Friday, July 1, 2011

የቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነት (ዶግማ) - ክፍል 3 የኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት --- Read PDF

ለብዙዎች መሳሳት አንደዋነኛ ምክንያት የሚቀርበው የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነት ጠንቅቆ አለመረዳት ነው።
Note: Parts 1 and 2 were posted on May 8 and 11.
 You can go back and review.

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ታላቅ ስፍራ ይሰጠዋል። የዘመን መቀዳደምና የክብር መበላለጥ በሌለበት በክበበ ሥላሴ ከሚገኙት ሦስት አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ቤተ ክርስቲያን የምታምነው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስትምህሮዋ ነው። (ዮሐ 1፥14፤ የሐዋ ሥራ 20፦28፤ ሮሜ 5፥9፤ ቲቶ 2፥13፤ 2ጴጥ 1፥1፤ 1ዮሐ 5፥20)
ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮታዊ ባሕርዩ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ የማያንስ፥ ትክክል የሆነ፥ የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ፥ ሁሉ በእርሱ የተፈጠረበት የአብ አካላዊ ቃል ነው። (ዮሐ 10፥30፤ 14፥9-11፤ 11፥1-3፤ ቄላ 1፥15-16)

በዘላለማዊ ልደቱ ከአብ የተወለደው የእግዚአብሔር ቃል (ወልድ ዋሕድ)በኋለኛው ዘመን ዓለምን ለማዳን ያለዘርዐ ብእሲ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ። (መዝ 2፥7፤ 2ሳሙ 7፥14፤ ሉቃ 1፥30-35)

ይህም ሲሆን አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሳይከፋፈል በመለኮቱ የእግዚአብሔር ልጅ ያለዘርዐ ብእሲ ሥጋንና ነፍስን መንፈስንም ነሥቶ በሥጋ ሥርዓት ከድንግል ማርያም በመወለዱ ደግሞ የማርያም ልጅ ነው። «እኮ ውእቱ ወልደ ማርያም በመለኮት አላ ዘከመ ሥርዓተ ትስብእት» «በመለኮት የማርያም ልጅ አይደለም፤ ሰው በሆነበት ሥርዓት ነው እንጂ» (ሃይ አበ ዘቴዎዶስዮስ ምዕራፍ 82 ክፍል 2 ቁ 20)

የቃል ሥጋ መሆን ምስጦር የተከናወነው በተዋሕዶ ሲሆን ይህም ተዋሕዶ ከመቀላቀል፥ ከመጠፋፋት ወዘተ የውሕደት ዓይነቶች ፈጽሞ የተለየ፥ የእግዚአብሔር ቃልና ሥጋ የባሕርይ መደባለቅና መለወጥ እንዲሁም የአቅዋም  ሽረትና ፍልሰት ሳይኖርባቸው ፈጽመው ሳይለያዩና ሳይከፋፈሉ ምንታዌን አጥፍተው በአንዱ የአካል ተዋሕዶ ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ነው የተሰኘበት ምስጢራዊ መገናዘብ ነው። በዚህ ተዋሕዶ የቃል የሆነው ነገር ሁሉ ለሥጋ፥ ከኃጢአት በቀር የሥጋ የሆነው ነገር ሁሉ ለቃል ገንዘቡ (ንብረቱ) ሆኗል። «ወእንቲአሁ ለቃል ኮነ ለሥጋ ወእንቲአሁ ለሥጋ ኮነ ለቃል» «የቃል የሆነው ነገር ሁሉ ለሥጋ ሆኗል፤ የሥጋ የሆነው ነገር ሁሉ ለቃል ሆኗል።» እንዲል

ይህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ባለመቀበል የኢየሱስ ክርስቶስን ፍጹም አምላክነትና ፍጹም ሰውነት ክዶ «ወልድ በመለኮቱ ፍጡር ነው» ያለውን አርዮስንና የተረገመች ትምህርቱን፥ የተዋሕዶ ምስጢር በመለወጥ እንደተፈጸመ ቆጥሮ የክርስቶስ ሰውነት ወደ አምላክነቱ ተለወጠ የሚለውን የአውጣኬን የውላጤ ትምህርት፥ እንዲሁም ከተዋሕዶ በኋላ በክርስቶስ ሁለት ህላዌና ሁለት ገጻት አለ የሚለውን የንስጥሮስን ክሕደትና የሌሎችንም በተዋሕዶ ትምህርት ላይ ኑፋቄ ያመጡትን ሁሉ ቤተክርስቲያናችን በአንድነቷ ለይታለች።

በመለየት ብቻ ሳትወሰን የተዋሕዶን ምስጢር በማደላደል አምልታና አስፍታ አስተምራለች። እንዲህ በማለት፦ «ተዋሕዶተ እሳት ምስለ ዕፅ ልምልምት እንተ ርእየ ሙሴ በኮሬብ ያጤይቅ ተዋሕዶተ መለኮት ወትስብእት፤ እሳት አምሳል መለኮት ውእቱ ዕፅኒ አምሳለ ትስብዕት ውዕቱ። ወኢመጽልዎቱ ለልምላሜ ዕፅ በተዋሕዶተ እሳት ያጤይቅ ከመ ኢጠፍአ ህላዌ ትእብእ ወአካለ ትስብእት በተዋህዶተ መለኮት ወኢጠፊኦቱ ለእሳት ተዋሕዶተ ዕፅ ልምልምት ያጤይቅ ከመ ኢጠፍአ ህላዌ መለኮት ወአካለ መለኮት በተዋሕዶተ ትስብእት --- ዝንቱ ምሳሌ አሰተጻደለ ራዕዮ ለፍና ትስብእት»

ትርጓሜ፦ «ሙሴ በኮሬብ ያየው የእሳትትና የቁጥቋጦ መዋሐድ የአምላክነትንና የሰውነትን መዋሐድ ያስረዳል። እሳት የመለኮት ምሳሌ ነው። ቁጥቋጦውም የትስብእት ምሳሌ ነው እሳት የተዋሐደው የቁጥቋጦው ልምላሜ አለመጠውለጉ የሰውነት ህላዌና አካል መለኮትን በመዋሓድ አለመጥፋቱን ያስረዳል። የቁጥቋጦው ልምላሜ የተዋሐደው እሳትም አለመጥፋቱ የመከኮት ህላዌና አካል በሰውነት መዋሐድ አለመጥፋቱን ያስረዳልና --- ይህም ምሳሌ የመዋሐድ ስልት ራዕይን አብራርቷል።» (ስምዐ ጽድቅ ብሔራዊ ገጽ 77)

የቃልና የስጋ ዘላለማዊ የተዋሕዶ ምስጢር እስከ ክርስቶስ ሞት ድረስ ብቻ የሚመስላቸው፥ ከትንሣኤውና ከዕርገቱ በኋላ ግን ሰው መሆኑ እንደቀረ የሚያስቡ የአውጣኬ ተከታዮች ዛሬም አይታጡም። ቤተክርስቲያን ግን የቃልና የስጋ ተዋሕዶ ከትንሣኤ በኋላም እንዳልቀረና ዘላለማዊ መሆኑን ታምናለች። «ሰው በመሆኑ መከራን ተቀበለ እንጂ ለዘለዓለሙ ሥጋን ተዋህዶ ይኖራል» እንዳለ ቅ/አትናቴዎስ (ሃይ አበ ምዕራፍ 26 ክፍል 7 ቁ 7)

ሰለዚህ ሞትን ድል ነሥቶ በአብ ቀኝ የተቀመጠው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬም ለዘለዓለምም የማይለወጥ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ነው። (ዕብ 13፥8)

ዛሬ ዛሬ ግን በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ላይ በብዛት የሚሰበከው የክርስቶስ አምላክነት ለብቻው ተነጥሎ ነው። አምላክነቱን ብቻ የሚሰብኩት ክፍሎች ሰው መሆኑን አልካድንም ቢሉም ከትንሣኤው በኋላ ያለውርደት በክብር የሆነውን የሰውነቱን ሥራ እንዳቆመ አድርገው ያስባሉ፣ ያስተምራሉም።

ሠኔ 21 ቀን 1982 ዓ/ም በታተመው «የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖትና የካህናት ተልእኮ» በተሰኘው መጽሐፍ ገፅ 28 ላይ «--- ስለዚህ ነቢረ የማን (በአብ ቀኝ መቀመጥ) ክርስቶስ ግብረ ትስብእት ከፈጸመ በኋላ እንደገና የሰውነትን ሥራ የማይሠራ ነገር ግን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በክብር መለኮታዊ ሥራውን እየሠራ የሚኖር መሆኑን የሚያስረዳ ቃል ነው።» የሚለው አባባል ይህንኑ የስሕተት ትምህርት ይደግፋል።

እንዲህ ማለት ግን ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ቀኝ እስኪቀመጥ ድረስ መለኮት ሥራውን ለሥጋ ትቶ ሥጋ ብቻ ይሠራ ነበር፥ ሥጋ ደግሞ አሁን በተራው የሥራ ጊዜውን ስለፈጸመ ሥራውን ለመለኮት ተወ አያሰኝብንምን? ነገሩ እንዲህ ከሆነማ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ሆኖ ያዳነን እርሱን ዕሩቅ ብእሲ፥ የእኛንም ድኅነት ከንቱ ማድረግ ይሆናል።

እኒህ ወገኖች የሰውነቱ ሥራ በመለኮቱ ሥራ እንዲዋጥ ያደረጉት ምናልባት አምላክነቱ እንዳይዋረድ በማሰብ ከሆነ «መጻሕፍት ግን ስለ አምላክነቱ የሚናገሩት አለ። ሰው ስለመሆኑም የተናገሩት አለ። እርሱ ሰው የሆነ አምላክ ሲሆን ስለ አምላክነቱ ሰው ስለመሆኑም አንድ አድርገው የተናገሩት አለ። እኔም ከእነዚህ ቃላት ለመለኮት የሚገባ ዳግመኛም ለትስብእት የሚገባ እንዳለ ይህንን እናገራለሁ» ይላል እንላቸዋለን። (ሃይ አበ ምዕራፍ 74 ክፍል 21 ቁ 37፤ ዮሐ 1፥1-14)

አዎን፤ ጥንታውያን አባቶቻችን በተዋሕዶ ትምህርታቸው ከትንሣኤው በኋላ ሰውነቱም ሆነ የሰውነቱ ግብር እንዳልቀረ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት በማደርግ ጽፈዋል። ለምሳሌ ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ራሱን በክርስቶስ ቦታ ተክቶ የሰጠውን ምስክርነት እንመልከት፦ «ይብል እስመ አነ አምላክ ወሰብእ ኅቡረ ወአነ አሐዱ ውእቱ፥ አነ እብል ዘንተ ወዝክተሂ አስመ ተወከፈኩ ኲሎ ዘዕጓለ አመሕያው ዘአልቦቱ ኃጢአት። ይብል እንሰ ነሣእኩ ዘበአማን ትስብእተ ወከመዝ ጸዋዕክዎ ለአቡየ አምላኪየ ዘከመ ይደሉ ለሥርዓተ ትስብእት ዘረሰይክዎ አሐደ ምስሌየ»

ትርጓሜ፦ «እኔ ሰው የሆንኩ አምላክ ነኝና እኔም አንድ ነኝና፤ ይህንንም ያንንም እኔ እላለሁ ይልላ። የሰውን ባሕርይ ገንዘብ አድርጌአለሁና። ኃጢአት የሌለበት እርሱ እኔ ነፍስን ሥጋን በእውነት ተዋህጄአለሁና ከእኔ ጋር አንድ ላደርግሁት ለሥጋ ሥርዓት እንደሚገባ እንዲህ አባቴን «አምላኬ» ብዬ ጠራሁት ይላል» (ሃይ አበ ምዕራፍ 68 ክፍል 19 ቁ 13)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባቱን አምላኬ ብሎ የጠራው ሰውነቱ ወይም የሰውነቱ ግብር ቀርቷል፤ አሁን አምላክ ብቻ ነው ብለው ከሚናገሩት ከትንሣኤው በኋላ እንደሆነ አስተውል። (የሐ 20፦17)

ምናልባት በግልጽ ለተቀመጠው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነትና የአባቶች ምስክርነት ሌላ አንድምታ በመስጠት «ይህማ ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ነው።» በሚል እውነትን ለማድበስበስ ይሞከር ይሆናል። አምላክ ሰው የመሆኑ ምስጢር በእንደዚህ ያለ ቀላል እንድምታ የሚታለፍ አይደለም። ይህ ምስጢር ያለጥርጥር ታላቅ ነው (1ጢሞ 3፥17) የምሲጢሩን ታላቅነት ለመረዳት አምላክ ሰው ሆኖ ለምን እንደመጣ ማወቁ አስፈላጊነት ይኖረዋል።

«አምላክ ለምን ሰው ሆነ?» በምል ርዕስ በሚቀጥለው ሳምንት እንቀጥላለን

የተቀበረ መክሊት ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ

7 comments:

 1. another lie? where is the other two parts about Jesus? oh my God. you guys ROCK! seriously.
  Ben

  ReplyDelete
 2. Even if this article has some truth, it is completely misleading and has emobodied the biggest lies that some propagate. The author is going to tell us that Christ is now interceding in heaven like he did on earth. He is positioning that big lie in the following statements.

  "ዛሬ ዛሬ ግን በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምሕረት ላይ በብዛት የሚሰበከው የክርስቶስ አምላክነት ለብቻው ተነጥሎ ነው። አምላክነቱን ብቻ የሚሰብኩት ክፍሎች ሰው መሆኑን አልካድንም ቢሉም ከትንሣኤው በኋላ ያለውርደት በክብር የሆነውን የሰውነቱን ሥራ እንዳቆመ አድርገው ያስባሉ፣ ያስተምራሉም።"

  The writer should note that this topic is beyond his capacity. He is just mixing up the tewahedo with the two natures believers and the protestant lies. The truth about Christ's intercession or mediation is that he has completed it on earth. Being the High Priest, he entered into the Holy of Holies with His blood and has given us His blood to be able to enter the same place He is in. That blood is the blood He shed on the Cross about 2000 years ago.

  His intercession upto and including His work on the Cross will continue to mediate and intercede all believers with God until the end of the world. Thus, Christ is the eternal High Priest and Intercessor/Mediator because that salvation work on the Cross serves every believer for eternity. Other than that, Christ does not do any special intercession in heaven. His eternal intercession is through the work or intercession He did on the Cross, including His prayers in Getesemanie. He did not do just history, but a life giving work that serves all believers for eternity. Again, that is the only eternal intercession that Christ does. Accomplished, but lives for ever so that we all can be saved. That accomplished work on the Cross makes Christ an eternal intercessor. The author's suggestion that Christ does another intercession in heaven because of His flesh is completely wrong and is a big lie. Guys, please don't listen to people who cite verses of the bible without having studied them well. satan does that as well. Remember that satan was quoting from the bible when tempting our Lord Christ Jesus.

  ReplyDelete
 3. At least you could say oh my bad! then fix it. Anyway its better now. What about the first comment? you don't like that,do you?
  Ben

  ReplyDelete
 4. Nathan, I think the writter is saying anything radically different from what you are saying in your last paragraph. Let's see what St. Paul says

  «ክርስቶስ በእጅ ወደተሰራች፣ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደምትሆን ቅድስት አልገባምና፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ። ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፤ ራሱን ብዙ ጌዜ ሊያቀርብ አልገባም፤ እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሰዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል። ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥ እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ የብዞዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያላ ኃጢዓት ይታይላቸዋል። » ዕብ 9፥24-28። I think this is what the writter is talking about. I also believe you agree with St. paul's message. The message is clear to me.

  ReplyDelete
 5. Nathye, mister confused. If you just accept the word of God as it is you would hv been Free man.

  "His intercession upto and including His work on the Cross will continue to mediate and intercede all believers with God until the end of the world. Thus, Christ is the eternal High Priest and Intercessor/Mediator because that salvation work on the Cross serves every believer for eternity."

  His intercession - is that past tense?
  continue to mediate - is that past tense?
  To the end of the world - is that past tense?
  eternal High Priest - is that past tense?
  for all eternity - is that past tense?

  Yes like I said u r getting closer. Gosh bereta. Aba Shenouda has a closer view like your in comparative theology.

  ReplyDelete
 6. ... More "He did not do just history, but a life giving work that serves all believers for eternity. Again, that is the only eternal intercession that Christ does. Accomplished, but lives for ever so that we all can be saved." I think the problem I see is the tense. If you agree that Christ does intercession for us now with the already completed work of the cross, we are on the same chapter. Bechifen gen ayamaledem malet adega neew. Yamaledal gen is that mean still abatun yelemenal? no Limenaw tesemalet (hebrew 3 or 4) Esum ke engdih selenante alemenem but he said u have my name. We can ask in the name of Jesus. Also sitting on the right side of his father, demun yezo now now now yetayelenal. That makes him the only only only mediator. Not Saints even St Mary or angeles.

  ReplyDelete
 7. This is all tehadiso menafikan timhirt

  ReplyDelete