Sunday, July 24, 2011

በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ላይ መዋሸት ይቁም! ... ክፍል 4 - - - Read PDF

በሰማይና በምድር የማርያምን ስም የጠራ ሁሉ ይድናል (ታምረ ማርያም 12፥43-53)

የእግዚአብሔርን ስም የጠራ ሁሉ ይድናል (መጽሐፍ ቅዱስ ሮሜ 10፥13)
እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው ተብሎ እንደተጻፈ (ሮሜ 10፥17) ማንኛውም ሐሳብና ሃይማኖት መመርመርና መገምገም ያለበት በእግዚአብሔር ቃል ነው። አባቶቻችን ሐዋርያት ከመንፈስ ቅዱስ የሰሙትን ለዓለም ሁሉ በአስተላለፉበት መልእክታቸው አንድ ተስፋ፣ አንድ መንፈስ፣ አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ጥምቀት ብቻ እንዳለ ነው። ይህም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ሞትና ትንሣኤ የተመሰረተው የሰው ልጆች ሁሉ የመዳኛ መንገድ ነው።
ሐዋርያው ጳውሎስ ለገላትያ ምእመናን ያስተላለፈላቸው መልእክት እንዲህ ይላል፦ «ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን፣ አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፣ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን» ገላ 1፥8-9
ሐዋርያት የሰበኩት ወንጌል ምንድር ነው? ብንል፤ ሐዋርያት የሰበኩት ውንጌል ቀጥተኛ እና ግልጽ ነው፦ መዳን በማን ስም እንደሆነ ሲያስተምሩ «መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለም» ብለዋል የሐዋ ሥራ 4፥12። ሐዋርያው ጴጥሮስ በአደባባይ በአይሁድ ሸንጎ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ የተናገረው ቃል ነው። የተጠየቀውም ጥያቄው «በምን ኃይል ወይስ በማን ስም ይህን አድረጋችሁ» የሚል ነበር። የሐዋ ሥራ 4፥7 ጴጥሮስ የመለሰው ቀጥታ ነው፤ ይህ መለኮታዊ ውሳኔ በማንም ሊሻር ስላማይችል እውነቱን አልደበቀም። መልእክቱ ግልጽ ነው። ኢየሱስ ከሚለው ስም ሌላ ለመዳን የሚሆን ስም ከሰማይ በታች አልተሰጠም፤ ንስሐም ሆነ የኃጢአት ሥርየት የሚደረገው በኢየሱስ ስም ብቻ መሆኑን በሌላ ስፍራም አስተምሯል። የሐዋ ሥራ 10፥43። አባቶቻችን ሐዋርያት የሰበኩልን ወንጌል ይህ ነው። ይህ ቀጥተኛ ትምህርታቸው በከሃዲዎች እንዳይቀለበስ «እኛ ከሰበክንላችሁ የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን» ብለው በተሰጣቸው የማሠር ስልጣን አስረዋል ይህ ቃል በሰማይም የጸና ቃል ነው «በምድር ያሠራችሁት በሰማይም የታሠረ ነው» የሚል ቃል ከጌታ አላቸውና።
ይህ ንጹህ የክርስቶስ ወንጌል ከተሰበከ ከ1400 ዓመት በኋላ አጼ ዘራ ያዕቆብና ደብተራዎቹ ይህን የሐዋርያት ቃል ከምንም ሳይቆጥሩ ልዩ ወንጌል አሾልከው ወደ ቤተ ክርስቲያናችን በማስገባታቸው በሐገራችንና በሕዝባችን ላይ እርግማንን አምጥተዋል። አንድ ሃይማኖት የሚለው ትምህርት ተለውጦ ወደ ብዙ ሐይማኖት ወደ ብዙ ተስፋ ሕዝብ እንዲያዘነብል ተደርጓል።  ሐዋርያት አባቶቻችን «የእግዚአብሔርን ስም የጠራ ሁሉ ይድናል» በማለት ያስተማሩትን እውነተኛ ወንጌልና አንድ ተስፋ ወደ ጎን በመተው «በሰማይና በምድር የማርያምን ስም የጠራ ሁሉ ይድናል» የሚል ከሐዋርያት የተለየ ወንጌልና ሌላ ተስፋ ሰብከዋል። ይህ ልዩ ወንጌል በመላው ሀገራችን ከመስፋፋቱ የተነሳ ጸሎታችን እና ዝማሬያችንም ከመበከል አልዳነም።
  ይትፌሳሕ ልብኪ በሚለው የኪዳን ሰላም ላይ «ብኪ ድህነ ዓለም ወበወልድኪ ኮነ ሰላም» ትርጉም «ዓለም ባንቺ ዳነ በልጅሽም ሰላም ሆነ» በማለት በናታችን ላይ የሚዘባበት ድርሰት ተደርሶ ሁልጊዜ እንዲዘመር ተደርጓል። በውኑ ዓለም የዳነው በማርያም ነው ወይስ በኢየሱስ ክርስቶስ? ይገርማል! እግዚአብሔርን ስለ ማርያም በማመስገን ፋንታ ነገር ገልብጠው ማርያምን ስለ እግዚአብሔር ያመሰግናሉ። ዓለም ባንቺ ዳነ የሚለው ቀጥተኛ አይደለም፤ እመቤታችን የዓለምን አዳኝ ወለደችልን የሚለው ግን ቀጥተኛ ነው።
«አድህነነ ሕዝበከ» [ሕዝብህን አድነን]  በሚለው የሠርክ ጸሎት ላይ «እግዝእትነ ነጽሪ ኀቤነ ወአድኅኒነ እምኩሉ ምንዳቤ ወኃዘን» ትርጉም «እመቤታችን ወደኛ ተመልከች ከኃዘን እና ከችግር ሁሉ አድኚን» የሚል የተደባለቀ ጸሎት ይጸለያል «ሕዝብህን አድነን» ሲል ደህና ጀምሮ መሀል ላይ «አድኚን» በማለት ድንጉር ያደርጋል። ጌታ ስለ ጸሎት ለአባቶቻችን ለሐዋርያት ሲያስተምር «ወደ ፈተና አታግባን ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ» በሉ ነበር ያለው። የልዩ ወንጌል አስተማሪዎች ግን ይህን ትዛዝ ቸል በማለት ማርያምን «አድኚን» እያሉ ይጸልያሉ።  በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ወደ ሰዎች የጸለየ የእግዚአብሔር ሰው አንድም ቦታ እናገኝም፤ ጸሎት አምልኮ ስለሆነ ወደ እግዚአብሔር እንጂ ወደ ማንም አይጸለይም። አዳኝም እግዚአብሔር ብቻ ነው።
የአምልኮ ጊዜ ተብሎ በሚታወቀው በቅዳሴያችን ሰዓት አሐዱ አብ ቅዱስ ብለን ጀምረን ምስጋና፣ አምልኮ፣ አንክሮ፣ ንስሐ ኑዛዜ የምናደርገበት ጊዜ ነው፣ መሐል ላይ ስንደርስ ግን «ደህንነትን የምንለምንሽ ቅድስት ሆይ» ብለን ከእመቤታችን ደህንነትን እንለምናለን። ነገሩ ግራ የሚያጋባ ነው። ደህንነትን ከጌታ ያጣን ይመስል እርሱን መታመን ሲገባን ወዲያው ዘወር ብለን ሌላ አምልኮ ውስጥ እንገባለን። ደህንነትን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው ስለዚህ እርሱን ብቻ መጠየቅ ይገባን ነበር። ይህ ሁሉ ሰርጎ ገብ ወንጌል አጼ ዘራ ያዕቆብ በጉልበት ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ያስገባብን ባዕድ ነገር ነው። የአባቶቻችን የሐዋርያት እምነት ግን አይደለም።    
እነዚህ የነገሥታት ደብተራዎች ይህን የስሕተት ትምህርት አንቀበልም ያሉትን ደቂቀ እስጢፋኖስን መናፍቅ ናቸው ብለው በእሳት አቃጥለው ገድለዋል። ዛሬም የአጼው  ተከታዮች ማኅበረ ቅዱሳን የሚባሉ ሐሰተኞች ይህን ልዩ ወንጌል እየሰበኩ ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ባሰ እርግማን ማስገባታቸው አላንስ ብሏቸው፣ የሐዋርያትን ትምህርት የሚከተሉ እውነተኛ ኦርቶዶክሳውያንን መናፍቅ እያሉ በማያስተውል ሕዝብ ለማስገደል ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።
ይህን የስሕተት ትምህርት ይደግፍልናል ብለው የሚያስቡትን ጥቅስ ሁሉ እያጣመሙ ወደ ራሳቸው ሐሳብ በመተርጎም ብዙ አበላሽተዋል።
ለምሳሌ በማቴዎስ 10፥42 ላይ «በደቀ መዝሙር ስም ቀዝቃዛ ጽዋ ውሃ የሚያጠጣ» የሚለው ቃል የተጣመሙ ትርጉሞች ከተሰጣቸው ቃላት አንዱ ነው።
ነገር ግን ምእራፉን በሙሉ ከላይ ጀምረን ብናስተውለው ሐሳቡ ግልጽ ይሆንልናል። ሐዋርያት ወደ ዓለም ሲላኩ ወርቅ ብር ከረጢት ወይም እጀ ጠባብ እንዳይዙ ታዝዘዋል፣ ነገር ግን በዚያው በደረሱበት ቤት እንዲቀመጡ የሚቀበላቸውም ሰው በረከታቸው እንዲተርፈው ነግሯቸዋል። እነርሱን የተቀበለ ሰው ጌታን እንደተቀበለ፤ ጌታን የተቀበለ አብን አንደተቀበለ ነው ብሏቸዋል። ነቢይን በነቢይ ስም የተቀበለ ጻድቅን በጻድቅ ስም የተቀበለ፣ ደቀ መዝሙርን በደቀ መዝሙር ስም የተቀበለ የነርሱን ክብር ይካፈላል። ይህ ማለት ነቢይን የጌታ ነቢይ ነው ብሎ፣ ጻድቅን የጌታ ባሪያ ነው ብሎ ደቀ መዝሙርን ደቀ መዝሙር ነው አገላጋይ ነው ብሎ አክብሮ መቀበል እነርሱን መታዘዝ፣ ቃላቸውን መስማት፣ ትምህርታቸውን መከተል ማለት ነው። በዚህ አንጻር በደቀ መዝሙር ስም ቀዝቃዛ ጽዋ ውሃ ማጠጣት ማለት ብርና ወርቅ የሌላቸውን የጌታ አገልጋዮች ወደ ቤት አስገብቶ ምግባቸውን ማቅረብ፣ በጉዟቸው ሁሉ የሚያስፈልጋቸውን መርዳት ማለት ነው። ይህ ቃል ለነርሱ ለራሳቸው  ማድረግ ስላለብን ነገር የሚናገር እንጂ በነርሱ ስም ለሌላ ሰው ስለምናደርገው ነገር የሚናገር አይደለም። ይህን ቃል በማርቆስ 9፥41 ላይ ምን ማለት እንደሆነ በግልጥ እናገኘዋለን «የክርስቶስ ስለሆናችሁ በስሜ ጽዋ ውሃ የሚያጠጣችሁ ሁሉ ዋጋው እንዳይጠፋበት እውነት እላችኋለሁ» ይላል። እንግዲህ በማቴዎስ 10፥42 ላይ የተነገረው ቃልም ለራሳቸው ለአገልጋዮች አገልግሎታቸውን የሚደግፍ ሥራ መሥራት እንዳለብን የሚያተምር ቃል እንጂ እነርሱ ካረፉ በኋላ ስለምናደርገው ነገር ለማናገር አይድለም። ሁሉንም በማን ስም ማድረግ እንዳለብን አባቶቻችን ሐዋርያት እንዲህ ብለው አስተምረውናል
«እግዚአብሔር አብን በእርሱ እያመሰገናችሁ፤ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታድርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አድርጉት» ቈላ 3፥17
እኛም አባቶቻችን ነቢያትን በነቢይነታቸው እንቀበላለን ትምሕርታቸውንም እንከተላለን፤ አባቶቻችን ሐዋርያትንም በሐዋርያነተቸው እንቀበላለን ትምህርታቸውንም ሳንጨምር ሳንቀንስ እንከተላለን፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንም የጌታችን እናት ናትና እናታችን አድርገን እንቀበላለን፤ እምነቷን ምሳሌነቷን እንከታለለን እጅግ አድርገንም እናከብራታለን፣ በኛ ዘመን ያሉ የጌታ ደቀ መዛሙርትንም በጌታ ስም ተቀብለን በአገልግሎታቸው የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ እናደርጋለን ይህን ሁሉ የምናደርገው ግን በጌታ በኢየሱስ ስም ነው። ከዚህ እውነተኛ የሐዋርያት ትምህርት ውጭ የሆነውን ክህደት እና ኑፋቄ ግን ከቤተ ክርስቲያናችን ይወገድ እንላለን።
ወገናችን የአገራችን የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በጉልበት እና በኃይል በማስፈራራት፣ በማግለል፣ በተጽእኖ፣ በዝምድና፣ በውርስ በመሳስለው ሁሉ የተጨነበትን ልዩ ወንጌል አንቀበልም። ሕዝባችን በተሳሳቱ የአንድምታ ትምህርቶች ወደ ተለያዩ ነፍሳት መላእክት እንዲጸልይ፣ እንዲማጸን፣ ስለት እንዲሳል ስለተደረገ በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን ስም አምልኮ ባዕድ ተስፋፍቷል። የተጻፉት ገድላትና ድርሳናት ሁሉ መጨረሻቸው ላይ ስምህን የጠራ፣ በስምህ የጸለየ፣ መታሰቢያህን ያደረገ ይድናል የሚል መልእክት ስለሚያስተላልፉ ሕዝባችን ጸሎቱን፣ ስለቱን የሚያደርገው ወደ ተለያዩ መላእክት እና የጻድቃን ነፍሳት ነው። ይህን ለመረዳት የጸሎት መጻሕፍትን አስተውሎ መመልከት የሚቻል ሲሆን በየቀኑ የሚከበሩትን ከአንድ ጀምሮ እስከ 30 ቀን ድረስ ያሉትን ጻድቃን ሰማዕታትን መላክትን በተመደቡበት ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያናቸው በመሄድ ምን ዓይነት ልመና እና ጸሎት እንደሚቀርብላቸው ማየት ነው። ቀናቱ ሁሉ በተለያዩ ሰዎች ስለተያዙ ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ የለም።
በሐምሌ አስራ ዘጠኝ ቀን ወደ ቁልቢ የሚሄድ ሁሉ ጸሎቱን ስለቱን፣ ልመናውን ስግደቱን ሁሉ ቅዱስ ለገብርኤል እንጂ ለእግዚአብሔር አያቀርብም። ይህ ባዕድ አምልኮ አይደለምን? ባዕድ አምልኮ ለመሆኑ ወደ ቁልቢ የሚሄደው እስላሙ፣ ባለውቃቤው፣ ጠንቋዩ፣ በወንጀል የበለጸጉ ሀብታሞች፣ ዝሙትን ለመፈጸም እቅድ ያላቸው ሁሉ ናቸው። ታዲያ እነዚህ ሁሉ ወደዚያ የሚጎርፉት ኃጢአታቸው አስጨንቋቸው ሳይሆን ፈቃዳቸውን እና ምኞታቸውን የሥጋ ፍላጎታቸውን ለመፈጸም ነው። እግዚአብሔርም ለፈቃዳቸው አሳልፎ ስለሰጣቸው አንዳች ነገር ይጣልላቸዋል።
እግዚአብሔር ከዚህ ሁሉ ጉድ የምንወጣበትን ቤተ ክርስቲያናችን ወደ ሐዋርያዊ ክብሯ የምትመለስበትን ጊዜ ያሳየን አሜን!
ሰባ ስምንት ነፍስ ያጠፋው ነፍሰ ገዳይ በማርያም ጥላ ዳነ.... ታምረ ማርያም ይቀጥላል
ዲያቆን ሉሌ ነኝ

8 comments:

 1. ዋው! this is amazing. Tewahedo and Nathan, what do you think about this article?

  ReplyDelete
 2. Dear, You are inviting us to talk about it even though I don't have time to write about this.

  This article as usual is a little true but conceptually totally wrong. The major concept you missed include:

  1. God has the right to do what ever he want in His Kingdom
  2. God told us that Yekidusan MEtasebia lezelalem yinoral /Saints memorial is forever
  3. God told us that Yekidusan Metasebia is for Bereket.

  4. In the bible itself we found when man is called Adagn /Saviour/ that means only the context of the word is different when used for God and for Kidusan. When we say ደህንነትን የምንለምንሽ ቅድስት ሆይ, it doesn't mean Mary herself will give us ደህንነት but she prays for Dehininet.

  5. You are wrong because you don't want to understand the motive behind verses. We orthodox christians clearly identify who is God and who are Kidusans. Kidusans are not God.

  Any how I don't expect you will hear my voice so there is no need to write more. For people who want to understand deeply i can take devotion and write but what is the benefit of adviciing ignorant people?

  Best wishes,

  ReplyDelete
 3. Tewahedo, Is it possible that you are one of our sebakian? You have already closed your mind and have no interest in exploring or re-thinking what you already know. You think you know it all ha? That is what they call arogance. የትህትናን መንፈስ እግዚአብሔር ይጨምርልህ ወንድሜ። የውይይቱ ነጥብ እኮ ግልጽ ነው። ስለዚህ «በሰማይ እና በምድር የማርያምን ስም የጠራ ሁሉ ይድናልi» የሚለውን ምንም ሳይጎረብጥህ ትቀበለዋለህ ማለት ነው? Could you give me one Biblical evidence (only one) that supports this claim? የእግዚአብሔርን ስም የጠራ ሁሉ እንደሚድን ግን መጽሐፍ ይናገራል። እንዴት ሁለቱ ነገሮች አብረው ይሄዳሉ? ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን ለማስታረቅ መከራ ከማየት እንዲህ ቢባል ጥሩ ነው ብሎ ማስተካከሉ አይሻልም?

  ReplyDelete
 4. እውነት,

  I think Tewahedo has acknowledged mistakes in the wording, but he has also elaborated his point well. In summary, what I believe is similar to what T is saying:

  (1) I believe in the bereket we get through kidusans. However, the church has expanded the role of kidusan beyond proportion and has adulterated the worhsip and practice in some bad ways by over emphasizing the role of the saints. I really think that the church has overshadowed Christ Jesus by making the faith as if it was all about the saints. I disagree with the chruch on that while I still beleive in the saints. I believe that our focus should be Christ Jesus, but most EOTC followers are attached to the saints and never have prayed in the name of Christ Jesus while the bible tells us to pray in the name of Christ Jesus. The awalid books we find in the church are full of mistakes - ordinary and gross. I don't want to defend those awalid books while at the same time I don't want to see people attacking our faith using those awalids.

  (2) For me "በሰማይና በምድር የማርያምን ስም የጠራ ሁሉ ይድናል" means that St Mary has huge power to intercede on behalf of believers. The writer simply exaggerated that power to intercede by borrowing the same phrase used for Christ. However, this does not mean that St. Mary has replaced Christ. It simply means that she can intercede with Christ for blievers. Nothing more than that. I hope the author of the article does not doubt that he can pray for his own friend or family. To say that St. Mary cannot pray for us is simply to put yourself (Lule) above st. Mary.

  (3) Again, I believe that we need to give more room for Christ Jesus at EOTC in terms of devotion and focus while keeping the saints with us. On the other hand, the pentes and the reformists should understand the role and power of the saints and stop attacking the church for venerating the saints. Yekidusan metasbia can bring us bereket. However, I argue that the saints cannot be salvation in and of themselves. I dislike the the primacy people give to the saints at EOTC and the denial of the pentes regarding the role of the saints.

  (4) People at EOTC give primacy to the saints because of the lack of education. Otherwise, it is not that difficult to see in the bible that the apostles fought to preach salvation through Christ, not anyone else. I nauseate when people equate the role of the saints to that of Christ.

  (5) Hopefully, the pentes and reformists will accept the positive role of the sainsts in our salvation in the future, and the EOTCs will make Christ the very center of our mahlet, hymn, mass, worship, meditation and prayers.

  ReplyDelete
 5. Nathan, thanks for your mature comments. I always enjoy your comments and learn a few things from them. I agree with most of the contents in your points 1 , 3, and 4. I have reservations on 2 and 5. This is the kind of discussion we need to continue having. Regarding your point 2, I think we should be able to simply say that the sentence is wrong and should be corrected to align with the Bible. Exaggeration is not a good thing you know. I am yet to find a single Biblical evidence that points me to the fact that St. Mary intercedes for us today. Nathan, could you point me to a good source? (please don't tell me John 2). On your point 5: I believe salvation is through Christ alone!!!! can Saints pray for us? sure. Are saints neccessary for salvation? The Bible doesn't say so. Our Lord never implied either.

  ReplyDelete
 6. የማቴዎስ ወንጌል ምህራፍ 10 ቁጥር 40 እንዲህ ያላል እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል : እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል : ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢዩን ዋጋ ይወስዳ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል ::ማንም ከእነዚህ ከታናናሾች አንድ ቀዝቃዛ ጽዋ ውሀ ብቻ በደቀ መዛሙርት ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሀለው ዋጋው አይጠፋበትም :: ተመልከቱ ወንጌል ይሁንን ነው የሚለው እናንተን ቅዱሳንን የሚቀበል እኔን ኢየሱስን ተቀበለ ይላል :: ቅዱሳኑን ያልተቀበል እኔን አልተቀበለም የላከኝንም አልተቀበለም ሉቃስ 10:16 :: ስለዚህ ቅዱሳኑን ሳይቀበል ኢየሱስን ተቀብያለሁ ቢል ከወንጌል ጋር አይስማማም ሕይወትም የለውም :: እንዴ ወገኖቼ ቅድስት ድንግል ማርያም ሳይቀበል ኢየሱስን ተቀብያለሁ ቢል ወንጌል ያንን ሰው ይቃመዋል :: ቅዱሳንን እየተሳደበ ኢየሱስን ተቀብያለሁ ቢል አንድ ሰው እጅግ ውሸታም እንደሆነ መጸሐፍቅዱስ ተናግሯል :: ስለዚህ ኢየሱስ እንዳለው ቅዱሳንን የሚቀበል እኔንም አባቴንም ተቀብሏል ብሏልና እኛ ክርስትያኖች ቅዱሳኑን እንቀበላለን :: እንድውም አለ ኢየሱስ በቅዱሳን ስም በደቀመዛሙት ስም አንዲት ዋንጫ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሀ በደቀመዛሙት ስም የሚመጸውት የሚሰጥ እውነት እላቹሀለው የቅዱሱን ዋጋ ይወስዳል ያላል :: ለዚህም እኮ ነው ስለ እመ አምላክ ስለ አቡነ ተክለሀይማኖት ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስለ አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ ስለ ዮሀንስ .... ሲባል የምንመጸውተው :: ተረት ተረት መሰላቹ እንዴ ? መጸሐፍቅዱስ የሚለውን ሁሉ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ትፈጽማለትች :: በቅዱሳ ስም መጽውቱ ይላል ይህንን የሚፈጽሙት ግን ክርስትያኖች ብቻ ናቸው :: ሌሎቹ ወንጌል እናነባለን ይላሉ ነገር ግን ወንጌል የሚያዝዘውን አይፈጽሙትም :: ታዲያ ይህ ወንጌልን መቀበል ነው ወይስ ወንጌልን መጣል ? ስለዚህ ጌታ ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል ጻድቃንን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋው ይወስዳል :: ተመልከቱ ዛሬ አለም የተቸገረው ነቢይን በነቢይ ስም መቀበል አቃተው ጻድቃንንም በጻድቃን ስም መቀበል አቃተው :: ወንጌሉ ግን ዛሬም ይጮሀል ጆሮ ያለው ይስማ ማንም በደቀመዛሙት ስም አንዲት ቀዝቃዛ ውሀ የሚሰጥ እውነት እላቹሀለው ዋጋው አይጠፋበትም ይላል ወንጌል :: ስለዚህ በቅዱሳን ስም የምትመጸውቱ በድንግል ማርያም ስምት የምትመጸውቱ ዋጋቹህን እግዚአብሔር አላስቀርባችሁም ይላል ደስ ይበላቹ ወንጌል እየፈጸማቹ ነውና :: ስለዚህ ዛሬ በቅዱስ ተክለሐይማኖት ስም ብሎ አንድ ሰው ቢለምነን እና ብንመጸውት ዋጋችን አይጠፋም :: መናፍቃኑ እና ከሐዲያኑ ግን እራሳቸውን ነው ቅዱስ የሚያደርጉት : በነሱ ስም በከሀዲያኑ ስም እንድንመጸውት ከሆነ የሚፈልጉ ሲያምራቹ ይቅር በሉልኝ :: ሲያምራቹ ይቅር :: የቅዱሳኑን ክብር ለራሳቹ አትውሰዱ ገሐነም አለና :: ስለዚህ መሐከላዊ እዚህ ላይ ነው ያለው እናንተን የሚቀበል እኔን ተቀበለ :: እናንተን የማይቀበል እኔን አልተቀበለም ይህን ያለው ኢየሱስ እራሱ ነው :: ሌሎች ግን ስለ ሰማይ ስለማያስቡ ይህንን ላይቀብሉ ይችላሉ :: እነርሱስንም ደግሞ ቅዱስ ጳውሎስ ሆዳቸው አምልካቸው ነው ክብራቸው በነውራቸው ነው : ሐሳባቸው ምድራዊ ነው እነሱ የመስቀል ጠላቶች ናቸው እያለቀስኩ እላለሁ መጨረሻቸው ጥፋት ነው ይላል ፊሊፕስዩስ ምህራፍ 3 ቁጥር 17 ጀምሮ :: ስለዚህ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱሳን ስም የሚመጸውተውን የቅዱሳኑን ዋጋ እንደሚሰጠው ተናግሯል :: እንደውም የቅዱሳን መታሰቢያቸው እንደማይጠፋ ተንግሯል ::

  ReplyDelete
 7. Annonymous - July 27,

  I believe the way you descibed it, but it has to be within the cpntext of Christ's salvation plan. EOTC has been teachng this for hundred of years so intensely that people have stopped following the word of God by mistakenly assuming that their mitswat (alms they give) in the name of the saints would save them. My answer to that it would not save them. The EOTC church has been wrongly presenting the intercession of the saints as an alternative route to salvation. That is a big mistake!!! There is no alternative to the salvation plan given by Christ Jesus. The intercession of the saints can only help us achieve that plan if and only if we are struggling for that single salvation by abiding by the word of God. For example, if we give trilions of dollars in the name of the saints without bearing the fruit of the Spirit and regulalry commiting sins, we cannot be saved.

  Otherwise, if we give alms in the name of the saints while abiding by the word of God, we can get blessings. Here is another verse that supports the claim that we can get blessings through the saints:

  Luke 16:

  9 እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ።

  ReplyDelete
 8. Allways devil doesn't like 3 things in the bible
  1,S/TtMERRY
  2'HollyFOTHERS/KIDUSAN
  3,The HOLLY CROSS
  B/c devil lost his power with these three POWERFULL NAMES.But still devil try to give wrong intrepritation.all tewahedo we belive that'«በሰማይና በምድር የማርያምን ስም የጠራ ሁሉ ይድናል»don't tell as how to understand this.we know how. tanks to our holl fothers.You better lern before try to teach.May Almaighty GOD give you the power to know about the holly.

  ReplyDelete