Friday, July 8, 2011

የቤተ ክርስቲያናችን መሠረተ እምነት (ዶግማ) ክፍል 4 - - READ PDF አምላክ ለምን ሰው ሆነ?

አምላክ ለምን ሰው ሆነ?
ይህን ጥያቄ በአግባቡ መመለስ ከቻልን  የመዳናችን መንገድ ሊጠፋን ከቶ አይችልም። አሊያ «አምላክነቱ እንዳይዋረድ» በሚል ሽፋን ልብ ያላልነውን የትሥጉቱን ምስጢር የአምላክነቱን ያህል ልንረዳው ሳንችል ብንቀር ከአምላክነቱ ጋር በተዋሐደው ትሥጉቱ የምናገኘውን ድኅነት ማስተዋል  አንችልም።
የሰው ልጅ ከውድቀቱ በኃላ በተሰጠው ሕግ ተመርቶም ይሁን በሌላ እድንበታለሁ ብሎ ባሰበው መንገድ ከኃጢኣት ሞትና ከዘላለማዊ ኩነኔ ሊድን ፈጽሞ አልተቻለውም። የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ጽድቅም ቢሆን እንኳን ለሌሎች ተርፎ ከዘላለም ኩነኔ ለማዳን ይቅርና ለራሳቸውም እንደመርገም ጨርቅ  ሆኖባቸው ነበር። (ኢሳ 64፥6) ምናልባት እግዚአብሔርን በመፍራታቸውና በትእዛዙ በመሄዳቸው በሰው ሚዛን ሲመዘኑ ቅዱሳንና ጻድቃን ተብለው ቢጠሩም ሕግን ሁሉ ስላልፈጸሙና የኣዳም ልጆች በመሆናቸው ምክንያት አዳማዊ ኃጢአት ስላለባቸው ከተጠያቂነት ነጻ አልነበሩም። (ኢዮ 15፥7፤ 10፤ 25፥4-6፤ ማቴ 12፥34፤ መዝ 50፥5፤ ሮሜ 3፥11፤ 23፤ 5፥12፤ ኢሳ 48፥8)
ሊቁ አቡሊዲስም እንዲህ ብሏል፦ «ብእሲ ኢይክል ያድኅን ዓለመ ወሞቱ ለብእሲ ኢያንጽሖ - - - ወኢይክል መኑሂ እምሰብእ ያብጥል መዊተ ወያብርሃ ለሕይወት በከመ ይቤ ዳዊት መኑ ውእቱ ሰብእ ዘየሐዩ ወኢይሬእያ ለሞት ወመኑ ዘያድኅና ለነፍሱ እም እደ ሲኦል ወዘኢክህለ ያድኅን ነፍሶ እፎኑመ ይክል ያድኅን ኲሎ ዓለመ እስመi ኃጢአት የኅድር ውስተ ሰብእ ወሞተ ይተልዎ። - - - ወሶበ አበሰ አዳም ወለደ ዘከመ አምሳሊሁ»
ትርጓሜ፦ «ሰው ዓለምን ለማዳን አይችልም፤ የሰው መሞትም ከኃጢአት አያነጻም። - - - ዳዊት «ሕያው ሆኖ የሚኖር ሞትንም የማያይ ሰው ማነው? ከሲኦል አጅስ ነፍሱን የሚያድን ማነው?» ሲል እንደተናገረ ሞትን ያጠፋ ዘንድ ሕወትንም ያበራ ዘንድ የሚቻለው ከሰዎች ይገኛልን? ነፍሱን ለማዳን ያልቻለ ከሆነማ ሌላውን ለማዳን እንዴት ይችላል? እንዱን ለማዳን ካልቻለስ መላውን ዓለም እንዴት ሊያድን ይችላል? ኃጢአት በሰው ውስጥ አድሮአልና። ሞትም ይከተለዋል። - - - አዳም በበደለ ጊዜ ሰውን የወለደው በራሱ አምሳል ነው።» (ሃይ አበ ምዕራፍ 42 ክፍል 8 ቁ 5፤7-8፤ ዘፍ 5፥3፤ ኤር 3፥24-25)
የሰው ዘር በሙሉ በኃጢአት መበከሉን በዚህም የኃጢአት ብክለት በራሱም ሆነ በሌላ ነጻ መሆን እንደማይችል የተረዳው ደራሲ እንኳ። «አድኅኖ ነፍሶሙ እምኲነኔ ነቢያት ኢክህሉ» «ከኩነኔ ነፍሳቸውን ማዳን ነቢያት እንኳ አልቻሉም» በማለት በሰው አመለካከት ብቁ መስለው የሚታዩት ነቢያት ሌላውን ቀርቶ ራሳቸውን እንዳላዳኑ ተናግሯል።
ወደፊት ለሚመጣው ፍጹም አዳኝ እንደጥላ ምሳሌ ሆኖ ያገለገለው የኦሪት ካህናት ምልጃና ጸሎት እንዲሁም መሥዋዕት ኅሊናን ሊያነጻ፤ ጊዜያዊ ስርየት ከማሰጠትም በቀር በኃጢአት ምክንያት የተቋረጠውን የእግዚአብሔርንና የሰው ግንኙነት እንደገና እንዲቀጥል ሊያደርግ አልተቻለውም። (ዕብ 9፥13-14)
በዕርቅ ላይ የሁለቱም ጥለኞች ወገኖች መገኘታቸው የግድ ነው፤ አሊያ ግን እውነተኛ ዕርቅ አይወርድም። ቅዱሳን አበው፥ ካህናትና ነቢያት ሰው ብቻ ናቸው። ፍጹምነት ይጎድላቸዋል። ይህም ሆኖ ሊወክሉ የሚችሉት እንደ እነርሱ ኃጢአተኛ የሆነውን ሰውን ብቻ እንጂ እግዚአብሔርን የሚወክሉ ስላልሆነ የሰውና የእግዚአብሔር ዕርቅ በሰው አስታራቂነት በኩል የማይሞከር ሆነ።
ቅዱሳን መላእክትን ብንመለከት ደግሞ እግዚአብሔርንም ሰውንም የመወከል ወገናዊነት የሌላቸው ረቂቃን መናፍስት ስለሆኑ ለማስታረቅ አልበቁም። እግዚአብሔርም እነርሱን አስታራቂ አድርጎ አልሾመልንም። የዮሐንስ አፈወርቅንና የጵርቅሎስን ምስክርነት እንጥቀስ፦ «እስመ ለሊሁ ነጸረነ ወናሁ ኮነ አፅራረ ለእግዚአብሔር ወአልብነ ምንትኒ ግሙራ ዘይክል ያቅርበነ ኀቤሁ ለዐቂበ ሀብቱ ኢኪዳን፥ ወኢመሥዋዕት ወበእንተ ዝንቱ ተሣሃለነ ወኢያንሥአ ለነ ሊቀ ካህናት እመላእክት ወኢእምኀይላት እለ እሙንቱ ይቀውሙ ዐውደ መንበሩ»
ትርጓሜ፦ «እርሱ ተመልክቶን አነሆ ለእግዚአብሔር ጠላቶች ሆነን ተገኘን። ሀብቱን ለማግኘት ኪዳንም ቢሆን፤ መሥዋዕትም ቢሆን፥ ወደ እርሱ ያቀርበን ዘንድ የሚችል ፈጽሞ አልነበረንም፤ ስለዚህ ይቅር አለን። ዙፋኑን ከብበው ከሚቆሙ ከመላእክት ከኃይላትም ወገን አስታራቂ አልሾመልንም፣ (ሃይ አበ ምዕራፍ 62 ክፍል 2 ቁ 15) በዚህ ክፍል ግእዙን ወደ አማርኛ የመለሱት ክፍሎች የፈጸሙት ስውር ደባ አለ። በግእዙ «ሊቀ ካህናት» ያለውን ወደ አማርኛ ሲመልሱ አልተረጎሙትም። እንደ ግእዙ «ሊቀ ካህናት»ነው ያሉት። በሌላ ስፍራ ላይ ግን «ሊቀ ካህናት» የሚለውን ግእዙን ወደ አማርኛ ሲመልሱ «አስታራቂ» ብለው ተርጉመውታል። ለዚህም በዚሁ ክፍል ቁ 14 ላይ በግእዙ «መኑ ውእቱ ሊቀ ካህናት ወምእመን ዘእንበሌሁ» ያለውን ወደ አማርኛ የመለሰው «ከእርሱ በቀር - - - የታመነ አስታራቂ ማነው?» ማለቱ ምስክር ሊሆነን ይችላል። ከላይ ስለመላእክት በተነገረበት ስፍራ ግን በግእዙ «ሊቀካህናት» ያለውን «አስታራቂ» ብለው መተርጎምን ለምን ፈሩ? መቼም ምክንያታቸው ሌላ ሳይሆን ዐዲስ ያቋቋሙትን ትምህርት የሚያፈራርስባቸው ስለሆነ መሆኑ ጥርጥር የለውም።

የጵርቅሎስ ምስክርነት ደግሞ እንዲህ ይላል፦ «ብእሲሰ ትሑት አድኅኖ እምኢክህለ እስመ ውእቱሂ ይፈዲ ምስሌነ ዕዳ ወመልአክሂ ኢክህለ ተሣይጦተነ እስመ አልቦቱ ቤዛ ሥጋ በዘይትቤዘወነ»
ትርጓሜ፦ «ወራዳው ሰው የገዛ ራሱ ከእኛ ጋር ዕዳን ስለሚከፍል ሊያድነን ባልቻለም፤ መልአክም ቢሆን ስለእኛ ቤዛ የሚሆንበት ሥጋ ስለማይኖረው ሊዋጀን አልቻለም (ስምዐ ጽድቅ ብሔራዊ ገጽ 150)

አንባቢ ሆይ፤ ሰውስ በድሏልና ሊያስታርቅ አልቻለም። ቅዱሳን መላእክት ግን አልበደሉም ነበር። ነገር ግን ለማስታረቅ ያለመቻላቸው ምስጢር ግልጽ ሆነልን?

ከላይ በተመለከትነው መሠረት ማንኛውም ፍጡር ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርበን አለመቻሉ የተረጋገጠ ነገር በመሆኑ ከዚህ በኋላ ድኅነታችን በፍጡር አማላጅ ወይም በመልእክተኛ (መልአክ) መሆኑ ቀርቶ በራሱ በሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስ ይከናወን ዘንድ የግድ ሆነ። ይህን ሲያስረግጥ ቄርሎስ እንዲህ ብሏል፦ «ወኢሳይያስኒ ነቢይ ይቤ አኮ ውእቱ መተንብል ወኢመልአክ አላ ለሊሁ እግዚእ ዘመጽአ ወአድኅነነ ወኢያድኅነነ በደመ ነኪር ወኢበሞተ ብእሲ አላ በደሙ በሕቲቱ»
ትርጓሜ፦ «ነቢይ ኢሳይያስ ሰው ሆኖ ያዳነን እርሱ ራሱ ጌታ ነው እንጂ ሌላ አማላጅ ወይም መልአክ አይደለም። በባዕድ ደም በዕሩቅ ብእሲም ሞት አላዳነንም። ራሱ በደሙ አዳነን እንጂ» (ሃይ አበ ምዕራፍ 77 ክፍል 46 ቁ 13፤ ኢሳ 63፥9 ግእዙን ተመልከት)

ስለዚህ እኛን ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስታርቅና ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርበን ሰው ሆኖ የመጣው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከኃጢአት ንጹሕ የሆነ፥ በሰውነቱ ሰውን በአምላክነቱ ደግሞ እግዚአብሔርን ሊወክል የቻለ፥ እንደ ኦሪት ካህናት አስታራቂነቱ በሞት የማይሻር ሕያውና ዘላለማዊ ሊቀ ካህናት ሆነ። (ኤፌ 2፥12-13፤ ዕብ 7፥23-25

አንዱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርንና ሰው ስለሆነ ተበድያለሁ የሚል እግዚአብሔርና በድያለሁ የሚል ሰው በእርሱ ተገናኙ። ይህም በመካከላችን የነበረውን ጥል አስወግዶ ዕርቃችንን ፍጹም አድርጎታል። በመጽሐፈ ምዕላድ የሚከተለው ተጽፎአል፦ «እምቅድመ ይሠጎ ተኅጥአ ንጹሕ ዐራቂ እምክልኤ ጾታ እምይእዜሰ ይደልዎ ይስረይ ኃጢአተ ምስለ አቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ በመለኮቱ እስመ ተረከበ ንጹሐ ዐራቂ ወመተንብለ በትሰብእቱ»

ትርጓሜ፦ «ሥጋ ከመልበሱ በፊት በሁለቱም ወገን ንጹሕ የሆነ አስታራቂ ታጥቶ ነበር። ከእንግዲህ ወዲህ ግን በመለኮቱ ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሆኖ ኃጢአትን ይሰርይ ዘንድ ተገብቶታል። በሰውነቱ ንጹሕ አስታራቂና የሚጸልይ ሆኗል።» (ስምዐ ጽድቅ ብሔራዊ ገጽ 112)
ኃጢአትን ሳይቀጣ እንዲሁ ማለፍ ለጻድቅ ባሕርዩ የማይስማማው ቅዱስ እግዚአብሔር የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ተሸክሞ በቤዛነት የሚሞትና የቁጣውን ትኩሳት የሚያበርድበት በእግዚአብሔር በግ የተመሰለው ልኩ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነውና ስለኃጢአታችን አሳልፎ ሰጠው። (የሐ 1፥29፤ 1ቆሮ 5፥7፤ ኢሳ 53፥7፤ ራእ 7፥14፤ ኢሳ 53፥10)

እኛን ከራሱ ጋር ለማስታረቅ እግዚአብሔር በልጁ በኩል ጣልቃ መግባት ያስፈለገው በፍጡራን ለመታርቅ ስላልተቻለ ነው። (ኢሳ 59፥16፤ 2ቆሮ 5፥19) ስለዚህም ኤፍሬም ሶርያዊ «ወኮነ ዐራቄ ለሐዲስ ኪዳን» «የዐዲስ ኪዳን አስታራቂ ሆነ» ብሎ እንደመሰከረ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዐዲስ ኪዳን ብቸኛ አስታራቂ ነው። (ውዳሴ ማር ዘእሑድ)

ዐዲስ ኪዳን አንድ ዕለት ብቻ አይደለም። በጌታችን መገለጥ ተወጥኖ በፈሰሰው ደሙ የጸናና እስከ ዳግም ምጽአቱ ድረስ ያለው ጊዜ ነው።

ክርስቶስ የዐዲስ ኪዳን ብቸኛ አስታራቂ መሆኑን ሲገልጽ ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ፦ «መኑ ውእቱ ሊቀ ካህናት ወምእመን ዘእንበሌሁ ዘይክል ለሊሁ ባሕቲቱ ሰራዬ ኃጢአት ወምንት ውእቱ መሥዋዕት ዘአዕረጎ በእንተ ዝንቱ ስርዓት ሥጋሁ ባሕቲቱ ዘነሥኦ በእንተ ዝንቱ ግብር»

ትርጓሜ፦ «ከእርሱ በቀር ራሱ ብቻውን ኃጢአትን ማስተስረይ የሚቻለው የታመነ አስታራዊ ማነው? ለማስታረቅ ኃጢአትን ለማስተስረይ ያቀረበው መሥዋዕትስ ምንድነው? መሥዋዕት ለመሆን የነሳው ሥጋው ብቻ ነው እንጂ» ብሏል። (ሃይ አበ ምዕራፍ 62 ክፍል 2 ቁ 14)

አስቀድሞ በፍጡራን በኩል ዕርቅ ስላልተገኘ የእርሱ ጣልቃ ገብነት እንዳስፈለገ ሁሉ ከእርሱ በሁዋላ ደግሞ በእርሱ ያልተፈጸመና የቀረ ነገር ኖሮ በእኛና በእግዚአብሔር መካከል የሚገባ ሌላ ጣልቃ ገብ አይኖርም። እዱሳን መጻሕፍት እንደመሰከሩ። (ዮሐ 14፥6፤ 1ጢሞ 2፥5-6፤ ዕብ 10፥19-22፤ ኤፌ 2፥18)

ስለሌላው የሚጸልዩ ቅዱሳን ቢሆኑ እንኳ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡት በክርስቶስ በኩል ነው። ምክንያቱም ሰው በራሱ ብቁ ሊሆን አይችልም፤ የሰው ብቃት ክርስቶስ  ብቻ ነውና። (2ኛ ቆሮ 3፥5፤ 1ኛ ቆሮ 15፥10)

በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የድርሰት ክፍል በ 1963 ዓ/ም በታተመውና «ጽድቀ ሃይማኖት የቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት ውሳኔዎች» በተሰኘው መጽሐፍ ገጽ 35 ላይ እንዲህ የሚል ጽሑፍ አለ፦ «- - - እንዲሁም የሞቱ ቅዱሳን ከእግዚአብሔር አብና ከእግዚአብሔር ወልድ የሚያርቁን አይደሉም። ከኛ ጋር አንድ ማኅበር ሆነው በክርስቶስ ፍቅርና በክርስቶስ ጸሎት የተያያዙ ናቸው እንጂ። ምእመናን ሁሉ በዓለምም ሆነ በሰማይ ቢኖሩ ወደ ሌላ ሳይሄዱ በቀጥታ በክርስቶስ በኩል ወደ እግዚአብሔር ሊቀርቡ ይችላሉ። እስመ ሐደሰ ለነ ፍኖት ሕይወት - - - ንቅረብ እንከ ይላል (የሕይወትን መንገድ ስላደሰልን እንዲህ እንቅረብ) (ዕብ 10፥19-23)

አንዳንዶች የክርስቶስን የአዳኝነት ሥራ እንዳለፈ ድርጊት ብቻ ስለሚቆጥሩ ዘላለማዊ አገልግሎቱን አምኖ የሚቀበል ዝግጁ ልብ የላቸውም። እነርሱ ጌታ ሰው ሆኖ የመጣው የአዳምንና የሔዋንን ኃጢአት (የኛን የውርስ ኃጢአት) ለማስትስረይ ብቻ ይመስላቸዋል። ስለሆነም ይህንን ሥራ ፈጽሞ በአብ ቀኝ በመቀመጥ አሁን የአምላክነቱን ሥራ ብቻ እየሰራ ነው ብለው በመናገር በክብሩ ሆኖ የሚሠራውን የሰውነቱን ሥራ ይክዳሉ።

ለዚህ አሳባቸው ግን ድጋፍ የሚሆናቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ የላቸውም፤ የክርስቶስን ስፍራ ለሌሎች ያወረሱበት የፈጠራ ድርሰታቸው ካለሆነ በቀር

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለሔዋን ኃጢአት ብቻ ሳይሆን ዛሬም ስለምንሠራው ኃጢአት ሁሉ ነው የሞተው። በሌላ አነጋገር ክርስቶስ ዋጋ ያልከፈለበት ኃጢአት የለም። ስለዚህ ዛሬም በቤዛነቱ መታረቂያችንና የኃጢአታችን ማስተስረያ ነው። (1ዮሐ 1፥7፤ 2፥2፤ ቆላ 1፥19-22)

መጽሐፍ ቅዱስ አምላካችን እግዚአብሔር በቀደሙት ዘመናት በብዙ ዓይነት በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት እንደተናገረና በዘመኑ መጨረሻ ግን ዓለማትን በፈጠረበት፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው በልጁ እንደተናገረ ይመሰክራል እንጂ በልጁ ከተናገረ በሁዋላ ሌላ የተናገረበት መንገድ ወይም ልጁን ከላከ በሁዋላ የላከው ሌላ አዳኝ እንዳለ አይናገርም። (ዕብ 1፥1-3፤ ማቴ 21፥30-41)

በልጁ በመድኃኒታችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የወደደውን ሁሉ አድርጓል። ከዚህ በሁዋላም ሊያደርግ ያሰበው አሳቡ በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው። (ኤፌ 1፥9-10)

ይህን ባለመረዳት ሰው የሆነበትን ዓላማ ዘንግተው ስለቀድሞው ኃጢአታችን ከሞተልን በሁዋላ አሁን ለምንሠራው ኃጢአት በክርስቶስ ሳይሆን በሌሎች ነው የምንታረቀው ብለው ሌላ ዐዲስ መሠረት መሥርተዋል። ነገር ግን ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልም፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (1ኛ ቆሮ 3፥11)

እነዚህ ወገኖች የተሳሳተ አመለካከታቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማስመሰል የእግዚአብሔርን ቃል ላልተነገረበትና ላልተጻፈበት ዓላማ እንዳሻቸው ይጠቅሳሉ። የተመሠረተውን አፍርሰው እነርሱ ላኖሩዋቸው ዐዳዲስ መሠረቶች ድጋፍ እንዲሆኑላቸው ከሚጠቅሱአቸው መካከል፦ «የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው - - - በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ» የሚለው ይገኝበታል። (2ኛ ቆሮ 5፥18-19) ከዚህ ቃል የምንረዳው ሐዋርያት ወንጌልን በመስበካቸው ምክንያት ስለተከናወነውና ዛሬም በሕይወተ ሥጋ ባሉት ሐዋርያትና ሰባኪያነ ወንጌል እየተከናወነ ስላለው የሰውና የእግዚአብሔር ዕርቅ ነው። ሐዋርያቱ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ባኖረው የማስታረቅ ቃል ለሰው ወንጌልን በመስበክ በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት አምኖ ንስሐ በመግባት በክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር እንዲታረቅ የሚያደርጉት ይህ የማስታረቅ አገልግሎት ትርጉሙ ይኸው ብቻ ነው።

በዚህ ምዕራፍ ቁ 20 ላይ «እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ» የሚለውን «በእኛ እንደሚማለድ» በሚለው በመተካት የእግዚአብሔርን አሳብ ወደ ራሳቸው ፍላጎት ለማምጣት ጥረት ያደርጋሉ። በዚህ ሁኔታ የቱንም ያህል ጥረት ቢደረግ የመልእክቱን ትክክለኛ አሳብ ማዛባት አይቻልም። ይህ ክፍል ቅዱሳን ወደ እግዚአብሔር ስለሚያቀርቡት የምልጃ ጸሎት አለመናገሩን በግልጽ የምንረዳው «ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለክርስቶስ እንለምናለን» በሚለው ቃል ነው። ይህ ልመና የቀረበው ለእግዚአብሔር ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር በክርስቶስ መታረቅ ለሚገባቸው ኃጢአተኞች ነው (የሐዋ ሥራ 13፥46)

ይህን የማስታረቅ አገልግሎት በሚመለክት ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። ለምሳሌ ያህል ግን ቅዱሳን ሐዋርያት ጳውሎስና ሲላስ ለወኅኒ ቤቱ ጠባቂ ያደረጉትን እንመልከት፤ ሐዋርያቱ ታስረው በመንፈቀ ሌሊት በዜማ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ሲጸልዩ በተደረገው ተአምራት ተደንቆ «ጌቶች ሆይ! እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል?» የሚል ጥያቄ ባቀረበላቸው ጊዜ በውስጣቸው በተቀመጠው የማስታረቅ ቃል «በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተሰዎችህም ትድናላችሁ» በማለት ከእግዚአብሔር ጋር በክርስቶስ በማመን በኩል እንዲታረቅና ዘላለማዊ ድኅነትን እንዲያገኝ አደረጉት። (የሐዋ ሥራ 16፥25-34) የዕርቅ ውጤት ደስታ ነውና ከእግዚአብሔር ጋር በመታረቁ ምክንያት ከመላው ቤተሰቡ ጋር ተደሰተ። በሰማይም ይህ ደስታ እንደሚደረግ እሙን ነው። (ሉቃ 15፥10)

አንባቢ ሆይ! በክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቅንና ከዳንን በኋላ ኃጢአት ሠርተን ብንገኝ ስለኃጢአታችን ከክርስቶስ በቀር ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት መንገድም ሆነ የሚቀርብልን መሥዋዕት አለመኖሩን አስተውል! (ዕብ 10፥26) ብዙዎች ይህንን እውነት የማይቀበሉት የክርስቶስ አምላክነት የሚዋረድ ስለሚመስላቸው ነው። እነርሱ እንደሚያስቡት በዚህ ምክንያት የክርስቶስ አምላክነት አይዋረድም። ይልቁንም ሰው መሆኑ ይገለጣል። እርሱ ለዘለዓለም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ነው። በክርስቶስ ፍጹም ሰው መሆን ቀድሞ የተከናወነውንና ዛሬም እስከ መጨረሻው የሚከናወነውን ቀጥሎ እንመለከታለን።

የተቀበረ መክሊት መጽሐፍ የተወሰደ 

31 comments:

 1. This is great. short and precise. I hope those who have wrong understanding of Jesus Christ will have tangible concept of his amalagenet and adagnenet. God bless you!!

  ReplyDelete
 2. Mr. Author,

  What is your name? Why did you hide it?

  Also, what is the difference between MASTAREK and MAMALED? Are they the same?

  ReplyDelete
 3. Does it really matter who wrote the article or where it came from? The article is using the Bible and writings of our forefathers as the only source.

  Mastarek and mamaled sound the same to me. we are told by some that "tehadeso"and "mamaled" are bad words, so sounds like the writter is using an alternative word to teach the word of God. So here you go - when some say kirostos yamaldal, they mean yastarkal. They don't mean Jesus continues to beg his father so that we will be saved. እርሱ መስዋዕት አቅራቢ ሆኖ፤ እርሱ ራሱ መስዋዕት ሆኖ፤ እርሱ ራሱ ደግሞ መስዋዕት ተቀባይ ሆኖ ለምናምነው ሁሉ ያድነን ዘንድ የታመነ ነው። አንዴ በቀራንዮ የሰራው የሊቀ ክህነት ስራ ወይም የማማለድ ስራ ወይም የማስታረቅ ስራ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ህያው ሆኖ ይኖራል። አሁንም የኛን ሥጋ ለብሶ ጌታችን በአብ ቀኝ አለ። ቅዱስ ጳውሎስ መያዣ አለን እንዳለው ጌታችን ለምናምነው ሁሉ ጠበቃችን ሆኖ ለምናምነው እየታየልን ይኖራል። ምን አስደናቂ የአምላክ ምስጢር ነው? ብዙዎቻችን ግን ይህ ምስጢር ተደብቆብን እንኖራለን።

  ReplyDelete
 4. ሰላም ወገኖች:

  ያስነበባችሁንን ጽሁፍ ካየሁ በሁዋላ አንዳንድ አስተያየቶችና ጥያቀቄዎችን ማቅረብ እንዳለብኝ ስለተሰማኝ :: እንደ ደጀ ሰላም ደግሞ አስተያየቶቸን እንዳትበሉት:: ደጀ ሰላሞች አንዳንዴ አስተያየቴን ይበሉብኛል:: ለነገሩ እናንተም ባለፈው በልታችሁብኛል:: ዛሬ ልሞክራችሁ ብየ ነው ቀላል አስተያየት የማቀርበው::

  ዛሬ ያቀረበችሁት ጽሁን በተመለከተ

  1 የክርስቶስን አስታራቂነት/አዳኝነት ማነኛውም የቤተ ክርስቲያን መምህር የሚያስተምረው ትምህርት ነው እናንተ ምን ብላችሁ እንዲህ ቤተ ክርስቲያን እንደማታምንበት አድርጋችሁ ለማቅረብ የሞከራችሁት:: ክርስቶስን አዳኝ ካላልነው ያስታረቀን እርሱ አይደለም ካልን ምን ልንል ነው? ክርስቶስ ኢየሱስ አስታራቂያችን መደሃኒታችን አይደለም የሚሉ ሰዎችን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አይታችሁ ታውቃላችሁ ወይ?

  2 ክርስቶስ አስታራቂነቱንና ምልጃውን እንዴት ታዮታላችሁ? የ ክርስቶስ የማዳን ስራ ለአንዴና ለመጪረሻ ጊዜ በመስቀል የተፈጸመ ነው:: የእኛ ሊቀ ካህን ግን ብዙ ጊዜ መግባት አላስፈለገውም ያን ባደረገ ጊዜ ያን ጊዜ ፈጽሞታልና:: የሚለውን የመጽሃፍ ቅዱስ ቃል እንዴት ታዩታላችሁ? እናንተ እንደምትሉ ክርስቶስ አሁን አብን ይለምናልን? ወይስ በመስቀል ባፈሰሰው ደመ ሁሉም ይታረቃሉ?

  3 ክርስቶስ አማላጅ ነው ስትሉ ምን ማለታችሁ ነው? አሁንም ክርስቶስ ይደክማል? ይጸልያል? ይለምናል? በምን መልኩ ክርስቶስ ይማልድናል? ለየትኛው ሃጢያት ይለምናል?
  4. መጽሃፍ ቅዱስ የክርስቶስ ስጋውና ደሙ ከሃጢያት የሚያነጻን/ መታረቂያችን እንደሆነ ይነግረናል::1ኛ ዮሃ 1:7 ሮሜ 3፡25 1ኤፌ 1:7 እብ9፡14 :: ታዲያ ክርስቶስ በስጋው አስታራቂነው ስትሉ ስጋውንና ደሙን በመቀበል የሚደረገ መታረቅ ነው ወይስ አባት ሆይ ይቅር በላቸው ብሎ ለጠላቶቹ እንደለመነ ለሃዋርያቱም ምልጃን እንዳቀረበ ዛሬም ወደ አብ ይለምናል::
  5 ከኦርቶዶክሳዊያን የቅርብም ይሁን የሩቅ አባቶች መካከል ብዙዎች ስላስታራቂነቱ ጽፈዋል:: ኢየሱስ አሁን አማላጅ ነው የሚል ጽሁፍ የጻፉ ግን የሉም ታዲያ እናንተ አማላጅ ነው የሚለውን ትምህርት ከየት አመጣችሁት?

  6 ቅዱሳንን በተመለከተ በቤተ ክርስቲያን የተጋነኑ የሚመስሉ ነገሮች አንዳሉ አውቃለሁ:: ግን የቅዱሳን ምልጃ ትምህርት አባቶቻችን የፈጠሩት እንጂ እግዚአብሄር የማያውቀው ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?
  If you can answer the above questions, I will give you response. I want to know exactly whether you are looking for improvement of some exaggerated teachings or anti-orthodoxes. Even though there are some problems in the awaled metsahifits Orthodox Creed and Beliefe is biblical and true.

  ReplyDelete
 5. Hi Brother Nathan,

  I knew you will comment on this & offcourse here you are. I love you brother. Why is that important to know his name? Read the whole book yetekebere Meklit.


  Mastarek and mamaled are two different terms.

  Eyesus is enough for both. Once astareken degmom siasfeleg likehanat hono selegna yemaledal.

  Mastarek yemiasfelegew betelanet lalu sihon - gena telatochu salen be liju mot tarerken.

  Mamaled telat banehonem behone mikniat mekereb banchil (Be hattiayt) lela mehal yemigeba mekakelegna yasfelegal. Silnesu liamaled, litay, mekakelegna hono zeweter behiwot yenoral.

  Alemamenehn yeredaw bezih bekul. BTW you are closer and one of these days you will see some light. Turning point in your life. Good luck

  Zebihere Beria.

  ReplyDelete
 6. Dear Orthodox,

  1 - If you never heard Ethio orthodox songs specially by mahebere kidusan, search it ena lelochin astarekun silu mesemat techelaleh.
  2 - Demun yezo gebetual wede kideste kidusan now as I am typing this. Demun yezo sele egna yetayal. Bechegna likekahen bechegna amalag esu neew brother. yehtatiyat masteseria adergo akomew. Deme sayfes sereyet yelem. Yebeluy kidan like kahen be sereyet ken dem yezo bemetayet new yemimaledew.
  3 - ye hatiyatachin seryet yemenagegnew be ersu becha neew. Be ersu sira wede Ab megebat alen
  4 - le hawariat becha alemaledem, lantem lene neew. Hiyaw neew bekalem silemiamenutem engy belual
  5 - ye orthodox yeruk abatoch, St Paul said, liamaled zeweter yenoral, St John said Tebekachin and Jesus himself said, Bene bekul kalhone wede AB megebat ayechalem
  6 - Please give me one biblical figure, who prayed to Saints (departed)asked for milja.

  Bless you.

  ReplyDelete
 7. Kiburan Participants,

  1. The Holy Spirit is also mentioned in the Bible as doing INTERCESSION (MILJA) for us? Roman 8. So, my question is: why don't we call then the Holy Spirit as our AMALAJ?

  2. If your doctrine is desgined to call Jesus as our only amalaj and then refute the saints, you are in big trouble. I think that is our difference with the pents. Anyone who is making himself as a proponent of this ideology/beleif is either pente or agent of pente. So, I say MK has a reason to fight you. Why do you have to reject the Saints in oroder to accept Christ Jesus? I can assure you that satan is playing on you like a ball. Eventually, the devil is positioning you to throw you to hell. Now you deny the intercession of the saints, next time the devil will make you deny Christ Himself. We have seen it on people. Don't make the center of all your argument the refutal of the saints.

  I NEED ANSWER FROM THE AUTHOR, ተዋሕዶ, AND THE REST.

  ReplyDelete
 8. Nathan, let's debate this topic, but let's refrain from labeling people as Pente's just because they have different views. Let's discuss using the Bible as the judge.

  I think the words are confusing us. When we use the word "Amalaj" "Tebeka" "Like Kahnat" "Astaraki" we need to understand exactly how they are used and for whom.

  First let me make sure I understand your question. Do you at least accept that Jesus is your "like kahin"? Do you feel that you need additional like kahinat? Jesus's 'like kihinet' is not good enough for you? Why don't you present all the biblical evidence you know of regarding the intercession of saints and angels. What is the purpose of intercession? If you want to discuss, avoid being judgmental. Let's just discuss based on what the Bible says.

  ReplyDelete
 9. Hi Blogers,

  Can you responsed to my questions please? I will go to the end biblically if you can answer me. Tewahedo

  ReplyDelete
 10. dear Tewahedo, here are my short answers to your questions:

  1 የክርስቶስን አስታራቂነት/አዳኝነት ማነኛውም የቤተ ክርስቲያን መምህር የሚያስተምረው ትምህርት ነው እናንተ ምን ብላችሁ እንዲህ ቤተ ክርስቲያን እንደማታምንበት አድርጋችሁ ለማቅረብ የሞከራችሁት:: ክርስቶስን አዳኝ ካላልነው ያስታረቀን እርሱ አይደለም ካልን ምን ልንል ነው? ክርስቶስ ኢየሱስ አስታራቂያችን መደሃኒታችን አይደለም የሚሉ ሰዎችን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አይታችሁ ታውቃላችሁ ወይ? መልስ፥ አዎ ጌታችን አስታራቂያችን መድኃኒታችን እንዳልሆነ አድርገው የሚናገሩ አስተማሪዎች አጋጥመውኛል። አስታራቂነቱን/አማላጅነቱን እንደ ታሪክ ቢቀበሉትም አሁን ግን ያ አገልግሎት እንደሌለ ያስተምራሉ መጽሐፍ ቅዱስ ግን ከነሱ ጋር አይስማማም።

  2 ክርስቶስ አስታራቂነቱንና ምልጃውን እንዴት ታዮታላችሁ? የ ክርስቶስ የማዳን ስራ ለአንዴና ለመጪረሻ ጊዜ በመስቀል የተፈጸመ ነው:: የእኛ ሊቀ ካህን ግን ብዙ ጊዜ መግባት አላስፈለገውም ያን ባደረገ ጊዜ ያን ጊዜ ፈጽሞታልና:: የሚለውን የመጽሃፍ ቅዱስ ቃል እንዴት ታዩታላችሁ? እናንተ እንደምትሉ ክርስቶስ አሁን አብን ይለምናልን? ወይስ በመስቀል ባፈሰሰው ደመ ሁሉም ይታረቃሉ? መልሴ፥ ልክ ነህ ከ ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ጋር እስማማለሁ። እነሆ የኛ ጌታ አንዴ መስዋዕቱን ካቀረበ በሁዋላ አሁን በአብ ቀኝ አለ። አንዴ በፈጸመው የመስዋዕት አገልግሎት የዘለዓለም ሊቀ ካህናችን ሆኖ ለሚያምኑ ሁሉ እየታየላቸው ያድናቸዋል/ያማልዳቸዋል/ያስታርቃቸዋል/ይቆምላቸዋል። ሌላ መስዋዕት አያስፈልገውም፣ ሌላ ልመና አያስፈልገውም።

  3 ክርስቶስ አማላጅ ነው ስትሉ ምን ማለታችሁ ነው? አሁንም ክርስቶስ ይደክማል? ይጸልያል? ይለምናል? በምን መልኩ ክርስቶስ ይማልድናል? ለየትኛው ሃጢያት ይለምናል? መልሴ፥ አሁን አይደክምም፥ ከላይ እንዳልኩት ይታይልናል የሚለው በይበልጥ ይገልጸዋል።

  4. መጽሃፍ ቅዱስ የክርስቶስ ስጋውና ደሙ ከሃጢያት የሚያነጻን/ መታረቂያችን እንደሆነ ይነግረናል::1ኛ ዮሃ 1:7 ሮሜ 3፡25 1ኤፌ 1:7 እብ9፡14 :: ታዲያ ክርስቶስ በስጋው አስታራቂነው ስትሉ ስጋውንና ደሙን በመቀበል የሚደረገ መታረቅ ነው ወይስ አባት ሆይ ይቅር በላቸው ብሎ ለጠላቶቹ እንደለመነ ለሃዋርያቱም ምልጃን እንዳቀረበ ዛሬም ወደ አብ ይለምናል:: መልሴ፥ ቅዱስ ቁርባንን በተመለከተ ራሱን የቻለ ትልቅ ውይይት ስለሚጠይቅ አሁን አልገባበትም። ዛሬ ወደ አብ መለመን አያስፈልገውም። የኛ ጌታ በኩራት ያቀረበውን የህይወት መስዋዕትነት በማሳየት ለምናምን ሁሉ ከራሱ፥ ከአባቱ እና ከሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያስታርቀናል። አሁንም ለኛ ይታይልናል የሚለውን ቃል አወደዋለሁ።

  5 ከኦርቶዶክሳዊያን የቅርብም ይሁን የሩቅ አባቶች መካከል ብዙዎች ስላስታራቂነቱ ጽፈዋል:: ኢየሱስ አሁን አማላጅ ነው የሚል ጽሁፍ የጻፉ ግን የሉም ታዲያ እናንተ አማላጅ ነው የሚለውን ትምህርት ከየት አመጣችሁት? መልሴ፥ አማላጅ የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ጊዜ ተወስቶአል። እንደኔ እንደኔ ግን ጠበቃ፥ አስታራቂ፥ ሊቀ ካህን፥ የመሳሰሉት ቃላት አማላጅ ከሚለው ጋር አንድ ናቸው።

  6 ቅዱሳንን በተመለከተ በቤተ ክርስቲያን የተጋነኑ የሚመስሉ ነገሮች አንዳሉ አውቃለሁ:: ግን የቅዱሳን ምልጃ ትምህርት አባቶቻችን የፈጠሩት እንጂ እግዚአብሄር የማያውቀው ነው ብላችሁ ታስባላችሁ? መልሴ፥ እኔ በበኩሌ ስለ ቅዱሳን አማላጅነት አስፈላጊነትም ሆነ ጥቅም በመጽሐፍ ቅዱስ አጥጋቢ መረጃ አላገኘሁም። አንድ ነገር ግን አምናለሁ። በክርስቶስ አምናለሁ፣ ሞቱን እንደሞቴ በመቁጠር እሱ አየታየልኝ የመንግስቱ ወራሽ እንደምሆን አምናለሁ። ለምኑ ይሰጣችሁዋልም ስላለ ልመናየን ጸሎቴን ለሱ በቀጥታ አቀርባለሁ ምንም ቀርቶብኝ አላውቅም። እንግዲህ አንተ በቅዱሳን በኩል ካልመጣህ አልሰማህም ካለህ (እሱ ይልም እንጂ) የሚጠቅምህን ማድረግ ትችላለሁ። ወንድሜ፥ አሁን ልጆች እንጂ ባሪያዎች አይደላችሁም ሲል ለምናምን ሁሉ የልጅነት ጸጋን ሰጥቶናል። አባቴ ልንለው የፈለግነውን ልንለምነው አናፍርም። በነገራችን ላይ ከልብህ ልጅነትህን የምታምን ከሆነ የምስራች ልነግርህ አወዳለሁ፥ እነሆ የቅዱሱ ልጅ አንተም ከቅዱሳን ወገን ትመደባለህ (በአንተነትህ ሳይሆን በጸጋው በቸርነቱ)

  If you can answer the above questions, I will give you response. I want to know exactly whether you are looking for improvement of some exaggerated teachings or anti-orthodoxes. Even though there are some problems in the awaled metsahifits Orthodox Creed and Beliefe is biblical and true.

  ReplyDelete
 11. Kiburan Participants,

  Those of you who were claiming to know the "right" doctrine about AMALJINET, why don't you answer my questions. If you know the bible in its fullness, then it should not be difficult to answer these questions. Of course, you cannot answer them with kinchbchabi knowledge.

  The questions again are:

  1. The Holy Spirit is also mentioned in the Bible as doing INTERCESSION (MILJA) for us? Roman 8. So, my question is: why don't we call then the Holy Spirit as our AMALAJ?

  2. If your doctrine is desgined to call Jesus as our only amalaj and then refute the saints, you are in big trouble. I think that is our difference with the pents. Anyone who is making himself as a proponent of this ideology/beleif is either pente or agent of pente. So, I say MK has a reason to fight you. Why do you have to reject the Saints in order to accept Christ Jesus? I can assure you that satan is playing on you like a ball. Eventually, the devil is positioning you to throw you to hell. Now you deny the intercession of the saints, next time the devil will make you deny Christ Himself. We have seen it on people. Don't make the center of all your argument the refutal of the saints.

  I NEED ANSWER FROM THE AUTHOR, ተዋሕዶ, AND THE REST

  ReplyDelete
 12. ተዋህዶ (በእንግሊዘናው)July 12, 2011 at 10:23 PM

  ሰላም እውነት:

  መጀመሪያ ስለመለስህልኝ አመሰግንሃለሁ:: መልስህን የእናንተ ዓይነት ሰዎች መልስ ነው ብየ ልውሰደውና:: አሁን አንድ ማብራሪያ ብቻ እጠይቅሃለሁ::

  ኢየሱስ አማላጅ ነው ነገር ግን አይለምንም የሚል እምነት እንዳላችሁ ተረድቻለሁ::
  1 አማላጂ ማለት እኮ ትርጉሙ የሚለምን ማለት ነው:: በመጽሃፍ ቅዱስ አማላጅ ካልን የሚለምን ማለት ነው:: ታዲያ ኢየሱስ አይለምንም ካላችሁ ለምን አማላጅ የሚለውን ቃል ለመጠቀም ፈለጋችሁ:: አማላጅ ካላችሁት ይለምናል ማለት ነው:: እስኪ አብራራው::

  2 የእብራዊያን መልእክት ጸሃፊ ኢየሱስ ይታያል እያለ ሁለት ጊዜ ጽፎ እናገኛለን:: እንደ እናንተ ገለጻ ይታያል የሚለውን ይማልዳል በሚል ተርጉማችሁታል:: ለመሆኑ በእናንተ አረዳድ ኢየሱስ ይታያል ማለት ምን ማለት ነው? ምልጃ የሚለውን ቃል ለመጠቀም ያበቃችሁ ምንድን ነው? መታየትና መማለድስ ልዩነት አለው ወይስ አንድ ነው::

  3 የኢየሱስ ክርስቶስን አዳኘነት የማያውቅና ኦርቶዶክሳዊ አለ ካላችሁ መቶ ፐርሰንት ተሳስታችሃል:: የቤተ ክርስቲያን መጻህፍት በሙሉ ሰለ አዳኝነቱ ይናገራሉና:: ሌላው ቀርቶ ታምረማርያምና ውዳሴ ማርያም እንካን የሚናገሩት ኢየሱስ አዳኝ እንደሆነ ነው::

  4 ፐሮቴስታንቶች ሲባሉ በጣም ከሚገርሙኝ ነገር ራሳቸውን ለእግዚአብሄር ቅርብ እናኛን ደግሞ ሩቅ ማድረጋቸው ነው::ልጅ እንጅ ባሪያ አለመሆናችንን እናውቃለን:: መጽሃፍ ቅዱስን አንብበናል::

  ሰላም ሁኑ

  ReplyDelete
 13. Tewahedo, ትልቁ በሽታችን የመለያየትና የጎራ ጥማታችን ነው። አኔ እንደማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን የእግዚአብሔርን ሀሳብ ለመረዳት ተሳትፎ የማደርግ ግለሰብ ሳለሁ የግድ ከሆነ ቡድን ጋር ለመመደብ ጥርት መደረግ የለበትም። አስተያየትህን የጀመርከው ከሆነ ጎራ ውስጥ ካስገባኸን በሁዋላ ነው። እንደኔ እንደኔ ከላይ በምናወራው የአማላጅነት ውይይት ላይ ሁላችንም አንድ ገጽ ላይ ነው ያለነው። ነገር ግን መለያየትን ስለምንወድ የግድ ያንተው እንዲህ ለማለት ነው፤ የኔው እንዲህ ለማለት ነው በማለት የተለያዩ ነገሮች ለማድረግ መከራ እናያለን። ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን ላይ እንዳብራራው የጌታችንን ሊቀ ካህንነት ተረድተህ ከሆነ ከዛ የተለየ ሌላ አማላጅነት የለም።

  ለማንኛውም ለ ትዋሕዶ እና ለ ኔተን፥ በ መፅሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ላይ ስለምልጃ የተጻፈው እንደሚከተለው ነው፥

  ክርስቶስ «ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና - - - በእርሱ ወደ እግዝአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።» የእርሱ ምልጃ ግን እንደ እኛ ልመና አይደለም፤ ምክንያቱም ሀ) አንድ ጊዜ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ በማቅረቡ ለምእመናን ፍጹም ደኅንነት አስገኝቶላቸዋል ለ) ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ በሰማይና በምድር ሥልጣንን ሁሉ በመቀበል በአብ ቀን ተቀምጦአል፤ ሮሜ 8፥34 ዕብ 7፥25 1ዮሐ 2፥1። መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ለምዕመናን ያማልዳል፥ ይህም ለድካማቸው ኃይልን ይሰጣል ማለት ነው፤ ሮሜ 8፥26

  እንግዲህ ወንድሞች የቃላት ጨዋታን ወደጎን ትተን የእግዚአብሔርን ሀሳብ ለመረዳት እንሞክር። ለሁለታችሁም የአንድ ሳምንት ጊዜ ውሰዱና የእብራውያንን መልዕክት ሙሉውን በጽሞና እንድታነቡ እጋብዛችሁአለሁ። ጥቅሶችን ከመቆነጣጠብ ሙሉውን ሀሳብ መረዳት የግድ ነውና።

  Tehahedo, your 4th point is confusing. What are you trying to say? Did you already assume that I am a pente? That is really sad. Let's top being judgemental and discuss on the word of God.

  ReplyDelete
 14. Ewnet Sorry if my comment is offending.I am a person who needs to understand bible or any other concepts in depth not just neka neka. And your responses are more of protestantism than True way. Otherwise I don't blame any one including protestants. It is God Himself who will judge. But I have to speak out what I feel.


  The letter to Hebrew stated that Jesus is the master priest (Like Kahinat). He is like Kahinat but is not amalaje. It is not a matter of reading the bible it is a matter of understanding in a right way. For example I have read the Epistle to Hebrew many times and try to understand and make analysis for a couple of times. The concept is stating about the priesthood of Jesus not interceedation. Jesus is the Master Priest which means his blood/body which he has given to the world during crusification is still alive and help every one who believes in Him to get the kingdom of God.

  Just don't take a verse partially read the whole paragraph and understand the concept.

  ReplyDelete
 15. Tewahedo, I agree with you. I know you don't like it when I agree with you because you want me to be pente right? ይብላኝ ላንተ እንጂ ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ ማህበረ ቅዱሳን ቢቆጣጠራት እንኩዋ ጴንጤ አልሆንም። ወደ ቀደመ ነገራችን፦ Do you mind explaining what it means to you when the Bible says «ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና»? ጥቅሱን የት ላይ እንዳለ ካላወቅከው ነገረኝ። ቤተ ክርስቲያናችን የምትቀበለው የ መጽሐፍ ቅዱስ መዘገበ ቃላት እንዴት እንደተረጎመው አታስተውልውምን? በዚህ ትርጉም የምትስማማ ከሆነ እኔም በሌላ ትርጉም አላምንም። ወንድሜ ገና ሳታየኝ ፔንቴ አደርግከኝ እንጂ የምንናገረው ነገር አንድ ነው (የመረዳታችን ደረጃ በቲቂት ይለያይ እንጂ)። As far as I am concered if you agree with our Lord's high priesthood and that his priesthood works today, we are on the same page.

  ReplyDelete
 16. ሰላም እውነት
  የኢየሱስ ክርስቶስን ማንነት አይሁድ እንዳልተረዱት ሁሉ ክርስቲያኖች ነን የሚሉና እርሱን እንከተላለን የሚሉት ሳይቀር በልዩ ልዩ ምክነያት ተሰናክለውበታል:: ይህ መቸስ የሚጠፋህ አይመስለኝም:: እኛው ቤት እንካን ብንመጣ ኢየሱስ የሚለውን ስሙን መጥራት የ ፕሮቴስታንት ነው ብለው ስሙን ከማይጠሩት እላዋቂዎች አንስቶ ቃላትን ብቻ እያዩ ክብር ይግባውና ሊቀካህንነቱን እንደ አንድ ተራ የኦሪት ሊቀ ካህንነት በማየት አማላጅ ነው እስከሚሉት ድረስ እናያለን::
  ወደ ቁምነገሩ ስመጣ
  የክርስቶስ ሊቀ ካህንነት ምንድን ነው የሚለውን መመለስ ያስፈልጋል:: ያማልዳል የሚል ቃል ስላለ ያን ይዞ መሄድ አግባብ አይደለም ሃሳቡ አጻጻፉ ምከነያት ጽህፈቱ ምንድን ነው:: የመጽሃፉስ የቋንቋ አጠቃቀም ምንድን ነው የሚለውን ማየት ተገቢ ነው:: መቸስ የዚህ ዌብ ሳይት አዘጋጅ ቢያን ሰንበት ትምህርት ቤተ የገባ ሰው ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለኝ:: ታዲያ መጽሃፍ ቅዱስ እንዴተ እንደሚጠና እንካን ትንሸ ግንዛቤ ሊኖረዎ ይገባል ብለን እናምናለን::

  ስለኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ከዚህ ቀደም ከጻፍሁት ውስጥ ጥቂቱንና የአንተን ድንግዝግዝ ያለ ሁኔታ የሚያጠፋውን እዚሁ አምጥቸዋለሁ:: ፈቃድህ ከሆነ ሙሉውን እጽፈዋለሁ አንብብ የምታነሳቸውን ጥቅሶችም እያነሳን እንወያያለን::

  1. የኢየሱስ ቤዛነት፤መድሃኒትና አስታራቂነት፡
  ኢየሱስ ክርስቶስ በነጻ ያለምንም ክፍያ በደላችንን ደምስሶ ስላዳነን ቤዛ ይባላል። የሚበዥ ሲባልም ነጻ የሚያወጣ ማለት ነው። ለዚህ ነው ሁለቱ የክርስቶስ ተከታዮች ከትንሳዔው በሗላ እንዲህ ያሉት “እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ አድርገን ነበር፤ ደግሞም ከዚህ ሁሉ ጋር ይህ ከሆነ ዛሬ ሦስተኛው ቀን ነው።” ሉቃ 24፤21
  እነርሱ እንደመሰላቸው ሞቶ አልቀረም እስራኤልን ብቻ ሳይሆን ለአለሙ ሁሉ ቤዛ ሆኖ አድኖናል። ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን። ለዚህ ነው ኤፌ 1፤6 በደሙ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት ነው ያለው። እንዲሁም ቤዛነቱ ለሁሉም መሆኑን ሲያስተምረን እንዲህ አለ ቅዱሱ ሐዋርያ 1ኛ ጢሞ 2፤6 ራሱን ስለሁሉ ቤዛ ሰጠ። ራሱን ስለሁሉ ቤዛ የሰጠ እርሱ ክብርና ወዳሴ ለእርሱ ይሁን አሜን።
  ኢየሱስ ክርስቶስ ስላዳንን መድሓኒት ይባላል። ለዚህም ነው ሐዋርያትም ሆነ እኛ መድሓኒታችን እያልን ስሙን ስንጠራ የምንቀጽለው። በሙሉ ስሙ እኛ ኦርቶዶክሳዊያን ስንጠራው ጌታችን አምላካችንና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንለዋለን። ክብር ለእርሱ ይሁንና ኢየሱስ ክርስቶስ መድሓኒታችን ነው።
  ከእግዚአብሔር አብ ከመድኃኒታችንም ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን ቲቶ 1፤4 መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል። ቲቶ 2፤14 በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው። ቲቶ 3፤7
  ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ መድሓኒት ነው መድሃኒታችንም እንለዋልን። ታዲያ ለዚህ ነው ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በእርሱ ላይ የጽረፈትን ቃል ሰዎች ሲናገሩ የምታዝነው እርሱ ከሁሉ በላይ ሆኖ አድኖናልና።
  ኢየሱስ ክርስቶስ ያዳነን ተጣልተው የነበሩትን ሰውንና እግዚአብሔርን /አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን/ በማስታረቅ ነው። በመካከል የነበረውን የጠብ ግድግዳ ያፈረሰው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ስለሆነም ኢየሱስ ክርስቶስ ያዳነን ቤዛ ሆኖ፤ በመድሓኒትነቱ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቆ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋው ወራት አባት ሆይ ይቅር በላቸው እያለ ለጠላቶቹ ሳይቀር ጸሎትን አድርጓል ነገር ግን ይህን አለም ከእግዚአብሔር ጋር ያስታረቀው በሞቱ ነው።
  1ኛ ቆሮ 5፤19 እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ሆኖ አለሙን ያስታርቅ ነበርና።
  ቆላ 1፤21-23 በሐሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁ አሁን በስጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።
  ሮሜ 5፤6 ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለሃጢያታችን ሞቷልና
  ሮሜ 5፤10 ጠላቶቹ ሳለን ከእግዚአብሔር ጋራ በልጁ ሞት ታረቅን ይልቁንም ከታረቅን በሗላ በልጁ ሞት እንድናለን።
  1ጴጥ 2፤24 ለሐጢያት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በስጋው ሀጢያታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ። በመገረፉ ቁስል እኛ ተፈወስን
  እንግዲህ ይህንን ጥበብ ምን እንላለን። ራሱ ፈቅዶ ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቆናልና። ኢየሱስ ክርስቶስ ያስታረቀው ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ አልነበረም ህዝብንና አህዛብን ጭምር እንጂ
  ኤፌ 2፤14-16 ጥልን በመስቀሉ ገድሎ ከሁለታቸው አንድን አዲስ ፍጥረት ይፈጥር ዘንድ ነው እንጂ እንዲል። ህዝብንና አህዛብን አንደ አደረገ ሰውና መላዕክት በአንድ እንዲዘምሩ የሰታረቃቸው ምክነያቱ እርሱ እግዚአብሔር ወልድ ነው።
  የኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ማዳን አንድ ጊዜ የተደረገ የማይደገም ነው
  ኢየሱስ ክርስቶስ አንዴ ዓለሙን ሁሉ ስላዳነ በስሙ የሚያምኑ ሁሉ በእርሱ በኩል በተደረገው ቤዛነት ይድናሉ እንጂ እርሱ አሁን እንደገና እያንዳንዳችንን ለማዳን፤ለማስታረቅ ድካም የለበትም። ያው አንዴ በሆነው የማዳን ስራ የሚያምኑና ግን ክርስቶስ በተሰቀለበትና ዓለምን ባዳነበት ጊዜ ያደረገውን የድህነት ስራ ተካፋዮች ይሆናሉ።
  ዕብ 9፤26 ራሱን በመሰዋት ሀጢያትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጧልና። እንዳለ ይህም ማለት ዓለምን ለማዳን ኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠው አንድ ጊዜ ነው። እንዲሁም “እርሱ አንዱን መስዋዕት ለዘለዓለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ” ዕበ 10፤12 እነዚህ ጥቅሶችም ሆነ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የሚያስረዱን ነገር ቢኖር ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ እንደተገለጠ፤በተገለጠበት ጊዜ ያደረገው የድህነት ስራ ለዘለዓለም እንደሚኖርና በእርሱ የሚያምኑ ሞቱንና ትንሳኤውን ያመኑ በአጠቃላይ በክርስቶስ አዳኝነት የሚያምኑ ሁሉ ሲያምኑ የዚህ ድህነት ተሳታፊዎች እንደሚሆኑ። እርሱ ግን አሁን በክብር ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንደሚከበር ነው።
  ከላይ እንደተመለከትነው ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው፤ ፈጣሪ ነው፤ ጌታ ነው፤ መድሐኒት ነው። እንዲሁም ይቅር ሊል የሚችል ለመኮነንም/ለመፍረድ/ ስልጣን ያለው ሐጢያትን የሚያስተሰርይ የሚራራ ነው። ዛሬ ደግሞ ሌሎቹን እንመልከ

  ReplyDelete
 17. Continued..........
  2. ኢየሱስ ክርስቶስ የሐዲሲ ኪዳን ሊቀ ካህን ነው፦ ኢየሱስ ክርስቶስ የሐዲስ ኪዳን ሊቀ ካህን /ካህናት አለቃ/ ነው። የተለዩ የእግዚአብሔር ካህናት ስላሉ የእነርሱ አለቃ መሆኑን ሲያመለክት ክርስቶስን ሊቀ ካህናት ይለዋል። የኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህንነት እንዴት ነው? የኢየሱስ ሊቀ ካህንነት እንደ ኦሪት ሊቃነ ካህናት ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ ስለኢየሱስ ሊቀ ካህንነት ምን ይላል የሚለውን እንመለከታለን።
  መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቶስን ሊቀ ካህነነት ከሌዋዊያን ሊቃነ ካህናትና ከሰላም ንጉስ ከመልከ ጼዴቅ ሊቀ ካህንነት ጋር አነጻጽሮ ይነግረናል።

  የመልከ ጼዴቅና የኢየሱስ ክርስቶስ ካህንነት
  - መልከ ጼዴቅ ፍጹም ጻድቅ የነበረ፤ ጻድቁ አብርሃም ከእርሱ የተባረከለት ካህን ነበር።ዕብ 7፤1-3፣ ዘፍ 14፤17-20 ኢየሱስ ክርስቶስም ፍጹም ጻድቅ ሁሉን የባረከ የሚባርክ ነው።
  - መልከ ጸዴቅ ሹመቱ ለዘለዓለም ነው፤ የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ሹመት የሚያልፍ የሚተካ ነበር ለምሳሌ ዘሁ 20፤22 ላይ እንደምናገኘው የአሮን ሊቀ ካህንነት ለልጁ ለአላዛር ሲሰጥ እናገኛለን። የመልከ ጸዴቅ ሊቀ ካህንነት ግን ለዘለዓለም ነበር። የኢየሱስ ክርስቶስም ሊቀ ካህንነት ለዘለዓለም ያለ የሚኖር ነው በዚህ ጊዜ ያልፋል አይባልም። ዕበ 7፤ 1-3፤መዝ 109፤4 ፡ ዕብ 5፤6
  - መልከ ጸዴቅ ሹመቱን ከማንም አላገኘውም። ሌሎች ሊቃነ ካህናት በሰው ይሾሙ ነበር። መልከ ጸዴቅ ግን ሹመቱን ከእግዚአብሔር አግኝቶታል እንጂ ማንም አልሾመውም። ኢየሱስ ክርስቶስም ሹመቱ ከሰማይ ከአባቱ ዘንድ የሆነች ናት እንጂ ሰው ሾመው አይባልም።
  - መልከ ጸዴቅ ያቀረበው መስዋዕት ህብስትና ጽዋ ነበር ዘፍ 14፤17-20 ኢየሱስ ክርስቶስም ለሐዲስ ኪዳን መስዋዕት ይሆነን ዘንድ ሰርቶ ያሳየን ስጋውንና ደሙን ነው።ማቴ 26፤57-65
  መልከ ጸዴቅ የክርስቶስ ምሳሌ ነው። በመሆኑም መልከ ጸዴቅን ከክርስቶስ ጋር አነጻጽሮ ሐዋርያው ብዙ ተናግሯል። በአንጻሩ የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ድካም ያለባቸው በመሆናቸው በአሉታዊ ጎኑ ከክርስቶስ ሊቀ ካህንነት ጋር አነጻጽሮ እንደሚከተለው ያቀርባቸዋል።
  የኦሪት ሊቃነ ካህናት እና የኢየሱስ ሊቀ ካህንነት፡
  የኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህንነት ዘለዓለማዊ ነው ነገር ግን አንድ ጊዜ ራሱን መስዋዕት አድርጎ ባቀረበ ጊዜ የተፈጸመ ነው። መስዋዕቱ ዛሬ ያው ነው ለሚያምኑበት ሁሉ ያለ የማያልፍ ነው ሐዋርያው የኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህንነት ከአይሁድ ሊቀ ካህንነት የተለየ እንደሆነ ሲናገር ዕብ 7፤27 እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።
  - የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ያቀርቡ የነበረው የእንስሳትን ደም ነበር ኢየሱስ ግን ያቀረበው የራሱን ደም ነው
  የኦሪት ሊቃነ ካህናት ወደ እግዚአብሔር እየለመኑ ሐጢያትን ያስተሰርዩ ነበር። በተለይም በአመት አንድ ጊዜ ካህኑ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ደም ይዞ በመግባት ስለህዝቡና ስለራሱ ጸሎት ያቀርባል። ዘጸ 30፤10 ይህንን አንዱ ሊቀ ካህን ሲሞት በሌላው እየተካ መስዋዕትን ያቀርባል። ዕብ 9፡7 በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፥ እርሱም ሰለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ስሕተት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤
  ለዚህ ነው ሐዋርያው ዕብ 9፤25 12 የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም። ያለው።በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎች ወይም በጥጆች ደም አይደለም። የሌላውን ደም ሳይሆን የራሱን ደም ነው ያቀረበው። በእንስሳት ደም አይደለም ዓለም የዳነው በእርሱ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም እንጂ።
  - የአይሁድ ሊቃነ ካህናት በልመና በእንስሳት ደም ሐጢያትን ያስተሰርዩ ነበር ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ በደሙ በራሱ ነው ሐጢያትን ያስተሰረየው
  ዕብ 1፤33 እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤
  - የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ሞትና እርጂና ነበረባቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ለሊቀ ካህንነቱ ሽረት /መለወጥ/ የለበትም
  የኦሪት ሊቃነ ካህናት ድካም ነበረባቸው ሐጢያት ይሰራሉ በሌላ በኩል ሰዎች ስለሆኑ ለዘለዓለም መኖር አይችሉም። ኢየሱስ ክርስቶስ ግን እርሱ ከሐጢያት የራቀ ፍጹም ነው እርሱም ለዘለዓለም የሚኖር የማያልፍ ነው። ዕብ 7፡28 ሕጉ ድካም ያላቸውን ሰዎች ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕግ በኋላ የመጣ የመሐላው ቃል ግን ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ይሾማል።
  - የአይሁድ ሊቃነ ካህናት በእየጊዜው እግዚአብሔር ይቅር እንዲል መለመን ነበረባቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ግን አንድ ጊዜ ባደረገው የመስቀል ስራ /ሊቀ ካህንነት/ አዳነን
  ዕብ 9፤26-27 ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤ እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል።
  ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ያደረገው የማዳን ስራ እስከዘለዓለም በስሙ ለሚያምኑ ሁሉ የተከፈለ ዋጋ ነው። ዛሬ በቤተ የሚሰዋው መስዋዕት በእለተ አርብ ከፈሰሰው ደሙና ከተቆረሰው ስጋው ጋር አንድ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በአምላክነቱ ፤ በሊቀ ካህንነቱ ዛሬም ከሞተ ስራችን ነጻ ያደርገናል። ደሙ ከሐጢያት ሁሉ የነጻልና።1ኛ ዮሐ 2፤1 ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።

  ReplyDelete
 18. የቀጠለ
  2. ኢየሱስ ክርስቶስ የሐዲሲ ኪዳን ሊቀ ካህን ነው፦ ኢየሱስ ክርስቶስ የሐዲስ ኪዳን ሊቀ ካህን /ካህናት አለቃ/ ነው። የተለዩ የእግዚአብሔር ካህናት ስላሉ የእነርሱ አለቃ መሆኑን ሲያመለክት ክርስቶስን ሊቀ ካህናት ይለዋል። የኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህንነት እንዴት ነው? የኢየሱስ ሊቀ ካህንነት እንደ ኦሪት ሊቃነ ካህናት ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ ስለኢየሱስ ሊቀ ካህንነት ምን ይላል የሚለውን እንመለከታለን።
  መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቶስን ሊቀ ካህነነት ከሌዋዊያን ሊቃነ ካህናትና ከሰላም ንጉስ ከመልከ ጼዴቅ ሊቀ ካህንነት ጋር አነጻጽሮ ይነግረናል።

  የመልከ ጼዴቅና የኢየሱስ ክርስቶስ ካህንነት
  - መልከ ጼዴቅ ፍጹም ጻድቅ የነበረ፤ ጻድቁ አብርሃም ከእርሱ የተባረከለት ካህን ነበር።ዕብ 7፤1-3፣ ዘፍ 14፤17-20 ኢየሱስ ክርስቶስም ፍጹም ጻድቅ ሁሉን የባረከ የሚባርክ ነው።
  - መልከ ጸዴቅ ሹመቱ ለዘለዓለም ነው፤ የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ሹመት የሚያልፍ የሚተካ ነበር ለምሳሌ ዘሁ 20፤22 ላይ እንደምናገኘው የአሮን ሊቀ ካህንነት ለልጁ ለአላዛር ሲሰጥ እናገኛለን። የመልከ ጸዴቅ ሊቀ ካህንነት ግን ለዘለዓለም ነበር። የኢየሱስ ክርስቶስም ሊቀ ካህንነት ለዘለዓለም ያለ የሚኖር ነው በዚህ ጊዜ ያልፋል አይባልም። ዕበ 7፤ 1-3፤መዝ 109፤4 ፡ ዕብ 5፤6
  - መልከ ጸዴቅ ሹመቱን ከማንም አላገኘውም። ሌሎች ሊቃነ ካህናት በሰው ይሾሙ ነበር። መልከ ጸዴቅ ግን ሹመቱን ከእግዚአብሔር አግኝቶታል እንጂ ማንም አልሾመውም። ኢየሱስ ክርስቶስም ሹመቱ ከሰማይ ከአባቱ ዘንድ የሆነች ናት እንጂ ሰው ሾመው አይባልም።
  - መልከ ጸዴቅ ያቀረበው መስዋዕት ህብስትና ጽዋ ነበር ዘፍ 14፤17-20 ኢየሱስ ክርስቶስም ለሐዲስ ኪዳን መስዋዕት ይሆነን ዘንድ ሰርቶ ያሳየን ስጋውንና ደሙን ነው።ማቴ 26፤57-65
  መልከ ጸዴቅ የክርስቶስ ምሳሌ ነው። በመሆኑም መልከ ጸዴቅን ከክርስቶስ ጋር አነጻጽሮ ሐዋርያው ብዙ ተናግሯል። በአንጻሩ የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ድካም ያለባቸው በመሆናቸው በአሉታዊ ጎኑ ከክርስቶስ ሊቀ ካህንነት ጋር አነጻጽሮ እንደሚከተለው ያቀርባቸዋል።
  የኦሪት ሊቃነ ካህናት እና የኢየሱስ ሊቀ ካህንነት፡
  የኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህንነት ዘለዓለማዊ ነው ነገር ግን አንድ ጊዜ ራሱን መስዋዕት አድርጎ ባቀረበ ጊዜ የተፈጸመ ነው። መስዋዕቱ ዛሬ ያው ነው ለሚያምኑበት ሁሉ ያለ የማያልፍ ነው ሐዋርያው የኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህንነት ከአይሁድ ሊቀ ካህንነት የተለየ እንደሆነ ሲናገር ዕብ 7፤27 እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።
  - የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ያቀርቡ የነበረው የእንስሳትን ደም ነበር ኢየሱስ ግን ያቀረበው የራሱን ደም ነው
  የኦሪት ሊቃነ ካህናት ወደ እግዚአብሔር እየለመኑ ሐጢያትን ያስተሰርዩ ነበር። በተለይም በአመት አንድ ጊዜ ካህኑ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ደም ይዞ በመግባት ስለህዝቡና ስለራሱ ጸሎት ያቀርባል። ዘጸ 30፤10 ይህንን አንዱ ሊቀ ካህን ሲሞት በሌላው እየተካ መስዋዕትን ያቀርባል። ዕብ 9፡7 በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፥ እርሱም ሰለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ስሕተት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤
  ለዚህ ነው ሐዋርያው ዕብ 9፤25 12 የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም። ያለው።በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎች ወይም በጥጆች ደም አይደለም። የሌላውን ደም ሳይሆን የራሱን ደም ነው ያቀረበው። በእንስሳት ደም አይደለም ዓለም የዳነው በእርሱ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም እንጂ።
  - የአይሁድ ሊቃነ ካህናት በልመና በእንስሳት ደም ሐጢያትን ያስተሰርዩ ነበር ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ በደሙ በራሱ ነው ሐጢያትን ያስተሰረየው
  ዕብ 1፤33 እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤
  - የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ሞትና እርጂና ነበረባቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ለሊቀ ካህንነቱ ሽረት /መለወጥ/ የለበትም
  የኦሪት ሊቃነ ካህናት ድካም ነበረባቸው ሐጢያት ይሰራሉ በሌላ በኩል ሰዎች ስለሆኑ ለዘለዓለም መኖር አይችሉም። ኢየሱስ ክርስቶስ ግን እርሱ ከሐጢያት የራቀ ፍጹም ነው እርሱም ለዘለዓለም የሚኖር የማያልፍ ነው። ዕብ 7፡28 ሕጉ ድካም ያላቸውን ሰዎች ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕግ በኋላ የመጣ የመሐላው ቃል ግን ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ይሾማል።
  - የአይሁድ ሊቃነ ካህናት በእየጊዜው እግዚአብሔር ይቅር እንዲል መለመን ነበረባቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ግን አንድ ጊዜ ባደረገው የመስቀል ስራ /ሊቀ ካህንነት/ አዳነን
  ዕብ 9፤26-27 ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤ እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል።
  ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ያደረገው የማዳን ስራ እስከዘለዓለም በስሙ ለሚያምኑ ሁሉ የተከፈለ ዋጋ ነው። ዛሬ በቤተ የሚሰዋው መስዋዕት በእለተ አርብ ከፈሰሰው ደሙና ከተቆረሰው ስጋው ጋር አንድ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በአምላክነቱ ፤ በሊቀ ካህንነቱ ዛሬም ከሞተ ስራችን ነጻ ያደርገናል። ደሙ ከሐጢያት ሁሉ የነጻልና።1ኛ ዮሐ 2፤1 ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።

  ReplyDelete
 19. የቀጠለ

  3. መካከለኛ፤ኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኛ ተብሏል ሆኗልም። የኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኝትም ስለሁለት ነገሮች ነው።
  ሀ. ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ሲሆን ሰው በመሆኑ መካከለኛ ተብሏል። ኢየሱስ ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን አምላክ እየተባለ በወለድነቱ ይከበር ይመለክ የነበረ እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔርነቱን ካላይ እንደተመለው ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ ከመምጣቱ በፊት እግዚአብሔር ነው፤ በስጋ ማርያም ከመጣም በሗላ እርሱ እግዚአብሔር ነው። እርሱ እግዚአብሔር ቢሆንም ግን የሰውን ገንዘብ ገንዘብ አድርጓል ማለትም ሰው ሆኗል። ኢየሱስ ሰው ብቻ አይደለም አምላክም ጭምር ነው እንጂ። አስቀድመን እንደተናገርነው ኢየሱስ ፍፁም ሰው ፍጹም አምላክ ነው። በክርስቶስ ስጋ የመለኮትን ባህሪይ ገንዘብ አደረገ፤ መለኮትም የሰውነትን ባህርይ ገንዘብ አደረገ። በዚህም መሰረት ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነትን ከአምላክነት ጋር አዋህዶ ስለያዘ መካከለኛ ተብሏል። 1ጢሞ 2፤5 አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ደግሞ መካከለኛ አንድ አለ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ራሱን ስለሁሉ ቤዛ ሰጠ።

  ለ. በሰውና በእግዚአብሔር፤ በህዝብና በአህዛብ፤ በሰውና በመላእክት መካከል የነበረውን የጸብ ግድግዳ አፍርሶ ራሱን ስለሁሉ ቤዛ አድርጎ በማስታረቁ መካከለኛ ተብሏል።
  አስቀድመን እንደተናገርነው ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው አለምን ለማዳን ነው። ዓለምን ማዳን ሲባልም ቆሽሾና ረክሶ ከእግዚአብሔር ጋር ተጣልቶ የነበረውን አለም አድኖ ከአባቱና ከራሱ ጋር አስታርቆ ለመሄድ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክንና ሰውን ብቻ ሳይሆን ያስታረቀው በእግዚአብሔር የሚያምኑ የነበሩ ህዝብ የተባሉና በእግዚአብሔር የማያምኑ አህዛብ በእርሱ በማመናቸው ምክነያት ለድህነት የሚበቁበትን መንገድ ሊከፍት ስለመጣ መካከለኛ ተብሏል። ኢየሱስ መካከለኛ ነው ስንል በመካከል ያለውን ጸብ በተጣሉት መካከል ገብቶ በማስታረቁ፤ ጠቡን በማስወገዱ ነው።
  እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ኤፌ 2፤14-16 በዚህ ጥቅስ እንደምናየው ኢየሱስ ክርስቶስ በመካከል ያለውን ልዩነት ያጠፋው በመሞቱ እንደሆነ ነው። ስለዚህ ለህዝብና ለአህዛብ ሞቶ እነርሱን በአንድነት ያለምንም ልዩነት ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንዲገቡ ስላዘጋጃቸው መካከለኛው ተብሏል ሆኗልም። 1ጢሞ 2፤5 አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ደግሞ መካከለኛ አንድ አለ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ራሱን ስለሁሉ ቤዛ ሰጠ።

  ReplyDelete
 20. Tewahedo, ቃለ ህይወት ያሰማልን። I agree with 99% of what you said, which makes me confortable to declare that we are on the same page (brothers in Christ).

  To close the 1% gap, we just need to better explain the use of the word መማለድ as it applies to Christ. Obviously the Bible usess this word for Christ even after his reserection (in the past, present and future). So we need to explain that better. የኛ ጌታ ዛሬም ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነው። የኛ ጌታ ዛሬም ከድንግል ማርያም የነሳውን የሰው ስጋ እንደለበሰ በአብ ቀኝ አለ። ይሄንም ጥሩ አድርገህ ገልጸኸዋል ግን በደንብ እናስበው እስኪ። እዚህ በምድር የነበረው ጌታ ካረገ በሁዋላ ማንነቱ ተለውጦአል? መለኮቱ ሰውነቱን ውጦታል ? የሰውነት ባህርይው ተቀንሶአል? ከእርገት በፊትና ከእርገት በሁዋላ ያለው ጌታችን ልዩነቱ ምንድን ነው? የመሳሰሉትን ጥያቄዎችም ከቃሉ አንጻር በደንብ ብናብሰለስላቸው ጥሩ ነው።

  ሌላው «ዛሬ በቤተ ክርስቲያን የሚሰዋው መስዋዕት» ያልከው ትንሽ ግር ይላል። መስዋዕቱ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ በጌታችን ተፈጽሞአል አላልንም? በቤተ ክርስቲያናችን ምስጢረ ቁርባን እሳተፋለሁ እጅግም ደስ ከሚለኝ ምስጢር አንዱ ነው። በቅዱስ ቁርባን ስሳተፍ ግን ጌታየ ለኔ የሞተውን ሞት በማሰብ የበለጠ አንድነት ለመፍጠር እንጂ ከዛ የዘለለ ትርጉም ሰጥቼው አላውቅም። «ስጋየን የበላ ደሜንም የጠጣ የዘላለም ህይወት አለው - - » የሚለውን ቅዳሴ አስቀድሶ ስጋና ደሙን መቀበል ማለት ነው ብለን እንዴት እንደተረጎምነው አይገባኝም። I think this contributes to about 0.8% of the 1% gap we have. perhaps this is a little too complicated for the discussion in this topic. ..

  God bless you

  ReplyDelete
 21. Tewahedo,

  Your analysis is great. However, you still need to tie it together and make a conclusion. I have not seen a clear answer as to whether we can call Jesus a Mediator or Intercessor.

  My understanding is that AMALAJINET is divided into two: yeAmilak amalajinet and yekidusan amalajinet. Because of the work He did on the cross, Christ Jesus is still the Mediator for eternity. This is because His work of salvation is still alive and is the only way for one to get salvation. Even if Jesus Christ has reconciled the world with God, it does not mean that every human being has been recociled with God. For example, if a non-believer wants to reconcile with God and get salvation, he can only get that by coming (meaning accepting) through Christ. Believers also get perpetual reconciliation with God by taking the Flesh and Blood of Christ, which our church serves after the formal worship or liturgy.

  Also, if we accept that Christ Jesus is the High Priest for eternity, He cannot have that title without doing the work that the title suggests. I agree with you that His work is the one He did on the cross. Therefore, Christ is still the Mediator through the work He did on the cross.

  The intercession of the saints is simply a prayer that they pray on our behalf. It is like what Moses and Abreham did.

  My question is: what is your understanding of the difference between intercession and mediation (mamaled ena mastarek)?

  ReplyDelete
 22. ሰላም ወንድም ናታን:

  እኔ ከላይ ሊቀ ካህን በሚለው ስር እንደገለጽሁት ኢየሱስ ክርስቶስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመስቀል ባደረገው ቤዛነት የሚያምኑበት ሁሉ ይድናሉ:: የክርስቶስ የመስቀል ማዳን ስራ ደግሞ አዳኝ ስለሆነ የሚገኝ እንጂ አማላጂ ሰለሆነ አይደለም::

  የኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ማዳን አንድ ጊዜ የተደረገ የማይደገም ነው
  ኢየሱስ ክርስቶስ አንዴ ዓለሙን ሁሉ ስላዳነ በስሙ የሚያምኑ ሁሉ በእርሱ በኩል በተደረገው ቤዛነት ይድናሉ እንጂ እርሱ አሁን እንደገና እያንዳንዳችንን ለማዳን፤ለማስታረቅ ድካም የለበትም። ያው አንዴ በሆነው የማዳን ስራ የሚያምኑና ግን ክርስቶስ በተሰቀለበትና ዓለምን ባዳነበት ጊዜ ያደረገውን የድህነት ስራ ተካፋዮች ይሆናሉ።
  ዕብ 9፤26 ራሱን በመሰዋት ሀጢያትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጧልና። እንዳለ ይህም ማለት ዓለምን ለማዳን ኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠው አንድ ጊዜ ነው። እንዲሁም “እርሱ አንዱን መስዋዕት ለዘለዓለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ” ዕበ 10፤12 እነዚህ ጥቅሶችም ሆነ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የሚያስረዱን ነገር ቢኖር ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ እንደተገለጠ፤በተገለጠበት ጊዜ ያደረገው የድህነት ስራ ለዘለዓለም እንደሚኖርና በእርሱ የሚያምኑ ሞቱንና ትንሳኤውን ያመኑ በአጠቃላይ በክርስቶስ አዳኝነት የሚያምኑ ሁሉ ሲያምኑ የዚህ ድህነት ተሳታፊዎች እንደሚሆኑ። እርሱ ግን አሁን በክብር ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንደሚከበር ነው።

  ታዲያ ይህንን ካልን ኢየሱስ ዛሬ በህይወታች ድረሻው የለም ወይ ይላሉ አንዳንድ ሰዎች:: ክርስቶስ አማላጅ ካልሆነ በህይወታች ድርሻ የለውም ማለት ነው የሚሉ ሰዎች ክርስቶስ መመለክ የለበትም የሚል ሃሳብ ያላቸው ይመስላል::

  የኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህንነቱ ማማለድን ሳይሆን መማርን ይቅር ማለትን ሃጢያትን ማስተስረይን የሚያሳዩ ናቸው::
  እብ 2: 17᎐18 ስለዚህ የሕዝብን ኃጢአት ለማስተስረይ፥ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ የሚምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን፥ በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው። እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና።

  የዚህን ጥቅስ መልእክት እስኪ እንመልከተው:
  ሊቀ ካህንነቱ
  1 ሃጢያትን ለማስተረይ ነው ይላል::
  2 ለመማር/የሚመርና የታመነ ነው ይላል::
  3 የሚፈተኑትን ይቅር ማለት /ማገዝ ይችላል

  ታዲያ በራሱ ነው ማስተስረይ መማር ይቅርማለትና መርዳት የሚችለው እንጅ አማልዶ አይደለም::

  ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ይቅርባ እንጅ አሁን አማላጅ አይባልም ራሱ እንደተናገረው አይለምንም:: ካልለመነ ደግሞ አማላጅ አይባልም::

  ቅዱሳን መላእክትም ሆነ ቅዱሳን ሰዎች ያማልዳሉ ስለኛ ይለምናሉ:: የቅዱሳን ምልጃ በሁለት እናየዋለን::

  1 ቃል ኪዳናቸው
  2 የሚያደርጉት ልመና

  አንዳንድ ሰዎች ቅዱሳን ሳያውቁን እንዴት ይለምኑልናል ይላሉ:: የዚህ ጽሁፍ ጸሃፊ ለማያውቃቸው ሰዎች በወል ይጸልያል ታዲያ እግዚአብሄር አይሰማምን:: እግዚአብሄረ ነው ጸሎቱን የሚሰማው:: በተለይም ደግሞ የ ቅዱሳን ቃል ኪዳን በመጽሃፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ የተነገረ ነው:: ለማነኛውም ይህ ራሱን የቻል ሰፊ ትንታኔ የሚሰጥበት ስለሆነ ወደ እርሱ አልገባም::  ኢየሱስ የመጣበት ዓላማ
  ሀ ለማዳን ነው
  1. ቤዛ ሆኖ
  2. በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ገብቶ ነው
  ለ ምሳሌ/መምህር ሊሆነን ነው
  ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቶ ስላዳነን የተሰጠው ቅጽል ስም፡
  1. ቤዛ/መድሓኒት ሆነ ነውም
  2. አስታራቂ ተባለ
  3. ሊቀ ካህን ተባለ
  4. መካከለኛ ተባለ
  ክርስቶስ ባህርይው፡
  1. አምላክ ነው
  2. የእግዚአብሔር ልጀ ነው
  3. እግዚአብሔር ነው
  4. የጌቶች ጌታ የነገስታትም ንጉስ ነው
  ኢየሱስ ክርስቶስ ስልጣኑ
  1. ሐጢያትን ያስተሰርያል
  2. ይራራል ይቅር ይላል
  3. ይቀጣል ይፈርዳል
  ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ ምን ይፈልጋል?
  - ሊመለክ ይገባዋል
  - በቃሉ ልንኖር ይገባናል
  ሰዎች ስለምን በእርሱ ይሰናከላሉ

  _ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ራሱን አላከበረም፡
  _በእምነት ስለማይቀበሉት

  ሰላም ሁኑ

  ReplyDelete
 23. Thanks Nathan and Tewahedo for mature discussions. I think Tewahedo agrees with all of the following:

  1) ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን ይታይልናል
  2) ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን ይከራከርልናል
  3) ኢየሱስ ክርስቶስ የዘለዓለም ሊቀ ካህናችን ነው
  4) ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ይቆማል
  5) ኢየሱስ ክርስቶስ በሰውና በእግዚአብሔር መካከለኛ ነው (የኛን ሥጋ በመልበሱ)
  6) ኢየሱስ ክርስቶስ ለምናምን ሁሉ እንደጠበቃችንም ነው

  የ Tewahedo ችግር ማማለድ ከሚለው ቃል ላይ ነው። ለኛ ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራል፤ ስለኛ የሚማልደው ወዘተ የሚሉትን የእግዚአብሔር ቃላት ምን ሊያደርጋቸው እንዳሰበ አልገባኝም። በነገራችን ላይ ጌታችን (ሥጋን በመልበሱ) አሁንም እንደሚጸልይልን የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እና የቀደሙት አባቶቻችን ምስክርነት በርካታ ናቸው። እነሱንስ ምን ብሎ ሊተረጉማቸው አስቦ ይሆን? የኛ ጌታ አሁንም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ ቢናገረውም በደንብ ያስተዋለው መስሎ አይታየኝም።

  God bless

  ReplyDelete
 24. ሰላም እውነት

  በመጽሃፍ ቅዱስ ላይ ላአንተ እንደመሰሉህ ክርስቶስ ይማልዳል የሚሉ ቃሎችን በጥንቃቄ አጥንቻለሁ ምን አልባት የመጽሃፍ ቅዱስን ሃሳብና ምስጢር ለመረዳት ፈቃድ ካለን ቃሎቹ ስለምልጃ አይናገሩም:: የሆነው ሆኖ ግን ስለ እራሴ ከመናገርህ ይልቅ እነኤ የጻፍሁትን አይተው ሰዎች ስለእኔ ግንዛቤ ቢወስዱ ይሻል ነበር አንተ ይህንን ያምናል ይህንን አያምንም ከማለት::

  ስለዚህ አሁንም ለጻፍከው በደፈናው ለመመለስ ያክል

  1) ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን ይታይልናል : ይታያል የሚለውን እናንተ ይማልዳል ብላችሁ በምትተረጉሙበት መልኩ አልቀበለውም
  2) ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን ይከራከርልናል:መከራከርን እናንተ ከአብ እንደ መለመን አላምነውም በአንጻሩ እግዚአብሄር ለልጆቹ ይከራከራል:: በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄር ከስይጣን ጋር ስለ እያሱ እንደተከራከረ በሃዲስ ኪዳንም እግዚአብሄር ልጆቹን ለሰይጣን አሳልፎ ላለመስጠት ይገስጽልናል::
  3) ኢየሱስ ክርስቶስ የዘለዓለም ሊቀ ካህናችን ነው፦ አወ ኢየሱስ ሊቀ ካህናችን ነው:: ሊቀ ካህንነቱ ግን በእግዚአሄር በሆነው ነገር ሁሉ ይቅር ለማለትና ለመማር እንጅ ለመለመን አይደለም::
  4) ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ይቆማል: መጽሃፍ አንድን መስዋእት አቅርቦ ለዘለዓለም በግርማው ቀኝ ተቀመጠ ይላል:: ተቀመጠ ያለውን እንዴት ቆመ እልሃለሁ:: ስራው ግን ለዘለአለም የቆመ ነው::
  5) ኢየሱስ ክርስቶስ በሰውና በእግዚአብሔር መካከለኛ ነው (የኛን ሥጋ በመልበሱ)፡ ኢየሱስ እኛን ስለማዳኑና ስጋ ስለመልበሱ መካከለኛ ነው ያማለት ግን ሙሴና አብርሃም መካከለኛ እንደሆኑት አይደለም::
  6) ኢየሱስ ክርስቶስ ለምናምን ሁሉ እንደጠበቃችንም ነው: አወ እግዚአብሄር ጠበቃችን ነው ደሙ ከሃጢያት ሁሉ ያድናልና ደሙ መተማመኛችን ነው:: ጥብቅናው መፍረድ እንደማይችል ሰው ለመከራከር አይደለም::

  ReplyDelete
 25. የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።

  እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ። ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤


  ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።

  እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ።

  እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።


  የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።

  እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።

  ReplyDelete
 26. Hi ato እውነት,


  "አሁንም እንደሚጸልይልን " - I fully and completely reject this kind of thinking and faith. To whom does he pray? This is haram for me. Do you think we know Chirst now as we knew Him during his days on earth? Prayer is the work of the saints. He mediates only through the work He did on the Cross period. That is what the Bible teaches and that is what our church believes. No single church father ever taught that Christ prays for us in heaven. I would say that this is not only menfekina but also completely diabolic. With that belief, you are making Chrsit to be inferior to God the Father and the Holy Spirit.

  ReplyDelete
 27. Dear Orthodox, Nathan, Ewnet and others, May the Holy Spirit help us to know our lord Jesus more and more. It is okay to have different view. we are here to learn from each other.  ይታይልናል የሚለውን አንዴት ትረዳዋለህ
  ሊቀ ካህናት ስራው ምንድን ነው፣ ዛሬስ ለኛ ለክርስቲያኖች ያለው ጥቅም
  ስለኛ ያማልዳል የሚለው ( በግሪኩ) ትርጉሙ ምን ማለት
  በርሱ በኩል ወደ ኣብ መግባት ኣለን የሚለውን ለክርስቲያኖች ምን ማለት ነው
  ሀጥያት አናረጋለን፣ ደም ሳይፈስ ስርየት የለም ማለት ምን ማለት ነው
  ደሙ ኣሁንም ይጮሀል ምን ማለት ነው፧
  ጠበቃችን ይለዋል ደግሞ ለክርስቲያኖች ነው የተነገረው ምን ማለት ነው
  ዋስ ይለዋል ምን ማለት ነው
  መሰላል የተባለው አርሱ ነው ዮሐ ፩፥፭፪ ምን ማለት ነው
  መካከለኛነቱ ለኛ ያለው ፋይዳ (ለዳነው) ምንድን ነው

  ReplyDelete
 28. እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን።
  ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን።
  እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።
  በእኛ ማለት በእኔና በስልዋኖስ በጢሞቴዎስም በመካከላችሁ የተሰበከ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አዎንና አይደለም አልነበረም፥ ነገር ግን በእርሱ አዎን ሆኖአል። እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ አዎን ማለት በእርሱ ነውና፥ ስለዚህ ለእግዚአብሔር ስለ ክብሩ በእኛ የሚነገረው አሜን በእርሱ ደግሞ ነው።
  በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።
  በእርሱም ዘንድ ባለ እምነታችን በኩል በመታመን ድፍረትና መግባት በእርሱ አለን።
  ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።
  በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማርያም ያገኛል።
  ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።


  የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።

  እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።

  ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

  ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።

  ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ።

  ReplyDelete
 29. I was following the discussions. I am taking the last Anonymous points since he has given us clear verses right from the bible. Yemaledal, Yastarkal in a present tense sounds right for me. Thanks.

  ReplyDelete
 30. simply he was one of the move away prophet

  ReplyDelete