Tuesday, July 26, 2011

ጥናቱ የማኅበረ ቅዱሳን ወይስ የቤተ ክርስቲያኒቱ? - - - Read PDF

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የራሷ የሆነ ዐቋም ያላትና ዐቋሟን የምትገልጸውም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ወይም እንደ ዜና ቤተክርስቲያን ባሉ ልሳኖቿ በኩል እንደ ሆነ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ውጪ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባል የሆነ አንድ ግለሰብ ወይም ለተለያየ ዐላማ ተሰባስቦ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥር ለመንቀሳቀስ ፈቃድ የተሰጠው አንድ ማኅበር ጽፎ ያሳተመውና ያሠራጨው የኅትመት ውጤት የቤተ ክርስቲያኒቱ ልሳን ተብሎ ለመጠራት ሕጋዊ መሠረት አለው ማለት ያስቸግራል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ሕጋዊ አሠራር ብዙ ጊዜ ሲጠበቅ አይታይም፡፡ ብዙው ሰው ከግንዛቤ ማነስ የተነሣ ወይም በቅንነት እንዲህ ያለ ጥያቄ አለማንሣቱ አይገርምም፡፡ መገናኛ ብዙኃን ይህን ልዩነት መለየት ተስኗቸው መታየቱ ግን ከማስተዛዘቡም በላይ፥ ጠያቂ አካል ቢነሣ ተጠያቂነትን ሊያስከትል እንደሚችል ጥርጥር የለውም፡፡


ይህን ለማለት ያበቃኝ፥ ነጋድራስ ጋዜጣ በቅጽ 08 ቁጥር 249 አርብ ጥቅምት 5/2003 ዓ.ም. ዕትሙ ገጽ 3 ላይ "ቤተክርስቲያኗ ጥናቷን ይፋ አደረገች" በሚል ርእስ ያስነበበው ዜና ነው፡፡ በዚህ ዜና መግቢያ ላይ "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ‘የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ጥናት መጽሔት’ (JOURNAL OF ETHIOPIA CHURCH STUDIES) የሚል ስያሜ የሰጠችውን የጥናት መጽሔት አስመረቀች" ተብሏል፡፡ በዝርዝሩ ውስጥ ግን በተባለው ጥናት ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ እጅ ስለመኖሩ አንድም የተጠቆመ ነገር የለም፡፡ እንዲያውም የጥናት መጽሔቱ የተዘጋጀው በማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማእከል እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡  ከዚያ የታተተው ሐተታ በጥናት መጽሔቱ ይዘት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በጥናት መጽሔቱ የፊት ሽፋን ላይ ያለው ዐርማም የማኅበሩ እንጂ የቤተ ክርስቲያኒቱ አይደለም፡፡ ታዲያ ማኅበረ ቅዱሳን በራሱ ስምና ዐርማ ያዘጋጀውንና ያስመረቀውን የራሱን ጥናት ቤተ ክርስቲያኒቱ እንዳዘጋጀችውና እንዳስመረቀችው ተደርጎ መቅረቡ አግባብ ያለው ነው ሊባል ይችላልን?

እርግጥ እንዲህ ዐይነቱ የጥናት መጽሔት መዘጋጀቱ በራሱ ጥሩ ጅምር በመሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን ሊመሰገን ይገባል፡፡ ሆኖም ማኅበረ ቅዱሳን ስለቤተክርስቲያኒቱ "ጥናት" ሊባል የሚችል ነገር ሊያቀርብ ይችላል ወይ? የሚል ጥርጣሬ አለኝ፡፡ እንዲህ የምለው በዚህ ሥራ ላይ የሚሠማሩት የማኅበሩ አባላት ጥናት ለማቅረብ የሚያስችል ብቃት የላቸውም ለማለት አይደለም፤ በዘመናዊ ትምህርታቸው የገፉ በርካታ ሰዎች በመካከላቸው እንዳሉ አምናለሁና፡፡ ነገር ግን እስካሁን በየልሳኖቹ ከሚያቀርባቸው "ጥናቶች" ለመረዳት እንደሚቻለው ጥናቶቹ ሚዛናዊነት የሚጎድላቸው ሆነው ይታያሉ፡፡ በአንድ በኩል ቤተክርስቲያኒቱን እንከን የለሽና ፍጽምት አድርጎ ያቀርባታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደካማ ጎኗን ጠቀሰ ቢባል እንኳ፣ ግመልን ውጦ ትንኝን የማጥራት ያህል ነው፡፡ ብዙ ጊዜም እንዲህ የሚያደርገው የእርሱ ህልውና የተነካ መስሎ ከታየው ነው፡፡

በሌላም በኩል ሌሎች የክርስትና ክፍሎች በዚች አገር ላይ የሠሩትን ሥራ ሁሉ በክፉ እንጂ በበጎ አያነሣም፡፡ መቼም ከእግዚአብሔር በቀር ፍጹም ስለሌለ እነዚህ ወገኖች በሠሩት ሥራ ውስጥ የፈጸሟቸው ስሕተቶች መኖራቸው አይካድም፡፡ በአንጻሩ ግን ለአገር የሚጠቅሙ ብዙ ሥራዎችንም አከናውነዋል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ግን ደካማ ጎናቸውን ብቻ እያነሣ ሲኰንናቸው ለበጎ ተግባራቸው ግን ዕውቅና መስጠት ይከብደዋል፡፡ ሌላው ቀርቶ እነርሱን በስማቸው እንኳ ለመጥራት ፈቃደኛነቱ የለውም፡፡ ከኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በቀር በዓለም ዐቀፍ ደረጃ በቤተ ክርስቲያንነት የሚታወቁትንና ከአንዳንድ አስተምህሮዎች በቀር በመሠረታዊ የክርስትና ትምህርት ልዩነት የሌላቸውን ሌሎች አብያተ ክርስቲያናትን "ቤተ ክርስቲያን" ብሎ ለመጥራት ሲቸገር ይታያል፡፡ ለምሳሌ፦ የካቶሊክንና የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናትን "ቤተ እምነት"፣ "መናፍቃን" ወዘተ እያለ ነው የሚጠራው (ሐመረ ተዋሕዶ ነሐሴ 2002)፡፡ በእንደዚህ ዐይነቱ ራስን ጻድቅ ሌላውን ኃጥእ አድርጎ የሚመለከት አሠራርን ከሚከተል ማኅበር በግብዝነት የተሞላ ስብከት እንጂ በእውነታ ላይ የተመሠረተና ሚዛናዊነትን የጠበቀ ጥናት መጠበቅ ያስቸግራል ባይ ነኝ፡፡

ብዙዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንንና ማኅበረ ቅዱሳንን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች አድርገው እንደሚመለከቱ ይታወቃል፡፡ እላይ ከጠቀስሁት ሕጋዊ መሠረት አንጻር ግን ትክክል መስሎ አይታየኝም፡፡ እንዲህ ስል ማኅበረ ቅዱሳን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባልና በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃና መመሪያ ሥር የተቋቋመ ማኅበር መሆኑን እየካድሁ አለመሆኑ በቅድሚያ ይታወቅልኝ፡፡ እያልሁ ያለሁት ማኅበረ ቅዱሳን በቤተክርስቲያኒቱ ስም በየልሳኖቹ የሚያስተላልፋቸው መልእክቶች ሁሉ የራሱ ዐቋም እንጂ የቤተ ክርስቲያኒቱ ዐቋም ተደርገው ሊወሰዱ የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም ነው፡፡

ይሁን እንጂ እነዚህ የተለያዩ ጉዳዮች በተለይ በየመገናኛ ብዙኃኑ ሲደበላለቁ ይታያል፡፡ በመንግሥትም ሆነ በግል ሚዲያ ቤተ ክርስቲያኒቱን የተመለከተ ጉዳይ ሲኖር፣ አንዳንድ ጋዜጠኞች የሚመለከተውን የቤተ ክህነት አካል ከማነጋገር ይልቅ ወደ ማኅበረ ቅዱሳን ነው የሚሮጡት፡፡ ይህም ባለማወቅ የሚደረግ ነው ለማለት እቸገራለሁ፡፡ ምልናባት ጋዜጠኞቹ በአንድም በሌላም መንገድ ከማኅበሩ ጋር ግንኙነት ያላቸው ይሆናሉ፤ ወይም ማኅበሩ በየዩኒቨርሲቲው ያፈራቸው የጊቢ ጉባኤው አባላት ይሆናሉ፡፡ በእነርሱም ጀርባ ታዝሎ ማኅበረ ቅዱሳን በየሚዲያውና በራሱም ልሳኖች የሚያሠራጫቸው ትምህርቶች የቤተ ክርስቲያኒቱ ዐቋም ተደርገው እንዲወሰዱለትና ራሱም የቤተ ክርስቲያኒቱ ልሳን ተደርጎ እንዲቆጠር ያላሰለሰ ጥረት እያደረገና በዚህ አቅጣጫ ስኬታማ እየሆነ መምጣቱን መገመት አያስቸግርም፡፡ ለምሳሌ፦ ሰሞኑን በኢቲቪ የእሑድ መዝናኛ ስለ ቆሎ ተማሪዎች የተሠራውን ፕሮግራም መጥቀስ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም በማኅበሩ በመስከረም 16-30/2003 ዓ.ም. ባወጣው ልሳኑ "ስምዐ ጽድቅ" ጋዜጣ ላይ "ንቁ!" በተሰኘው ዐምዱ ሥር "‘ቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር’ በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀሰው ‘ማኅበር’ ስውር ተልእኮ ተጋለጠ" በሚል ርእስ ባወጣው ጽሑፍ ውስጥ ይህን ሁኔታ በግልጽ አንጸባርቋል፡፡

የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን የተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት ለማኅበረ ቅዱሳን ልሳናት (ሐመር መጽሔትና ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ) በጻፉት ደብዳቤና የደብሩ አስተዳዳሪም በሰጡት ቃል በስም የተጠቀሰው ማኅበር በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እያደረሰ ያለውን ተጽዕኖ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ለማሳወቅ "የቤተ ክርስቲያኒቱ ልሳናት" ያሏቸውን የማኅበረ ቅዱሳን መጽሔትና ጋዜጣ መጠቀም ተገቢ መሆኑን እንደ ጻፉና እንደ ተናገሩ 3 ጊዜ ያህል ጠቅሷል፡፡ ሰንበት ትምህርት ቤቱም ሆነ የደብሩ አስተዳዳሪ የማኅበረ ቅዱሳንን ልሳናት ሲጠቅሱ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልሳን የሆነውና ከ60 ዓመታት በላይ ያስቈጠረው አንጋፋው "ዜና ቤተ ክርስቲያን" ጋዜጣ ግን ትዝም አላላቸው፤ ወይም ሐመርና ስምዐ ጽድቅ አስረስተዋቸዋል፡፡   

ማኅበረ ቅዱሳን እንደ ማኅበር ሲታይ በአንድ መምሪያ ሥር ያለ ማኅበር ነው፡፡ እርሱ ግን በሚያደርገው ሰፊ እንቅስቃሴ ምክንያት የሚገኝበት መዋቅራዊ ስፍራ የጠበበው ይመስላል፡፡ ራሱን በመምሪያው ሥር እንዳለ ማኅበር ሳይሆን ከዚያ በላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ብቸኛው ልሳን የሆነ ያህል የሚሰማው መሆኑ ከሚያስተላልፋቸው መልእክቶች መገንዘብ ይቻላል፡፡ በዚህ ሁኔታ ራሱን ብቸኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ ልሳን አድርጎ ለማቅረብ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ቢሆንም፣ ከሕግም ከሞራልም አንጻር ግን ይህን ለመቀበል ያዳግታል፡፡

በሌላ በኩል ይህን ኢሕጋዊና ኢሞራላዊ አካሄድ ዐውቀውም ይሁን በቅንነት እያስተጋቡና ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያኒቱ ልሳን ተደርጎ እንዲታይ ገጽታውን እየገነቡ ያሉት መገናኛ ብዙኃን ናቸው ማለት ያስደፍራል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ማኅበር ዐቋሙን እንዲያንጸባርቅ ዕድል መስጠት አንድ ነገር ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱን ወክሎና ልሳኗ ሆኖ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም የተለያየ ነገር እንዲናገር ማድረግ ግን ሌላ ነገር ነው፡፡ ይህን ሁኔታ ዐውቀው የሚያመቻቹት ምናልባት የማኅበሩ አባላትና ወዳጆች የሆኑ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች (ጋዜጠኞች) ሊሆኑ እንደሚችሉ እጠረጥራለሁ፡፡ ነገሩን በቅንነት የሚያቀርቡቱ ደግሞ ማኅበሩ በሚያደርገው ሰፊ እንቅስቃሴ እንደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ልሳን የቆጠሩት ይሆናሉ፡፡ ከዚህ አንጻር ነጋድራስ ጋዜጣ የቱ ጋ እንደቆመ ግልጽ ሊያደርግ ይገባል፡፡

ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልሳን የመሆን መብት የለውም የምለው በሌላም ምክንያት ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የሚያወጣቸውን የመጽሔትና የጋዜጣ መልእክቶቹን እንደ ማንኛውም መጽሔትና ጋዜጣ በራሱ ኤዲቶሪያል ቦርድ ወስኖ እንጂ፣ ጉዳዩ በሚመለከተው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጋዊ አካል በሕጋዊ መንገድ አሳይቶና ይሁንታን አግኝቶ ስለማይሠራጭም ጭምር ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ መስከረም 23/2002 ዓ.ም. በታተመው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኀላፊ አባ ሠረቀ ብርሃን ማደራጃ መምሪያው የማኅበሩን ልሳኖች የማየት፣ የማረምና አስተያየት የመስጠት እድል እንደሌለው መናገራቸው ይታወሳል፡፡ የማኅበሩ ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ዶ/ር ሙሉጌታ ለዚህ ክስ በሰጡት ምላሽ በማኅበሩ ደንብ መሠረት ይህ ጉዳይ የሚመለከተው ማኅበሩ ያቋቋመው ኤዲቶሪያል ቦርድ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

እስካሁን ለማስረዳት ከሞከርሁት አንጻር ማኅበረ ቅዱሳን የሠራውን ቤተ ክርስቲያኒቱ ሠራችው ብሎ በመገናኛ ብዙኃን ማስተጋባቱ ትክክል አይመስለኝም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንም ራሱን የቤተ ክርስቲያኒቱ ብቸኛ ልሳን አድርጎ ገጽታውን ከመገንባት ባሻገር የቤተ ክርስቲያኒቱ ልሳን እንዲሆን የተሰጠውን ውክልና ሊያሳየን ይገባል፡፡ ነጋድራስ ጋዜጣም የማኅበረ ቅዱሳን ጥናት የሆነውን መጽሔት የቤተ ክርስቲያኒቱ ጥናት መጽሔት አድርጎ ያቀረበውን ዘገባ እንደገና መፈተሽ ይኖርበታል፡፡

መምህር በቃሉ
ከ5 ኪሎ

ምንጭ፡- ነጋድራስ ጋዜጣ የሐምሌ 1/2003 ዓ.ም. እትም

8 comments:

 1. what is the crime? as far as MK published results are in line with the perfect line of the religion, u say this because your different mission could not be achieved as these published products follow-up and publicize the devil act of tehadisos. MK published products ARE NOT CRITICIZED FOR THEIR RELIGION AFFAIRS.PERIOD. AND THEY WILL CONTINUE TO PUBLICIZE THE ENEMIES, EVER!!!!

  ReplyDelete
 2. አንጋፋው ዜና ቤ/ን አላፊ ሰዎችን ማወደስ ትቶ መች የቤ/ን ልሳን ሆነ እና ነው?የፓትርያርኩ ጋዜጣ ቢባል አይሻልም? ማቅ ከሚሰሩት ዘርፈ ብዙ ሥራ አንጻር በአብዛኛው ምዕመን እና ሚዲያ እንደቤ/ን ልሳን መወሰዳቸው አያንስባቸውም። የሚመለከተው ክፍል ሥራውን በተገቢው መንገድ እና ጊዜ ቢሰራ ችግሩ ይቀረፍ ነበር።

  ReplyDelete
 3. Negeru tikikil new hulum guday yasazinal hulu defar- hulu medede-hulu awak-hulu nekafi-hulutekawami-hulu kesashi-hulu balebet-hulu balenbret- meche new and hasab-and kal-and lib yeminhonew Mahibere Kidusan lemahiber mekomu kerto lechurch yemikombet zemen yimetsa yihon tesfa adergalehu kenu siders-kunaw simola ayikerm ahun yalewn enkisikase beyekenu teketatlachihu asnebibun D.Daneil Kibret yetemesegene sew new lehager-lewegen -maseb yichilal bemahiber dereja kemewesen yilk lemelaw ethiopia hizib mekom yishalewal D.Daneil Kibret giltsina mihur awak derek sew nena Egiziabher Kekifu neger Yitsebkew

  ReplyDelete
 4. Yenatenem tshufe beZena bate-krestiyan awetuna asayune

  ReplyDelete
 5. oh my god!! how many optimist-menafkan are there? would u need to replace 'abaselama' as the church representative media instead? don't u know that 'hammer' and 'siema tsiedk' are ,thoroughly, evaluated by church fathers before being issued? ok, have u ever got ,religious based problems in these medias? why do u oppose the truth?DREAM!!!!!
  Download: www.ieType.com/f.php?Fnnw9W

  ReplyDelete
 6. To All:
  Dialogue...Dialogue....discuss! Don't fight. Care for your salvation so you may save me your brother. No one shall put anything before the church( mahbere miemenan)...we are of diffrent origin background and level of understanding...we should teach and win the heart of others through patience and sermons and good deeds not by accusation...do not insult anyone but teach them...show them where they are wrong according to the teaching of the chruch.... don't call anyone "menafiq" instead challenge there mistake.... if you don't know the answer then learn from your fathers!

  God bless!!

  ReplyDelete
 7. lemin fird bet atihedum????????ha?

  ReplyDelete
 8. ማህበሩ የቤተ ክርስቲያኒቱ አይደለም ነው እያሉን ነው:: ማህበረ ቅዱሳን የሚሰራቸው ስራዎች የቤተ ክርስቲያን ለመሆናቸው ምንም አያጠያይቅም:: ማ/ ቅ የቤተ ክርስቲያን ነኝ ማለቱ እና በመሆኑ እርስዎ ያሉዋቸው ክስተቶች ሊፈጠሩ ችለዋል ወደፊትም ይችላሉ:: ችግር የሚሆነው ማ/ቅ ቤተ ክርስቲያን የኔ ናት ያለ ዕለት ነው:: ያንን ደግሞ ብሎም አያውቅም ወደፊትም እንዳይል የራሱ ህግ ይገዛዋል::ካቶሊካውያን እና ፕሮቴስታንትን ቤተ ክርስቲያን ብሎ መጥራት ይከብደዋል ላሉት ከአራተኛው ጉባኤ በኋላ ካቶሊኮች ሁለት ባህርይ ሲሉ ተዋህዶዋውያን ደግሞ አንድ ባህሪ ብለው ተለያይተዋል:: መለያየታቸውን ማ/ቅ የፈጠረው አይደለም የቀደኑ አባቶቸችንስ ጉባኤውን የውሾች ጉባኤ ብለውት የለ:: ስንት ሰውስ አለቀ:: መለየታቸው በትንሹ እንድህ ሁኖ ሳለ ማ/ቅ የለያቸው ለምን ያስመስላሉ::

  ReplyDelete