Thursday, June 16, 2011

የመጽሐፍ ቅዱስና የመልክአ ሚካኤል አለመግባባት - - - Read PDF

መጻሕፍት በመንፈስ ቅዱስ አሳሳቢነት በቅዱሳን አባቶች የተጻፉ የእግዚአብሔር መልእክት ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ  የታቀፉ እና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተወስነው የሃይማኖት ማስተማሪያ ሆነው የኖሩት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስድሳ ስድስት ሲሆኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተወስነው የቤተ ክርስቲያኒቱ የሃይማኖት መመሪያዎች ግን ሰማኒያ አንድ መጻሕፍት ናቸው። አንድ ሰው ሃይማኖቱ ትክክለኛነት ተመዝኖ ሊወገዝም ሆነ ሊመሰገን የሚችለው በነዚህ መጻሕፍት መሠረት ነው።

ነገር ግን በአሁኑ ዘመን በቤተ ክርስቲያናችን በቀኖና የማይታወቁ ከቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና ውጭ የሆኑ መጻሕፍት በቤተ ክርስቲያናችን ስም ወደ ሕዝብና አገልጋዮች ሾልከው ገብተው ቦታውን በመቆጣጠር፣ ባገሪቱ መጽሐፍ ቅዱስ የሌለ እስኪመስል ድረስ ውሸታቸውን አጋነው በማቅረብ አገሪቱን በክለዋል።

መልክዐ ሚካኤል የሚባለው ድርሰት በአጼ ዘራአ ያዕቆብ ዘመን እንደተደርሰ ይገመታል፣ መጽሐፉ በየወሩ የሚካኤል ማህሌት በሚቆሙ የቤተ ክርስቲያችን ተቀጣሪዎች በየተራ በቅብብሎሽ እየተዜመ ሚካኤል የሚመለክበት፣ የሚመሰገንበት ድርሰት ነው። ይህን መጽሐፍ ሁልጊዜ በመድገም ወደ ሚካኤል የሚጸልዩ ምእመናንና ደብተራዎች በርካታ ናቸው። የሚካኤል በአል ሲሆን ካህናቱ ሌሊቱን ሙሉ ሲዘምሩና ሲያሸበሽቡ ዚቅ የሚባለውን ሌላ ድርሰት ጨምረውበት ሲዘሉበት የሚያድሩት ይህን ድርሰት ነው። ምእመናን ግን ይህን  በቤተ ክርስቲያን እና በእግዚብሔር ላይ ሲካሔድ የሚያድረውን አመጽ ስለማያውቁ ካህናቱ ረጅም ሌሊት ሲጸልዩ በማደራቸው ይደክማቸዋልና ምርጥ ምርጡን ቁርጥ ቁርጡን እንጋብዛቸው በረከታቸውን እንካፈል እያሉ ይሽቀዳደማሉ። በነገው ዕለት በሚከበረው የሰኔ ሚካኤል ወደ አንዱ ቤተ ክርስቲያን ጎራ በማለት ይህን ድርሰት ማዳመጥ የሚቻል መሆኑን ሳንጠቁም አናልፍም። ነገር ግን በግዕዝ ብቻ ስለሚባል እግዚብሔር እና እነሱ ብቻ ናቸው የሚሰሙትና ላይገባችሁ ይችላል። ለሁሉም በመልክአ ሚካኤል እና በመጽሐፍ ቅዱስ መካከል ያለውን አለመግባባት እንዲህ አቅርበነዋል።

ከመልካ ሚካኤል

ሰላም ላአእዛኒከ እለ ያጸምአ ንባበ፣
ወጸሎተ ኩሉ ዘተመንደበ፣
ሚካኤል አቅልል እምላእሌየ እጸበ፣
ከመ ትመአድኒ ውትምህረኒ ጥበበ፣
ረስየኒ ወልደርሰይኩከ አበ፤

ትርጉሙ

ለጆሮዎችህ ሰላምታ አቀርቫለሁ፤
የተቸገረን ሁሉ ጸሎትና ልመናን ያዳምጣሉ፣
ሚካኤል ሆይ ችግሬን አቅልልኝ፣
ምከረኝ እውቀትንም አስተምረኝ፤
አባት አድርጌሃለሁና ልጅ አድርገኝ፤

ይህ ለሚካኤል የቀረበ ጸሎት እና ምልጃ ቤተ ክርስቲያናችን በተቀበልችው ሰማኒያ አንድ መጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኝም ወይንም ይህን ሐሳብ የሚደግፍ ንባብ የለም።  ቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎታቸውን ያቀረቡት ወደ እግዚአብሔር እንጂ ወደ መላእክት አልነበረም።  ወደ መላእክት ጸሎት ያቀረበ የእግዚአብሔር ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምንም አይገኝም። የኛ ደብተራዎች ግን ሚካኤልን እናነግሳለን በሚል ፈሊጥ እግዚአብሔርን ሲያስቀኑ እያደሩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሊመስሉ ይሞክራሉ። ሚካኤል የእግዚአብሔር ክቡር መልአክ አገልጋይና ተላላኪ የመላእክት አለቃ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚናገር ይህን ማንም አይክድም። ነገር ግን ጸሎትን የሚሰማና ጸሎትም ወደ እርሱ መቅረብ እንዳለበት የሚናገር ክፍል ፈጽሞ የለም፡  ደብተራዎች ለሚካኤል የሰጡትን ቃላት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለማን እንደተሰጠ እንመልከት፤

መጽሐፍ ቅዱስ

"ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል መዝ 652 እግዚብሔር በዓለም ምሉዕ በመሆኑ የሥጋን ሁሉ ጸሎት ምስማት ይችላል።

ታዲያ መነፍቃን ደብተራዎች "የተቸገረን ሁሉ ጸሎት የምትሰማ በማለት ለሚካኤል የሰጡት ከምን አምጥተውት ነው? ዛሬ የቤተ ክርስቲያናችን ሕዝብ በዚህ ክህደት እንዲተባበር የሚደረገውስ ለምንድን ነው? "ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል ሲል የኢትዮጵያን ሕዝብ አይጨምርምን? ሥጋ ሁሉ ካለ ኃጥአንም ሆኑ ጻድቃን ወደ እግዚአብሔር መጸለይ እንዳለባቸው የሚናገር አይደለምን? እንስሳት እንኳ ወደ ማን ማንጋጠጥ እንዳለባቸው የሚያውቁ መሆኑን እንዲህ ተብሎ ተጽፏል።

"እጓለ አንብስት ይጥህሩ ወይመስጡ ወይስእሉ ኀበ እግዚአብሔር ሲሳዮሙ
"የአንበሳ ግልገሎች ለመንጠቅ ይጮሃሉ፣ ምግባቸውንም ከእግዚአብሔር ይለምናሉ መዝ 10321

"ለሚጠሩት ለቁራዎች ጫጭቶች ለእንስሳትም ምግባቸውን ይሰጣል መዝ 1479
በጣም ትናንሽ የሆኑ የቁራ ጫጭቶች እግዚአብሔርን እንደሚጠሩ በዚህ ቃል ይታወቃል በእግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረው ያገሬ ደብተራ ግን ወደ ሚካኤል በመጸለይ የአምልኮ ዝሙት ይፈጽማል። ይህ እጅግ ያሳዝናል።

ችግሬን አቅልልኝ  መባል ያለበት እግዚአብሔር ነው። ዳዊት "ሕግህን አልረሳሁምና ችግሬን ተመልከት አድነኝም ብሏል።  ችግርን ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ መፍትሔን ያስገኛል። ሚካኤል ግን በእግዚአብሔር ሲላክ ብቻ ተልኮውን ይፈጽማል እንጂ እኛ ወደ እርሱ ስለጸለይን ደስተኛ አይሆንም ያለ እግዚአብሔርም ፈቃድ አንዳች ነገር ሊያደርግ ይችልም።

"በትእዛዛትህ ታምኛለሁና መልካም ምክርና እውቀትን አስተምረኝ  
መዝ 11966
 ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ መልካም  ምክርንና እውቀትን ይሰጣል እርሱ ልብና ኩላሊትን ይመረምራል፣ ለሁሉም የሚያስፈልገውን ያውቃል፣ ሶሎሞን "ማስተዋልን ስጠኝ በማለት የለመነው እግዚአብሔርን ነው። የኢትዮጵያ ደብተራዎች ግን የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ሥራ ለፍጡር በመስጠት "ሚካኤል ሆይ ምከረኝ እውቀትን አስተምረኝ እያሉ ወደ ሚካኤል ሲጮሁ ያድራሉ። ሚካኤል ግን ከእግዚአብሔር ሲላክ የእግዚአብሔርን ምክር ወይም የእግዚአብሔርን  ፈቃድ ሊያስተምርና ሊናገር ይችላል። በዳንኤል እንደተጻፈው የእግዚአብሔርን ምሥጢር መላእክት ይናገራሉ። ሆኖም ግን ዳንኤል የጸለየው ወደ እግዚአብሔር እንጂ ወደ መላኩ አልነበረም ይህን እራሱ መላኩ እንዲህ ሲል ያረጋጣል፦

"እነሆም አንዲት እጅ ዳሰሰችኝ፥ በጉልበቴና በእጄም አቆመችኝ። እርሱም እጅግ የተወደድህ ሰው ዳንኤል ሆይ እኔ ዛሬ ወደ አንተ ተልኬያለሁና የምነግርህን ቃል አስተውል ቀጥ ብለህም ቁም አለኝ። ይህንም ቃል ባለኝ ጊዜ እየተንቀጠቀጥሁ ቆምሁ። እርሱም እንዲህ አለኝ፣ ዳንኤል ሆይ አትፍራ፣ ልብህ ያስተውል ዘንድ ሰውነትህም በአምላክህ ፊት ይዋረድ ዘንድ ካደረግህበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ቃልህ ተሰምቷል  እኔም ስለቃልህ መጥቻለሁ
ዳን 1010-12
"እኔ ዛሬ ወደ አንተ ተልኬያለሁ የሚለው ቃል የመላኩን ዋና ሥራ ያመለክታል፣ "ልብህ ያስተውል ዘንድ ሰውነትህም በአምላክህ ፊት ይዋረድ ዘንድ ካደርግህበት ቀን ጀምሮ የሚለው ዳንኤል በአምላኩ ፊት እንጂ በመላኩ ፊት አለመውደቁን ያመለክታል። "ቃልህ ተሰምቷል ስለቃልህ መጥቻለሁ የሚለው ደግሞ የዳንኤል ጽሎት በጌታ ዘንድ መሰማቱን እና መልሱ በመላኩ እጅ መምጣቱን ይናገራል። እናም ሰው መጸለይ ያለበት ወደ እግዚአብሔር እንጂ ወደ መልክተኛው መሆን የለበትም። ዛሬ ደብተራዎች በቤተ ክርስቲያችን ገብተው በጉልበት የሚያደርጉት ባዕድ አምልኮ ከሰማኒያ አንድ መጻሕፍት ውጭ ነው።

"አባት አድርጌሃለሁና ልጅ አድርገኝ

በዚህ የደብተራዎች አባባል አባታቸው ሚካኤል እንጂ እግዚብሔር አይደለም። እንዲህ ባለ እምነት ግን ክርስቲያን ሊሆን አይሞከርም። ክርስቲያኖች በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የእግዚብሔር ልጆች ናቸው

"ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከወንድ ወይም ከሥጋ ፈቃድ አልተወለዱም ዮሐ 112-13

"አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና ማቴ 239

አንድ ሰው ከሁለት አባት ሊወለድ እንደማይችል ሁሉ ክርስቲኖችም አባታቸው አንዱ እርሱም የሰማዩ የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት አብ ነው። ከመንፈስና ከውሃ ዳግም የተወለድን ሁሉ አባታችን አንድ ነው እርሱም መንፈስ ስለሆነ በመንፈስ ወልዶናል፣ ታዲያ መናፍቃን ደብተራዎች ሁለተኛውን አባት ከየት አመጡት እንዴትስ ወለዳቸው? መጽሐፍ ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይና ከኛ ጋር አብሮ የእግዚአብሔር ባሪያ መሆኑን ይናገራል እንጂ የክርስቲያኖች አባት መሆኑን አይናገርም።

"ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምሥክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ ለእግዚአብሔር ስገድ.. አለኝ ራእይ 1910

በምድር ላይ በመንፈሳዊ ምክር ያሳደጉንን የምናውቃቸውን ቀሳውስትን አባቶች እንላቸዋለን ይህ ከነርሱ ጋር ስለምንተዋወቅ ምንም ነውር አይኖረውም ምክንያቱም እነሩሱን[ቀሳውስትን] ስለመንፈሳዊ ሕይወታችን እናማክራቸዋለን እንጂ ወደ እነርሱ እየጸለይን አንሰግድላቸውም።
በሰማይ የሚኖሩ መናፍስትን አባት እያሉ መጥራት መጸለይና መስገድ ግን ባዕድ አምልኮ ስለሆነ ቅዱሳን የሆኑ መላእክትም አይቀበሉትም።  ትሑቱ ሚካኤል "እንዳታደርገው ተጠንቀቅ ይላል እንጂ፤ አይቀበለውም።

አንዳድ ደብተራዎች በተለኮሰው የወንጌል እሳት ምክንያት ማስተዋል ጀምረዋል።  አሁን የሚካኤልን ታቦት እናነግሣለን እያሉ ሕዝብ እንዲሰበሰብ የሚያደርጉት ያመት ቀለባቸውን ለመሰብሰብ የሚሠሩት ድራማ እንጂ እውነት  እንደዚህ ከሐዋርያት እምነትና ሥርዓት ውጭ በሆነ ልምምድ ሚካኤልን ለማንገሥ እየሞከሩ አለመሆኑን አውቀውታል። ይህን ምሥጢረ ገንዘብ የማያውቁ ምእመናን ግን እጅግ ያሳዝናሉ የሚያደርጉትን አያስተውሉምና አምላካችን ይግለጥላቸው።

ማንገሥ ምንድር ነው?

ማንገሥ መሾም! ይሁን! ይሁን! ይገባዋል ማለት ነው፤ ሚካኤል ግን በእግዚአብሔር ከተሾመ እጅግ ብዙ ዘመን አለፈ እርሱ የመላእክት አለቃ እንጂ የሰው ዘር አለቃ አይደለም።  በሰውና በመላእክት በፍጥረት ሁሉ ላይ ሥልጣን ያለው በተዋሕዶ የከበረው የድንግል ልጅ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነው። አምልኮ ክብር ምስጋና ለርሱ ይገባዋል። ሚካኤልን "ማንገሥ ማለት ምንድር ነው? " ማምለክ የምተለዋን ቃል ዘወር አርገው "ማንገሥይላሉ መናፍቃኑ እንዳይንቃባቸው የፈጠሩት ይመስላል። ማንገሥ ማምለክ ነው፤ ሌላ ምንትርጉም ሊኖረው አይችልም።  እልል እየተባለ የሚሰገደው ለሚካኤል ታቦት አይደለምን? ሚካኤልን በአካል እንደ ዮሐንስ ቢገለጥልን በእውነቱ ዝቅ ብለን ተንበርክከን ልንቀበለው እንችላለን፣ ነገር ግን ታቦቱ የሚካኤል ነውና እንስገድለት የሚለው አስተሳሰብ ፍጹም ከሰማኒያ አንዱ መጻሕፍት ውጭ ነው።

ሌላ መልክአ ሚካኤል

ሰላም ለእመትከ ዘይሜጥን ተራድኦ፣
አኮ ሰንዱነ ወአልባሰ ረፍኦ፣
ሚካኤል ኀቤከ አወዩ በአስተቍዖ፣
ከመ ታድኅነኒ ሥመር እግዚኦ፣
እስመ ኩሉ ይትግህ ከመ ያድኅን ሰብኦ፤

ትርጉም

እርዳታን ለሚሰጥ ለክንድህ ሰላምታ አቀርባለሁ፣
የበፍታ ልብስም ሆነ የልብስ እራፊ አለምንህም፤
ሚካኤል ሆይ በምልጃ ወደ አንተ እጮሃለሁ፤
አቤቱ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤
ሰው ሁሉ ዘመዱን ለማዳን ይተጋልና፤

በቅዳሴያችን ሰዓት "ሥመር እግዚኦ ከመ ታድኅነነ ሥመር እግዚኦ ከመታድኅነነ አቤቱ ታድነን ዘንድ ውደድ አቤቱ ታድነን ዘንድ ውደድ እንላለን መባል የሚገባውም እንዲህ ነው። ደብተራዎች ግን ሚካኤልን "እግዚኦ አቤቱ ታድነን ዘንድ ውደድ ብለውታል። ደብተራዎች የጌታን ለሚካኤል ይሰጣሉ። ይህ ባዕድ አምልኮ አይደለምን? ይህ ባዕድ አምልኮ ያለፈ እና የተተወ ነገር ቢሆን ኖሮ ዝም ባልን ነበር፤ ነገር ግን ዛሬም የሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ባለበት እና በበአሉ ቀን የሚባለው እና የሚጸለየው ይህ ስለሆነ ምእመናንን ማንቃት ማስጠንቀቅ ግዴታ ሆኖብናል።
ለቤተ ክህነቱና ለጳጳሳቱ ስናቀርብ እባካችሁ ዝም በሉ ይህን ሕዝብ ታስገድሉናላችሁ ጊዜ ይፈታዋል ይሉናል። ማህበረ ቅዱሳንን ይህ መታረም አለበት ስንለው መናፍቅ ናችሁ እያለ ስማችንን ያጠፋል ከዚያም አልፎ በማጅራት መች ያስደበድበናል፣ በዚህ ምክንያት ስንት የቤተ ክርስቲያን ልጆች መከራና ችግር ደርሶባቸዋል! ይህ እልከኝነት ግን ችግር አይፈታምስሕተታችንን ብናርም ይሻላል እንጂ ስም ማጥፋቱና ማባረሩ አይበጅም።

ሰላም እብል ለመልክአቲከ ኩሎን፣
በበአስማቲሆን፣
ሚካኤል ሥርግው በልብሰ ብርሃን፣
ሠናይ ተአርኮትከ በኩሉ አዝማን፣
ሠራየ ኃጢአት አንተ አርከ ነፍስ መመን፤

ትርጉም

ለመልኮችህ በሙሉ በየስማቸው ሰላም እላለሁ፣
ሚካኤል ሆይ አንተ በብርሃን ልብስ የተሸለምክ ነህ፣
በዘመናት ሁሉ ያንተ ወዳጅንት መልካም ነው፣
የአማኝ ወዳጅህን ነፍስ ኃጢአት የምታስተሠርይ አንተ ነህና፤

ኃጢአትን የሚያስተሥርይ እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ኃጢአታችንን ያስተሠርይልናል። ደሙ ለዘላለም ሕያው ነው መለኮት ብቻውን የሚሠራውን የኃጢአት ሥርዬት ሥራ ከሚካኤል መለመን ምን የሚሉት ነው? ይህ ክህደት ከቤተ ክርስቲያናችን መነቀል አለበት ሚካኤልን እያመለኩ ሲያስመልኩ የኖሩ ሰዎች ፍርዳቸውን እንደሚያገኙ ባንጠራጠርም ዛሬ ግን በቃችሁ ሊባሉ ይገባል።

ሰላም እብል ለአክናፊከ ስፉሐት፤
ምስካቤ ኩሉ ፍጥረት፣ ሚካኤል ክቡር ሊቀ ካህናት፣
አድህነነ እምዕለት እኪት፣
ወባልሃነ እምኩሉ መንሱት፤

ትርጉም

ሰፋፊ ለሆኑ ክንፎችህ ሰላም እላለሁ፣
የፍጥረት ሁሉ መጠጊያ ናቸው፣
ሚካኤል ሆይ አንተ የከበርህ ሊቀ ካህናት ነህ፣
ክፉ ከሆነች ቀን አድነን፣
ከጥፋትም ሁሉ ታደገን፤

የፍጥረት ሁሉ መጠጊያ እግዚብሔር ነው ወይስ የሚካኤል ክንፍ? ሚካኤል የፍጥረት ሁሉ መጠጊያ ከሆነ አምላክ ሆኖአል ማለት ነው። ሁለት አምላክ የለም የፍጥረት ሁሉ መጠጊያ እግዚአብሔር ብቻ ነው "ነፍሳችን እግዚአብሔርን ተስፋ ታደርገዋለች ረዳታችንና መጠጊያችን እርሱ ነውና መዝ 3320 ተብሎ ተጽፏልና የእግዚአብሔርን ለሚካኤል አንሰጥም።

ሊቀ ካህናትስ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን? "በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናል የተባለለት ኢየሱስ ክርስቶስ የት ሄዶ ነው ሚካኤል ሊቀ ካህናት የሆነው? ወይስ የትኛውን መስዋእት አቅርቦ ይሆን? እራሱን ነውን? ወይስ እንስሳትን? መስዋእት ማቅረብ የሊቀ ካህናት ሥራ እንጂ የመላእክት አይደለም መላእክት ኃጢአት የለባቸውምና መስዋእት ማቅረብ አይጠበቅባቸውም ስለዚህ "ሊቀ ካህናት ካህነ ምስዋዑ የሚለው ጌታን ብቻ ይመለከታል፡

ከክፉ አድነን ብለን መጸለይም ወደ እግዚአብሔር ነው፣ ጌታ "ከክፉ ሁሉ አድነን ብላችሁ ጸልዩ ብሎ ሲያስተምረን ወደ ሚካኤል ነውን? ወይስ በሰማይ ወደሚኖረው አባታችን? ይህን ጥያቄ አንባቢ ይመልሰው።
ማህበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ሃያ አራት ሰዓት የሚጸልዩ አባቶች አሉን እያለ የሚመካባቸው ደብተራዎች የሚጸልዩት ጸሎት ይህን ይመስላል።
ይህን አባባል አሜን ብለን ብንቀበል እንኳ የሚጸለየው ጸሎት ግን ከላይ ያየነውን ስለሚመስል ዋጋ የለውም የእግዚአብሔርን ቁጣ የሚጋብዝ እንጂ ኢትዮጵያን ከድህነት፣ ከጦርነት፣ ከእርስ በእርስ ንትርክ፣ አውጥቶ ትውልዱን ከስደት የሚያሳርፍ ጸሎት አይደለም።

እንግዲህ በየወሩና በየአመቱ ሚካኤል ሲነግሥ ደብተራዎች ሲዘሉበት የሚያድሩት ማህሌት ከዚህ በላይ በጥቂቱ ያየነውን የሚመስል ነው።

 ውድ አንባብያን፥ ከዚህ በፊት እንደጠቆምኩት ከላይ ያየናቸው ሰይጣን በየጊዜው ያስገባብን የስህተት ትምህርትች የጥንታዊቷ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ አይደለም። ክቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም ከአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን አካባቢ ጀምሮ በነገስታቱ ጣልቃ ግብነትና ባልተማሩ ደብተሮች አማካኝነት ሰይጣን ቤተ ክርስቲያናችንን በክሎብናል። እነ አባሰላማ እና ሌሎች ጥንታውያን አባቶች የሰበኳት ክርስትና እንዲህ አይነት መላ ቅጡ የጠፋ ባዕድ አምልኮን ያዘለ አልነበረም።

በዲያቆን ሉሌ


27 comments:

 1. betikikl protestant nachihu

  ReplyDelete
 2. Gud bel Habesha

  ReplyDelete
 3. I think the veneration of the saints and angels may have gone beyond the limit at EOTC, but it is not fair to say that the angels cannot pray for us. Venerating the angels and the saints is normal among all ancient christian denominations; however, it appears it may have gone beyond that and approached "worship" in some circumstances.

  However, the pente teaching of angels is wrong at any rate. Yet the author has a point in the sense that some of the wordings in the melke may not be applicable to the angels. Nevertheless, praising the angels and praying to the angels are consistent with the bible. There is nothing wrong with that. The angels can pray for us as can the priests and any other christian brother do. The author seems to have adopted the pente doctrine on angels. God won't be jealous if we praise his servants. However, we have to be careful not to raise our praise to the extent of worship. We praise the saints or angels once in a while, but we worship God every day, all day, all the time, now, always and for ever, amen.

  ReplyDelete
 4. Also,

  (1) If you are willing to call priests and bishops as "Fathers," what is wrong with calling St. Michael as "Father"? After all, Michael is much closer to God than ordinary priests and bishops.

  (2) According to the Revealation, St. John the Appostle continued to kneel down infront of the angel despite the angel's advice not to do it. Do you think St. John committed a sin against God by continuing to bow for the angel?

  (3) In the liturgy, we always praise the saints and pray to them seeking their help and intercession. For example, we say "kidus hawaiyaw paulos senay melket fewesa duyan zenasayk aklele se'al wetseley benteane yadhin nefsatene bebzeha sahilu wemhiretu beentesemu kidus" after the epistel from Paul is read. This prayer is similar to the melka Michael. Is this also against the bible? If so, are you also asking the liturgy to be modified eliminating this and other similar prayers? If not, why not?

  (4) Do you know the other orthodox (eastern, coptic, syrian etc...) doctrine about angels? If so, is it different from the EOTC doctrine? If so, in what respect? If not, do you see merit for your crticism?

  I expect detailed answers for the foregoing questions from the author.

  ReplyDelete
 5. 1) father? Any biblical reference?
  2) Either the angel or St John is wrong, I believe St John has mistaken, for your info... saints sin too.
  3) if we are praying to St Pual, offcours it is a mistake, Even coptic & catholic churchs agrer that we should not pray to saints but only to our heavenly father
  4) they don't pray to angels ... google it

  ReplyDelete
 6. While I was accusing MK for being more traditional you (owners of the site) are also lost people who are propagating Protestantism in orthodox society. For sure we know there are some problems in the church but you are exaggerating them being mouth for protestants. Even if there is a problem in the church and you are orthodoxes, this is not the way to solve.
  If you are really looking for expansion of orthodoxy and correction of problems this is not the way. Work with Synods, and the responsible organ of the church will correct any problem in the church. Otherwise you are trying to divide the church and take flock to your masters.
  My comments the whole orthodox society
  1. We should preach Gods power and ability and his aim toward the people
  2. We should preach Jesus in modern and understandable way that he is lord, God and savior as it is being done in Ethiopia. Encourage young preachers.
  3. Keep faith on Mary, Angles and other saints as usual and venerate them as in orthodox church. This is the faith of the early Christians and even biblically true if studied properly
  4. Correct some awaledi metsahift which are having problems. Those which are exaggerating veneration.
  5. Remove some people like MK who are strictly very traditional even who don’t want to call Jesus’s name and these Tehadiso’s who don’t respect the church and who don’t believe in orthodox church’s teachings
  6. Have faith in God and pray for Synod to give time to such things and solve in a wise way

  Once again I want to say that Tehadisos are people who are non-orthodoxs ( protestants) but don’t want to change the church they are going. They want the orthodox church to be their wish. MK’s exaggerated the Gedils and want to undermine Jesus’s role in the Christians life and on the church.

  ReplyDelete
 7. ተሾመ ዘተዋህዶJune 18, 2011 at 5:54 PM

  ከሚካኤል በቀር የሚያፅናናኝ የለም።ዳን 10;21
  የእግዚአብሄር መልዐክ በሚፈሩትሰዎች ዘሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል።መዝ 33፡7
  ቅዱስ መልአክ ደአንኤልን እንዳስተማረው ጥበብና ማስተዋል እንደሰጠው ዳን 9;21-23
  በአጠቃላይ እነዚህን የመሳሰሉትን ምን ልትላቸው ነው፡፡ ሉሌ መጀመሪያ መጽሀፍ ቅዱስን አንብብ፡ አባቶችንም ጠይቅ፡;ለመሆኑ ደብተራ ማለት ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ራሱን ከፍ ከፍ ያደረገው ዲያቢሎስን መሰልክ!
  ቅዱስ ሚካኤል ከእገዚአብሄር በተሰጠው ጸጋ ያድንማል ከተባለ በጸጋ አባቴ፡ጸሎቴን የሚያደሚጠኝ;የሚሰማኝ ነው ብዬ ማመኔ ምኑ ላይ ነው ስሀተቱ። እንደኔ አንተ እየተቃወምህ ያለሀው መጽሀፍ ቅዱስን እንጅ ድርሳነ ሚካኤልን እንዳልሆነ ላስረግጥልህ እወዳለሁ፡፡እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ቀእዱሳን መላዐእክት ተራዳይ;አማላጅ እንደሆኑ እናምናለን እንጂ ፈጣሪ አምላክ ነአቸው አላልንም።ያልተባለውን;የማናምነውን ያልተደረገን አትጻፍ።ስለማታውቀው መስሎህ ካልሆነ።ለመሆኑ ሀዋርያት በአስራሁለቱ የእስራአል ዙፋን ተቀምጠው እንደሚፈርዱ በመጽሀፍ ቅዱስ የተጻፈው እንደ አንተ አባባል ስህተት ስለሆነ ይታረም?ለነገሩ የምታነበው መጽሀፍ ቅዱስ ላይኖረው ይችል ይሆናል ተደልዞ ስለሚሆን....ልቦና ይስጠን!!!

  ReplyDelete
 8. Instead of accusing the doctrine of our church and Mahiber kidusan, why don't u teach ur doctrine well for your followers. Tirefu melalat new enji ayisakalachihum.

  ReplyDelete
 9. On #3 - "pray to them" but the eastern, coptic, syrian, the catholic etc... will say that is wrong. We don't pray to them. We only pray to God but we pray with the saints. google it...

  ReplyDelete
 10. የተምታታበት ምእመን
  ለተጠረበው እንጨት በፊቱ ወድቀው የሰገዱ ሚካኤልን በአካል ቢያገኙማ የጉድ ነው
  የግምት መመዝሙራቸው እንዲህ ይላል
  በአምሳለ እርግብ ወረደ መልአክ ወረደ 2
  ወረደ ወረደ 2 ሚካዔል መላክ ወረደ
  ጌታ ሲጠመቅ መንፈስ ቅዱስ እንጂ ሚካዔል አለመሆኑን ወንጌል ይነግረናል እነ ልበ ደንዳኖች ግን ሚካዔል መንፈስቅዱስ ነው እያሉ ሲያዘሙ በ እውነት ያሳፍራሉ

  ReplyDelete
 11. Anonymous said... @June 18, 2011 12:00 PM

  You are simply a very uninformed guy. You are trying to deny what I know well. You responses are as shallow and tainted as your knowledge of the bible and the different christian faiths around the world.

  I suggest that you read more and inform yourself better. If you crave much for pente faith, the door is open for you and you don't have to bother us here. Go practice your new found faith with your likes. We don't need to to incorporate a pente doctrine to know Christ and serve Him better. We don't need to lie to make our points as well. It is sad that some evil people are taking advantage of the ignorance of many innocent people.

  ReplyDelete
 12. Well angel's help and protect us. Daniel was not praying to the angle, he was praying to God and God sent the angel. That is all.

  ReplyDelete
 13. the syrians, coptic, armenian, indian, ethiopian with eritrean are all the same orthodox groups. We all pray to saints, angles, apostles and the mother of god virgin Mary. The coptics even take st. Teklehaymanot as a saint and they have made many churches in his name and pray to him for his blessing.

  ReplyDelete
 14. እረ ክርስቲያኖች መጀመሪያ አባቶቻችንን እንጠይቅ!!! እምነቱን ስርዓቱን ትውፊቱን ያስረዱናል እኮ:: እኛ ዝም ብለን ላይ ላዩን እያነበብን እንደመሰለን የምንተረጉም ከሆነማ ኦርቶዶክሶች መሆናችንን ጥያቄ ውስጥ ያስገባል::

  በአምሳለ እርግብ ወርደ መልአክ ወረደ የምንለው እኮ መንፈስ ቅዱስን ለማለት አይደለም::

  ቁራው ከኖህ ተልኮ በዛው ሲቀር እርግብ ግን የምስራች ያመጣች ናት::
  ሚካኤልም ለኛ ለሰው ልጆች የምስራች ነጋሪያችን ነው ለማለት ይመስለኛል:: እኔ እንኳን በጠባቧ አእምሮዬ ሳስበው::

  የኛ ችግር እኮ የእውቀት ሳይሆን ያለመጠየቅ ይመስለኛል:: እኔም እናንተም እንጠይቅ እንማር:: አንድን ነገር ባለማወቅ ከመንቀፋችን በፊት::

  የጥበብ አምላክ ጥበቡን ይግለጽልን!!! አሜን!!!

  ReplyDelete
 15. “በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወደአዘጋጀሁት ስፍራም ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ። በፊቱ ተጠንቀቁ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሰሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት። “ ዘጸአት ምዕራፍ 23 ከቁጥር 20 ጀምሮ
  ይህም ከምጽሃፍ ቅዱስ ውጭ ነው????? እስቲ ደጋግመህ አንብበው::አታስቆጡት አይምርም ይቀጣል እኮ ነው ያለው::ምን ያህል ስልጣን እንዳለውሃ የህ???

  ReplyDelete
 16. Tebebene yegltselehe ! yekere yeblehe .

  ReplyDelete
 17. ሲጀመር ጻድቃኑን ማናናቅ እና ተጋድሏቸውን ማንቋቋሸሽ ተጀመረ ቀጠለና እርሱ እራሱ የመረጣትንና ለእናትነት ያዘጋጃትን በማጣጣል ቀጠለና ከዛ ደግሞ መላእኩ ላይ ተደርሷል:: ከዚያስ ወደት ይሆን የምታመሩት? እናንተ ታውቁታላችሁ:: አውሮጳውያን መጀመሪያ ላይ እንድህ ነበሩ መጨረሻቸው ግን በመስቀል ተሰቅሎ በሞቱ እኛን ከዘላለማዊው ሞት ወደዳግም ህይዎት ያመጣንን እርሱን ጌታችን መድኃኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክደውት የፈላስፎች መጫወቻ ሁነዋል:: የናንተም አካሄድ ወደዛው ነው:: ሲሆን ከታሪክ መማር ትችሉ ነበር ነገርግን አልፈለጋችሁም:: የፍናፍንት ቄስና ጳጳስ መሆን የተጀመረውም የናንተን አይነት ትርጉም ለኃይማኖት ያደርጉ ከነበሩት ነው:: እርግጥ አሁን በዘመን ብዛት ስማቸው ብዙ ቢሆንም ምንጩ ሉተር ነው:: ጻድቃኑን የምትጠሉ ከሆነ ጽድቅን እንደምትቃወሙ አታውቁምን፣ እናቱን ማጥላላቱና ንጽህናዋን ማንቋሸሹ በመወለዱ ላይ ጥርጥር እናዳላችሁ አይመሰክርባችሁም:: መላእኩን ማራከሳችሁስ እርሱ በመላእክት ያላቋረጠ ምሥጋና የሚመሰገነውን በመመስገኑ ምስጉን በመሆኑ የቀናችሁ አያስመስልባችሁም:: ለነገሩ ጻድቃኑን ከጽድቅ ስራቸው ሊያሰንክል ይታገላቸው የነበረው ሰይጣን የነሱ ስራ ጽድቅ ሁኖ ከተቆጠረ በኋላ ዓለም ስለጽድቅ አውቆ ለጽድቅ እንዳይበቃ እየታገለ እንደሆነ ይገባናል:: ጻድቃኑማ ከስራቸው የተነሳ ከብረዋል የነሱን ፈለግ ተከትለን በእምነት በጎውን ነገር ሁሉ አድርገን የተስፋ መንግስተ ሰማያት ቪዛ እንዳናዘጋጅ የተደቀነው መሰናክል የተወጠረው መናፍቃኑን መሰረት አድርጎ ነውና ገብቶናል::

  ReplyDelete
 18. መጀመሪያ ደረጃ ጹሁፍ መጻፍ ጥሩ ነው።እስኪ ሌሎች ደግሞ መልሳችሁን ጻፍና እናብብ።ከዚያም ለምርጫ ይመቸናል።

  አባት አባት ለመትሉ ደግሞ የትኛውን አባት ነው የምትሉት ?? የትኛውን ጳጳስ እንጠይቅ ??? የሚጠየቁት ጳጳሥ ይህን ጽሁፍ እውነት ነው ቢሉ ልንቀበላቸው ነው ወይስ ያው እንደተለመደው መናፍቅ ብለን ልንሰድባቸው ??በአሁን ሠዓት ቤተክርስትያኗ አባት የላትም።አባት ቢኖራት ኑሮ እንዲህ ዓይነት ንትርክ ውስጥ ባልገባን ነበር።

  ለማንኛውም ይህን ጽሁፍ የምትቃወሙ አብራርታችሁ ለመጻፍ ሞክሩና እንማርበት።
  ከምስጋና ጋር

  ReplyDelete
 19. Yes I think we can call it protest-O. AKA protesto

  The pentes are Protest-C for protesting wrong Cahatolic teachings and ours is Protest-O for protesing wrong Orthodox teaching.

  F

  ReplyDelete
 20. Protest means rebellion against something or someone. Why would not protestants focus of the good news of the Gospel and try to reach the corners of the wolrd where Christianity has not reached yet?

  Why don't you protest other non-Christian faiths? Why don't you go to the mosques and tell the muslims to accept Christ as their personal savior and reform their faith? The EOTC is firmly founded on Christ. Any reform we need, we will do it ourselves.

  Protestants ( or protestasnt leaning reformers) who are engaged in undermining the EOTC should know that yoou are not serving God by engaging in these behaviors. Also, you are creating a precdence by wrongly interfering in the affairs of another church. You can even be prosecuted ( I mean when the rule of law prevails in the country) as your behaviors and actions are tantamount to a crime. We have seen blood shed in some places because of squabbles between protestant reformers and anti-reformers. Why go to this lelvel while you can worship the way you choose at your protestant halls? Again, your time will be well spent if you reach out to non-christian communities and bring them to Christ, instead of interfering in the internal affairs of another church.

  If your interference cannot stop, it could become a national security concern in the future and the EOTC people could raise arms against you. No one wants to see that. Muslim militants have been attacking our church for many years now; protestants have joined the muslim militants and are now assailing the EOTC inside and out. Please stop this animosity and focus on serving the Lord. Humility and respect for others are some of the ways you can serve the Lord. You can be whatever you want to be, but don't tell me what to be and what not to be. Your attempt to reform EOTC in a protestant way could fire back and eat you up. We are Orthodox and you are protestant. It is not in the Orthodox tradition to go around and sabbotage other religions. However, it is interesting to note that your attempt to sabbotage our church has even further strengthened the church. Perhaps, aggressive protestants are to Orthodox as satan was to St. Paul. Again, we, the Othodox followers, will clean up our church if there is any dust; we don't need any help from folks who don't share our faith. You better pluck out the long stick in your own eyes.


  The above rebuke only applies to those aggressive protestants who are attempting to reform our church their way and are planting people here and there and financing reform operations across the country. Otherwise, the ordinary meek protestant followers are our brothers and sisters. We don't have anything against them.

  ReplyDelete
 21. Aye Nathan, you are cool. You are not that far from the kingdom. Few questions

  Are you born again?

  "I tell you the truth, no one can see the kingdom of God unless he is born again" John 3:16


  Do you have the witness of the Holy Spirit that you are saved?

  "The Spirit himself testifies with our spirit" Romans 8:16

  Do you know for sure that you have eternal life?

  "I write these things to you who believe in the name of the Son of God so that you may know that you have eternal life." 1 john 5:13


  Hope you seriously think of these. We can discussed it if you wish.

  ReplyDelete
 22. coptic chuch do not pray to saints  Coptic Forums
  The official forums of the Coptic Media Network, focusing on Coptic hymns, Orthodoxy, spirituality, friendship, and member experiences.
  We do not pray to the saints. We pray to God only, and at the same time ask the saints to pray to God for us
  Bishoy is right. We pray to God only, however we ask the saints to intercede for us

  ReplyDelete
 23. ለቅዱስ ሚካኤል ምስጋና ይግብው አሜን!! አዋ በምልጃው በጥበቃው በበረከቱ የምናምን እኛ ዛሬም ነገም እናመሰግነዋለን:: አልተሳሳትንምም!!! ኦርቶዶክስ ሳትሆኑ ውስጥ ለውስጥ በመሆን የበግ ለምድ ለብሳችሁ ላማሳሳት አትሞክሩ:: እውነቱ ከፍሬያችሁ ያስታውቃል:: ሴጣንን ከገነት አዋርዶ ላስወጣው ምስጋና አይገባም ነው የምትሉት? "እንሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ ትንቢተ ዳንኤል ምአራፍ 10 ቁጥር 13" እንደሚረዳ ተመስክሮዋል:: የምታመልከውን ጠንቅቃ የምታውቅ ሃይማኖት ናት ይሔ ሁሉ የተሃድሶ(የሴጣን) ስራ ነው:: ጆሮ ያለው ይስማ አይን ያለውም ይመልከት እውነቱ አይናችን ስር ነው በተኩላዎች አትሳሳቱ:: ሚካኤል ማለት እራሱ እኮ ማን እንደ እግዚአብሔር ማለት ነው:: መጽሃፍ ቅዱስ እንዳስተማረን ምስጋና ለሚገባቸው ሁሉ ምስጋና እናቀርባለን:: ሃጥያተኞች ነንና ከአምላካችን አስታርቁን ብለን እንለምናቸዋለን::አምላካችን እግዚአብሔርን እናመልካለን:: ኦርቶዶክስ ነን ካላችሁ ይሔ በገባችሁ ነበር:: ኢትዮጵያ ከአባ ሰላማ በፊት በጀንደረባው ጊዜ ነው ክርስትናን የተቀበለችው ከዛም ጊዜ ጀምሮ ሳትለወጥ ብዙን ፈተና አልፋ እስከዛሬ ትገኛለች:: መቼም አትለወጥም:: ከናንተ የባሰ ስንቱን አልፋ ዛሬም ቆማለች:: ክርስቶስ በደሙ የዋጃትን የናንት ርካሽ መንፈስ አያፈርሰውምና አትልፉ ይልቁኑ ንሰሃ ገብታችሁ በቆፈራችሁት ሳትገቡ ተመለሱ:: የናቃችሁት ሚካኤል ያደረባችሁን መንፈስ አሳፍሮ እውነቱን ይግለጽላችሁ አሜን!!!!

  ReplyDelete
 24. ከሚካኤል በቀር የሚያፅናናኝ የለም።ዳን 10;21
  የእግዚአብሄር መልዐክ በሚፈሩትሰዎች ዘሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል።መዝ 33፡7
  ቅዱስ መልአክ ደአንኤልን እንዳስተማረው ጥበብና ማስተዋል እንደሰጠው ዳን 9;21-23
  በአጠቃላይ እነዚህን የመሳሰሉትን ምን ልትላቸው ነው፡፡ ሉሌ መጀመሪያ መጽሀፍ ቅዱስን አንብብ፡ አባቶችንም ጠይቅ፡;ለመሆኑ ደብተራ ማለት ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ራሱን ከፍ ከፍ ያደረገው ዲያቢሎስን መሰልክ!
  ቅዱስ ሚካኤል ከእገዚአብሄር በተሰጠው ጸጋ ያድንማል ከተባለ በጸጋ አባቴ፡ጸሎቴን የሚያደሚጠኝ;የሚሰማኝ ነው ብዬ ማመኔ ምኑ ላይ ነው ስሀተቱ። እንደኔ አንተ እየተቃወምህ ያለሀው መጽሀፍ ቅዱስን እንጅ ድርሳነ ሚካኤልን እንዳልሆነ ላስረግጥልህ እወዳለሁ፡፡እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ቀእዱሳን መላዐእክት ተራዳይ;አማላጅ እንደሆኑ እናምናለን እንጂ ፈጣሪ አምላክ ነአቸው አላልንም።ያልተባለውን;የማናምነውን ያልተደረገን አትጻፍ።ስለማታውቀው መስሎህ ካልሆነ።ለመሆኑ ሀዋርያት በአስራሁለቱ የእስራአል ዙፋን ተቀምጠው እንደሚፈርዱ በመጽሀፍ ቅዱስ የተጻፈው እንደ አንተ አባባል ስህተት ስለሆነ ይታረም?ለነገሩ የምታነበው መጽሀፍ ቅዱስ ላይኖረው ይችል ይሆናል ተደልዞ ስለሚሆን....ልቦና ይስጠን!!! GIN EKO ABA SELAMA, ANTEM ENKUAN "ABA=ABAT" TEBILEHAL ENKUAN MIKAEL.

  ReplyDelete
 25. kewanegnochu aleqoch andu MICHAEL liredagn meta.

  ReplyDelete
 26. Please read this bible verses to stop worship angles:
  Colossians 2: 17-18

  ReplyDelete