Monday, August 29, 2011

በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የተሠወረውን አመጽ ማጋለጥ ለምን አስፈለገ?

 አባ ሰላማ ድረ ገጽ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ መጻፍና የተሠወሩ ክህደቶችን ወደ አደባባይ እያወጣች ማስነበብ ከጀመረች ጀምሮ ብዙ ጩኾቶችን እየሰማን ነው። ብዙ ሰዎች በኢሜይል አስተያየታቸውን ጽፈውልናል። የሕዝቡን፣ የጳጳሳቱን፣ የካህናቱን፣ የአገልጋዮችን እንዲሁም የማህብረ አዱሳን አባላትን አስተያየት አዳምጠናል። ያገኘናቸው አስተያየቶችና ምላሾቻችንን እንደሚከተለው አቅርበናል።

 ቤተ ክህነቱ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ ድንጋጤና መረበሽ እናያለን፤ እሰይ እግዚአብሔር ይመስገን የሚሉም አሉ። በማህበረ ቅዱሳን አካባቢ ብስጭትና ተስፋ መቁረጥ፣ ፍርሐትና መርበትበት ተስተውሏል። በሕዝቡ አካባቢ ግን መደነቅ፣ መደሰት፣ ማዘን፣ መጨነቅ፣ ግራ መጋባት ባጠቃላይ ሁሉም አይነት የስሜት አይነቶች ታይቷል። በቤተ መቅደሱ አገልጋዮች አካባቢ ከፍተኛ የሆነ ደስታ፣ መሸፋፈን፣ መሸማቀቅ፣ ሐፍረት እና መታወክ ተስተውሏል ተሀድሶ ከሚባሉ ሰዎች አካባቢ ደግሞ ደስታ፣ እልልታ፣ ዝምታ፣ ለቅሶና ኃዘን ተሰምቷል።
 አንዳድ የገድልና የድርሳን አምላኪዎች አንባቢዎችና አድናቂዎች ያልጠበቁት ሁኔታ ገጥሟቸዋል።  ያነቡት የነበረውን ማስተዋል ጀምረዋል። ከተሰሙት  ድምጾች ውስጥ ጥቂቶቹእንደዚህ አልተረዳሁትም ነበር፣ እስካሁን ድረስ በከንቱ ጊዜየን አጥፍቻለሁ፣ ካህናቱ እንዴት እንደዚህ አፈዘዙን? ሲኖዶሱ ለምን ይህን ስሕተት ሳያርም ኖረ? እግዚአብሔር ዓይኔን ገለጠልኝ፣ እስካሁን ወደ ኋላ ሲጎትተን የኖረው ይህ ባዕድ ነገር ነው፣ ባዶነት ተሰማኝ፣ እስከ አሁን ምንም ሳልይዝ ነው የኖርሁት፣ ሃይማኖቴን ገና ብየ ልጀምር ነኝ፣ ተሸውጄ ኖሬያለሁ ወዘተ… የሚሉት እና የመሳሰሉት ናቸው።
 እውነቱን እያወቁ ሐስትን ምሥጢር አድርገው ይዘው ይኖሩ የነበሩት ወይም ለሆዳቸውና ለማህበራዊ ግንኙነታቸው ሲሉ ብቻ ሲያነቡ እና ሲደግሙ የሚኖሩት ደግሞ እንደሚከተለው ድምጻቸውን አሰምተዋል ጌዜው አሁን አይደለም፤ የቤተ ክርስቲያንን ገመና ወደ ውጭ ማውጣት ተገቢ አይደለም፣ ይህ ለጠላት ያጋልጠናል፣ ሕዝቡ ደንግጦ ወደ ፕሮቴስታንት ሊሄድብን ይችላል፣ ወዮልን ጉዳችን ፈላ፣ የት ልንደበቅ ነው፣ የተሃድሶን እንቅስቃሴ ሊጎዳ ይችላል፣ የሚያንጽ አይደለም፣ የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና አደጋ ላይ የሚጥል ነው ወዘተ… የሚሉት ናቸው።
 ሲኖዶሱ እና ሊቃውንቱ ምን አስተያየት እንዳላቸው ገና አልታወቀም። በግል ያናገርናቸው ግን ሠርግና ምላሽ ነው ብለዋል፣ እኛን አሳረፋችሁን፣ ሥራችንን እየሰራችሁልን ነው ያሉ የመጻሕፍት መምህራን አሉ። በርካታ ጳጳሳት ግን አጠገባቸው ያለውን ሰው አንቡልን እያሉ ሲያዳምጡ ታይተዋል። እኛም እራሳችን ለተወሰኑ ጳጳሳት የአባ ሰላማን ሥራ አንበንላቸዋል። እኛ ያነበብንላቸው ጳጳሳት  በፊታችን ከባድ ፈተና ተቀምጧል፤ እንግዲህ ተሠውሮ መኖር አበቃ፣ ወዮልን ሲሉ ተደምጠዋል። በርከት ያሉት የቤተ ክህነት ሠራተኞችና አንዳድ ጳጳሳት እንዲሁም የማህበረ ቅዱሳን አባላት ግን የቤተ ክርስቲያን ገመና በመጋለጡ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። እኛም ለነዚህ አስተያዮቶች መልስ ለመስጠት ይህን ጽፈናል። እነሆ
 ቤተ ክርስቲያን የተደበቀ ገመና ሊኖራት አይገባም። የቤተ ክርስቲያን ምሥጢር ኢየሱስ ክርስቶስ እና በርሱ ያለው በረከት፣ ሕይወት እውነት፣ ብርሃን፣ ንጽሕና፣ ቅድስና፣ ፍቅር፣ ሰላምና ደስታ የመሳሰለው ሁሉ ነው።  ክህደት፣ ሐሰት ዘረኝነት፣ዓለማዊነት፣ ስግብግብነት፣ ዝሙት፣ ጉቦ፣ ፖለቲካ አመጽ፣ አድማ፣ የመሳሰለው ሁሉ የዲያብሎስ ምሥጢራት ናቸው። ይልቁንም ከጌታ እና ከሐዋርያቱ ትምህርት ውጭ የሆኑ  የፈጠራ ልብ ወለዶችና የሐሰት ትምህርቶች የክርስቶስ ተቃዋሚ የሆነ መንፈስ አሾልኮ ያስገባቸው የአመጽ ምሥጢር ሥራዎች እንጂ የቤተ ክርስቲያን ምስጢር አይደሉም። ገመና የምትሉት ይህን ከሆነ በጣም ያሳዝናል።
በዚች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን ነውር ዘርዝረን ልንጨርሰው አንችልም። ወገናችን የክህደት ትምህርቶችን እንደ ሃይማኖት ይዞ ሲንከራተት እናየዋለን። በጌታ ፊት ቀርቦ ንስሐ ገብቶ ሥጋውና ደሙን እንዳይቀበል፣ ሠርቶ በበረከት እንዳይኖር፣ በኢኮኖሚና በፖለቲካው ስኬት እንዳያገኝ በዚህ የክህደት ትምህርት ምክንያት አደንዛዥ መንፈስ ወድቆበታል። ወገናችን ከመንፈስ ባርነት ገና ነጻ ያልወጣ ነው። እግዚአብሔርን ይወዳል ነገር ግን እግዚአብሔርን አላገኘውም። እግዚአብሔርን ያመለክሁ እየመሰለው መላእክትን በየቀናቸው፣ ጻድቃንን በየበዓላቸው፣ ያረፉ ቅዱሳንን በየስማቸው እየጠራ ወደ እነርሱ እየጸለየ፣ ስዕለት እየተሳለ፣ እየሰገደ፣ እየዘመረ ያመልካል። እግዚአብሔርን ማምለክ ያልቻለበት ምክንያት ቀናቱን ሁሉ የያዙ የተለያዩ ነፍሳት በርሱ ፋንታ ስለሚከበሩ ነው።
ወገናችን በእግዚአብሔር ስም ሳይሆን በቅዱሳን ስም ተታሏል። ደብረ ሊባኖስ የተቀበረ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ ምህረት ያገኛል፤ ግሸንን የረገጠ ያአርባ ቀን ሕጻን ያህል ኃጢአቱ ይሰረይለታል፤ ላሊበላን የሳመ ዘር ማንዝሩ ሁሉ ይድናል፤ ክርስቶስ ሠምራ በቀን ሦስት ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል ታወጣለች፤ ያለ ማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መቶ ዓመት ወደ ታች ተዘቅዝቀው ስለጸለዩ ኢትዮጵያ አሥራት ሆና ተሰጥታቸዋለችና ያለ እርሳቸው ፈቃድ ወደ ገነት ማለፍ አይቻልም ተብሎ ለሕዝባችን ተሰበከለት።
በዚህ ምክንያት ጽድቅን ፍለጋ በየሐገሩ የሚንከራተተውን ወገናችንን እግዚአብሔር ይቁጥረው። ጌታ ግን እናንተ ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ እኔ አሳርፋችኋለሁ ቢልም ሊሰማው የፈቀደ ግን አልተገኘም።  የኛ ጥያቄ ጌታ ወደ እኔ ኑ! ብሎ የጠራውን ሕዝብ የኛ ደብተራዎች መንገዱ ላይ ቆመው ወደ ተክለ ሃይማኖት፣ ወደ አቡዬና ወደ ንጉሥ ላሊበላ ለምን ይመሩታል? ነው። ጌታ ወደ እኔ አለ እንጂ  ወደ አቡየ ሂዱ፣ ደብረ ሊባኖስ ተቀበሩ፣ ክርስቶስ ሠምራን ዝከሩ፣ አቡየን ተማጸኑ አላለም። እዚህ ላይ ስሕተት ነው የምንለው ሕዝቡ ወደ ተለያዩ ሥፋራዎች መሄዱን አይደለም የሚሄድበትን ምክንያት እንጂ። ጽድቅ በክርስቶስ እያለ በሌላ ተራራ ወይም በርሃ ለማግኘት ማሰብ ክርስቶስን መተው አይደለምን?
 ታዲያ እኛ ለምን በድረ ገጽ ለማስተማር ተነሣሳን?
 እርማት እንዲደረግበት ለሲኖዶስም ለሊቃውንት ጉባኤም በጽሑፍ በቃልና በአካል በመገኘት ጥያቄ አቅርበናል።  እኛ ያቀረብነው ሀሳብ ተገቢ መሆኑን እነርሱም በዚህ ስሕተት የማያምኑበት መሆኑን ነግረውናል። ነገር ግን ይህን ያህል ዘመን ስናስተምረው የኖርነውን ዛሬ ተሳስተናል ብንል ሞት እንጂ ሌላ አይጠብቀንም። ይህን ሕዝብ ለማስተማር እናንተ በርቱ በመጀመሪያ ሕዝቡ ስሕተቱን ይወቀው ከዚያ እኛም ለማረም ይቀለናል ተባልን።  በዚህ ተስማማንና እኛም ማስተማር ጀመርን። በአደባባይ ብቻ ሳይሆን በግልም ምመናንን ለመርዳት ሞከርን። ነገር ግን ሌሎች ሐሰተኛ ወንድሞች ይህ እኛ ይታረም የምንለው ስሕተት የፖለቲካቸውን መሠረት የሚያፈርስባቸው ሆኖ ስላገኙት በኛ ላይ ዘመቻቸውን አደረጉ። ሴት ይልኩብናል፣ ባሕታዊ ይሰዱብናል፣ ቴፕ፣ ቪድዮ ይዘው ይከታተሉናል። ወገናችችን ለመርዳት ስንሞክር መናፍቅ ናችሁ ብለው በድንጋይ ወገሩን የተገደሉም አሉ። ሊቃውንት ጉባኤውና ሲኖዶሱም እነርሱ የወደዱትን ሲያደርጉብን ዝም አለ፣ ከሥራ ስንፈናቀል ተባባሪ ሆነ። ስማችን ያላግባብ ሲጠፋ እውነተኛ ዳኝነት ሊሰጠን አልቻለም። ከቤተ ክርስቲያናችን ያላግባብ ተሰደድን ተደበደብን ተገፋን። እኛ ያቀርብነው ጥያቄና  ማህበረ ቅዱሳን የሚቃወመው በጉባኤ ፊት ለፊት ሆነን እንወያይበት መጻሕፍት በሚያስተምሩት መሠረት ይወሰን እንጂ በተደራጀ የፖለቲካ ቡድን ለምን እንሰደዳለን ብለን አቅርበን ነበር፤ ማንም ሊሰማን አልወደደም።
 ታዲያ እኛ በሊቃውንት ጉባኤ አቅርበነው ሊቃውንት ጉባኤው ተቀብሎት ጳጳሳት አምነውበት እያለ እንዴት ብቻችንን መናፍቅ እንባላለን? ፍትሕ ጠፋ እውነቱ እየታወቀ እንደ ሐሰተኛ ተቆጠርን። እንግዲህ ሕዝብ ይወቀው፣ ሊቃውንቱ የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት አልደፈሩም። ስለዚህ ወገናችን ራሱን ያድን፣ ሃይማኖቱን ይመርምር እውነቱን ይወቅ ብለን ተነሳን። ወገናችን እውነቱን የሚነግረው ሰው ስላላገኘ እግዚአብሔር እንዲረዳው ስሕተቱን ስሕተት እወነቱን እውነት ብለን ልናሳውቅው ወደድን ምርጫው ግን የራሱ ነው።
 ሲኖዶሱ በግልጥ በአዋጅ ስህተቱን ስሕተት ብሎ እስኪያርም ድረስ በአባ ሰላማ ድረ ገጽ በተለያዩ መጻሕፍት፣ በጋዜጦች፣ በሬድዮ፣ በተለያዩ ዘመን በሰጠን የመገናኛ ዘዴዎች መጮኻችንን አናቋርጥም። ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንን በተደራጀ የፖለቲካና የዘር ቡድን ተገፍተን ልንለቅ አንችልም ጦጣ ባለቤቱን አስወጣ እንደተባለው እኛን ለማፈናቀል የሚደረገው እንቅስቃሴ የበለጠ እሳት የሚጭር እንደሆነ እንጂ ሌላ ውጤት የለውም። ሐሰት እውነት ይመስላል እንጂ ከመጋለጥና ከመዋረድ አምልጦ አያውቅም።
 ሐዋርያው ጳውሎስ ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ ይልቁንም ግለጡት እንጂ ብሎ አስተምሮናልና ገና እንገልጠዋለን ኤፌ 511
ማሳሰቢያ
ተዋረድን ለምትሉ ወንድሞች ሁሉ ምን ሆናችሁ ተዋረዳችሁ? በሐሰት ከብራችሁ ለመኖር ነበር እቅዳችሁ? እውነተኞች ነን ካልችሁ ለምን ውርደት ይሰማችኋል? ከናንተስ እግዚአብሔር አይቀድምምን? የእግዚአብሔር ክብር ተንቆ ሐሰት ቦታ አግኝቶ እውነት ተጥሎ ምን ክብር አለ? የተዋረደው ሐሰተኛው ነው። እናንተ ሐስተኛ ከሆናችሁና ከሐሰት ጋር ተስማማታችሁ ጊዜ ለማሳለፍ አስባችሁ ከሆነ ግን ልንተባበራችሁ አንችልም።
 እውነቱን ተረድታችሁ በማስመሰል ለምታገለግሉ፣ ለሰው ፊት ስትሉ እውነትን ትታችሁ ወደ ጥቅም ዘወር ያላችሁ ወንድሞች ሁሉ፦ እግዚአብሔር የረዳችሁ ይህን ሕዝብ እንድትረዱት ነበር። የወገን፣ የሀገር፣ የቤተ ክርስቲያን ፍቅር  የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲህ ነውን?  የመርዶክዮስን ቃል ላስታውሳችሁና ጽሑፌን ልቋጨው።
አንቺ። በንጉሥ ቤት ስለ ሆንሁ ከአይሁድ ሁሉ ይልቅ እድናለሁ ብለሽ በልብሽ አታስቢ።  በዚህ ጊዜ ቸል ብትዪ ዕረፍትና መዳን ለአይሁድ ከሌላ ስፍራ ይሆንላቸዋል፥ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ፤ ደግሞስ ወደ መንግሥት የመጣሽው እንደዚህ ላለው ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል? አስቴር 413

አባ ነኝ

17 comments:

 1. Deaer MK & Abalatochu- Here is the latest Libweled or ye aganent sira - gedel (teAmer) for your Awaled library. You can also add it at the end of Tamre Mariam. May be The bihere bulega guy can make some business out of this. If this was happend some years ago and some crazy guy writes the witnesses it would have been best seller EOTC book, shefafenen enesalemewem neber.


  Watch an Ethiopian Lady claiming that she is Virgin Mary (Mother of Jesus).She also has testimonies who are following her. Watch the video for yourself. The fruits of EOTC CULTS - Mahbret Kidusan

  F

  ReplyDelete
 2. wooooooooow, thank God, we are finally waking up .. Bless God.

  ReplyDelete
 3. Abaselamawoch, at first I was nervours about what are doing. After reading this, I realize that you guys have no choice but to do this. In fact, God may be using you guys to help our Church. God bless you. As long as you stand for the truth, keep it up.

  ReplyDelete
 4. Hello,

  The demand for reform should not be coming in the form of vengeance. Although there is a need form some clean up, the core of the church's teaching is the best and is pure truth. Nevertheless, the false hopes that the writer has enumerated are my real issues. We need to bury the false hopes, like the following...

  "ደብረ ሊባኖስ የተቀበረ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ ምህረት ያገኛል፤ ግሸንን የረገጠ ያአርባ ቀን ሕጻን ያህል ኃጢአቱ ይሰረይለታል፤ ላሊበላን የሳመ ዘር ማንዝሩ ሁሉ ይድናል፤ ክርስቶስ ሠምራ በቀን ሦስት ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል ታወጣለች፤ ያለ ማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መቶ ዓመት ወደ ታች ተዘቅዝቀው ስለጸለዩ ኢትዮጵያ አሥራት ሆና ተሰጥታቸዋለችና ያለ እርሳቸው ፈቃድ ወደ ገነት ማለፍ አይቻልም ተብሎ ለሕዝባችን ተሰበከለት። "

  But still our core faith is the purest of all. We only need to clean the dust and focus on the Gospel. Mind you we closed the Gospel for years and lived christianity through intermediaries, I thnik it will take sometime to correct that. We need to balance between venerating the saints and worshiping God. Any thing above normal veneration should be criticized... The saints and the martyrs lived and died for the love of God. We need to do the same. Nevertheless, leaning towards Pente or promting it is the beginning of the final DEATH that does not have any ressurrection.

  ReplyDelete
 5. oh God. where is the truth?
  k

  ReplyDelete
 6. The truth? Jesus is the truth. He said "I am the truth". Let us not be like Pilot (Pilatos) who asked what the truth is and when he was told he did not seem to take an action. Ewnet Eyesus neew.

  F

  ReplyDelete
 7. To the author of the article:
  From your words and thought patterns in the article, I have clearly understood that you are a man of blinded mind. You are looking for a black cat in a dark room that doesn’t exist there. You are a man with a mind being shielded and fenced with a hard cover not to see, recognize, analyze and contemplate the reality. You haven’t any wisdom of yourself, in yourself and with yourself. You are simply rushing to open your mouth and to utter and compile all type of heresies which the westerners have fabricated in their all age since the apostles time. All what you have listed are sales manufactured by Gnostics, Marcean, Arius, Macedonius, Nestorius and later by your forefather, Lutter, the Protestant General who diverted the whole west [majority of Europe and America] upside down from all wisdom, salivation and all eternal life qualities. This is not at all a new heresy. It was there since the beginning to now. You bought this article from them, and are translating and uttering it to your people just as strange news. You are of those types who sold all their identity and humanity to the west and finally, who found themselves empty and corrupted. You are doing this, selling this, redistributing this,... just for living, to earn an amount of money for your daily food…. nothing more than this! But, I advised you to be, at least, a man who can think by himself and from himself!! Then, you will have a mind that can:
  1. learn the reality.
  2. think the reality.
  3. believe in the general truth that man is a created being who can’t say something on the deeds of the Almighty.
  4. analyze, contemplate and meditate to find the once solid true, holy, apostolic and universal religion.
  To be so:
  1. Read the history of the world, especially, history of the west!
  2. Ask your giants, forefathers, foremothers and their writings, at least, to know who you are, from which source you germinated.
  3. Get formatted from the fenceless westernized jargons and thinking patterns to be yourself and to begin thinking and living as a human.
  After doing this all, you will begin living according to your Cosmic order!!

  From One Ethiopian!!!

  ReplyDelete
 8. Anonymous above ("one Ethiopian"), ምንድን ነው የምትቀባጥረው ባክህ? ፕሮፓጋንዳ ጥሩ ያስተማሩህ ትመስላለህ። አንተ መስማት ማስተዋል አልፈለግህም እንጂ ጸሐፊው ሰምቶ አንብቦ፣ አይቶ ብቻ ሳይሆን እራሱ ከደረሰበትም ተነስቶ ነው እየጻፈ ያለው። ይህን ሁሉ ስትዘባርቅ የጸሐፊውን አንድን ነጥብ አንስተህ ይሄ ትክክል አይደለም መረጃውም ይሄ ነው አላልክም። ደብረ ሊባኖስ የተቀበረ እስከ ሰባት ትውልድ ይማርለታል ብለህ የምታምን ወንድሜ፦ በመጀመሪያ ራስህን መርምር፣ መጀመሪያ የዘረዘርካቸውን ነጥቦች አንተ አድርጋቸው። ወደ ክርስቶስ ህብረት በእምነት ግባ። ደብረ ሊባኖስ ተቀብሬ እድናለሁ ብለህ እንዳትሸወድ።

  ReplyDelete
 9. @"One Ethiopian",You said the author of this article is blind I do't know you and also the author of this article ,I read both of your writing .For me You yourself are blind for spiritual life you seems Politician because you do not point to the holy Bible your evidence is just reading Western History selling things and distributing as a christian we do't need to hate any one except devil if you hate(westerner) any one who is created by the Image of God you are exactly politician not spiritual man so I would like to suggest you this If you have a Bible read It ,If you do't try to get one and put your faith on the Word of God.I do't hate you I love you.

  ReplyDelete
 10. Beshtegnaw wendeme one Ethiopian!!! @ August 31, 2011 4:14 AM

  Do you have mental health problem? Please go to Emanuel hospital asap :)

  ReplyDelete
 11. የፃፋችሁትን አይቼአለሁ ግን እናንተ ማናችሁ? ያስነበባችሁን በውነትም ምስጢራችን ነው ፡፡ ሺ ትውልድ የሚያድን የደብተራ ተረት ተረት ነውና አምነብታለሁ ግፉበት ፡፡ስለናንተ በግልፅ ማወቅ ፈልጋለሁና አስረዱን፡፡ማሕበር ናችሁ? በክልልስ ሰው አላችሁ? ለውጥ አስቸጋሪ ባህሪ አለው እሱም ከነበረበትና ከተላመደበት ካመነበት ትክክልም ባይሆን ለመውጣት ጊዜ ይፈልጋል፡፡

  ReplyDelete
 12. Hi Abaselama,

  I as an orthodox christian who grew up with word of God know there are some things to be cleaned in the church with regard to Tamirs and Gedlis. However your faith is not right because the orthodox church has no problem with its core believe. It doesn't have problem with regard to its Dogma and cannon. The only problem lies interpretation of some concepts. All we know is the true dogmatic church but some false histories and in correct orders.

  The major problem I saw with you is you are not defending orthodox rather you look like Protestant in your dogmatic understanding. I think every one wants the Orthodox church to be good and correct. For that we are all working but there are mis conceptions in some awalede metsahift like Tamire Mariam and Seatat which should be corrected.

  Let the Likawunit and Synod do their responsibility.

  ReplyDelete
 13. I am sure the time will come and Holy Synod will understand and lead this precious Vision.And I pray to see the fullfillment of this Vision.Please LORD help me?!
  M

  ReplyDelete
 14. demo eneman nachu yemegeremegn eko lemen tedebeqachu temetalachu begelets we are protesetant lemen atelum lemen lebet kereseteyan yetqoreqore temeselalachu newer new atasemeselu enante lebetekeresetiyan asebachu ayedelem yaw sewr alamachun protesetanten masefafat new. eshi senodos men yareg new teyakew beawaje getan tekebelu hulachume pente gebu endel new yemetefelegut yehe yeleje sera new.egezeabeher beformula ena bekemere yemegegn ayedelem terarame wetan nefesetenem teketelen geta yemeyayew teru sew mehonen ena beselase sem metemeken becha new kezaw weche beyebelet enanete letekem endekomachu enawekalen selehonem rasachun meremeru yehechin betekereseteyan lamadekem betelayaye menged batedekemu teru new kewenet yehone hulu menem betedekemu ayetefam bekemere sayehone betsome bteselot begzeabeher tebeka ebakachu leteru neger seru yechi betekereseteyan betetefa huwala segebachu tsetsetu lenanetem new.

  ReplyDelete
 15. You are clearly writing Fictious stories and Fictious Commnets. Why don't you reveal yourself?... From your writing you seem to have no idea about "Orthodox Tewahedo" or you are kowingly doing "Machberber": Typical "Tehadeso"!!!... "Enen Meselu"... Kidusan Ersun Yemselu Nachwu. Gedle + Tehamer= Yewngel Frewoch Nachewu. And Saymeremer Yseytan sera hulu gedle Aybalem. ... The main thing is your Agenada:-"Astemhero Cheger Yelewum. Gedle + Tehamer Gen Yewged....bla bla bla"... You are not Orthodox Tewahedo Believers. You are typical "Tehadeso" with the mission and goal of the Weseterners!!!.... By the way nice to have you online though you don't reveal yourself clearly!!!

  ReplyDelete
 16. this is insane. Do you think we orthodox chiristians can't differentiate you(menafikan) and other who really care about our church. You are tekula with yeBeg cover. I am sure one day you will regret you wrote this. Emebirhan Ayinichachihun tabiralach. Medhanialem Eyesus Chiristos yemetadergutin atawekumena yikur Yibelachihu.

  ReplyDelete