Friday, July 29, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን የሃይማኖት ወይስ የስለላ ድርጅት? - - - Read PDF

ብዙዎች ለኦርቶዶክሳዊት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ቅርብ የሆኑ እንደሚያውቁት ማህበረ ቅዱሳን የተባለው ማህበር ከምድር ተነሥቶ ስም ያጠፋል፣ በሰው ነገር እየገባ እርስ በርስ ያጋጫል፣ ይደበድባል፣ ካስፈለገም ይገላል ለዚህ ሁሉ በመቶ የሚቆጠር ማስረጃ አለን። አሁን እጅግ የከፋውና በጣም አሳሳቢ የሚሆነው ፐርሰናል የሆኑ ጉዳዮችን ወደ አደባባይ ማውጣቱ፣ የግለሰብን ሕይወት ከትውልድ እስከ ዘር ማንዘር አስተሳሰቡና ጠቅላላ ሕይወቱ እየተሰለለ ለማን እንደሚሰጥ በማይታወቅበት ሁኔታ ለአደጋ መጋለጡ ነው።
ይህ መንፈሳዊ ነኝ ብሎ እየተንቀሳቀሰ ያለ ድርጅት በስለላ ሥራ ብቻ እንደተሰማራ የራሱን አባላት እንኳ እንደሚሰልል ዲያቆን ዳንኤል አጋልጧል። መንግሥት የግለሰብን ሕይወት ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ማህበሩ እንዲሰልል ፈቅዶለት እንደሆነ አናውቅም፣ ነገር ግን የግለሰቦችን ሕይወት በምሥጢር እየሰለለ እንደሚሰበስብ ካገኘናቸው በርካታ መረጃዎች ውስጥ አንዱን ከዚህ በታች ባለው ደብዳቤ ይመልከቱ ። (ሰነዱን ለማንበብ እንዲችሉ ርዕሱ ላይ ተጭነው PDF ይክፈቱ)

የመንግሥት ያለህ?
የሀገራችን ሕገ መንግስ ይህንን ጉዳይ እንዴት እያየው ይሆን? ሕገ መንግሥት የዜጎችን መብት ለማስጠበቅና የሕዝቦችን ደህንነት ለማረጋገጥ በሕዝብ የጸደቀ የሀገር ሰነድ ነው። ይህን ሕገ መንግሥት ለማስፈጸም የሚሠሩ ሕዝብ ይሹማቸው ወይም በጉልበት ይሾሙ ከላይ እስከ ታች ባለ ሥልጣኖች አሉ። ታዲያ እንደዚህ አይነት ዓይን ያወጣ ወንጀል በምድሪቱ የተፈቀደ ነውን?  በአደጉ አገሮች እንኳንና እንደ ማህበረ ቅዱሳን አይነቱ ማህበር ይቅርና መንግስት ራሱ ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍቃድ አስፈቅዶ፤ ምክንያትን አብራርቶ ነው ዜጎቻቸው ላይ ስላለ ማካሄድ የሚችሉት። ያውም ከባድ ወንጀል እየሰራ እንደሆነ ከታመነበት።

Tuesday, July 26, 2011

ማህበረ ቅዱሳንን ለመምራት የሚሞክር ሥውር አመራር አለ። (ዲ. ዳንኤል ክብረት) - - - Read PDF

 
ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ጽሑፍ በደጀ ሰላም ከወጣ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ጽሑፉ ተነሥቷል። ጽሑፉ ብዙ ቁምነገሮችን ያዘለ ስለሆነ አባሰላማ ላይ እንዲወጣ ተደርጓል።   ዲ. ዳንኤል ከጠቆማቸው ሀሳቦች መካከል ጥቂቶቹ፦
. ከአመራርነት እራሴን ያገለልኩት መምህር ሙሉጌታ እንዳለው በልማት ሥራዎች ላይ ተመድቤ ስሠራ በተፈጠረ ድክመት አይደለም በእኔና በአመራሩ መካከል የአመለካከት ልዩነት ስለተፈጠረ፣ ይህንንም ልዩነት ተነጋግሮ ለመግባባት አመራሩ እምቢ ስላለ ነው።
. የማህበሩ አመራር የዕለት ተእለት ነገሮችን ለማየት የሚሰበሰብ ስለቤተ ክርስቲያኒቱም በቂ መረጃ የሌለው ነው።
. የማህበሩ ጉዞ ቤ/ክርስቲያኒቱን የት ለማድረስ እንደሆነ ግልጽ ግብ የለውም።
. ማህበሩ ሥራውን ትቶ የገዛ አባላቱን እስከ መሰለል ደርሷል።
. በማህበሩ የግል ጋዜጦችን ማንበብ የተከለከለ ነው።
. ተሃድሶን ለማጋለጥ እንጂ ተሃድሶን ያመጣውን መሠረታዊ ችግር ለመፍታት ያስቀመጠው ስትራቴጂ የለም።
. አመራሩ ማህበሩ ለቤ/ክርስቲያኒቱ የተመሠረተ መሆኑን ዘንግቷል አሁን ቤ/ክርስቲያኒቱ ለማህበሩ ወደሚል አመለካከት ዞሯል።
. በጋሻውን የሚከሰው ማህበሩን ስለነካው እንጂ ለቤ/ ክርስቲያን አደጋ ነው ብሎ ስላሰበ አይደለም።
. አባ ሠረቀንም ቢሆን በእምነት ችገር ይከሳቸዋል እንጂ ከርሳቸው ጋር ያለው ችግር ማህበሩን መንካታቸው ነው አባ ሠረቀ ማህበሩን ሳይነኩ የፈለጉትን ቢሆኑ ኖሮ አይነገራቸውም ነበር።
በቀጥታ ደጀ ሰላም ያወጣውን ሙሉውን ጽሑፍ ከዚህ ቀጥለው ያንብቡ።

ጥናቱ የማኅበረ ቅዱሳን ወይስ የቤተ ክርስቲያኒቱ? - - - Read PDF

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የራሷ የሆነ ዐቋም ያላትና ዐቋሟን የምትገልጸውም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ወይም እንደ ዜና ቤተክርስቲያን ባሉ ልሳኖቿ በኩል እንደ ሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ውጪ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል የሆነ አንድ ግለሰብ ወይም ለተለያየ ዐላማ ተሰባስቦ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥር ለመንቀሳቀስ ፈቃድ የተሰጠው አንድ ማኅበር ጽፎ ያሳተመውና ያሠራጨው የኅትመት ውጤት የቤተ ክርስቲያኒቱ ልሳን ተብሎ ለመጠራት ሕጋዊ መሠረት አለው ማለት ያስቸግራል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ሕጋዊ አሠራር ብዙ ጊዜ ሲጠበቅ አይታይም፡፡ ብዙው ሰው ከግንዛቤ ማነስ የተነሣ ወይም በቅንነት እንዲህ ያለ ጥያቄ አለማንሣቱ አይገርምም፡፡ መገናኛ ብዙኃን ይህን ልዩነት መለየት ተስኗቸው መታየቱ ግን ከማስተዛዘቡም በላይ፥ ጠያቂ አካል ቢነሣ ተጠያቂነትን ሊያስከትል እንደሚችል ጥርጥር የለውም፡፡

Sunday, July 24, 2011

ዜና - ማሕበረ ቅዱሳን በአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ስም ለአመጽ እየተዘጋጀ ነው . . . Read PDF

የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ‹‹እስከ መሥዋዕትነት ድረስ›› ተዘጋጅተናል ሲሉ ሀገረ ስብከቱን አስጠነቀቁ

በኢቤኤስ ቻናል የሚተላለፈውን ፕሮግራም አውግዘናል
የአዲስ አበባ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ሠራተኞችም ደሞዛቸውን ለአክሱም ሙዚየም ግንባታ ሰጡ መባላቸው ቅሬታ ፈጥሯል

ሰኞ በ11/2ዐዐ3 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ‹‹የወቅቱን የተሀድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴና ተዛማጅ ችግሮችን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በጋራ የተሰጠ የአቋም መግለጫ›› በሚል ርእስ ስር ባወጡት መግለጫ ላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህር ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ኃላፊውን አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤልን፣ በኢቢኤስ ቻናል ታኦሎጐስ በሚል ስም በተሰየመው የአየር ሰዓት የሚተላለፈውን ፕሮግራም አባ ሰላማ፣ ደጀ ሰማይ እና ኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ዶት ኦርግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን የማይወክሉ በመሆናቸው እንቃወማቸዋለን ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡

በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ላይ መዋሸት ይቁም! ... ክፍል 4 - - - Read PDF

በሰማይና በምድር የማርያምን ስም የጠራ ሁሉ ይድናል (ታምረ ማርያም 12፥43-53)

የእግዚአብሔርን ስም የጠራ ሁሉ ይድናል (መጽሐፍ ቅዱስ ሮሜ 10፥13)
እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው ተብሎ እንደተጻፈ (ሮሜ 10፥17) ማንኛውም ሐሳብና ሃይማኖት መመርመርና መገምገም ያለበት በእግዚአብሔር ቃል ነው። አባቶቻችን ሐዋርያት ከመንፈስ ቅዱስ የሰሙትን ለዓለም ሁሉ በአስተላለፉበት መልእክታቸው አንድ ተስፋ፣ አንድ መንፈስ፣ አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ጥምቀት ብቻ እንዳለ ነው። ይህም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ሞትና ትንሣኤ የተመሰረተው የሰው ልጆች ሁሉ የመዳኛ መንገድ ነው።

Friday, July 15, 2011

የቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነት (ዶግማ) - ክፍል 5 - - - Read PDF

ኢየሱስ ክርስቶስ የዐዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት

እግዚአብሔር በቅዱስ ቃሉ ውስጥ እንደገለጸው ለዐዲስ ኪዳን ጥላና ምሳሌ ሆኖ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሕዝቡን ሲያስተዳድርና ሲመራ የኖረው በሕዝቡና በእርሱ መካከል መካከለኛ አድርጎ ባቆማቸው ተቀብተው በተሾሙ ካህናት፥ ነቢያትና ነገሥታት አማካኝነት ነበር። በዐዲስ ኪዳን ግን  ለተለያዩ ነገዶችና ግለሰቦች ተሰጥተው የነበሩትን እነዚህን ሦስቱን ሹመቶች ሊቀ ካህንነትን፥ ነቢይነትንና ንጉሥነትን ሰው ሆኖ የተገለጸው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠቅልሎ ይዟቸዋል።

Monday, July 11, 2011

በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ላይ መዋሸት ይቁም! ክፍል 3 --- Read PDF

«ምሥጋናየን የጻፈ በምከበርበት ቀን ስሜን ያመሰገነ»
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታን በጸነሰችበት ጊዜ «ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል» ብላለች። እግዚአብሔር ያከበራት በፊቱ ሞገስ ያገኘች በመሆኗ እጅግ ደስ ብሏታል መልአኩም ደስ ይበልሽ ነው ያላት፤ ይህን የድንግል ማርያም ደስታ እኛም ልጆቿ የምንካፈለው ደስታ ነው፤ ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይሉኛል አለች። አዎ እውነት ነው።  ድንግል ማርያም በጌታ ፊት ሞገስ አግኝታለች፤ አካላዊ ቃልን እሳታዊ መለኮትን ለመውለድ የተመረጠች በመሆኗ ከዚህም በላይ ትሕትናዋ ቅድስናዋ ርኅሩህነቷ ታግሽነቷ ወዘተ ብጽእት ያስኛታል። እኛም ልጆቿ ድንግል ማርያምን እናከብራታለን፣ እንወዳታለን፤ ብጽእት እንላታለን በእምነቷም እና በመታዘዟ ምሳሌያችን ናትና እጅግ እናደንቃታለን አሜን።

Friday, July 8, 2011

የቤተ ክርስቲያናችን መሠረተ እምነት (ዶግማ) ክፍል 4 - - READ PDF አምላክ ለምን ሰው ሆነ?

አምላክ ለምን ሰው ሆነ?
ይህን ጥያቄ በአግባቡ መመለስ ከቻልን  የመዳናችን መንገድ ሊጠፋን ከቶ አይችልም። አሊያ «አምላክነቱ እንዳይዋረድ» በሚል ሽፋን ልብ ያላልነውን የትሥጉቱን ምስጢር የአምላክነቱን ያህል ልንረዳው ሳንችል ብንቀር ከአምላክነቱ ጋር በተዋሐደው ትሥጉቱ የምናገኘውን ድኅነት ማስተዋል  አንችልም።

የቤተ ክርስቲያናችን መሠረተ እምነት (ዶግማ) - ክፍል 2 - - Read PDF

የስህተት ትምህርትን በስፋት ይዘው ከሚያራግቡት መካከል ፈሊጠኞች የሆኑት ደግሞ በጊዜው በለስ ቀንቶት ተቀባይ ያገኘው አስተምህሮአቸው የእውነትን ካባ ካልደረበ በቀር ወደፊት ዕርቃኑን እንደሚቀር ቀድመው ስለተረዱ ስሕተታቸውን ይዘው ወደ እውነት መጠጋትን እንደ አማራጭ በመውሰድ ከጸሎተ ሃይማኖትም ሆነ ከስድስቱ የቤተ ክርስቲያን ዶግማዎች ላይ ቅርጫፍ አበጅተው ኑፋቄአቸውን በማዳቀል ከእውነት ግንድ የወጣ ቅርንጫፍ ለማስመሰል ቢደክሙም የነርሱ ቅርንጫፍ ተቀጽላ እንጂ የግንዱ ትክክለኛ ቅርንጫፍ አለመሆኑን መንፈሳዊ ዐይኑ የበራለት ሁሉ ይለየዋል።

Wednesday, July 6, 2011

በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ላይ መዋሸት ይቁም! ክፍል 2- - READ PDF

ቤተ ክርስቲያን በስሜ የሚሠራ 
«እኔም እልሃለሁ አንተ ጴጥሮስ ነህ በዚህችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ የገሃነም ደጆች አይችሏትም» ማቴ 16፥18። ቤተ ክርስቲያን ማለት «የክርስቲያን ወገን» ማለት ሲሆን ምሥጢሩ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የተመሠረተ የሕዝብ ሕብረትን፣ አንድነትን መንፈሳዊ ጉባኤን ያመለክታል።

Friday, July 1, 2011

የቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነት (ዶግማ) - ክፍል 3 የኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት --- Read PDF

ለብዙዎች መሳሳት አንደዋነኛ ምክንያት የሚቀርበው የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነት ጠንቅቆ አለመረዳት ነው።
Note: Parts 1 and 2 were posted on May 8 and 11.
 You can go back and review.

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ታላቅ ስፍራ ይሰጠዋል። የዘመን መቀዳደምና የክብር መበላለጥ በሌለበት በክበበ ሥላሴ ከሚገኙት ሦስት አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ቤተ ክርስቲያን የምታምነው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስትምህሮዋ ነው። (ዮሐ 1፥14፤ የሐዋ ሥራ 20፦28፤ ሮሜ 5፥9፤ ቲቶ 2፥13፤ 2ጴጥ 1፥1፤ 1ዮሐ 5፥20)