Tuesday, February 21, 2012

ጾም ለአዲሱ ሰው - - - Read PDF

እንኳን ለዐቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ!!! ጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ በዚህ ምድር ላይ እየተመላለሰ በሚያስተምርበት ወቅት የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ቀርበው «እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው? አሉት» {ማቴ 9፥14} እነዚህ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት መጾማቸው መልካም ነበር። በጾማቸው ውስጥ ግን የሚያዩት እግዚአብሔርን ሳይሆን የሌሎችን አለመጾም ነበር። ስለዚህ ጾማቸው «በክስ የተሞላ ሥነ ሥርዓትን» ብቻ ያሟላ እንጂ የልብ መሠበር፣ የንስሐ መንፈስ፣ ፍቅር የነበረው አልነበረም። ጾማቸውን ለሃይማኖታዊ ውድድር አውለውታል። ስለዚህ መልስና እርካታ ያለው አልነበረም። ጾም ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት መንፈሳዊ መስመር፤ ቅዱስም ተግባር ነው። ቅዱስ ተግባር የሆነው ጾም ዋጋውን ከሚያጣባቸው ነገሮች በጥቂቱ ብንጠቅስ፦
1. ጾማችን ትዕቢትን ሲወልድ
2. ጾማችን የሌሎችን አለመጾም ሲያይ
3. ፈተናው የራቀልን ጸጋ የበዛልን በቸርነቱ መሆኑ ቀርቶ በጾማችን ሲመስለን
4. በግድ ያለፈቃዳችን ስንጾም ዋጋ እናጣለን።
   የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ብዙ ቢጾሙም መጾማቸው ግን የሐዋርያትን አለመጾም ያሳያቸው ነበር። ራሳቸውንም የጾም ፖሊስ አድርገው አቁመው ነበር። በሌላ ሥፍራ ላይም አንድ ፈሪሳዊ እርሱ በሳምንት ሁለት ቀን እንደሚጾም ቀራጩ ግን ያልተገራ ሕይወት እንደሚኖር ለእግዚአብሔር ተናግሯል። በዚህ መመጻደቁ ግን ተዋርዶ ተመልሷል። ጽድቅ አለኝ ያለው ፈሪሳዊ ባዶ እጁን፣ ምንም ጽድቅ የለኝም ያለው ቀራጭ ግን በጽድቅ ተመልሰዋል። {ሉቃ 18፥9-14} የሚጾም ሰው የማይጾሙ ሰዎችን በጸሎት የሚያስባቸው እንጂ የሚከሳቸው አይደለም። ጾም ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ጉዳይ የምንፈጽምበት እንጂ እየተያየን በመፈራራት የምንጾመው መሆን የለበትም። በጾም ውስጥ እራስችንን ማየት ይገባናል እንጂ ከኋላችን የቆሙ የሚመስሉንን ሰዎች ማየት አይገባንም። ከምግብ ብቻ ሳይሆን ከኃጢአትም ካልተከለከልን ጾም እውነተኛ አይደለም።
   በነቢዩ ኢሳይያስ
«ስለ ምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም? ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።
 እነሆ፥ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም።
 እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ዘንድ ነውን? በውኑ ይህን ጾም፥ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደደ ቀን ትለዋለህን?
 እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?
 እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?
 የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል።  የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም። እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ ጣትህንም መጥቀስ ብትተው፥
 ባታንጐራጕርም፥ ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፥ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፥ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል።  እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ» ኢሳ 58፥3-11።
  በእግዚአብሔር ፊት ተወዳጅ ጾምና ጸሎት ለማቅረብ አስቀድሞ ርእስ መያዝ፣ ንስሐ መግባትና ይቅር መባባል ይገባል። ከጾሙ ቀጥሎ ደግሞ ረሀብተኞችን ማጥገብ፣ የታረዙትን ማልበስ ይገባል። እነዚህ ነገሮች በሌሉበት የሚደረግ ጾም ዋጋው ያነሰ ነው። ጌታችን የራሳቸውን መጾም ተናግረው የሌሎችን አለመጾም ክስ አድርገው ላቀረቡት የጾም ፖሊሶች «ሚዜዎች ሙሽራው ከነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉ ነገር ግን ሙሽራው ከነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል በዚያ ጊዜም ይጦማሉ» አላቸው [ ማቴ 9፥5]
  በእሥራኤል ባሕል ሙሽራና ሚዜዎች እንዲጦሙ አይፈቅድም። ጾም በሀዘን በለቅሶ ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት በመሆኑ ሙሽሮች እንዲጦሙ አይፈቀድም ነበር። በእኛም ሀገር መንገደኛ፣ የታመመ፣ አራስ፣ ወታደር፣ መጾም እንደሌለባቸው ይታወቃል። ጌታችን በእስራኤል ባህል መልሱን ሰጣቸው። እርሱ ሙሽራ እንደሆነ እንደሚሄድም አብሮ ተናገረ።
  ጌታችን ሙሽራ ነው። ሙሽራ ለአንድ ቀን ሙሽራ ይሆንና ከዚያ ቀጥሎ የኑሮ ታጋይ ይሆናል። ጌታችን ግን ሁለት ሺህ ዓመት ሙሽራ ነው። ሙሽራ የማይጠገብ፣ የደስታ ምንጭ፣ የሁሉ ዓይን የሚያየው፣ በምስጋና የሚከብር፣ ነው። ጌታችንም ሙሽራ ነውና አይጠገብም። ሁሉም ነገር ገና በአፍ ውስጥ ይሰለቻል፣ እንደጨበጡት ያረጃል፣ የዚህ ዓለም ነገር በምኞት ትልቅ፣ ሲይዙት ትንሽ ነው። ሙሽራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የደስታ መፍለቂያ፣ የተድላ አገሯ የሕይወት ወደቧ ነው።
  ጌታችን የሁሉ ዓይን የሚያየው የልብ ሁሉ ናፍቆት፣ የአገልግሎትም ማዕከል ነው። ነቢያት ስለ እርሱ ትንቢት ተናገሩ ስለዚህ ነቢያት ተባሉ፣ ሐዋርያት ስለ እርሱ ሰበኩ ስለዚህ ሐዋርያት ተባሉ። እግዚአብሔር አብ «በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት» አለ ማቴ 17፥5። ቅድስት እናቱ ድንግል ማርያምም «የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ» በማለት ወደ ልጇ አመለከተች [ዮሐ 2፥5] ቀስት ሁሉ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ያመለክታል። እርሱ ሙሽራ ነውና በምስጋና እና በምሥክርነትም ይከብራል። ሙሽራ በሌለበት ሚዜዎች የሉም። ሚዜዎች ለሙሽራው ክብር ይቆማሉ። ክብራቸው እርሱ ነውና። ኢየሱስ ክርስቶስም የመላእክት ማዕርጋቸው፣ የቅዱሳን ጌታቸው ለኃጢአተኞች ቤዛቸው ነው። እርሱ ስለ እራሱ ይከብራል፣ እነርሱ ግን በእርሱ ይከብራሉ። ዛሬ ግን ወገናችን ሙሽራውን አባሮ ሚዜዎችን የያዘ ይመስላል። የሙሽራው ስም ሲጠራ ይከፋልና። «ኢየሱስ» የሚለውን ስም ሳይቀር ለሌሎች ሰጥቶ ባዶ እጁን የሆነ ትውልድ እንዳናተረፍ መምህራን ተግተን ልናስተምር ይገባናል። ያለ ክርስቶስ ክርስትና ሊኖር አይችልምና። ሰባክያን ሳይቀር ይህን ስም ደጋግማችሁ ጠራችሁ እየተባሉ ክፉ ስም ሲሰጣቸው እናያለን። በሚያሸልመው ነገር መካሰስ ከጀመሩ ቆይተዋል። ትልቁ ትክክለኛነት የሆነው፣ የጌታችን ስም የክስ አንቀጽ ተደርጎ መወሰዱ፣ ትልቅ ኃጢአት ደግሞም ክህደት ነው። ከእኛ ክርስትና በቀርም በስሙ የሚያፍር የየትም አገር ክርስትና እምነት የለም።
  ጌታችን ለዮሐንስ ደቀ መዛሙርት እንዲህ አላቸው «በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚያኖር የለም መጣፊያው ልብሱን ይቦጭቀዋልና መቀደዱም የባሰ ይሆናል። በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጥጅ የሚያኖር የለም። ቢደረግ ግን አቁማዳው ይፈነዳል፣ የወይን ጠጁም ይፈሳል፣ አቁማዳውም ይጠፋል፣ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል ሁለቱም ይጠባበቃሉ» (ማቴ 9፥16-17)
   የደቀ መዛሙርቱ ሕይወት አሮጌና በመንፈስ ቅዱስ መታደስን ያላገኘ ነበር። በዚህ አሮጌ ማንነት ላይ ጾም ቢታዘዝ ይከብደዋል። ደግሞም ያብሰዋል። ብዙዎች ሕይወታቸው ሳይለወጥ ጾም ሲመጣ ጾመኛ ይሆናሉ። ጾም ሲፈታ በበለጠ ኃጢአት ውስጥ ይወድቃሉ። መጠጥና ዝሙትን በጾም ወራት ያቆማሉ እንጂ አይተዉትም። ኃጢአትን አዳፍነው እንጂ አጥፍተው አልመጡም። ጾም ለነርሱ ለኃጢአት የዓመት ፈቃድ መውሰጃ ነው። ያለማቋረጥ ከጠጡ ጉበታቸው ይፈርሳልና፣ ብዙ ዘመን ለመጠጣት ጾምን ይጠቀማሉ። «የቀበሮ ባሕታዊ» ማለት እንዲህ ነው። ኃጢአት ግን ቅበላና ፋሲካ የሌለው ሁልጊዜ ልንርቀው የሚገባ ነው። ከእነዚህ ሰዎች ጋር የሚኖሩ እንደሚያውቁት ከጾም በኋላ አመጻቸውና ባሕርያቸው እየከፋ፣ አብረዋቸው የሚኖሩትን ያስመርራሉ። ላልተለወጠ ሰው የሚያስፈልገው የክርስትና ሙሉ ትምህርት ንስሐና እምነት ነው። ለብዙዎች ግን ጾም ራሳቸውን የሚያታልሉበት፣ መንፈስዊ ድራማ የሚሠሩበት ነው። በጾማቸው ሰዓት ሃይማኖተኝነት ይታይባቸዋል። ለሃይማኖታቸውም ይሳደቡላታል። ሃይማኖት ግን የሚኖርላት እንጂ የሚሳደብላት አትፈልግም። ሃይማኖት በራሳችን ላይ ድልን ታቀዳጀናለች እንጂ በሌሎች ላይ ሥጋዊ ድልን አትሰጥም።
በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያምኑና አዲስ ሰው ለሆኑ ጾም ከጸሎት ጋር አስፈላጊ ነው። ለልማድ ክርስቲያን ግን አስፈላጊ አይደለም። ጾም ርእስ፣ ይቅርታና ንስሐ ያስፈልገዋል። ጾም በአዋጅ ሲደረግ ቤ/ ክርስቲያን ርእስ መስጥት ይገባታል። በግላችን ስንጾምም ርእስ መያዝ አለብን። አሊያ እግዚአብሔርን ባስቸኳይ እፈልግሃለሁ ብሎ ዝም እንደማለት ነው። በውነት ለአዲሱ ሰው ጾም አስፈላጊ መሆኑን ጌታችን ተናግሯል። ማቴ 9፥16-17።
ከዲያቆን አንድ ሰው አሜሪካ

25 comments:

 1. Kalehiywot yasemalen,

  Amazing, educational and timely message, Thanks D. 1 sew.

  F

  ReplyDelete
 2. እኔ እንጃ ምን ማለት እንዳለብኝ ሰለ አባ ሰላማ እግዚአብሔር ይህን የምትሰሩትን አይቶ ሀሳባችሁን ያሳካላችሁ።

  ReplyDelete
 3. This is a good piece; perhaps the best of all I have seen on this site. However, the author is afraid of being accused for writing the article because he is hiding under ከዲያቆን አንድ ሰው አሜሪካ. Mr. Deacon, don't worry much; you have done a good job. No file will be opened against you.. just kidding. Ye Filseta Tsom berket kehulachin keminaminibet gar yehun. I have been fasting it with an agenda as the author has suggested; I believe and hope that God will respond positively.

  ReplyDelete
 4. Very interesting article. May God bless your work. Indeed, the Lord Jesus is the bridegroom of the Church. And his bride, the Church, longs for him, chanting MARANATHA (O Lord Come) so that he may come and take her to the Kingdom. This concept is clearly reflected in the genuine literary sources of the Ethiopian Orthodox Church. For instance, the preparatory service of QEDDASE says: "who has seen a bridegroom who gives his flesh as a meal on the day of his wedding?" This unique bridegroom, is Jesus Christ, the only begotten Son of God, our Redeemer who has freed us from the bondage of the enemy.

  ReplyDelete
 5. it is reasonable! keep writing...

  ReplyDelete
 6. kalehiwot yasemalen,

  ReplyDelete
 7. Great!!! God Bless You

  ReplyDelete
 8. ደጀ ሰላም ለምን "ይቅርታ ከዳንኤል ክብረት" የሚለውን ፖስት ካደረጉ በኋላ አስወጡት? መጀመሪያ ለወሬ ይቸኩላሉ:: ከስህተታቸው አይማሩም:: ደግሞ "ስለ ተሐድሶ እና ተያያዥ ጉዳዮች የዘሪሁን ሙላቱ ቃለ ምልልስ" ከሚለው የዳንኤልን ፎቶ ቆርጠው ለምን አወጡት? ዘመኑ የመረጃ መሆኑን የዘነጉት ወይንም ያወቁት አይመስሉም::  http://www.dejeselam.org/2011/08/blog-post_14.html

  ReplyDelete
 9. This is just tooo beautiful EGZIABHER ABEZETO YEBARKACHEHU uffeyee MENFES QEDUS BESEWOCH ADERO SERAWEN SISERA ENDET DES YELAL YE DINGEL LIJ EYESUS YEKBER. BEZIH AYENET SHEE AMET BETSOM AYKEBEDEGNEM YE HELINA EREFT AGENEHBUT YEHENE TSEHUF EGZIABHER ABEZETO YEBARKACHU KEEP UP THE GOOD WORK KE ("DEJE/SELAM" DEJE SETANEN) YANEBEB LEBU YEQOSELE EZIHE METO YEFEWESAL.

  LONG LIVE TEWAHEDO

  ReplyDelete
 10. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲያቆን። ማኅበረ ሰይጣን የተባለው የስም ማኅበረ ቅዱሳን ጾምን መካሰሻ ማድረጉን ተከትሎ ብዙዎች ጾማቸውን ወደ እግዚአብሔር መቅረቢያ ሳይሆን ለሃይማኖተኝነታቸው ማስመስከሪያ አድርገዋል። ይህም ከነቅዱስ ያሬድ መንፈስ ምን ያህል መራቃቸውን ያመለክታል። ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ። ጾምን እንጹም ወንድማችንን እህታችንን ደግሞ እንውደድ የሚለው ቃል በዚህ በጾም ወራት ልናስበው የሚገባን ነው። ወገናችን የኢትዮጵያ ሕዝብ ወንድማችን ነው። በረሃብ አለንጋ እየተመታ ያለው ወንድማችን ነው።
  ለማንኛውም ቃለ ሕይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete
 11. 14 በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው? አሉት።

  15 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ጊዜም ይጦማሉ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. yemihedbet gize derswal atsnagn menfes kab yemiweta elklachewalehu ale slezih kehede buhuala atsnagn telkolachew tsomn jemrewal

   Delete
 12. `የሚጾም ሰው የማይጾሙ ሰዎችን በጸሎት የሚያስባቸው እንጂ የሚከሳቸው አይደለም`

  ጸሃፊውን ቃለ ህይወት ያሰማልን
  ትልቅ ወቅቱን የጠበቀ ትምህርት ነው
  እግዚአብሔር ይመስገን

  ReplyDelete
 13. Aba selamoch melse lemaget enanetega tiru noew bzhi atlanta nekatebeb yemibal debetra tenqwyi al ena yesiquar beshat albegne eyal aytomem selzihe tenkolawom kidasawom tayayezotalna you guys have nice teaching system to preach as modern world to keep eotc in right map of road so please say or write some thing. This the time to reform traditional way of debtera life one hand bible in other hand tenwuola.

  ReplyDelete
 14. aba selama if you didn't know this article is not written by diacon ande sew it was taken from anketse birhan newsletter. u better write the true source. i think it is the sign of truth and Christianity.

  ReplyDelete
 15. አባ ሰላማዎች፣ ይህንን ጽሁፍ የዛሬ 6 ወር በፊትም አስነብባችሁናል፡፡ አሁንም የአብይን ጾም ምክንያት አድርጋችሁ እንደገና መልቀቃችሁ በጣም ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም አብዛኞቻችን የምንጾመው በልማድ እንጂ ርዕስ ይዘን ወደ ክርስትና ስላልመጡ ወገኖቻችን፣ ስለታመሙት ወገኖቻችን፣ በአጋንንት አሰራር ስለታሰሩ ወገኖች ወዘተ… በማሰብ አይደለም፡፡ ስለዚህ መልዕክቱ በጣም ጠቃሚ ስለሆነ እንደገናም ስላስነበባችሁን እናመሰግናለን፡፡

  ReplyDelete
 16. orthodoxn mesadebh mehonu algebahm malet new....diyacon tebyew.......besme diyacon zim bleh tzefnaleh adel? Orthodox comment yesetachihu sewoch eski astewulut.......... Lehulachin lib yisten.

  ReplyDelete
 17. tigermalachu sele ewnate kehona ewnate yezo memtate new yemen macbarebare
  sirachu hulla macbarebare kirstose bihone achbarebru alalem yemen besem managade new  TEKULAWACH

  ReplyDelete
 18. GOD BLESS YOU!!!

  ReplyDelete
 19. A honey tainted poison..."«ኢየሱስ» የሚለውን ስም ሳይቀር ለሌሎች ሰጥቶ ባዶ እጁን የሆነ ትውልድ እንዳናተረፍ መምህራን ተግተን ልናስተምር ይገባናል። ያለ ክርስቶስ ክርስትና ሊኖር አይችልምና። ሰባክያን ሳይቀር ይህን ስም ደጋግማችሁ ጠራችሁ እየተባሉ ክፉ ስም ሲሰጣቸው እናያለን።" That is not the case!!! People are labelled based on their hidden practice and not because they used the name Jesus intensively in their teaching...! Don't pull the cart before the horse.

  ReplyDelete