Monday, August 29, 2011

በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የተሠወረውን አመጽ ማጋለጥ ለምን አስፈለገ?

 አባ ሰላማ ድረ ገጽ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ መጻፍና የተሠወሩ ክህደቶችን ወደ አደባባይ እያወጣች ማስነበብ ከጀመረች ጀምሮ ብዙ ጩኾቶችን እየሰማን ነው። ብዙ ሰዎች በኢሜይል አስተያየታቸውን ጽፈውልናል። የሕዝቡን፣ የጳጳሳቱን፣ የካህናቱን፣ የአገልጋዮችን እንዲሁም የማህብረ አዱሳን አባላትን አስተያየት አዳምጠናል። ያገኘናቸው አስተያየቶችና ምላሾቻችንን እንደሚከተለው አቅርበናል።

Friday, August 26, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን የራሱ ብቻ እንጂ የቤተክርስቲያኒቱ ልሳን ሊሆን አይችልም - - - Read PDF

ጥናቱ የማኅበረ ቅዱሳን ወይስ የቤተ ክርስያኒቱ በሚል ርእስ በነጋድራስ ጋዜጣ ሐምሌ 1/2003 ለወጣው ጽሑፍ፣ ትዝብት ዘቀኖና “የጥናት መጽሔት ልሳን አይደለም!” በሚል ርእስ በዚሁ ጋዜጣ የሐምሌ 8/2003 እትም ላይ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ መላሹ በመጀመሪያ በመምህር በቃሉ የተጻፈውን የሕጋዊነት ጥያቄና የቀረቡትን ማስረጃዎች በሚያመዛዝን አእምሮ ከመመለስ ይልቅ፣ በጽሑፉ ፈጽሞ ያልተነሡ ጉዳዮችን መምህር በቃሉ እንዳነሡ አስመስለው በማቅረብ ጉዳዩን ወደ ሌላ አቅጣጫ ለመውሰድ ጥረዋል፡፡ ይህም የተለመደ የማኅበረ ቅዱሳን አካሄድ ስለ ሆነ፣ ችግሩ ከቤቱ (ከማኅበረ ቅዱሳን) ነው ከማለት በቀር ሌላ ምንም ሊባል አይችልም፡፡ ምላሽ ብለው የሰጡት አስተያየትም ሌሎች ጥያቄዎችን የሚያስከትል በመሆኑ ይህ ምላሽ ትኩረቱን በነዚያ ላይ ያደርጋል፡፡ 

Thursday, August 25, 2011

ተረፈ ኤርምያስ ትርፍ ነገር ይናገራል . . . Read PDF

«ተረፍ» ከዋናው ያልተቆጠረ፤ የቀረ፤ የተረፈ፤ ሳይጨመር የተተወ፤ ትራፊ፤ ቀሪ የሚል ጽንሰ ሃሳብ የያዘ ቃል ትርጓሜ ነው። እንደዚሁ ሁሉ «ተረፈ ኤርምያስ» በሚል ርእስ ከአዋልድ (ዲቃላ) መጽሐፍ ዝርዝር የተቆጠረው መጽሐፍ ከነቢዩ ኤርምያስ ዋናው የትንቢት መጽሐፍ ተጎርዶ የቀረ፤ ያልተጨመረ፤ የተተወ ስለሆነ፤ ምንም እንኳን በአይሁዳውያን ዘንድ በቋንቋቸውና በነቢያቶቻቸው የተጻፈ ስላይደለና ስለማያውቁት እንደብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ባይቆጥሩትም የካቶሊክና የኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት እንደብሉይ ኪዳን ትርፍ የኤርምያስ መጽሐፍ ቆጥረው ይቀበሉታል።  

ሙሉውን ለማንበብ የጽሑፉ ርዕስ ላይ ይጫኑ

Sunday, August 21, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን (ማቅ) VS ተሐድሶ = አይሁድ VS ክርስቲያኖች - - - Read PDF


ዘመኑ የቱንም ያህል ቢሠለጥን፣ ሰዎች የፈለጉትን እምነት የመከተልና የማስፋፋት ተፈጥሮኣዊ መብታቸው በሕገመንግሥት ቢረጋገጥ፣ የወንጌል ጠባይ ግን አይለወጥም፡፡ ወንጌል ትናንት በመከራና በስደት ውስጥ ነው የተሰበከው፤ ዛሬም ወንጌል በዚያው በተለመደው የስደት ታሪክ ውስጥ ነው የሚሰበከው፤ ነገም ቢሆን የሚለወጥ ነገር የለም፡፡ ይህም የሚሆነው ወንጌል ጠብአጫሪ መልእክት ስላለው አይደለም፤ እንዲያውም ለሰዎች ሰላምና ዕረፍት ያለበት የምሥራችን የያዘ መልካም ዜና ነው፡፡ ነገር ግን ምንም መልካም ዜና ይዞ ቢመጣ፣ የዚህ ዓለም አምላክ የተባለ ሰይጣን ልቡናቸውን ያሳወረባቸውና እግዚአብሔርን በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መሠረት ያላወቁት ሰዎች፣ በተለይም ሃይማኖተኛ ነን ባዮች አጥብቀው ይቃወሙታል፡፡

Saturday, August 20, 2011

የዓመቱ አሳዛኝ ታሪክ

«ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይነጋም» .......  የጌታን ቃል ጠንቅቀን እናስተምር
በሪፖተር
ሰላማዊት ከበደ (ስሟ ተቀይሯል)፡፡ በሁለት ዓይነት የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ትገኛለች፡፡ ቤት ተከራይቶ ያስቀመጣትና የሚረዳት የውጭ ዜጋ ወጣት አለ፡፡ በሌላ በኩል አፈቅረዋለሁ የምትለው ሌላ ኢትዮጵያዊ ጓደኛም አላት፡፡
ዕድሜዋ አሥራ ዘጠኝ እንደሆነ፤ ከፍቅረኛዋ ጋር ከሦስት ዓመት በላይ አብረው መቆየታቸውን ትናገራለች፡፡ እሷ እንደምትለው ከውጭ ዜጋው ወዳጇ ጋር ከተገናኙ ከአንድ ዓመት በላይ ሆኗል፡፡

ታላቅ እህቷ የውጭ ዜጋ ወዳጅ ነበራት፡፡ በዚህም በተደጋጋሚ ወደ ውጭ ትመላለስ ነበር፡፡ ደህና ሊባል የሚችል ገንዘብም ነበራት፡፡ ቤተሰባቸው በጣም ችግረኛ የሚባል ያልነበረ ቢሆንም የታላቅ እህቷ ከውጭ ዜጐች ጋር ወዳጅነት በመመሥረትና ገንዘብ ማግኘት የቤተሰባቸውን ይሁንታ አግኝቶ ነበር፡፡ ዛሬም ታላቅ እህቷ የአንድ የውጭ ዜጋ ቅምጥ ስትሆን ሐበሻ የወንድ ጓደኛም አላት፡፡ በዕድሜ የገፋው (ሰባ ዓመት) የውጭ ዜጋ ወዳጇ ሕልፈተ ሕይወትን እሷም ፍቅረኛዋም በጉጉት እንደሚጠባበቁ በተለያየ ጊዜ በግልጽ ስትናገር ትደመጣለች፡፡

Wednesday, August 17, 2011

ፓትርያርኩ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖና ውጪ ለሚንቀሳቀሱ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

በጋዜጣው ሪፖርተር
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ፣ ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቀኖና እና ሥርዓት ውጭ በሆነው ሁኔታ ‹‹እገሌ ተሐድሶ ነው››፤ ‹‹እገሌ መናፍቅ ነው›› የሚል እንቅስቃሴ፣ ከሐምሌ 25 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ሕገወጥ መሆኑን እና ጥብቅ ቁጥጥርም እንደሚካሄድበት አስታወቁ፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ አረጋግጦ ካልወሰነ በስተቀር ከዚህ ውጭ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚካሄድበትም ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡

Monday, August 15, 2011

ለዳንኤል ክብረት - - - Read PDF

እውነቱን በማውጣትህ እናመሰግንሃለን፣ ይቅርታ በመጠየቅህ እናደንቅሃለን፣ ለማስተባበል በመሞከርህ ግን ለክብርህ እንጂ ለእውነት የማትቆም ሰው መሆንህን እንረዳለን።
ማህበረ ቅዱሳን የፖለቲካ ድርጅት ነው የምንለው ስም ለማጥፋት ሳይሆን እውነትን በድርድር ለመቅበር ሲታገል እያየነው ስለሆነ ነው። ሃይማኖት የፖለቲካ ሥራ አይደለም። ዳንኤል የማህበረ ቅዱሳንን አላማና አካሄድ ምንም ሳይደብቅ ነግሮናል። ይህን ዳንኤል ሳይነግረን ብዙዎቻችን አስቀድመን ተናግረናል። ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን የተባለው መጽሐፍ ከሦት ዓመት በፊት አስረግጦ ነግሮን ነበር። ያን እውነታ መንፈስ ቅዱስ አፉን ጸፍቶ የማህበሩ ቀንዳም አወጣው። ይህ ለዳንኤል ስሕተት ሊሆን ይችላል (በማህበሩ አባላት ካለው ክብር የተነሣ) አባላቱ ከነርሱ ተሰውሮ የሚኖረውን የማህበሩን ምሥጢራዊ እውነታ ማወቃቸው አደጋ ስለሚሆን ለዳንኤል ይህን ምሥጢር ማጋለጡ ስሕተት ነው። እርሱም ምሥጢሩን ከጊዜ በኋላ የደረሰበት መሆኑን ለቅርብ ጓደኞቹ ከሚያወራው ወሬ ለመገንዘብ ችለናል። 

በማህበረ ቅዱሳን የተተከሉት የ“አቡነ መንግስቱ” እና የ“አቡነ መስፍን” መናብርት ለጽድቅ ወይስ ለቄሳርነት? - - - Read PDF

መልከፀዴቅ ዘማህበረ በኵር
27/11/2003ዓ.ም.
ክፍል ፩
የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰ ስፍራ ሲቆም

እንግዲህ በነብዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል
ማቴ.፳፬፥፲፭
የቤተክርስቲያን ራስ የሆነው እየሱስ ክርስቶስ የዳግም ምጽዓቱ ምልክት ምን እንደሆነ ሃዋርያቱ ሲጠይቁት በነብዩ ዳንኤል የተነገረውን ትንቢት በመጥቀስ የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰ ስፍራ ሲቆም ያኔ አስተውሉ  የሚል ምላሽ ሰጥቶ ነበር። ይህንንም ያነሳሁት ስለእለተ ምጽአት መቃረብ ሀተታ ለመስጠት አይደለም። ትንቢቱም ምልክቱን ባየን ቁጥር አለም መጥፊያዋ ደረሰ እንድንል አልተነገረም።  ዋናው ቁም ነገር ከጥፋት ርኩሰቶች ውስጥም አንዱና ዋናኛው ፖለቲካ ዓላማ አራማጅ የሆነ ዓለማዊ ሃይል በተቀደሰው ስፍራ ተደላድሎ ሲቆም ቤተእግዚአብሄርንም ለፍላጎቱ ማስፈጸሚያ ሲያደርግ ታላቅ ጥፋት እንደሚያደርስ አስተውሉ የተባለውን ላሰምርበት ፈልጌ ነው። ይህም እውነት በዘመን ፍጻሜ ብቻ ሳይሆን ምንጊዜም ርኩሰት በተቀደሰው ስፍራ ሲቆም ጥፋት ሊከሰት እንደሚችል አውቀን እንድናስተውልም ትንቢቱ ያስጠነቅቃል። ላለፉት ሃያ ዓመታት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ደጄ ሰላም የቆመው ማህበረ ቅዱሳን  ይህ የማስጠንቀቂያ ደወል እንድናስተውል የግድ የሚለን የጥፋት ርኩሰት መሸከሙ ይስተዋልበታል።

Saturday, August 13, 2011

የጥናት መጽሔት ልሳን አይደለም! - - - Read PDF

ሐምሌ 1 ቀን 2003 ዓ.ም. በዚሁ ጋዜጣ በመምህር በቃሉ ከ5 ኪሎ የጻፉት ጽሑፍ ‹‹ጥናቱ የማኀበረ ቅዱሳን ወይስ የቤተክርስቲያኒቱ›› በሚል ርዕስ የቀረበውን ጽሑፍ አንብቤአለሁ፡፡ የራሴንም አስተያየት ለመጻፍ ተገድጃለሁ፡፡ የወንድሜ ጽሑፍ ቅንነት የጐደለው መሆኑ የሚታወቀው በጥቅምት 5 ቀን 2003 ዓ.ም. ለወጣ ጽሑፍ ከ10 ወራት በኋላ ሐምሌ 1ቀን 2003 ዓ.ም መልስ ለመስጠት መሞከራቸው በቂ ማሳያ ነው፡፡ ጸሐፊው ራሳቸውን መምህር የሚጠበቅ ስላልሆነ ከይቅርታ ጋር አቶ ብዬ ልጠራዎት ተገድጃለሁ፡፡

በመጀመሪያ አቶ በቃሉ ያነሱት ሐሳብ ከተነሱበት ጭብጥ ያፈነገጠ እዚያም እዚህም የሚረግጥ፣ አንባቢን ግራ ለማጋባት ታስቦ መሆኑን መረዳት አያዳግትም፡፡

Tuesday, August 9, 2011

ውዳሴ ማርያም - - - Read PDF

ልመናስ ከዚህ በኋላ ስንኳን በእርሷ በሌሎችም የለባቸውም። በቀደመ ልመናዋ የምታሥምር ስለሆነ እንዲህ አለ እንጂ። {የሰኞ ውዳሴ ምርያም ትርጉም፣ ሰዓሊ ለነ ቅድስት የሚለውን ሲተረጉም}
ውዳሴ ማርያም የተባለው መጽሐፍ የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ድርሰት ነው። በዚህ ድርሰት ውስጥ ምስጢረ ሥላሴን፣ምሥጢረ ሥጋዌን በጠቅላላው ነገረ መለኮትን ልንማርበት እንችላለን። ድርሰቱ ድንግል ማርያም ከጌታ የተሰጣትን ክብር በማድነቅ ጠለቅ ያለ ሥነ መለኮታዊ ምስጢር ያስተምራል። ውዳሴ ማርያም ከሚለው ስያሜ ይልቅ ነገረ መለኮት የሚል ስያሜ ቢሰጠው ለያዘው ሐሳብ በጣም ቅርብ ይሆናል። ቅዱስ ኤፍሬም ይህን ድርሰት ሲደርስ በራሱ ነገረ መለኮትን መተርጎሙ ስለሆነ የቅዱስ ኤፍሬም ሥነ መለኮት ትርጉም ሊባልም ይችላል።

Thursday, August 4, 2011

በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ላይ መዋሸት ይቁም! ክፍል 5 - - - Read PDF


ሰባ ስምንት ነፍ የገደለው ሰው [በላኤ ሰብእ]በጥርኝ ውሃና በማርያም ጥላ ዳነ [ታምረ ማርያም 1289-120]
እኔ መንገድ እውነት ሕይወትም ነኝ በኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም [መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐ 146]

ታምረ ማርያም የተባለው ጉደኛ መጽሐፍ ድንግል ማርያምን ያከበረ የሚመስል ነገር ግን ስድብ እና ክህደት የሞላበት መጽሐፍ መሆኑን ደጋግመን ለማሳየት ሞክረናል። መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈ 1400 ዓመት በኋላ በኢትዮጵያ ንጉሥ በዘርዓ ያዕቆብ የተደረሰ ሲሆን በወቅቱ የነበሩ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት እና ምእመናን ይህ ልዩ ወንጌል ከሐዋርያት ትምህርት የወጣ ስለሆነ አንቀበለውም በማለታቸው፣ እስከ አንገታቸው በጉድጓድ ተቀብረው በጭንቅላታቸው ላይ የፈረስና የከብት መንጋ እንደተነዳባቸው ምላሳቸውንና አፍንጫቸውን እንደተቆረጡ እራሱ ታምረ ማርያም ይመሰክራል። [ታምር 24 እና 25 ገጽ 112- 121]