Thursday, August 4, 2011

በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ላይ መዋሸት ይቁም! ክፍል 5 - - - Read PDF


ሰባ ስምንት ነፍ የገደለው ሰው [በላኤ ሰብእ]በጥርኝ ውሃና በማርያም ጥላ ዳነ [ታምረ ማርያም 1289-120]
እኔ መንገድ እውነት ሕይወትም ነኝ በኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም [መጽሐፍ ቅዱስ ዮሐ 146]

ታምረ ማርያም የተባለው ጉደኛ መጽሐፍ ድንግል ማርያምን ያከበረ የሚመስል ነገር ግን ስድብ እና ክህደት የሞላበት መጽሐፍ መሆኑን ደጋግመን ለማሳየት ሞክረናል። መጽሐፍ ቅዱስ ከተጻፈ 1400 ዓመት በኋላ በኢትዮጵያ ንጉሥ በዘርዓ ያዕቆብ የተደረሰ ሲሆን በወቅቱ የነበሩ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት እና ምእመናን ይህ ልዩ ወንጌል ከሐዋርያት ትምህርት የወጣ ስለሆነ አንቀበለውም በማለታቸው፣ እስከ አንገታቸው በጉድጓድ ተቀብረው በጭንቅላታቸው ላይ የፈረስና የከብት መንጋ እንደተነዳባቸው ምላሳቸውንና አፍንጫቸውን እንደተቆረጡ እራሱ ታምረ ማርያም ይመሰክራል። [ታምር 24 እና 25 ገጽ 112- 121]
ታምረ ማርያምን ቁጭ ብለን በማስተዋል ብንመረምረው መጽሐፍ ቅዱስን ለመቃወም የክርስትናን ትምህርት ለመበረዝ በጠላት ሆን ተብሎ የተቀመመ ይመስላል። አጼ ዘርዓ ያዕቆብ እስራኤላዊ ነኝ ስለሚል ምን አልባት አይሁዶች መሲሐዊ እምነታችንን ለማጠፋት የፈጸሙት ሴራ ይሆን? ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል። ዘራ ያዕቆብ አይሁዳዊ ነኝ እያለ ይመካ ነበር፤ ከዚያም አልፎ የይሁዳ ነገድ ነኝ ይል ነበር። አባ እስጢፋኖስ ግን ኢትዮጵያዊ ነህ አትዋሽ ከአይሁዳዊነት ይልቅ ክርስቲያን መሆን ይበልጣልና በዚህ አትመካ በማለት እንደተከራከረው ገድለ እስጢፋኖስ ይናገራል [በሕግ አምላክ በፕሮፌሰር ጌታቸው]
መጽሐፉን ዛሬ መመርመር ለምን አስፈለገ? የሚል ጠያቂ ሊኖር ይችላል፣ መልሳችን አብዛኛው የዋሕ ምእመን እምነቱን የመሠረተው በታምረ ማርያም ላይ ነው የሚል ሥጋት ስላለን ነው። ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄድ ታምሯን ሰምቼ ልምጣ እንጂ ወንጌል ሰምቼ ልምጣ ብሎ አያስብም፣ እሑድ እሑድ ታምር የሚያነብ እንጂ ወንጌል ለማስተማር የሚያስብ ቄስም የለንም። 400 000 ካህናት እንዳላት የሚነገርላት ቤተ ክርስቲያናችን ታምረ ማርያም አንብቦ ከማሳለም ያላፈ አገልግሎት የሚሰጥ አይደለም።  በተለይም ታምሯን ሰምቶ የሄደ ሥጋውና ደሙን እንደተቀበለ ይቆጠርለታል የሚለው ባዕድ ወንጌል ብዙ ሕዝብ ወደ ስጋውና ደሙ እንዳይደርስ ስላደረገው ይህም የስሕተት ትምህርቶች ውጤት ሆኖ ስላገኘነው፣ ሲኖዶሱ ከተኛበት እስኪነቃ ድረስ ጩኸታችንን አናቆምም። ወደ ተነሳንበት እርስ እንመለስ፥
መጽሐፉቅምርበሚባል አገር አንድ ሰው ነበር በማለት ታሪኩን ይጀምራል
ወኢየበልዕ እክለ ወኢ ሥጋ ላሕም ወኢ ካልአ እንሥሣ አላ ይበልዕ ሥጋ ሰብእ
ትርጉም እህል፥ የላም፥ ሥጋ የሌሎችንም እንሥሳ ሥጋ አይበላም ነበር የሰው ሥጋ ይበላ ነበር እንጂ 68
«ወዘበልዖሙሰ ሰብእ የአክሉ ፸ወ፰ተ ነፍሳተ ወኀልቁ ወተወድኡ ዓርካኒሁ ወፍቁራኒሁ ወአዝማዲሁ ወመገብቱ»  ትርጉም «የበላቸውም ሰዎች 78 ነፍሳት ያህላሉ ባልንጀሮቹ ወዳጆቹም ዘመዶቹም ቤተ ሰቦቹም አለቁ ተጨረሱ» 69
ሰውየው ልጆቹን ከበላ በኋላ ከቤት ወጥቶ ሄደ በማለት ታሪኩ ይቀጥላል። ሲዞርም ሁለንተናው በደዌ ሥጋ የታመመ ሰው አገኘ።( 92) ሊበላው አስቦ ነበር ነገር ግን በደዌው ምክንያት ሰለጠላው ሊበላው አልወደደም። በደዌ የተያዘው ሰው ግን ፈጽሞ የተጠማ ስለነበረ በላዔ ሰብን ስለ እግዚአብሔር ብለህ ውሃ አጠጣኝ አለው፣ በላዔ ሰብእ ግን ተቆጣ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ስለ ጻድቃን እና ስለ ሰማዕታት አጠጣኝ አለው፤ አሁንም በላዔ ሰብእ ፈጽሞ ተቆጣው ሊያጠጣው አልፈለገም። የተጠማው ሰው ሦስተኛ ፈጣሪን ስለወለደች ስለማርያም አጠጣኝ አለው። በዚህ ጊዜ በላዔ ሰብእ እስኪ ቃልህን ድገመው አለ፤  አምላክን ስለወለደች ስለማርያም ብለህ አጠጣኝ አለው በዚህ ጊዜ በላዔ ሰብእ «ስለዚህች ስም ከሲኦል እንደምታድን ሰምቻለሁ» አለ አሁንም እኔ በሷ ተማጽኛለሁ በማርያም ስም እንካ ጠጣ አለው። ውሃው ትንሽ ስለነበር እጁ ላይ ፈሶ ቀረ ጉሮሮውንም አንጣጣው እንጂ ጥሙን አልቆረጠለትም በማለት ያጭውተናል። ነገሩን ስናስተውለው በላዔ ሰብእ ስለ እግዚአብሔር ተብሎ በእግዚአብሔር ስም ሲለመን፣ እግዚአብሔርን አላውቅም ብሏል። እንዲያውም ስሙ ሲጠራ ተቆጥቷል። በማርያም ተብሎ ሲለመን ግን ውሃውን ሰጠ። የእግዚአብሔርን ይቅርታ ተጠራጥሮ በማርያም ስም በሰጠው ውሃ እንደሚድን ነው ያመነው። የክህደቱ ምሥጢር እዚህ ላይ ነው። ይህ ትምህርት ህዝባችንን በሚቀቀለው ንፍሮ፣ በሚጠመቀው ጠላ፣ በሚዘከረው ዝክር እድናለሁ የሚል አጉል ተስፋ እንዲይዝ አድርጎታል። ዝክርሽን የዘከረ፣ ስምሽን የጠራ ይድናል የሚለው ባዕድ ወንጌል ተቀባይነት እንዲያገኝ የበላዔ ሰብን ልብ ወለድ ታሪክ እንደማስረጃ አድርጎ ለማሳመን ለሕዝብ የቀረበ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ ይላል፦

«እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።
ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ፥
እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤
ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው» ቲቶ 33-7

እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለነበረው ሥራ አይደለም የሚለውን እውነተኛ ወንጌል ለመሸፈን ጠላት በጥርኝ ውሃ ጽድቅ አለ ብሎ አታለለን። ይገርማል!
ታሪኩ ይቀጥልና የምድሩን ጨርሶ በላይ በሰማይ በእግዚአብሐር የፍርድ ዙፋን የተከናወነውን በታዛቢነት ተቀምጦ ያየ ይመስል ሊነግረን ይሞክራል።  በላዔ ሰብእ አንድ ዋሻ ውስጥ ገብቶ ሞተ «ወመጽኡ መላእክተ ጽልመት በአፍርሆ ወበ አደንግጾ ወከበብዎ ወአውጽኡ ነፍሶ በጕጸት ወበግዱድ» ትርጉም «በማስፈራትና በማስደንገጥ የጨለማ አበጋዞች አጋንንት መጥተው ከበቡት በመቀማትና በግድ ነፍሱን ከሥጋው ለዩ» ይላል ደራሲው ይህ ሁሉ ሲሆን ቁጭ ብሎ የሚመለከት ይመስላል
ይህ በእንዲህ እንዳለ መላእክት ይህን ጉዳይ ለማርያም ነገሯት ድንግል ማርያም ግን በስሟ ያጠጣውን ቀዝቃዛ ጽዋ ውሃ በጎኑ ተሸክሞ ስላየችቅው ደስ አላት
«ወርእየት እግዝእትነ ቅድስት ድንግል ወላዲተ አምላክ በገቦሁ ማየ ምልአ ሕፍን ዘአስተየ ለነዳይ ምጽዋተ ቤእንተ ስማ ወተፈስሐት ሶቤሃ»
 ትርጉም «እመቤታችን ስለ ስሟ ለድሀ ምጽዋት አድርጎ ያጠጣውን ጥርኝ ውሃ በጎኑ አይታ ያን ጊዜ ደስ አላት» ማለት ነው።
ነፍሳት በምድር ላይ እንደፈለጋቸው ሲቀላውጡ ኖረው አንድ ቀን የሰጡትን ውሃ ወደ ሰማይ ሲሄዱ ተሸክመው እንደሚገኙ የሚያስተምር የክርስትና ትምህርት የለም። የዚህ ነፍሰ ገዳይ ነፍስ ግን  በጎኗ ጥርኝ ውሃ ተሸክማ ስትሄድ ማርያም አየችና ደስ አላት ይለናል። ነፍሳት ወደ ማርያም ሳይደርሱ ወደ እግዚአብሔር እንደማይቀርቡ 111 ላይ ይናገራል ድንግል ማርያም የበላዔ ሰብእን ነፍስ ውሃ ተሸክማ ያየቻት በዚህ ምክንያት ነው።
በመጨረሻ መላእክት የባላዔ ሰብእን ነፍስ ወደ እግዚአብሔር ፊት አደረሷትና ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ጣሏት የሚል ትእዛዝ ከዙፋኑ ወጣ ይላል። በዚህ ጊዜ ድንግል ማርያም ማርልኝ እያለች ለመነች በስሜ ቀዝቃዛ ጽዋ ውሃ ያጠጣውን ልትምርልኝ ቃል ገብተህልኝ አልነበረምን? አለች። እግዚአብሔርም ፍርዱን ገልብጦ ሚካኤልን ጥርኝ ውሃንና 78ቱን ነፍሳት መዝንልኝ አለው። ሚካኤልም ውሃንና 78ቱን ነፍሳት ሲመዝን ውሃ ቀለለ ነፍሳት ግን ክብደት አሳዩ ይላል። ድንግል ማርያም ግን ፈጠን ብላ በውሃው ላይ ጥላዋን ጣለችበት በዚህ ጊዜ ውሃው ክብደት አሳየ ነፍሳት ግን ቀለሉ፤ በላዔ ሰብም በማርያም ጥላ ምክንያት ለትንሽ ከሲኦል አመለጠ በማለት አስቂኝ ልቦለድ ያስነብበናል። ይህም ታሪክ እውነት ነው ተብሎ  አመታዊ በአል ሆኖ እንዲከበር፣ ዜማ ተዘጋጅቶለት መልክ ተድርሶለት እንዲነገር ተብሎ በየካቲት 16 ቀን ታስቦ ይውላል። የየካቲት አስራ ስድስት የኪዳነ ምሕረት በዓል ይህን ቃል ኪዳን የተመለከተ ነው።
ታሪኩን በጌታና በሐዋርያቱ ቃል ስንገመግመው
የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነው። ሮሜ 623 ኃጢአት እና መልካም ሥራ በሚካኤል እንደሚመዘኑ መጽሐፍ ቅዱስ አይናገርም። ኃጢአት በመልካም ሥራ መልካም ሥራ ከኃጢአት ጋር የሚመዘኑ እና ሰውም በዚህ መሠረት የሚድን ከሆነ ክፉ እየሠሩ መልካም መሥራት ይችላል ወደሚል የስሕተት ትምሕርት ይወስዳል።
ታምረ ማርያም የሚያስነብበን ግን ሥራንና ኃጢአትን ከመመዘን ያለፈ ነው በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠሩ ክቡራን ነፍሳትን እና ትንሽ ውሃን ነው በአንድ ሚዛን ተመዘኑ ያለው። በእውነቱ  78 ነፍሳትን ከትንሽ ውሃ ጋር ማወዳደሩ እግዚአብሔር ለሰው የሰጠውን ክብር የሚያንጸባርቅ አይደለም። ሰው በእግዚአብሔር ፊት ክቡር ነው ይህም እውነት ኢየሱስ ክርስቶስን እስከሞት አድርሶታል። ሰው ከትንሽ ውሃ ጋር ሊመዘን አይችልም።
 የእግዚአብሔር መንግሥት የፍርድ አሠራር እንደ ደብረ ብርሃን ሸንጎ የተዛባ አይደለም። ነፍሳትም በስማይ እንደ ሽንኩርት እየተመዘኑ የሚገመገሙበት ሁኔታም የለም። ፍርድ የሚጠናቀቀው በዚሁ በምድር መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ያስረዳል "በእርሱ በሚያምን አይፈረድበትም በእርሱ የማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታልዮሐ 317 ፍርድ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እና ባለማመን የሚፈጸም ነው። ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው ተብሎ ተጽፋል። በሚካኤል መዛኝነት ሌላ ፍርድ የሚሰጥ መሆኑን ከጌታም ሆነ ከሐዋርያት አልተማርንም። ይህ ባዕድ ወንጌል ነው።
እመቤታችን ድንግል ማርያም ሚዛኑ የሚፈርደውን በመጠበቅ ፋንታ ሚዛን እንዲያጋድል ለማድረግ ጥላዋን ጣለች እያሉ ያላደርገችውን አደረገች በማለት እናታችንን ተሳድበዋል። እጅግ ያስዝናል። እመቤታችን የእግዚአብሔርን ፍርድ የምትጠብቅ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያላት በእግዚአብሔር መለኮታዊ ክብር የከበረች ናት። ሚዛን እንዲያጋድል በጥላዋ የፈጸመችው የፍርድ ማዛባት ሥራ የለም። ድንግል ማርያም ቅድስት ናት ቅድስናዋም እግዚአብሔርን በመታዘዝ ቃሉን በመፈጸም እንደቃሉ በመኖር ነው። እግዚአብሔርን አላውቅም ያለ ነፍሰ ገዳይ ለማዳን ስትል ከእግዚአብሔር ይልቅ ለራሷ ስም ክብር በመስጠት ያደረገችው የፍርድ ማዛባት የለም። በናታችን በድንግል ማርያም ላይ የሚነገረው ውሸት ሁሉ ይቁም! ጠላት እርሷን እያከበርሁ ነው እያለ ክብሯን ይንዳል
በእውነቱ ፍርድ በሰማይም እንዲህ የሚዛባ ከሆነ ምን ዋስትና ይኖራል? በዚህ ዓለም ያሉ ዘመድ እና ገንዘብ ያላቸው ሁሉ ፍርድ ሲያዛቡ እናያለን። ብዙዎቻችን እውነተኛ ፍርድ አጥተን እያለቀስን እንኖራለን። የዚህ ዓለም መንግሥት ፍርድ ቤቶች በአድልዎ በጉቦ የተበላሹ ናቸው። በሰማይም ግን እንዲህ ዓይነት የፍርድ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን ሁሉ የሥራውን እንደሚያገኝ እንጂ በመሽሎክሎክ ወደ መንግሥተ ሰማያት ፈጽሞ መግባት እንደማይቻል ነው።
«ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ ርኩሱም ወደ ፊት ይርከስ ፤ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ ቅዱሱም ወደ ፊት ይቀደስ ለእያንዳዱ እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከኔ ጋር አለ» ራእ 2211 እንዲል።
 በላኤ ሰብእ በሥራው ሳይሆን በተዛባ ሚዛን ነው ወደ መንግሥተ ሰማያት እንደገባ ተደርጎ የሚቆጠረው። ሚዛን አዛብተው ወደ መንግሥተ ሰማያት ለማስገባት ከማስተማር ይልቅ በክርስቶስ ቤዛነት የእግዚአብሔር ምህረት ተድርጎለት ዳነ ቢል ወንጌል ስለሆነ እውነት ነው እንቀበለዋለን። የኃጢአት ዋጋው የክርስቶ ሞት ሆኖለታልና እኛም በዚህ ነው የዳነው። ሚዛን ተዛብቶ ዳነ የሚለው ትምህርት ግን ክህደት ስለሆነ አንቀበለውም አናስተምረውምም።
የእግዚአብሔር መንግሥት እንዲህ የሚጭበረበር መንግሥት ነውን? አይደለም! ድንግል ማርያምም ይህን ታሪክ አታውቀውም። እንግዲህ ድንግል ንጽሕት፣ ቅድስት፣ ክብርት፣ ብጽዕት እናታችንን እናክብራት፣ ያላደረገችውን አደርገች ያልሰራችውን ሠራች እየተባለ በስሟ ውሸት ሲነገር ዝም አንበል። በረከቷ ይደርብን አሜን!
ዲያቆን ሉሌ ነኝ


51 comments:

 1. ay belaeseb, sent zemen techawetuben... sewoch tsefewet hezbun yasmelekutal. nefsachew aymarem ye metsehafu tsahafiwoch.

  ReplyDelete
 2. ምናልባት የተሻለ እውነት ከያዝክ ተናገራ፤ ተአምረ ማርያሙን በሙሉ ተቃውመህ ካልሆነ መመስገን፣ ጾምና ጸሎት በስሟ መደረግ እንዳለበት፣ ለወዳጆቿ ብላ ከሀድያንን ልትበቀል እንደምትችል ከመጻሕፍትም ሆነ ከተአምሯ ያለውን አትካድ።

  ReplyDelete
 3. ወይ ጉድ! ዲያቆን ሉሌ እግዚአብሔር ይስጥህ። በጣም የሚያሳዝን አንገት የሚያስደፋ ጉድ ነው። እነዚያ ደብተሮች እና ነገስታት እግዚአብሔር ይይላቸው። ይህችን ቤተክርስቲያናችንን አበላሹብን። የደጋጎቹን ሊቃውንት አትናቴዎች፤ ቄርሎስ፣ ያሬድ የመሳሰሉ ትምህርቶችን አጥፈው የራሳቸውን ባዕድ አምልኮ አስገቡ። ቤተ ክርስቲያናችንን ከዚህ ጉድ ያጽዳልን አሜን

  ReplyDelete
 4. Mamameya!!! Men woooow. Is this the book I kiss every sunday?

  F

  ReplyDelete
 5. በነገራችን ላይ በቤተ ክርስቲያናችን የተሐድሶ እንቅስቃሴ መንስኤ የሆነው እንደዚህ አይነቱ ጉድ ነው። ይህ የተበላሸ እና ዓይን ያወጣ ክህደት እንዲስተካከል/እንዲጠፋ የሚፈልጉ ናቸው ተሐድሶ ተብለው የሚጠሩት። በቅርቡ ዳንኤል ክብረት እንዳለው። የተሐድሶን መንስኤ አጣርቶ ለመንስኤው መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ አጅሬ ማህበረ ቅዱሳን ሰዎች ላይ ስም እየለጠፈ ለማሳደድ ይሞክራል። ክንቱ ልፋት! አይናችን እያየ፤ አእምሮአችን እያለ መቼስ ይህ ትክክል ነው፤ የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት ነው ብለን አንቀበለውም።

  ReplyDelete
 6. DN. Lulae bilehal abat yelhim endae!??? lemin yabathin sim atfim?!!

  ReplyDelete
 7. ዲያቆን ሉሌ ቃለ ሕይወት ያሰማልን። ተሸፍኖ የኖረውን የዘመናት ጨለማ በጊዜው እንዲገለጥ ያደረገ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን። ይህንን የእርግማን መጽሐፍ ለማረምና ለማስተካከል የሚችለው አካል ማለትም ቅዱስ ሲኖዶስ ከእንቅልፉ ነቅቶ፤ ዓይኑን ገልጦ ይህንን የቤተ ክርስቲያናችን ማፈሪያ የሆነውና ዘርዐ ያዕቆብን ተጠቅሞ ሰይጣን በወንጌል ላይ የደረተው ተአምረ ማርያምን እንዲያርምና ሕዝባችንም ከእርግማኑ እንዲያላቀቅልን የዘወትር ጸሎታችን ነው።

  አባ ሰላማዎች በርቱ እግዚአብሔር ከእናንተር ጋር ይሁን።

  ዲያቆን የባሰው ነኝ።

  ReplyDelete
 8. O My God!

  This is amazing and incredible story. I would like to say this is the time God want to reveal our shadow and open our eyes to what we are doing on our faith.

  Thank you Deacon Lule!

  Grimachew

  ReplyDelete
 9. በረከቷ ይደርብን አሜን!
  ዲያቆን ሉሌ yetgnaw bereketua new yemiadrbn? i haven't ever heard such words from you.for sure,u have a share of those wrong teaching?

  ReplyDelete
 10. ማነህ ሙሉጌታ አባክህን ይህን ውሸት አና ቀደዳህን አቁመው:: አባክህ:: ውሽት እኮ እንክዋን በክርስትና ቀርቶ ለአሕዛብ እንክዋን አስጠያፍና ቆሻሻ ኃጢያት ነው::
  እባክህ አትዋሽ:: እያቃረኝ ላንብብህ ብየ ብጀምር ውሸትህ አቀረሸኝ:: አንተ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ታምረ ማርያምን በውሸት ጻፈ ብለህ ልትኮንን አየሞከርክ አንተ ራስህ አሁን የተተረጎመን መጽሐፍ ለርካሽ አላማህ ለማዋል ያደረከው ጥረት አስፎገረህ:: በነገራችን ላይ

  "ታምረ ማርያምን ቁጭ ብለን በማስተዋል ብንመረምረው መጽሐፍ ቅዱስን ለመቃወም የክርስትናን ትምህርት ለመበረዝ በጠላት ሆን ተብሎ የተቀመመ ይመስላል። አጼ ዘርዓ ያዕቆብ እስራኤላዊ ነኝ ስለሚል ምን አልባት አይሁዶች መሲሐዊ እምነታችንን ለማጠፋት የፈጸሙት ሴራ ይሆን? ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል። ዘራ ያዕቆብ አይሁዳዊ ነኝ እያለ ይመካ ነበር፤ ከዚያም አልፎ የይሁዳ ነገድ ነኝ ይል ነበር። አባ እስጢፋኖስ ግን ኢትዮጵያዊ ነህ አትዋሽ ከአይሁዳዊነት ይልቅ ክርስቲያን መሆን ይበልጣልና በዚህ አትመካ በማለት እንደተከራከረው ገድለ እስጢፋኖስ ይናገራል [በሕግ አምላክ በፕሮፌሰር ጌታቸው]"

  ገድለ እስጢፋኖስ ያልከው ላይ አንዲህ የሚል የለም:: በዛ ላይ እንዲህ አንደሚልስ ታውቃለህ::

  "በዛ ላይ አንደ ሌሎቹ ሁሉ የቅዱስ ኤፍሬምን ውዳሴ ማርያም እና የቅዱስ ያሬድን አንቀጸ ብርሃን ይደግሙ ነበረ:: እነዚህ ሁለት ድርሰቶች እመቤታችንን ይምያደንቁና የሚያመሰግኑ:በየአንቀጹ 'ሰአሊነ ቅድስት' (ቅድስት ሆይ: ኃጢያታችንን ይቅር እንዲለን ከልጅሽ ከወዳጅሽ ዘንድ አማልጅን)የሚል ንባብ ያለባቸው ናቸው::ጳጳሱም ለቅድስት ድንግል ማርያም ብትሰግዱ ስህተት አይሆንባቹም ብለዋቸው አብረው መስገዳቸውን መስክረዋል::" ገጽ 30
  አንተ አሁን ገድለ እስጢፋኖስ ተቀብለህ ታምረ ማርያምን ለማቃለል ትሞክራለህ? ነው ወይስ አጼ ዘርዓ ያዕቆብን ይሰድብልኛል ብለህ ነው? ገድለ እስጢፋኖስም እኮ አስከሬናቸውን ፈወሰ ይላል:: አመንከው?????
  እና እኛ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆነው እስከችግሩ ነው የምንቀበለው:: አንተ ካልተመቸህ ከቤተክርስቲያናችን ውልቅ በልልን:: ጌታ እውነተኛ ይወዳልና ነገሮችን ከእውነት ጀምር:: ዲያቆን የሚለውን ማስመስያህንም ተወው::

  Ben

  ReplyDelete
  Replies
  1. tthhaannkk yyoouu!!!!!!!!!!!!!!!!

   Delete
 11. አባ ሰላማዎች ምን ዓይነት ጉድ ነው የምታስነብቡን? በውነቱ ይህን ታሪክ እንደዚህ አይቸው አላውቅም። እንዴት ሳልውቀው አባቴን እና እናቴን ስሳደብ ኖሬያለሁ? አምላኬ ይቅር ይበለኝ። ብዙ መመራመር ጀመርሁ ነገሩን ሳስተውለው ውሸት ስማርና ሳተስተምር ኖሬያለሁ አሁን ግን በማጣራት ላይ እገኛለሁ። ነገ ደግሞ ምን ታስነብቡን ይሆን? አይዟችሁ በርቱ ዓይናችንን ከፈታችሁት። መልካም ሥራ ጀምራችኋል፣ ሊቃውንት ጉባኤ መንካት ያልፈለገውን እናንተ እየሠራችሁ ነው።
  እኔ ከናንተ ጋር ነኝ
  ታምረ ማርያም በማንበብ ጊዜ ያጠፋሁ ቄስ ነኝ ይቅር ይበለኝ

  ReplyDelete
 12. ዲያቆን የባሰውAugust 6, 2011 at 12:10 AM

  ዲያቆን ሉሌ እስትንፋሰ መለኮት በሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተመሥርቶ ያቀረበልን በእመቤታችን ላይ የተለጠፈ የሰይጣን ትምህርት (ተአምረ ማርያም) ነው። ነገር ግን ስለበረከት ጉዳይ አልነበረም። ምንአልባት አስፈላጊ ከሆነ ወደፊት ስለበረከት መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን እውነት ይገልጽልን ይሆናል። ለማንኛውም ከላይ ያለውን ሀሳብ ያቀርብህ ወንድም ስለተአምረ ማርያም የምትከራከርበት እውነት ካለህ ለምን ማስረጃህን አታቀርብም? ያለዚያ ግን ስለተአምረ ማርያም አንብበህ ስለበረከት የምታወራ ከሆንክ ለእውነት ልብህን አልከፈትክምና ከእግዚአብሔር ቃል ጋር አትሞግት። ለእውነት መሽነፍ ሕይወት ነው። እኔም እድሜዬን ሁሉ ስሳለምና ሳሳልም ኖሬ ነበር። አሁን ግን መሳለም ቀርቶ ሲነበብም ከቤተ ክርስቲያን ወጥቼ እሔዳለሁ። ምክንያቱም በጌታዬ እናት ስም አልራገምም፤ አልሳደምም።
  ለአንተም እንዲሁ ይገልጽልህ ዘንድ እጸልያለሁ።

  ዲያቆን የባሰው ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከቤተ ክርስቲያን ከወጣህ ዲያ_ _ የሚለውን ስም ተውልን።
   ለነገሩም ዲያብሎስም በ ዲያ ነበር የጀመረው ወጥቶ ቀረ እንጅ ይበጅ ያድርግላችሁ

   Delete
 13. mejemeriya belayeseb malete heyewetu feriha egziabhre yalew engeda tekebaye neber seytan kento asestot new keza aykmron tekotatrot 78 nefse endibla yaderegew ena bemebetachen sem weha siyateta wede aymrow temelse enji kedro jemero chekagn sew alneberem egziabhre degmo yedro manentun yawekal selzi new yesedekew mejermeriy tariken mawek yasefelgal betekrestiyan Zem bela yemetesefew tarik yelatem enantem asteyayet yemetsetu sewoch ye thadison manente menkate alebachw zem belchw becha yemilwachehun atekebelu wedehwal temelsachew tarik anbebu

  ReplyDelete
 14. Alkerebachihum letewahido lijoch mazenachihu yih tinbit benante lay mefesemu ayidenkenim yetemeretutin.......aydel yalew? bemechereshaw seat seytan silehone yemiyanagrachihu Eyesus Eyesus tilalachihu gena degimo kemehalachihu Eyasus negi yemil yimetal yihim ayidenikenim.yihim tetifolinal.

  ReplyDelete
 15. ye Dingil mariam ligAugust 6, 2011 at 7:13 PM

  tehadiso yemitifewn bicha new ende post yemitadergut

  ReplyDelete
 16. የዮሐንስ ወንጌል
  13፥35 "እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ። " This hase been just revealed. GLORY TO GOD AMEN. http://www.blogger.com/comment.g?blogID=432263961826186937&postID=7328278930737411245

  ReplyDelete
 17. It is an interesting analysis!

  ReplyDelete
 18. Wondimie Ben,

  Ebakih kenezih sewoch minim yemitagegnew tikim yelem ena gizehin atabakin. betselot bicha asibachew. Yekihidet merzachewun eyerechu new enji, bewustachew minim yeminet ersho yelem. Yebelayeseb tamir bemetsihaf kidus wust kalut tamiratoch bians enji yibezal ende? There were people eating grasses... kegeta bekegn yetesekelew sew ecko, edimie likun kemagna neber, gin bezach siat nisiha gebto bemengistih asibegn silale dinoal. Belaesebim ecko, endezaw betirign wuha new yedanew. Legeta fekadu kehone min yigedewal. yemitastemirut haymanotawi meseret yelewum. Demo, hasabachinin silematikebelu enazinalen!!!!!!!! Geta yikir yibelachihu!

  ReplyDelete
 19. ወይ ጉድ ... እኛ የወንጌልን እውነት ተረድተን እውነትን መቀበል አቅቶን ስንሙዋገት መናፍቅ ይፈነጭብናል.. እውነት ያልሆነውን ነገር መቀበል የለብንም!!እባካችሁ ጸልዩ ሁላችሁም ... በጣም የሚገርም ነው ... አባ ሰላማ በርቱ ..እውነት ከሆነ ምንም ተባሉ ምንም አውጡት..እግዚያብሄር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን።

  ReplyDelete
 20. engidih min enilalen............

  ReplyDelete
 21. if we want to be saved from eternal death so,we have to be live only according with bible but this is does not mean that we are not accepting other books written by different christian follower but only when consistence with bible.therefore it is better finding the truth rather than debating.lets GOD make clear his word for us.

  ReplyDelete
 22. Lesew Mesenakeya kemehon yedingay wefcho bangetu tasro wede bahir bital yiqelewal new yemilew qidus metsihafachin!!!...endih ayin yaweta wushet ena kihidetin gin man astemarachu??? Yewahun Me'emen besenkala yebeg lemd belebese nufakeiAchu Atasenakilu... bezih tsihun tesenaklo lemitefa nefs....lenante letsehafiwochu weyolachu...Emebirihan Yebelaieseb Emebiet Ayinachihun Tigiletsilachu.

  Kehulachu yanesku tazabiyachu

  ReplyDelete
 23. Part I

  I am not comfortable with that story as well. However, we should not use that unpalatable story to deny the intercession of St. Mary. I was happy when the writer says "bereketiwa yideribin." That is exactly what we need. Otherwise, the bela'e sebe story is a mockery on the Gospel. Having said that,

  (1) I want to remind you that what we do on earth, while being in faith, will be judged by God. Mat 25: 33-46. Unless our faith is accompanied by good deeds, we cannot get salvation.

  "33 በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።
  34 ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።
  35 ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥
  36 ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።
  37 ጻድቃንም መልሰው ይሉታል። ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?
  38 እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ?
  39 ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?
  40 ንጉሡም መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።
  41 በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል። እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።
  42 ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥
  43 ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።
  44 እነርሱ ደግሞ ይመልሱና። ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል።
  45 ያን ጊዜ። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል።
  46 እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ። "

  ReplyDelete
 24. Part II

  (2) It is not fair to protest throwing feast in the name of Jesus Christ (MedhaneAlem), St. Mary and the rest of the saints. While I agree that the feast (feeding the poor) is not salvation in and of itself, it is a way to express our faith and serve the Lord. On the Final Day, God will judge us based on the deeds we have done while being in faith. Again, mere faith is not enough for salvation. It is true that faith is the most essential element for salvation, but we will be judged based on the deeds we do with the recourses, opportunities, and time that we have been given while being in faith. If a person repents and accepts Christ Jesus now as his savior and dies a minute later, he will be saved. This is because the guy has done what he could given the opportunity he has been given. On the other hand, if a person repents and accepts Christ as his savior, but regresses back to his sins over the coming years and dies with his sins, he cannot get salvation despite his faith. This is because this person has spoiled the salvation he was given with later time sins that he never repented for and cleansed himself from. At the Orthodox Church, there is widespread belief that the saints can help us when we lack good deeds, not faith, in the face of God. The lack of faith does not have any solution after we have departed this world. What is sad is that our church has excessively exploited, in fact abused, the very mercy of God by preaching mostly the help of the saints, not the very Gospel He has give us. By the way, I firmly believe in the help of the saints within the framework of the Gospel, but I reject all useless stories that they tell all day long that are against the bible.

  (3) Don't forget that St. Michael the Archangel is one of the closet and most chosen servant of God. So, your protest of the his role in God's judgment is deplorable. In the Revelation, it is written that the earth will shine because of the grace of the Lord's angel at the Final Day when Christ comes for judgment. That angel will probably be St. Michael. Be cautious not to offend the most chosen angel, who is so kind like his master, Christ Jesus.

  ReplyDelete
 25. Part III

  (4) I fully agree with the author that the EOTC faithful have been made to abstain from partaking in the Holy Communion (Kidus Kurban) because of the false hope learned from such similar stories. Zikirishen Yazekere or Zekeirhin Yazekeren will be saved upto 7 or more generations. Ezhe Gedam yetekiberen emirewalhu... Frankly, most people have been misled and lost their lives because of such stories. The church is fully and squarely responsible for that.

  (5) I think such criticisms are good for spiritual revival at EOTC, and to clean up some of the dusts and mud thrown at the church over the years. However, we should oppose any criticisms that come from our spiritual opponents and their sympathizers. Our opponents don't wish us well and don't care for our well being. What they want is to destroy us, steal some sheep, and propagate their own views, beliefs and cultures. So, we warn our spiritual opponents (mostly the pentes) and their sympathizers to stop provoking our church and the faithful. Otherwise, the ensuing fire will consume them.

  ReplyDelete
 26. <<400 000 ካህናት እንዳላት የሚነገርላት ቤተ ክርስቲያናችን ታምረ ማርያም አንብቦ ከማሳለም ያላፈ አገልግሎት የሚሰጥ አይደለም።>>

  ወንድሜ በጣም ተሳስተሀል፡፡ በጣም ታሳዝናለህ፡፡

  ReplyDelete
 27. Nathan - welcome, I knew you will not try to defend this story, Thank you. But why do you try to shift the attention to other topics?

  ReplyDelete
 28. Tazabi- "tesenaklo lemitefa nefs" Denkem mesenakel. You are already lost & in dark eko brother..

  "Emebirihan Yebelaieseb Emebiet Ayinachihun Tigiletsilachu."


  "Kehulachu yanesku tazabiyachu" agul tihetena

  ReplyDelete
 29. I did not divert attention. All my comments are in response to the issues that the writer has raised.

  ReplyDelete
 30. min meseleh eni emtisleyew ant behizeb mehal komeh teamer mariyamen tanbaleh.

  ReplyDelete
 31. ante tsere orthodoxawi , hizbun gira lemagabat yetirtare sibket yemtiletif. Ene lengerih aydel seba siminet nefs madan yikelal weys awlaken bemahisen meshekem. Ante akeberkat alkebrkat kibrwa aykensim.
  Emebrehan yelbonahin birhan tiglet

  ReplyDelete
 32. as the name of the father and of the son the holly spirit amen!!betam yemitgerm sew neh okay?400,000 yemihonu kahnat endalat yeminegerlat hagerachin;p neger gin ke-te-amre mariam balefe ayawkum sitil koy aykebdihim enezih kahnat abatoch endalastemaruh kotkutow endalasadeguh ante satfeter yetemark awekung bay?degmom teamre mariam kihdet new eske ahun dires haimanot tebkew yakoyulin abatoch tesastewal yemitil:i am sorry betam azinalehu! diakon aydelehim.

  ReplyDelete
 33. very very shame on you ! aba selama blogers now i am truly believing that you are the biggest tehadiso in our church , please show your self talk with likawint of tewahido and then you will be out of our church like Ariyos ! May God Bless tewahido and give you time to think for tehadiso like you !!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ትክክል፥እግዚአብሔር ይገስጻቸው።

   Delete
 34. @ Haile do you know who Ariyos is? I don't think. you may know him by name if you know Ariyos you are spouse to denounce such kind of false teachings Like church fathers.They excommunicate Ariyos by his false teaching I personally believe that Aba selama is posting the real and very true teaching of Orthodox tewahido Church which is authentic and Biblical .We have to excommunicate such kind of false teachings from our beloved church please stand up for the truth !!!!!!!!

  ReplyDelete
 35. enante sewoch tena yelachum ende ande gize emebetachin fered tebakinat telaleh ande geze degemo berketuwa yedereben telaleh men gude new beka protesetant yesew hayemanot kalesedebe ayesebekem ende.lemen ateteyekem metsehafu selemen endemeyawera enkuwan eko alegebahem zeme belaeh lante yememch yemeselehen yezehe qentebeh ezeh laye aweteteh sewochin lemasekade memeokereh tegebi ayedelem ewenetegna yehayemanote ena yekeresetena fekere kaleh begzeabeher yemayamenuten chelet belew yekaduten hedeh lemen metsehaf kedus atasetemerem menew yezehech betekeresetyan telat baza ewnet eyetefa enedemihed endenanete ayenet yesedeb afe enedemekefet kedusanene hulu endemisadeb asekedemen enawekalen enenete eko yalachun neger endanaremachu yetetsafe menem heg ena memereya yelachume meseret yelachume maneshachu ayetawekem zeme belachu beayer laye new yetgegnachut ebakachu buzu lekawent yamenubeten bezuwach yetesewuleten bezuwoch bezih tetekemeqwe bezu tsega yagegnbeten yesewn emenet menekefe newer new kesene megebare yeweta negere new ebakachu tewu atenekun ena yebelae seb tarek kedemo yalewn ayetehewal betame dege sew endenebere yegeletsal ante demo endeteredahew getse nebabe ayedelem tareku yegezeabeher cherenet enea sewochen lemadan yalewn felagot yemeyasaye new.emebetachen eko berasuwa amelakenat alelenem hulum negere ersuwa yemetadergewe hulu kelejuwa kefetare yetegegne new berasuwa ayedelem ersuwa deg honech setel yefeteratema men yahil deg endehone yamyasereda new. ene gen ande yemamesegenew esekahun aleweledechiwem alemaletachun new.wedefet gen yeh kehedetachu adego getan aleweledechim ersum amelak ayedelem maletachu yemyeker yemeselegnal sente kedusan betegebare yaregagetuten emenet enanet telant yemetachu tekem felagewoch egeziabeheren beqemer lemagegnt memokerachu yegeremegnal. ebakachu tewu temechen belachu kehedetachun atezeru ebakachu tewu??????????????????

  ReplyDelete
  Replies
  1. ትክክል፥እግዚአብሔር ይገስጻቸው።

   Delete
 36. aye aba selama denkem deyakon maregu nafekacehu kebetwa setwetu lebonawen yestacehu lanebew gemrew geze mabaken honobegne tewkut weshet yetsedek menged hone ende enante ga?

  ReplyDelete
  Replies
  1. ትክክል፥እግዚአብሔር ይገስጻቸው።

   Delete
 37. yale weladetamelake Alem haydeneme tamer mareyame betam tekekele nwe ytesase hedeleme ok

  ReplyDelete
 38. ከሃዲው ሉሌ አንተ አስመሳይ እመቤታችን ድንግል ማሪያምን ትላንት ምን ስትላት ነበር ዛሬ ከቢጤዎች ጋር የምትሉትን ስታጡ በዚህ መንገድ ብናስተምር ተቀባይነት እናገኛለን ብላችሁ የመረጣችሁት አካሄድ የሞኝ አስተሳሰብ ስለሆነ ብታቆሙ ጥሩ ነው ለመሆኑ ዓፀ ዘሪያዕቆብን የምትሰድብብበት አንደበት አለህ እንደእናንተ ለገንዘብ ብለው ሀይማኖታቸውንና ሀገራቸውን የሸጡ አይምሰልህ ለዘለዓለም ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ታላላቅ ሥራ ሰርተው አልፈዋል ስማቸውም እንዳንተ በካሐዲነት ሳይሆን በክብር ሲጠራ ይኖራልና ማን እንደሆንክ ተነቅቶብሀል አርፈህ ቁጭ በል !!!! ተ.ኦ

  ReplyDelete
 39. ከእናተ ይልቅ የ፮ወር ህጳን በእዉቀት ይበልጣል፥ መማር ማጥፉት አይደለም፥እግዚአብሄር ይገስጳችሁ።።አንድ ቀን ግን<< >>

  ReplyDelete
 40. ለመሆኑ የየትኛዉ ሀይማኖት ተከታይ ነህ እዉነት እዉነት ተናጋሪ ነኝ ትላለህ ታዲያ ለምን ነዉ እራስህን የምትደብቀዉ እዉነት ተናጋሪ ከሆንክ ዲያቆን ሉሌ ነኝ ሳይሆን የሰይጣን ሎሌ ነኝ በል....

  ReplyDelete
  Replies
  1. PLEASE DICARD TAMREMARIAM FROM OUR CHURCH

   Delete
 41. አሜን በረከቷን ያሳደረብን !!! ደስ ሲል!!! በረከቷ አልክ? እውነት ነው ምልጃዋ እና ልመናዋ አለና ይህን መናገርህ በራሱ እራስህን ልትፈትሽ እንደሚገባ ከማን በልጠህ በክብሯ ዘመቻ??? ደግሞ ዲያቆን?! ለነገሩ ይህ ስልት እጅግ ለዚህ ዘመን ትውልድ በአግባቡ ስለገባን በስሟ ጥቂት ቀዝቃዛ ውሃ ስጥን ተማጸናት:: እርስዋም ሩህሩህ ናትና ይቅርታን ትስጥህ ታሰጥህ አሜን !!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጸሓፊው ሰውየ

   እርሳቸው ግን ይህን ተ አምረ ማርያም ተቃወሙት የሚል ታሪክ አልሰማሁም። አንተን ምን አነሳሳህ ስጋዊ ሰው መንፈሳዊውን ሊመረምር አንዴት ይችላል።

   ከምትወናብድ በህይወት እባክህ ጸንተህ ኑር ።

   Delete
 42. ዲያቆን ሉሌ በጣም ይገርማል ተዓምረ ማርያም ከወንጌል ጋር ይቃረናል ብለሀል ግን ከመናፍቃን አልተለየህብኝም ምክንያቱም እነርሱ ክብሯን ስለሚንቁ ምንም ልታደርግ አትችልም ይላሉ እኛ ታማልዳለች እንላለን አሁንም አንተ ክብሯን በደንብ ለማጤን ሞክር አስበው በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ ሰለሞን ከነገሰ በኋላ እናቱ ቤርሳቤህ ስትገባ ተነስቶ ሳማት በቀኙም አስቀመጣት ይላል ከዛም እናቴ የፈለግሽውን ጠይቂኝ አላት ጌታ ለእናቱ ምን ያህል ክብር ይሰጣት ይሆን ይሄን የጠቀስኩበት ምክንያት ለመቀበል እንደተቸገርክ ስለመሰለኝ ነው ካንተ አልፎ ሰውንም እያጠራጠርክ ነው በሰማይ ያለውን ስርዓት በቅዱሳን አበው ድርሰት በጥቂቱ ተፅፎልናል ጌታ ለኒቆዲሞስ የምድሩን ካለመንክ የሰማዩን ብነግርህ እንዴት ታምናለህ እንዳለው ጌታችን ካመናችው የሚሳናችው ነገር የለም ነው ያለው ጌታችን በላይ ሰብም በእድሜው ሙሉ ቢያጠፍም በጥርኝ ውሃ ተማረ ቢባል በወንጌልም እኮ ከጌታ በስተቀኝ የተሰቀለው በእድሜው ሙሉ ኃጥያትን ሲሰራ የኖረ ነበር መስቀል ላይ ነው የዳነው ባለቀ ሰዓት ታምሯን የሰማ ሥጋ ወደሙን እንደተቀበለ ይቆጠርለታል የሚለው በቤተ ክርስቲያል ትምህርት መሰረት ሰው ሊቆርብ ወስኖ እያለ እንዳይቆርብ የሚያደርጉት ነገሮች ቢገጥሙት ለምሳሌ እንደ እንቅፋት ትንኞች ወደ አፉ ለመግባት ቢሞክሩ...ያኔ መቀበል ባይችል ታምሯን ይስማ እንደ ተቀበለ ይቆጠርለታል ነው ለሁሉም በሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን አንተም ለሀይማኖትህ ለፈጣሪህ ቀንተህ እንጂ በክፍት አይመስለኝም እና ተግተን እንፀልይ ዋናው እሱ ነው በፀሎት እግዚአብሔርን ማነጋገር ይቻላልና

  ReplyDelete