Wednesday, July 6, 2011

በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ላይ መዋሸት ይቁም! ክፍል 2- - READ PDF

ቤተ ክርስቲያን በስሜ የሚሠራ 
«እኔም እልሃለሁ አንተ ጴጥሮስ ነህ በዚህችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ የገሃነም ደጆች አይችሏትም» ማቴ 16፥18። ቤተ ክርስቲያን ማለት «የክርስቲያን ወገን» ማለት ሲሆን ምሥጢሩ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የተመሠረተ የሕዝብ ሕብረትን፣ አንድነትን መንፈሳዊ ጉባኤን ያመለክታል።
ሦስት መቶ አሥራ ስምንት የሚያህሉ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጥንታዊ አባቶች  ስለ ቤተ ክርስቲያን በተናገሩበት አንቀጽ እንዲህ ሲሉ መስክረዋል «ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላእለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት»
ትርጉም «ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን»  
ቤ/ክርስቲያን ሐዋርያት የሰበሰቧት የክርስቶስ አካል እንጂ በጭቃና በደንጋይ የተሠራ ሕንጻ አለመሆኗን የእግዚአብሔር ቃል የሚያስተምረው እና የጥንታውያን አባቶቻችን እምነት ነው። ቤ/ክርስቲያን ከነገድ ከቋንቋና ከሕዝብ በደሙ የተዋጁ ምእመናን ጉባኤ የክርስቶስ መንፈሳዊ አካል ናት  «ከሁሉ በላይም እራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው እርሷም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት» ኤፌ 1፥22። ድንግል ማርያም የምታውቀው ይህችን የክርስቶስ አካል የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ነው። ጸጋን የተሞላችው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የምትመራው እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የቤተ ክርስቲያንን ትርጉም ከነምሥጢሩ ታውቃለች። ድንግል ምርያም ስሟ የሚጠራው እና እየተጠራ ያለው መለኮታዊውን አካል በማሕጸኗ ለዘጠኝ ወር ተሸክማ ወልዳ አሳዳጋ ከእግዚአብሔር በተሰጣት ጸጋ እግዚአብሔርን መታዘዟ ነው። ከዚህ በላይ ስሟን የሚያስጠራ ምንም ነገር የለም። ከሞቱ በኋላ ስማቸው እንዲጠራላቸው የተለያየ ሐውልት የሚያሠሩ፣ ልዩ ልዩ ሥራዎችን በመሥራት የሚደክሙ ሥጋውያን ናቸው፤ ቅድስት እናታችን ግን ስለስሟ መጠራት አስባም ሆነ ለምና አታውቅም እርሷ እጅግ በጣም ትሑት ናት።  
ነገር ግን ሰዎች ለድንግል ማርያም ካላቸው ፍቅር ተነሥተው አንድን ሕንጻ [የጸሎት ቤት] በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በቅዱሳን፣ ሐዋርያት ስም ለመታሰቢያ መሥራታቸው ነውር ነው ብለን አናምንም። የቅዱሳንን እምነታቸውን፣ በእምነታቸው በመጽናት የፈጸሙትን ገድል ለማስታዎስ ይረዳናል።   «በስሜ ቤተ ክርስቲያን ይሠራ ብላ ለምናለች» የሚለው የፈጠራ ድርሰት ግን ውሸትና ስድብ ነው።
በቅዱሳን ስም ሕንጻን መሰየም ዋጋ ያሰጣል የሚባለውም የስሕተት ትምህርት ነው ነው። ምክንያቱም ዋጋ የሚያስጠን ሕንጻውን መሥራታችን እንጂ የሕንጻው ስያሜ አይደለም። ሕንጻን መሥራት እንጂ ሕንጻን መሰየም ዋጋ የለውም።
ቅድስት እናታችን ድንግል ማርያም ዋጋ እንዴት? በምን? ለምን? በማን? እንደሚሰጥ ጠንቅቃ ታውቃለችና «በስሜ ቤተ ክርስቲያን የሠራ» በማለት እራሷን ከፍ ከፍ አላደረገችም። ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ስለሆነች በራሱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ትገነባለች። ድንግል ማርያም የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አካል ናት። ይህ ለድንግል የተሠወረ አይደለምና ያላለችውን አለች በማለት ስሟን ከማጥፋት መቆጠብ ይገባል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ድንግል ማርያምን እንደሚወድ የተረዱት ተንኮለኛ ደብተራዎች በማርያም ስም የፈጠራ ኪዳን እያስተማሩ ሲበዘብዙ ሲያመልኩ እና ሲያስመልኩ ኖረዋል። አሁን ግን መጽሐፍ ቅዱስ በአማርኛ ታተመና ማንበብ ጀመርን እውነተኛውንም የሚያድን ኪዳን አገኘን። ነገሩ ደብተራዎች እንደሚሉት ሳይሆን ቀረ።  ለምን ይህ ሆነ? ስንላቸው መናፍቅ ናችሁ አሉን። በሐዋርያት አባቶቻችን እምነት መጓዛችን መናፍቅ የሚያሰኝ ከሆነ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ አልናቸው። እኛስ ድንግል ማርያምን የሚሳደብ መጽሐፍ [ታምረ ማርያምን] አናስተምርም አልን። ይህ መጽሐፍ የሚቃጠል እንጂ የሚታረም አይደለም  ነውራችንን እናስወግድ አልን አልን አልን አልን የሚሰማን ግን አላገኘንም ትውልዱ ግን እየሰማን ወደ እውነት እየጎረፈ ስለሆነ እግዚአብሔርን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን ።
«ምስጋናየን የጻፈ በምከበርበት ቀን ስሜን ያመሰገነውን» ቁ 39 ይቀጥላል
ዲያቆን ሉሌ ነኝ

10 comments:

 1. Ato deacon Lule,

  Aweyeeee... my brother. You may be perhaps venting your anger against mk by refuting the value of the saints in our lives. Whether St. Mary prayed that prayer or not, it does not matter. The bible fully supports the values and blessings that we can get through the saints. When we build the church in the name of St. Mary or any other saint, that saint, his/her service to God and his/her spiritual struggles get remembered by fellow christians. That remeberance is not in vain. We rather get tremendous values from it, such as:

  (1) We get good lessons from among one of us (i.e. Christians of the old days) on how to live a Christian life. For example, dedicating a church in the name of St. Mary would teach us about humility, faith, love of God, trust worthyness, the incarnation of the Word God, etc.. Similarly, dedicating a church in the name of St. George would teach us about firm belief in Christ in the face of unimaginable adversities and the saving power of God. Besides, St. Estifanos saw Christ Jesus on the right hand of God the Father while he was being stoned by the pharisis; he also prayed to God not to reckon the crimes of his enemies or adversaries. Dedicating a church in his name would teach us all these invaluable lessons.

  (2) We remember the saints. As we remember them, they remember us and pray for us in the presence of God. We get immense blessings from that.

  (3) We are listening to God and following His instructions by dedicating churches in the name of the saints. God has promised in the bible that to whomever abandons the world and pleases Him that He would give him/her a name greater than great sons and daughters. Building a church in the name of the saints is one form of greater name that God has given to the saints. We get blessings by follwoing the instructions of God.

  (4) The saints provide us with empirical evidence about Christianity. There are numerous beliefs around the world, but none have empirical evidence as much as Christianity does. The saints, be it current or departed, provide that evidence about the saving power of Christ Jesus. Christiainity is not imagination or some sort of ideal thought, but rather a practical way to eternal life and union with the Almighty God. The saints, as documneted in the bible and the gedles, are the prime evidence of that. We follow Christ hoping Him to save us as He saved the saints; hoping Him to guide us as He guided the saints; hoping Him to give us eternal life as He gave to the saints. Therefore, dedicating our children's name and those of our churches to the saints is another way of preaching about Christ both to believers and non-believers. It is the exression of our hope in Christ.

  (5) ....etc...

  ReplyDelete
 2. LeDengele Mariam mazen endi new...?LeDengele Mariam mazen endi new...?

  ReplyDelete
 3. Ato deacon Lule,

  It appears you don't believe on the words at Luke 1: 48 - "የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ ". I think you seem to believe that St. Mary is not being humble by saying "ብፅዕት ይሉኛል." The bible is testifying against your reasoning and way of interpretation. Your interpretation of the words and prayers as if she was seeking pride and prominence is wrong. You should first learn the bible and the other holy books before writing a commentary. Otherwise, jilajil eyehonek sew hulu yisekibehal.

  Luke 1:

  "40 ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን ተሳለመቻት።
  41 ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥
  42 በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።
  43 የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?
  44 እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና።
  45 ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።
  46 ማርያምም እንዲህ አለች።
  47 ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤
  48 የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤
  49 ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።
  50 ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል።
  51 በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤ ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤
  52 ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤
  53 የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል።
  54-55 ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል።
  56 ማርያምም ሦስት ወር የሚያህል በእርስዋ ዘንድ ተቀመጠች ወደ ቤትዋም ተመለሰች።"

  ReplyDelete
 4. aned sew diacon sibal wudase mariamen degmo new diacon yemibalew ante gen yetegnaw debetera endeseteh betenegeren tiru yemeselegnal.

  ReplyDelete
 5. Brother Nathan, Ena tamre Mariam koshasha aydelem eyalek neew?

  Last Anonymous @ July 7, 2011 10:12 PM , debetera ... that means you don't like debetera and believe the church is blamless? Debeters are not Pente.

  ReplyDelete
 6. 47 ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤
  48 የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤
  49 ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።
  50 ምሕረቱም ለሚፈሩት እስከ ትውልድና ትውልድ ይኖራል።
  51 በክንዱ ኃይል አድርጎአል፤ ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኖአል፤
  52 ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል
  53 የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ባለ ጠጎችንም ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል።

  ReplyDelete
 7. Anonymous @ July 8, 2011 8:35 AM,

  Did you see me quoting anything from tamre Mariam? Why become so naive and not focus on the truth? We should only question those points that are not consistent with the bible? If we oppose anything that is consistent with the bible, we may find ourselves fighting with God. I think you don't want to get into that...

  FYI, we cannot use any awalid book (dersan, teamir etc...) to substantiate any major faith related issue. Any faith or belief that is not supported by the bible cannot stand. The teamirs, dersans and awalids are simply additional and can only be used in conjunction with the bible. If there is anything in it that is inconsitent with the bible, I reject it and don't even want to read and hear about it. That is my benchmark. I did not find the intercession of St. Mary to be inconsistent with the bible. So, I believe it.

  However, it does not mean that I believe all the stories people say or write about St. Mary. Of course, some defteras have written some stories about St. Mary and other saints that are completely contrary to the bible. While most of the awalid books are okay, some are definitely worse than paganic or satanic verses. However, no awalid is still the source of our faith. The awalids are simply stories of the ancient christians or books composed by ancient believers, not necessarily with the blessing and guidance of the Holy Spirit.

  ReplyDelete
 8. wow! God bless you yiAbaselama azegajoche How God is doing wonderful activities through you. God's word revels what is truth in our time. The darkest age of our church is ending. The main subject of our Bible and Church (Christ) will be preached. Be strong God is healing many of us by your messages. Bezu chelema gedeloche getan endanay eskahun kilkeliwenal... zare kenachen new!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 9. ብፅዕና ለማርያም ብቻ አልተሰጠም; ሳያዩ ለሚያምኑ ጭምር እንጅ " ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው::"

  ReplyDelete
 10. እናታችን ድንግል ማርያም የተሃድሶ መነገጃ አይደለችም! የምትመለሱ ከሆነ ወደቅድስት ቤተክርስትያን የጥንቷ ክርስትናኦርቶዶክስ ተመለሱ! ኑፋቄያቹ ግን ጥንታዊቷ አይወክልም! “ቤተክርስትያን ማለት በጭቃ የተሰራ አይደለም ስትሉ ተደምጣቹዋል.! ለመሆኑ እናንተ ተሓድሶ “ጌታችን በማቴ 21 ላይ “ቤቴ የፀሎት ቤት ትባላለች አለ እንጂ እኔ ከመጣሁ በሗላ አታስፈልግም አላለም..! “ለዘላለምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ” (1ኛ ነገ 9:3)።

  ReplyDelete