Monday, July 11, 2011

በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ላይ መዋሸት ይቁም! ክፍል 3 --- Read PDF

«ምሥጋናየን የጻፈ በምከበርበት ቀን ስሜን ያመሰገነ»
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታን በጸነሰችበት ጊዜ «ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል» ብላለች። እግዚአብሔር ያከበራት በፊቱ ሞገስ ያገኘች በመሆኗ እጅግ ደስ ብሏታል መልአኩም ደስ ይበልሽ ነው ያላት፤ ይህን የድንግል ማርያም ደስታ እኛም ልጆቿ የምንካፈለው ደስታ ነው፤ ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይሉኛል አለች። አዎ እውነት ነው።  ድንግል ማርያም በጌታ ፊት ሞገስ አግኝታለች፤ አካላዊ ቃልን እሳታዊ መለኮትን ለመውለድ የተመረጠች በመሆኗ ከዚህም በላይ ትሕትናዋ ቅድስናዋ ርኅሩህነቷ ታግሽነቷ ወዘተ ብጽእት ያስኛታል። እኛም ልጆቿ ድንግል ማርያምን እናከብራታለን፣ እንወዳታለን፤ ብጽእት እንላታለን በእምነቷም እና በመታዘዟ ምሳሌያችን ናትና እጅግ እናደንቃታለን አሜን።
ነገር ግን ምሥጋና እና አምልኮ እራስን አዋርዶ መገዛት ስለሆነ ለልዑል አምላክ ብቻ የሚቀርብ ነው። ስለዚህ ድንግል ማርያም «ምሥጋናየን የጻፈና በምከበርበት ቀን ያመሰገነ»በማለት ልዩ ምሥጋና ወይም የምትከበርበት ቀን እንደ ለመነች አድርጎ ታምረ ማርያም ያስነበበን ታሪክ የናታችንን ጠባይ የማይገልጥ ስለሆነ እንደ ስድብ እናየዋለን። ሉቃስን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳን የድንግል ማርያምን ክብር ቅድስናዋን ትሕትናዋን በማድነቅ ብዙ ጽፈዋል፤ ይህም ስለሚገባትና ከሃይማኖታችን ጋር የተያያዘ ታሪክ ስላላት እንጂ መንግሥተ ሰማያት ለመግባት አስበው የጻፉት አይደለም። የሰኔ ጎልጎታ የተባለው የአብዛኛው ሕዝባችን የጸሎት መጽሐፍ  ምስጋናየን የጻፈ ያጻፈ ያነበበ የሰማ መጽሐፉን ባንገቱ የጻፈ ድርቅ ረሐብ ቸነፈር ብርድ አያገኘውም ይላል። ከሰኔ ጎልጎታ የከፋው ታምረ ማርያም ግን «በምከበርበት ቀን ያመሰገነኝን ማርልኝ» ስትል ጠየቀች ብሎ ዓይን ያወጣ ውሸት ያስነብበናል። እናታችን ትዕግሥተኛ እና እጅግ ትሑት ከመሆኗ የተነሳ ምሥጋናዋ እንዲጻፍና የምትከበርበት ቀን ተለይቶ ምሥጋና እንዲቀርብላት አልጠየቅችም። ይህ የናታችን ባሕርይ አይደለምና ታምረ ማርያም ስድቡን ያቁም ስንል እንማጸናለን። ቅዱሳን የተቀደሱት በትሕትናቸው ነው ስለዚህ ለራሳቸው ለስእላቸው ጭምር ስግደት ምሥጋና እና የክብር ቀን ሊለምኑ አይችሉም። የመታሰቢያ ቀናቸውም አባቶች ታሪካቸውን ለመዘከር በፈቃዳቸው የወሰኑት እንጂ ቅዱሳን ወይም ድንግል ማርያም በልመናቸው ከጌታ ያስወሰኑት አይደለም። ቅዱሳን ከዚህ ሐሳብ ፈጽሞ የራቁ ናቸው። ሰይጣን የወደቀው ምሥጋናን ከፍጥረታት ለመቀበል በመሞከሩ ነው። ስይጣን ይህን ሐሳብ ከማመንጨቱ በፊት ቅዱስ ነበር። ነገር ግን ምስጋና የሚገባው ከርሱ በላይ የሆነ አምላክ መኖሩን እያወቀ የማይገባውን ማግኘት ፈለገና የነበረውን እንኳ አጥቶ ተሰደደ።
የቅድስናን ትርጉም ያላወቁ ደብተራዎች በነገሥታት ፊት እየተቀኙ ጠጅና ቁርጥ እንደሚጋበዙት መስሏቸው በቅድስት እናታችን እና በቅዱሳን መላእክት በጻድቃንም ላይ አፋቸው እንዳመጣው ዘባርቀዋል። ይህን ስሕተት መሆኑን አምነው ንስሐ በመግባት ፈንታ እንደ ሃይማኖት አድርገው ይዘው ያላስተማሩ ወንድሞችን መናፍቅ እያሉ ያሰድዱበታል። ቅዱሳን የተሰበረ መንፈስ ያላቸው በእግዚአብሔር ፊት  ራሳቸውን ያዋረዱ የጌታን ክብር ከማየታቸው የተነሳ እጅግ የሚንቀጠቀጡ ናቸው እንጂ በጌታ ቦታ ሆነው ምሥጋና የመቀበል ሐሳብ የላቸውም።  ኢሳይያስ «እኔም ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ ከንፈሮቻቸው በረከሰባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን ስላዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ አልሁ» ኢሳ 6፥5 የጌታን ክብር ያዩ ቅዱሳን እንዲህ ይንቀጠቀጣሉ እንጂ ምስጋናየ ይጻፍልኝ በዓሌ ይከበርልኝ ብለው ሊጸልዩ አይችሉም። ታዲያ ቅድስተ ቅዱሳን እናታችን ድንግል ማርያም የበዓል ቀን ተወስኖላት እንድትመስገን እንዴት ትጠይቃልች? ይህ የትሕትና ጸሎት ነውን? እሁድ እሁድ ይህን ስድብ የምታነቡ ወገኖቼ ሁሉ አስቡበት።
ውዳሴ ማርያም በሚባለው ድርሰት የትርጓሜው መግቢያ ላይ «ወድሰኔ ኤፍሬም»የሚለውን ቃል ሲተረጉሙ «የወርቅ ወንበር ይዘጋጃል፣ የብርሃን ምንጣፍ ይነጠፋል፣ የብርሃን ድባባ ይዘረጋል በዚያ ላይ ድንግል ማርያም ተቀምጣ ኤፍሬም አመስግነኝ ትለዋለች፣ እርሱም መልሶ ምን ብዬ ላመስግንሽ ይላታል «በከመ አለበወከ መንፈስ ቅዱስ» [መንፈስ ቅዱስ እንደገለጠልህ] አለችው» በማለት ይናገራል [የሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ] እዚህ ላይ እግዚ ኦ በሉ! ድንግል ማርያም በወርቅ ዙፋን ተቀምጣ አመስገነኝ አለች? በውነቱ ይህ የጌታየ እናት የድንግል ማርያም ተግባር ነው? በፍጹም አይደልም ይህ የጌታ እናት ጠባይ አይደለም እኛ ድንግል ማርያምን የምናውቃት በትሕትናዋ፣ በዝምታዋ፣ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች እንዳለች የእግዚአብሔርን ክብር የምታስቀድም መሆኗን ነው ። በዙፋን ላይ ተቀምጣ አመስግኑኝ አለች በማለት ስሟን ማጥፋት እጅግ ነውር ነው።  የጌታችን እናት ድንግል ማርያም እንዲህ አይደለችም ክብሯ በራሷ ጥረት እና ፍላጎት የመጣ አይደለም እግዚአብሔር መርጦ በፈቃዱ አከበራት እንጂ። ስለ ስሟ ከፍተኛ ክብር በመስጠት የለመነችው ልመና የለም። ጠላት እርሷን የሚወድ በመምሰል ያላለችውን አለች በማለት ስሟን አጠፋ እንጂ እርሷስ እጅግ ትሑት እና ቅድስተ ቅዱሳን ናት።
 ልደት እና ፋሲካ ሲሆን ጳጳሳት ጠቅላይ ቤተ ክህነት በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ በተዘጋጀ ዙፋን ተቀምጠው እኛ ያዲስ አበባ ደብትራዎች ምስጋና እና ቅኔ ስናቀርብ እንደምናረፍድ በዚህም አባቶች ፈገግ እንደሚሉ ቀምሰነው የማናውቀውን ወይንና ኬክ ተቋድሰን እንደምንመለስ አውቃለሁ። ይህ ከጥንት ነገሥታት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ልማድ ነው። የአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ደብተራዎች ዘርዓ ያዕቆብ ያስለመዳቸውን አደራረግ ድንግል ማርያምም የምታደርገው መስሏቸው በአይናቸው ያዩትን በአእምሯቸው በመሳል «ድንግል ማርያም በወርቅ ዙፋን ተቀምጣ አመስገነኝ አለች» እያሉ ይሳደባሉ። «አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት መጽሐፍ አጠበች» እንደተባለው በነገሥታቱ የለመዱትን ከንቱ ውዳሴ ድንግል ማርያምም የምታደርገው መስሏቸው በስሟ ዋሽተውባታል።
በቤተ ክርስቲያናችን የስሕተት መዝሞሮችን በማስፋፋት የሚታወቀው የዘመናችን ክፉ ደብተራ እንግዳ ወርቅ የጥንት ደብተራዎችን ስድብ በመዝሙር አቅርቦታል «ውዳሴ ማርያም እደግማለሁ ድንግል እናቴን እጣራለሁ እንዳ አባ ኤፍሬም ማሪኝ ወድሰኒ ድንግል በይኝ» እያለ ዘምሮታል። የዚህን ክፉ ደብተራ የንግዳ ወርቅን መዝሙሮችና የሰውየውን ታሪክ ወደ ፊት በመጽሐፍ ጽፈን ሥራውን ለፍርድ እናቀርባለን።
በዚሁ ታምረ ማርያም በ12ኛው ታምር ቁ 47-52 ላይ የተጻፈው የመጽሐፉን ሥውር አላማ እንድናውቀው ይረዳናልና እንዲህ አቅርበነዋል።
«ወፍቁራኒሃ ዘንተ ኪዳነ ወመንክራተ ዘያስተፌስሕ ወእፁበ  መሐላ ዘያዴምም ዘወሀበነ እግዚእነ አኃዜ ኵሉ ሂሩታት ወሠነያት በጸውዖ ከመ ይድኅን ኩሉ ዓለም በምድር ወበሰማይ  ኦ ፍትሐ ዚአሁ ዘእንበለ አቂበ ሕግጋት ወገቢረ ሠናያት---ኦ አኃውየ ኃጥአን እለ ከማየ እምይእዜሰ ኢንሕሥሥ ከዊነ አግብርተ እግዚአብሔር ለፈጽሞ ሕግጋት ፲ወ፮ቱ እስመ ውእቱ መጠውነ ኪያሃ እግዝእተ ኪዳን»
ትርጉም «ወዳጆቿ የምትሆኑ ደስ የሚያሰኝ ይህን ድንቅ ኪዳን ቸርነትንና በጎነትን ሁሉ የያዘ ጌታ በሰማይና በምድር ያለ ሁሉ ስሟን በመጥራት ይድን ዘንድ የሰጣትንም ድንቅ የሚሆን መሐላን ታዩ ዘንድ ኑ፣ በጎ ሥራን ሳይሠሩ ሕግጋትን ሳይጠብቁ መዳን የሱ ፍርድ ምን ይረቅ እንደኔ ያላችሁ ኃጣአን ወንድሞቼ ሆይ እንግዲህስ ወዲህ አሥራ ስድስቱን ትእዛዛት[አሠርቱ ትእዛዛትና ስድስቱ ቃላተ ወንጌል]ለመፈጸም የእግዚአብሔር ባሪያዎች መሆን የለብንም የቃል ኪዳን እመቤት እርሷን ሰጥቶናልና» ታምር 12፡ ቁ 53።
የታምረ ማርያምን ሥውር አላማ በዚህ ንባብ ውስጥ እናስተውል «አሥራ ስድስቱን ትእዛዛት በመጠበቅ የእግዚአብሔር ባሪያዎች መሆን የለብንም»የሚለው ነው። ጌታ ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ ብሎ ማስተማሩን አንርሳ። ሰይጣን የድንግል ማርያምን ስም ሽፋን አድርጎ ሕዝብን ከእግዚአብሔር ለይቶ ለመግዛት የረቀቀ ተንኮሉን እንደተጠቀመ እናስተውላለን።
እንግዲህ የማርያም ታምር ተብሎ የሚነበብና በጨርቅ ተሸፍኖ የሚሳም የሚነበብና ንባቡን ሰምቶ ስጋውና ደሙን እንደተቀበልን የሚቆጠረው ይህ ወንጀል ተሰምቶ ነው። በጣም የሚያሳዝኑን ግን ታምረ ማርያም ስሕተት የለበትም እያሉ የሚያስተምሩ ቤተ ክርስቲያናችን ከስሕተት ትምሕርቶች እንዳትጸዳ እስከ መግደል ድረስ የሚደርሱት  የማህበረ ቅዱስን አባላት ናቸው። ይህን ጽሁፍ ባደባባይ ለማውጣት የተገደድነው ለሊቃውንት ጉባኤ ስናቀርብ ሊሰሙንም ሊረዱንም ስላልወደዱ ነው። ቃሉም «ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ ይልቁንም ግለጡት እንጂ» በማለት ይደግፈናል ኤፌ 5፥11።
"በሰማይና በምድር ያለ ሁሉ ስሟን በመጥራት ይድን ዘንድ‚ ቁ 52 ይቀጥላል
ዲያቆን ሉሌ ነኝ

24 comments:

 1. Waaaw! ይሄ በጣም የሚገርምና የሚያሳፍር ነው። ምነው አባቶቻችን እነዚህን ነገሮች ቀስ ብለው አስተካክለው ከሃፍረት ቢያድኑን? እነዚህን ነገሮች ካሁን በፊት አይቻቸው ባውቅም በእመቤታችን ላይ የተቃጣ የውሸትና የስድብ ናዳ አንደሆነ አድርጌ አስተውየው አላውቅም። እንደዚህ አይነቱን የቤተ ክርስቲያን ገመና ለህዝብ ማቅረቡ ምን ያህል ጥቅም እንዳለው ባላውቅም የነገሩ እውነታነት ግን መጽሐፍ ቅዱስን በመጠኑም ቢሆን ለተረዱ ሁሉ ግልጽ ነው።

  ReplyDelete
 2. OMG I have never heard such amazing history. but i want to hear the idea of MK or some other opposition of this idea. so if you can write and let us accept the strongest one.

  the peace of God upon u!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 3. Gudbel Dejene Shiferaw, birhanu gobena, yared gm, daniel kibret and meseloch - fighting with truth. Ras dejenen gefaw yehen yemetekawem kaleh.

  F

  ReplyDelete
 4. :) በጎ ሥራን ሳይሠሩ ሕግጋትን ሳይጠብቁ መዳን የሱ ፍርድ ምን ይረቅ (:

  I think I heard of this from the bible.

  God gave us one person to be saved with out works by faith and grace alone?

  "ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤

  ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። " Epheson 2:8-9

  ReplyDelete
 5. Dear Readers,

  Of course, teamere Mariam has a lot of mistakes. However, it does not mean that our mother's powerful intercession can be doubted. I am a witness to our most beloved mother. I have received numerous blessings in her name from Lord Jesus Christ; our mother is so intimate and so lovely; I belive that I can get numerous blessing both in heaven and on earth through the intercession of our most beloved mother.

  The author has made some sensibe comments and brought out some mistakes from the TM. However, I will say shame on you for comparing satan with the saints and St. Mary. Satan fell because he wanted to depose God and take His seat. The saints sacrficed their lives for the sake God. God Himself has instructed us to venerate the saints and have remembrance for them.

  I wish St. Mary could ask me to praise her. I would priase her a billion times; bow for her to respect/venerate her. She is a sweet and graceful mother; the Lord is with her all the time. We will give our lives for the love of St. Mary and her Son, Lord Christ Jesus. In Orthodoxy, unlike in protestant circles, we don't separate the mother from the Son. We worhip her Son while we venerate the mother for bearing the Son. The priase we offer to St Mary is not an expression of worship, but it is an expresion of veneration like she said in the bible «ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል». Yaltadele tiwiled gen zembilo yezebarkal.

  Neverteless, the authors of the book of TM have made big mistakes. There cannot be any salvation by disobeying God. It is just the creation of some useless defteras. They have just mixed up some good stuff with some other poisonous stuffs. I agree with the author of the article on that.

  ReplyDelete
  Replies
  1. hey my bro ,i got you but you need to be more wise before you condemn our intelligent fathers who wrote TM !~~!

   Delete
 6. To Nathan,
  "...ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል" "...all generations will call me blessed" ማለት ምን ማለት ነው?? ብፅዕት ወይም blessed የሚለው ቃል ምን ማለት ነው?? ይሄንን በደንብ ከተረዳህ በኋላ የዲያቆን ሉሌን ጽሁፍ (the first paragraph of part 3) ደጋግመህ አንብበው:: ጥቅሱን በደንብ አድርገው አብራርተውታል:: የቅድስት ድንግል ማርያምን ብፅዕትነት, ትሁትነት, እኛም ምን ያህል እንደምንወዳት, ብፅዕት እንደምንላት, እንደምናከብራት,... በሚገርምና በሚያስደስት ሁኔታ ገልጸውታል::

  Post የሚደረገውን ነገር አታነብም ወይም ሳትረዳው ተቃውሞ ለመጻፍ ትሮጣለህ:: እግዚአብሔር እንደዲያቆን ሉሌ አይነት ሰው ለቤተክርስቲያናችን ሲሰጠን ማመስገን ይገባናል:: መቃወም ያለ ነገር ነው ነገር ግን መሆን ያለበት የሰውን ጽሑፍ ወይም ሀሳብ በደንብ ከተረዳን በሁላ ነው::

  With all due respect, you like to hear yourself talk. Or you're Just writing for the sake of writing. Please read, read, read and understand....I've been reading your comments for quite some time now. It really doesn't make any sense because, you always disagree without understanding.....

  ReplyDelete
 7. ... continued

  Part II

  In summary, I love everyone within the family of Christ Jesus. I perceive the Christian Church as a body of one family (remember the vine tree parable). God is our Father, St. Mary is our mother, and the saints are our brothers, sisters, uncles, aunts etc.., who have joy and interest in our salvation. We worship God and venerate the saints. That is what I believe and practice.

  However, to blindly say that all the writings that we inherited are good and should not be corrected would leave our church to remain weak. During the times of the Apostles, many people wrote gospels and epistles, but the holy fathers of the time filtered out the bad ones and passed the good ones to us with the help of the Holy Spirit. In our church, same thing happened over the years, but some of the bad ones infiltrated the church. Not having a strong Synod of our own early on was one of the reasons that such bad writings infiltrated our church. So, the current Synod needs to review some of the controversial books, clean up the church, and work on the revival or renaissance of the church. Considering all the blessings God has given us, we should have been able to reach to other African communities and bring them to Christ, instead of leaving them to westerners, who may have ulterior motives. In reality, the EOTC has not even reached most communities in southern, eastern and western Ethiopia, leave alone the rest of Africa, and has not been able to teach and protect its own sheep that are for the most part amhars and tigres. One of the reasons for this grave failure, among others of course, is that the church is not focusing on the main message that Christ Jesus has told us to carry and disseminate to the world. You don’t have to believe me; just contemplate about it and evaluate it yourself.

  I pray that the God of our holy fathers help us make EOTC a shining star for the sake of His Name and through the intercession of St. Mary, the apostles, the martyrs, the archangels and the holy fathers. Amen!

  Thank you all, brothers in Christ.

  ReplyDelete
 8. To Zeraf,
  Can you give me a bible verse that says Virgin Mary (mother of Jesus) is our mother?
  Thank you

  ReplyDelete
 9. Even the Copts accept St. Tekle Haimanot! See it for yourself.

  http://st-takla.org/

  ReplyDelete
 10. Anonyous on 7/15/11 @ 2:10pm

  You will find the answer at John 19:27.

  When Christ our Lord was on the Cross, He said about that to his disciple the beloved saint John: "Behold your mother" (John 19:27).

  Hope this answer your question.

  ReplyDelete
 11. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን:

  ብሎገሮች እባካችሁ እናንተን የማይደግፍ የመሰላችሁን ሃሳቤን ከማውጣት አትቆጠቡ::

  ሰላም ወገኖች

  ናታን የጻፍከው ጋር በጣም እስማማለሁ በአንዳንድ የቤተ ክርስቲያን መጻህፍት ላይ አላዋቂዎችና መናፍቃን በልይ ልዩ ልዩ ምክነያት የስህተት ትምህርት አስገብተዋል:: ያ ማለት ግን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በአጠቃላይ ስለ ቅዱሳንም ይሁን ስለ እመቤታችን ያላት አመለካከትና እምነት ስህተት ነው ማለት አይደለም:: እኔ የዚህን ብሎግ አዘጋጆች ከምነቅፍባቸው ዋና ምከነያቶች አንዱ አንድን ጽሁፍ ይዞ አጠቃላይ እምነትን ለመጣልና ለማናናቅ የሚያደርጉትን ክፉ ሴራ ስላየሁ ነው::

  እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ሆነ ቅዱሳን በሙሉ ከእግዚአብሐር የተሰጡን ስጥታወቻችን ናቸው እነርሱን አይተን ቃላቸውን አድምጠን በህይወት እንድመስላቸው ምከነያት የሆኑን ናቸው:: ስለዚህም እናከብራቸዋለን እንወዳቸዋለን እናፈቅራቸዋለን:: እነርሱ ስለ እኛ ይለምናሉ እኛ ደግሞ በስማቸው እንለምናለን:: ይህ መጽሃፍ ቅዱሳዊና ኦርቶዶክሳዊ እምነት ነው::

  የሚገርመው ድንግል ማርያምን እናታችን አትበሉ ያልከው ሰው ጉዳይ

  ለመሆኑ ፊሊሞና ጢሞቲዎስና ቲቶ ቅዱስ ጳውሎስን አባታችን ይሉት እንደነበር መጽሃፍ ቅዱስን አንብበሃል:: እርሱም ልጆቸ ይላቸው እንደነበር:: /1ኛ ቆሮ 4:17 1ኛ ጢሞ 1፡2 1 18 ቲቶ 1፡4 ፊሊ 1 11) ታዲያ ልጆቹ የሆኑት ስለወለዳቸው ነውን? አይደለም መንፈሳዊ ትምህርትን ስላስተማራቸው ነው እንጂ::

  እኛም ቅዱሳን አበው የእውነትን መንገድ ስላስተማሩን ቅዱስ ፓውሎስን ጴጥሮስን ዮሓንስን ተክለ ሃይማኖትንም ሆነ ሌሎችን አባቶቻችን እንላቸዋለን::

  የድንግል ማርያም እናትነትማ እጅግ ድንቅና ክቡር ነው :: የጌታየ እናት ለእኔ እናቴ ናት ብዙ ነገር አስተምራኛለችና:: ትህትናን ትግስትን ወንጌልን ያስተማረችኝን እናት እናቴ እመቤቴ እላታለሁ:: እናቴ እመቤቴ እላታለሁ:: በመጨረሻው ሰዓትም ራሱ እናቴ እንድትሆን ራሱ ጌታ ለእኔ የሰጣትን እናት ድንግልን እናቴ ለማለት አላፍርም:: የክርስቶስ ፍቅርና ሚስጢር የለለው ግን በድንግል ማርያም እናትነት ያፍራል:: እናቱን እናት አድርጎ የስጠን ጌታ የተመሰገነ ይሁን:: ሃሌ ሉያ !!!

  ተጨማሪ ማብራሪያና ማስታወሻ ለተሃድሶዎች አንድን ኮንሰፕት ለመረዳት ስትሞክሩ መነሻችሁ ተዋህዶን ለማጣጣል አይሁን እስኪ በመጀመሪያ እውነትን ለማወቅ ጣሩ ከዚያ ጻፉ:: ቅድስት ድንግል ማርያምን ብጽህት ብሎ ማመስገን ነውሩ ምንድ ነው::
  መጽሃፍ እንደሚለው ያእ 5፡11 እነሆ፥ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንደ ታገሠ ሰምታችኋል፥ ጌታም እንደ ፈጸመለት አይታችኋል፤ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና።

  ReplyDelete
 12. የቀጠለ ___

  ብጹሃን ልዩዎች የተመሰገኑ እንላቸዋለን በትእግስት እግዚአብሄርን አምልከዋልና አገልግለዋልና ይላል:: እንዲያውም እናመሰግናቸዋለን ደጋግ ናቸውና::
  መዝ 33:1 ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ ለቅኖች ምስጋና ይገባል።

  ቅኖችን እንወዳለን መልካም መንገድ ያሳዮንን እናመሰግናለን:: ቅድስት ሆይ የመአዛ ሽቱ የሚሆን ጣፋጭ ክርስቶስን ወልደሽልናልና እንወድሻለን እናክብርሽ እናመሰግንሽማለን::

  የእግዚአብሔርን ምርጦች እንድናውቅ እንድናከብራቸውም የረዳንን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን::

  ለእኛ በጎ ነገርን ያደረገ እግዚአብሄርን እናመሰግነዋለን:: ይቅርባይ የጌታችን የአማላካችንና የመድሃኒታችን አባት ሰውሮናልና ረድቶናልና ጠብቆ አቅርቦናልና:: ወደ እርሱም ተቀብሎናልና አጽንቶ ጠብቆናልና:: እስከዚህ ሰዓት አድርሶናልና:: ስለ ስራው ሁሉ በስራው ሁሉ _ ቅዳሴ ባስሊዎስ

  ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወለድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ አሜን::

  እጅግም ጻድቅ አትሁኑ እናንተ ብቻ እንደተማራችሁ መጽሃፍ ቅዱሱን እናንተ ብቻ እንደምታውቁ አትመጻደቁ እኛም እናውቃለን መንፈስ ቅዱስ አስተምሮናል መጻህፍትን መርምረና ከአበው ጋር ተረድተናል::

  መልካም ጊዜ

  የማርያም ወዳጂ የኢየሱስ ክርስቶስ ፍጽም አገልጋይ ዘተዋህዶ

  ReplyDelete
 13. You Guys today you have difficulties of practicing fasting , genuinely respecting Angels saints and the mother of God ,And who can trust you for not denying God tomorrow?

  You have to understand that even believing and accepting Jesus Christ and the holy bible is based of faith and not proof? And if you have the sense of spirituality and believed what Jesus said listen what he has to say "He who receives you receives Me,and he who receives me receives Him who sent me.he who receives a prophet in the name of a prophet shall receive a prophet's reward.And he who receives a righteous man in the name of a righteous man shall receive the righteous man's reward.And whoever gives one of these little ones only only a cup of cod water in the name of a disciple. Assuredly , I say to you , he shall by no means lose his reward" Matt 10+40-42

  ReplyDelete
 14. zeraf are u john?

  ReplyDelete
 15. Tewahedo: Your comments makes it clear than you don't even read the first paragraph of the article presented here. The writer never said "Emebetachin Bitsihit aydelechim" "Emebetachin enatachin aydelechim" etc. YOu do you need to fabricate rethoric to make a point? By the way, you are one of the the few people who at lease acknowledge that some of the writtings in the church gedlat and tamirat have problems. That is a good start. Please be open minded and let's continue to discuss instead of label each other and acuse each other.

  ReplyDelete
 16. Tewahedo,

  Your comment is great. Hope the guys with heretic views can look inside themselves. Please keep up the participation.

  Anonymous at 10:59am - 7/19/11

  What kind of other denials and heresy do you expecte to hear from the author? He already told us that "writing praises for Mary and praising her" is wrong and hence he advised us not to do it. However, we, the orthdox faithfuls, would tell you on your face that we will contiue to praise St. Mary on earth and in heaven (heaven-after we depart). Since satan knows that we get immense blessings through the intercession of our mother, St. Mary, he (the devil) strongly targets our relationship with Mary and always opens his mouth by attacking mother Mary. We know and understand the approach and way of satan. We condemn it! If the author had cared for the church, his target would not have been St. Mary. Mother Mary is not the problem of our church, but rather she is the solutions for many of the problems we face. She already gave us one, her beloved Son. Why on earth prasing Mary becomes an offence to any christian? I know it is a serious offence to satan and its children. Satan debin bilo yinded enji mesganan LeDingil anakomim anakuaritim.

  ReplyDelete
 17. We believe in what we believe not just because it is in the bible but also because we have experienced it, we have seen it happening in our lives . Don't bother to tell me what is written in Tamire Mariam. I am Tamire Mariam myself. Imebete has done lots of miracles in my life. Yes she prayed for me and I am saved of so many misereable conditions. So what is wrong if I thank her and give her respect?
  Respecting His mother doesn't make me none believer or less believer in God. So what is your problem? Don't waste your time with this nonesense unless you have some hidden agenda behind ths.

  ReplyDelete
 18. Gudbel Dejene Shiferaw, birhanu gobena, yared gm, daniel kibret and meseloch - fighting with truth. Ras dejenen gefaw yehen yemetekawem kaleh.
  ትምህርት ከንቱ ይህንን ክህደት ነበር በቲዎሎጂ ውስጥ የተማሩት ማፈሪያ ሁሉ ማርያም ማርያም የምትሉት ለካ ለዚሁ ነበር በስሟ ታምኖ ገነት ሊገባ ዲንቄም ገነት!
  በስሟ ከማመን በስሙ ማመን
  ስሟን ከማወደስ ስሙን ማወደስ
  መስሟ ከመማጸን መስሙ ማማሰን
  መስን ተስፋ ከማድረግ ስሙን ተስፋ ብናደርግ ኢንዴት ባለጸጎች በሆን ነበር!
  ይህ የኢየሱስ ቃል ነው “ አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር ስምስህ ይቀደስ”
  አሜን የአምላካችን ስም ዘወትር ይቅደስ

  ReplyDelete
 19. እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ሆነ ቅዱሳን በሙሉ ከእግዚአብሐር የተሰጡን ስጥታወቻችን ናቸው እነርሱን አይተን ቃላቸውን አድምጠን በህይወት እንድመስላቸው ምከነያት የሆኑን ናቸው:: ስለዚህም እናከብራቸዋለን እንወዳቸዋለን እናፈቅራቸዋለን:: እነርሱ ስለ እኛ ይለምናሉ እኛ ደግሞ በስማቸው እንለምናለን:: ይህ መጽሃፍ ቅዱሳዊና ኦርቶዶክሳዊ እምነት ነው::!matios21 4-5 ለጽዮን ልጅ። እነሆ፥ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሉአት ተብሎ በነቢይ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ esayas 60:14የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።


  የሚገርመው ድንግል ማርያምን እናታችን አትበሉ ያልከው ሰው ጉዳይ

  ለመሆኑ ፊሊሞና ጢሞቲዎስና ቲቶ ቅዱስ ጳውሎስን አባታችን ይሉት እንደነበር መጽሃፍ ቅዱስን አንብበሃል:: እርሱም ልጆቸ ይላቸው እንደነበር:: /1ኛ ቆሮ 4:17 1ኛ ጢሞ 1፡2 1 18 ቲቶ 1፡4 ፊሊ 1 11) ታዲያ ልጆቹ የሆኑት ስለወለዳቸው ነውን? አይደለም መንፈሳዊ ትምህርትን ስላስተማራቸው ነው እንጂ::

  እኛም ቅዱሳን አበው የእውነትን መንገድ ስላስተማሩን ቅዱስ ፓውሎስን ጴጥሮስን ዮሓንስን ተክለ ሃይማኖትንም ሆነ ሌሎችን አባቶቻችን እንላቸዋለን::

  የድንግል ማርያም እናትነትማ እጅግ ድንቅና ክቡር ነው :: የጌታየ እናት ለእኔ እናቴ ናት ብዙ ነገር አስተምራኛለችና:: ትህትናን ትግስትን ወንጌልን ያስተማረችኝን እናት እናቴ እመቤቴ እላታለሁ:: እናቴ እመቤቴ እላታለሁ:: በመጨረሻው ሰዓትም ራሱ እናቴ እንድትሆን ራሱ ጌታ ለእኔ የሰጣትን እናት ድንግልን እናቴ ለማለት አላፍርም:: የክርስቶስ ፍቅርና ሚስጢር የለለው ግን በድንግል ማርያም እናትነት ያፍራል:: እናቱን እናት አድርጎ የስጠን ጌታ የተመሰገነ ይሁን:: ሃሌ ሉያ !!!matios21 4-5 ለጽዮን ልጅ። እነሆ፥ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሉአት ተብሎ በነቢይ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ esayas 60:14የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።

  ተጨማሪ ማብራሪያና ማስታወሻ ለተሃድሶዎች አንድን ኮንሰፕት ለመረዳት ስትሞክሩ መነሻችሁ ተዋህዶን ለማጣጣል አይሁን እስኪ በመጀመሪያ እውነትን ለማወቅ ጣሩ ከዚያ ጻፉ:: ቅድስት ድንግል ማርያምን ብጽህት ብሎ ማመስገን ነውሩ ምንድ ነው::
  መጽሃፍ እንደሚለው ያእ 5፡11 እነሆ፥ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንደ ታገሠ ሰምታችኋል፥ ጌታም እንደ ፈጸመለት አይታችኋል፤ ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና።

  ReplyDelete
 20. I got the author, i want to give him some advise because i know the motive behind him, i am telling him to be brave and ask the owners who wrote TM !!! they will tell him what exactly it says !! but he may be enemy for himself. Millions of orthodox church followers read and love what he is trying to tell us. He is also believe that they are not old en eff to understand that.so wired ! + he may not know it but he asking...did HE became a man ? yes GOD became a man and st MARY is HIS mother !! you may know it, but you are denying and you are telling us not praise her because you do not believe HE is her son.
  peoples may see our action but the almighty see our motive.You can make a money i different way. please do not sell your faith for it. i wish you, you to become on the right side. do not let people to go the evil way !! you will may pay for it. Bonjure

  ReplyDelete
 21. Shame on the author of such an article the very fact of the birth of Christ is tamer in itself written in the holy bible, to refutethat is bible just as good as being a none believer.

  ReplyDelete