Friday, September 2, 2011

በምርምርና ተመራማሪነት ስም እውነትን ማፈን - የዳንኤል ክብረት ፈሪሳዊ ስልት

በርእሱ ወደ ተጠቀሰው ጉዳይ ከመገባቱ በፊት ባለፉት አስተያየቶች ላይ ጥቂት ነገር ማከል አስፈልጓል፡፡ ባለፉት ሁለት እትሞች ላይ ለማሳየት እንደ ሞከረው፣ ትዝብትና ተመራማሪ ዳንኤል ክብረት ለመቀበል ባይፈልጉም፣ ጸሓፊው በማኅበረ ቅዱሳን የጥናት መጽሔት ባለቤትነት ላይ እንጂ በይዘቱ ላይ ምንም የሰጠው አስተያየት አለመኖሩ ግልጽ ነው፤ የጥናት መጽሔት መዘጋጀቱም መልካም መሆኑን ሳይጠቅስ አላለፈም፡፡ የጥናቱ ባለቤት ወይም ያስጠናው ማኅበረ ቅዱሳን እንጂ ቤተ ክርስቲያኒቱ አይደለችም፣ ስለዚህ ከነጋድራስ ጋዜጣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አለአግባብ የተሰጠው የጥናት መጽሔት ባለቤትነት ትክክል አይደለም ነው ክርክሩ፡፡

ዳንኤልም “ጥናቱ የማኅበረ ቅዱሳን አይደለም፤ የቤተ ክርስቲያኒቱም አይደለም” በሚል በአንድ በኩል የመምህር በቃሉን ሐሳብ ደግፎ ጥናቱ የቤተ ክርስቲያኒቱ አለመሆኑን መስክሯል፤ እውነት ነው፡፡ በሌላ ወገን ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳን የእኔ ያለውን ጥናቱን የእርሱም አይደለም በማለት ለአጥኚዎቹ ባለሙያዎች ሰጥቶበታል፤ ምናልባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት በጥናት መጽሔቱ አማካሪ ቦርድ ውስጥ አባል ስለሆነ ባለቤቱን ያውቅ ይሆናል፤ ለሁሉም ይህን ማኅበረ ቅዱሳን ሊከራከርበት ይችላል፡፡

በዚህ መካከል ግን ርእሰ ነገሩ እንዲጫር ያደረገው ነጋድራስ ጋዜጣ በቅጽ 08 ቁጥር 249 አርብ ጥቅምት 5/2003 ዓ.ም. ዕትሙ በገጽ 3 ላይ “ቤተ ክርስቲያኗ የጥናት መጽሔቷን ይፋ አደረገች” ላለው ርእሰ ዜና እስካሁን ማስተካከያ ሊሰጥ አልደፈረም፡፡ ከዚህ ይልቅ አንባብያን እንዲነጋገሩበት የመረጠ ይመስላል፡፡ እንዲህ ማድረጉ በአንድ በኩል መልካም ቢሆንም፣ ስሕተቱን ይሸፍንለታል የሚል እምነት ግን የለኝም፡፡ ስለዚህ ተሳስቼ ነው ብሎ ማስተካከያ መስጠት፤ አሊያ አልተሳሳትኩም ብሎ ምክንያቱን ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ ለሦስተኛ ጊዜ አስተያየት መሰጠቱ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ውሃ የመውቀጥ ያህል ስለሚሆን፣ የተለየ መከራከሪያ ካልተነሣ በቀር በጉዳዩ ላይ ጸሓፊው የሚለው አይኖርም፡፡ የዚህ ጽሑፍ ትኩረት ነጋድራስ ጋዜጣ ከተመራማሪ ዳንኤል ክብረት ጋር ባደረገውና በሁለት ክፍል በቀረበው ቃለ ምልልስ ላይ የተመሠረተ ይሆናል፡፡

በቅድሚያ ዳንኤል ክብረት በተለያዩ የግል ጋዜጦችና መጽሔቶች ላይ በኢኮኖሚያዊ፣ በማኅበራዊ፣ በፖለቲካዊና በባህላዊ ጉዳዮች ላይ በተረቶችና በብሂሎች አዋዝቶ ለሚጽፋቸው መጣጥፎቹ ጸሓፊው ያለውን አድናቆት መግለጽ ይወዳል፡፡ በዚህ አቅጣጫ የተዋጣለት ጸሓፊ ነውና፡፡

ጸሓፊው፣ ዳንኤል ክብረትን ከሚሰጠው ከዚህ ስፍራ ላይ ወርዶ የሚያገኘው ግን አለቦታው ገብቶ በምርምር ስም ሌሎች ጉዳዮችን ከሃይማኖት ትምህርት ጋር በማደበላለቅ ክርስቲያናዊ እውነትን ለማፈንና ለማጣመም የሚያደርገውን ጥረት ሲያስተውል ነው፡፡ ስለ ጥናትና ምርምር ጥሩ ቲዎሪዎችን ይተውራል፡፡ በተመራማሪ ስም የሚያስተላልፋቸው አንዳንድ መልእክቶች ግን በትክክል በምርምር የተደረሰባቸው የጥናት ውጤቶቹ ሳይሆኑ፣ እርሱ ወይም ማኅበሩ ከሚፈልገው ድምዳሜ ላይ የደረሰባቸው፣ ወይም በእርሱ አነጋገር፣ “እዚህ ቦታ እንድትደርሱ አድርጋችሁ አጥኑልኝ ካለ እርሱ ጥናት አይደለም” ያለው ዐይነት ሃይማኖታውያን አቋሞቹ ናቸው፡፡ ስለዚህ እርሱ ሁለቱን ለይቶ ካልተመለከተና ካደበላለቀ ተመራማሪ የሚለው “ታይትል” ብዙም ይገልጸዋል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ከዚህ ሌላ ራሱ “አንድ ፕሮፌሰር ያጠናው እና አንድ የእኔ ቢጤ ያጠናው እኩል” አይደለም ያለው፣ እንደ ትሕትና የሚቆጠርለት ሳይሆን ከምር ሊወሰድ የሚገባው ኑዛዜው ነው ማለት ያስኬዳል፡፡ እስካሁን ለማስተዋል እንደሚቻለውም የእርሱ ጥናት በዚህ ደረጃ ነው ሊታይ የሚገባው፡፡

ዳንኤል በክፍል ሁለት ቃለ ምልልሱ ውስጥ ለጥናትና ምርምር ከሚያስፈልጉ ነገሮች አንዱ ገለልተኛነት መሆኑን ተናግሯል፡፡ ቀደም ብለው የቤተ ክርስቲያኒቱን ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ሥነ ጽሑፍና ባህል ያጠኑ አውሮፓውያን ሊቃውንት፣ ሃይማኖታቸው ሌላ ቢሆንም በአብዛኛው በመረጃዎች ላይ ተመሥርተው ታሪክን ከታሪክ አንጻር፣ ቋንቋን በቋንቋነቱ፣ ሥነ ጽሑፍንም በሥነ ጽሑፍነቱ በማጥናት ከድምዳሜ ላይ የደረሱ በመሆናቸውና ከሃይማኖቱ ጋር ባለ ማደበላለቃቸው የጥናቶቻቸው ገለልተኛነት ከጥያቄ ውስጥ አልገባም፡፡ እርግጥ ሃይማኖታዊ አስተምህሮውም ሆነ ሥርዐቱ ራሱን ችሎ ሊጠና ይችላል፡፡ ዳንኤል ክብረት ምርምርን ተተንተርሶ ሲናገርና ሲጽፍ ቤተ ክርስቲያኒቱ የያዘችውን ነገር በየፈርጁ አጥንቶ ከደረሰበት ድምዳሜ ይልቅ፣ በጥናት ያልተረጋገጠውንና በልማድ ሲሠራበት የቆየውን ነገር ደግሞ ይነግረናል፤ ወይም ትክክለኛውን የጥናት ውጤት በፈሪሳዊ ስልቱ ያድበሰብሰዋል፡፡

“ኦርቶዶክስ መልስ አላት” በሚለው መጽሐፉ ቤተ ክርስቲያኗ ስለምትቀበላቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ቁጥር ይህን ያህል ነው ብሎ አልገለጸም፡፡ እንደሚታወቀው ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትቀበላቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ቊጥር ሰማንያ አንድ ነው፡፡ ይህም በልማድ የተወሰደ ቊጥር መሆኑንና በየትኛውም ቀኖና ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ 81 የሚል አለመኖሩን ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ለምሳሌ፡- በመስኩ ሰፊ ጥናት ያደረጉት ዶ/ር ዲበ ኩሉ ዘውዴ “… 81 ቁጥር አንድ በአንድ ተዘርዝሮ የተላለፈበት መንገድ ያው እንደ ተለመደው በቃል - በትውፊት እንጂ በግልጥ በጽሑፍ ተቀምጦ የተላለፈ …” አለመሆኑን ለማስረዳት ሞክረዋል (81 ቅዱሳት መጻሕፍትና ምንጮች-ቀኖናት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ገጽ 13)፡፡ የታወቁት የቅዱሳት መጻሕፍት ቀኖናትም 6 መሆናቸውን በዝርዝርና በንጽጽር በሠንጠረዥ አሳይተዋል፡፡

ዳንኤል ግን ሌሎቹን ሁሉ ትቶ የጠቀሰው 85 ሐዋርያውያን ቀኖናትን ነው፡፡ በዚህ ቀኖና መጻሕፍት ውስጥ የብሉይ ኪዳን ተጨማሪ የተባሉት መጻሕፍት በዝርዝር ተገልጠዋል ብሏል፡፡ ነገር ግን በዚህ ቀኖና ውስጥ የተካተቱት መጻሕፍት ቁጥር 41 ብሉያትና 36 ሐዲሳት በድምሩ 77 መጻሕፍት ናቸው እንጂ 81 አይደሉም፡፡ በእነዚህ መካከል ደግሞ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ ውጪ ዳንኤል በራሱ የኦሪት አካል ነው ብሎ የመደበው መጽሐፈ ሄኖክ የለም፡፡ እንዲያውም መጽሐፈ ሄኖክ “በሰብአ ሊቃናት ብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ ከአለመኖሩም የተነሣ ከ6ቱ ቀኖናተ መጻሕፍት በአንዱም አልተወሳም፡፡ ከዚያም በእነዚህ ቀኖናተ ቅዱሳት መጻሕፍት ግእዝ ትርጉሞች አልተመለከተም” (ዝኒ ከማሁ ገጽ 199)፡፡ ዳንኤል እንደ አጥኚ ሁሉንም ምንጮች መርምሮ ወደ ተሻለ ድምዳሜ መድረስ ሲችል፣ እርሱ ግን በልማድ የተያዘው አቋም የጥናት ውጤት እንዲመስል ጥረት ያደርጋል፡፡

ዳንኤል ክብረት በተመራማሪነቱ መጽሐፈ ሄኖክ የኦሪት መጻሕፍት ክፍል ነው ብሏል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ባሳተመው የዓባይነህ ካሤ መጽሐፍ ደግሞ፥ “ሄኖክ የጻፈው (መጽሐፈ ሄኖክ) ከመጻሕፍት ሁሉ ቀዳሚው መጽሐፍ ነው” ይላል (የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ገጽ 43)፡፡ በሌላ አነጋገር መጽሐፈ ሄኖክ ከኦሪት ዘፍጥረት በፊት የተጻፈ መጽሐፍ ነው ማለት ነው፡፡ ይህ እንዲህ አፍን ሞልቶ ለመናገር በሚያበቃ ጥናት የተደረሰበት ድምዳሜ ነው ማለት ግን ያስቸግራል፡፡ የኦሪት ባለቤቶች የሆኑ አይሁድ መጽሐፈ ሄኖክን ‘የኦሪት ክፍል ነው፤ አይደለም’ በሚል ሊከራከሩበት ቀርቶ ከቅዱሳት መጻሕፍት ቁጥር እንኳ አላስገቡትም፡፡ መጽሐፉን ሄኖክ ይጻፈው ወይም በሄኖክ ስም ሌላ ሰው ይጻፈው አልታወቀም፡፡ መቼ እንደ ተጻፈም ሊጠና ይገባል፡፡ በሄኖክ ስም ስለ ቀረበ ብቻ መጽሐፉን ከሄኖክ ጋር በቀጥታ አገናኝቶና ወደ ሄኖክ ዘመን ወስዶ የመጀመሪያው ቅዱስ መጽሐፍ አድርጎ መቁጠር አያስኬድም፡፡

በቁምራን ከተገኙት የሙት ባሕር ጥቅሎች አንዱ መሆኑ፣ ከእርሱ በቀር ማንም የማይመልሳቸው ጥያቄዎች መኖራቸው፣ ከዚህ የተነሣ በዓለም ላይ ያሉ የጥናት ማእከላት ሁሉ በሰፊው የሚፈልጉት መጽሐፍ መሆኑ፣ በይሁዳ መልእክት ውስጥ ከሄኖክ መጠቀሱ መጽሐፈ ሄኖክ ከቅዱሳት መጻሕፍት አንዱ ለመሆኑ ማስረጃዎች መሆናቸው በዳንኤል ቃለ ምልልስ ውስጥ ተጠቅሷል፡፡ እነዚህ ግን ሚዛን የሚደፉና ሌሎች መልስ የሚያሻቸውን ጥያቄዎች የማያስከትሉ ድምዳሜዎች ናቸው ማለት ይከብዳል፡፡ ዳንኤል እንዲህ ያለው ግን እንደ አጥኚ ነው ወይስ እንደ ሃይማኖተኛ? የሚለውን መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡

በቁምራን የተገኙት የመጻሕፍት ጥቅሎች ቅዱሳት በተባሉትም ሆነ በሌሎቹ መጻሕፍት ዙሪያ ለሚደረገው ጥናት እጅግ ጠቃሚ መሆናቸው አያጠያይቅም፡፡ በዓለም ላይ ያሉ የጥናት ማእከላት መጽሐፈ ሄኖክን መፈለጋቸውም ከጉዳያቸው ጋር ተያይዞ እንጂ ከሃይማኖት ወይም ለክርስትና ባለው ፋይዳ ላይሆን ይችላል፡፡ በእነርሱ መፈለጉም መጽሐፉ በቅርስነቱ ታላቅ ቦታ የሚሰጠው መጽሐፍ መሆኑን ያመለክታል፡፡ በአብዛኛው ከፀሓይና ከጨረቃ ዑደት ጋር የተያያዘ ነገር ስላለው ለዚያ ይሆናል የፈለጉት የሚል እምነት አለ፡፡ መጽሐፉ በዚህ መስክ ካለው ፋይዳ አንጻር ብቻ ሳይሆን፣ ከብሉያትና ከሐዲሳት ትምህርት አንጻርም መጠናት ያለበት ይመስለኛል፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት ተብለው በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ተቀባይነትን ካገኙ መጻሕፍት ቁጥር ውጪ ለምን ሆነ? የሚለውም እንዲሁ ተድበስብሶና ሌሎች አልተቀበሉትም ተብሎ ብቻ የሚተው ሳይሆን ጥናትና ምርምር የሚያሻው ጉዳይ ነው፡፡ በጥቅሉ ግን ከታወቁት ቅዱሳት መጻሕፍት ጋር መጽሐፈ ሄኖክ በቁምራን መገኘቱ ብቻውን የቅዱሳት መጻሕፍት አካል ሊያሰኘው የሚችልበት ምክንያት ግን አይኖርም፡፡

በዚህ ዓለም እስካለን ድረስ ከዕውቀት ከፍለን ነው የምናውቀው፡፡ የሰው ልጅ ጥናትና ምርምር የሚያደርገውም ጥያቄዎቹን ለመመለስ፣ ችግሮቹን ለመፍታት፣ ዕውቀቱን ለማስፋትና ለመሳሰሉት ዐላማዎች ነው፡፡ ይሁን እንጂ የሰው ልጅ በጥናትና ምርምር ካወቃቸው ነገሮች ይልቅ ያላወቃቸው ነገሮች እጅግ ይበዛሉ፡፡ መጽሐፈ ሄኖክ ብቻ መመለስ የቻላቸው ጥያቄዎች ካሉ ያ በራሱ መልካም ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ይህ መጽሐፈ ሄኖክን ከቅዱሳት መጻሕፍት ቁጥር ሊጨምረው የሚችል በቂ ምክንያት ነው ማለት ያስቸግራል፡፡

ዳንኤል በይሁዳ መልእክት ውስጥ ሄኖክ መጠቀሱ መጽሐፈ ሄኖክ የቅዱሳት መጻሕፍት አካል ተብሎ እንዲቆጠር የሚያደርገው ሌላው ማስረጃ ነው ብሏል፡፡ ይህም ቢሆን ሌላ ጥያቄን ማሳነሣቱ አይቀርም፡፡ እንደ መጽሐፈ ሄኖክ ሁሉ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የተጠቀሱ፣ ነገር ግን የቅዱሳት መጻሕፍት አካል ተደርገው የማይወሰዱ ምንጮች አሉ፡፡ ለምሳሌ፡- የግሪክ ባለቅኔዎች የተናገሩትን ሐዋርያው ጳውሎስ በስብከቱ ጠቅሶታል (የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 17 ቁጥር 27-28)፡፡ ለቲቶ በጻፈለት መልእክት ውስጥም ስለ ቀርጤስ ሰዎች የገዛ ራሳቸው ነቢይ የተናገረው ሁሉ እውነት መሆኑን አውስቷል (ቲቶ ምዕራፍ 1 ቁጥር 12-14)፡፡ ነገር ግን እነዚህ ነገሩን ለማስረገጥ መጠቀሳቸውን እንጂ የባለ ቅኔዎቹም ሆነ የቀርጤሳዊው ነቢይ ንግግሮች ቁጥራቸው ከቅዱሳት መጻሕፍት ነው ወደሚል ድምዳሜ አያደርሰንም፡፡ መጽሐፈ ሄኖክም ከዚህ አንጻር መታየት ይኖርበታል የሚል አመለካከት አለ፡፡

መቼም ክርስትና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ሃይማኖት መሆኑ ሁላችንንም ያስማማናል፡፡ የክርስትና አንድ ክፍል የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሠረትም መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑ አያከራክርም፡፡ ክርስትና መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ ቢሆንም በየተሰበከበት አካባቢ ባህል ውስጥ ተስፋፋ እንጂ፣ ለክርስትና ተብሎ የተለየና ከእግዚአብሔር የተሰጠ አንድ ባህል የለም፡፡ የትኛውም ባህል ከመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ጋር ተቃርኖ እስካልተገኘ ድረስ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባይሆንም እንኳ ቅቡልነት ይኖረዋል፤ - ለሚያመዛዝን ክርስቲያን፡፡ የአጥኚ ዐላማና ግብ ደግሞ ሌላ ስለሚሆን ይህን አቋም ይያዝ አይባልም፡፡

ባህል ዘርፈ ብዙ የሕይወት መስክ እንደ መሆኑ በውስጡ የያዛቸው ልዩ ልዩ ዘርፎች ራሳቸውን ችለው ሊጠኑ ይችላሉ፡፡ ከክርስትና ጋር ባላቸው መስተጋብር፣ ለክርስትና ካበረከቱት አስተዋፅኦም ሆነ በክርስትና ላይ ካደረሱት አሉታዊ ተጽዕኖ አንጻርም ሊጠኑ ይችላሉ፡፡ ከዚህ ውጪ ክርስትናንና ባህልን ቀላቅሎ መመልከት መብት ሊሆን ቢችልም፣ ክርስትናን በመጽሐፍ ቅዱስ መነጽር ለሚመለከት ሰው ግን ክርስትናን ዋጋ ማሳጣት ይሆናል፡፡

ዳንኤል ክብረት ግን የቱ ጋ እንደ ቆመ ግልጽ አይደለም፡፡ ሃይማኖተኛ ሆኖ ሲጽፍ መጽሐፍ ቅዱስን የተሟላና ያልተሟላ ብሎ ይፈርጃል፡፡ በ“ኦርቶዶክስ መልስ አላት” መጽሐፉ ውስጥ 66ቱን ቅዱሳት መጻሕፍት ያልተሟላ መጽሐፍ ቅዱስ ሲል ይጠራቸዋል፡፡ ይህ ምናልባት ከሃይማኖታዊ ቅናት በመነሣት የተሰጠ ስያሜ እንጂ በጥናት ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡ ይህ በአብዛኛው የማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች የሚያቀነቅኑት እንጂ የቤተ ክርስቲያኒቱ ትምህርትም አይደለም፡፡ የተለመደውና ሊሆን የሚገባው አገላለጽ የተሟላና ያልተሟላ በሚል አንዱን ምሉዕ ሌላውን ሕጹጽ አድርጎ የሚገልጽ አቀራረብ ሳይሆን፣ እኛ የምንቀበለው 81፣ እነርሱ ደግሞ 66 ነው ብሎ የመጻሕፍቱን ቊጥር መጥቀስ ነው፡፡ አሊያ ካቶሊክም፣ የግሪክ ኦርቶዶክስም፣ ሌሎቹም የተቀበሏቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ቁጥር ቤተ ክርስቲያናችን ከተቀበለቻቸው መጻሕፍት በቁጥር ያነሡ ስለሆነ እነርሱንም ያልተሟላ መጽሐፍ ቅዱስ የተቀበሉ በሚለው ፍረጃ ውስጥ ማካተት ግድ ሊሆን ነው፡፡

ዳንኤል ሆይ! ለመሆኑ የተሟላና ያልተሟላ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚለው ድምዳሜ ላይ የደረስኸው በምርምር ነው፤ ወይስ በፈሪሳዊ እውነትን የማፈን ስልትህ ተጠቅመህ? አካሄድህ ሲገመገም “ሁሉን ፈትኑ መልካሙን ያዙ” በሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሕ ከመመራት ይልቅ “ሃይማኖት በየዋህነት” በሚለው የምእመናን መርሕ የምትመራ ነው የሚመስለው፡፡ “ጥናትንና ትምህርተ ሃይማኖትን አልለዩም” በማለት የራስህን ሥራ ለመምህር በቃሉ አዛወርህ እንጂ፣ ብዙ ጊዜ ጥናትንና ትምህርተ ሃይማኖትን በማደባለቅህ ምክንያት ጥናትህ ወደሚያደርሰው ድምዳሜ መሄድ የምትፈልግ ገለልተኛ አይደለህም፡፡ መድረሻህን ቀድመህ ያወቅህና በጥናት ስም መጽሐፍ ቅዱሳዊውን እውነት ለማጣመምና ለማፈን፣ በሰው ባህል፣ ወግና ልማድም ለመሸፈን የምትፈልግ መሆንህ ነው ጎልቶ የሚታየው፡፡

ዳንኤል ተመራማሪ ሆኖ ሲናገር ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስና ገድላትን እናትና ልጅ እንኳ አድርጎ አያቀርባቸውም፤ እኩል ያደርጋቸዋል፡፡ ካሁን ቀደም ከዕንቁ መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ “… የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እኮ በማይክሮ ፊልም የተነሡ ብቻ ወደ አምስት ሺ መጻሕፍት ያሏት ናት፡፡ እንዴት ነው በአማርኛ የታተመ መጽሐፍ ቅዱስን ገጽ በገጽ ተመልክተን ስለ ቤተ ክርስቲያኗ በድፍረት የምንናገረው? እንዴት የአንድን ቤት የአጥሩን አንድ ብሎኬት ብቻ አይተህ ስለቤቱ በጠቅላላ በድፍረት ትናገራለህ? ለዚህ ነው በአሁኑ ጊዜ ከማስተማር ይልቅ ወደ ጥናትና ምርምሩ ያተኮርኩት፡፡” ብሏል (መጋቢት 2002፣ 38)፡፡ መቼም ሌላ እንጂ ክርስቲያን ነኝ የሚል ተመራማሪ እንዲህ ይላል ተብሎ አይታሰብም፡፡ 

አንዲትን ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን የሚያሰኟት የተለየ ባህሏና ሥርዐቷ ሳይሆኑ፣ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ላይ መቆሟ ነው፡፡ በዚህ መሠረት ላይ የቆመች ቤተ ክርስቲያን የራሷ ባህልና ሥርዐት ይኖሯታል፡፡ ሁሉም ግን በየመልክ በየመልኩ ነው መታየት ያለበት፡፡ የዳንኤል ክብረት አንዱ ችግር ቤተ ክርስቲያናችን እንደ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችበትን መሠረት መቀበል አለመፈለጉ ይመስለኛል፡፡ ከላይ በተጠቀሰው ዕንቁ መጽሔት ላይ እንደ ተናገረው፣ ለእርሱ መጽሐፍ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያናችን የቆመችበት ዋና መሠረት ሳይሆን የቤተ ክርስቲያኒቱን አጥር ለመገንባት ከተደረደሩት ብሎኬቶች አንዱ ብሎኬት ተደርጎ የሚቆጠር ነው፡፡ በምርምር ውጤቱ መሠረትም ለእርሱ መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች አዋልድ መጻሕፍት እንደ አንዱ እንጂ የተለየ መሠረቷ አይደለም፡፡ ይህ ግን ለአጥኚ ምንም ባይሆን፣ የቤተ ክርስቲያንን መሠረት የሚንድ ትልቅ ኑፋቄ ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያኗ የብዙ መጻሕፍት ባለቤት ናት፤ በእነዚህ መጻሕፍቷም ትታወቃለች ማለት አንድ ነገር ነው፡፡ የመጻሕፍቶቿን ብዛትና ይዘት በመልክ በመልኩ ፈርጆ ማጥናትም ብዙ ነገሮችን እንድናውቅ ይረዳናል፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ የምትገኝበት ክርስቲያናዊ አቋም ሊመዘን የሚገባው ግን በአንድ መጽሐፍ ቅዱስ ነው እንጂ በአዋልድ መጻሕፍት ሁሉ አይደለም፡፡ አዋልድ መጻሕፍት ራሳቸው የያዙት ትምህርት ክርስቲያናዊነት መመዘን ያለበት በመጽሐፍ ቅዱስ መሆኑ ከቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮ ውጪ አይደለም፡፡ ዳንኤል ሃይማኖትን ከባህል ደበላልቆ የጀመረው ጥናት ያደረሰው ግን የመጽሐፍ ቅዱስን ደረጃ እጅግ ዝቅ ወደሚያደርግ፣ ገድላትን ደግሞ እጅግ ከፍ ወደሚያደርግና ቤተ ክርስቲያንን በሌላ መሠረት ላይ መጣል ወደሚመስል ድምዳሜ ነው፡፡

በሃይማኖታዊ አስተምህሮ ላይም ጥናት ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን የዳንኤል አካሄድ በአብዛኛው ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ሃይማኖታዊ ትምህርትና ሥርዐት በገለልተኛ መንገድ ማጥናት፣ የሚሻሻል ካለ የሚሻሻልበትን መንገድ መጠቆም፣ መጽናት ያለበት ነገርም ካለ እንዲጸና ማመላከት መሆን ይገባው ነበር፡፡ አሊያ የኖረውን ተቀብሎ በምእመናን ደንብ በየዋህነት መመላለስ አንድ ነገር ነው፤ ተመራማሪ ብሎ ራስን ለሠየመ ሰው ግን ይህ የሚመጥን አይደለም፡፡

በመጨረሻም መነሣሣት ያለበት ነጥብ አንተም ሆንህ ሌሎቹ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በየአጋጣሚው የቤተ ክርስቲያኒቱን ገጽታ እያኮሰሳችሁ የማኅበረ ቅዱሳንን ገጽታ ለመገንባት የምታደርጉት ጥረት ከምን የመነጨ ነው? ትርፉስ ምን ይሆን? ከትምህርተ ሃይማኖት ነጻ የሆነውን የጥናት “መድረክ በማዘጋጀት በኩል ማኅበሩ ቅድምናውን ወስዷል” ስትል፣ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ምንም እንዳልሠራ አድርገህ አቅርበሃል፡፡ የማኅበሩን የጥናት መጽሔት እንደ ስለት ልጅ በስስት እንዲታይ በማድረግና ማንም የጎነተለው ሳይኖር “… አንድ ቢኖረን እርሱንም መጎንተል” ስትልለት፣ ጥናት በዜና ቤተ ክርስቲያንና በበልሳነ ተዋሕዶ መታተም አለበት ተብሎ የተጻፈ ይመስል የቤተ ክርስቲኒያቱን ልሳናት በአሽሙርና በስላቅ መንካት፣ የማኅበርህን ሰዎች “ኤክስፐርት” ስትላቸው፣ የቤተ ክርስቲያኗን ሊቃውንት የፖለቲካ ሹመኞች ብቻ አስመስለህ “ባለሥልጣን” ማለትህ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ትናንት እንጂ ዛሬ ወጥተው የሚያስተምሩና የሚጽፉ ሊቃውንት እንደሌሏትና የማኅበረ ቅዱሳን “ኤክስፐርቶች” እንደ ተኳቸው መግለጽህ ከማሳዘኑም በላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ ገጽታ እስካልኮሰሰ ድረስ የማኅበረ ቅዱሳን ገጽታ የሚገነባ እንደማይመስላችሁ አሳብቆብሃል፡፡

መምህር በቃሉ
ከ5 ኪሎ
ምንጭ፡- ነጋድራስ ጋዜጣ የሐምሌ 15 ዕትም

24 comments:

 1. በቃሉ አሁን ከአንተ በላይ ፈሪሳዊ አለ እንዴ ቢያንስ ዳንኤል ክብረት ሙሉ ስሙን ስትጠቀም የአንተን የውሸት ሰምህን ሙሉ ለማድረግ የደከመህ ምን ሆነህ ነው? አለመታደልህ ድከም ብሎህ::

  ReplyDelete
 2. kante belay ferisawe,dikem biloh tdekmalek negeroch eskemiteru bicha tengetaget keziya wy beyfa tiwetalh wey beyifa timelesalh.ante bilo asteyayet sechi bekalu aluh anath lay eshoh yibkelbh.ewket ema endybekl aemrohn qolfeh yazkew.qolafa!!!!!!!!!!!!!!i am wubshet tentaw!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 3. ayyyy, bekalu!!! shame on u,who u are to accuse him? u are nowhere to daniel,who is well contributing to the people of Ethiopia in general and to the church in particular.

  ReplyDelete
 4. I think Bekalu has a vested interest of initiating conflict between MK and church fathers while splitting hairs. Besides, you are undermining the book of Henok while you are saying you are one of the church fellowers. I can imagine that you are not a memeber of tewahido Orthodox. Egziabher lehulachinim mastewalun yisten!

  ReplyDelete
 5. By the way, who gave the title "ተመራማሪ" to Daniel? Is the Church or MK ?In which profession? I don't believe but may be from MK.

  I think he is foolish if he accepts the title from his followers. As for me, if he has an addiction of names it is better for him to be called'Megabie-mistir' because last time he fed us a wonderful MK's 'Gemena'.

  ReplyDelete
 6. ይገርማል እሱ እኮ ለቤ/ክ ሁሉ ነገሩን የሰጠ ሰው ነው ፡፡ እንደርሱ ለመሆን ገና ብዙ ነገር የጠበቅባችኋል፡፡ የምትጽፉት ሁሉ በቅናት መንፈስ እንደሆነ ጽሁፋችሁ የናገራል፡፡

  ReplyDelete
 7. አይይ ምን አለ ጊዜህን በከንቱ ባታጠፋ ውሸታም ዲ ዳንኤል እኮ ለቤተ ክርስትያን ያበረከተውን ያህል ትንሽ ብትጥር አይሻልህም ነበር??እውቀትህ አፍህ ሲከፈት አእምሮህ ታየ እናም ውስጡ ባዶ ነው

  ReplyDelete
 8. እርግጠኛ ሁኑ እውነት ትቀጥን እንደሆን እንጂ አትበጠስም የናንተ ማንነትም ታውቋል የበግ ለምድ ለመልበስ አትሞክሩ የኋለኛው ዘመን መልእክተኞች

  ReplyDelete
 9. Ere bacachehu Atelfu ! Manenetachehu Teleytual!!

  ReplyDelete
 10. why dont you gays focuse on the truth did u get anything wrong in bekalus idea. if u do tell us or accept the truth. only the truth is the writw way.

  ReplyDelete
 11. አይ እኛ ኦርቶዶክሳውያን መቼ ይሆን ከጭፍን ድጋፍና በጅምላ ከማመን የምንወጣው? በቃሉ በነጋድራስ ጋዜጣ ላይ ዳንኤል ላወጣቸው ጽሁፎች በጭብጥ እየነቀሰ ማብራሪያ ፤የእውነት ምስክርነትና ሚዛናዊ ባለሙያነት የሚጠበቅባቸው ነጥቦች እነዚህና እነዚህ ናቸው በማለት እያዋዛ፤ ለዛ ባለው አማርኛ ጽፎ አስነብቦናል። በቃሉ የተሳሳተው ነጥብ ካለ ያንን እያነሱ መልክ ያለው መልስ መስጠት ሲያቅተን የመንደር ትርኪምርኪ ነቀፋ መሰንዘር «ህዝቤ ዕውቀት ከማጣት የተነሳ ጠፍተዋልና» የተባለው ቃል በኛ ላይ እየሰራ በመሆኑ ዕውቀታችን ከደረጃ በታችና ግራና ቀኝ የማያይ መሆኑን ያረጋግጣል።

  ReplyDelete
 12. those of u insulted ato bekalue, why don't u challenge him by presenting convincing idea?

  ReplyDelete
 13. Hi Wondime Bekalu, Anten yemesele Researcher yebete christian lij " memhir" sibal. Daniel gin berasu Gizie tenestu erasun Diacon ale keyet endametaw sayitawok - endiawum leziachi yebehardar giorgis sunday school temari wotat " DIKALA ASTAKIFO ( Liju Tinbite Daniel ) Tibalalech.

  Keziam Degimo from MK members " Menbere Kemitibal" Yewahi Ye'bole Akababi wotat Liji Woldo Abarerat. Yihim be mahibere kidusan abalat hulum miawokew ewuneta new - Menbere Le'MK council members Lijun Tekebelugne bila endeneber yitawokal.

  Finally, Liji agered yalinberechi yesidist kilo temar - Alemawi boyfriend yeneberat lerejim gizie " Tsilat Yimitibal" Wotat gar gabicha betelo fetseme. Wanawim mikiniyat Enatua mutew sileneber endihum abatua Ayine Siwir sileneberu bematalel erisuan ke' alemawi boyfriendu kemito ageba,

  To me, Daniel Ayaminim neger gin enjera hunobet sile eminet yasitemiral. By the way, he didnot finish his under grad from AAU. So, how can this gay can be a researcher. He was not in Theology college, Be ' lela bekul degimo minim ayinet ye'diacon or temesasay timihirt yelewum. Yihin Degimo Hulum Yakababiw memhiran minawikew new.

  Ahun degimo, EPRDF member negne eyale MK abalatin masiferarat jemirual. Aboy Sibihat Guadegnaye new Yilal tebilo neber. Aboy Sibihat Gin Alawikewim New Yalut. Endiawum Eyetefelege Eyale kene betesebu Wode America Feretete Yibalal. Be-kirib CD ena Metsehaf Ke-Addis Ababa Yilekekal.

  Egziabhere masitewal Yistew. Yene Abune Mereha Kirstos ena Megabi Biluy Seife Amlak Yifaredew. Tehadiso Bemalet Asazino Gedelachew. Megabi Biloy Seife lememotachew teteyaki BE'MEDIHANIT Andu Erisu new. Lewodefitu Yigeletsal.

  Aschalew
  Ze-behardar Giorgis

  ReplyDelete
  Replies
  1. ዕቃቃ የምትጫዎት ይመስላል::
   ምናለበት ስድቡን ትተህ ቁም ነገር ብታወራ::
   ጊዜህን ባታቃጥል::

   Delete
 14. አስቻለው ፤ ይህንን ስትጽፍ ትንሽ እንኻን አታፍርም ?፤ እግዚአብሄርን እንኻን አትፈራም? እኔ ግን ላንተ አፈርኩልህ፤ ይቅር ይበልህ

  ReplyDelete
 15. aschalew yerashen gudef betay ayeshalehem lemehonu ante haymanoteh mende new daniel seraw lalkew egziabher engi ante ateteyekwem legna leortodoxawyane teru adrego astemeronal eyastemarenem new ena bekentu were gezehen kemetatefa melkam serabet mehretune yelakeleh

  ReplyDelete
 16. በይሁዳ መልእክት ውስጥ ከሄኖክ መጠቀሱ መጽሐፈ ሄኖክ ከቅዱሳት መጻሕፍት አንዱ ለመሆኑ ማስረጃዎች መሆናቸው በዳንኤል ቃለ ምልልስ ውስጥ ተጠቅሷል፡፡what about the book of Jude(yihuda) is that from the holy book or not...?if so is it right the holly book to use non holly book as a reference?
  what shameful speaking and writing do have?have you ever read what the bible says"remove the dirty in your eye before you look on others" anyway it is not that much amazing b/c it says "you know from their fruit" and "their proud is on their shame"..................

  ReplyDelete
 17. መምህር በቃሉ you say your self teacher but the bible says "don't say am a teacher"but you oppose the title given to DN DANIEL(researcher) and the bible says search the truth,don't believe all spirit but search whether the spirit is from God or not?
  who is right you or Dn Daniel according to the bible?
  am sorry am really shocked by your writing being you are a teacher

  ReplyDelete
 18. To Aschalew
  Ze-behardar Giorgis you have said a lot about dn Daniel.but could you tell us some thing about you?and some thing about your contribution to the church? and your personal quality?
  "any one who seems stand should care not to fall"
  plus to that i invite you to read about moss the black

  ReplyDelete
 19. To bekalu,I am sorey to say you are the one you didn't know what you are taking. let me ask you one question , why are you going to oppose always the activities of Mk and Dn danieal. I am sure that you are not the member of this church.please why you don't leave us? go to your member. you are not our religious brother.

  ReplyDelete
 20. Betem Tasafiralehi "Dedeb" nehe bileh kir yilihal?

  ReplyDelete
  Replies
  1. አውሬው ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥
   ራዕ 13፣5

   Delete
 21. ይገርማል አንዴ መጽሃፈ ሄኖክ ከቅዱሳት መጽሃፍ መካከል አይደለም አንዴ ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ መሆን

  ReplyDelete
 22. ጽሁፍ ሁሉ የጥላቻ እንጂ የሃይማኖኛ ሰው አይመስልም!!!

  ReplyDelete