Saturday, August 13, 2011

የጥናት መጽሔት ልሳን አይደለም! - - - Read PDF

ሐምሌ 1 ቀን 2003 ዓ.ም. በዚሁ ጋዜጣ በመምህር በቃሉ ከ5 ኪሎ የጻፉት ጽሑፍ ‹‹ጥናቱ የማኀበረ ቅዱሳን ወይስ የቤተክርስቲያኒቱ›› በሚል ርዕስ የቀረበውን ጽሑፍ አንብቤአለሁ፡፡ የራሴንም አስተያየት ለመጻፍ ተገድጃለሁ፡፡ የወንድሜ ጽሑፍ ቅንነት የጐደለው መሆኑ የሚታወቀው በጥቅምት 5 ቀን 2003 ዓ.ም. ለወጣ ጽሑፍ ከ10 ወራት በኋላ ሐምሌ 1ቀን 2003 ዓ.ም መልስ ለመስጠት መሞከራቸው በቂ ማሳያ ነው፡፡ ጸሐፊው ራሳቸውን መምህር የሚጠበቅ ስላልሆነ ከይቅርታ ጋር አቶ ብዬ ልጠራዎት ተገድጃለሁ፡፡

በመጀመሪያ አቶ በቃሉ ያነሱት ሐሳብ ከተነሱበት ጭብጥ ያፈነገጠ እዚያም እዚህም የሚረግጥ፣ አንባቢን ግራ ለማጋባት ታስቦ መሆኑን መረዳት አያዳግትም፡፡

ጸሐፊው እንዳሉት፣ በቤተክርስቲያኒቱ ሥር ለመንቀሳቀስ፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የተሰጠው አንድ ብቸኛ ማኅበር፣ ጽፎ ያሳተመውና ያሠራጨው የኅትመት ውጤት፣ የቤተክርስቲያኒቱ ልሣን ተብሎ ለመጠራት ሕጋዊ መሠረት ምን እንደሆነ አልነገሩንም፡፡ ለነገሩ የጥናት መጽሔት ልሳን አይደለም /ልሣን የሚለው ቃል እዚህ ላይ መተንተኑ አስፈላጊ መስሎ ስላልታየኝ ሌላ ጊዜ የምመለስበት ይሆናል/

ማኀበረቅዱሳን ባለፉት 19 ዓመታት፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድና እውቅና ተሰጥቶት፣ በቤተክርስቲያኗ የስብከት ወንጌልና የልማት ዘርፍ ሰፊ ሥራ እየሠራ የሚገኝ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ለማኅበሩ እንዲመራበት የሰጠው መመሪያ፣ ይህንን የጥናትና ምርምር ሥራ እንዲያከናውን ይፈቅድለታል፡፡ በመሆኑም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ማኅበሩ የጥናትና ምርምር ማዕከል በማቋቋም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ማዕከል ያደረጉ፣ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር በማካኼድና በቤተክርስቲያን ዙሪያ ጥናት ማድረግ ለሚሹ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እንዲሁም ለተመራማሪዎች፣ አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ለይ ይገኛል፣ ጥናትና ምርምር ማዕከሉ የሥነ ቤተክርስቲያት የጥናት መድረክ እና ዓመታዊ የጥናት ጉባኤ ያካሄዳል፡፡ ዓመታዊ የጥናት መጽሔት /Journal/ ያሳትማል፡፡

አቶ በቃሉ የጀርመን ዩኒቨርሲቲዎች ግእዝን በሁለተኛ ዲግሪና በዶክትሬት ሲሰጡ ቅዱስ ሲኖዶስ እኔ ባለመፍቀዴ አያገባችሁም አይልም እንዳውም ቤተክርስቲያኗ በማቴሪያልና በሞራል መደገፍና ማበረታታት ያለባት ይመስለኛል፡፡ አልሰሙ እንደሆነ እንጂ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ጥናትና ምርምር ተቋም በአሜሪካ አገር ተቋቁሟል፡፡

እዚህ ላይ አቶ በቃሉን መጠየቅ የምፈልገው፣ አንድ አጥኚ የቤተክርስቲያኗ መገለጫዋ የሆነውን ነገር፣ አንድ ጥናት ማሟላት ያለበትን መስፈርት በማሟላት ለንባብ ቢያበቃ፣ መረጃው ተጨባጭና ሙሉ እስከሆነ ድረስ ርእሱ ቤተክርስቲያኗን ስለሚገልጽ የግድ ካልፈቀድን በስተቀር በዚህ  ርእስ ምንም ዓይነት ጥናት ማድረግ አይቻልም የሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር ማድረግ የሚቻል አይደለም፡፡ እርስዎ ግን የቤተክርስቲያኒቷ አካል እንደሆነ እያወቁ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ጥናት መጽሔት የሚለውን ርዕስ በመምዘዝ፣ ጥናቱ የቤተክርስቲያኒቱ እጅ የለበትም በማለት ማኅበሩን ከቤተክርስቲያን ሊነጥሉት ይፈልጋሉ፡፡ ባይሳካልዎትም፡፡

በሌላው አንቀጽ ላይ ደግሞ፣ ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተክርስቲያኒቱ ‹‹ጥናት›› ሊባል የሚችል ነገር ሊያቀርብ ይችላል ወይ? ሲሉ ይሞግታሉ እኔ ግን  በድፍረት አዎ ይችላል እላለሁ፡፡ ማንኛው ለእምነቱና ለቤተክርስቲያኑ ቅን አሳቢ ዜጋ የሚታየውን ጎደሎ ወይንም መልካም ነገር፣ በጥናት አስደግፎ በተሻለ ነገር በማቅረብ የቤተክርስቲያኗን ገጽታ በመገንባት በኩል ሰፊ ሥራ ለመሥራት፣ ጥናትና ምርምር ጥቅሙ የጎላ መሆኑን ማኅበሩ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ራሱ ምስክር ነው፡፡ ለአብነት ይህ በጥናት መጽሔቱ ላይ የቀረበውን በአባ ገሪማ ገዳም ስለሚገኘው፣ በዘመነ አክሱም ስለተጻፈው ወንጌል የተጻፈውን ያንብቡት፡፡ ይህን ጥናት BBC ሬድዮ ለዓለም ከመንገሩ በፊት የማኅበሩ ልጆች፣ የመመረቂያ ጽሑፋቸው እንዳደረጉት ያውቁ እንደነበር ተስፋ አለኝ፡፡ ይህን እንድል ያስቻለኝ የጥናትና ምርም ፋይዳ ሰፊና ሌሎችን ለተጨማሪ ጥናት ስለሚያነሳሳ ነው፡፡ BBC የዜና ሽፋን የሰጠው ከዚሁ ፋይዳ የተነሣ መሆኑ አይካድም፡፡

ሰውየው ለተነሱት ሀሳቦች መቋጫ ሳያደርጉ፣ ማኅበሩ ራሱን ጻድቅ አድርጎ እንደሚያሳይ የገለጹበት አካኼድ የሚያስረዳኝ ነገር፣ በትክክል ማኅበሩን የተመለከቱት በጥቁር መነጽር ነው ለማለት ያስችላል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና ሌሎች ‹‹የካቶሊክና ፕሮቴስታንት የእምነት ተቋማት መሠረታዊ የክርስትና ትምህርት ልዩነት የላቸውም እያሉን ይገኛሉ፡፡ ይህን ትምህርት ከየት ነው የተማሩት? እነ አርዮስ፣ መቅዶንዮስ፣ አውጣኬና የመሳሰሉት መናፍቃን የተወገዙት ከሊቃውንተ ቤተ ከርስቲያን የተለየ አስተምሮ በመያዛቸው ወይንስ ሌላ?

በሌላው አንቀጽ ላይ በኢቲቪና በሌሎች ጋዜጠኞች ላይ ያነሱት ሐሳብ፣ በራሱ የመጻፍና የመናገር ነጻነትን የሚያፍን ከመሆኑም በላይ፣ እኔ ለምን አልተጠየኩም የሚል ቅናት ያደረብዎት ያስመስልብዎታል፡፡ አንድ ጋዜጠኛ ለሚያዘጋጀው የጽሑፍም ሆነ የምስል ዘገባ፣ ይሆነኛል የሚለውን መረጃ የሚወስደው በነገሩ ላይ ዕውቀት አላቸው ከሚላቸው ወገኖች መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ቤተክርስቲያናችንም ብዙ ሊቃውንት እንዳሏት አይክዱም፡፡ ከእኛ አልፎ ለዓለም የሚተርፍ ዕውቀት አላቸው፡፡ እኔ እንደሚገባኝ አንድ ጋዜጠኛ ይዞት የመጣው ሐሳብና ለዚያ ማጎልበቻ ሐሳብ የተጠቀመባቸው ሰዎች ሐሳብ ስህተት ከሆነ ፣ ማስተካከያ መስጠት የሊቅ ደንብ ነው፡፡ እኔ ብቻ ልጠየቅ ሌሎች ከእኔ ውጭ መናገር አይችሉም ወይም አያውቁም ብሎ ማሰብ ግብዝነት ነው፡፡ በአጠቃላይ አቶ በቃሉ፣ የጥናታዊ ጽሑፍ መሠረታዊ ሐሳብ ምን እንደሆነና የጥናታዊ ጽሑፍ ፋይዳ የገባቸው አልመስለኝም፡፡ መፍትሔው ደግሞ በሰከነ መንፈስ ጽንሰ ሐሳቡን መረዳትና ባለሙያ መጠየቅ መሆኑን እየገለጽኩ፣ ቅን ልቡናና አስተዋይ አዕምሮ ፈጣሪ እንዲያድልዎት በመጸለይ ነው፡፡ ቸር ያሰማን፡፡

ትዝብት ቀኖና
ከአራት ኪሎ

(ምንጭ፡- ነጋድራስ ጋዜጣ አርብ ሐምሌ 8 ቀን 2003 ዓ.ም. ገጽ 11)

2 comments:

 1. Aba Selama azegajoch,

  When I read that article (I only had my dark glasses of MK) I had agreed with the article but the reply I just read (thank you for posting it, shows how commited you are for dialoge) I think the writter had a good point.

  The writter also should understand why most people including myself see MK just with dark glass. Its because of so many dark and unchristian, unOrthodox and un Ethiopian act that I personally witnessed by MK. That is an open secret. So, to the writter (Tizbit Kenona), beneka ejiwot put on your "white" glasses and write about this organizations dark secrets so we all can drop our dark glasses.

  To the original wirtter/ Aba selama,

  WHile I understand the whole msg you trying to advance, I think its also important to see things logically, facts as opposed to out of hatered to the status quo of the church. That will help the readers (including myself) to see things as matter of fact. As Paul said, hulum befikir yihun.

  Just to mention an article that I raised my eye brow, rediculing some of "awalid" books of the Orthodox church doesnt advance the cause of eliminating parts that are contrary to the Bible, original orthodox teachings.

  Ex, why is it so difficult for me as a christian that Saint marry saved belaEseb, why is it hard to belive a murderer can be saved. For me wheather it happened or not is not that important for the God I believe can do more than that. Making fun of and rediculing this and other such incidences of what is written in these and other books is now knowing God in what he can do.

  So, Aba selamawoch, stay focused on what I thought is a novel goal of making some unbiblical and contrary to bible teachings of our church with factual presentation. After all, MK started with a novel goal for now to turn into a liability to the church,

  SElam hunu,

  Tazabi negn

  ReplyDelete
 2. አለ አንተ መናፍቅ ስለሆንክ ጫፍ ይዘህ ትሮጣለህ፡፡ ራዕየ ዮሐንስ 6 ላይ ስለሞቱ ሰዎች ነፍስ ጸሎት እናያለን፡፡ ይህን ምን ልትለው ነው ፡፡ ደግሞስ አማልዶ ምህረት ማሰጠት ነው ከባዱ ወይንስ የሞተ ቅዱስ አጥንት የሞተ የሞተ ሰው ማስነሳት ፡፡ መልስ የለህም እንግዲያው መጽሐፈ ነገስትን ስታነብ (ጥቅሱን አልነግርህም ምክንያቱም መናፍቅ ስለሆንክ) የሞተው የቅዱስ ኤልሳ አጽም የሞተ ስው አስነስቷል፡፡ ስለዚህ መልስህ ምንድነው፡፡ የሞተው አልአዛርና ያ ሃብታም በነፍስ እያሉ በሥጋ ሞተው ሳሉ ያ ኃጢያተኛ ላልሞቱ ዘመዶቹ በነፍስ ሆኖ አማልዷል ፡፡ ኃጥአን ካማለዱ ቅዱሳን እንዴት አያማዱም ትላለህ፡፡ በሥም የምትነግድ ማነፍቅ ገና የማኅበረ ቅዱሳን ነገር እንደ እግር እሳት ያነገበግብሃል ታብዳለህ ምን ታመጣለህ፡፡ እግዚአብሔር የመሰረተውን አንተ ምን ታደርገው ፡፡ እንግዲህ አብደህ በጸበል ስለማታምን አማኑኤል መጥቼ እጠይቅሀለሁ፡፡

  ReplyDelete