Friday, July 15, 2011

የቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነት (ዶግማ) - ክፍል 5 - - - Read PDF

ኢየሱስ ክርስቶስ የዐዲስ ኪዳን ሊቀ ካህናት

እግዚአብሔር በቅዱስ ቃሉ ውስጥ እንደገለጸው ለዐዲስ ኪዳን ጥላና ምሳሌ ሆኖ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሕዝቡን ሲያስተዳድርና ሲመራ የኖረው በሕዝቡና በእርሱ መካከል መካከለኛ አድርጎ ባቆማቸው ተቀብተው በተሾሙ ካህናት፥ ነቢያትና ነገሥታት አማካኝነት ነበር። በዐዲስ ኪዳን ግን  ለተለያዩ ነገዶችና ግለሰቦች ተሰጥተው የነበሩትን እነዚህን ሦስቱን ሹመቶች ሊቀ ካህንነትን፥ ነቢይነትንና ንጉሥነትን ሰው ሆኖ የተገለጸው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጠቅልሎ ይዟቸዋል።

«ክርስቶስ» የሚለው የግሪክ ቃል የጌታችን የሹመት ስሙ ነው። ትርጉሙ በዕብራይስጥ መሲሕ በአማርኛ የተቀባ፥ ቅቡዕ እንደ አሮንና እንደ ዳዊት ተመርጦ የተሾመና የነገሠ ማለት ሲሆን መቀባትም ለሦስቱ ሹመት ነው። ካህን ነቢይና ንጉሥ ለመሆኑ። (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ገጽ 549-550)

አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ሰውነቱ ካህንነትን ነቢይነትንና ንጉሥነትን ገንዘብ ማድረጉን ሊቃውንተ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርገው አስተምረዋል።

አባ መልከ ጼዴቅ በ 1984 ዓ/ም ባሳተሙት «ትምህርተ ክርስትና» 2ኛ መጽሐፍ ላይ ያሰፈሩትን እንመልከት፦ «ሦስቱ የድኅነት መሣሪያዎች በሦስቱ መዓርጋት የተፈጸሙትን የድኅነት ሥራዎች የሚገልጡ ናቸው። ሦስቱ መዓርጋት የተባሉትም ነቢይነት፥ ሊቀ ካህንነትና ንጉሥነት ናቸው። እነዚህንም ሦስቱን የማዕረግ ስሞች ክርስቶስ የማዳን ሥራውን የፈጸመባቸው ስለሆኑ የእርሡ መጠሪያ ስሞች ሆነዋል።

የክርስቶስ የነቢይነቱ መዓርግ ዞሮ ማስተማሩን ሕዝቡን ለድኅነት ማዘጋጀቱን ያመለክታል። ስለዚህም ራሱ «ናሁ ነዐርግ ኢየሩሳሌም ወይእኅዝዎ ለወልድ ዕጓለ እመሕያው» እያለ ትንቢት ትናግሯል (ማቴ 20፥18)። ኢየሱስ ነቢይነት ገንዘቡ እንደሆነ ነቢይም እንደሚባል «ኢይደልዎ ለነቢይ መዊት በአፍአ ዘእንበለ በኢየሩሳሌም» ሲል ራሱ ተናግሯል። (ሉቃ 13፥33)

ሊቀ ካህንነቱ ድግሞ በሥራ ተገልጧል ማለት ክርስቶስ ዐቢይ ሊቀ ካህናት ሆኖ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ለአባቱ አቅርቧልና . .. ሊቀ ካህናታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባቀረበልን መስዋዕት ድነናል። እርሱ ቤዛ ሆኖ ተለውጦ አድኖናል። ንጉሠ ነግሥትነቱም ክርስቶስ ማለት የተቀባ፥ የከበረ፥ የነገሠ ማለት እንደመሆኑ የጠፋውን ልጅነት መለሰ፥ ፍዳን ደመሰሰ፥ ምርኮነ መለሰ። ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ብለን ጌታችንን ስንጠራው የዳንን ወገኖች መድኅንም ያለን ሕዝቦች ነን። ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ አምነን እንቀበላለን» (ገጽ 36-37 እንዲሁም የቤ/ክ ታሪክ በዓለም መድረክ ከአባ ጎርጎርዮስ ገጽ 51)

ከላይ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያደረገውን የአባቶችን ምስክርነት እንደተመለከትነው ካህንነት፥ ነቢይነትና ንጉሥነት የክርስቶስ ገንዘቦቹ ናቸው። እኛንም ያዳነንና ለዘላለምም የሚያድነን በነዚህ በሦስቱ ሹመቶቹ አማካይነት ነው። በዚህ ክፍል ግን ስፍራ ሰጥተን በስፋት የምንመለከተው ሊቀ ካህንነቱን ነው።    

ሊቁ ቄርሎስ (በሃይማኖተ አበው ም 81 ክፍል 52 ቁ 8 ላይ) እንደመሰከረው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰው በመሆኑ፦ ብእሲ፥መሲሕ፥ ኢየሱስ፥ ታቦት፥ አስታራቂ፥ ስሙታን በኩር፥ ከሙታን ወገን ለሚነሣም በኩር የቤተ ክርስቲያን (የምእመናን) ራስ ተብሏል። በነዚህም ስሞች ይጠራል።

እርሱ  ፍጹም አምላክ ብቻ ሳይሆን ፍጹም ሰውም ነውና ከኃጢአት በቀር በነገር ሁሉ እኛን ቢመስልም (ዕብ 4፥15) የአምላክነቱ ክብር ለቅጽበት እንኳ አልተቀነሰም። ክቡር አምላክ ሲሆን በፈቃዱ ራሱን ስለኛ ዝቅ አደረገ እንጂ በተዋሕዶ ምስጢር አንድ የሆነው እርሱ የአምላክነቱንም የሰውነቱንም ሥራ ሠርቷል። (1ጴጥ 3፥18)

«አንስ አአምን ከመ ውእቱ ሞተ በሥጋ ወሐይወ በኃይለ እግዚአብሔር» «እኔ በሥጋ እንደሞተ በእግዚአብሔርነቱ ኃይልም እንደተነሣ አምናለሁ» እንዳለ ቄርሎስ (ሃይ አበ ም 80 ቁ 9)

እንደዚሁም በአምላክነቱ ኃጢአትን ሁሉ የሚያስተሰርይ ሲሆን ሰው በመሆኑ ደግሞ የዐዲስ ኪዳን አስታራቂ ሆኗል።

«ወውእቱ መዋዔ ኩሉ ኃጢአት በመለኮቱ ኮነነ ሊቀ ካህናት በትስብእቱ» «በመለኮቱም ኃጢአትን ሁሉ የሚያጠፋ እርሱ ሰው በመሆኑ አስታራቂ ሆነን» (ሃይ አበ ምዕ 79 ክፍ 50 ቁ 68)

በፍጹም ሰውነቱ የክርስቶስ የአስታራቂነቱ ግብር የተገለጸው በሊቀ ካህንነቱ ነው። የሊቀ ካህንነቱን ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ በስፋት ተጽፎ የምናገኘው በዐዲስ ኪዳን ክፍል በተለይ በዕብራውያን መልዕክት ውስጥ ነው።

መልእክቱ በመጀመሪያ የተጻፈላቸው ዕብራውያን በሥጋ የአብርሃም ዘሮጽ የሆኑ ከሁሉ አስቀድሞ ልጅነትና ክብር፥ ኪዳንም ሕግም የተሰጣቸው የምድራዊ መቅደስ ሥርዓት የነበራቸው፥  በኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት የሚፈጸመውንና ለአብርሃም የተሰጠውን የተስፋ ቃል የተቀበሉ ነበሩ። (ሮሜ 9፥4-5)

ለዕብራውያን ተሰጥተው የነበሩት እነዚህ ሁሉ ነገሮች ለሚመጣው ዐዲስ ነገር ጥላና ምሳሌ ነበሩ። (ዕብ 10፥1፤9፥9-10፤ ቆላ 2፥17)

አሁን በዐዲስ ኪዳን በተስፋ ሲጠበቅ የቆየው የጥላው አካል ስለተገለጠ ብሉይ ኪዳን የአገልግሎት ዘመኑን ፈጽሞ ለተተኪውና እስከመጨረሻ ለሚጸና ለዐዲስ ኪዳን አገልግሎት ስፍራውን ለቅቋል። (ዕብ 8፥1-13፤ 9፥1-10፤ 2ቆሮ 3፥7-18)

የዕብራውያን መልእክት ጥላውን ከአካሉ፥ ምሳሌውን ከአማናዊው ጋር በማነጻጸር የተሻለውና ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበትን ዐዲስ መንገድ ይጠቁመናል። መልእክቱ ለዕብራውያን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ነውን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየድርሳናቸው ውስጥ ከሐዋርያት እንደተቀበሉት የክርስቶስን ሊቀ ካህናትነት ጽፈውልን ዐልፈዋል። ይሁን እንጂ የመዳናችን ዋስትን የቆመበት የክርስቶስ ሊቀ ካህናትነት ትምህርት ከመቃብር በታች ውሎ ብዙ ነገር ከተጫነበት ዘመናት ተቆጥረዋል።

ከውድቀት በኋላ ምንጊዜም ቢሆን ያለመካከለኛ በራሱ ብቻ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የማይሆንለት የሰው ልጅ የመቅረቢያው መንገድ ስለጠፋበት ሌላ መንገድ ለመፈለግ ተገድዷል።

በጉዞው መጨረሻ ሊገጥመው የሚችለውን ለማያውቅ የሰው ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህንነት በኩል ሳይሆን በሌላ ወደ አብ እንደርስበታለን ብሎ ባሰበው መንገድ ሁሉ ላይ መጓዙ ለጊዜው ዝም ብሎ ከመቆምና ግራ ከመጋባት አማራጭ መስሎ ቢታየውም እግዚአብሔር ያላዘጋጀው መንገድ ወደ እግዚአብሔር የማያደርስ መሆኑ ግን በእጅጉ ያሳዝናል። (ዮሐ 14፥6፤ ዕብ 10፥19-20)

ከብሉይ ኪዳን አገልግሎት እንደምንረዳው የካህን አገልግሎት በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ሆኖ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ማስታረቅ ሲሆን ካህኑ የማስታረቁን አገልግሎት የሚፈጽመው ለኃጢአተኛው ሰው መስዋዕት በማቅረብና በመጸለይ ነው (ዘሌዋ 4፥1-35)

ክርስቶስ ካህን ሆኖ ለኃጢአት ሁሉ የሚበቃውን መሥዋዕት ራሱን በማቀረቡ የአሮንን ክህነት አስቀርቷል። (ዕብ 7፥11-28) የክህነቱን ሥራ የፈጸመው በምድራዊ ሳይሆን በሰማያዊ መቅደስ፥ በእንስሳት ደም ሳይሆን በራሱ ደም ነው። (ዕብ 9፥11)

ክርስቶስ ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ከማቅረቡ ባሻገርም በሊቀ ካህንነቱ ጸሎትና ምልጃን አቅርቧል። ይህም የሆነው፥

1) በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ከመሞቱ በፊት በነበረው ጊዜ (ዮሐ 17፤ ሉቃ 22፥31-32) «አንቃዕደወ ሰማየ ኅበ በቡሁ ወአስተምሐረ ወላዲሁ ወአማኅጸነ አርዳኢሁ ከመ ይዕቀቦሙ እምኩሉ እኩይ» ትርጉም « ወደ ሰማይ ወደ አባቱ ቀና ብሎ አየ፤ ወላጅ አባቱንም ማለደ፤ ደቀ መዛሙርቱንም ከክፉው ሁሉ ይጠብቃቸው ዘንድ አደራ አስጠበቀ፣» (ቅዳ ማር ቁ 113)

2) በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለ (ኢሳ 53፥12፤ ሉቃ 23፥34፤ ዕብ 5፥7) « ወሰአሎ ለአብ ያኅልፍ እምኔነ መዓተ ዘረከበነ እምቅድም ከመ ዘለሊሁ ይኌልቊ ስእለተ ሎቱ እስመ ውእቱ ነሥአ አምሳሊነ ከመ ይስአሎ ለአብ በእንቲአነ ከመ ምዕረ ዳግመ ይዝክረነ ወኢይኅድገነ እምኔሁ»  ትርጉም «እርሱ ለራሱ ልመናን የሚሻ መስሎ ከጥንት ጀምሮ ያገኘንን ፍዳ ከእኛ ያርቅ ዘንድ አብን ማለደው። እንደገና ደግሞ እንዲያስበን ከእርሱም እንዳይለየን ስለእኛ አብን ይማልደው ዘንድ ባሕርያችንን ነስቷልና» (ሃይ አበ ም 79 ክፍል 50 ቁ 38)

3) ከትንሣኤውና ከእርገቱ በኋላ (ሮሜ 8፥34፤ ዕብ 7፥25፤ 1ዮሐ 2፥1)  «ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ አዐርግ ሰማየ ኅበ አቡየ ወእስዕሎ በእንትአክሙ»  ትርጉም «ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ አባቴ ዐርጋለሁ ስለእናንተም አለምናለሁ አላቸው።» (የፋሲካ ድጓ ገጽ 291 3ኛው ዓምድ ላይ)

«ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ አዐርግ ሰማየ ኅበ አቡየ ኀበ እስእል ምሕረተ በእንተ አሊአየ» ትርጉም «ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን የኔ ስለሆኑት ምሕረትን ወደምለምንበት ወደ አባቴ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ አላቸው» (የሠኔ ሚካኤል ዚቅ (ዓራራይ))

«ወልድ ሆይ እንደታመመ ሰው አስምተህ ተናገር። ኤልማስ ላማ ሰበቅታኒ በል። በአፋቸውም ውስጥ ሳለ አባ አባቴም ሆይ፤ ሥጋዬን የበሉትን ደሜን የጠጡትን ማራቸው ይቅር በላቸው በል» (ቅዳ አትናቴዎስ ቁ 144)

ቀደምት አባቶቻችን በዚህ መልክ የክርስቶስን ዘላለማዊ ሊቀ ካህንነት ቢመሰክሩም በኋላ የተነሡት አንዳንዶች ግን አስተባብለውታል። ደግሞም የጌታ ሊቀ ካህንነት ያለፈ ድርጊት ብቻ እንጂ ቀጣይነት እንዳለው አይናገሩም። ይህም ዘላለማዊ ሊቀ ካህንነቱን የሚቃወም አመለካከት ነው። (ዕብ 5፥7) ይህን እውነት ለማጣመም የተጠቀሙበት ዘዴ የተለያየ ሲሆን ዋናው ግን የግእዝ መጻሕፍትን ሲተረጉሙ ለንባቡ የማይስማማ ትርጉም በመስጠት እንደሆነ ተደርሶበታል። ለምሳሌ ያህልም በሃይማነተ አበው ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ የተናገረውንና በግእዙ «እስመ ውእቱ ይተነብል በእንቲአነ» «እርሱ ስለኛ ይማልድልናል።» የሚለውን በቀጣይ ድርጊት የተገለጸውን ገጸ ንባብ ያለ አንቀጹ በኃላፊ ድርጊት «ማልዶልናል» ብለው ተርጉመውታል። (ሃይ አበ ም 63 ክፍል 2 ቁ 26)

በሮሜ 8፥34 የግእዙ ዐዲስ ኪዳን «ወይትዋቀሥ በእንቲአነ» «ስለእኛ ይከራከራል» የሚለውን ያለፍቺው «ስለእኛ ይፈርዳል» ብለው ተርጉመውታል። «ተዋቀሠ» ስለሚለው ግስ የኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዘገበ ቃላት የሚሰጠው ፍቺ «በቁሙ (ተዋቀሠ) ተሟገተ፥ ተከራከረ» የሚል ነው እንጂ ፈረደ አይልም። (ገጽ 401) ስለጌታ ፈራጅነት በሌላው ስፍራ ሲናገር የግእዙ ዐዲስ ኪዳን የሚጠቀመው ግስ «ኮነነ» የሚለውን ነው። (ዮሐ 5፥27 ግእዙን ተመልከት)

መቼም ለጥቂት ጊዜ ካልሆነ በቀር ሁልጊዜ መዋሸት አይቻልም። አሁን አሁን ግን ከየአቅጣጫው ጫናው እየበዛና አውነቱ እየተገለጠ ሲመጣ ሮሜ 8፥34ን በፊት «ይፈርዳል» እያሉ የተረጎሙ ሁሉ «ይከራከራል» ወደሚለው ሐቅ እየመጡ ነው። ለዚህ አለቃ አያሌው ታምሩ ተጠቃሽ ናቸው። በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፍ እንዲህ ብለዋል፦ «እንግዲህ ቅ/ጳውሎስ «ለእመ ለሊሁ ያጸድቅ መኑ ዘይኴንን ክርስቶስ ኢየሱስ ዘሞተ ወተንሥኦ እምውታን ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር ወይትዋቀሥ በእንቲአነ» «እርሱ ቢያጸድቅ የሚኮንን ማነው? ሞቶ የተነሣ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው በአብ ቀኝ ተቀምጦአል ስለኛ ይከራከራል» (ሮሜ 8፥34) (ምልጃ ዕርቅና ሰላም 1992 ዓ/ም ገጽ 27)

በ1ኛ ዮሐ 2፥1 ላይ «ወእመኒ ቦ ዘአበሰ ጰራቅሊጦስ ብነ ኅበ አብ ኢየሱስ ክርስቶስ» ይህም ማለት «የበደለ ሰው ቢኖር ከአብ ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ጠበቃ አለን» ማለት ነው። ነገር ግን የግእዙ «ጰራቅሊጦስ ብነ» ያለውን በአማርኛ ዐዲስ ኪዳን ትርጉማቸው ላይ «ጰራቅሊጦስ አለን» በማለት የክርስቶስን ጠበቃነት ለማስካድ ተሞክሯል። የኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዘገበ ቃላት «ጰራቅሊጦስ» የሚለው ቃል በግሪኩ (ፓራክሊቶስ) እንደሆነና ትርሩሙም፦ አማላጅ፥ አስታራቂ፥ አፍ፥ ጠበቃ . . . . እንደሆነ ይናገራል። (ገጽ 907) የግእዙ ዐዲስ ኪዳን የገሪኩን ቃል ወደ ግእዝ ሳይተረጉም እንዳለ ነው የተጠቀመበት አማርኛው ዐዲስ ኪዳን ግን በመተርጎም «ጠበቃ» ብሎት እናነባለን።

ለአብነት ያህል እነዚህ ብቻ ተጠቀሱ እንጂ በዚህ መንገድ ትርጉማቸው የተለወጠ ብዙ ናቸው። የትርጉም ለውጥ ከተደረገ በኋላ ደግሞ የአስተምህሮቱ ይዘት መለወጡ አይቀርምና ቀጣይነት ያለውን የሊቀ ካህንነቱን አገልግሎቱ ጠቅሰው ገለጻ ሲሰጡ «የዕለተ ዐርቡን ይዞ ይከራከራል፥ ይለምናል አለ እንጂ አሁን የባሕርይ አምላክ ነው» ይላሉ።

ከዚህ ዐልፈው ደግሞ ሁሉም የማያስኬዳቸው ሆኖ በጥያቄ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡ «እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ነው፤ ታዲያ ወደ ማነው የሚማልደው?» የሚል ከተጠያቂነት የማያድን ጥያቄ ያነሣሉ። ጥያቄያቸው የሥላሴን ትምህርት ገደል ይጨምራል። በአውጣኬ የትምህርት ስልት ሥጋን በመለኮት እንዲዋጥም ያደርጋል። ይህ እንዳይሆን እግዚአብሔር ሦስትነት ያለው አንድ አምላክ ነው። ሦስትነቱ ተከፋፍሎ ሦስት አማልክት አይሆንም። በተጨማሪም ክርስቶስ ለዘለዓለም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ነው።

መቼም ቢሆን ይህን ኑፋቄ የሚያስምሩት ወገኖች ክርስቶስ በሥጋው እስከ መስቀል ሞት መማለዱን አይክዱም ተብሎ ይታመናል። እስኪ ይጠየቁና ጌታ ከመሞቱና ከመነሣቱ በፊት የማለደው አምላክነት ስለጎደለው ነውን? እንዲህ ማሰብ ትልቅ ክህደት። ስለዚህ «እርሱ ራሱ እግዚአብሔር ነው ወደማነው የሚማልደው? ለሚለው ተጠያቂ ጥያቄአቸው ዐጭሩ መልስ ቀድሞ ወደ ማለደበት» የሚል ይሆናል።

ከላይ እንዳየነው በአንድ ወገን ሦስትነቱን በመጠቅለል ሲጠይቁ በሌላ ወገን ደግሞ አንድነቱን በመከፋፈው «አብ እንደማለደ በኤር. 7፥25 ወልድ እንደሚማልድ በሮሜ 8፥34 መንፈስ ቅዱስም እንደሚማልድ በሮሜ 8፥27 ይናገራልና ሦስቱም ወደማነው የሚማልዱት?» በማለት የተለያየ መልእክት ባላቸው ጥያቄዎች ለማደናገር ይሞክራል። የሦስቱንም ጥቅሶች መልእክት ለመረዳት በየክፍል በየክፍላቸው ማጤን ያስፈልጋል።

ስለአብ የሚጠቅሱትና «አባቶቻችሁ ከግብጽ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በየዕለቱ እየማለድሁ ባሪያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር» ተብሎ የተጻፈው ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እያከታተለ  በላካቸው ነቢያት አማካይነት ወደ እርሱ እንዲመጡ በየጊዜው የጠራቸው መሆኑን ይገልጻል። ዛሬም በዐዲስ ኪዳን በሐዋርያትና በሌሎቹም አገልጋዮች እየማለደ ድኅነት የሚገባቸውን ሁሉ እንደሚጠራ ማለት ነው። (2ቆሮ 5፥20)

በጥሪው የተገኘው ውጤት «ነገር ግን አንገታቸውን አደነደኑ እንጂ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም። አባቶቻቸውም ካደረጉት ይልቅ የባሰ አደረጉ» (ኤር 7፥26) የሚል ሲሆን «በየዕለቱ እየማለድሁ» ለሚለው ቃል ሙሉ ትርጉም ይሰጣል። እግዚአብሔር በነቢያቱ ኑ! ብሎ የለመናቸውና እንቢተኛ የሆኑት እነርሱ ናቸው ማለት ነው እንጂ አብ ወደ ሌላ አምላክ ማለደ አያሰኝም።

ስለመንፈስ ቅዱስ በሮሜ 8፥26-27 «እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና ነገር ግን መንፈስ ራሱ የማይነገር መቃተት ይማልድልናል። ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደሆነ ያውቃል፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለቅዱሳን ይማልዳልና» የተባለው በጸሎታቸው ጊዜ ክርስቶስን በማመን ቅዱሳን የሆኑትን ሁሉ መንፈስ ቅዱስ እንደሚረዳቸውና በድካማቸው እንደሚያግዛቸው ያመለክታል። ቅዱሳን በመንፈስ ሆነው ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ በውስጣቸው ሆኖ መንፈሳዊ ነገርን ማለትም ምስጋናን፥ ስለሌሎች ምልጃን፥ ልመናን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከመስጠት ጀምሮ ኃጢአታቸውንም ኢያሳሰበ እንዲናዘዙበትና ከዲያብሎስ ክስ ነጻ እስከማድረግ ድረስ የሚያደርግላቸው እገዛ ነው እንደ ምልጃ የተቆጠረው።

በተጨማሪም መንፈስ ቅዱስ በምእመናን ልብ ውስጥ ለውጥንና መታደስን ያመጣል። (ሮሜ 8፥9፤ ቲቶ 3፥5-7) ለአማኙ የእግዚአብሔር ልጅነቱን እየመሰከረ ወራሸነቱን ያረጋግጣል። (ሮሜ 8፥16፤ 2ቆሮ 1፥22፤ ገላ 4፥6፤ ኤፌ 1፥13-14) መንፈስ ቅዱስ የወረደው ምእመናንን በዚህ መንገድ ለመረዳትና እውነት ወደ ሆነው ሁሉ ለመምራት ነውና። (ዮሐ 16፥13)

ወደ ክርስቶስ ሊቀ ካህንነት ጉዳይ ስንመለስ በተሳሳተ የአተረጓጎም ስልታቸው ንጹሑን የትምህርት ምንጭ እያደፈራረሱና የድኅነታችንን አድራሻ እያጠፉ ሰውና እግዚአብሔርን ለማለያየት ጥረት ቢያደርጉም አባቶች በግእዙ ቋንቋ ያሰፈሩት ጽሑፋቸው ግን እንደፈለጉ የሚያስፈነጭ አይደለም።

ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ የዕብራውያንን መልእክት በተረጎመበት 13ኛ ድርሳኑ ቁ 156 ላይ «ወጊዜ ፈቀደ ይተነብል ሎሙ አኮ በዝንቱ ጊዜ ባሕቲቱ አላ በእንተ ዘትመጽእ ሕይወት ዘለዓለም» ትርጉም፦ «በወደደ ጊዜ ይለምንላቸዋል በዚህ ጊዜ (በዕለተ ዐርብ) ብቻም አይደለም። ከዚያም በኋላ ባለው ጊዜ ለዘላለም ነው እንጂ» በማለት የካቡትን የስሕተት ካብ በትክክለኛ ትምህርቱ ይንዳል።

ትክክለኛውን አስተምህሮ እየበረዙ እየከለሱ ያሉት ወገኖች አምላክነቱ እንዳይዋረድ ሠግተው ከሆነ ቀድሞም ቢሆን ይህ የሊቀ ካህንነቱ አገልግሎት የተከናወነው በሰውነቱ ነው። ስለሆነም በዚህ ምክንያት አምላክነቱ እንዳልተዋረደ ሁሉ አሁንም የሚሆነው ይኸው ነውና አይሥጉ እንላለን።

ለዚህ የከበረ እውነት ጠንቃቆች የነበሩት አባቶቻችን (2ጴጥ 1፥19) ክርስቶስ በሊቀ ካህንነቱ «ስለኛ ይማልድልናል» ካሉ በኋላ «ወኢተናገረ በዝየ በእንተ ህላዌ መለኮት አላ ተናገረ በእንተ ሥርዓተ ትስብእቱ እስm ትስብእቱ ግቡር ውእቱ»  ትርጉም፦ « በዚህ አንቀጽ ስለ ባሕርየ መለኮት አልተናገረም አምላክ ሰው ስለመሆኑ ሥርዓት ተናገረ እንጂ ስጋ ፍጡር ነውና» (ሃይ አበ ምዕራፍ 63 ክፍል 2 ቁ 28)

እንዲሁም ቄርሎስ «ይህ ነገር ፍጡር የሚል እንደሚመስል ነገሩ ግልጽ ነው። ይህም ሰው ስለመሆኑ እንጂ በሌላ አልነበረም። እሱ የባሕርይ አምላክ ሲሆን ሰው በመሆኑ ከአብ ክብርን ይቀበላል። «ሃይ አበ ም 79 ክፍል 50 ቁ 74)

እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን አንድ ነገር አለ፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሁላችን በመሞቱ አንድና ህያው መስዋዕት አድርጎ ራሱን አንድ ጊዜ ለዘላለም አቅርቧል። በተጨማሪም «በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለእነዚህ ብቻ አልለምንም» (ዮሐ 17፥21) በማለቱ ስለሁላችን አንድ ጊዜ ምልጃን አቅርቧል። ይህን ሁሉ ፈጽሞ በአብ ቀኝ ከተቀመጠ በኋላ ዛሬም እንደቀድሞው በመውደቅ በመነሳት፥ ከዳኛ ፊት እንደሚከራከር ጠበቃ በአብ ፊት ስለኛ ይከራከራል ወይም አብን ስለኛ ዘውትር ይለምነዋል ማለት አይደለም። 

ክርስቶስ ከትንሣኤው አስቀድሞ በነበረበት የውርደትና የዝቅተኛነት ሁኔታ አሁን አይታይም። አሁን ያለው ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው ሆኖ በታላቅ ክብር ውስጥ ነው። (2ኛ ቆሮ 5፥16፤ ፊልጵ 2፥9-11፤ ዕብ 2፥9)

ነገር ግን በቀደመው አገልግሎቱ ዛሬም አስታሪቂያችን እሱ ብቻ በመሆኑ በስሙ ስንጸልይና ስንለምን የቀድሞው ጸሎቱና መስዋዕቱ ስለእኛ ጽድቅ ሆኖ በእግዚአብሔር ፊት ይታይልንና (ይቆጠርልንና) ተቀባይነት እናገኛለን። ሐዋርያው እንደመሰከረ ቤዛነቱን ተረድተው በስሙ አምነው በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ሁሉ ለማዳን የዘላለም ምክንያተ ድኂን ሆኖ በሰማያዊቱ መቅደስ እነሆ አለ። በእርሱ መካከለኛነት በኩል ለሚመጡትም ጽድቃቸው ሆኖ በእግዚአብሔር ፊት ለለእነርሱ ይታይላቸዋል። እርሱ የዐዲስ ኪዳን ዋስ ነውና። (ዕብ 5፥9-10፤ 7፥25፤ 9፥24፤ 7፥22)

ዛሬ በእግዚአብሔር ፊት ጽድቅ ሆኖ ያለኃጢአት የሚኖረው በመስቀል ላይ ሥራው ጠላቶች የሆኑትንና በእርሱ አምነው በአስታራቂነቱ በኩል የመጡትን ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ መሆኑን ቄርሎስ እንዲህ ሲል ይገልጠዋል፥
«ዛሬስ በምን ሁኔታ በእግዚአብሔር ፊት ተገለጠ (ታየ)? አምላክ የሆነ ቃል እንደኛ ሰው ሆኖ በዐዲስ ሥራ ታየ። ዛሬ ስለኛ በእግዚአብሔር ፊት በእኛ ባሕርይ በአስታራቂነት ታየ። . . . ዛሬ ስለኛ በእግዚአብሔር ፊት እንደታየ የምንናገረው ነገር ይህ ነው። በአዳም ትእዛዝ ማፍረስ ምክንያት ተዋርዶ የነበረ የሰውን ባሕርይ ገንዘብ አድርጎ በአባቱ በእግዚአብሔር ፊት ገልጦታልና በገንዘቡ ግብር በእግዚአብሔር አብ ፊት አቆመው ቀድሞ እንደነበረው አይደለም። ሰው ሆኖ ታየ እንጂ ዳግመኛ ወደ አባቱ ያስገባን ዘንድ» (ሃይ አበ ምዕ 79 ክፍ 50 ቁ 72-73)

ክርስቶስ ምትክ የሌለው የዐዲስ ኪዳን ብቸኛ አስታራቂ እንዲሆን ካደረጉት ምክንያቶች አንዱና ዋነናው ሕያውና የማይሞት መሆኑ ነው። ሌሎች ቅዱሳን ሰዎችን ስንመለከት የማስታረቅ አገልግሎታቸውን የሚያከናውኑት እስኪሞቱ ድረስ ነው። ከሞቱ በኋላ ግን አይችሉም ነበር። የብሉይ ኪዳን ካህናት በቁጥር የበዙበት ምክንያትም ይኽው ነው። ካህኑ አሮን ከሞተ በኋላ ማስታረቅ ቢችል ኖሮ ሌላ ካህን ልጁ አልዓዛር መተካት አያስፈልገውም ነበር (ዘኍ 20፥22፤ ዕብ 7፥23)

የማስታረቅ አገልግሎታቸው በሞት የመገደቡ ነገር ቁጥራቸውን አበራክቶታል። ሕያው ሊቀ ካህናት ክርስቶስ ግን ለዘለዓለም አይሞትምና የሚተካው አላስፈለገውም።

«ወእመሰ ኢኮነ አሐደ ውእቱ እምኢኮነ ዘኢይመውት ወእልከቱሰ ካህናት ኮኑ ብዙኅነ፥ መዋትያን እሙንቱ ከማሁኬ ዝንቱ አሐዱ በእንተ ዘኮነ ዘኢይመውት ይቤ አስመ ይክል አድኅኖቶሙ ለዝሉፋ እለ ይቀርቡ ኅበ እግዚአብሔር እንተ መንገሌሁ እስመ ለግሙራ ሕያው ውእቱ ወይተነብል ሎሙ። ጠየቀኑ ኦ፤ ፍቁር ከመ ብሂሎቱ ኮነ በእንተ ሥጋዌሁ . . . እመሰኬ ካህን ውእቱ አሜሃ ይተነብል። . . . ይቤ አስመ ይክል አድኅኖቶሙ ለዝሉፋ እስመ ሕያው ውእቱ ለዓለም ወአልቦ ተውላጥ እምድኅሬሁ»

ትርጉም «እርሱ አንድ ባይሆን ኖሮ የማይሞት ባልሆነም ነበር። የኦሪቱ ካህናት ግን የሚሞቱ ስለሆኑ ብዙ ናቸው። እንደዚሁም ሁሉ ይህ አንድ የሆነው የማይሞት ስለሆነ ነው። ሐዋርያው በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ዘወትር ሊያድናቸው ይችላልና ለዘላለም የማይሞት ሕያው ስለሆነ፤ ስለእነርሱም ይማልድላቸዋል። ወዳጅ ሆይ፤ ይማልድላቸዋል ብሎ ያለው ሰው ስለመሆኑ እንደሆነ ተረዳህን? ሊቀ ካህናት በመሆኑ ያን ጊዜ ይማልድላቸዋል አለ . . . ለዘላለም ሕያው ስለሆነ ለዘወትር ያድናቸው ዘንድ ይችላልና አለ። ከእርሱ በኋላም የሚተካ የለም» (የዮሐንስ አፈወርቅ 13ኛ ድርሳን ቁ 129-131፤ 135-136)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሊቀ ካህንነቱ የዐዲስ ኪዳን ብቸኛና ብቁ የሆነ አስታራቂ መሆኑን ስናስብ ብቃቱ የተለካባቸውን መስፈርቶች ማስተዋል ይጠበቅብናል። እግዚአብሔር ከእኛ ከሰዎች ፈልጎ ያጣውን ነገር ያገኘው ፍጹም ሰው ከሆነው ከክርስቶስ ብቻ ነው። ይህም ተፈልጎ የታጣብን ነገር ሕግን ሁሉ መፈጸም ነው። በመሆኑም አንድስ እንኳ ጻድቅ የለም ተባለ። (ሮሜ 3፥11-12) እንደተጻፈው «ሕግን ሁሉ የሚጠብቅ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከል ማንም ቢኖር በሁሉ በደለኛ ነው። » (ያዕ 2፥10)

ካሁን በፊት እንዳየነው የአንዳንድ ቅዱሳን ሰዎች የተወሰነው መልካም ሥራ እነርሱን አስመስግኖ ጻድቅ ቢያሰኛቸው እንኳ የጽድቅ ስራቸው ከኃጢአት ነጻ የሆነ ነበር ለማለት አያስደፍርም። ኖኅንና ሙሴን ብንወስድ እንኳ ስለእነርሱ ሲናገር የእግዚአብሔር ቃል ቅዱሳን መሆናቸውን ይመሰክራል (ዘፍ 6፥9፤ ዘኍ 12፥3፤ 6-8፤ ዘዳግ 34፥10) ይህ ማለት ግን ኖኅና ሙሌ ሕግን ሁሉ ጠብቀዋል፥ ኃጢአትንም አላደረጉም ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። በጻድቅነቱ የተመሰከረለት ኖኅ ከጥፋት ውኃ በኋላ በወይን ጠጅ ሰክሮ ይታያል። ስካር ኃጢአት ነው። (ዘፍ 9፥21) ሙሴም በበኩሉ በቃዴስ በረሃ ለተጠማው ሕዘበ እስራኤል ውኃን ከዐለት ሲያፈልቅ እግዚአብሔርን ያለመቀደስ ኃጢአት ሠርቶ ነበር። በዚህም ምክንያት ወደ ተስፋይቱ ምድር አልገባም (ዘኍ 20፥11-13) እንዲህ ዓይነቱ ኃጢአት ያልተለየው የሰው ጽድቅ በመርገም ደም ከተበከለ ጨርቅ ተለይቶ አይታይም። የኛ የምንለው ጽድቅ በእግዚአብሔር ፊት ምንኛ አስጸያፊ ነው! (ኢሳ 64፥6)

ክርስቶስ ግን በሰውነቱ ኃጢአትን ባለማድረጉና ሕግን በሙሉ በመፈጸሙ የሕግ ፍጻሜ ከመሰኘቱም በላይ በሕግ ፈጻሚነቱ እግዚአብሔር ደስ ተሰኝቶበታል። (ሮሜ 10፥4፤ ማቴ 12፥18-21፤ 3፥15)

በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር ሊመለከተው የሚችል ፍጹምና ጻድቅ ሰው ክርስቶስ ብቻ ሆኗል። ስለዚህም እግዚአብሔር በክርስቶስ ጽድቅ ብቻ ተሽፍነው በክርስቶስ በኩል የሚመጡትን ሁሉ ይቀበላል። ያለክርስቶስ ሰው በራሱ ነገር ወደ እግዚአብሔር ሊቀርብ ፈጽሞ አይችልም። (ሮሜ 3፥21-24፤ ኤፌ 2፥13፤ 18፤ ገላ 2፥15-16)

እኛ በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር እንድንቀርብ ቤዛችን ኢየሱስ ክርስቶስ የኛን ኃጢአት በሥጋው ተሸክሞ በመስቀል ዕዳችንን ለመክፈል ኃጢአተኛ ሳይሆን ኃጢአት ሆኖ ነበር (2ቆሮ 5፥21)

ኃጢአት ማየት ለጻድቅ ባሕርዩ የማይስማማው አምላካችን እግዚአብሔር ልጁን ክርስቶስን ኃጢአት ሆኖ በተመለከተው ጊዜ ፊቱን ከእርሱ መለሰ። ሰዎችም በበኩላቸው የኃጢአታችን ቅጣት ያጎሳቆለውን መልኩን እንኳ የመመልከት ድፍረት ስላልነበራቸው በመሰቀቅ ፊታቸውን ሰውረውበታል። በዚህን ጊዜ ነበር «አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ» ያለው (ማቴ 27፥46፤ ኢሳ 53፥1-6)

እርሱ በእግዚአብሔር ትክክለኛ ፍርድ የኃጢአታችንን ተገቢ ቅጣት በሥጋው ከተቀበለ በኋላ ኃጢአታችን ይቅር ስለተባለ፥ ዕዳችን ስለተከፈለ ከዚህ በኋላ ያድናቸው ዘንድ በእምነት ለሚጠባበቁት ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሆኖ ያለኃጢአት ይታይላቸዋል። (ዕብ 9፥22)

ስለዚህ በአዳኝነቱ አምነን በስሙ ስንጸልይና ስንለምን የእርሱ የጽድቅ ሥራ ለኛ በእምነት ተቆጥሮልን እንጸድቃለን። በመስቀል ላይ የፈሰሰው ደሙም ዛሬም ሕያው ነውና ኃጢአታችንን ያስተሰርይልናል (ዮሐ 14፥13፤ 15፥16፤ 16፥23-24፤ ቆላ 3፥17፤ ሮሜ 3፥25፤ ዕብ 12፥24፤ 1ዮሐ 1፥7)

በጽሑፍ የሰፈሩ ብዙ የቤተ ክርስቲያናችን ጸሎቶች ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የሚቻለው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመጸለይ ብቻ መሆኑን ያስገነዝቡናል። ለምሳሌ እንደሊጦን፥ መስተበቁዕ ዘይነግሥ እንዲሁም በቅዳሴ ላይ እንደ ኅዳፌ ነፍስና መስተብቁዕ ያሉት ጸሎቶች በስተ መጨረሻቸው ላይ «በአሐዱ ወልድከ» «በአንድ ልጅህ» በሚል ተማጽኖ ይደመደማሉ።

በመጽሐፈ ሰዓታት፥ «ኦ! አብ በእንተ ኢየሱስ ርድአነ ክርስቶስ ኅበ አቡከ ኄር አማኅጽነነ» ትርጉም «አብ ሆይ ስለኢየሱስ ብለህ እርዳን ክርስቶስም በቸር አባትህ ዘንድ አደራ አስጠብቀን» የሚልና በኢየሱስ ክርስቶስ መካከለኛነት የቀረበ ጸሎት አለ።

በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የመጸለይን ተገቢነት አባ መልከጼዴቅ በትምህርተ ክርስትና 2ኛ መጽሐፋቸው ሲገልጹ ፦ «ጸሎታችን በእግዚአብሔር ዘንድ ተወዳጅ እንዲሆንና ተቀባይነትም እንዲኖረው በግድ ያስፈልጋል። ያለዚያማ ጻማ ከናፍር ብቻ ሆኖ ይቀራል። ሰማያዊ አባታችን ክብሩ በግልጥ እንዲታወቅ የኛም የድኅንነት እንዲጸድቅ ያስፈልጋል። ስለዚህ ሊጸልይ የሚፈልግ ሁሉ እንዴት መጸለይ እንዲገባው ማወቅ አለበት። ማለት በጌታችን ስም እዲጸልይ እንዲለምን ያስፈልጋል። »  (ትምህርተ ክርስትና 2ኛ መጽሐፍ ገጽ 189)

በአጠቃላይ ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። «አልቦ መኑሂ ዘይክል በጺሐ ኅበ እግዚአብሔር ዘእንበለ ወልድ» «ያለወልድ ወደ እግዚአብሔር መድረስ የሚቻለው ማንም የለም» (ሃይ አበ ም 76 ክፍል 36 ቁ 8)

ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅም በ 33ኛ ድርሳኑ ከቁ 209-218 ባለው ክፍል እንዲህ ብሏል፦ «ይቤ ወናቀርብ ሎቱ መሥዋዕተ ለእግዚአብሔር እመንገለ ዐራቅይናሁ መሥዋዕት ዘይቤ ፍሬ ከናፍር ውእቱ እለ ይትአመኑ በስሙ ወእሉሰ አቅረቡ አባግዐ ወአልህምተ ወንሕነኒ ኢናበውእ ምንተኒ እምእሉ ግብራት አላ አኮቴተ . . . አስመ እግዚአብሔር ይሠምር በዘከመዝ መሥዋዕት መፍትው ለነ ናብእ ሎቱ ዘከመዝ መሥዋዕተ ከመ ያብእ ውእቱኒ ለአብ ወኢይትከህል ያቅርቡ ምንተኒ ዘእንበለ በዐራቅይናሁ ለወልድ»

ትርጉም፦ «በወልድ አስታራቂነት በኩል ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን እናቅርብ አለ። መሥዋዕት የሚለው ስለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮች ፍሬ ነው። እነርሱም (የኦሪት ካህናት) ላሞችንና በጎችን ሠው። እኛ ግን ከእነዚህ መካከል ምንም ምን አናቀርብም፥ ምስጋናን እንሠዋለን እንጂ። እንዲህ ባለው መሥዋዕት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛልና። እንደዚህ ያለውን መሥዋዕት እናቀርብ ዘንድ ይገባናል። እሱም (ወልድ) ለአብ ያቀርብ ዘንድ፤ ያለወልድ አስታራቂነት ምንም ምን ያቀርቡ ዘንድ አይቻልም»

የተቀበረ መክሊት ከተሰኘው መጽሐፍ የተወሰደ

24 comments:

 1. የጌታችን ሊቀ ክህነት እንደዚህ ተተንትኖ አይቼ አላውቅም ነበር። የቀደሙት ኦርቶዶክሳውያን አባቶቻች (እነ ቄርሎስ አትናቴዎስ . . . ያስቀመጡልን ምስክርነት ይገርማል ደስ ይላል። ጽፈው ባያስቀሩት ኖሮ በቢጽ ሀሳውያት ትምህርት ጉድ ሆነን ነበር። በጣም ጥሩ ጽሑፍ ነው።

  ReplyDelete
 2. Hi all,

  Can anyone tell me where I can find the so-called "የተቀበረ መክሊት " book? I would love to read it. The author has attempted to tell us about Jesus Christ's High Priest profile and the purpose. I know EOTC believes that Christ Jesus is the High Priest for eternity through the work He did on the Cross.

  On the other hand, the writer has been inconsistent with himself because:

  (1) First off, he tells us that Christ, being the High Priest, still prays in heaven to His Father for all believers for mercy and remission of our sins. By saying that, he accuses EOTC for not believing that and teaching about it properly and correctly. He further criticizes the church for teaching that His Mastarek (Mediation) is the through His work on the Cross.

  - Evidence:
  *… አይቀርምና ቀጣይነት ያለውን የሊቀ ካህንነቱን አገልግሎቱ ጠቅሰው ገለጻ ሲሰጡ «የዕለተ ዐርቡን ይዞ ይከራከራል፥ ይለምናል አለ እንጂ አሁን የባሕርይ አምላክ ነው» ይላሉ። ---> Look he is protesting Mediation through His work on the Cross. Of course, He is perfect God and perfect Man.

  *«ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ አባቴ ዐርጋለሁ ስለእናንተም አለምናለሁ አላቸው።» (የፋሲካ ድጓ ገጽ 291 3ኛው ዓምድ ላይ)

  * «በወደደ ጊዜ ይለምንላቸዋል በዚህ ጊዜ (በዕለተ ዐርብ) ብቻም አይደለም። ከዚያም በኋላ ባለው ጊዜ ለዘላለም ነው እንጂ»

  * …«ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን የኔ ስለሆኑት ምሕረትን ወደምለምንበት ወደ አባቴ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ አላቸው» (የሠኔ ሚካኤል ዚቅ (ዓራራይ))


  (2) Second off, the author tells us that His Mediation is through His work on the Cross. (Is this not quite opposite to what he said under #1 earlier)

  - Evidence

  * "እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን አንድ ነገር አለ፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሁላችን በመሞቱ አንድና ህያው መስዋዕት አድርጎ ራሱን አንድ ጊዜ ለዘላለም አቅርቧል። በተጨማሪም «በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለእነዚህ ብቻ አልለምንም» (ዮሐ 17፥21) በማለቱ ስለሁላችን አንድ ጊዜ ምልጃን አቅርቧል። ይህን ሁሉ ፈጽሞ በአብ ቀኝ ከተቀመጠ በኋላ ዛሬም እንደቀድሞው በመውደቅ በመነሳት፥ ከዳኛ ፊት እንደሚከራከር ጠበቃ በአብ ፊት ስለኛ ይከራከራል ወይም አብን ስለኛ ዘውትር ይለምነዋል ማለት አይደለም።"

  * "ነገር ግን በቀደመው አገልግሎቱ ዛሬም አስታሪቂያችን እሱ ብቻ በመሆኑ በስሙ ስንጸልይና ስንለምን የቀድሞው ጸሎቱና መስዋዕቱ ስለእኛ ጽድቅ ሆኖ በእግዚአብሔር ፊት ይታይልንና (ይቆጠርልንና) ተቀባይነት እናገኛለን።"

  * "ስለዚህ በአዳኝነቱ አምነን በስሙ ስንጸልይና ስንለምን የእርሱ የጽድቅ ሥራ ለኛ በእምነት ተቆጥሮልን እንጸድቃለን። በመስቀል ላይ የፈሰሰው ደሙም ዛሬም ሕያው ነውና ኃጢአታችንን ያስተሰርይልናል (ዮሐ 14፥13፤ 15፥16፤ 16፥23-24፤ ቆላ 3፥17፤ ሮሜ 3፥25፤ ዕብ 12፥24፤ 1ዮሐ 1፥7)"

  How do you reconcile the above inconsistencies? I believe Christ is the High Priest and eternal Mediaotr between God and the human race. However, your inconsistent narrations are troubling. Also, I am surprised to see you quoting from awalid books.

  ReplyDelete
 3. Nathan, great analysis. I can tell you read the whole thing. I was actually a little confused when I saw the paragraph that started with " እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን አንድ ነገር አለ . . . " You are correct that it seems to contradict with a number of quotes listed in the article. I wish we can ask the writter to elaborate. But if you were to review all the quotes in the article including the once you have pointed out, how would you reconcile it with your current thinking?

  ReplyDelete
 4. to Natan said.. u can follow the ff link to read "yetekebere meklit"

  http://good-amharic-books.com/onebook.php?bookID=179

  ReplyDelete
 5. Thank you so much for the link.

  In Christ, amen!

  ReplyDelete
 6. Nathan and all, I think the writter knows what he is talking about, but somethings don't flow well. Here is how I understand the quotes mentioned


  *«ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ አባቴ ዐርጋለሁ ስለእናንተም አለምናለሁ አላቸው።» (የፋሲካ ድጓ ገጽ 291 3ኛው ዓምድ ላይ)

  ይህ ማለት ይታይልናል ማለት ነው። ወደ እሱ ስንሄድ በክርስቶስ በተሰጠን ድኅነት አምነን ከሆነ አምላካችን የልጁን ንጹህነት ለኛ አድርጎ ሞቱንም የኛ ሞት አድርጎ በመቁጠር ይቀበለናል ማለት ነው። ጌታችን አባቱን እነዚህን ማራቸው ብሎ መለመን አያስፈልገውም። እዚህ ላይ መለመን የሚለው፥ መታየት በሚለው ሲተረጎም ለአእምሮ ይመቻል።

  * «በወደደ ጊዜ ይለምንላቸዋል በዚህ ጊዜ (በዕለተ ዐርብ) ብቻም አይደለም። ከዚያም በኋላ ባለው ጊዜ ለዘላለም ነው እንጂ»

  ይህም ይታይላቸዋል ተብሎ ቢተረጎም የበለጠ ትክክል ነው።

  * …«ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን የኔ ስለሆኑት ምሕረትን ወደምለምንበት ወደ አባቴ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ አላቸው» (የሠኔ ሚካኤል ዚቅ (ዓራራይ))

  አሁንም ይሄ ለእናንተ ወደምታይበት፥ ዋስ ወደ ምሆንበት እንደማለት ነው። ጌታችን መደረግ ያለበትን ሁሉ ስለፈጸመ መለመን አያስፈልገውም።

  ዋናው ነገር፦ እኛ በክርስቶስ ሞት ለምንታመን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ስንታይ የሚታየው የኛ ጎዶሎ ሕይወት ሳይሆን የክርስቶስ ሕይወትና ሞት ነው። እግዚአብሔር የሚያየው እኛን ሳይሆን ልጁን ነው። ልጁ ንጹህ ስለሆነ፥ ዓለም ለበደለውም በደል ካሳ ስለሆነ እኛ ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብ ንጹሐን ሆነን እንታያለን። ይህንን ካመንን አንድ ገጽ ላይ ነው ያለነው።

  ReplyDelete
 7. ሰላም ወገኖች

  ጽሁፋችሁን ባነበውም ትክክል ያልሆኑትን ነገሮች መልስ ለመስጠት ጊዜ ስለሌኝ ጥሩ ጽሁፍ አልጽፍም:: አንዳንድ ነገሮችን ለመጠቆም ያክል::

  1 በመጽሃፍ ቅዱስ በግልጥና በማያሻማ መልኩ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደማይለምን ተገልጿል:: ታዲያ ሌሎች ይለምናል ቢሉ እንዴት ታስማሙታላችሁ:: ጌታ እኔ አልለምንም እናንተ በስሜ ትለምናላችሁ እንጂ ብሏል:: ይህ ቃል የማይቀየርና የማይፋቅ የማይጠፋም ነው:: ታዲያ ዚቁ ይለምናል ይላል ካላችሁ ከመጽሃፉ ቃል ጋር አይጋጭባችሁም ወይ? ወይንስ የእናንተን ሃሳብ ስለሚደግፍ ብቻ ደገፋችሁት?

  2 በክርስቶስ ስም መለመን ማለት እርሱ አማላጅ ነው ማለት አይደለም:: በእግዚአብሄር አብ ስም ራሱ እንለምናለን:: ኪዳናችን ስለቅዱስ ስምህ ስለውዱ ልጂህ ስለኢየሱስ ክርስቶስም ይላል:: ይህ ማለት ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ ለማኝ ስለሆነ ሳይሆን ስሙ መለመኛ ስለሆነ ነው::

  3 ጸሃፊው ተዋህዶን ከመጥላቱ /የራሱን ሃሳብ ለማስረጽ ብቻ ከማሰቡ የተነሳ የግእዙ መጽሃፍ ቅዱስን ኮንኖታል:: ለመሆኑ በሌሎች ትርጉሞች መካከል ያለውን ልዩነቶች ምን ሊላቸው ነው? መጽሃፍ ቅዱሱን ዛሬ በአዲስ በቀላል በዚህ በዚያ እያሉ ልዩ ልዩ ትርጉሞች ሰጥተው ከእውነተኛው ትርጉም እንዲርቁ እያደረጉ ያሉትን አሰልጣኞችህን ምን ትላለህ:: በግሪኩና በግእዙ ብቻ ሳይሆን በራሳቸው ከግሪኩ ተቀዱ በተባሉ የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉሞች ላይ ብዙ ልዩ ነቶች እንዳሉ እስኪ ይረዱልን ጌታው::

  4 ናታን እንዳለው ይህ ጽሁፍ በራሱ የተምታታ ነው:: አላማውም ኦርቶዶክሳዊያንን የቤተ ክርስቲያናቸው ትምህርት አስመስሎ ማደናገር እንጅ ኦርቶዶክሳዊ አይደለም::

  በአጠቃላይ ጊዜ ካገኘሁ የሳታችሁበትን የሚመልስ ነገር ለመጻፍ እሞክራልሁ በተለይ እብራዊያን መልእክትን በሚገባ ማጥናት ስለሚገባ::

  ReplyDelete
 8. እውነት,

  It is a good attempt to mend the big hole and reconcile the inconsistencies. However, I would love to hear from the author himself or anyone who represents him.


  Anonymous,

  I just read the book (190+ pages). The author has thrown some interesting crticisms againt the establishment, which I somehow accept. I thank him for that. However, for the most part, the author has used EOTC books and materials to justify his protestant leaning faith. He seems to disagree with at least 90% of what EOTC teaches. As I said, some his crticisms are justifiable; however, some other are simply misplaced and appear to be an attempt to tell us that "we are wrong and protestant is right" type of thing. The author is smart in the sense that he used only the bible and the EOTC books/awalids to make his point in an attempt to apear orthdox than pente. Anyways, the criticism is a good wakeup call for the chuch. Have we seen any substantive improvement in our church for th last 10 years? If so, the book may have contributed.

  ReplyDelete
 9. የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን! በአንድ ጎን በጥቃቅን የሀሳብ አገላለጽ ልዩነቶች ጎራ በመለየት ለመከፋፈል ማከራ ማየታችን ቢያሳዝነኝም በአንድ ጎን ደግሞ የምናወራው ነገር መሰረታዊ ሀሳብ እጅግ ተቀራራቢ በመሆኑ ደግሞ የተስፋ ጭላንጭል ይታየኛል። ወገኖች እኛ የአንዱ ንጉስ ልጆች ነን። የዚህ ጽሑፍ ጸሐፊም ሆነ አስተያየት ሰጭዎች በክርስቶስ ወንድሞቼና እህቶቼ እንደሆናችሁ አውቃለሁ። ውይይታችንን ሳንዘላለፍ እንቀጥል፦

  Nathan, again thanks for your thoughtful approach to things. When you say "90% of what EOTC teaches", are you saying you know exactly waht EOTC teaches? by the way, I read the book too. What the writter claims is that the true EOTC teaching has been burried under a lot of dirt (overtime by bad teachers and kings). He is claiming that all of the bad teachings in the awalid books are not EOTC teachings. Do you think EOTC has a clearly documented stand on everything? do you really claim to know the exact teaching of the EOTC church? For example, do you know our church fathers are divided almost in half on the doctrin of "የእመቤታችን ጥንተ አብሶ"? Do you know why our fathers are not on the same page on this? Let's not start the 'tinte abso' discussion here, but do you know the EOTC official stand on this? The way I see it, our church needs to do a lot of work to clean up, document, educate her members on "official" teachings.

  Tewahedo, I don't know how you concluded that the writter is EOTC's enemy. To me he is defending the church. To me he is trying to save the church. Do you know that the protestant congregation is increasing members at an exponential rate while ours decrease at the same rate? This generation reads, asks, thinks. ያሉትን ብቻ እየሰማ የሚያምነው ትውልድ አለፈ። so the best way to reverse this trend and save the church is to expose every unbiblical thing and correct it. Blindly defending the church is killng the church in my view. Now questions for you (when you have time)

  How would you explain the quotes mentioned in this article. The quotes that say our Lord prays to his father? Do you think the Zik and the other books need to be correcte?

  ReplyDelete
 10. I love you Nathan, I am sure he has contributed a lot for good. At least I am one of them who are beneficiary from him and other books. Your point is from my understaning, there are some serious problems that our church (Holy Synod) needs to look in to (make correction). But we still need to protect our church from protestantism. Back to the Bible, back to basics & offcourse back to the Lordship of Christ. He is the teacher, highprist and king. He only owns these three titles. Amen!!!

  ReplyDelete
 11. Tewahedo,

  "1 በመጽሃፍ ቅዱስ በግልጥና በማያሻማ መልኩ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደማይለምን ተገልጿል:: ታዲያ ሌሎች ይለምናል ቢሉ እንዴት ታስማሙታላችሁ:: ጌታ እኔ አልለምንም እናንተ በስሜ ትለምናላችሁ እንጂ ብሏል:: ይህ ቃል የማይቀየርና የማይፋቅ የማይጠፋም ነው::"


  You can't take one verse and make doctrin. You have to see whole concept.

  how about the promise (Holy Spirt)?

  እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል - "ይህ ቃል የማይቀየርና የማይፋቅ የማይጠፋም ነው::"

  እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል

  የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።

  ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።

  ሊያማልድ - ሊያድናቸው

  "ታዲያ ዚቁ ይለምናል ይላል ካላችሁ ከመጽሃፉ ቃል ጋር አይጋጭባችሁም ወይ? ወይንስ የእናንተን ሃሳብ ስለሚደግፍ ብቻ ደገፋችሁት?" You may need to answer Ewnet - Do you think the Zik and the other books need to be correcte?

  ReplyDelete
 12. This is the general view that i have regarding our church awalid metsahifit, the tehadisos and you the owners of this blog.
  About the church:
  1. The church has passed lots of ups and downs due to different problems. All dogmatic teachings of the church are right including yekidusan amalagement or any other controversial issue that differ us from Protestants. According to my genuine analysis and comparisons and studies for long period I don’t find that Orthodox Church has false doctrine teachings.
  2. The Synod is very weak that cannot make adjustments on teachings or on administration or any other issues. I can say the synod is dead. It is not seeing any development issues that go for the future generation and that saves the church.
  3. Despite the fact that orthodox has right dogmatic creed and good cannon, there are incorrect histories/gedels that are contained in our books.
  4. The fact that our church is losing many people is not because orthodox has wrong doctrine it is because of the following issues according to my understanding
  a. The church is not addressing its flock properly and in right way. Currently our preachers are preaching the word of God and everything is right as far as I know. However we don’t have very organized way of flock keeping method.
  b. We don’t have enough teachers outside of Addis Ababa.
  c. Our people are poor and becoming psychologically doesn’t respect his own tradition and history. Because of this people especially in the cities are leaving the church.
  d. The church need to be a little modernized. Even though some people like to make some modernizations some group see it as heretic. This leads division.
  e. The church luck modern administration because of non spiritual / non visionary leaders
  5. Some preachers/ specially uneducated ones don’t differentiate tradition, dogmatic and cannons. And they took everything as religion.

  ReplyDelete
 13. Continued ........


  The Tehadisos
  6. I see the tehadisos in two different categories:
  a. Those who want the church to be in correct position:- Knowingly or unknowingly there are some mistaken books and exaggerated concepts which i don’t have to hide. However it doesn’t mean that the church as a whole is wrong in its doctrine or cannon or total belief. So some tehadiso groups may need the church to correct the mistakes. These groups want the correction to be made by the church itself. They don’t want to expose the church to the world and undermine the church of Christ. Rather they want to strength the synod and synod itself will correct any issues that might need correction.
  b. The other group of Tehadiso’s are those who are financed by Protestants. They might get the teaching itself from protestants. They want to create Protestantism inside the Orthodox Church. They want the Orthodox Church to accept every protestant teaching whether it is correct or wrong. They say they are orthodox but they are not real orthodoxs. They are not working for the correction of the church but for changing the church to Protestantism.

  The fight against Tehadiso’s
  7. The fight against tehadiso’s is a little difficult. It has so many controversial issues.
  a. It is not easy to identify who is protestant tehadiso as they are hiding themselves
  b. I know the protestant tehadisos are few in the church but still they are problems
  c. Sometime non protestants may be labelled as protestants
  d. The church is not able to see itself while it is under so many problems
  e. Some people go in the extreme side in fighting against them
  8. From what I saw in this website, I categories this website owner as protestant tehadiso

  ReplyDelete
 14. Dear Blogger,
  When did Jesus said I will beg my Father? It is in Chapter 14 verse 16. Then Jesus begged his father on chapter 17. He begged for all of us. As he said “እኔ ስለ እነዚህ እለምናለሁ፤ ስለ ዓለም አልለምንም ስለ ሰጠኸኝ እንጂ፤ የአንተ ናቸውና፤” on chapter 17 verse 9. He is not saying he will beg for us once he went to heaven. So please check time when Jesus spoke. Jesus had begged for all of us when he was here with us. Now he will no more beg for us.

  ReplyDelete
 15. Good view Tewahedo. Keep it up.

  F

  ReplyDelete
 16. Dears,

  Can you please post my responses as well? I know most bloggers don't want to post their opponent's ideas.


  When did Jesus said I will beg my Father? It is in Chapter 14 verse 16. Then Jesus begged his father on chapter 17. He begged for all of us. As he said “እኔ ስለ እነዚህ እለምናለሁ፤ ስለ ዓለም አልለምንም ስለ ሰጠኸኝ እንጂ፤ የአንተ ናቸውና፤” on chapter 17 verse 9. So please check time when Jesus spoke. Jesus had begged for all of us when he was here with us. Now he will no more beg for us.
  One thing I want to notice you is that you might have learnt the verses that seem as if Jesus is amalage from Westerns but I studied them all in detail. So know that Jesus has begged for us while he was on earth. Now he is no more amalage. It is very wide issue and needs devoted study rather than just taking a verse and posting it here.

  ReplyDelete
 17. Tewahedo,

  It is an excellent observation. I agree with you on most of the points...

  ReplyDelete
 18. lol Tewahedo nice try, but that is told about the Holy Spirt which happens to be ke Erget behuala, read Act 1.


  Sele enante alemenem yalew chapter 16 and yelemenew 17 ...

  ReplyDelete
 19. Tewahedo sorry I hv to say this, you hv not studied at all. Rasehen atatlel bro. The fact that u mentioned chapter 17 is very funy & out off context. selenante alemenem is in chapter 16 & 17 lay lemene. Selemenfes kidus yetenegerew lemena was after Erget ... read Act #1. Menfes kidus degmo yemiwetaw ke Ab becha neew not ke weled ...

  ReplyDelete
 20. Anonymous! It is upto you to accept the justification or not. But Jesus said "I will not beg to U". If you say He begs for us that means Jesus is not keeping His words which will lead you to make Him False teacher. Please just don't defend your idea alone try to understand the whole Christianity concept.

  Peace,

  ReplyDelete
 21. how about
  Jhon 16,26
  1car.5,17

  ReplyDelete
 22. "Tewahedo" Geta Yibarkeh !!! "ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።" 1ኛ ጢሞ.5:8.Ena bakeh lewut latameta yekdeme emnetehen bettebek yeshalehal!!! LEBONA YESTEH LEHULUM WODAJA.

  ReplyDelete
 23. It will take years to gain a specialty in such a spot.
  Promise rings start at $59 and Engagement rings start at about $98 and go to $1998.

  But these colored diamonds were just as large if not larger than many
  of the best colorless diamonds like the Star of Africa, Hope Diamond, etc.


  Also visit my website webpage

  ReplyDelete
 24. The the signs of melasma are dark, irregular well demarcated
  hyperpigmented macules to patches commonly found about the
  upper cheek, nose, lips, upper lip, and forehead.
  As a health supplement, coconut oil is said to deal with skin conditions throughout, as well as help one slim
  down, improve all-around health, and possibly even extend lifespan.
  It might be applied to minor and medium cases but is best suited with severe acne.
  Microtia can demonstrate an inherited pattern among several family members though the specific genes inducing the
  problem may 't be identified by science.

  Also visit my web site :: zeno acne device []

  ReplyDelete