Wednesday, August 17, 2011

ፓትርያርኩ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖና ውጪ ለሚንቀሳቀሱ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

በጋዜጣው ሪፖርተር
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ፣ ከኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ቀኖና እና ሥርዓት ውጭ በሆነው ሁኔታ ‹‹እገሌ ተሐድሶ ነው››፤ ‹‹እገሌ መናፍቅ ነው›› የሚል እንቅስቃሴ፣ ከሐምሌ 25 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ ሕገወጥ መሆኑን እና ጥብቅ ቁጥጥርም እንደሚካሄድበት አስታወቁ፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ አረጋግጦ ካልወሰነ በስተቀር ከዚህ ውጭ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚካሄድበትም ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በወቅታዊ የቤተክርስቲያን ሁኔታ ላይ ተመሥርተው ሐምሌ 25 ቀን 2003 ዓ.ም. በቁጥር ል/ጽ/598/755/ዐ3 በኢትዮጵያና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ አህጉረ ስብከት ባስተላለፉት መመሪያ እንደተመለከተው ከቤተክርስቲያኒቱ ቀኖና እና ሥርዓት ውጭ በሆነ ሁኔታ እገሌ ተሐድሶ ነው፤ እገሌ መናፍቅ ነው የሚል ጽሑፍ ሲበተን ይታያል፤ ከዚህም ጋር በካሴት በሲዲ እና በመሳሰሉት መሣሪያዎች ሲሰራጭ ይስተዋላል፡፡
የሃይማኖት ሕጸጽ ሲያጋጥም ስለእውነትነቱ በሕጋዊ ማስረጃ የተደገፈ ጽሑፍ ቀርቦ፣ በሊቃውንት ጉባኤ ተመርምሮና ተጣርቶ ትክክለኛ መሆኑ ሲረጋገጥ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ታይቶ የመጨረሻ ውሳኔ ማግኘት እንዳለበት ቀኖና ቤተክርስቲያን እንደሚያዝ ያመለከቱት ፓትርያርኩ፣ ከጥንት ጀምሮ ሲሠራበት የነበረ አሠራርም ይህ እንደሆነ በአርዮስ፣ በመቅዶኖዮስ እና በንስጥሮስ ላይ የተላለፈው ሲኖዶሳዊ እና ቀኖናዊ ውሳኔ ማስረጃ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
‹‹ይህን መርሕና ቀኖና ቤተክርስቲያን ተከትሎ ውሳኔ ባልተሰጠበት ሁኔታ በግል ስሜትና ቀኖናው በማይፈቅደው ሁኔታ የግለሰቦችን ስም ማጥፋት በስም አጥፊነት በሕግ ከማስጠየቅ ያለፈ ሌላ ፋይዳ አይኖረውም›› ብለዋል፡፡
ሕግን፣ ሥርዓትንና የሥልጣን ገደብን ጠብቆ የማይፈጸም ድርጊት የምእመናን ህሊና በማሻከር በቤተክርስቲያኒቱ የአስተዳደር ሥርዓትና በአገሪቱ ሰላም ላይ እንቅፋት ለመፍጠር ሆን ተብሎ የሚደረግ ሙከራ መስሎ ስለሚታይ፤ ጐጂነቱ ቀላል አለመሆኑን የገለጹት አቡነ ጳውሎስ፣ የቤተክርስቲያኒቱ ተከታዮች የሆኑ ምእመናንና ምእመናት በተሳሳቱ ግለሰቦች አድራጎት እንዳይማረኩ አሳስበዋል፡፡ ቀደም ባሉት ዘመናት በመምህራንና በንስሐ አባቶች ጥብቅ ክትትልና ጥበቃ ሲደረግ መኖሩን የጠቆሙት ፓትርያርኩ ዛሬም ቢሆን የቤተክርስቲያኒቱን ሃይማኖትና ቀኖናዊ ሥርዓት የሚጥስ፣ አንድነትዋንም የሚያደፈርስ፣ ሰላምን የሚያሳጣ አዝማሚያ የሚታይበት ሁኔታ ሲያጋጥም ቸል የተባለበት ጊዜ አለመኖሩን፣ መኖርም እንደሌለበት ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ቀኖናው በማይፈቅደው አካሄድና በሌለው ሥልጣን ራሱ ወስኖ ከመሮጥ ይልቅ፣ የእምነት ሕጸጽ በትክክል አጋጥሞ ከሆነ በቂ ማስረጃ አለኝ የሚል ካለ፣ አለኝ የሚለውን ማስረጃ ቀኖናው በሚፈቅደው መርሕ መሠረት ለቅዱስ ሲኖዶስ ማቅረብ እንደሚኖርበት ፓትርያርኩ አስታውቀዋል፡፡
በዚህ ሁኔታ ሥርዓትንና ቀኖና ቤተክርስቲያንን በመጠበቅ የሚቀርብ ማስረጃ ካለ እንደጌታችን ትምህርት ተደጋጋሚ ምክር፣ ትምህርትና ተግሣጽ መስጠቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የማይታረም እና የማይመለስ ሆኖ ሲገኝ፣ በሕገ ቤተክርስቲያን መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ከመስጠት ወደኋላ እንደማይል ሁሉም ሊረዳ እንደሚገባ አቡነ ጳውሎስ አስገንዝበዋል፡፡ የሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት እንዲህ ዓይነቱ ችግር ሲያጋጥመው ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለሚመለከተው የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ አካል አቅርቦ፣ ቅዱስ ሲኖዶስም አረጋግጦ ሲወስንና አውግዞ ሲለይ ካልሆነ በስተቀር፣ ከዚህ ውጭ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ የቤተክርስቲያንንና የአገርን ሰላም ለማወክ የሚደረግ አካሄድ መሆኑ ታውቆ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግም አሳስበዋል፡፡
ፓትርያርኩ ያስተላለፉትን መመሪያ ተከትሎ ባለፈው ረቡዕ ሐምሌ 27 ቀን 2003 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ አዳራሽ የአዲስ አባባ ገዳማትና አድባራት አለቆችና ጸሐፊዎች፣ ሰባክያነ ወንጌል በተገኙበት መግለጫ መሰጠቱን፣ ከስብሰባው በኋላም በተለያዩ መንገዶች ስማችን ጠፍቷል በሚል የሰባክያንና መዘምራን ተወካይ የሆኑ ለፓትርያርኩና  ለቅዱስ ሲኖዶስ አቤቱታ ማቅረባቸውን፣ ‹‹ተሐድሶ በሚል የአየር ላይ ስም አደጋ ላይ የወደቁትን የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ቅዱስ ሲኖዶስ መፍትሔ  እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን፤›› ማለታቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ምንጭ፡- ሪፖርተር ጋዜጣ እሑድ ነሐሴ 1 ቀን 2003 ዓ.ም.  ገጽ 3
  
ይህን መመሪያ ተከትሎ ፀረወንጌል እንቅስቃሴው እክል እየገጠመው ያለውና እርስበርሱ እየተባላ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን፣ የውስጥ ችግሩን አቅጣጫ “ተሐድሶ” እያለ ወደሚጠራቸው ወገኖች በማዞር፣ ቅዱስ ፓትርያርኩ ያወጡትን መመሪያ በስውርም በግልጽም ተቃውሟል፡፡ በሐመር መጽሔት  ነሐሴ 6/2003 .. ዕትም ላይ፣ “ሐሰት አንናገርም፤ እውነትንም አንደብቅም” በሚል ርእስ ያስነበበው ጽሑፍ ስም ሳይጠቅስ፣ “በቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር ውስጥ ያሉ አንዳንድ አካላት ተሐድሶ የለም በሚለው ሐሳብ ተስማምተው በአንዳንድ መድረኮች በቀጥታና በተዘዋዋሪ ይህንኑ አስተሳሰብ የሚያጸና አስተያየት ሲሰጡ መታየታቸው” ያሳዘነው መሆኑን ገልጿል፡፡ የቤተክርስቲያናችን አስተዳደር በማለት የጠቀሰው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን መሆኑን ለማኅበረ ቅዱሳን “ስም አይጠሩ” ጽሑፎች በአንድምታ እያስተነተነ ግልጥልጥ የሚያደርገውና የሚያብራራው ደጀሰላም ድረገጽ ግልጽ አድርጓል፡፡ ደጀሰላም ድረገጽ የማኅበረ ቅዱሳን ንብረት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሐመርና ደጀሰላም ያወጧቸው ጽሑፎች በተከታታይ ከዚህ ቀጥሎ ቀርበዋል፡፡
ሐሰት አንናገርም፤ እውነትንም አንደብቅም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተነጣጠረው ተሐድሶዘመቻ ውጥን ብዙ ዐሥርት ዓመታት ያለፉት ቢሆንም 1992 .. የካቲት ወር ጀምሮ ግን ማኅበረ ቅዱሳን ተጨባጭ በሆኑ የምስልና የድምፅ ማስረጃዎች ዘመቻውን በማጋለጥ የቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ሲኖዶስ ውግዘት ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ ከዚያ በኋላተሐድሶስልቶቹን በመቀያየር ሃይማኖታችንን ለማጥፋትና በሌላ ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮ ለመተካት የሚያደርገውን ሩጫ ቀጥሏል፡፡ በመሆኑም ማኅበረ ቅዱሳን ካለፈው ነሐሴ 2002 . ጀምሮ ይፋዊ የሆነ ከእነዚህ ሴረኞች ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ እንቅቃሴ ጀምሯል፡፡ የሐመር መጽሔት ልዩ እትምን በማዘጋጀት የተጀመረውን አገልግሎት በሌሎችም በኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች ከካህናቱ ከሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ከሕዝበ ክርስቲያኑ ጋር ፊት ለፊት በተደረጉ ውይይቶች በመታገዝ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል፡፡ በዚህም ተሐድሶ ምንነት፣ መሠረት፣ ግብና ዓላማ፣ ስልት፣ ያለበትን ደረጃ፣ በሌሎች እኅት አብያተ ክርስቲያናት ፈጥሮት የነበረውን ቀውስና መዘዝ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዒላማ ለማድረግ በይፋ በተለያዩ የኅትመት ውጤቶች እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለማብራራት ጥረት ተደርጓል፡፡
ይህንን በማድረግ ሂደት ውስጥ ይህንን ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቁን እንቅስቃሴ ለማጨናገፍ የተሐድሶአራማጅ ቡድኖች የተለያዩ ስያሜዎችንና አካላትን በመጠቀምናየተሐድሶእንደ ሸረሪት ድር ሠርቶት የነበረውን የጥፋት መረብ ሳይበጣጠስና በውስጥም በውጭም የሠራው መሠረት ሳይናድ ለማስቀጠል ባለ በሌለ ኃይሉ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እያንዳንዱ ምእመን በእግዚአብሔር ረድኤት የዕለት ከዕለት ተግባሩን ከማከናወን ጋር የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ በንቃት መከታተልና መቆጣጠር በሚችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው፡፡
 በዚህ ተስፋ እየቆረጠ ያለው ተሐድሶመሠሪ ኃይል ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ተላላኪዎቹ በኩል ሊነዛ የፈለገው ተራ ማታለያተሐድሶ የለምተሐድሶየሚል ነገርን የፈጠረው ማኅበረ ቅዱሳን ነውየሚለውን አባባል ነው፡፡ ይህን አካሔድ ተራ ማታለያ ነው የምንለው ተሐድሶመኖር ሊስተባበልበት የማይችልበት ደረጃ ላይ መሆኑን ራሱተሐድሶአለመረዳቱ ነው፡፡ መሣሪያ አድርጎ የተጠቀመባቸው መነኮሳትና ካህናት በየፕሮቴስታንቱ አዳራሽ ሲጨፍሩ እየታየ፣ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ የቅዱሳንን ገድልና ድርሳን እንደልቦለድ የሚቆጥሩ ጋዜጣና መጻሕፈት እንዳሸን እየተሠራጩ፣ ዕቅድና ስልት አውጥቶ እየሠራ መሆኑን ራሱተሐድሶበሚዲያዎቹ እየገለጸልን፣ ቤተ ክርስቲያን ከዕለት ዕለት እየተፈተነችበት፣ ከጥቅመኞችና የሥነ ምግባር ችግር ካለባቸው በቤተ ክርስቲያንኒቱ አስተዳደር ውስጥ ካሉ አንዳንድ ግለሰቦች ጋር በማበር አያወካት እየታየተሐድሶ የለምየሚለው ልፈፋ የዘገየ ስልትና ተራ ማታለያ ከመሆን አይዘልም፡፡
 ከዚሁ ጋር ተያይዞ የታየው ሌላው አስደንጋጭ ነገር በቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር ውስጥ ያሉ አንዳንድ አካላትተሐድሶ የለምበሚለው ሐሳብ ተስማምተው በአንዳንድ መድረኮች በቀጥታና በተዘዋዋሪ ይህንኑ አስተሳሰብ የሚያጸና አስተያየት ሲሰጡ መታየታቸው ነው፡፡ እነዚህ አካላት ቅዱስ ሲኖዶስ ከዚህ ቀደም የችግሩን መኖር አምኖ፣ አሳማኝ ማስረጃዎች ቀርበውለት ውግዘት ማስተላለፉን ዘንግተውና በተለያዩ ዘመቻዎችተሐድሶቤተ ክርስቲያን ላይ የሚወረውረውን ፍላጻ ከምንም በመቁጠር ተሐድሶሴራ ታይቶ እንዳልታየ፣ ተሰምቶ እንዳልተሰማ ሆኖ በምእመናን እንዲታለፍ በመቀስቀሳቸው ብዙዎችን ከማሳዘናቸውም ባለፈ ከፍተኛ ጥርጣሬ አሳድሯል፡፡ እነዚሁ ወገኖች ሐሰትን ሊነግሩን እውነትንም ሊደብቁን የፈለጉበት ምክንያት በሂደት ግልጽ እየሆነ የሚሔድ ሆኖ ሁሉም አካላት ግን የእነዚህን ወገኖችና የመሰሎቻቸውን አቋም እንዲያጤኑ ማኅበረቅዱሳን መልእክት ለማስተላለፍ ተገዷል፡፡
 “ተሐድሶ የለምእያሉ በተለያየ መንገድ ለሚነዙት ማደናገሪያዎች ማብራሪያና ማስተባበያ እንዲሰጥባቸው የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ያነሡትን ጥያቄ ተገቢ መሆኑን ማኅበራችንም ያምንበታል፡፡ እነዚሁ አካላት በዚሁ አቋማቸው የመጽናት ፍላጎት ካላቸው ግንተሐድሶበአደባባይ በሠራቸው ፀረ ቤተ ክርስቲያን ዐዋጆች፣ ስድቦች፣ በጋዜጣ፣ በመጽሔትና በመጻሕፍት በሚያሠራጫቸው የተደበላለቁ ፕሮቴስታንታዊ አስተምህሮዎች ይስማማሉ ወደሚል መደምደሚያ ሊያደርስ ይችላል፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ በተሐድሶ ላይ የምናደርገውን ዘመቻ የሚያደናቅፍ ለየትኛውም ፀረ ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴ በር የሚከፍት በመሆኑ ለቤተ ክርስቲያን ህልውና፣ አስተምህሮ እና ሥርዐት በመቆም ችግሩን በመቅረፍ ሂደት ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ የድርሻውን ለመወጣት ያለውን መንፈሳዊ ቅናት ምን ጊዜም ይገልጻል፡፡
 ማኅበረ ቅዱሳን ማኅበር ሆኖ በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የተቋቋመበት ዓላማ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል ነው፡፡ የአገልግሎቱ መገለጫ ደግሞ ስብከተ ወንጌልን ማስፋፋት የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማና ቀኖና መጠበቅና ማስጠበቅ እንዲሁም ከአጽራረ ቤተ ክርስቲያን መጠበቅ ካልቻልን የምናገለግላት ቤተ ክርስቲያን ወዴት አለች? በመሆኑም የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች የያዙትንብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝየሚለው የቅዱሳን መሓላ በእኛና በሁሉም አማኝ ክርስቲያን ደም ውስጥ ማደሩ የግድ ነው፡፡ ስለዚህ በዚሁ ረገድ እውነት እንዲደበቅ፣ ሐሰትም እንዲነገር የሚወዱ አጽራረ ቤተ ክርስቲያንን መገሰጽ፣ መምከርና ከአባቶች ጋር በመመካከር አስፈላጊውን ክርስቲያናዊ እርምጃ በየደረጃው መውሰድ የሁሉም የክርስቲያን ወገን ግዴታ ነው፡፡ በመሆኑምተሐድሶበሚል ሥያሜ በአጽራረ ቤተ ክርስቲያን የረጅም ጊዜ ዕቅድና ስልት የቤተ ክርስቲያንን ህልውና ለመፈታተን፣ አስተምህሮዋንና ሥርዐቷን ለመናድ በከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እና ዕቅድ እየተደረገ ያለው ዘመቻ ያለና ተጨባጭ እውነታ እንጂ ማኅበረ ቅዱሳን ከመሬት ተነሥቶ ያወራው አለመሆኑን ማኅበረ ቅዱሳን በአጽንኦት ያሳስባል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፡- ሐመር 19 ዓመት .3 ሐምሌ 2003 .
የማ/ቅዱሳን መልእክት ምን ያስተምረናል?
by Deje Selam on Monday, August 15, 2011 at 5:24am
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 15/2011) ከዚህ በታች የተቀመጠውና /ቅዱሳን በወርሃዊ ልሳኑ በሐመር መጽሔት ላይ ባወጣው መልእክቱ ማህበሩ አጠንክሮ ለያዘውፀረ-ፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶእንቅፋት በሆኑ ነገሮች ላይ በድጋሚ ማብራሪያ እና አቋሙን አሳይቶበታል። በተለይምተሐድሶየለም ለሚሉ አካላት መኖሩን ለማሳየት ሞክሯል በዚህ ጽሑፍ።
 ጽሑፉተስፋ እየቆረጠ ያለው ተሐድሶመሠሪ ኃይል ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ተላላኪዎቹ በኩል ሊነዛ የፈለገው ተራ ማታለያተሐድሶ የለምተሐድሶየሚል ነገርን የፈጠረው ማኅበረ ቅዱሳን ነውየሚለውን አባባልበጽኑ ይኮንናል። እነዚህተላላኪዎችያላቸውን አካላት ማንነትን ግን እንድንገምት ለአንባብያን ትቶልናል። ወይም ከዚህ በፊት የተናገረውን ወደ ኋላ መለስ ብለን እንድንመለከት የቤት ሥራውን ለአንባቢው ሰጥቶታል። በተጨማሪምበቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር ውስጥ ያሉ አንዳንድ አካላትተሐድሶ የለምበሚለው ሐሳብ ተስማምተው በአንዳንድ መድረኮች በቀጥታና በተዘዋዋሪ ይህንኑ አስተሳሰብ የሚያጸና አስተያየት ሲሰጡ መታየታቸውእጅግ አስደንጋጭ መሆኑን ይጠቅሳል። አክሎምእነዚሁ ወገኖች ሐሰትን ሊነግሩን እውነትንም ሊደብቁን የፈለጉበት ምክንያት በሂደት ግልጽ እየሆነ የሚሔድ ሆኖ ሁሉም አካላት ግን የእነዚህን ወገኖችና የመሰሎቻቸውን አቋም እንዲያጤኑ ማኅበረ ቅዱሳን መልእክት ለማስተላለፍ ተገዷልሲል ያብራራል።
 /ቅዱሳን የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ ተቃውሞውን በጥናት ላይ በተመሠረተ መንገድ የጀመረ እና ያስፋፋ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ሌሎች ኦርቶዶክሳውያን ጉዳዩን የራሳቸው በማድረግ ቤተ ክርስቲያናቸውን መጠበቁን ቀጥለዋል። በቅርቡ አዲስ አበባ //ቤቶች በይፋ የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶን እንቅስቃሴ የተቃወሙ ሲሆን በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የሰንበት /ቤቶች አንድነትም እነርሱን ደግፎ አጋርነቱን ገልጿል።
 ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱ ርዕስ/ ራስ እና መሪ የሆኑት ቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ጳውሎስተሐድሶዎችን አትንኩብኝየሚል ይዘት ያለው ጦማር አሰራጭተዋል። በዚህም ታሪካዊ ስሕተትን በመፈጸም በእምነት በኩል ለሚጠረጥሯቸው ሰዎች ማረጋገጫ የሚሆን ትልቅ ዶኩመንት ሰጥተዋቸዋል። በደጀ ሰላም ደረጃ ከተመለከትነው ፓትርያርኩ ቤተ ክርስቲያኒቱ አይታው ወደማታውቀው ዝቅጠት እንድትወርድ ያደረጉ መሆናቸው እርግጥ ቢሆንም በፀረ-ኦርቶዶክስነት ጠቅሰናቸው አናውቅም ነበር። አሁን ግን ፓትርያርኩ ሰልፋቸውን ከተሐድሶዎቹ ጋር በማድረጋቸው ከዚህ ጀምሮ የሚኖረን ተቃውሞ ዓይነቱ እና ይዘቱ ይለያል ማለት ነው። ጥብቅናቸው ለቤተ ክርስቲያን ሳይሆን ለአጽራረ-ተዋሕዶ ነውና። ለማንኛውም ለጊዜው ከዚህ በታች [እኛ ከላይ አድርገነዋል] ያለውን የማ/ቅዱሳን ጽሑፍ እንመልከተው።
ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን     

ሙሉውን የ ፓትርያርኩን መግለጫ ለማንበብ የሚከተለው ላይ ይጫኑ


ስለሚያስቷችሁ ሰዎች ይህንን ጽፌላችኋለሁ 1 ዮሐ.227

17 comments:

 1. We have already seen how paulos is trying to protect tehadiso. For the time being he can do that because of his position in our church, but in the nean future when the truth come out he will be nothing and will go to hell with his tehadiso folowers!!!! Oh I forgot. You sereke will be number one in that line and will go to hell with paulos!!!

  ReplyDelete
 2. ጉድ ጉድ ጉድ ጉድ ጉድ! በቃ ማቅ ሊያብድ ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. የምን ጉድ ጉድ ነው፣
   ያውም ጸበል ለማያድነው፣
   ለማቅ በጥቅም ላበደው፣
   ቤተክርስቲያኑን እንዲያምሰው፣
   እሳቸውም ሲጠቀሙበት ቆይተው፣
   ሙልጭ አድርጎ ሲሰድባቸው ዝም ብለው፣
   በሽማግሌ ሲያባብሉ ቆይተው፣
   ከትልልቅ ሚኒስተሮች አስተዋውቀው፣
   ማንም እንዳይነካው ያለ ገደብ አፉን አስከፍተው፣
   ባሾሉት ምላሱ ጳጳሱን ሁሉ አስጨፍጭፈው፣
   አሁን ሕዝቡን መንፈስ ቅዱስ ሲያባንነው፣
   ውጣልን በቃን አትከፋፍለን ሲለው፣
   በቃ አለቀለት ማቅ አበደ ማለት ምንድ ነው፣
   ማስፈራራቱስ ምን ሊጠቅመው፣
   ሞቶ እሬሳው ብቻ ለተጋደመው።

   Delete
 3. bravo abaselama keep doing your good work

  ReplyDelete
 4. ymahibere seyitan gudu fella weqt true new gud ayen zendro wedfitm enayaln bgeta feqad abaa selama bertu geta yirdachu

  ReplyDelete
 5. gibe kereye wedehaye weyewedik weste geb zegebre.as kidus dawit said gudguaden kofere azegaje wedeazegajew gudguad rasu yigebatal.Twahido haymanot gin enkuan yezemenu tekula tehadisso yikrena yesiol dejoch aycheluatim biloal medhanialem kirstos
  .

  ReplyDelete
 6. ተዋህዶ ሁሌም አዲስ ናት ተሀድሶዎች እባካችሁ አታወናብዱ ከቻላችሑ ራሳችሁን አድሱ!ሳያረጅ ያረጀው ህሊናችሁ ነውና!

  ReplyDelete
 7. Where were Abune Paulos when MK was labeling Abune Zena Markos and Abune Merkorious bla bla.
  Was Abune Paulos not using the same tactic to undermine those who challenge his legitimacy.
  He was even working hand in hand with MK for many yrs until MK turns against him.
  " By the measure you measure against others then you get it, even more...."
  Habesha said " YEENQULALU GIZE BEQETASHIGN"
  Now it is too late to stop MK.
  May be MK is God's hand against corrupt and racist clergies be it in Ethiopia or in diaspora.

  ReplyDelete
 8. ፓትርያኩ በመግለጫቸው ያወጡትን ውሳኔ ስመለከት ቅዱስ ሲኖዶስ አረጋግጦ ካልወሰነ በስተቀር ብለው በመግለጫቸው የተናገሩት አሁን ነው እንዴ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ እንዲከበር የሚፈለጉት? ለመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣን እንዳለው በመንፈስ ቅዱስ እንደሚመራና የእሱ ውሳኔ መከበር እንዳለበት የሚሰብኩንና የሚናገሩት ምን ፈልገው ይሆን? ምዕመኑ ስለተሃድሶ እያወቀ መሄዱ አስፈርቷቸው ካለሆነ በቀር፣ ስለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መከበርና አለመከበር ተቆርቁረው አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ይከበር ብለው የተሟገቱ ብፁአን አባቶችን ድብደባና ማስፈራርያ ሲደረግባቸው፣ እያዩና እየሰሙ በዝምታ መታለፉ ይታወሳል፡፡ በተጨማሪም ቅዱስ ሲኖዶስ የእርስዎን የቦሌ ሐውልት እንዲፈርስ ሲወስን እሺ በጀ ብለው ያልተቀበሉትን፣ አሁን የሲኖዶሱ ውሳኔ አስከባሪ ሆነው መቅረብዎት ትንሽ ግርምትን የሚፈጥር አይሆንም ይሆን? ፍርዱን ለፈጣሪና ለእርስዎ ትቻለሁ፡፡
  http://www.ethiopianreporter.com/component/content/article/307-letter-to-reporter/3060-2011-08-20-11-03-56.html

  ReplyDelete
 9. TEWAHIDO SELATBAL AYEDANEM BHAYMANOT ATEDENEM BKERESTOS ENEJE

  ReplyDelete
 10. I am realy sorry by aba paolos because he try to cover the truth. God protect our saint church . bertu mahibere kidusan

  ReplyDelete
 11. Be'ahizab fit matezazebia liyadergu kemichilu dergitochin kemaramed yebase min ale? Andande besekene menfesawi bikat sayihon besimiet yeminadergachew silebetekristiyanachin kena'inetachin ketikimu gudatu yameznal. Yihewum yeamlakachinin kibir yemiyasineka kemehonum belay kekiristina astemro'achinina emnetachin gar yigachal. bezihim yetenesa eminetachinin tiyakewesit yiketal. Silehonem lene mahibere kidusanim hone Aba paulos sihitet eyefesemachihu mehonachihuin astefwlu.Sile betekristiyan andnet; selamna fikir hulachin ye'emebetachinin milija yizen bertiten enitseliy. Bebetachini(bebetekiristiyan kitsir) wusit meweyayetin; mewekakesinina megetsatsesin egzizbher amlakachin yastemiren.

  ReplyDelete
 12. በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምስሉ እንዳለን ቅዱስ ቃሉ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ኣማኞች ልባችንን እናድስ። በገብራኤልና በሚካኤል ስም የሚነግደውን ጠንቋይና ደብተራ ትተን እግዚኣብሄርን እንከተል። ሌላ ይታደስ የተባለ ምን አለ ???

  ReplyDelete
 13. አየ ጉድ ማኅበረ ርኩሳን!ለመሆኑ እናንም ለገንዘብ አለቃችሁም ለገንዘብ ያደራችሁ መሆናችሁ እየታወቀ ምነው ባትመጻደቁብን ብታርፉ ምን አለ?

  ReplyDelete
 14. አየ ጉድ ማኅበረ ርኩሳን!እናተም ለገንዘብ አለቃችሁም ለገንዘብ ማደራችሁ እየታወቀ ምነው ባትመጻደቁ የፈጣሪን ጽድቅ መናገጃ አደረጋችሁ ማዓቱን እስቲያመጣባችሁ

  ReplyDelete
 15. ወንዳታ ካድሬ ጵውሎስ ይሄን ሠራዊትህን ልክ አስገባልን አለበለዚያ ለቤተክርስቲያናችን፣ ለካህናቶቻችን በተለይም ደግሞ ለምስኪኑ ምዕመን ብቻ ሳይሆን ኢብራሂም በተባለ ጳጳስ ጋር መፈንቅለ ፕትርክና እየታሰበ ስልሆን "ጠርጥር ከገንፎም..." ስለሚባል በጊዜ ይህ ምሃበር መፍረስ አለበት። እግዚአብሄር ቤተክርስቲያናችን ያስባት።

  ReplyDelete