Monday, August 15, 2011

በማህበረ ቅዱሳን የተተከሉት የ“አቡነ መንግስቱ” እና የ“አቡነ መስፍን” መናብርት ለጽድቅ ወይስ ለቄሳርነት? - - - Read PDF

መልከፀዴቅ ዘማህበረ በኵር
27/11/2003ዓ.ም.
ክፍል ፩
የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰ ስፍራ ሲቆም

እንግዲህ በነብዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል
ማቴ.፳፬፥፲፭
የቤተክርስቲያን ራስ የሆነው እየሱስ ክርስቶስ የዳግም ምጽዓቱ ምልክት ምን እንደሆነ ሃዋርያቱ ሲጠይቁት በነብዩ ዳንኤል የተነገረውን ትንቢት በመጥቀስ የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰ ስፍራ ሲቆም ያኔ አስተውሉ  የሚል ምላሽ ሰጥቶ ነበር። ይህንንም ያነሳሁት ስለእለተ ምጽአት መቃረብ ሀተታ ለመስጠት አይደለም። ትንቢቱም ምልክቱን ባየን ቁጥር አለም መጥፊያዋ ደረሰ እንድንል አልተነገረም።  ዋናው ቁም ነገር ከጥፋት ርኩሰቶች ውስጥም አንዱና ዋናኛው ፖለቲካ ዓላማ አራማጅ የሆነ ዓለማዊ ሃይል በተቀደሰው ስፍራ ተደላድሎ ሲቆም ቤተእግዚአብሄርንም ለፍላጎቱ ማስፈጸሚያ ሲያደርግ ታላቅ ጥፋት እንደሚያደርስ አስተውሉ የተባለውን ላሰምርበት ፈልጌ ነው። ይህም እውነት በዘመን ፍጻሜ ብቻ ሳይሆን ምንጊዜም ርኩሰት በተቀደሰው ስፍራ ሲቆም ጥፋት ሊከሰት እንደሚችል አውቀን እንድናስተውልም ትንቢቱ ያስጠነቅቃል። ላለፉት ሃያ ዓመታት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ደጄ ሰላም የቆመው ማህበረ ቅዱሳን  ይህ የማስጠንቀቂያ ደወል እንድናስተውል የግድ የሚለን የጥፋት ርኩሰት መሸከሙ ይስተዋልበታል።

ማህበሩ ሙሉ በሙሉ  እኩይ ነው ባይባልም ፖለቲከኞች አቅደውና ተልእኮ አስይዘው በተቀደሰችው ቤተክርስቲያናችን ተክለው ባሻቸው ቦታ ሁነው ለፈለጉት ግብ በረቀቀ መንገድ እየመሩት ስለሆነ ቤተክርስቲያኗንና ሃገርን ወደ ጥፋት የሚወስድ ጎዳና ላይ ነው። እርግጥ ማህበሩ በተወሰነ ደረጃም ያከናወናቸው በጎ አድራጎታዊ እንቅስቃሴዎች አሉት። ቤተክርስቲያኗንም በቀና ልቦና የሚያገለገሉ መንፈሳዊ አባላቱንም የማከብር መሆኔን እዚህ ላይ አበክሬ መግለጽ እሻለሁ። ነቀፌታየም ማህበሩን ለፖለቲካ አጀንዳቸው ሲሉ የመሰረቱት በውስጡ መናብርታቸውን ተክለው ከአመሰራረቱ እስካሁን ሳይለዩት በራሱ በማህበሩ በቤተክርስቲያኒቱና በአጠቃላይም በሃገራችን ላይ አሉታዊ እንድምታ ባላቸው መንገዶች ሁሉ እንዲንቀሳቀስ እያደረጉ ባሉ ህቡእ አመራሮችና የነሱ ማህደር በሆነው የማህበሩ ፖለቲካዊ ገጽታ ላይ ነው። ከማህበሩ ህቡእ ገጽታም የሚመነጭ የጥፋት ርኩሰት (the abomination of desolation) በማህበሩ በጎ ገጽታ ተከልሎ እተቀደሰው ስፍራ ቆሟልና ልናስተውለው ግድ ነው። ርኩስ ገጹ ጥፋት ሳያስከትል እሚመለከታቸው ሁሉ ( በተለይም ቀና የማህበሩ አባላት፣ ቤተክርስቲያንኗ እና ምእመናን) ትኩረት ሰጥተው መላ ሊፈልጉ ይገባል በሚል እምነትም ነው ስለጉዳዩ አንዳንድ ነገሮችን ለመግለጽ የተነሳሳሁት።
በጽሁፌ ርእስ ስለ ተጠቀሱት አቡኖች፣ መናብርቶቻቸውና ፈረሳቸው (ማህበረ ቅዱሳን) እውነቱ ስለማይነገር ትስስራቸውን ላስረዳ ስሞክር አንዳንድ ጥያቄዎች ሊነሱ ግድ ነው። ቀድሞ ነገር ቅዱሳን በዓለማዊ ፖለቲካ ምን ጉዳይ አላቸው?  ደግሞስ መንግስቱ ና መስፍን የሚባሉ  አበው አሉ ወይ? ካሉስ እንዴትና ለምን እቅዱሳን መንደር ተገኙ? እዚያስ ምን ዓይነት መናብርት ተከሉ?  ቅዱሱ ማህበርስ በውስጡ  የመሸገውን የጥፋት ርኩሰት ሳያጸዳ ለምን እስከዛሬ በተቀደሰው ስፍራ ቆሞ ሊኖር ቻለ? ርኩሰት የተፈናጠጠበት ቅዱሱ ፈረስ ወዴት እየሄደ ነው? እነዚህ ና መሰል ጥያቄዎች መመለስ የግድ ይላል።
አዎ! ፖለቲካና ቅዱስነት ለየቅል ናቸው። ሰዎች ራሳቸውን በጀማ ቅዱሳን የሚል መጠርያ ሰጥተው በይፋ መንቀሳቀሳቸው ራሱ ችግሮች አሉበት። በጥላቻ የሚመራ ጽንፈኛ  ዓለማዊ አጀንዳ ለማስፈጸም በፖለቲከኞች ሲደረግ ደግሞ ችግሮቹ የከፉ ናቸው። ቅድሚያ ነገር ስም ይመርሆ ለግብር ቅድስና ላይ አይሰራም። ቅዱስ ስም ፍጹም እምነትንና ቅዱስ ምግባርን ተከትሎ የሚመጣ ነገር ነው። በተጨማሪም ጥቂቶችም ሆኑ ብዙሃን ተደራጅተው ራሳቸውን በወል ቅዱሳን ብለው መሰየም የግብዝነታቸውና የትእቢታቸው መጠን ከፍ አድርጎ ከወደ ቤተ ሳጥናኤል እንደመጡ ይነግረን  እንደሁ እንጂ ከእግዚአብሄር ቤት እንዳልሆኑ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። በይበልጥም በአስተምህሮተ ቤተክርስቲያን ይህ ድርጊት መንፈስ ቅዱስን እንደመሳደብም ይቆጠራል። የቄሳርን ለቄሳር ቁም ነገር ያስተዋሉ የሚመስሉት የዘመናችን ፖለቲካዊ አስተሳሰቦችም ይህንን አይደግፉም። ከየትኛውም ቲዮሎጂያዊም ሆነ ዓለማዊ ፍልስፍና እና አመክንዮ አንጻር ሲታይም ድርጊቱ ርኩሰት ነው።
በስሙ በአመሰራረቱና በግብሩ ይህን መሰል ርኩሰት የተሸከመ ወገን በሃገራችን ስለመኖሩ ተጨባጭ ማስረጃ እንደ ማህበረ ቅዱሳን ያለ የለም። የማህበሩ አባላት ሙሉ በሙሉ ፖለቲከኞች ባይሆኑም አመሰራረቱ፣  መስራቾቹና እስካሁንም እየመሩት ያሉት ፖለቲካኞች እንጂ ሃይማኖት መሪዎች አልነበሩም።አሁንም አይደሉም። እርግጥ በመንፈሳዊ ሰናይ ምግባር ቤተክርስቲያኗን ሊያገለግሉ ማህበሩን የተቀላቀሉ ብዙ ቀና ወጣቶችና አባቶች ነበሩበት።አሁንም አሉ። እነሱም ስላሉ በጎ ገጽታ እንዲኖርው ስለማድረጋቸውም በማንም አይካድም። ቢሆንም እስትንፋስ ዘርተው ይዞት እንዲጓዝ የፈለጉትን ፖለቲካዊ ተልእኮ በማሸከም ማህበሩን ያቆሙትና የሚመሩት ፖለቲከኞች ነበሩ። እነሱ የሰጡት ተልእኮ በልቦናው አሳድሮ ሲመሰረትም በውስጡ ተሰውረው የተተከሉት ሁለት መናብርት ማህበሩ የሙታን ቄሳሮች አደራ ከህልመኛ ቀሳሮች ተስፋ ጋር አዳብሎ ተሸክሞ ለቅልበሳ ፖለቲካ እንዲጓዝ አድርገውታል። 
እርግጥ ማህበሩ ራሱ መችና በማን እንደተመሰረተ እውነቱን ሲናገር አይሰማም። ማህበረ ቅዱሳን እንዲቋቋም ያደረገው በ1983 ዓ.ም አጋማሽ በሃገሪቱ የተፈጠረው ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሃይል ሚዛን መለዋወጥ ያስተከተለው መደናገጥ ነበር። የኢህአዴግ ሰራዊት በወቅቱ ወደመሃል ሃገር እየገሰገሰ አዲስ አበባን ባጭር ጊዜ መቆጣጠር ወደሚያስችለው ደረጃ ስለተሸጋገረ ሁኔታው ከፍተኛ ስጋት የደቀነባቸው መዲናይቱ ውስጥ የነበሩ ፖለቲከኞች ፈልገውና እቅደው ነበር ማህበሩን የመሰረቱት። በምድራዊው የማርክሲዝም ርእዮትም ሆነ  ኢትዮጵያ ወይም ሞት ባዩ መፈክር መራሽ ብሄርተኝነት የደርግን አገዛዝና የሃገሪቱን አሃዳዊ ቅርጸ  መንግስት ከውድቀት ማዳን ባለመቻሉ በሃይማኖት መር ትግል ተዓምር መስራት ከተቻለ ለመሞከር ቅዱሳን ተዋጊዎች ማሰለፍ እንደአማራጭ ተቆጥሮ በፖለቲከኞቹ ተቀባይነት ሲያገኝም ማህበሩ እውን  ሆኗል። ለዚህም ሲባል ምስጢራዊ ተልእኮ  የተሰጣቸው መስራች ወንድሞችቄሳራዊ ዓላማ ሲባል እግዚአብሄርን የሚፈልጉ ቀና ምእመናን አጥምደው በመልመልና አንዳንዶቹንም ስልጠና በመስጠት ነበር ማህበሩን የፈጠሩት።
የማህበሩ ህላዌ አርቃቂዎችና ተግባሪዎችም የተለያዩ መነሻዎች ቢኖሯቸውም ተጣድፈው ወደ አንድ ግንባር የመጡ ሁለት ወገኖች ናቸው። በአንድ በኩል ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ፓርቲያቸው ኢሰፓና የሳቸው ወታደራዊ አምባገነናዊ አገዛዝ ግብዓተ መሬቱ ሳይፈጸም ለማዳን በነበራቸው ጥቂት ተስፋ በሃይማኖታዊ ማህበሩ ባለድርሻ ለመሆን ፈልገው ፈቃዳቸውንና ወኪሎቻቸውን አሰለፉ። በሌላ በኩል ደግም አገዛዙ ጨርሶ ሳይሞት ኢህአዴግም ጠቅልሎ አገሪቱን ሳይቆጣጠር የብሄራዊ እርቅ መንግስት በመመስረት ስልጣን ለመጨበጥ በቋመጡት በፕ/ር መስፍን ወልደማርያም የሚመሩ የምሁራኖችና የስልጣን ተስፋ የታያቸው ግለሰቦች ስብስብ ሙሉ እምነት ጥለውበት እውን ሊያደርጉት በመንቀሳቀሳቸው ነው። አንዱ ወገን ከቤተመንግስት ላለመፈናቀል ሌላኛው ወገን ደግሞ ከዩኒቨርስቲ ወደ ቤተመንግስት ቀድሞ ለመግባት ይፈልግ ነበር። የኢህአዴግ ፈጣን ግስጋሴ የፈጠረባቸው ፍርሃትና ጭንቀት የያንዳናዳቸው ግብ እውን የማይሆንበት ሁኔታ እየፈጠረ በሄደ ቁጥር የኢህአዴግን ህብረብሄራወዊ ግብና አካሄድ በአንድ መመከት የጋራ አጀንዳቸው ሆነና አብረው ቅዱሳንን ፈለጉ። ከሁለቱም ፖለቲካ ፍላጎቶች የተወከሉ አደራጅ ሴሎች በብላቴ የጦር ማሰልጠኛ ካምፕ የነበሩ ወጣት ተማሪዎችን አሰባስበው ማህበሩን በመመስረት ህላዌውን አበሰሩ።  ራሱን በቅዱሳን ስም እንዲጠራ፣ የዋህ ምእመናን አቅፎ ለመንፈሳዊ አግልግሎትና ለምግባረ ሰናይ የቆመ መስሎ ነበር በይፋ የተደራጀው። ፖለቲካዊ ተልእኮውም በህቡእ ውስጡ አስርጾ በማቆየት ባስፈለገ ወቅት እንዲተገብር በሚያስችል የረቀቀ ዘዴ ስለተፈጠረም ማህበሩ መንታ ገጽታዎች መያዙ አልቀረም። መንፈሳዊና ፖለቲካዊ ።
በተለይ ፖለቲካዊ ገጹን ከጥንስሱና ከአመሰራረቱ ጀምረው ለሚያውቁት እና ማህበሩም በተግባር የሚያከናውናቸው ኢሃይማኖታዊ ነገሮች ለሚታዘቡ እንጂ ለብዙሃኑ አባላቱ ጭምር እስከቅርብ ጊዚያት ግልጽ አልነበረም። እርግጥ ከውጭ ለሚመለከት ታዛቢ በአንዱ ገጽታው በሚከውነው የምግባረ ሰናይ  ስራ ለቤተክርስቲያኗ የተደረገውን በጎ አገልግሎት ብቻ በማየት የማህበሩን እኩይ ተልእኮና ምግባር ቢጋረድበት አይገርምም። ምክኒያቱም በይፋ ከሚነገረው ተቋማዊ ቅርጹ የማህበሩ  ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ገጽታዎች ድንበራቸው በግልጽ ተሰምሮ አይታይም። የተፈጠረበት ሁኔታ እና እያደረሰ ያለው መጠነ ሰፊ ጥፋት እንቅስቃሴ በአንዳንድ ወገኖች አለመታወቁ ወይም እንዳይታወቅ መደረጉ ማህበሩን በደፈናው የቅዱሳን ነውና ተውት የሚያስብል አይደለም።  ሀቁ ግን ማህበሩ በአቡነ መንግስቱ ና በአቡነ መስፍን ብላቴ ጦር ማሰልጠኛ ካምፕ ላይ በከተቱ ተማሪዎች መካከል ልዩ የቅዱሳን ብርጌድ ሁኖ እንዲሰማራ ለየት ያለ ተልእኮ ተሰጥቶት የተመሰረተ ሲሆን ሁለቱንም አቡኖች በመወከል ደግሞ ታላላቅ ወንድሞች ተብለው የሚጠሩት ማህበሩን በቀጥታ  በማደራጀት እስካሁንም በግንባር ቀደምትነት ይመሩታል።
በ1966ቱ አብዮት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የበላይ የነበሩት አጼ ኃይለስላሴ ከስልጣን ወርደው ክርስትናም ከመንግስታዊ ሃይማኖትነት አብራ በመውረዷ ቤተክህነትም ሲሶ መንግስትነት አጥታለች። አብዮቱን ተከትሎም በሃገራችን ታሪክ  ለመጀመሪያ ጊዜ እግዚአብሄር የለም የሚለው የደርግ መንግስት ስልጣን በመያዙም የእምነት ነጻነት ነፍጎ አብያተ አምልኮዎች እንዲዘጉ በማድረግ  የሃይማኖት መሪዎችም ህይወት የቀጠፉ እርምጃዎችም ወስዷል። ደርግ የቤክርስቲያኗን ፓትርያርክ ጨምሮ ሌሎች ብጹዓን  አባቶችና ምእመናን በግፍ ገድሏል። ብዙዎቹንም አስሮ አሰቃይቷል አልያም ለስደትና ለመከራ ዳርጓል። ይህን አድራጊው ኮሎኔል መንግስቱና አምባገነኑ አገዛዛቸው ደግሞ የሶሻሊዝም ርእዮት ተጠምቀው በየቀኑ ኢትዮጵያ ትቅደም  እና  ኢትዮጵያ ወይም ሞትን በትጋት እየፎከሩና  እያስፎከሩ ወደ ውድቀት ነበር ያመሩት። የተጓዙበትም መንገድ ሃገሪቱን ለከፍተኛ ጭፍጨፋ ርሃብ ስደትና አውዳሚ ጦርነቶች ዳርጎ ለመበታተን አቃረበ እንጂ ምንም ሳይፈይድ አገዛዛቸው እለተ ሞቱን መቁጠር ሲጀምር ህጻንና ሽማግሌ ሳይለዩ ሁሉንም ወደ ጦር ግንባር ለማስከተት በጭንቀት ሲወራጩ የሃይማኖት መንገድ ድንገት ተገለጸላቸው። ስልጣናቸውን ለማራዘም ከሃይማኖት መላ ቢገኝ ብለውም በቀሪዎቹ የስልጣን ጊዚያቶቻቸው ማህበሩ እንዲፈጠር የሚያስችሉ ሁኔታዎች አመቻቹ።
ኮሎኔሉ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ግቢ በአካል ተገኝተው  ሁሉም ተማሪዎች ወያኔን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ ወደ ጦር ሜዳ እንዲዘምቱ ሊማጸኑ ሲንቀሳቀሱ ነበር አጋጣሚው የተመቻቸው። ይህም ሁኔታ ኋላ ማህበሩን እውን ላደረጉት ወገኖች ፍላጎታቸው አቀራርበው በአንድ መድረክ እንዲገናኙ አድርጓል። ከእነሱም ውስጥ አንዱና ዋና የደርግ ደህንነት ሃይል ሲሆን ወኪሎቹን በተማሪው መካከል በብዛት በማስረግ እሺ እንዘምታለን የሁሉም ተማሪ ምላሽ እንዲሆን ለማድረግ በዩኒቨርስቲው ይንቀሳቀስ ነበር። ሌላኛው ወገን ደግሞ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ወደ ፖለቲካ ስልጣን መፈናጠጫ ለማድረግ ቀደም ብለው ሲሯሯጡ የነበሩ ምሁራን ከደህንነት ወኪሎቹ ጋር በመናበብ ተማሪዎቹን ለማሳመን ያሰማሩዋቸው ሃይማኖተኛ ወኪሎች ናቸው። ሶስተኛው ወገንም ወደጦር ሜዳ እንዲዘምት በሁለቱም ሰርጎ ገቦች ይቀሰቀስ የነበረው የዩኑቨርስቲውና የሁሉም ከ/ትም/ ተቋማት ተማሪ ነበር። ዘመቻው የግዴታ ቢሆንም ልደት አዳራሽ በመገኘት ኮሎኔል መንግስቱ ተማሪውን እዚያውኑ “እንዘምታለን” እንዲል ማድረግ የቻሉትም የደህንነቱና የምሁራኑ ወኪሎች አብረው ሲያነሳሱ በመሰንበታቸው ነው። ከእንዘምታለን ውሳኔው በኋላ ደግሞ ሁለቱም ወገኖች በዘማች ተማሪ መካከልም የቅዱሳን ዩኒት በልዩ ሃይልነት ስለመኖር አስፈላጊነት የጋራ ስምምነት ተደርሶ ማህበሩን የመፍጠር ሽር ጉድ በሚስጥር አጣድፈው ማህበሩን ወለዱት።
ከደርግ ደህንነትና ከምሁራኑ የጋራ ወኪሎችም ውስጥ አንድ ህቡእ ቡድን እንደ ታናሽ መንጋ ሆኖ ቅዱሳን ሊያሰባስብና በእርሾነትም ማህበሩን አስጀምሮ  ሂደቱን እየመራ ተፈላጊውን ተልእኮ እንዲያስፈጽም ተቋቋመ። የቡድኑ አባላትም ብዙም በፖለቲከኝነት ከማይጠረጠሩ ወይም የሃይማኖተኝነት ዝንባሌ ከሚታይባቸው እንደ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት በመሰሉ መምህራን እንዲመራ ተደረጎ ስለነበር ስራውን ማፋጠን አልተቸገረም። በተለይ ፕ/ሩ ለቤተክርስቲያን ቅርብ ሰው ስለነበሩና የሃይማኖተኝነት ዝንባሌም ስልሚያመዝንባቸው መሰባሰቡን ለመንፈሳዊ  ዓላማ መስሎ እንዲታይ ማድረግም አልተሳናቸውም። እንዲያውም  ከ1980 ዓ.ም. ጀምሮም በእሳቸውና በሚረዷችው አንዳንድ መምህራን ጓደኞቻቸው አስተባበሪነት  የከየከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ወደ ዝዋይ ሃመረ ብርሃን ቅ/ገብርኤል ገዳም የካህናት ማሰልጠኛ በመላክ ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረጉ ነበር።
ለስልጠና የተላኩትም በተናጠል ወይም በጋራም እየተሰባሰቡ መንፈሳዊ ትምህርት ይከታተሉ ከነበሩት ውስጥ የፈለጓችውን በመምረጥ ነው። ወደ ብላቴ ዘመቻ ከመደረጉ በፊትም በየአመቱ ለሶስት ተከታታይ ዙሮች ስልጠና ተካሂዶ ከ150 ያላነሱ ተማሪዎች በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ሰልጠና ወስደው ተመርቀው በየግቢያቸው ሊሰብኩ ተሰማርተው ነበር። ከዚህ ጊዜ ጀምሮም ፕ/ሩና ጓደኞቻቸውን ያቀፈው ታናሽ መንጋ ስልጠና በወሰዱት ተማሪዎች ታላላቅ ወንድሞች የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል። ምንም እንኳ የክተት ጥሪ ሲጎሰም እኒህ ታላላቅ ወንድሞች ወደ መድረክ ወጥተው ተማሪዎችን ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች እንዲዘምቱ ሲማጸኑ ብዙዎች ግራ ቢጋቡም ለጸሎትና ለሃይማኖታዊ አገልግሎት  በሚል ማህበሩን ሊመሰርቱ ሲያስተባበሩ ስልጠና ከወሰዱት መካከል እምብይ ያላቸው አልነበረም።
ተማሪዎችን ለስልጠና ወደ ዝዋይ ሲልኩ ከነበሩ ታላላቅ ወንድሞች መካከል ብዙዎቹ ሃይማኖተኝነት ውስጣቸው ዘልቆ አይታይባቸውም ነበር። ተማሪዎችን ወደ ብላቴ ካምፕ ቀስቅሰው ሲያስገቡ ግን የጸሎተኝነት ታሪካቸውን በመዘርዘር ጭምር አማኝ ተማሪዎች እንዲሰባሰቡና ማህበር እንዲመሰርቱ መቀስቀስ ጀመሩ። ቀደም ባሉት ጊዚያት ማለትም ተማሪዎቸ በ1960ዎቹ መጨረሻ ለእድገት በህብረት እንዲሁም በ1977 አስከፊ ድርቅና ርሃብ ሲከሰት ምእራብና ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ በተቋቋሙ ሰፈራ ጣቢያዎች ዘመቻ ሲያሂዱ እነሱ ተማሪዎች ሁነው ዘምተው እንደነበር ያኔም በደርግ እምነት የለሽነት ውስጥ ተደብቀው እየተሰባሰቡ ስለመጸለያቸው እንዲሁም በህቡእ የሃይማኖት ማህበር እንደነበራቸው በመግለጽም የጋራ ምስላቸውን ሃይማኖታው ልባስ የሚሰጥ ትረካም ለሚመሰረተው ማህበር አበርከተዋል።  ይህንን ገድል ተከትለው ደግሞ የብላቴ ዘማቾችም  “ወያኔና ሰሜነኞች የሚያመጡትን መዓት በጾም ጸሎት ለመዋጋት” መሰባሰብ እንዳለባቸው በመንገር ደጋግመውም ሰብከዋል።የሚገርመው ከፕ/ር ታደሰ በስተቀር ሌሎቹ ታላላቅ ወንድሞች ቢያንስ ሃይማኖተኝነትን በተመለከተ ይዋሹ እንደነበር ግልጽ ነበር። ገሚሶቹ በእድገት በህብረትም ሆነ በሰፈራ ጣብያዎች ጭራሽ ያልዘመቱ ሲሆን ዘምተው ከነበሩትም ብዙዎቹ የደርግ መንግስት ቀንደኛ ካድሬዎች እንደነበሩ፤ በተለይም እነ ሺፈራው በቀለን የመሳሰሉ ያኔ መንግስትን ወክለው ተማሪውን በማዝመት ግንባር ቀደም ተዋንያን መሆናቸውም ያንን ባልወደዱ ተማሪዎች ከባድ ድብደባ እንደደረሰባቸው ለሚያውቁት የወንድሞች ገድል እንዲህ ሲተረክ አስቂኝም ነበር። ትረካውን ያመጣው በ “ታላቅ ወንድምነት” ገብተው ለዘማች ምእመናን በአርኣያነት ራሳቸውን ማቅረብ በመሻታቸው ነበር።  ማህበሩን በዚህ ስልት በማቋቋም የፈለጉትን ፖለቲካዊ ተልእኮ ፈጻሚ   ፈረስ ለማድረግ አስበው ስለመነሳታቸው በወቅቱ የተረዱት ጥቂቶች ብቻ ናቸው ባልይባልም ብዙዎች አባላት ሊናገሩት አይፈቅዱም ወይም ይፈራሉ እንጂ መራራው እውነት ግን እሱ ነው።
ሌላው ተጨባጩ ሃቅ ደግሞ እኒህ ወንድሞች በዚህ ዘዴ ማህበሩ ብላቴ ላይ እውን ካደረጉበት ጊዜ ጀምሮም ራሳቸውን ሰወር ባለ ስፍራ አስቀምጠው እስካሁንም እየመሩት ይገኟሉ። ማህበሩ  የሚጓዝበትንም አቅጣጫ ከየወቅቱ የፖለቲካ ፍላጎታቸው ጋር አቀናጅተው በቤተክርስቲያኗም ሆነ በመንግስት ላይ የረቀቁ የቅልበሳ ሙከራዎች እያደረጉ በውስጡ የአቡነ መንግስቱንና የአቡነ መስፍን መንበር አደላድለው የሚኖሩትም እነሱ ናቸው። ብዙዎቹ የማህበሩ አባላት ይህን እያወቁም ዝምታን መምረጣቸው ለእምነቱ ያላቸው ቀናኢነት እየያዛቸው ወይም “የውስጥ ገመና” አሳልፎ ወደ ደጅ ማውጣት እየመሰላቸው ነው። በተጨማሪም ማህበሩን ለመመስረት የተሰገሰጉት ጥቂት ግን ንቁ ተኩላዎች በደርጉ ደህንነትና በታላላቆቹ ወንድሞች ቀድመው ስለመመልመላቸው ፍንጭ ሳይሰጡ ስለተንቀሳቀሱ አስመሳይ መንፈሳዊነታቸው  የተዋጣለት ስለነበር ህቡእ ተልእኮውና አደረጃጀቱ በግልጽ ተለይቶ ባይታወቅ አይገርምም። ሃይማኖታዊ ስብከቱና የማጠናከር ስራውም እንደ አቡነ ጎርጎርዮስ በመሰሉ ሊቃውንትና  የሃይማኖት አባቶች በኩልም ጎን ለጎን  ይካሄድ ስለነበር መሰባሰቡ ከፖለቲከኞች ጋር ንክኪ የሌለው እስመስሎ ለማሳየት አላስቸገረም።
ዝዋይ የሰለጠኑትም ተማሪዎችም ማህበሩ መንፈሳዊ ክንፍ ታቅፎ ምስረታው እንዲፋጠን ከፍ ያለ ሚና ተጫውተዋል።  ስልጠና የወሰዱትም  በስነመለኮታዊ እውቀታቸውና በስነምግባራቸው መንፈሳዊ መነቃቃት መፍጠር ከሚያስችል ትኵስ ወጣትነትና መስህብ ጋር ተላብሰው ስለነበር በስብከት በጾም ጸሎትና በልዩ ልዩ አገልግሎት ወጣቱን ወደ ክርስቲያናዊ ህይወት እንዲመለስ አድርገዋል። የነሱም አነሳሽነትና አብሮነት ማህበሩን እየፈጠረና እየጠፈጠፈ የመራው የታላላቅ ወንድሞች ርኵሰት ለጊዜውም እንዳይታይ አድርጓል። ትምህርት አቁመው ብላቴ የተከተቱት ተማሪዎችም የወያኔ ማሸነፍ አይቀሬነት በመረዳታቸውም በፍርሃትና በሞራል ድቀት ተጨናነቀውም ስለነበር ተኩሰው ከማያቸንፉበት መሳርያና የጦር ልምምድ ይልቅ በመጽሃፍ ቅዱስ ልባቸው መቸነፉም ግድ ነውና በብዛት መሰባሰብና አብረው መጸለይ ጀመሩ። ማርክሳዊነትም ዓለማቀፋዊ ኪሳራ እየገጠመው ስለነበር ጊዜው እመኑ ተጠመቁ ለሚል ጥሪ ተቀባይነት ማግኘት አመቺ ነበር። በዚህ ሁኔታም የብላቴ ዘመቻ ኢኣማኒ የነበረን መንግስትና ኢአማንያን የነበሩ ምሁራን ቄሳራዊ ፍላጎት በአንድ ክንፉ፣ ጽኑ ኣማኒያን ሆነው የቆዩ መንፈሳዊ አባቶችና ተማሪዎች በሌላኛው ክንፉ ያቀፈ ማህበር የሚፈጠርበትን መድረክ ማምጣት ችሏል። መድረኩን የፈጠሩትና ተልእኮውን የጠነሰሱትም የአቡነ መንግስቱ እና የአቡነ መስፍን መናብርት በወከሉት ታናሽ መንጋ በመድረኩ ተገኝተው በአጭር ጊዜ ማህበሩን እውን አደረጉ።
በሚያዝያ 1983 ዓ.ም. ማህበሩ ብላቴ ላይ ሲመሰረት ማህበረ ቅዱሳን የሚል ስም በመያዝ ነበር። ማህበሩ ከዝምታ ወይም ከአደናጋሪ ወሬ ውጭ አንዳችም ስለ አመሰራረቱና ስለ አመራሩ መረጃ የሚሰጥ ባይሆንም ቀና ከሆኑት መስራች ኣባላቱ መካከል አንዱ የሆነው ኤፍሬም እሸቴ በቅርቡ በብሎጉ ካወጣው ጽሁፍ ስለ መስራቾቹ ታላላቅ ወንድሞች እንዲህ ብሏል።
በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ የእኛው ቢጤ ተማሪ “ዕድገት በሕብረት” ተብሎ አገር ለማቅናት፣ ለማስተማር ወደ ገጠር ነጎደ። ወደ አራቱም የአገራችን አቅጣጫዎች ዘመተ። የዚያ ትውልድ አባላት የሆኑ የያኔ ተማሪዎች ዛሬ ጎልማሶች እና ባለ መካከለኛ ዕድሜ ‘ሽማግሌዎች’ ናቸው።
ከዚያም ቀጥሎ በ1977 ዓ.ም የኮሌጅና የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በሙሉ “ለመንደር ምሥረታ ዘመቻ” ወደየገጠሩ ነጎደ። ...ተማሪው በጋምቤላ፣ በመተከል፣ በወለጋ … ጎጆ ቤት ሲሠራ፣ ተፈናቃዩን ሲያቋቁም ቆይቶ ተመለሰ። በደህና ወጥቶ ለመመለስ ያልቀናውም ነበር። እነዚያ መንደር ሊመሠርቱ የወጡት ታላላቅ ወንድሞቻችን በየዛፉ ሥር፣ በየመንገዳቸው ጸሎተ ማርያም ማድረሳቸውን፣ ሲችሉም ተገናኝተው ቃለ እግዚአብሔር መስማታቸውን እንዳላስታጎሉ ሲናገሩ ሰምቻለሁ። እኛን ቃለ እግዚአብሔር ያስተማሩን የዚያ “መንደር መሥራች ትውልድአካላት የሆኑ ወንድሞች ናቸው። ወደ ዝዋይም የላኩን እነርሱ ናቸው። እኛ እና እነርሱ በአንድ ላይ ስንሆን ጊዜ በጋራ “ማ/ቅዱሳን” ተባልን።
አዎ! ኤፍሬም በትክክል እንዳስቀመጠው በወንድሞች እቅድና አመራር ብላቴ ላይ እነኤፍሬምን የመሰሉ መንፈሳውያንና ፖሊተከኞቹ ወንድሞች አንድ ላይ ማህበረ ቅዱሳን ተባሉ። እንደብዙዎቹ የማህበሩ አባላት ኤፍሬምም ሊናገረው ያልደፈረው መስራቾቹ ፖለቲካዊ ግብ ይዘው ማህበሩን ማቆማቸውና ከውልደቱ ጀምሮም በህቡእ እየመሩት ስለመሆናቸው ነው።  ብዙዎች ቅና አባላቱም ጭምር ይህንን ለመናገር ፈራ ተባ ሲሉ የሚታዩት ፖለቲካዊ ስነፍጥረቱ እንዳይታወቅ በመስጋት ብቻ አይደለም። ማህበሩ በተፈጠረ ማግስት ደርግ መውደቁና ወያኔ ወደ ስልጣን በመምጣቱ ማህበሩ ተልእኮውን በህቡእ ይዞ እንዲሰነብትና የወንድሞችም ህቡእ አመራር ሳይጋለጥ እንዲቆይ ለማድረግ ብላቴ ላይ በነ እገሌ አመራር ተመሰረተ ብሎ መተረክ አስጠቂ ስለሚመስላቸውም ነው። ማህበሩ ከአቡነ መንግስቱና ከአቡነ መስፍን የተቀበለውን ፖለቲካዊ ተልእኮ ውስጡ ላይ አስርጾ በወንድሞች ህቡእ አመራር እስካሁን ለመዝለቅም ዝምታው ከፍ ያለ ጠቀሜታው ስላለውም ጭምር።
ገና ከመመስረቱ ሁለት ወራት ባልሞላ ጊዜ (ግንቦት 20 ቀን 1983.ም.) ኢህአዴግ አዲስ አበባን በመቆጣጠሩ ማህበሩ በቅዱሳን ተዋጊዎቹ ወያኔን በመጽሃፍ ቅዱስና በጠመንጃ ተፋልሞ የአቡነ መንግስቱን ዙፋን ለማቆየት ባይታደልም ራሱንና ተልእኮውን ግን በህቡእ አመራሩ ትጋት ማስቀጠል አልተሳነውም። በተለይ የወንድሞች አመራር የአቡነ መንግስቱን ክብር በማህበሩ ልቡና አድሮ እድሏን ካልሞከረችው ከአቡነ መስፍን መንበር ጋር ጸሃያቸው የምትወጣበትን ቀን ለማብሰር ከመንቀሳቀስ ማንም አላገደውም።ኢህአዴግ ስልጣን ይዞ በፌዴራላዊ ህገመንግስት የሚመራ የአብዝሃ ፓርቲ ስርዓት ከተከለ በኋላም ማህበሩ ወያኔና ሰሜነኞች ያመጡትን መዓት ተግቶ በህቡእ የመቀልበስ ድርሻውን በቤተክርስቲያን አጸድ መሽጎ ሊከውን እየተንቀሳቀሰ እስካሁን ዘልቋል። ይህንንም ለማሳካት በ1984 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ስር በበጎ አድራጎት ስም ተመዝግቦ ነበር መንቀሳቀስ የጀመረው። ቅዱስ ስሙን እና በይፋ ያስመዘገበው የምግባረ ሰናይ ዓላማው ከመንፈስ ቅዱስ የተላከ የሚያስመስል ገጽታ ስለደረበለት የውስጡን ርኩሰት ለመሸፈንም አስችሎታል። መስራቾቹ፣ አመሰራረቱ፣ ሊፈጽመው የተነሳበት አጀንዳ እና የወንድሞች ህቡእ አመራር ላይ የተለወጠ ነገር ሳይኖር ላለፉት አስራ ዘጠኝ አመታትም በተጨባጭ ያደረገው ጉዞውው የምግባረ ሰናይ ካባ  ብቻ ከመደረቡ ውጭ የተለየ ነገር ሳይኖረው ቅዱስ ነኝ ማለቱ ግን አደገኝነቱን ያሳያል። ከነዚህ ገጽታዎቹና ህቡእ ባህሪያቱጋር ግልጽ ፍቺ ሳይፈጽም እስካሁን መጓዝ መምረጡም የአቡነ መንግስቱየአቡነ መስፍን መንበሮች ስጋና መንፈሱ ሆነው በሚስጥር ስለሚመሩትና ስለሚቆጣጠሩት ነው።
ሁለቱ መንበሮች ከእለተ ውልደቱ በፊት አዲስ አበባ ላይ በጋራ አስበው ብላቴ ላይ  ቢወልዱትም ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ ወዲህ ባሉት ሁለት ዓስርት ዓመታት ማህበሩን በመካከሉ ተገኝቶ የሚያሽከረክረው የአቡነ መስፍን መንበር ነው። አቡነ መንግስቱ በአካል ማህበሩ ላይ ባይኖሩም መንበራቸውና መንፈሳቸው ግን አብሮና ተከብሮ በማህበርተኞቹ መካከል የመኖር መብቱ አልተነፈገም። እድሜ ለህቡእ አመራሩ።
ከሁለቱ መናብርት ውጭም በምስረታው ወቅት በህይወት ያልነበሩት አቡነ ጃንሆይም የማይተናነስ ክብር የተቸረው መንበር በመህበሩ ውስጥ አላቸው። እርግጥ የጃንሆይ መንበር የተደላደለው በከፊል በአቡነ መስፍን መንበር በኩል እየተወከለ ሲሆን በከፊል ደግሞ የማህበሩ ፖለቲካዊ ፍልስፍናዎች እና ስነዘዴዎች “ድሮ ቀረ” ከሚለው አስተምህሮ ስለሚመነጩ ነው። በተጨማሪም ጃንሆይ በዘመናቸው የቤተክርስቲያኗ አባት እንደነበሩ መናገር ማህበሩን በድሮ ናፋቂ ምእመናን ዘንድ ተወዳጅ እንደሚያደርግ አያጠያይቅም። ለዚህም ይመስለኛል አዲስ ነገር ጋዜጣ ላይ መሽገው የኢህአዴግን መንግስት ተቀባይነት ለመንሳት አብጠልጣይ ፖለቲካዊ ጽሁፎች በመጻፍ ንቁ ከነበሩት የማሀበሩ አባላት አንዱ የሆነው ታምራት ነገራ “የመለስ መንግስት ትምክህተኞች ብሎ በጥቅል ከሚሰድበን ኒዮ ደርጊስቶች እና ኒዮ ሞናርኪሰቶች ቢለን የተሻለ ይገልጸናል” ብሎም የጻፈው። ታምራት በጥቅሉ ራሱንና ተቃዋሚዎችን በሙሉ በአንድ ጎራ አድርጎ የሰጠው ኒዮ ደርጊስቶች እና ኒዮ ሞናርኪሰቶች የሚለው ስም ማህበረ ቅዱሳንን ህቡእ ልቡን በትክክል ይገልጻል ባይ ነኝ።    
ሁለቱ ስርኣቶች በአካለ ስጋ በነበሩበት የአገዛዝ ዘመናቸው የነበራቸው ተፈጥሮና ባህርይ ተቃራኒ ቢሆንም በህይወት በሌሉበት ወቅት የማህበረ ቅዱሳን ዳግመደርጊዝምና ዳግመ ሞናርኪዝም በፍቅርና በአንድ እቅፍ አስማምቶ ያኖራቸዋል። በሁለት አሰርተ አመታቱ የማህበሩ ጉዞም የተጻራሪዎቹ አገዛዞች ሙት መንፈሶች ቅዱሳን ወኪሎች ላይ አድረው አንድ ጥምር ርእዮት ሆነዋል። ሸማቂ አመራሩ  እኒህ መንታ ርእዮቶች በማህበሩ ሰርጸው እንዲኖሩ በተግባሩም የሚገለጹ ተጨባጭ እውነቶች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ፊውዳላዊውና ዘውዳዊው የንጉሱ አገዛዝ “አንድ ሃይማኖት፤ አንድ ቋንቋ፤ አንድ ሃገር” በሚል እሳቤ የሚመራ አሃዳዊ የስርዓተ መንግስት ቅርጽ ነበረው። ወታራዊው የደርግ አገዛዝ ደግሞ ፊውዳሊዝምንና ክርስትናን በመቀነስ እንዲሁም ማርክሲዝም ሌኒኒዝምን በእምነት ደረጃ ተቀብሎ ሶሻሊስታዊ መንግስት ቢያውጅም  በተጨባጭ ያው አንድ ቋንቋ አንድ ሃገር... እሳቤ ላይ ተመስርቶ የተራጀ አሃዳዊ ስርአተ መንግስት ነበረው። ሁለቱ አገዛዞች በህይወት እያሉ  ብዙ ተጻራሪ ባህርያት ቢኖሯቸውም ከሞት በኋላ በአጸደ ነብስ አንድ ሁነው መንቀሳቀስ የቻሉት በዚህ ማህበር ነው ማለት ይቻላል። ማህበሩ የሙት ቄሳሮቹ መንፈሶች በአንድ አዋህዶ የሚጋልብ ፈረስ እንዲሆን ያሰቻሉትም ሁኔታዎች የተፈጠሩትም በምስረታው ወቅት ከነበሩ ከሶስት ዋና ዋና ምክኒያቶች እንደመነጨ ለመገመት አይከብድም።
አንደኛው ምክኒያት የደርግ አገዛዝ ግብዓተ መሬቱ ሲቃረብ ማርክሲዝምን አሽቀንጥሮ መጣሉና በአሃዳዊው እሳቤ የተቃኝው የሃገሪቱ ስርዓት መንግስት ቅርጽ ለዘለቄታው እንዲኖር ከሚሹ ማናቸውም ወገኖች ጋር ሊሰራ በመፍቀዱ ነው። ሁለተኛው ምክኒያት ደግሞ በሃገሪቱ ለሚኖሩ ህብረ ብዙ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች በቋንቋቸው መናገርና መጻፍ መፈቀድ፣ ለሃይማኖቶች በነጻነት መከበር፣  ለባህሎች እኩልነት መረጋገጥ፣ ብሎም የክልሎች ራስን በራስ ማስተዳደር እና ከዚያም አልፎ በመፈቃቀድ ብቻ ለሚመጣ ሃገራዊ አንድነት መረጋገጥ ሲል እንደሚዋጋ ያሳውቅ የነበረው ኢህአዴግ አሸናፊነቱን ሊያረጋግጥ ተቃርቦ ስለነበር ነው። ኢህአዴግ ስልጣን ሲጨብጥ አሃዳዊውን የመንግስት አወቃቀር ፈርሶ  በፌደራላዊ ስርዓተ መንግስት እንደሚተካ አሃዳዊውን እሳቤ ማስቀጠል ለሚሹ ወገኖች ሁሉ ግልጽ ነበርና ወደ አንድ ጎራ እንዲሰባሰቡ አስገድዷቸዋል። ስለዚህም ቀቢጸ ተስፋው ደርግና ተስፈኞቹ ምሁራን አሃዳዊው እሳቤ ለማስጠበቅና መጤ ያሉትን ፌዴራላዊ እሳቤ እንዳስፈላጊነቱ በህቡእም በይፋም ለማጥቃት በጋራ ማሴርና መንቅሳቀስ ግድ ሆነባቸው። በሁለቱም ምክኒያቶች ተጻራሪዎቹ መንፈሶች አሃዳዊነት በአደራ ለማስቀመጥ ሲሶ መንግስትነቷ በቀረባት ቤተክርስቲያን አጸድ እጅ ለእጅ ተያይዘው ገቡና በቅዱሳን ስም ሊጠለሉ “አንድ አካል አንድ አምሳል” ሆነው ማህበሩን ፈረሳቸው አደረጉ።
ሶስተኛው ምክኒያት ደግሞ  ኢህአዴግ ወዲያው ስልጣን ላይ እንደወጣ በተገበረው የመደራጀት መብት በአቡነ መንግስቱና በአቡነ መስፍን ወኪሎች ተጠፍጥፎ የተሰራው ማህበር የመብቱ ተጠቃሚ ሆኖ በይፋ እንዲንቀሳቀስ ማስቻሉ ጋር ይያያዛል። የ“ወንድሞች” አመራር ማህበሩን በ “ቅዱሳን ሰራዊትነት” አሰልፎ ደርግን የመከላከል ግቡ የብላቴው ስጠና ሳይጨረስ ቢጨናገፍበትም ኢህአዴግ ባመጣው የመደራጀት መብት ጥላ ስር ህልውናውን ማስቀጠያ እድል ማግኘቱ በበጎ አድራጎት ስም ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ በነጻ መንቀሳቀስ አስችሎታል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ዳግመደርጊስትና ዳግመሞናርኪስት ተልእኮውን በነጻነትና በወጥነት ተሸክሞ ለማሳካትም ምቹ አጋጣሚ እያፈላለገ በመጓዝ ላይ ነው። ድርጊቱንም  በግልጽና በህቡእ ኢህአዴግን ከሚቃውሙ ሃይሎች ጋር እስተሳስሮ እየተገበረ ይገኛል። ፌዴራላዊ ስርዓቱ ስር ሰዶ ለሙቱ አሃዳዊ እስተሳሰብ ጀምበር መጥለቁ አስረጅ ነባራዊ ሁኔታዎች እየዳበሩ ሃገሪቱንም በብዙ ዘርፎች ብዙ ለውጦችና ግስጋሴዎች ማስጨበጡ ለማንም በገሃድ ቢታይም በቅዱሳኑ ሰፈር ይህ ሁሉ በዝምታ ወይም በጩሀት የሚካድ ነገር ነው። ማህበሩም ሆነ ተቀጥላ የሆነላቸው ጽንፈኛ ተቃዋሚ ወገኖች  ሁሉም ነገር ድሮ ቀረ እያሉ አብረው በማዜም  አሃዳዊው  አስተሳሰብን የሚናፍቁ ጨለምተኛ እንቅስቃሴዎች በይፋና በትጋት ከመከወን አልተገቱም።በማህበሩ ክብረ መንበር ያላቸው አቡነ መስፍን ከማህበሩ ውጭ በይፋ ለሚንቀሳቀሱ የተቃውሞ ሃይሎች ዘንድ አንዴ እንደ መንፈሳዊ አባት  አልፎ አልፎም እንደ “የተቃውሞው ጎራ አባወራ” ሆነው እስካሁን መዝለቃቸው ዳግመደርጊዝምና ዳግመሞናርኪዝም የ“ቅዱሳኑ” ርእዮት  ሁኖ እንዲቆይ በማድረገ አይነተኛ ድርሻም አለው።
ይህ ማህበር የወደቁ ቄሳሮች ዳግም ትንሳኤያቸውን ለማረጋገጥ ተስፈኞች ደግሞ የስልጣን  ጥማታቸውን ለመወጣት ሙታንና ህያዋን በሚገናኙበት የቤተክርስቲያን አጸድ ውስጥ በበጎ አድራጎት ሽፋን ፖለቲካዊ ተልእኮ ይዘው እንደሚንቀሳቀሱ በገሃድ ያሳያል። ኒዮ ደርጊዝምና ኒዮ ሞናርኪዝም ክርስትና ተቀብሎ ቅዱሳን ሃይሎቹን አሰልፎ ቤተክህነትን ጸረ መንግስት ዓመጽ መቀስቀሻና የኢህአዴግን መንግስትን ገልብጦ ስልጣን መጨበጫ መሳርያ ለማድረግ ተግቶ እንደሚንቀሳቀስም የማህበሩ ህቡእና ርኩስ ገጽ ይመሰክራል።
በተለይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ራሱን ባደባባይ ወጣ ማድረግ ህቡእ የነበረው ተልእኮውን ማራመድ ጀምሯል። የጥፋት መንገዱ የአኩይ ገጽታው እጣ በተመሳሳይ መንገድ እስካሁን እንደሄዱት ወገኖች ያደርገዋል እንጂ ይሳካለታል ማለት አስቂኝ ቢሆንም እርኩስ አካሄዱ ቤተክርስቲያኗን በታሪኳ ካሳለፈቻቸው ቀውሶች ጋር የሚተካካል ችግር ውስጥ እንደከተታት ግን አይካድም። ይህ ደግሞ በሃገራችን ህዝቦችና መንግስት ላይም አጋጣሚ ጠብቆ ሊፈነዳ የሚሻ ብጥብጥ ከማነሳሳት ወደኋላ እንደማይል ስለሚያረጋግጥም አደጋ ሳያደርስ መላ ሊባል ይገባል። የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ በሮች ለምእመናን ክፍት ስለሆኑ ከየትኛውም የህብረተሰብ ክፍልና የአመለካከት ወገን የሚመጡ ለመንፈሳዊ ዓላማ ወይም ለበጎአድራጎት ተደራጀተው  ቢንቀሳቀሱ በጎ ነገር ነው። ህቡአን ወንድሞቹ  ማህበሩን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረውት የጥላቻ ፖለቲካና የዓመጽ እንቅስቃሴ በገሃድ እንዲያካሂድ እስኪያደርሱት ድረስ ቸል ማለት ግን ሌላ ነገር ነው።  ማህበሩ ከተፈቀደለት ተልእኮና ዓላማ ውጭ  እንደሆነም ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ እስከ መንበረ ፓትሪያርክ ጽ/ቤቶች ባሉ ማህደሮቹ በእኩይ ምግባሩ ዙርያ በሚቀርቡ ክሶችና ስሞታዎች ተጣብበው ማየት ብቻ ይበቃል። ከቅርብ ጊዚያት ወዲህም ርኩሰቱን ታግሰው የነበሩ አባላቱ ማህበሩ ወደ ቤተክርስቲያን አገልጋይነት ምግባሩ እንዲመለስና ከስውር አመራሩ እንዲጸዳ በመፈለግ ድምጻቸውን በግልጽ ወደ አደባባይ አውጥተው እየተነፈሱም ነው።
በቅዱሳን ስም ተሸፍኖ በቤተክርስቲያኗ ሲፈጽማቸው የኖረና አሁን ሊፈጽም ስለሚንቀሳቀስባቸው ድርጊቶች እንዲሁም የህቡእ አመራሩ የእዝ ማእከላትና የእንቅስቀሴ ምህዳር በተመለከተ በቀጣዩ ክፍሎች ለማስረዳት እሞክራለሁ።

*****************

24 comments:

 1. It is so interesting which I have never known. Please, continue.............

  ReplyDelete
 2. o! the next title to condemn MK will be associated with, i think, racism. we have read many including accusation associated with politics and terrorism.generally, people who condemn MK with false accusations have their own hidden agenda, but shall they succeed?

  ReplyDelete
 3. nice script please convert to film

  ReplyDelete
 4. I have never heard such kind of agenda because you guys always write false about MK. Ke chefen tilacha ena mederege silfelegachut dibik agenda enkifat silhonebachihu new hule le MK metifo negere new yemititsifut. Why you can discus MK members to solve your problem? Tikikilegna chrstian yihn yadergale gin Enante.....?

  ReplyDelete
 5. This is a marvelous article. it embraces a telling truth about MK which no one has yet tried to tell. Abune Mengistu, Abune Mesfin, Talalaq wondimoch, Bilate etc waaaaooow! all these show undeniable connection between MK and its ye Qesar Menged. It is time to cleanse MK off the political party hidden deep inside its heart!!!

  ReplyDelete
 6. Very interesting assessment on MK.

  ReplyDelete
 7. This article helps those of us who prefer to burry our heads in the sand like the proverbial ostrich. This fact based analysis reminds all of us to adher ye Qesarn le Qesar.

  ReplyDelete
 8. የማህበረ ቅዱሳን ፖለቲከኝነት ጥቂቶች የተነፈሱት ግን እንዲህ ያልተተነተነ ሐቅ ነው። አሁንም ለሁሉም አባላቱ ልቦና ሰጥቶ ርኩሰቱን እንዲያጸዱ የእግዚአብሔር እርዳታ አይለይ ስንል በጸሎት መትጋት ያስፈልጋል።

  ReplyDelete
 9. Abyiet !abiey! abyiet! Ye Mahbere kidusanina chir sil alwodim mister (balefew Daniel Kibret Yagaletew) bezih tsihuf bmigeba tefreterete....yiqetil!

  ReplyDelete
 10. Hmmm...who is Mahbere bekur?

  ReplyDelete
 11. የጆሊ ባር ሚስጥር ይፋ ሆነ ማለት ነው? “እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል” የተባለው ሐቅ ተፈጸመ መሰለኝ። እንዴት ያስደስታል። ለማንኛውም ክርስቶስ እንዳለው እውነት ነጻ ያወጣል ብሎ ማህበረ ቅዱሳን በንስሃ ወደቀናው የእግዚአብሄር መንገድ ለመመለስ ይዘጋጅ። አለበለዚያ የሚፈራው እውነት ጨው አይደለህም ተብሎ እንዲወረወር ያደርገዋል።
  ዮሐንስ ከአራት ኪሎ

  ReplyDelete
 12. There are things I don't like about MK.
  But I am going to hate everything Aba Selama is doing after reading this Abune Mengistu and Abune Mesfin lie.
  Please chand your name from Aba Selama to radio fana.
  How come you lie this big while you have Abune Gorgorious' picture on your webpage.

  ReplyDelete
 13. tad, you need to be ready to listen brutal truth. Even to the extent it compels cutting a cancerous finger out of your hand. you don't need to blame this article or aba selama for revealing the truth. whether you like to hear it or not the presence of Abune Mengistu's and Abune Mesfin's thrones in the association is real. that is also what lies inside MK right from its inception to the present.

  ReplyDelete
 14. May be this analysis has strong political tone. that sounds good. because it is explaining about the political origines of Mk and its political activities. in light of this, it is based on factual truth. Is there any one who denies the fact that MK was established and still it is led by talalaq wondimoch? who are talalaq wondimoch? aren't they politicians? We know them all. and mentioning their names is not difficult. lemin yiwashal gobez?

  ReplyDelete
 15. It is not fair to blame Aba selama by calling it radio fana. I disagree with some of the points in this article. for example, I am not sure whether Abune Mengistu is connected to MK. But the connection between Abune Mesfin and MK is right. Prof. Mesfin and his colleages are founding smember of Mk and they are upporting MK in tinat ena mirimir. their presence is not also free from their political motives.
  Emnet

  ReplyDelete
 16. It is not coincident to hear Sibhat Nega's theory in this article. That is why I stick to "Radio fana"

  ReplyDelete
 17. Whether it resembles with accusations spoken by Sibhat or any other person what really matters is its substance, WHICH IS UNDENIABLE TRUTH. The true colour of MK is political. Mahbere Kidusan is like the scarelet lady (Galemota) spoken in Revelation 17: 4, ...a beautiful jewellery made of gold...cup in her hand full of abominations and filthiness of her fornication...
  Better to repent Tad!!!

  ReplyDelete
 18. God bless you.The truth revealed the blood of brothers and sisters shed by them spoken more and more.This is the time of repentance for them.I am really eager to see part II.
  Mk accusing and beating also silently killing so many innocent who not willing to accept their agenda.I am live testimony on what they doing on my friends while I have been Bahirdar and Gonder.I have seen also with may naked eye here in Addis.
  No one can hide the truth behind the carpet.

  ReplyDelete
 19. Indeed MK is a galemota calling itself a saint while it is a bed fellow with hatemongering politicians. i am specially grateful of this writer who demonstrated rightly calling oneself a saint is a blasphemy( mensfes qidusin mesadeb). can a group of people with a political mission call themselves "Saints"? This is talaq rikuset.

  ReplyDelete
 20. ይበል! የደቂቀ ብላቴ ጉድ ወጣ

  ReplyDelete
 21. ለዛ ነው እንዴ የማህበረ ቅዱሳን መሪ(ስማቸውን ረሳሁ)በመጽሄት ላይ አስሬ የኢሃዴግ ደጋፊ ነን ብለው የተናገሩት ስውር አጀንዳ ከሌላቸው ይኢሃደግ ደጋፊ ነን ማለት ምን አመጣአው

  እግዚአብሄር ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን
  መንሹ በእጁ ነው ፍሬውን ከገለባው ይለያል

  ReplyDelete
 22. Yes, MK's leader(at least in its official face) is Memhir mulugeta and he has given a deliberately confusing remark recently.
  As you observed rightly, Mulugeta stated, most members of MK are members of EPRDF. He said so when every one including government authorities started to question the unholy motives and activities of MK. The reason why he resorted to utter such an untrue information is because his masters( the clandstine leaders of MK) instructed him to say so in order to divert attention. But every body knows that MK belongs to the camp of the extremist opposition. Mulugeta himself is the primary witness. Besides, Daniel Kibret has also expliitly explained what the true colour of MK is, including its Hibu'e Amerar. If there is any body who is not clear with who and where are the Hibu'e Amerar, I call up on every one to check the very institution in which memhir Mulugeta and other key leaders of MK are currently employed,i.e., an institute in AAU which is very close to St Mark Church. Guys go and make a little research to satisfy your curiosity. Definitely you will start to open your eyes as to what and where the Erkus beast is. Hope you reflect your observations in a way it helps to bring MK back to THE WAY OF GOD, rather than its WAY OF the Qesar!!!

  ReplyDelete
 23. አይ... መምህር ሙሉጌታ! አበው ሲተርቱ ‹‹የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች›› እንደተባለው እደብቃለሁ ብሎ አፍረጠረጠው። የማህበሩ አባላት ኢህአዴጎች ናቸው ቢል የሚያዋጣ መስሎት አደጋ ለመከላከል ነበር አሳቡ። ይህ ውሸቱ ግን የማህበሩ ድብቅ ማንነትን አጋለጠ እንጂ እንደታሰበው እልሆነም። ወይ አለመጠርጠር! ዲያቆን ዳንኤል (አሁን ቢልፈሰፈስም) በሚገርም ሁኔታ በሆድ ታብቶ የነበረውን ሁሉ አንድ በአንድ ዘክዝኮ ጽፏል። በዚህ ጽሁፍ ደግሞ መልከፀዴቅ ማህበሩን የተጣባ ቄሳራዊ መንፈስ ምንነት ከብላቴ ጀምሮ በደንብ ገልጾልናል። በቀጣይ ክፍሎች ተጨማሪ መረጃዎች እንደሚሰጠን ተስፋ አለን። ሌሎችም እንዲሁ። በማህበሩ ውስጥ የተደበቀውን የቄሳር ቋጠሮ ሁሉም ሊፈቱልን የሚሞክሩት ወደ እግዚአብሄር መንገድ እንዲመለስ ብለው ነው። ይህም ቅዱስ ሃሳብ ነውና ይደገፋል። ጎሽ! እግዚአብሄር ይስጣችሁ።
  ሌሎቻችንም ማህበሩ ከተጣባው ቄሳራዊ ደዌ እንዲነጻ የተቻለንን ያህል እውነቱን እንናገር። የማህበሩ ቀና አባላት ከእንቅልፋቸው እንዲነቁ እንርዳ። ቤተክርስቲያናችንም ከዚህ ርኩሰት እንድትገላገል በጸሎት እንትጋ፤ ህያው እግዚአብሄር መልስ ስለሚሰጥ።

  ReplyDelete
 24. I have been a regular reader of Abaselama as I wanted to be conversant on all issues related to my Church. I have been genuinely following and appreciating the teachings and the dialogues regarding our church practices. I never thought that it stands for one or another political party. My heart is broken. Why should you worry whether MK is a political entity or not? That is upto the contending parties to fight back. Who are you to tell us all these shit in the name of AbaSelama? If you are really the followers of Jesus, you should have taken a strong stand on how to liberate the Church from wrong teachings instead of painting MK a colour that would give you the muscle to wipe them out. Why should you go to the extent of condemning the newspapers that are critical of EPDRF and have been closed. If you beleive this justice, then this blog is all about defending EPRDF. Your move is satanic and I feel sorry for you. I got sick and I felt like throwing up. I will never, never open this blog what so ever. Good Bye Addis Lisan!!

  ReplyDelete