Monday, August 15, 2011

ለዳንኤል ክብረት - - - Read PDF

እውነቱን በማውጣትህ እናመሰግንሃለን፣ ይቅርታ በመጠየቅህ እናደንቅሃለን፣ ለማስተባበል በመሞከርህ ግን ለክብርህ እንጂ ለእውነት የማትቆም ሰው መሆንህን እንረዳለን።
ማህበረ ቅዱሳን የፖለቲካ ድርጅት ነው የምንለው ስም ለማጥፋት ሳይሆን እውነትን በድርድር ለመቅበር ሲታገል እያየነው ስለሆነ ነው። ሃይማኖት የፖለቲካ ሥራ አይደለም። ዳንኤል የማህበረ ቅዱሳንን አላማና አካሄድ ምንም ሳይደብቅ ነግሮናል። ይህን ዳንኤል ሳይነግረን ብዙዎቻችን አስቀድመን ተናግረናል። ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን የተባለው መጽሐፍ ከሦት ዓመት በፊት አስረግጦ ነግሮን ነበር። ያን እውነታ መንፈስ ቅዱስ አፉን ጸፍቶ የማህበሩ ቀንዳም አወጣው። ይህ ለዳንኤል ስሕተት ሊሆን ይችላል (በማህበሩ አባላት ካለው ክብር የተነሣ) አባላቱ ከነርሱ ተሰውሮ የሚኖረውን የማህበሩን ምሥጢራዊ እውነታ ማወቃቸው አደጋ ስለሚሆን ለዳንኤል ይህን ምሥጢር ማጋለጡ ስሕተት ነው። እርሱም ምሥጢሩን ከጊዜ በኋላ የደረሰበት መሆኑን ለቅርብ ጓደኞቹ ከሚያወራው ወሬ ለመገንዘብ ችለናል። 
ዳንኤል  ባለማወቅ ተሳስቶ ሲሠራ የኖረውን ስሕተት ባደባባይ መናዘዙ ንስሐ ሊሆነው ይችል ነበር። ነገር ግን አሁንም ኑዛዜው ለርሱ ስሕተት ስለሆነ ዕድል አመለጠው። ነገሩ፣ በሽማግሌ፣ በጓደኛ፣ በሰው ግፊት፣ በዲፕሎማሲ፣ በራሱ በደረሰበት ያልታሰበ ድንጋጤ ለማድበስበስ ቢሞከርም፣ ማህበሩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም እየፈጸመው ያለውን ወንጀል ከትውልድ ዓይን መሠወር አይቻልም። የተገፉት የቅዱሳን እንባ እና የፈሰሰው ደም እንደ አቤል ደም እየጮኸ ይኖራል። የዳንኤል ኑዛዜም የዘላለም እውነት ሆኖ ይኖራል። ዳንኤል በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ካመራሩ ጋር ተስማማ ማለት ከእውነት ጋር ተስማማ ማለት አይደለም። እውነት በዲፕሎማሲ ብዛት ሐስት ሊሆን አይችልም።
የማሕበሩ ልጆች የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ እንዲገቡ አልፈልግም። እግዚአብሔር እንዲህ ዓይነቱን ህሊና አልሰጠንም። እርቁም ክፋት የለውም። እውነትን ለመሸፈን እና ነገሩን ለመደበቅ የተደረገ ስምምነት መሆኑን ስለምናውቅ አታስመስሉ ነው እንጂ ተጣሉ አንልም ማህበሩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ለመጠቀም እንጂ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመጥቀም የተቋቋመ አይደለም። ይህ ነገም እንደገና የሚፈነዳ እውነት ነው። ዳንኤል የተናዘዘው ይህን ብቸኛ እውነት ነው። አመራሩ. ማህበሩ ለቤተ ክርስቲያኒቱ መመሥረቱን ዘንግቷል አሁን ቤተ ክርስቲያኒቱ ለማህበሩ ወደሚል አመለካከት ዞሯል የሚለው የዳንኤል ክብረት ኑዛዜ የማይታበል ሃቅ ነው። ዳንኤል ይቅርታ ጠየቀ ማለት ይህ አባባል ውሸት ሆነ ማለት አይድለም።
የዳንኤልን ኑዛዜ ተሃድሶ የለም  በሚል ትርጉም የተረጎመው አንባቢ ያለ አይመስለኝም። ዳንኤል ተሃድሶ የለም ብሎ አያውቅም። ዳንኤል ከልጅነቱ ጀምሮ፣ በሕልሙም በውኑም ሲያስጨንቀው የሚኖር አንድ ነገር አለ፣ እርሱም ተሃድሶ ነው። ከገሃነም ይልቅ ተሃድሶን ይፈራል፣ ዳንኤል ክብረት እንደተሃድሶ የሚፈራው የለም። ሲተኛም፣ ሲበላም፣ ሲጠጣም፣ ሲሄድም፣ ሲጸልይም፣ ሲጽፍም፣ ተሃድሶን እያሰበ ነው። ዳንኤል ተሃድሶ በሚለው ነገር የሥነ ልቡና ቀውስ የደረሰበት ታማሚ ወንድም ይመስላል የጤና ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት ከሆነ አንድ ሰው ስለ አንድ ነገር በመጨነቅ ብዙ ጊዜ የሚያጠፋ ከሆነ የአእምሮ በሽታ ምልክት መሆኑን ይናገራሉ። ዳንኤል ክብረት ከልጅነቱ ጀምሮ ስለተሃድሶ በመጨነቅ፣ በመጻፍና በማስተማር ያረጀ ሰው ነው። ስለተሃድሶ የሚጨነቀውን ያህል ስለ እስልምና አይጨነቅም፤ ስለጥንቆላ፣ ስለባዕድ አምልኮ ስለ ስህተት ድርሳናት አይጨነቅም አይናገርምም። ተሃድሶ ግን ያስጨንቀዋል ምሥጢሩ ምን ይሆን? ስለዚህ ዳንኤል ተሃድሶ የለም ብሎ ሊናገር አይችልም፣ ዋና በሽታው ይህ ነውና።
አባ ሠረቀ እና በጋሻው ማህበሩን ስለነኩ እንጂ... የሚለው የዳንኤል ኑዛዜ ግን ማስተባበል የማይቻል ሐቅ ነው። አባ ሠረቀ እና በጋሻው ተሃድሶዎች አይደሉም። ማህበሩ  በጋሻውን የተጣላው ዳንኤል እንዳለው ማህበሩን ስለነካ ብቻ አይደለም፤ በጋሻው በሚገጥማቸው መዝሙሮችና በሚሰብካቸው ስብከቶች ሕዝብን በመማረኩ፣ በገንዘብ እና በተደማጭነት ማህበሩን ስለበለጠ፣ ሕዝብ ለማህበሩ ጀሮውን በመንሣት ወደ በጋሻው በመዞሩ፣ የማህበሩ የገቢ ምንጭ ወደ በጋሻው እየዞረ በመምጣቱ፣ በምቀኝነት የተካሄደበት ዘመቻ ነው እንጂ በጋሻው ተሃዶሶ አይደለም። በጋሻውን ተሃድሶ የሚሉት በዚህ ምክንያት ብቻ ነው። ተሃድሶ የሚባሉት እንዲህ በመድረክ ዘራፍ የሚሉ ሰዎች አይደሉም። ቤተ ክርስቲያናችን ከጊዜ በሁዋላ የገቡ አጉል ነገሮችን በመተው መስተካከል/ተሃድሶ/ጽዳት ያስፈልጋታል በሚል እንቅስቃሴ እናዳለ አምናለሁ ነገር  ግን በጋሻውና አባ ሠረቀ ተሃድሶዎች አይደሉም።
ማህበሩ አባ ሠረቀን የሚከሳቸው ማህበሩ ኦዲት ይደረግ፣ ድርሻውን ይወቅ፣ በሥራት ይሂድ በማለት አጣብቂኝ ውስጥ ስለከቱት ብቻ ነው። እኔ በግሌ አባ ሠረቀ ተሃድሶ ይሁኑ አይሁኑ ለማወቅ ቢሮአቸው ተገኝቼ ፈትኛቸዋለሁ፣ እንኳን ተሃድሶ ሊሆኑ የተሃድሶን ጽንሰ ሐሳብም በሚገባ አይረዱትም። ዳንኤል ስለ አባ ሠረቀ የመሠከረው ትክክል ነው።  ይልቁንስ በርካታ ተሃድሶዎች በማህበረ ቅዱሳን ውስጥም አሉ። ዳንኤል ማህበሩ የገንዛ አባላቱን ይሰልላል ሲል የገለጠው ተሃድሶዎች ማህበረ ቅዱሳን ውስጥ በወረራ መልኩ በመግባታቸው ነው። ተሃድሶዎች በማህበሩ ውስጥ በስፋት እንዲገቡ በተደረገው መሠረት እንደ ሰደድ እሳት በመቀጣጠል ላይ ይገኛሉ። የማህበረ ቅዱሳን አመራር በተሃድሶዎች ብዙም ሳይዘገይ ይያዛል። አዎ የማይቀር እውነት ነው።
ዳንኤል የብዙዎቻችንን ጩኸት በኑዛዜው በማረጋገጡ እናመሰግነዋለን፣ ከዚህ በኋላ የፈለገውን ያህል ለማስተባበል ቢሞክር አይታመንም። ምናአልባት ማህበሩ ተሳስቻለሁ አላማዬን እና አካሄደን አስተካክላለሁ ቢል ትንሽ ከቁስሉ ሊፈወስ ይችላል ብለን እንጠብቃለን። ምክንያቱም የሚከተሉትን የዳንኤል ኑዛዜዎች ማስተባበል አይቻልምና።
. የማህበሩ ጉዞ /ክርስቲያኒቱን የት ለማድረስ እንደሆነ ግልጽ ግብ የለውም።
. ማህበሩ ሥራውን ትቶ የገዛ አባላቱን እስከ መሰለል ደርሷል።
. በማህበሩ የግል ጋዜጦችን ማንበብ የተከለከለ ነው።
. ተሃድሶን ለማጋለጥ እንጂ ተሃድሶን ያመጣውን መሠረታዊ ችግር ለመፍታት ያስቀመጠው ስትራቴጂ የለም።
. አመራሩ ማህበሩ ለቤ/ክርስቲያኒቱ የተመሠረተ መሆኑን ዘንግቷል አሁን /ክርስቲያኒቱ ለማህበሩ ወደሚል አመለካከት ዞሯል።
. በጋሻውን የሚከሰው ማህበሩን ስለነካው እንጂ ለቤ/ ክርስቲያን አደጋ ነው ብሎ ስላሰበ አይደለም።
. አባ ሠረቀንም ቢሆን በእምነት ችገር ይከሳቸዋል እንጂ ከርሳቸው ጋር ያለው ችግር ማህበሩን መንካታቸው ነው አባ ሠረቀ ማህበሩን ሳይነኩ የፈለጉትን ቢሆኑ ኖሮ አይነገራቸውም ነበር።
. እኔ እንደምገምተው የማኅበሩ አባላት መንግሥትን እንዲፈሩ እና እንዲጠሉ የሚፈልጉ አካላት በአመራሩ ውስጥ ሳይኖሩ አይ ቀርም።
. ማህበሩ ቤተ ክርስቲያንን እመር ሊያደ ርጉ የሚችሉ ሃሳቦችን አመንጭቶ በማኅበረሰቡ ውስጥ አስርጾ ተገቢ ለውጥ እንዲመጣ ከማድረግ ይልቅ የተለመደው ዓይነት መሥሪያ ቤታዊ ሂደት ውስጥ ገብቷል፡፡
. በዚህ ርእዮቱ ምክንያትም «ራስ ደኅና» ብሎ ቤተ ክህነቱን ለመጠቀሚያነት ብቻ ይገለገልበት ጀመር፡፡ አንዳንዴ እንዲያውም ማኅበሩ ቤተ ክህነቱን ከማጠንከር ይልቅ ከቤተ ክህነቱ ድክመት ተጠቃሚ መሆንን የመረጠ ያስመስለው ነበር፡፡
. ማኅበረ ቅዱሳንም በአመራር እጦት ምክንያት ለቤተ ክህነቱ ችግር መፍትሔ ያመጣል ሲባል እርሱ ራየቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር እየሆነ ነው፡፡ ምናልባትም የማኅበሩ አሠራር እና አመለካከት ጊዜ ያለፈበት/ኤክስፓየር እያደረገ/ ያለም ይመስላል ፡፡ ከዚህ በኋላ ማኅበረ ቅዱሳን በዚህ አስተሳሰቡ፣ አካሄዱ እና አሠራሩ ለውጥ አምጭ ሆኖ መቀጠል አይችልም፤ ቆሟል/ስታክ አድርጓል/፡፡ ምናልባት እንግሊዝኛ ተናጋሪ ቤተ ክህነት ሆኖ ሊቀጥል ይችል ይሆናል
. ቤተ ክህነቱ ቢበላሽ፣ ቤተ ክርስቲያን ብትጠፋ፣ ችግሮች እየተባባሱ ቢመጡ እርሱን እስካልነካው ድረስ ዝምታን ይመርጣል፡፡
. ማኅበሩ ከተመሠረተ በኋላ በቤተ ክህነት ምን ዕድገት መጣ? ምን ዓይነት የአሠራር መሻሻል መጣ? ምን ዓይነት የዕውቀት ሽግግር ተደረገ ምናልባት አንድ ሁለት ኮምፒውተሮች ተገዝ ተው ተሰጥተው ይሆናል፡፡ ለዚህም ነው የአመራተወካይ ከአቦይ ስብሐት ጋር ሲወያይ ማኅበሩ በቤተ ክህነቱ ምን ለውጥ አመጣ? ለተባው ጥያቄ መልስ መስጠት ያቃተው
ማኅበሩን ለመምራት የሚሞክር ሥውር አመራር አለ
ለብቻው ተወያይቶ፣ ለብቻው ወስኖ ወደ አመራሩ እየመጣ አጀንዳዎቹን የማኅበሩ አጀንዳ የሚያደርግ፤ አንዳንዴም ጽ/ቤቶቹን ተጠቅሞ ውሳኔዎቹን የሚያስኬድ አመራር አለ፡፡ {የማይታበል ሐቅ ነው }
ዳንኤል ተስማማ አልተስማማ ከዚህ በላይ የተጠቆሙት ኑዛዜዎች ግን ሐቅ ናቸው።

ሙሉውን የዳንኤልን ኑዛዜ የሚከተለውን በመጫን ማንበብ ይችላሉ
https://docs.google.com/viewer?a=v&pid=explorer&chrome=true&srcid=12qs9ytXQ-A4m4g1la4WRtpj_9-ukZD2X4RzL4DNdsMKv0h4aEfFodtQcTI8_&hl=en_US
መላከ ሰላም ተሰማ ነኝ

26 comments:

 1. እኔ እንደ ሚመስለኝ የማህበረ ቅዱሰን ነገር እያበቃለት ነው ዳንኤል ሁሉን ነግረ ነግሮናል የምናውቀውን አውቀናል ከመህበሩም የነበርን ሰዎች ወተናል። ዳንኤልም የታረቀበት ምክንያቱ እኔ እንደ ሰማሁት ከማህበሩ አባላት ጔደኞቸ ሌላ ጉድ ስለማህበሩ አወጣለሁ ስላለ ከማውጣቱ በፊት የሚፈልገውን ገንዘብ እንስጠው እና አፉን እንክደነው በለው ነው። አንድ ነገር ግን የምለው ዳንኤለን እግዚአብሔር ይስጥህ መህበሩ ምን እንደ ሆነ ስላሳወከኝ ገንዘቤንም ከመስጠት ስላስቆምከኝ ይህንን አስተያየት የምታነቡ የማህበረ ቅዱሳን አባላት ወንድሞቸ በተሎ ከመህበሩ ውጡ ገንዘባችሁ የነ ዳንኤል የአሜሪካ መጔጔዣ አይሁን። በቃ በቃ

  ሆዳም ማለት ይህ ነው።

  ReplyDelete
 2. እኔ እንኳ ከማህበሩ አባልነት ከወጣሁ ብዙ ጊዜ ሆኖኛል ግን ይህንን ሁሉ ትርምስ ስሰማ እግዚአብሔር በጊዜ እንደገላገለኝ ተረዳሁ። ሳላውቅ ቤተ ክርስቲያኔን ከመበደል እና የወንጌል ደንቃራ ከመሆን ስላተረፈኝ አመሰግነዋለሁ። ቤተ ክርስቲያናችን ከማህበረ ቅዱሳን ጥርስ ወጥታ፤ ሲኖዶሳችን ጠንክሮ ሰውን በማዳን ላይ ያተኮረ ተልዕኮዋን እንድትቀጥል እግዚአብሔር ይርዳን።

  ReplyDelete
 3. Well said! The facts that DK revealed remain facts. We know them as well. However, DK should not be belittled for worrying about Tehadso because any Tehadso insitigated and planted by external forces would damage the chrch for good. His worry is justified! We know that most of the Tehadso wings are sponosred by protestants. Any meaningful Tehadso should come from within and should be led by the Synod and the true fathers.

  If the church preached the cean bible (salvation through Christ Jesus) without those killer and useless false hopes, I think the church would be in greater shape and there would no be a need for Tehadso. As Orthodox Christians, we will not ever share the heresy and denial of protestantism. We remain faithful to the whole Gospel of Christ Jesus and continue to love and venerate the most kind Mother He has given us. Unfortunately, protestants accept only a part of the Gospel, and, as a result, they will be called inferior, according to the word of God, in heaven. We don't want to be called inferior and would like to receive our full wage. So, we remain Orthodox, but would work for ways to clean up some of the dust thrown at our church over the years.

  ReplyDelete
 4. You guys, I didn't understand you. Indeed, MK tried to declared as if Daniel will have a plan to give modification. But still whether it is true or false we are waiting for his usual pen, from him.
  So, do you mean he has posted a modification? If he did so, please post it or shows us?
  Then, we will pay him his salary.

  ReplyDelete
 5. Where is the evidence?

  ReplyDelete
 6. If he said what you wrote, he is downing to Hell more than MK

  ReplyDelete
 7. «ያለንም እኛ የሞትንም እኛ ተረጋጋ» አሉ ልጅ እያሱ፡፡
  ያለንም እኛ የሞትንም እኛ፡፡ የሞትንም እኛ የሞትንም እኛ

  አሌሳክንድርያ፤ ቨርጅንያ


  Daniel Kibret.

  ReplyDelete
 8. Aba Selamawoch

  Ye Danielin yikrta deje selam segn tewat post adrigot endetelemedew mahiberu sinchcha delete adrgotal ke kidamew enku metsihet scan adrigachu post adrigut bakachu!

  ReplyDelete
 9. ዳንኤል ተስማማ አልተስማማ ከዚህ በላይ የተጠቆሙት ኑዛዜዎች ግን ሐቅ ናቸው።

  ሙሉውን የዳንኤልን ኑዛዜ የሚከተለውን በመጫን ማንበብ ይችላሉ
  https://docs.google.com/viewer?a=v&pid=explorer&chrome=true&srcid=12qs9ytXQ-A4m4g1la4WRtpj_9-ukZD2X4RzL4DNdsMKv0h4aEfFodtQcTI8_&hl=en_US

  ReplyDelete
 10. መላከ ሰላም ተሰማ ነኝ

  ----ስምና ምግባር የተለያዩ ናቸው!!!

  ReplyDelete
 11. ደጀ ሰላም ለምን "ይቅርታ ከዳንኤል ክብረት" የሚለውን ፖስት ካደረጉ በኋላ አስወጡት? መጀመሪያ ለወሬ ይቸኩላሉ:: ከስህተታቸው አይማሩም:: ደግሞ "ስለ ተሐድሶ እና ተያያዥ ጉዳዮች የዘሪሁን ሙላቱ ቃለ ምልልስ" ከሚለው የዳንኤልን ፎቶ ቆርጠው ለምን አወጡት? ዘመኑ የመረጃ መሆኑን የዘነጉት ወይንም ያወቁት አይመስሉም::  http://www.dejeselam.org/2011/08/blog-post_14.html

  ReplyDelete
 12. u see?? the enemy of devil/tehadiso/protestant is unity/excuse/love,that is why followers of this blog get much,much gutted/angered. IT IS ONLY IN YOUR DREAM THAT MK BE DESTROYED,KEEP ON YOUR DREAMING

  ReplyDelete
 13. የተከበራችሁ የአባ ሰላማ ብሎግ ባለቤት

  እባካችሁ ስለ ክርስቶስ የዳንኤል ክብረት ይቅርታ ፖስት አድርጉልን። አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ሰኞ በደጀ ሰላም ወጥቶ እንደነበረ ጠቁመዋል፤ እኔ እንዴት አድርጎ እንዳመለጠኝ እንጂ ያገኝሗትን በቅድሚያ ኮፒ ሳላደርግ አላነብ ነበር። ወይጉድ! በዛን ቀን አንቀላፍቼ ነበረ ማለት ነዋ!
  አደራ/3/ ፖስት አድርጉልን የዳንኤልም ሆነ የማህበሩ ሚስጢር አውቀን ተገቢውን ዝግጅት እንድናደርግ ይጠቅመናል

  ReplyDelete
 14. Dear Zewde, በዚህ ጽሑፍ «ለዳንኤል ክብረት» መጨረሻ ላይ ያለውን ሊንክ በመጫን የዳንኤልን የይቅርታ መልእክት ማንበብ ይችላሉ።

  አባሰላማ

  ReplyDelete
 15. አባ ሰላማ ብሎግ አመሰግናለሁ
  በዕንቁ መጽሔት የወጣው አንብቤዋለሁ፤ ነገሩ ብርሌ ከነቃ አይሆንም ዕቃ ነው።
  በኢትዮጵያ ሀገራችን ለመጀመርያ ጊዜ በታሪክ መዝገብ፣ መጀመርያ ጽፎ ለህዝብ ሲያስተዋውቅና በህዝቡ ሲተች ደግሞ ‘አሁንም ስለጻፍኩት ነገር ሁሉ ትክክል ነኝ” ብሎ ሁለት ጊዜ በአደባባይ መስክሮ ሲያበቃ በ3ኛ ጊዜ መቶ በመቶ ተጠያቂ ነኝ ብሎ የተናገረ ሰው ዳንኤል ክብረት ብቻ መሆኑን ተረድተናል።
  በእርግጥ የማሕበሩ ስራ እንደዛ ስለሆነ ብዙ አያስገርመንም። ለማነኛውም ቅዳሜና እሁድ ስለ ዳንኤል ክብረት ቅሌት/ክህደትና ስለ ማህበሩ ሀገርና ቤተ ክርስቲያን አውዳሚ የሆነ ስራ ለመዘገብ ፕሮግራም ይዣለሁ።

  ReplyDelete
 16. ተሃድሶዎች ምን ይውጣችሁ እንግዲህ

  ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ‘’የዓለም የሰላም አምባሳደር’’ የሚል ማዕረግ ተሰጠውwww.gebrher.com

  (ምንጭ፡-አዲስ ዘመን ነሐሴ 12 ቀን 2003ዓ.ም. 70ኛ ዓመት ቁጥር 342)

  ቪዥን ኢትዮጵያ ፎረ ዲሞክራሲ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት መልካም ዜጋን በመቅረጽ እና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል ያላቸውን አራት ግለሰቦች ሊቀ ዲሞክራት እና ስድስት ግለሰቦችን ‘’የዓለም የሰላም አምባሳደር’’ የሚል ማዕረግ ሰጥቷል፣ በዚህም የነገረ ቤተክርስቲያን ተመራማሪ እና ደራሲ የሆነው ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ‘’የዓለም የሰላም አምባሳደር’’ የሚል ማዕረግ ሰጥቶቷል፡፡ ስነስርዐቱ ላይ በመገኘት ማዕረጉን የሰጡት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ሲሆኑ የፌደራል ጉዳዮች ሚንስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ‘’የዓለም የሰላም አምባሳደር’’ የሚል ማዕረግ ካገኙት ግለሰቦች አንዱ ናቸው፡፡ ቪዥን ኢትዮጵያ ፎረ ዲሞክራሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ታደለ ደርሰህ በስነስርዐቱ ላይ እንደገለጹት የተመረጡት ግለሰቦች በግልና በመንግስታዊ ተቋማት የላቀ ሥራ የሰሩ ናቸው፡፡ የዜጎች መብት እንዲታወቅ ና እንዲከበር ከፍ ያሉ ተግባራት አከናውነዋል አርአያና ምሳሌ ሆነው የሚጠቀሱም ናቸው ድርጅታችን ወደፊትም እንዲህ ያሉ ግለሰቦችንና ኃላፊዎችን ለተግባራቸው ዕውቅና በመስጠት የመሸለም ሥራ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ ለአገልግሎት ባሕር ማዶ የሚገኘው ዲ/ን ዳንኤል ክብረትም በባለቤቱ አማካኝነት የማዕረግ ስጦታውን ተቀብሏል፡፡

  ReplyDelete
 17. I want expalnations about the following Questions

  1. To whom did Daniel ask forgivness
  2. Who gave him the forgivness
  3. Can we concider the Issue as the issue the concern much of us I think it is an issue of few freinds

  ReplyDelete
 18. የተወደዳችሁ አባ ሰላማዎች
  በዳንኤል ክብረት የይቅርታ ጽሁፍ ላይ የሰጣችሁት አስተያየት ደስ ብሎኛል። ትክክለኛ ግምጋሜ ነው ብየ አምናለሁ። ልክ እናንተ የቀድሞው ሐሳቡንና አሁን ያቀረበውን አወዳድራችሁ እንዳያችሁት እኔም በግሌ ቃል በቃል አንብቤ የራሴን አስተያየት መስጠት ፈልጌ ሳለ ሙሉ ጽሁፉን የት ላግኘው? ደጀ ሰላም እንደ ልማዱ አንድ ጊዜ ብልጭ አድርጎ አጠፋው። እባካችሁ ለተወሰኑ ጊዜያት ለጥፉልንና የዋሸውንና ያመነውን በደንብ እናመሳክረው።
  አመሰግናለሁ

  ReplyDelete
 19. እኔ በግሌ አባ ሠረቀ ተሃድሶ ይሁኑ አይሁኑ ለማወቅ ቢሮአቸው ተገኝቼ ፈትኛቸዋለሁ፣ እንኳን ተሃድሶ ሊሆኑ የተሃድሶን ጽንሰ ሐሳብም በሚገባ አይረዱትም።ሀሰት አባ ሠረቀ ተሃድሶ ናቸዉ

  ReplyDelete
 20. DENDANA LEBONA......

  ReplyDelete
 21. aba selama yikerta malet bediacon DK adelem yetegemerew yelekes beadam geze new.Enanet lemen yehen kemetaragebu endeMKidusan teru neger ateserum Lemesale sente gedam serachehu,sente yeabenet temehert bet atenakerachehu,sente yewengel masfafiya guzo aderegacheu.MELSUN LERASACHEHU KALACHEHU MALETE NEW.DK eyhen bemetsafu maheberu endeteneker yadergewal enge ayadakemewem.Bedaniel lay adro yemenager geta sente nebse yekeyeral,yehen maseb alebachehu.Aba Selama and teyake leteyekachhu why do U prefer this name rather than using like abune teklhaymanot.maheber kidusanin maheber seytan kemaletachehu befit yerasachehun aterar mawek alebachehu.

  ReplyDelete
 22. እረ ለመሆኑ "አባ ሰላማ" ብሎ ተሃድሶ አለ እንዴ? አባ ፍሬምናጦስ ወይም በኃላ አባ ሰላማ እኮ በእውነት ለኢትዮጵያውያን የወንጌልን ብርሃን ያበሩልን አባት ናቸው፣ የወንጌል ገበሬ የተባሉት አባ ሰላማ ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ ከኤርትራ እስከ ሲዳሞ፣ ከሐረር እስከ አርባ ምንጭ በአስራ አራቱም ጠቅላይ ግዛት የሰበኩ ለእኛ ብርሃንን ያሳዩ አባት ናቸው።
  ታዲያ እናንተ ትንሽ ከዚህ እውነታ የወጣችሁ አይመስላችሁም? ምናልባት ስማቸው እንደሚያሳየው የሰላም አባት ከሆኑ አባት ሥም ወስዳችሁ የሰላም ጠላት ከሆናችሁ እኮ፣ በሥራም መምግባርም ከማትመስሏቸው አባት ጋር ማበራችሁ፣ በጥላቸው ሆነን ሥር እንንቀል እንደማለት ያስመስላል ብዪ ስላሰብኩ ነው።

  አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕም ቢሆኑ እናንተ ከተነሳችሁበት ሃሳብ ጋር የሚመስል ሥራ የላቸውም፣ ምግባራቸው፣ ገድላቸው፣ በአጠቃላይ ሕይወታቸው እናንተ ከምትሉት ጋር ምንም የሚመስል ነገር የለባችሁም፣ ታዲያ በስም አመሳስሎ . . . ለማለት ካልሆነ በስተቀር እናንተን መቼም ለማወቅ ፓስት ያረጋችሁትን መመልከት ብቻ በቂ ነው ምናልባት ደማችሁን ማስመርመር ሳይኖርብን ምንፍቅናችሁን ለማወቅ ጊዜ የሚወስድበት የተዋሕዶ ልጅ ያለ አይመስለኝም።

  እኔ የማንም ማኅበር አባል አይደለሁም፣ አባልነቴ የእግዚአብሔር ብቻ ነው ነገር ግን አንዳንዴ ስጎበኛችሁ የማገኘው ነገር ምንም አያስደስትም፣ ታዲያ በዚህ አካሄዳችሁ ማን ይሆን የሚጠቀም? የኢትዮጵያ ሕዝብ ማኅበረ ቅዱሳን ማን እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል፣ ሥራቸውንም፣ ምግባራቸውንም፣ ለቤተክርስትያን ያላቸውን አቋም አበጥሮ ያውቃል።
  እናንተስ? ማናችሁ? ግብራችሁ ምንድነው? አላማችሁስ? የመጨረሻ ግባችሁስ? ለቤተክርስትያን ምን ራዕይ አላችሁ? እንደ እኔ ያለውን እንዴት ንሰሃ ገብተን እግዚአብሔር ማገልገልን እንዴት ነው የምታሥተምሩን? ለምንስ ስም የላችሁም? ተቀማጭነታችሁስ? እውነት የምታወሩ ከሆነ ማንነታችሁን ግለጹ ለምን መደበቅ አስፈለጋችሁ።

  በመጨረሻ በአሁን ሰዓት እውነት የምመሰክር በጠፋበት ጊዜ እውነትን ለመመስከር እንጣር፣ ከንቱ ጥላቻን እናስወግድ፣ የማይሆን ነገር ስለ ማኅበርም ሆነ ግለሰብ ከማውራት እኛ በምን ሰውን ከከንቱ ሃሳብ እንመልስ አርአያ እንሁን፣ መንገዶችን እንጠቁም፣ አገራችንን የተለያዩ ሃይማኖቶች የጦርነት አውድማ ከመሆን ለማዳን እንሥራ፣ እንደ ሰሜን አየርላንድ መሆን የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም እምነታችን የራሣችን ሃገራችን የጋራችን ስለሆነች በእምነት አንድ ከሆን የንሰሃ መንገድን እንጥረግ፣ ካልሆንም ደግሞ ስለ ትልቋ ሃገራችን እንመካከር፣ ድህነትን፣ ረሃብን፣ ድንቁርናን፣ ኃላቀር ባህልን፣ ለማጥፋት እጅ ለእጅ ተያይዘን አብረን እንጓዝ።
  ሃገራችንን ከጥፋት፣ ሕዝባችንን ከረሃብና ስደት ይጠብቅልን
  ሰላም ለኢትዮጵያ ይሁን

  ReplyDelete
 23. ለካ "ተሐድሶ" እስከዚህ ድረስ ለመናገር ችላችኋል? እስካሁን ድረስ ሳታውቁ በየዋህነት የምትንቀሳቀሱ ይመስለኝ ነበር፡፡ አሁን ጉዳችሁ ሁሉ በምስል በተደገፈ መረጃ ለህዝብ ሲደርስ አፍ አወጣችሁ፡፡ እስከዛሬ በማር የተለወሰ መርዛችሁን ስትግቱን የቆያችሁት ይበቃናል፤ አሁን ግን ማንነታችሁን እንኳንስ ፊደል የቆጠረው አይደለም የገጠሩ ህዝብም ተረድቷል፡፡ እንዲሁ በከንቱ ትደክምላችሁ እንጂ ይህችን ተዋህዶ ልታጠፏት ግን አትችሉም፡፡ ይልቁንስ "ከእግዚአብሔር ካልሆኑ ራሳቸው ይጠፋሉ፤ ከእግዚአብሔር ከሆኑ ደግሞ ልታጠፏቸው አትችሉም" ብሎ አይሁድን የመከራቸውን የገማልያልን ምክር አስቡና ተመለሱ፡፡
  ክፍለ ማርቆስ፣ ከደብረ ማርቆስ

  ReplyDelete
  Replies
  1. it is amusing thing "selling the word of god in birr."

   Delete
 24. የመናፍቅ ሳይት መሆኑ ከላይ ባለው ጽሁፍ ማረጋገጥ ይቻላል ንግግሩ ይገልጠዋልና

  ReplyDelete
 25. AY ANCHI BETE KIRISTIAN MAN YIHON ALEHU YEMILISH? TEMELKECHI LIJOCHISHN MIN ENDEMISERU!!BICHA BEZIH ZEMEN MEFETERAE ASAZINOGNAL!!

  ReplyDelete