Sunday, July 24, 2011

ዜና - ማሕበረ ቅዱሳን በአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ስም ለአመጽ እየተዘጋጀ ነው . . . Read PDF

የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ‹‹እስከ መሥዋዕትነት ድረስ›› ተዘጋጅተናል ሲሉ ሀገረ ስብከቱን አስጠነቀቁ

በኢቤኤስ ቻናል የሚተላለፈውን ፕሮግራም አውግዘናል
የአዲስ አበባ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ሠራተኞችም ደሞዛቸውን ለአክሱም ሙዚየም ግንባታ ሰጡ መባላቸው ቅሬታ ፈጥሯል

ሰኞ በ11/2ዐዐ3 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ‹‹የወቅቱን የተሀድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴና ተዛማጅ ችግሮችን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በጋራ የተሰጠ የአቋም መግለጫ›› በሚል ርእስ ስር ባወጡት መግለጫ ላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህር ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ኃላፊውን አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤልን፣ በኢቢኤስ ቻናል ታኦሎጐስ በሚል ስም በተሰየመው የአየር ሰዓት የሚተላለፈውን ፕሮግራም አባ ሰላማ፣ ደጀ ሰማይ እና ኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ዶት ኦርግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን የማይወክሉ በመሆናቸው እንቃወማቸዋለን ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡


በዚሁ መግለጫው ላይ ‹‹ቅዱስ ሲኖዶሱ በተለያዩ ጉባኤያት ያስተላለፋቸውና የሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲተገበሩ በአጽንኦት እንጠይቃለን፡፡›› ሲሉም ለቅዱስ ሲኖዶሱ አቋማቸውን  ግልጽ አድርገዋል፡፡

በተሃድሶ ሰባክያን ዘማርያንና በአባ ሠረቀብርሃን አማካይነት በቤተክርስቲያኒቷ ላይ ጥፋት እየደረሰ እንደሆነ የገለጸው የአቋም መግለጫ ‹‹ከቤተክርስቲያን በፊት እኛን ያስቀድመን፣ የቤተክርስቲያንን ጥፋት አያሳየን የሚሉ እስከ ሰማእትነት ራሳቸውን ያዘጋጁ እንደሚኖሩ ማሰቡ ሳይበጅ አይቀርም›› ሲል ሁኔታው በጊዜው መፍትሄ ካላገኘ ሊከሰት የሚችለው ችግር የከፋ እንደሆነ አሳስቧል፡፡ የአቋም መግለጫው እነዚህ ችግሮች ጊዜውን የጠበቀ መፍትሄ ሳይሰጣቸው ቀርተውና ተደፍነው ከቆዩ የምእመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ቁጣ ውስጥ ውስጡን ሲቀጣጠል ቆይቶ ድንገት ከፈነዳ አደጋው በቤተክርስቲያንም ሆነ በአገር ላይ የከፋ ጉዳት ስለሚያደርስ ውጥቅንጡ ከወጣ በኋላ መፍትሄ ለመስጠት ስለሚያስቸግር ሳይቃጠል በቅጠል ማለት ይበጃልና ዛሬ ነገ ሳይባል የእርምት እርምጃ መውሰድ እየተጋጋለ የሚሄድ የሕዝብ ቁጣ ለማስታገስ ይረዳል፡፡ ያለበለዚያ ለሚከሰተው ጥፋት ሁሉ ባለድርሻ አካላት ተጠያቂ ከመሆን አይድኑም›› ሲል ማስጠንቀቂያውን አስተላልፎአል፡፡

በሌላ በተያያዘ ዜና ደግሞ ከትናንት በስቲያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ‹‹የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤት የሥራ አመራር አባላት በሙሉ እንዲጠሩ ስለመጠየቅ›› በሚል ርእስ በላከው ደብዳቤ ‹‹ወጣቶችን በማያውቁት መንገድ ለአመጽና ለሁከት በሚያነሳሳ መልኩ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሆኑት በጠነሰሱት መሠረት የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችን ባልታወቀ መንገድ ፊርማ በማሰባሰብ ማደራጃ መምሪያውን ባለማወቅ እንዲቃወምና ወዳልተፈለገ እንቅስቃሴ እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሏል›› ሲል ከገለጸ በኋላ እሑድ ሐምሌ 17 ቀን 2003 ዓ.ም. ከቀኑ 7፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መሰብሰቢያ አዳራሽ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሚገኙ ገዳማትና አድባራት ያሉ የሰንበት ትምህርት ቤት የአመራር አካላት በሙሉ እንዲገኙ ጥብቅ ጥሪ እናስተላልፋለን ሲል ገልጾአል፡፡

እንዲሁም በሌላ ዜና ቅዱስ ሲኖዶሱ በቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮችና ሠራተኞች ያደረገው የደመወዝ ጭማሪ ለአክሱም ሙዚየም ግንባታ የአንድ ወር ደመወዝ ሁሉም ሠራተኛና አገልጋይ እንዲለቅ በቅድመ ሁኔታ መሆኑና ይኸውም ይተገበር ዘንድ ለግንባታው በቅድሚያ ከቁልቢ ቤተክርስቲያን 15 ሚሊዮን ብር ወጥቶ መከፈሉን ተከትሎ ከሠራተኛው እንዲቀነስ መባሉ ቅሬታ እንደፈጠረ የፍትሕ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፡- ፍትሕ ጋዜጣ ዓርብ ሐምሌ 15 ቀን 2003 ዓ.ም. ገጽ 13

በዚህ ዜና ዙሪያ የአባ ሰላማ ምንጮች ያነጋገሯቸው አንዳንድ የሰንበት ትምህርት ቤት አመራሮችና መግለጫ ለተባለው ሽብር ነዢ ሐተታ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደገለጹት፣ መግለጫው የተቀነባበረውና ፊርማ እንዲሰባሰብ የተደረገው በማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች መሆኑን ጠቁመው፣ ማኅበረ ቅዱሳን ተስፋ ወደመቁረጥ እንደመጣና ሊወሰድበት የታሰበ እርምጃ እንዳለ በመገንዘቡ አባላቱን በየሰንበት ትምህርት ቤቱ እንዲሠራጩ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው፣ ከተቻለ እንዲህ በማስፈራራትና እርሱ የሚፈልገው ለውጥ ካልታየ በቤተክርስቲያኒቱና በአገሪቱ በአጠቃላይ አመጽ ለማስነሣት እየተዘጋጀ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ይህ መግለጫም የዚሁ የሽብር እንቅስቃሴው አካል ነው ይላሉ፡፡ መግለጫው የእርሱ መሆኑን ከሚጠቁሙት ነገሮች መካከል አባ ሰላማ የተባለውን ድረገጽ ጨምሮ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ኃላፊውን፣ በኢቢኤስ ቻናል ታኦሎጐስ በሚል ስም በተሰየመው የአየር ሰዓት የሚተላለፈውን ፕሮግራም፣ ደጀ ሰማይ እና ኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ዶት ኦርግ የተባሉትን ሁሉ መክሰሱ ነው ይላሉ፡፡ ከእነዚህ ከተጠቀሱት ድረገጾችና ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኀላፊ ጋር በባላንጣነት የቆሙት የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አመራሮች ሳይሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን ብቻ ነው ሲሉም የመግለጫው ባለቤት ራሱ ማኅበረ ቅዱሳን እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ መግለጫው በኢትዮጵያ እንዲዘጋ ስለተደረገው ደጀሰላም ስለተባለው የማኅበረ ቅዱሳን ድረገጽ ምንም አለማለቱ ወይም ሊዘጋ አይገባም ይከፈትልን አለማለቱ አያስገርምም ሲሉ እነዚሁ ምንጮች ያክላሉ፡፡

አባሰላማ

14 comments:

 1. so whats wrong with this news? you are one of Tehadisos we want you to clean from our church along with Sereqe. So for me this is a good news.
  Bertu MK and AA senbete temeherete betoche.
  Ben

  ReplyDelete
 2. yehae web site gedilatn dirsanatin yemekawm! non orthodoxawie new!!! tadya leaba sereke tibkina mekom mindin new? tegbarachihu and yhonala!!!!

  ReplyDelete
 3. በቃ ማቅ (ማህበረ ቅዱሳን) እንደ ክርስቲያን ሳይሆን እንደ አልቃይዳ እና ታሊባን ቦምብ በየመንገዱ መጥመድ ሳይጀምር አይቀርም። ድሮም ክርስትና ያልገባው ሁሉ ተሰብስቦ ሌላ ምን ይጠበቃል። ተናግሮ፥ አስተምሮ፥ ተወያይቶ ነገሮችን መፍታት ስለማይቻላቸው ወደ ድብድብ መዞሩ ይቀላቸዋል። የጥፋታቸው ጊዜ እንደቀርበ ያስታውቃል። አይ ክርስትና! ከሞተው ከጌታቸው ምን ተምረው ይሆን?

  ReplyDelete
 4. AbaSelama may not represent EOTC, but it is a free forum unlike DejeSelam that does not allow any view different from theirs and that does not represent EOTC either. DejeSelam represents only Mahibere Kidusan.

  Even if i don't agree with most of the articles that I read on AbaSelama blog, I admire their editorial policy and the free discussion that we enjoy at AbaSelama.

  ReplyDelete
 5. ማቅ እናንተ እንደምታስቡት የወረደ ተግባር ላይ አይሳተፍም፡፡መልሱን የሰ/ት/ቤት ወጣቶች ተሰብስበው ከሚናገሩት ታገኙታላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 6. የሚገርመው ማ/ቅ እራሱ መናፍቅ ነው የአጼ ዘርአ ያእቆብ ተከታይ ነው

  ReplyDelete
 7. Asazagn tiwld malet bewnet igna nen.some forms a group for their own purpose others follow such groups with no info abt them.if one or a group is not on their side ,they do whatever they can to make them hated by the society.what I see on this blog is especially amazing ,it seems ertrian amharic radio which always deal abt EPRDF.You always talk abt MK.The words you use to express MK are ........Ashebari,mahbreseitan ....I am not a member of mk .this mahber has its own defects .but by one or the other way ,i can't compare them to every other mahiber .this is becose this mahiber is doing some objective activities to the church(but others are only talkative either using such blogs or private newspapers).their defect is they consider themselves as the only true church members,their system of administration of their mahiber is complex ,have some errors on their multimedia post,is fast to nominate others as tehadso without trying to discuss with them.but what all they do on tehadiso is right for the current church as they are some forces with in the church who are really devastating.For this bloggers I personally advice u at least to a sensible article on a certain issue.

  ReplyDelete
 8. www.betepawlos.com

  ReplyDelete
 9. Hey,
  you look great on your analysis but still you lack the core. You tried to convince by your literal interpretation. First of all pick the pictures of the true fathers you posted as disguise to be judged as the true hero.
  I knew well Aba Melketsadik, Aba Gorgorious all the rest you posted but they have no any connection with your Agenda. They tried to teach the true way but because there are 'sorgogebs' like you no body heard them even mahbere Kidusan, but still they never get offend because they knew that some are working hard for the sake of our church. They want to exercise as our forefathers did long long time ago. Unfortunately, Nasty 'Hodamoch' like Tehadiso confused all changing their colors like chameleon.
  I understand that politicians joined Mahbere kiqusan through their hidden Agenda and attacked every innocent people who are fighting for true salivation in our church.
  I think you are one of them. If you were not, you shouldn’t write accusing on public the church doctrine and fathers without shame. Those issues you mentioned were able to be corrected inside the church. That was the responsibility of the church fathers not ordinary people like you. Besides we all know that the help of St Michael or St. Gabriel is not due to the script we read but we all exercised through our life. So what? Did you save yourself by writing this? Don’t twist yourself rather pray crying to understand the true confession. I knew my people run to our church when we are in trouble but when we feel we are ok just we would like to act as an outsider.
  There might be some manmade problems in the church that can be corrected through time without our knowledge. As far it doesn’t affect your salvation. Our forefather did a lot of great things through their belief. Go back to the beginning what St. Yared was enjoying while others were still running naked. St. Yared was running from Axum to Gondar and vise versa teaching with guide of the holy spirit. While the western where still looking for the True God, our fathers were enjoying with grace and Holy Spirit. They never run for accusation. They resolve issues inside with ‘Armimo’ not exposing to outsiders. You Gossip the church and act like the true hero. Aba melketsadik never complain infront of the outsiders or in front of others who are ignorant to the church though accused wrongly. They never worry about their name while they are accused throughout their life but for the Dignity of the True God. I knew that they are hardliner but it is for good.
  I knew a lot of tehadiso finding shelter like you but soon things will change God will reveal the true path and Mahbere kidusan will find the true members as before who were working for the church from the bottom of their heart.

  ReplyDelete
 10. ENANTE ERASACHU AGAGAY NACHU LEHEZBU BELACHU NEW YEHENEN ZANA YAKEREBACHEHUT?DARU ANKESEBREHANEM HONE YEKASANCHESU BEROACHU LEGENZEB YETEKUAKAME DEREGET NEW HEZBUN ATAWENABDU.

  ReplyDelete
 11. ene yemilachihu ke kristina wuchi yalu comment adragiwoch slemahibere kidusan metfo biyaworu aygerm'm....bemejemeriya abaselama yemibalew dihregets ketilo lelochachihu min nekachihu mahibere kidusanin endih metechet yawum bemayigeba qal??? bewunet yasaznal.....tehadisowoch ebakachihu yehagerachin higemengist lehaymanot besetew mebt meseret rasachihun chalu enji be ende Mahibere kidusan yemeselu tekuwamat lay yemtworewirutn flatsa tewu mnm yereba gudat layaders atdkemu.....lehulachinim lib yisten...

  ReplyDelete