Thursday, September 29, 2011

አለቃ ነቅዐ ጥበብ

ይህ ጽሑፍ የተወሰደው ከጮራ መንፈሳዊ መጽሔት ቁጥር 40 ከአለቃ ነቅዐ ጥበብ ዐምድ ላይ ነው፡፡
ከደመራ መልስ የሁለት መሪጌቶች ውይይት

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ታሪካቸው የተመዘገበው ኒቆዲሞስና ዮሴፍ ዘአርማትያስ (ዮሐ. 3፥2፤ 19፥38) ያደርጉት እንደ ነበረው፥ መሪጌታ ብርሃነ መስቀልም ጨለምለም ሲል ራሳቸውን ለወጥ አድርገው ወደ አለቃ ነቅዐ ጥበብ እየሄዱ ከሚማሩ ስውር ደቀ መዛሙርት መካከል አንዱ ነው፡፡ በሚያገለግልበት ደብር ውስጥ እርሱ ከሚኖርበት የመቃብር ቤት ጥቂት ዕልፍ ብሎ በሚገኘው በሌላው መቃበር ቤት ውስጥ ለሚኖረው ባልንጀራው ለመሪጌታ በትረ ጽዮን ግን ወዴት እንደሚሄድ አይነግረውም ነበር፡፡ ምክንያቱም ካሁን ቀደም በወንጌል ስለ ተገለጠው የእግዚአብሔር ጽድቅ ሊያስረዳው ቢሞክር፥ ፍጹም ተቃዋሚና እርሱንም አሳልፎ ሊሰጠው የሚችል ዐይነት ሰው ሆኖ ስለ ተመለከው፥ በሌላው ጒዳይ ካልሆነ በቀር ለጊዜው በዚህ ነገር ዳግም ላያነጋግረው ወስኖ ነበር፡፡

Monday, September 26, 2011

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ምን ምን ነገረን? ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኗል) ካለፈው የቀጠለ

5. ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር እየሆነ ነው
በዲያቆን ዳንኤል እይታ ማኅበሩ “በአመራር እጦት ምክንያት፣ ለቤተ ክህነቱ ችግር መፍትሔ ያመጣል ሲባል እርሱ ራሱ የቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር እየሆነ ነው፡፡” በመሠረቱ እንዲህ ዐይነት ራእይ የሰነቀው ራሱ ማኅበሩ ነው እንጂ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ችግሬን ይፈታልኛል ብላ እንዳላቋቋመችው ይታወቃል፡፡ ሌሎች እያሉ ያለው ደግሞ ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያኒቱ መፍትሔ ያመጣል ሳይሆን፣ ከተቋቋመበት ዐላማ ውጪ በሚያደርገው ኢመንፈሳዊ አካሄድና ያራምደዋል በሚባለው ድብቅ ፖለቲካዊ አጀንዳ ቤተ ክርስቲያንን ትልቅ ችግር ላይ ጥሏል ነው፡፡ አቦይ ስብሐት በቅርቡ “ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክህነት ዕዳ ነው” ማለታቸውን ከፍትሕ ጋዜጣ አንብበናል (ፍትሕ፣ ሐምሌ 15/3003 ገጽ 6)፡፡

Thursday, September 22, 2011

የፈጣሪ ምስጋና ይገባቸዋል

 

"ለእሉ ክሌቱ ፍጡራን ስብሐተ ፈጣሪ ይደልዎሙ እስመ ተአረዩ በክብሮሙ"

ትርጉም "ለነዚህ ለሁለቱ ፍጡራን ለማርያምና ለመስቀል የፈጣሪ ምስጋና [አምልኮ] ይገባቸዋል። በክብር ከፈጣሪ ጋር እኩል ሆነዋልና" [መስተብቍዕ ዘመስቀል]
 አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ደቂቀ እስጢፋኖስን ከገደለና እውነተኛ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምመናን እና መምህራን እመነታቸውን በሰማዕትነት ከፈጸሙ በኋላ። የግል ደብተራዎቹን በማሰባሰብ መስተብቁዕ ዘመስቀል የሚባል ድርሰት ደርሷል። ይህ ድርሰት "ወካዕበ ናስተበቁዖ ለእጸ ቅዱስ መስቀል‚  ትርጉም "ዳግመኛ ቅዱስ የሆነ የእንጨት መስቀልን እንማልደዋለን‚ ብሎ ይጀምራል። ድርሰቱ የመንፈስ ብክለት የደረሰበት ሰው የደረሰው ለመሆኑ ገና ካጀማመሩ ያስታውቃል። መስቀልን እንማልደዋለን ሲል የሚሰማ ሰው አድርጎታል። መስቀል ግኡዝ ፍጥረት ነው፤ ጸሎትና ምልጃን ሊሰማ የሚችል አምላክ አይደለም። ምን አልባት ደራሲው በሰከረበት ቀን ደርሶት

Monday, September 19, 2011

ጠባቡ የማህበረ ቅዱሳን አስተሳሰቦች by Berhane Tsegaye on Monday, September 5, 2011 at 4:01am

ካሁን በፊት ስለማኅበረ ቅዱሳን ከውጪ ሰዎች እንጂ ከማኅበሩ ሰዎች ብዙም ሲነገር አልሰማንም፡፡ ቢነገርም የማኅበሩ ሚዲያዎች የማኅበሩን ጽድቅ እንጂ ኀጢአት ሲያወሩ አላየንም፡፡ እንደችግር የሚነሡ ቢኖሩም እንኳ መከራ ደረሰብን ከሚል ያለፈ ትክክለኛ ድካምን የሚገልጽ አስተያየት እንኳ ማንበብ ሳይቻል ቆይቷል፡፡ አሁን ግን ማኅበሩ ወደ ውድቀቱ እየተፋጠነ መሆኑን የሚያሳዩ አንዳን ድ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው፡፡ በአስተያየቶቹ ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን የት ላይ እንዳለ መገመት ይቻላል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የቀረበው የብርሃን ጸጋዬ ጽሑፍ ደጀሰላም ፌስቡክ ላይ የወጣ ነው፤ ያንብቡት::

Friday, September 16, 2011

ዋናና ወቅታዊው ጉዳይ


¨c’< ›g“ò
(Ÿ›^Ç ¡/Ÿ}T)
በተለያዩ ጊዜያት አገርን አንዳንዴም ቤተ ክርስቲያንን የሚመለከትና መፍትሔ የሚሻ  አንገብጋቢ ወይም ወቅታዊ ጉዳይ ይነሳል፡፡ በወቅቱ ለሚነሳ ጉዳይ በቅድሚያ ትክክለኛ ግንዛቤ ማግኘት የመፍትሔ ዋና አካል ነው፡፡ የሚቀጥለው በተገኘው ግንዛቤ መሠረት ትክክለኛውን መፍትሔ መስጠት ነው፡፡
የአንድን በሽተኛ ሕመም ሳያውቅ ሐኪም መድኃኒት አያዝም፤ በሽታውን ከሕመሙ ሊፈውስ የሚችለው ሕመሙን ከተረዳ በኋላ ሐኪሙ የሚያዘው መድኃኒት ነው፡፡ በግምት መፍትሔ ይሆናሉ ብሎ አንድ በሽተኛ የሚወስዳቸው መድኃኒቶች ግን በሽተኛውን የባሰ የጤንነት ችግር ውስጥ ከመክተት በቀር ሌላ ፋይዳ የላቸውም፡፡

Monday, September 12, 2011

የ2004 ዓ. ም. አጽዋማትና በዓላት


የ2004 ዓ. ም. አጽዋማትና በዓላት


መስከረም 1 ቀን 2004[September, 12 2012]

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መስከረም 1 ቀን የዘመን ነገር የአጽዋማትና በዓላት አወጣጥ ከቅዳሴ በኋላ የሚታወጅበት ነው፡፡ የባሕረ ሐሳቡ ሊቅ ሥነ ፍጥረቱንና የአጽዋማትና በዓላቱን አወጣጥ ሲተርኩ መስማት እጅግ ደስ ያሰኛል፡፡ በዓላትና አጽዋማት ሲወጡም አሥርቆት ይደረጋል፡፡ አሥርቆት ማለት የሌሊትና የመዓልት መባቻ የሚታወቅበት መንገድ ነው፡፡
የአጽዋማትና የበዓላቱን አወጣጥ በዝርዝር እንመልከት፡፡

በንጉሥ አዋጅ የገቡ ባዕድ አምልኮዎች

በንጉሥ አዋጅ የገቡ ባዕድ አምልኮዎች
ለማርያም ስእልና ለመስቀለኛ እንጨት ያልሰገደ ይገደል[የዘራ ያዕቆብ ሸንጎ ዘደብረ ብርሃን]
የሃይማኖታችን መሠረት የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ ደጋግሞ የሚያስጠነቅቀን ሌሎች አማልክትን እናዳናመልክ ነው። ባዕድ የሚለው ቃል ሌላ፤ ወይም የተለየ የሚል ትርጉም አለው። ሐሳቡ ከእግዚአብሔር ሌላ መመለክ የሚገባው ወይም ሊመለክ የሚችል ምንም ነገር ስሌለ ባዕድ ከተባለ ከእግዚአብሔር ውጭ ከእግዚአብሔር ሌላ ማለት ነው። በዚህ ቃል ውስጥ ማንኛውም ፍጥረት ሰውም ሆነ መላክ እንሥሳም ይጠቃለላል። በእግዚአብሔር የተፈጠረ ሁሉ ምንም ዓይነት ኃይል ይኑረው ያው ፍጡር ነውና ሊመለክ አይችልም።
አማላክት ዓይነታቸው ብዙ ነው፤ ዘርዝረን ልንወስናቸው አንችልም መጽሐፍ ቅዱስ እገሌና እገሌ ሳይል የተቀረጸ ምስልን እና የማንኛውንም ስእል ሁሉንም ጠቅለል አድርጎ እንዲህ ሲል ያስጠነቅቃል።

Sunday, September 11, 2011

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ምን ምን ነገረን?

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ምን ምን ነገረን?
(ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኗል)

ሦስተኛው የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን በሕዝቡ ላይ የአገዛዝ ቀንበር አክብዶ ነበር፡፡ በዘመነ መንግሥቱ መጨረሻ ላይ ከእግዚአብሔር መንገድ በመውጣቱ፣ እግዚአብሔር ከሰሎሞን ሞት በኋላ መንግሥቱን ከሁለት ከፍሎ ዐሥሩን ነገድ ለኢዮርብዓም፣ ሁለቱን ነገድ ደግሞ ለልጁ ለሮብዓም ሰጠ፡፡ በዚህ ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ወደ ሮብዓም ቀርቦ፣ አባትህ ያከበደብንን ቀንበር ካቀለልህልን እንገዛልሃለን ቢለው፣ የሽማግሎችን ጠቃሚ ምክር አቃሎ ተመለከተ፡፡ በባልንጀሮቹ ጎጂ ምክር ተነዳ፤ የአገዛዝ ቀንበሩንም ከአባቱ የበለጠ እንደሚያጠነክረው ነገራቸው፡፡ እነርሱም ከዳዊት መንግሥት ወጥተው በኢዮርብዓም አገዛዝ ሥር ገቡ፡፡ አንድ የነበረው የእስራኤል መንግሥት ከሁለት ተከፈለ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ይህ የሆነበትን ምክንያት ሲያስረዳ፥ “እግዚአብሔርም በሴሎናዊው በአኪያ አድርጎ ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረውን ነገር እንዲያጸና ከእግዚአብሔር ዘንድ ተመድቦ ነበርና ንጉሡ ሕዝቡን አልሰማም” ይላል (1ኛ ነገሥት ምዕራፍ 12 ቁጥር 15)፡፡

Wednesday, September 7, 2011

የዳንኤ ክብረት ባዕድ ወንጌል --- Read PDF

"የሚያናውጧችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳዳዶች አሉ እንጂ። ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መላክ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን"። ገላ 1፥8።
ማህበረ ቅዱሳን የተባለው ድርጅት ወንጌልን በማጣመም ለወጣቶች አያስተማረ ስንት ዜጎችን እንዳጣመመ እግዚአብሔር ይወቀው፤ ከአጋንንት መንፈስ የሚመጣውን ባዕድ ነገር ያለምንም ፈሪሃ እግዚአብሔር በሕዝብ ላይ በመዝራት የፈጸመው ወንጀል በምድር ባይሆይንም በሰማይ ግን ፍርዱን ያገኛል።
የክርስቶስን ወንጌል በማጣመም የታወቀው ዳንኤል ክብረት የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ራሱ አመለካከት እየተረጎመ ሲያስተምር ምንም ስቅጥጥ አይለውም። ባንድ የስብከት ፕሮግራሙ ላይ “ያዕቆብ በሕልሙ ያየው በመሰላል  አማሳል ያያት እመቤታችን ናት” ይላል።  መጽሐፍ ቅዱስ ግን ከጥንት ደብተራዎችም ሆነ ከዘመኑ ደብተራ ከዳንኤል ክብረት ጋር ፈጽሞ አይስማማም።

Monday, September 5, 2011

“አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ ለእናንተ አድርጉ” /ሕዝ 18፥31/ - - - Read PDF

በማሞ አየነው
የሰው ልጅ ለሥጋዊና መንፈሳዊ እንቅስቃሴው አመች በሆነ መልኩ እግዚአብሔር ለሚያፈራርቃቸው ዘመናት ቀመር ሲያወጣ ኖሯል፡፡ ጊዜያትንም ከደቂቃ ሽራፊ እስከ ሺህ ዘመናት ድረስ ከፋፍሎ ይጠቀማል፡፡ በዚህ የጊዜ ቀመርም ትናንትን ያስረጃል፤ ዛሬን ደግሞ አዲስ ያደርጋል፡፡ በጊዜ ዑደትም ብዙ ሺህ አዲስ ዓመታት አልፈው ብዙ ሺህ አዲስ ዓመታት መጥተዋል፡፡ የዘመናት መፈራረቅ ሰው የእግዚአብሔርን ሥራ እንዲያደንቅ፣ መግቦቱንም እንዳይረሳ ያደርጋል፡፡ እግዚአብሔር አምላክም ቃል ኪዳኑን እንዳልረሳ፣ ፍጥረቱን እንዳልዘነጋ ያመለክታል፡፡

የመጻተኞችና የጃንደረቦች መታሰቢያ - - - Read PDF

"ወደ እግዚአብሔርም የተጠጋ መጻተኛ። በእውነት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ይለየኛል አይበል፤ ጃንደረባም። እነሆ፥ እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ አይበል።  እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና።  በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።  ያገለግሉት ዘንድ የእግዚአብሔርንም ስም ይወድዱ ዘንድ ባሪያዎቹም ይሆኑ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የሚጠጉትንም መጻተኞች፥ እንዳያረክሱት ሰንበትን የሚጠብቁትን ቃል ኪዳኔንም የሚይዙትን ሁሉ፥  ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፥ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና የሚቃጠለውን መሥዋዕታቸውንና ሌላ መሥዋዕታቸውን በመሠዊያዬ ላይ እቀበላለሁ" ኢሳ 56፥3-7

Friday, September 2, 2011

በምርምርና ተመራማሪነት ስም እውነትን ማፈን - የዳንኤል ክብረት ፈሪሳዊ ስልት

በርእሱ ወደ ተጠቀሰው ጉዳይ ከመገባቱ በፊት ባለፉት አስተያየቶች ላይ ጥቂት ነገር ማከል አስፈልጓል፡፡ ባለፉት ሁለት እትሞች ላይ ለማሳየት እንደ ሞከረው፣ ትዝብትና ተመራማሪ ዳንኤል ክብረት ለመቀበል ባይፈልጉም፣ ጸሓፊው በማኅበረ ቅዱሳን የጥናት መጽሔት ባለቤትነት ላይ እንጂ በይዘቱ ላይ ምንም የሰጠው አስተያየት አለመኖሩ ግልጽ ነው፤ የጥናት መጽሔት መዘጋጀቱም መልካም መሆኑን ሳይጠቅስ አላለፈም፡፡ የጥናቱ ባለቤት ወይም ያስጠናው ማኅበረ ቅዱሳን እንጂ ቤተ ክርስቲያኒቱ አይደለችም፣ ስለዚህ ከነጋድራስ ጋዜጣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አለአግባብ የተሰጠው የጥናት መጽሔት ባለቤትነት ትክክል አይደለም ነው ክርክሩ፡፡