብሰው የመጣሉና ተጠንቀቁ"
  ኦርቶዶክስ በማስመሰል አይሆንም. ከጀርባችሁ ያለውን ምስጠር ማወቅ ለአንድ ክርስትያን ቀላል ነው " ኦ ማርያም ሆይ,የሰው ሃጽያት ውረስ የሌለብሽ አንቺ ቅድስት ከልጅሽ ዘንድ የቀርታና ምሕረተን ለመኝለን"

  ReplyDelete
 41. ለወፎች መጠለያ ለቀበሮዎች ጉድጓድ አላቸው የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት እንኳ የለውም‚ በማለት ጌታ አስቀድሞ ባይናገር እጅግ ይገርመን ነበር።

  ሲጀመር ይህ የከበረ ቃል ለመካን እይጠቀስም ሲቀጥል የክርስቶስ እቅዱም አላማውም አይደለም
  ይታሰብበት

  ReplyDelete
 42. እባካችሁ እናንተ አስመሳዮች የበግ ለምዳችሁን አውልቁና ወደ ነበረችሁበት ተመለሱ ተዋሕዶ በእናንተ አትታደስም፣አትፈርስም ለዘላለም ፀንታ ትኖራለች ይህ ደግሞ ይሆናል አሜን፡፡

  ReplyDelete
 43. ሌባ ሁሉማስመሰልህን ተውና ወደ ቀድሞ ሃይማኖትህ ተመለስ ይህ ከስልጣኔ አይቆጠረም ማንንም ለማሳሳት አትሞክሩ፡፡፡

  ReplyDelete
 44. "አንተ ሰው ሆይ"
  ብዙህ አልፅፍልህም ምክንያቱ ሆነ ብለህ ፀረ ይህ ትክክለኛው መንገድ ስለ ተነሳህ .እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ ግን እላለሁ.
  ሌላው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እኮ ኢየሱስ ክርስቶስ የናዝሬቱ ኢየሱስ አልፋ የሰማይና የምድር። እይለቸው ናት እኮ .የጌቶት ጌታ..የንግሶች ንጉስ...የአማልክት አምላክ..ብላ የምትጠራው ናት እኮ እስቲ ውዳሴ ማርያም ተመልከት.
  "አንተ ሰው ሆይ"
  በቅዱሳንስ እንዴት ያለ ድፍረት ነው ያለህ?አንድ የመፅሓፍ ቅዱስ እንንገርህ። ሉቃ 3:4-6 የውሓንስ መጥመቅ የጌታችን የመድሓኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ እንደ ጠረገ አንተ ደግሞ በእግዚአብሄር እና በሰማይ የሚኖሩ ቅዱሳን ላይ የመሳደብ አፍ የተሰጠው አውሬው (ራኢ 13:6) መንገድ እየጠረክ ነህ.እውነተኛ ከሆንክ ለምን ማንነትህ አትገልጥም?
  "አንተ ሰው ሆይ"
  አሁን ሰአት በድብቅ ሆንክ የሚትሰድባት ቤተ ክርስቲያን.... በግልጽ እንደ ምትመሰክርላት የሚያደርግ አንላክ ነው!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 45. "አንተ ሰው ሆይ "
  ብዙህ አልጽፍልህም ምክንያቱ ፀረ ስልዚህ ቤተክርስትያን ሆነ ብለህ ስለ ተነሳህ..እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ ግን እላለሁ።
  ኦርቶዶክስ እኮ ኢየሱስ ክርስቶስ የናዝሬቱ ኢየሱስ ወይ ኢየሱስ ጌታ ብቻ ሳይሆን የጌቶት ጌታ... የንጉሶች ንጉስ...የአማልክት አምላክ እያለች ናት። ራእስህ እና ተከታዮችህ መሸወድ ትችላለህ ።ውዳሴ ማርያም ብታነበው ግን ታገኘዋለህ።
  "አንተ ሰው ሆይ"
  ሌላው በቅዱሳንስ እንዴት አይነት የስድብ ቃል ተሰጠህ?አንድ የመጽሓፍ ቅዱስ ቃል እንስጥህ (ሉቃ 3:4) የውሃንስ መጥምቅ የጌታ መንገድ እንደ ጠረገ ይናገራል ።አንተ ደግሞ በእግዚአብሄር እና በሰማይ የሚኖሩ የመሳደብ አፍ የተሰጠው አውሬው (ራኢ 13:6) መንገድ እየጠረግክ ነህ።
  "አንተ ሰው ሆይ"
  እሺ እውነተኛ ከሆንክ ለምን ማንነትህ አትገልጥም?ተደብቀህ የሚትሰድባት ቤተ ክርስትያን በግልጽ እንደምትመሰክርላት የሚያደርግ አምላክ ነው!!!!!!!!

  ReplyDelete
 46. አባ ሰለመ!!አባ ሰለመ!!እንደዚህ አይነት የወረደና የኑፋቄ ጽሁፍ አይቼ አላውቅም፡፡የተክልየ ስም ሲነሳ ያማችኋል አይደል?ማህበረ ቅዱሳን የሚሰራውን መልካም ተግባርና ትሩፋት እያየ ምእመኑ መትፋት ብቻ አደለም የድንጋይ ናዳ ቢያዎርድባችሁ ምን ይገርማል?ፀሐይ የሆነውን የናዝሬቱን እየሱስንማ ከጥልቅ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ጋር እየገለጡት አይደለምን ?

  ReplyDelete