Tuesday, August 2, 2011

ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል ማቴ 6፥33 - - - Read PDF

 • ማህበረ ቅዱሳን የተባለው ማህበር በሥጋም ሆነ በእምነት ወንድሞቻችን የሆኑ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ያቋቋሙት ማህበር ነው።
  • የመጀመሪያው አላማቸው ቅንነትና ተስፋ የሞላበት ሀሳብ ነበር። 
  • በኋላ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን መጣል ጀመሩ።
  • የሕዝባችንን ሞኝነት በመጠቀም የራሳቸውን አላማ ለመፈጸም አሰቡ፣ የሕዝቡን ልማድ እምነት እና ስሜት በማጥናት ያንን ማሟሟቅ፣ በዚህ ሙቀት ራስን ማደራጀት የሚል የሥጋ ጥበብ መጠቀም ጀመሩ።
  • የሕዝብ ልማድ፣ እምነት፣ ስሜትና አስተሳሰብ ጠላት ናቸው ተብለው የሚታሰቡትንም እንዋጋለን ብለው ራሳቸውን ወዶ ዘማች ወታደር አደረጉ።
  • ከእግዚአብሔር  መንግሥትና ጽድቅ ይልቅ ለሕዝብ ስሜት ትልቅ ዋጋ በመስጠት ማገልገል ጀመሩ።
  የእግዚአብሔር መንግሥት ሰማይና ምድርን የምትገዛ ሁሉንም የምትቆጣጠር ዘላለማዊና የማትፈርስ መንግሥት ናት። መንግሥተ እግዚአብሔር ከአድልዎና ከክፋት ነጻ የሆነች ለሚቀበሏት ሁሉ ዋስትናን የምትሰጥ የሰላምና የደስታ መንግሥት ናት። እግዚአብሔርን መታዘዝ ለፈቃዱ መገዛት ሐሳቡ ምን እንደሆነ መርምሮ በእውነተኛ ሕሊና ከጉልበቱ ሥር ወድቆ ማምለክ የእግዚአብሔርን  መንግሥት ለመቀበላችን ምልክት ነው። ዳዊት መንግሥትህ የዘለዓለም መንግሥት ናት ግዛትህም ለልጅ ልጅ ነውአለ መዝ 14413-14 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥትህ ትምጣብላችሁ ጸልዩ ብሎ አስተማረን። መጽሐፍ ቅዱስ ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ደጋግሞ የሚያስተምረው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ነው። እግዚአብሔር ዓለምን እና በውስጡ ያለውን ሁሉ የራሱ ነውና መግዛት ይፈልጋል። በአዳም በኩል ፍጥረትን መግዛት ስላሰበ አዳምን በፍጥረት ላይ ንጉሥ አድርጎ ሾሞት ነበር። ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ግዟትምእንዲል ዘፍ 128 አዳም ግን በሌላ ኃይል ተገልብጦ የተሰጠውን የመግዛት ሥላጣን አስነጥቆ ኖረ። በኋላ ግን ለሚመጣው መሲሐዊ መንግሥት መጀመሪያ የሚሆን በደብረ ሲና መገለጥ፣ በይሁዳ ነገድ የሚመራ የካህናት መንግሥት ተቋቋመ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ፣ እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ ይላል ዘፍ 196 በተለይም የዳዊት መንግሥት ለሚመጣው የመሲሑ መንግሥት ዓይነተኛ ምሳሌ ሆኖ በኢየሩሳሌም ተገልጦ ነበር።
  የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት የእግዚአብሔር መንግሥት ተገለጠች አዋጁም የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንሥሐ ግቡ የሚል ነው። ጌታችን አስቀድማችሁ መንግሥቱን ጽድቁንም ፈልጉ ያለው ይህችን ሰማያዊ መንግሥት ነው። ለዚህች መንግሥት የማይገዛ ሁሉ ከጥፋት አይድንም ሰላምም የለውም።
  በነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ለዘላለም የማይፈርስ መንግሥት ያስነሣል ለሌላ ሕዝብም የማይሰጥ መንግሥት ይሆናል እነዚያንም መንግሥታት ሁሉ ትፈጫችዋለች ታጠፋቸውማለች ለዘላለምም ትቆማለች እንዳለ ዳን 242
  ጽድቁን ፈልጉ ማለት እውነቱን ከእግዚአብሔር የሆነውን እና እርሱ ሊያደርግ የሚፈልገውን አድርጉ ማለት ነው። እግዚአብሔር እንዲሆን የሚፈልገውን በቃሉ ተናግሯል። ብዙ ጊዜ እውነቱን እያወቅን የራሳችንን ጉዳይ ስለምናስቀድም እናጠፋለን። እግዚአብሔር ግን ከእኛ ጉዳይ በላይ ነው። አላማችን ልናደርግ ያሰብነው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ያገለለ ከሆነ አይከናወንልንም። ሥራችን ሁሉ እውነትን ያላገለለ ቢሆን ይከናወንልናል፣ ነህምያ የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን አለ ነህ 220 ነህምያ ሊሠራው የተነሣው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነው ስለዚህም ተሣካለት እግዚአብሔርን ያገለለ ሥራ ቢጀምር ኖሮ ባልተሳካለት ነበር።
  ማህበረ ቅዱሳን የተባለው ማህበር በሥጋም ሆነ በእምነት ወንድሞቻችን የሆኑ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ያቋቋሙት ማህበር ነው። የመጀመሪያው አላማቸው ቅንነትና ተስፋ የሞላበት ሀሳብ ነበር። በምስካየ ኅዙናን መሰባሰብ እና ሌላ አላማ የነበራቸው ሰዎችን ማግኘት ከነርሱም ጋር ጊዜ ማሳለፍ ሲያዘወትሩ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን መጣል ጀመሩ። የሕዝባችንን ሞኝነት በመጠቀም የራሳቸውን አላማ ለመፈጸም አሰቡ፣ የሕዝቡን ልማድ እምነት እና ስሜት በማጥናት ያንን ማሟሟቅ፣ በዚህ ሙቀት ራስን ማደራጀት የሚል የሥጋ ጥበብ መጠቀም ጀመሩ። የሕዝብ ልማድ፣ እምነት፣ ስሜትና አስተሳሰብ ጠላት ናቸው ተብለው የሚታሰቡትንም እንዋጋለን ብለው ራሳቸውን ወዶ ዘማች ወታደር አደረጉ። ከእግዚአብሔር  መንግሥትና ጽድቅ ይልቅ ለሕዝብ ስሜት ትልቅ ዋጋ በመስጠት ማገልገል ጀመሩ።
  የሕዝብ ስሜት ለማርካትና አእምሮውን ለመማረክ ከተጠቀሙበት ዋናው መንገድ ኦርቶዶክስን ለማጥፋት የመጣ ኃይል አለ፤ ይህን እኛ እንዋጋለን፣ እናጋልጣለን አሉና ላሰቡት አላማ እንቅፋት ይሆንብናል ብለው ያሰቡትን ሁሉ ለማሳደድ እድል ያገኙ መሰላቸው። በዚህ ስልታቸው ብዙ ቲፎዞ ማግኘታቸውን ሲያውቁ በከንቱ ውዳሴ ሰከሩና ወደ ትልቅ ስሕተት መግባት ጀመሩ። ሌላው ሁሉ ቀርቶ የኢየሱስን ስም መቃወማቸው ነው። ይህ ነው አስቸጋሪው ነገር! ኢየሱስን የተቃወመ ሁሉ የትም እንደማይደርስ በታሪክ የተረጋገጠ ነው።
  ጌታ ኢየሱስያለ ሁሉ መናፍቅ ነው። ስለ ኢየሱስ ብቻ የሚሰብክ ጴንጤ ነው፣ ጌታ ኢየሱስ አይባልም፣ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ የሚያዘወትር ከሆነ ተሃድሶ ነው በማለት ኢየሱስን ያከበሩ መስለው እራሱን ኢየሱስን ተቃወሙ። ስለ ኢየሱስ ብቻ መዝሙር ሲዘመር ኦርቶዶክሳዊ አይደለም፣ ያሬዳዊ አይደለም፣ የተዘመረው በሌላ መሣሪያ ነው፣ ባህላችን አይደለም፣ ዘፈን ይመስላል፣ በማለት በተለያየ ምክንያት በዚያም በዚህም ተቃወሙ። ከእግዚአብሔር መንግሥትና  ጽድቅ ይልቅ ለባህልና ለወግ ቅድሚያ በመስጠት  ከጌታ ክብር ይልቅ ለአላማቸው በመንጠንቀቅ የጌታን ስም የጠሩትን ሁሉ አሳደዱ። ሐሰት ማህበሩን የማይነካ ከሆነ እውነት ይሆናል፣ እውነት ማህበሩን የሚነካ ከሆነ ሐሰት ይሆናል፣ ነገሩ እየተድበሰበሰ ይቀራል። እግዚአብሔር በምሕረቱ የሸፈነው የሰዎች ግላዊ ገመና ባማህበሩ እየተሰለለ በሐመር መጽሔት እየወጣ ለገብያ ይቀርባል፣ የሰው ገመና ለሽያጭ ይውላል። ኢየሱስን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ መዝሙሮች በሱቆቻቸው እንዳይሸጡ በምትኩ ተክልዬ አቡየ፣ እያሉ የሚሸበሸቡ መዝሙሮች ገነው እንዲሸጡ ተደረገ፣ ይህ ሁሉ የሕዝብን ቀልብ ለመግዛት እና በሕዝብ ሞኝነት ላይ ተዳራጅቶ አላማን ለማሳካት ታስቦ ነው።
  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል ከኔ ጋር የማያከማችም ይበትናል ማቴ 1230  እንዳለ ጌታን ገለል አድርጎ እርሱ በደሙ የዋጃቸውን ነፍሳት ከፍ ከፍ በማድረግ የርሱን ምሥጋና በማንቋሸሽ የሌሎችን ምስጋና በማሞገስ አመርቂ ሥራ መሥራት አይቻልም። በየትኛውም ባህል ዜማና ግጥም ጌታ ሊከብር ይችላል። ዋናው የእግዚአብሔር ክብር እንጂ የዜማው ዓይነት አይደለም ዜማ ለእያንዳዱ ሰው የሚሰጠው ስሜት የተለያየ ነው። በዜማ አመካኝቶ የእግዚአብሔርን ክብር መቃወም የሰይጣን ምቀኝነት እንጂ እግዚአብሔርን የሚወድ ሰው ስሜት አይደለም።
  ያም ሆነ ይህ ማህበሩ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን እስካላስቀደመ ድረስ ጤነኛ ሆኖ አይቀጥልም ወይም እንደ ፓርቲ የፖለቲካ ራእይ ካለው በእግዚአብሔር ስም መነገድ የለበትም በእግዚአብሔር ስም እየሠሩ የእግዚአብሔርን እውነት ገለል ማድረግ መፍረስ ብቻ አይደለም መቅሰፍትንም ያመጣል። ማህበሩ ራእዩንም በጌታ ስም ቢያደርገው እንቀበላለን አብረንም እንሠራለን። እኛን የገረመን ግን በእግዚአብሔር ስም እየተጠቀሙ የእግዚአብሔርን እውነት መጣላቸው ነው። ቤተ ክርስቲያናችን ብዙ ማስተካከል ያለባት ነገሮች እንዳሉ እያወቁ፣ ብዙ ስሕተቶች እና እግዚአብሔር የማይወዳቸው ባዕድ አምልኮዎች፣ ነውሮችና ርኩሰቶች፣ እንደ ቃሉ ያልሆኑ የሐሰት ትምርህርቶች  በቤተ ክርስቲያናችን መሙላታቸውን እያወቁ ለማስወገድ እና እግዚአብሔርን ለማክበር በመሥራት ፈንታ፣ እንዲያውም እነዚህን ከላይ የዘረዘርናቸውን ነውሮች ለአላማቸው መጠቀሚያ አድርገው እያስተማሩ የእግዚአብሔርን ቃል መናቃቸው፣ ወንድሞችን ለማሳደድና ለመክሰስ እንደ ጥሩ አጋጣሚ መያዛቸው ለመከፋፈልና እርስ በርስ ለመካሰስ አብቅቷቸዋል። እንደዚህ አይነቱ የማህበሩ አካሄድ ቤተክርስቲያናችንን እጅግ እንደሚጎዳ ጤነኛ ኣእምሮ ሁሉ ያስተውላል።
  አሁንም የማህበሩ አባላት ወንድሞቻችንና  ቤተ ክርስቲያናችን እንድትነቃ እንድትስተካከልና እንድትጠነክር የሚፈልጉ ወገኖች ሁሉ የአንዲት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ናቸው።  ልዩነት ቢኖር እንኳ በሚያስማማ ነገር አብሮ መጓዝ ይቻላል። በቤተ ክርስቲያን፥ በፖለቲካውም ሆነ በኢኮኖሚው ለውጥ ማምጣት ይቻላል ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስን በማግለል አይደለም  ይህ የማይሞከር ነገር ነው። ቅድሚያ ለኢየሱስ ክብር እንሥራ  ሌላው ሁሉ ይጨመርልናል እንላለን። በመናቅ እና በሃሳብ የተለየውን ሁሉ በማሳደድ ቆመን እንሄዳለን ብላችሁ አስባችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል። የማህበሩ አባላት የሆናችሁ ሁሉ ቤተ ክርስቲያንን እንጠቅማለን ብላችሁ ቤተ ክርስቲያናችሁን እናዳታቆስሉና ጌታችሁን እንዳታዛዝኑ የማህበራችሁን አካሄጥ እንድትመረምሩ አሳስባለሁ።
  ተስፋ ነኝ      

15 comments:

 1. You guys , you dont have any other topic other than mahebere kidusan. shame!!!!

  ReplyDelete
 2. woooooooooooooooooow, Amazing rasen enday aderegegne. I have been one of them. Medehanialem yeker yebelegn, Ye Eyesus sim sinesa des ayelegnem neber. Amelak hoy yeker belegne. Gen kidaselay Eyesus yebal yele eyaleku neger gen ewenet semu sinesa aledesetem neber. Pente becha yemeselegn neber. Tesfa ewenetem tesfa - Kale Hiywot yasemah.

  ReplyDelete
 3. “ጌታ ኢየሱስ” ያለ ሁሉ መናፍቅ ነው። ስለ ኢየሱስ ብቻ የሚሰብክ ጴንጤ ነው፣ ጌታ ኢየሱስ አይባልም፣ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ የሚያዘወትር ከሆነ ተሃድሶ ነው በማለት ኢየሱስን ያከበሩ መስለው እራሱን ኢየሱስን ተቃወሙ።

  Where is the evidence? This is an absolute lie....
  You simply accused them out of nothing.

  ReplyDelete
 4. ዘአምላኪየ

  ኦ ንፉቅ እንተለመስቴማ ፀወኑ፤
  ፀሐየ ቃለ-ተዋህዶ ዘይሔድስ መኑ፤
  ገቢሮ ሓዳሰ ፈጣሪ እንተ ፈጠራ አኮኑ፡፡

  ReplyDelete
 5. the mahber will collapse soon.

  ReplyDelete
 6. Shame on you. "Mk" lekek.

  ReplyDelete
 7. እረ ደጀ ሰላም ሊዘህ ፍናፍንት ማህበር ጊዜአችሁን አታጥፉ በዕርግማን የተጨማለቀ የከሃዲዬን ማህበር ነው ስራውን እረስቶታል የቤተ ክረስቲያን ልጅነቱን አጥቷል አሁን ቀማኛ የመናፍቃን ጎራ ሆኗል ስለዚህ ምን ይደንቃችሁል ገና ገና ብዙ ትሰማላችሁ ታያላችሁ የዛ ሁሉ ሰው ደም እንደፈሰሰ አይቀርም የነዛ ሁሉ ልጃ ገረዶች ድንግልና መጫወቻ ሆኖ አይቀርም እረ ስንቱንቱን ተጫወቱበት ለነገሩ ማህበሩ ሳይሆን ጥፋተኛ ደንባራው ወጣት ነው እምነቱን ለይቶ ያላወቀውና ማሀበር አምላኪው። እነሱ ምን ያርጉ የታምራት ገለታ ቢጤዎች ናቸው። ይቆየን

  ReplyDelete
 8. please please let's focus on our religion. We are making big mistake. why we are so divided and hater. let's pray to be nice. kegna haymanot yelelachew sewoch yishalalu ecko. tilacha bicha new ende mitisebikut. esti sile niseha sile sigana demu ensbek. sile meleyayet, metelalat mesbek enakum

  ReplyDelete
 9. EYESUSE GETA BECHA SAYEHONE YEBHARI AMELAKE NEW...EYESUSE GETA BECHA SAYEHONE YEBHARI AMELAKE NEW...yehe new Ementachen!

  ReplyDelete
 10. wey mekoyet ay mahebertegnoch mecha yehon semechu tekeyero christinochu yemetebalut ahun yememles gezea new M/K BEAK gezeaw yewenegeal new yemeserach yezew yemetuten aglegayoch aterebeshu yegetan mekedes ategeredu shekemachenen enaragef befkeru teneketen kenea enebel wenegeal semu heiowetachu hulu wenegel selehone METERAT ENDALE TERSA ENDE?/

  ReplyDelete
 11. የቋንቋ ችግር ሳይሆን የእምነት ችግር ከሌለባችሁ ምን ያስጨንቃችኋል? በተለያየ ቋንቋ እየሱስ ሲነገር አንድ አይነት አይደለም እኮ የስም አጠራር ችግር ሳይሆን የእምነት ችግር ስላለብን ይመስለኛል በቋንቋ አሁንም አያድንም በእምነት ና በምግባር ግን ከሆነ ያድናል ስለዚህ እመን፤ ስራ ትድናለህ:: ግን ተመሳስለህ እትመን ለስጋ ፍለጎት ብለህ እምነትህን አታጠጋጋ ለአፍህ ስለጣፈጠህ ብቻ የክርስቶስን ስም በከንቱ አታንሳው ማመንህን አይገልፅምና የአምላክ ስሙ ክቡር ነው ይህንን ልብ በል ልቦና ይስጠን ማስተዋሉን ያድለን:: አሜን
  ወስብሀት ለእግዚአብሄር ለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር

  ReplyDelete
 12. ኢትዮጵያ ገና አሁን ክ እንቅልፏ እየነቃች ነው። በ 16ተኛው ክፍለ ዘመን የተጀመረው የ ፕሮቴስታንት እንቅስቃሴ ብጥብጡ ባለቀ በ አራት መቶ ዘመኑ ገና አሁን በ 21ኛው ዘመን ኢትዮጵያኖች ከ እንቅልፋቸው ነቅተው ክርክሩን መጀመራቸው በጣም ያሳዝናል።
  ሃይማኖቱን የሚወድ ሰው የሰው ሃይማኖት እይሳደብም። ይህን ጭቅጭቅ ቤተ መቅደሱ ዉስጥ ቆመው በ እስላምና በ ጴንጤ ብሎም በ ጥሮቴስታንት ላይ ይደርስ የነበረውን አስጠያፊ የስድብ ዉርጂብኝ በዳላስ ከተማ አካባቢ በሚገኘው በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በነ ቄስ ሲደልልና በነ ቄስ መስፍን በነ ዲያቆን አለማየሁ አፍ ሲሰበክ ሰምተናል። ዛሬ ደግሞ አልፎ ተርፎ አዲስ አበባ ያለው የማህበረ ቅዱሳን ሰላዮች በግለሰቡና በህዝቡ መካከል ተሰግስገው የየግለሰቡን ስም ማጥፋት ተያይዘው ጳጳሱም ተው ሲሏቸው አንሰማም እያሉ ጳጳሱን መዘርጠጥ በግልጽ ያሳዩ ነው።
  ይህንንም በዛሬው እትሙ http://www.dejeselam.org/ ያሳያል አባካችሁ አንብቡላቸው።

  ReplyDelete
 13. በመጀመሪያ በያላችሁበት የክርስቶስ ሰላም ይብዛላችሁ.ያለንበት ዘመን ሳስበዉ በጣም ያስጨንቃል.ሰባኪውም ካህኑም አገልጋዩም ምእመኑም ባጠቃላይ ሁላችንም ክርስትና ማለት ምን ማለት እንደሆነ የጠፋብን ይመስለኛል.ክርስትና ማለት ጣትን ወደሌላ መጠቆም አይደለም ክርስትና እኮ ሰው በማይሆን ወድቆ ቢገኝ ማበርታት መጎዳት እንኩዋን ካለብን ስለፍቅር መጎዳት እስከመሞትም እንኩዋን ደርሰን የጠፋውን መመለስ በእምነት የዛለዉን በእምነት ማቆም ይተበቅብናል.በሌሎች የምንፈርድ እኛ ማነን? ክርስትናችንስ መለኪያው መፍረድና መኮነን ነው?ከየትስ ተምረነው ይሆን?በምንም አይነት መልኩ ይሁን ፈራጆችና የጥላቻ ሰዎች ከሆንን ከማስተማራችን በፊት መማር ያስፈልጋል የእምነት የፍቅር ሰው መሆን አለበት.የእምነት ሰው እንዴት ጥላቻ ይሰብካል??? በእውነት የሚያስጨንቅ ጊዘ ነው.

  ReplyDelete
 14. መናፍቃን፣ተሐድሶ፣አባ ሰላማዎች፣ የመሳሰላችሁት ሆይ!!!!!!!! ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ሁሉ ስራችሁን አወቋል እናንተ እንደ ይሁዳ ገንዘብን የምትወዱ ጌታችሁንም የምትሸጡ፣ አባታችሁን የሰለባችሁ፡፡ ነጩን ጥቁር፣ ጥቁሩን ነጭ፣ ዳቦውን ድንጋይ ድናጋዩን ዳቦ፣ ሊጡን ብስል ብስሉን ሊጥ ፣ ረዥሙን አጭር አጭሩን ረዥም፣ አፈሩን ዱቄት ዱቄቱን አፈር፣ ያለውን ሞተ የሞተው አለ የምትሉ በአጠቃላይ ክደትን እንደሸማ የተኮናነባችሁ፣ እውነትን እንደመርገም ጨርቅ ጦስ-ጡንቡሳቴን ብላችሁ አሽቀንጥራችሁ የጣላችሁ የሰይጣን ልጆች ናችሁ!!! ኢሳ ፩፥፲፱ እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ፥ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እምቢ ብትሉ ግን ብታምፁም፥ ሰይፍ ይበላችኋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና። ስለዚህ ቢያንስ አታምጹ ኦርቶዶክስ ምእመናኑና እግዚአብሔር እንደሆነ ማኔ፣ቴቄል ፋሪስ ብላችኋል፡፡

  ReplyDelete
 15. መናፍቃን፣ተሐድሶ፣አባ ሰላማዎች፣ የመሳሰላችሁት ሆይ!!!!!!!! ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ሁሉ ስራችሁን አወቋል እናንተ እንደ ይሁዳ ገንዘብን የምትወዱ ጌታችሁንም የምትሸጡ፣ አባታችሁን የሰለባችሁ፡፡ ነጩን ጥቁር፣ ጥቁሩን ነጭ፣ ዳቦውን ድንጋይ ድናጋዩን ዳቦ፣ ሊጡን ብስል ብስሉን ሊጥ ፣ ረዥሙን አጭር አጭሩን ረዥም፣ አፈሩን ዱቄት ዱቄቱን አፈር፣ ያለውን ሞተ የሞተው አለ የምትሉ በአጠቃላይ ክደትን እንደሸማ የተኮናነባችሁ፣ እውነትን እንደመርገም ጨርቅ ጦስ-ጡንቡሳቴን ብላችሁ አሽቀንጥራችሁ የጣላችሁ የሰይጣን ልጆች ናችሁ!!! ኢሳ ፩፥፲፱ እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ፥ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እምቢ ብትሉ ግን ብታምፁም፥ ሰይፍ ይበላችኋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና። ስለዚህ ቢያንስ አታምጹ ኦርቶዶክስ ምእመናኑና እግዚአብሔር እንደሆነ ማኔ፣ቴቄል ፋሪስ ብላችኋል፡፡

  ReplyDelete