Thursday, August 25, 2011

ተረፈ ኤርምያስ ትርፍ ነገር ይናገራል . . . Read PDF

«ተረፍ» ከዋናው ያልተቆጠረ፤ የቀረ፤ የተረፈ፤ ሳይጨመር የተተወ፤ ትራፊ፤ ቀሪ የሚል ጽንሰ ሃሳብ የያዘ ቃል ትርጓሜ ነው። እንደዚሁ ሁሉ «ተረፈ ኤርምያስ» በሚል ርእስ ከአዋልድ (ዲቃላ) መጽሐፍ ዝርዝር የተቆጠረው መጽሐፍ ከነቢዩ ኤርምያስ ዋናው የትንቢት መጽሐፍ ተጎርዶ የቀረ፤ ያልተጨመረ፤ የተተወ ስለሆነ፤ ምንም እንኳን በአይሁዳውያን ዘንድ በቋንቋቸውና በነቢያቶቻቸው የተጻፈ ስላይደለና ስለማያውቁት እንደብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ባይቆጥሩትም የካቶሊክና የኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት እንደብሉይ ኪዳን ትርፍ የኤርምያስ መጽሐፍ ቆጥረው ይቀበሉታል።  

ሙሉውን ለማንበብ የጽሑፉ ርዕስ ላይ ይጫኑ

4 comments:

 1. Is the bible said I'm only 66?

  ReplyDelete
 2. Mattew 2:23 And he came and dwelt in a city called Nazareth: that it might be fulfilled which was spoken by the prophets, He shall be called a Nazarene.

  Wondimeye - chemirewut ne'w endemitil baliteraterim yih tinbit keyet yigegnal...yalebeleziya Matios washitual libal new'n...wongelinim yelem litilen ne'w endet ne'w negeru? esti tenager

  ReplyDelete
 3. ከላይ የቀረቡትን ሁለት አስተያየት አይቻለሁ። ተረፍ የተባለውን መጽሐፍ ከነብዩ ዋናው የትንቢት መፅሀፍ ጋር ያለውን በነጥብ በነጥብ ያቀረብኩትን ያለመስማማት ጦርነት ቢሻቸው ከገድል ወይም ከተአምር አምጥተው መርታትና ማስተማር ሲያቅታቸው እኔ ያላነሳሁትን ሃሳብ በማንጠልጠል ለመከላከል ወደ ጉድጓድ ቁፋሮ ለመሄድ መሞከራቸው በጭፍን ከማመን ባሻገር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጭብጥን የማያውቁ ሰዎች መሆናቸውን ያሳያል። ተረፈ ኤርምያስ 81 ከሚባሉት ሊቆጠር የሚያስችል አሳማኝነት የለውም ላልኩት ሃሳብ- የለም!ከ81ዱ የሚቆጠርበት አስረጂ ይሄ ይሄ ነው ማለት ሲያቅታቸው 66 ነው ብዬ ያላቀረብኩትን ሃሳብ በማንሳት ጥያቄ ወደማቅረብ ይሮጣሉ። ስለ81 አለመሆን ያመነ ና ስለ66 መሆን ምክንያት ለመማር የፈለገ ወይስ 81 ስለመሆን ማሳመን ስላልቻለ የመሸሺያ ጥያቄ ለማቅረብ የተሰጠ አስተያየት? አንባቢ ይፍረደው?
  ሌላኛው ደግሞ ማቴዎስ 2፤23 ላይ ስለኢየሱስ ናዝራዊነት የተነገረውን የነብያት ትንቢት ፍጻሜ በመጥቀስ እኔ ለሰጠሁት የተረፈ ኤርምያስ መከላከያ አቅርቧል። የሚገርመው ግን ስለኢየሱስ ናዝራዊነትና ናዝሬት ስለመኖሩ የተሰጠ ትንቢት በየትኛው ተረፈ ኤርምያስ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ማስቀመጥ አልቻለም። እስኪ ምዕራፍና ቁጥሩን ንገረን!! ስለነብያት ትንቢት መናገር የካደ ያለ ይመስል በጥቅሉ የኢየሱስን ናዝራዊነት ትንቢት ነቢያት ተናገረዋል ማለት ምን ማለት ነው? ስለኢሱስ ናዝራዊ የሚል ትንቢት በተረፈ ኤርምያስ ላይ ካለ ያንን በማቅረብ ተረፈ ኤርምያስ የትንቢት መጽሐፍ ለመባል ያበቃዋል ብለህ መከራከር ወይም በአዲስ ኪዳን ውስጥ ባሉት መጻህፍት በአንዱ ውስጥ እንኳን የተጠቀሰ ካለ ያንን መጥቀስ በግምት ከምትቀበለው እምነት ሊያወጣህ ይችላል። ግን አልቻልክም፤ አትችልምም። ተረፉን መጽሐፍ ለመከላከል ከፈለግህ ስለኤርምያስ ነብይ የተነገሩ እውነታዎች ከትንቢቱ መጽሐፍ ጋር ይህ ለማዳን የምትታገሉለት ተረፍ ላይስማማ የተጻፈ ነጥቦችን መያዙ ነው ትልቁ ጉዳይ። የጽሁፉን ጥቅሶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር አገናዝበህ እውነቱን ተናገር፤ እኔም በአስረጂ ልቀበልህ!! በጥቅሉ ግን ብዙዎች ኦርቶዶክሳውያን ነን የምንል ሰዎች ከሰማነው ውጭ ለመስማት ያለመፈለግ፤ ለሚቀርቡ ሎጂኮች በአስረጂ መልስ ለመመለስ ከመሞከር ይልቅ ስድብ፤ ሽሙጥ፤ ዋናውን ጉዳይ ትቶ በእንቶ ፈንቶ መከራከር፤ አስተምሮ ከመለወጥ ይልቅ ጥርግ በሉ ዓይነት ክርስቲያናዊ ያልሆነ መደዴ ቃል መናገር ይታያል። ለምን ይሆን? ወግና ልማድ ከሃይማኖት ጋር በመቀላቀሉ ነው።

  ReplyDelete
 4. Wegenoche,

  Please let's focus on value-adding issues instead of attacking our church for being comprehensive and for preserving holy books. Some people were attacking our church for including Metsehafe Henok among the holy books, but it has now been proved that that book is truly a holy one. Also, only Ethiopia (EOTC) has the true complete copy.... We owe lots of gratitude to our fathers.

  It is sad that the current generation admires and believes anything foreign and from the west while despising anything of our own. This is a serious moral crisis... Even if the west is superior to us in science and technology, they are not a match for us in spirituality. We just need to learn the core of our faith and the true teaching as documented in the bible, the andimita, the haimanote abew, and the other good books written by the holy fathers.

  As the saying goes... "A nail becomes stronger as it gets hit on its head..." Our church will become stronger as we get hit from different angles. That is what happened to the apostles, the martyrs and the saints.

  However, the author deserves an answer if he is genuinely attempting to learn. We know some present their opposition and disguise themselves as open minded while carrying their poison at the bottom of their heart. Anyway, please let's not attack for the sake of attacking. My only issue with the EOTC is that it needs to teach the pure Gospel well to all and all the time, instead of telling some useless stories all day long and making the church a place of quarrel. That is somehow coming and we need to support those who are doing this. We only need to fight those who are standing on the way of the bible.

  ReplyDelete