Sunday, September 11, 2011

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ምን ምን ነገረን?

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ምን ምን ነገረን?
(ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኗል)

ሦስተኛው የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን በሕዝቡ ላይ የአገዛዝ ቀንበር አክብዶ ነበር፡፡ በዘመነ መንግሥቱ መጨረሻ ላይ ከእግዚአብሔር መንገድ በመውጣቱ፣ እግዚአብሔር ከሰሎሞን ሞት በኋላ መንግሥቱን ከሁለት ከፍሎ ዐሥሩን ነገድ ለኢዮርብዓም፣ ሁለቱን ነገድ ደግሞ ለልጁ ለሮብዓም ሰጠ፡፡ በዚህ ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ወደ ሮብዓም ቀርቦ፣ አባትህ ያከበደብንን ቀንበር ካቀለልህልን እንገዛልሃለን ቢለው፣ የሽማግሎችን ጠቃሚ ምክር አቃሎ ተመለከተ፡፡ በባልንጀሮቹ ጎጂ ምክር ተነዳ፤ የአገዛዝ ቀንበሩንም ከአባቱ የበለጠ እንደሚያጠነክረው ነገራቸው፡፡ እነርሱም ከዳዊት መንግሥት ወጥተው በኢዮርብዓም አገዛዝ ሥር ገቡ፡፡ አንድ የነበረው የእስራኤል መንግሥት ከሁለት ተከፈለ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ይህ የሆነበትን ምክንያት ሲያስረዳ፥ “እግዚአብሔርም በሴሎናዊው በአኪያ አድርጎ ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረውን ነገር እንዲያጸና ከእግዚአብሔር ዘንድ ተመድቦ ነበርና ንጉሡ ሕዝቡን አልሰማም” ይላል (1ኛ ነገሥት ምዕራፍ 12 ቁጥር 15)፡፡

እግዚአብሔር ማንም ያልጠበቀውን አስደናቂ ነገር በማድረግ የታወቀ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው፡፡ በሰው ፊት አይቻልም፤ አስቸጋሪ ነው፤ ማን ያውቀዋል፤ ማን ይደርስበታል፤ የተባለውን ነገር ባልታሰበና ባልተጠበቀ ሁኔታ ይገልጠዋል፤ በቃህ ያለውንም ከመንገድ ያስወግደዋል፡፡ ይህን ለምን እንዲህ አደረግህ? የሚለው ግን የለም፤ እግዚአብሔር በሰዎች መንግሥት ላይ ሥልጣን ያለውና መንግሥቱን ለወደደው የሚሰጥ ልዑል ነውና (ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 4 ቁጥር 32)፡፡ አንዳንድ ጊዜ ማንም አይደፍረንም ያሉትን ባላሰቡትና ባልጠበቁት መንገድ፣ በራሳቸው አንደበት አናግሮ ቋንቋቸውን ይደበላልቃል፤ እውነትን ይገልጣል፤ ፍርድን ይሰጣል፡፡ የሰሞኑ የማኅበረ ቅዱሳን ውዝግብም የዚህ አምላካዊ አሠራር አንዱ መገለጫ ነው ማለት ይቻላል፡፡

ከላይ የተጠቀሰው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማኅበረ ቅዱሳን አመራርና በዲያቆን ዳንኤል ክብረት መካከል የሆነውን ነገር ሊያሳይ ይችላል፡፡ እስካሁን ማኅበረ ቅዱሳን በውስጡ ስለ ተፈጠረውና በቤተ ክርስቲያኒቱም ውስጥ እየፈጠረ ስላለው ችግር፣ ከውጪ እንጂ ከውስጥ ከራሱ ሰዎች እዚህ ግባ የሚባል ነገር ተነግሯል፤ ተጽፏል ማለት ያስቸግራል፡፡ ሰሞኑን በዲያቆን ዳንኤል ተጽፎ በደጀ ሰላም ድረ ገጽ ላይ የተለቀቀው ጽሑፍ ግን የእርሱ ቅሬታ የተገለጸበት ብቻ አይደለም፡፡ ብዙው ሰው ሊያውቀው ይመኘው የነበረ  የማኅበረ ቅዱሳን ብርቱ ምስጢር ነው፡፡

ደጀ ሰላም ድረ ገጽ የዳንኤል ጽሑፍ በብዙዎቹ የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር አባላት ዘንድ፣ “የማኅበሩን ህልውና እና አንድነት አደጋ ላይ የሚጥል፣ ለአጽራረ ቤተ ክርስቲያን አጋልጦ የሰጠ፣ እና ከመንግሥት ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋራ የሚያጋጭ ስም አጥፊ” የሚል ግንዛቤ እንደ ተወሰደበት ጽፏል፡፡ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ቢባል፣ በሮብዓም የደረሰው በማኅበረ ቅዱሳንም ደረሰ ከማለት በቀር ምን ይባላል? በመጀመሪያ መምህር ሙሉጌታ ዲያቆን ዳንኤልን በነገር ተነኮሰው፤ እርሱም አለወትሮው ለዚያ ምላሽ ለመስጠት ተነሣ፤ በዚህ መካከል መንፈስ ቅዱስ የዳንኤልን ፊቱን ጸፍቶ፣ አፉን ከፍቶ፣ እንዲሁም ብርዑን አትብቶ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን የተሰወረውን እንዲገልጥ አደረገው፡፡

የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ጽሑፍ ከግል ጉዳዩ ባሻገር ስለ ማኅበረ ቅዱሳን አንዳንድ ሊታወቁ የሚገቡ ጉዳዮችን ግልጽ አድርጓል፡፡ በእኔ እይታ የሚከተሉት ጉዳዮች ተገልጸዋል ብዬ አስባለሁ፡፡

1.    ደጀ ሰላም ድረ ገጽ የማን ነው?
ካሁን ቀደም ስለ ደጀ ሰላም ድረ ገጽ በተለያየ መንገድ ብዙ ተብሏል፡፡ ድረ ገጹ የማኅበረ ቅዱሳን መሆኑን ብዙዎች ቢያምኑም፣ ማኅበሩ ግን የእኔ አይደለም በሚል ያስተባብላል፡፡ ዲያቆን ዳንኤል ጽሑፉን ወደ ማንም አልላከም፡፡ ወደ ማኅበረ ቅዱሳን ልሳኖች ሐመርና ስምዐ ጽድቅ፣ ወይም ወደ ግሉ ፕሬስ አልላከም፡፡ በይቅርታ ጽሑፉ ላይ እንደ ገለጸው ለወንድሞቹ በኢ-ሜይል አሠራጨው፡፡ ከዚያ ጽሑፉ በደጀ ሰላም ድረ ገጽ ላይ ወጣ፡፡ ወንድሞቼ ካላቸው አንዱ ልኮታል ማለት ነው፡፡ ጽሑፉ በዚህ ድረ ገጽ ላይ እንዲወጣ ለምን ተፈለገ? ላኪው መልእክቱ ሊደርሳቸው የሚገባቸውን አንባብያን የመረጠለት ይመስላል፡፡ ምክንያቱም አሁን ባለው ሁኔታ ሐመርና ስምዐ ጽድቅ ጽሑፉን ሊያስተናግዱት አይችሉም፡፡ እንኳን ይህን ማኅበሩን ያሸበረ ጽሑፍ ይቅርና ከዚህ ቀደም ዳንኤል ይጽፋቸው የነበሩትን የተለመዱ ጽሑፎች እንዳያወጣ ስውሩ አመራር እግድ የጣለበት መሆኑን ነግሮናል፡፡

ጽሑፉን ወደ ወንድሞች ላክሁት የሚለው ማስተባበያ አንጀት የሚያርስ አይደለም፡፡ በጽሑፉ ውስጥ ምላሽ ለመስጠት የተገደደው “የፕሬስን ጉዳይ በፕሬስ መልስ መስጠት የተለመደም የሚገባም አሠራር” ስለሆነ ነው የሚል ምክንያት አቀርቧል፡፡ ፕሬስ ማለት ወንድሞቼ ያልኋቸው ናቸው እንደማይል ግን ተስፋ ማድረግ ነው፡፡ ምናልባት ጽሑፉ በወንድሞች መካከል ውስጥ ወስጡን እየተብላላ ከቆየና አስተያየቶች ከታከሉበት በኋላ በመጨረሻ ወደ ፕሬስ ይወጣል የሚልም ይመስላል፡፡ በሌላ በኩል የጽሑፉ ግልባጭ የሚደርሳቸው ተብለው የተዘረዘሩት፡- የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጉባኤ፣ ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ፣ የማኅበሩ ሰብሳቢ፣ ዋና ጸሓፊ፣ ኦዲት እና ኢንስፔክሽን አገልግሎት፣ ዋና ክፍሎች፣ ሁሉም ማእከላት፣ የሚመለከታቸው አባላት እንዲሁም ዕንቁ መጽሔት ናቸው፡፡ ይህም ጽሑፉ ለሚመለከታቸው የማኅበሩ ክፍሎችና የዋና ጸሓፊው ቃለ ምልልስ በወጣበት መጽሔት ላይ እንዲወጣ ተብሎ የተዘጋጀ መሆኑን ያስረዳል፡፡ በአጠቃላይ ለማኅበረ ቅዱሳንና ለዕንቁ መጽሔት ነው የላከው ማለት ነው፡፡ ሆኖም በይቅርታው ላይ ዳንኤል “ወንድሞች” ያላቸው ሁሉንም የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ይሁን፣ ወይም የተወሰኑትን ግልጽ አይደለም፡፡ በተጨማሪ “የፕሬስን ጉዳይ በፕሬስ መልስ መስጠት” የሚለው ተገቢ አካሄድና ዳንኤል ምላሽ ለመስጠት የመረጠው መንገድ ፈጽሞ ተለያይተዋል፡፡ ከዚህ አንጻር ለወንድሞች ልኬው ደጀ ሰላም ድረ ገጽ ላይ ወጥቶ ተገኘ የሚለው ማስተባበያው ሚዛን የሚደፋ ሆኖ አይታይም፡፡

ዳንኤል በጽሑፉ እንደ ጠቆመው “በማኅበሩ የግል ጋዜጦችን ማንበብ በስውር የተከለከለ ነው፡፡” ጽሑፉን ወደ ግል ጋዜጦች ወይም መጽሔቶች ቢልከው ይህ ክልከላ ከአንባብያኑ ጋር እንዳይገናኝ ሊገታው ይችል ይሆናል፡፡ ስለዚህ ማስተባበያው ሚዛን አለመድፋቱ እንደ ተጠበቀ ሆኖ፣ ከወንድሞቹ አንዱ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ነው ተብሎ በሰፊው በሚነገርለትና የማኅበሩ አባላት በሚከታተሉት በደጀ ሰላም ድረ ገጽ ላይ ጽሑፉን መልቀቅ አማራጭ የሌለው መንገድ ሆኖ አግኝቶታል ማለት ነው፡፡

ደጀ ሰላም የዲያቆን ዳንኤልን ጽሑፍ ካወጣ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ጽሑፉን ከድረ ገጹ ላይ ድራሹን አጥፍቶታል፡፡ ድረ ገጹ ለምን እንዲህ አደረገ? በመጀመሪያ ጽሑፉን ተቀብሎ ለምን አስነበበ? ለብዙ ጊዜያት ድረ ገጹ ላይ የቆዩና ያረጁ አያሌ ጽሑፎችን ከተሰቀሉበት ሳያወርድ ለዳንኤል አስገራሚ ጽሑፍ የቀን ዕድሜ እንኳ ለምን ነፈገው? በመጀመሪያ ሳያነብና ሊያስከትል የሚችለውን ውጤት ሳይገነዘብ ነው ያወጣው? ወይስ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኗል? ጽሑፉ እንዲወርድ ትእዛዝ የሰጠውስ ማነው? ስውር አመራሩ ወይስ ሌላ? ይህን የማድረግ ሥልጣኑስ የት ድረስ ነው? ለምን የዳንኤል ጽሑፍ ሳይጠፋ የማኅበረ ቅዱሳን ስውር አመራር ድምፅ በሚዛናዊነት እንዲቀርብ አልተደረገም? ደጀ ሰላም ለነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ምላሾች የሚጠበቅበት ቢሆንም፣ እርሱ ግን ጽሑፉን ለጥቂት ጊዜ ሰቅዬ ያወረድሁት፣ ልዩነቱ በማኅበሩ የውስጥ አሠራር እንዲፈታ ዕድል ለመስጠት ነው የሚል ውሃ የማያነሣ ምክንያት ያቀርባል፡፡ “ቀድሞም ባልዘፈንሽ ኋላም ባለፈርሽ” አሉ!

ለመሆኑ ደጀ ሰላም ከሚዲያ ሥነ ምግባር ወጥቶ እንዲህ “መንፈሳዊ” ለመሆን ምን አነሣሣው ይሆን? የቤተ ክርስቲያኒቱን አባቶችና ልጆች ክብር እየነካ በምእመናን መካከል ልዩነት እንዲፈጠርና ሕዝቡ ለቤተ ክርስቲያን መሪዎች እንዳይታዘዝ ሲቀሰቅስ፣ የማኅበረ ቅዱሳንን በጎ ገጽታ ደግሞ እያጋነነ ሲገነባ እንደ ኖረ ይታወቃል፡፡ አሁንም በዚህ ከፋፋይና የቤተ ክርስቲያንን ሰላም በማደፍረስ ተግባሩ ቀጥሎበት ይገኛል፡፡ ነገር ግን አንድም ቀን “ይህ የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጉዳይ ነውና በቤተ ክርስቲያኒቱ የውስጥ አሠራር እንዲፈታ ዕድል ልስጥ” አላለም፡፡ እርሱ ቤተ ክርስቲያኒቱን በሁለተኛ ደረጃ ነው የሚያያት፤ ቅድሚያ የሚሰጠው ደግሞ ለማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ይህም የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ሁሉ የሚያሳዩት “ማኅበረ ቅዱሳናዊ” ጠባይ ነው፡፡ ታዲያ ደጀ ሰላም በዚህ ጠባዩ የማኅበረ ቅዱሳን ንብረት መሆኑን አላስመሰከረም ማለት ይቻል ይሆን?

ማኅበረ ቅዱሳን ደጀ ሰላም ድረ ገጽ የእኔ አይደለም በማለት በየጊዜው ቢያስተባብልም፣ ድረ ገጹ የእርሱ ለመሆኑ ግን በዳንኤል ጽሑፍ ላይ በሠራው ሰቅሎ የማውረድ ተግባር ግልጽ ያደረገ ይመስላል፡፡ ሰቅሎ ማውረድ ለድረ ገጹ እንግዳ ተግባር አይደለም፡፡ ድረ ገጹ በጀመረባቸው ጊዜያት ለምሳሌ በ2009 “Deje Selam web site owned by Mahebere Kidusane” የሚል ባለቤትነትን አመልካች ጽሑፍ በመጀመሪያው ገጽ ላይ ሰፍሮ ነበር፡፡ ወዲያው ግን ጠፍቷል፡፡ ከመጥፋቱ በፊት ኮፒ አድርገው ለያዙ ሰዎች ምስጋና ይሁንና፣ በዚህ ጽሑፉ ማኅበረ ቅዱሳን እቆጣጠረዋለሁ፣ የእኔ ንብረት ነው ያለውን ደጀ ሰላምን፣ በአሁኑ ጊዜ የእኔ አይደለም ብሎ በአደባባይ ይክደዋል፡፡ በየጊዜው “ደጀ ሰላም ድረ ገጽ የአንተ አይደለም ወይ?” ተብሎ ሲጠየቅም የእኔ አይደለም በማለት ሲያስተባብል ነው የቆየው፡፡ አሁን ግን በዳንኤል ጽሑፍ ምክንያት ድረ ገጹ የማን መሆኑንና ለማን እንደ ቆመ የጠቆመ ይመስላል፡፡

በአንድ በኩል ድረ ገጹ የማኅበረ ቅዱሳን ነው ማለት አያስኬድም፤ ምክንያቱም ደጀ ሰላም የማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ ቢሆን ኖሮ የዳንኤልን ጽሑፍ ከመጀመሪያውኑ አያወጣውም ነበር የሚል ሰው ይኖር ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከዳንኤል ወንድሞች አንዱ ከሌላው ይልቅ ደጀ ሰላምን ለምን መረጠ? ጽሑፉን ያሳለፉት የድረ ገጹ ሰዎችስ እንዴት አሳለፉት? የሚሉት ጥያቄዎች ከቶም ሊታለፉ አይገባም፡፡ ራሱ ዳንኤል ጽሑፉን ለማውጣት የተገደደበትን ምክንያት ሲገልጽ “የፕሬስን ጉዳይ በፕሬስ መልስ መስጠት የተለመደም የሚገባም አሠራር” መሆኑን ጠቅሶ ነበር፡፡ ለቅሬታው መነሻ የሆነው ቃለ ምልልስ በወጣበት በዕንቁ መጽሔት ላይ ምላሹን መስጠትም ከዳንኤል የተሰወረ አልነበረም፤ ነገር ግን ወደ እርሱ አላከም፡፡ ስለዚህ በማንኛውም መንገድ ዋናው የጽሑፉ ተቀባይ ደጀ ሰላም ድረ ገጽ ሆኗል ማለት ነው፡፡

ቀደም ብሎ መስከረም 12/2002 ዓ.ም. በማኅበሩና በማደራጃ መመሪያው መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት ተደርጎ በነበረው ስብሰባ ላይ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያው በማኅበሩ ላይ ካሰማቸው ቅሬታዎችና ሮሮዎች መካከል “ደጀ ሰላም በተባለው ድኅረ ገጹ ጁላይ 9/2009 ዓ.ም. ባወጣው ጽሑፉ ብፁዓን አባቶችን መወረፉ” የሚል ይገኝበታል፡፡ ይሁን እንጂ ማኅበሩ ለቀረቡበት ሌሎች ቅሬታዎች ምላሽና ማስተባበያ ለመስጠት ሲሞክር በደጀ ሰላም ጉዳይ ላይ ያለው ነገር ስለ መኖሩ የስብሰባው ቃለ ጉባኤ አያስረዳም፡፡

2.   ማኅበረ ቅዱሳን የስለላ ክፍል አለው
ዳንኤል ሌላ ያረጋገጠልን እውነት ማኅበረ ቅዱሳን የስለላ ክፍል ያለው መሆኑን ነው፡፡ ይህ ክፍል ለአመራሩ በቂ መረጃ ለመስጠት በሚል “የመረጃ ክፍል” ተብሎ እንደ ተቋቋመ ጠቁሟል፡፡ ነገር ግን “የፕሮቴስታንት ኅትመቶችን ከመግዛት ባለፈ መሥራት አልቻለም፡፡ እንዲያውም ሥራውን ትቶ የገዛ አባላቱን እስከ መሰለል ነው የደረሰው፡፡ ወሬና መረጃ መለየት የተሳነው ክፍል ነው፡፡” ሲልም እየሠራ ያለውን ሥራ ፀሓይ ላይ አስጥቶታል፡፡ ይገርማል! ማኅበረ ቅዱሳን አንዳንዶቹን የቤተ ክርስቲያን ልጆች የወነጀለበት ክስ የፕሮቴስታንቶችን ኅትመቶች ያነባሉ የሚል ነበር፡፡ ራሱ ግን ለበጎም ይሁን ለክፉ የፕሮቴስታንት ኅትመቶችን የሚከታተልበት ክፍል አደራጅቷል፡፡ ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን በመናፍቅነትና በተሐድሶነት ይጠርጠርልናማi

ከዚህ ቀደም ማኅበሩ የስለላ መረብ እንዳለው ይታወቃል፤ በስለላ መረቡ ተይዘው በሕገ ወጥ መንገድ ከቤተ ክርስቲያን የተሰደዱ አባቶችና ወንድሞች ይህን ደኅና አድርገው ያውቁታል፡፡ በመረጃ ክፍሉ እየታገዘና የቤተ ክርስቲያንን ልጆች በተሐድሶነትና በመናፍቅነት ፈርጆ እየሰለለ ከቤተ ክርስቲያን እንዲባረሩ ማድረጉም አገር ያወቀው ፀሓይ የሞቀው ሐቅ ነው፡፡ በቅርቡም ከመቐሌ ንኡስ ማእከል የወጣውና በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ድረ ገጽ ላይ የተለቀቀው ደብዳቤ፣ እየሰለላቸው ያሉ የቤተ ክርስቲያን አባቶችና ልጆች መኖራቸውን ጠቁሟል፡፡ ማኅበሩ ግን ሌሎች ያዘጋጁትና የማኅበሩን ስም ለማጉደፍ ያረቀቁት ደብዳቤ አድርጎ ለማስተባበል ሞክሯል፤ ምስጋና ለዳንኤል ጽሑፍ ማኅበሩ የስለላ ክፍል ያለው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

ክርስትና የሚስፋፋው በስለላ አይደለም፤ ወንጌልን ሰብኮ የሰውን ሁለንተና በመለወጥ ነው፡፡ ወንጌል ሃይማኖታችንን በስለላ እንድንጠብቅ አያስተምረንም፡፡ ክርስቲያኖች በሌሎች ይሰለላሉ እንጂ እነርሱ ማንንም አይሰልሉም፡፡ የእግዚአብሔርን ሕግ ትቶ በሰው ወግና ልማድ በተተበተበው የአይሁድ ሃይማኖት አሠራር ውስጥ ግን ስለላ እንደ ነበረ ከመጽሐፍ ቅዱስ እናነባለን፡፡ በጊዜው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚሰልሉ ሰዎችን በየሚያስተምርበት ቦታ ሁሉ ያሰማሩ ነበር፡፡ ሐዋርያትንም በተመሳሳይ መንገድ ይሰልሏቸው ነበር (ገላትያ ምዕራፍ 2 ቁጥር 4)፡፡ መቼም ስለላ የዚህ ዓለም መንግሥታት አሠራር ነው፡፡ በክርስትና ውስጥ ግን የለም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የቆመው በምን ላይ ይሆን? ክርስቲያናዊ ማኅበር ነው እንዳይባል ክርስቶስ ሲሰበክ ይበሣጫል፤ ወንጌልን የሚሰብኩትን የቤተ ክርስቲያን አባቶችና አገልጋዮች ይሰልላል፤ ይወነጅላል፤ ያሳድዳል፡፡ በዚህም ከአይሁድ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ሌላው ጥርጣሬ ግን “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ” እንዲሉ፣ ምናልባት ፖለቲካዊ ንክኪ አለው ስለሚባል፣ ፖለቲካዊ አሠራሩ የፈጠረበት አካሄድ ሊሆን ይችላል የሚለውም የሚናቅ ሐሳብ አይደለም፡፡
 
3.   ማኅበረ ቅዱሳን ተሐድሶ ያስፈልገዋል
ማኅበረ ቅዱሳን ራሱ የተሐድሶ ውጤት ቢሆንም፣ ዛሬም እንኳ ከሚገኝበት ችግር አንጻር ተሐድሶ እንደሚያስፈልገው በዲያቆን ዳንኤል ቢነገረውም፣ እርሱ ግን ተሐድሶ የተባለውን መንፈሳዊ እንቅስቃሴ፣ የተሳሳቱ የሚመለሱበት፣ የወደቁ የሚነሡበት የእግዚአብሔር የንስሓ ጥሪ መሆኑን እያስተባበለ፣ ሰዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማፈራረስ ያቋቋሙት ድርጅት አድርጎ ነው የሚያቀርበው፡፡ ይሁን እንጂ ከተሐድሶ ውጪ መኖር የማይቻል በመሆኑ፣ ቃሉን እርሱ ጠልቶ በሌሎች ቢያስጠላውም የተሐድሶን ግብር መፈለጉ ግን አልቀረም፡፡ ስለዚህ ዳንኤል “አካሄዳችንን እንገምግም፤ አመራሩን እንገምግም፤ እንደ ገና መነሣት /ሬናይዛንስ/ ያስፈልገናል፡፡” ብሏል፡፡

እንደ ገና መነሣት ምንድን ነው? ሬናይዛንስስ ምንድን ነው? ያው ተሐድሶ አይደለምን? መንግሥት እንኳ በሚሌኒየሙ መባቻ ላይ ዘመኑን የሕዳሴ ዘመን ያለው “ሬናይዛንስ” የሚለውን ቃል ተርጉሞ አይደለምን? እናንተ ስታረጁና “ስታክ” ስታደርጉ እንታደስ እያላችሁ፣ ሌላው ግን ለእናንተ መጠቀሚያነት ሳይታደስ ያርጅ፣ ያፍጅ፣ ይጃጅ ማለታችሁ ተገቢነት የለውም፡፡

ዲያቆን ዳንኤል የተሐድሶ ግብር ተጠቃሚ ሆነህ ሳለና ለማኅበርህ አመራሮችም ተሐድሶን እየተመኘህላቸው ተሐድሶ የሚለውን ስም መሸሽህና በሌላ ቃል ለመተካት መፈለግህ ግን ምን ይባላል? ተሐድሶ እኮ ሌላ አይደለም፤ ያው አንተ እንደ ገና መነሣት ያልኸው ነው፡፡ ስለዚህ በፅንሰ ሐሳቡ ከተግባባን ስያሜው ሊያጣላን አይገባም፡፡  
4.   ማኅበረ ቅዱሳን ፖለቲካዊ ንክኪ አለው
ሌላው ዳንኤል የጠቆመን ነገር ማኅበረ ቅዱሳን የፖለቲካ ንክኪ ያለው ማኅበር መሆኑን ነው፡፡ በተለያየ ጊዜ በማኅበሩ ላይ ከሚቀርቡት ክሶች መካከል አንዱ ማኅበሩ ሃይማኖት ለበስ ፖለቲካዊ ድርጅት ነው የሚል ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን በፖለቲካ ጉዳዮች ጣልቃ የሚገባ መሆኑ በመስከረም 12/2002 ዓ.ም. ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት ከተደረገው ስብሰባና ለማኅበሩ ከተሰጠው መንግሥታዊ ማስጠንቀቂያ መረዳት ይቻላል፡፡ ከክቡራን ሚኒስትሮች በተሰጠው መመሪያ ውስጥ የሚከተለውን እናገኛለን፣ “ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያንና ከመንግሥት እይታ ውጪ እየሄደ የሚታይ ቢሆንም ችግሩ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና በማኅበረ ቅዱሳን መካከል ነው በማለት ብቻ መታለፍ የለበትም፡፡

“ማኅበሩ ሃይማኖትንና ፖለቲካን እያጣመረ የሚሄድ መሆኑን የሚያስገነዝብ መረጃ የተገኘበት ስለሆነ በፈጸመውና በሚፈጽመው ስሕተት ሁሉ ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት ለሕግ አቅርቦ አስፈላጊውን ውሳኔ እንዲያገኝ ማድረግ ይቻል ነበር፤ ሆኖም ከአባቶቻችንና ጉዳዩ ከሚመለከተው ጋር በመሆን በጉዳዩ ዙሪያ መወያየት አስፈላጊ ነው የሚለውን ቀና አስተሳሰብ ይዘን ቀርበናል፡፡ … ማኅበሩ ማስተማር የነበረበት ስለ እምነቱ ነው፤ የፖለቲካ ማኅበር ነኝ የሚል ከሆነ የፖለቲካ የሥራ ፈቃድ ማውጣት አለበት፤ ሃይማኖትንና ፖለቲካን ሁለቱን እያጣቀሱ መሄድ ግን አይቻልም” (የስብሰባው ቃለ ጉባኤ)፡፡

በምርጫ 97 ጊዜም ማኅበሩ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጎን ተሰልፏል የሚል ነገር በሰፊው ይወራ እንደ ነበር የሚታወስ ነው፡፡ በመንግሥት በኩል “በአማራ እና በደቡብ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች ኢሕአዴግ ለደረሰበት ሽንፈት፣ ተቃዋሚዎች ላገኙት ድጋፍ ሚና ከነበራቸው አካሎች አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን ነው” የሚል አቋም መያዙንም፣ የመስፍን ነጋሽ ጽሑፍ ያስረዳል (addisnegeronline.com July 22,2011 at 7:00am)፡፡ በቅርቡም አቦይ ስብሐት ነጋ በፍትሕ ጋዜጣ ላይ ከተቃዋሚዎች ጋር ንክኪ አለው የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ከማኅበሩ መሥራች አባላት አንዱ የሆነው ዲያቆን ኤፍሬም እሸቴ፣ አደባባይ በተባለው ድረ ገጹ ላይ በለቀቀው ተከታታይ ጽሑፍ ውስጥ፣ ማኅበረ ቅዱሳንን የጠንሰሱት፣ በ1977 ዓ.ም. ለመንደር ምሥረታ ዘመቻ ወደየገጠሩ ሄደው የነበሩ የዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ተማሪዎች መሆናቸውን ጠቅሷል፤ እንዲህ በማለት:- “እነዚያ መንደር ሊመሠርቱ የወጡት ታላላቅ ወንድሞቻችን በየዛፉ ሥር፣ በየመንገዳቸው ጸሎተ ማርያም ማድረሳቸውን፣ ሲችሉም ተገናኝተው ቃለ እግዚአብሔር መስማታቸውን እንዳላስታጎሉ ሲናገሩ ሰምቻለሁ። እኛን ቃለ እግዚአብሔር ያስተማሩን የዚያ “መንደር መሥራች ትውልድአካላት የሆኑ ወንድሞች ናቸው። ወደ ዝዋይም የላኩን እነርሱ ናቸው። እኛ እና እነርሱ በአንድ ላይ ስንሆን ጊዜ በጋራ ‘ማ/ቅዱሳን’ ተባልን።” (hh://www.adebabay.com).

አባ ሰላማ የተሰኘ ድረ ገጽ ላይ በ27/11/2003 ዓ.ም. “በማኅበረ ቅዱሳን የተተከሉት የ‘አቡነ መንግሥቱ’ እና የ‘አቡነ መስፍን’ መናብርት ለጽድቅ ወይስ ለቄሳርነት?” በሚል ርእስ የወጣ ጽሑፍ፣ ይህን የኤፍሬምን ገለጻ መሠረት አድርጎ ትንታኔ ሰጥቷል፡፡ በዚሁ መሠረት ኤፍሬም ወንድሞች ሲል የጠራቸው፣ ፖለቲከኞች መሆናቸውና መንፈሳውያን የሆኑትንና እንደነኤፍሬም ያሉትን ይዘው ብላቴ ላይ በአንድነት ማኅበረ ቅዱሳን መሰኘታቸው እውነት ነው ይላል፡፡ እነዚህ ወንድሞች የማኅበሩን ዕቅድ ያወጡና በኅቡእ አመራር ሲሰጡ የነበሩ፣ አሁንም እየሰጡ ያሉ መሆናቸውን የሚያትተው ጽሑፉ፣ አብዛኞቹ የማኅበሩ አባላት ግን እነዚህ ወንድሞች ፖለቲካዊ አጀንዳ ይዘው ማኅበሩን ማቋቋመቸውንና እስካሁንም በኅቡእ እየመሩት መሆናቸውን መናገር እንደማይፈልጉ ገልጿል፡፡ መናገር የማይፈልጉበት ምክንያትም “ፖለቲካዊ ሥነ ፍጥረቱ እንዳይታወቅ በመሥጋት ብቻ አይደለም፡፡ ማኅበሩ በተፈጠረ ማግሥት ደርግ በመውደቁና ወያኔ ወደ ሥልጣን በመምጣቱ ማኅበሩ ተልእኮውን በኅቡእ ይዞ እንዲሰነብትና የወንድሞች ኅቡእ አመራር ሳይጋለጥ እንዲቆይ ለማድረግ ብላቴ ላይ በነእገሌ ተመሠረተ ብሎ መተረክ አስጠቂ ስለሚመስላቸውም ነው፡፡” ብሏል፡፡

ከዚህ ጽሑፍ ቀደም ብሎ ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ “ማኅበረ ቅዱሳን አሁን የሚጠራበትን የክርስትና ስም ወደ ዝዋይ ወርዶ ሳያገኝ ምን ዐይነት ስመ ተጸውዖ እንደ ነበረው አሁን ያሉት የማኅበሩ አባላት እንኳን ሊያውቁት አይችሉም፤ ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ግን የቀድሞ ስሙን ገና ከጅምሩ ያውቀዋል፤ በአንድ ወንዝ ላይ ተመሥርቶ የሁለተኛውን ፓትርያርክ (የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን) አባትነት ላለመቀበል፣ ዐላማቸውን ለማደናቀፍና ለመኮነን አጠቃላይ ጉባኤ በሚል ስያሜ የተቋቋመ ማኅበር ነበር” የሚል ምስክርነት ሰጥቷል፡፡ (ዜና ቤተ ክርስቲያን፣ መጋቢትና ሚያዝያ 1996)፡፡
ይኸው ጋዜጣ በነሐሴ 2003 ዕትም በርእሰ አንቀጹ ላይ ደግሞ “… ጎጠኛ ማኅበርስ አለን? የለም፤ ሊኖርም አይገባም፡፡ ምናልባት ቀደም ባሉት ዘመናት በነበረው የፖሊቲካ ዘይቤ ከቤተ ክርስቲያን ዓላማ ውጭ በቤተ ክርስቲያን ስም በጎጠኝነት የተመሠረተ ማኅበር ያለ ከሆነም ዛሬ የብሔር ብሔረሰቦች አንድነትና እኩልነት በሰፈነበት ወቅት ይኖራል ተብሎ በጭራሽ አይገመትም፤ ቢኖርም ሊሠራ አይችልም፡፡” በማለት የገለጸው ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ነው የሚል ግምት አለ፡፡
መምህር ካሕሣይ ገብረ እግዚአብሔር በዚሁ የነሐሴ 2003 ዓ.ም. ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ላይ፣ “የሌሊት ወፎችና የምናምንቴዎች ዘመን” በሚል ርእስ ባቀረቡት ጽሑፍ ውስጥ፣ በዘመናችን በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ በሁለት ተከፍለው የሚታዩ የሌሊት ወፍ ጠባይን የተላበሱ ወገኖች እንዳሉ ጠቁመው፣ የመጀመሪያዎቹ ያሏቸውን እንዲህ ሲሉ ገልጸዋቸዋል፤ “ዋና ዐላማቸው ዓለማዊ የፖለቲካ ሥራና ሥልጣን ለመያዝ ሆኖ፣ ቤተ ክርስቲያንዋን ለሽፋንና ለጊዜያዊ ዓላማቸው ማስፈጸሚያት ለመጠቀም የሚፈልጉ ወገኖች ናቸው፡፡ እነዚህን ወገኖች ዓላማቸውን ለመተግበር ያመቻቸው ዘንድ በቡድንና በመንፈሳዊ ማኅበራት ስም ነው የሚንቀሳቀሱት፡፡
“በዚህ ምድብ የሚካተቱት የሌሊት ወፎች ላይ ላዩን ላያቸው ከእነርሱ ወዲያ ለቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ የሌለ ይመስላሉ፤ ገዳማትን ይጐበኛሉ፤ በገንዘብና በቁሳቁስ ይረዳሉ፤ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም፣ የጻድቃንና የሰማዕታትን ስምና ገድል መጥራትና መናገር ያዘወትራሉ፤ በስማቸው የጽዋ ማኅበራት ያቋቁማሉ ወዘተ፡፡ የእነዚህ ወገኖች ሌላ መለያ ጠባይ ልክ እንደ ፈሪሳውያን ተረትና ታሪክ፣ ባህልና ወግ ከእምነትና ሃይማኖት ጋር ቀላቅለን ካልተጓዝን ባዮች መሆናቸው ነው፡፡ በቅርስ ድለላና ሽያጭ ሰፊ ሚና የሚጫወቱትም እነዚህ የቀበሮ ባሕታውያን ናቸው፡፡
“ብዙውን ጊዜ የእነዚህ ወገኖች ድብቅ ዐላማ ይፋ የሚወጣው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሞቅ በሚልባቸው ወቅቶች ነው፡፡ ያኔ ስለ ሐዋርያትና ስለ ጻድቃን ባወሩበት አፋቸው፣ ስለጾምና ስለምጽዋት በሰበኩበት አንደበታቸው ስለአሜሪካና አውሮፓ የዲሞክራሲ አራማጅ ግለሰቦች ታሪክ፣ ስለ ነጻ ገበያ በማስተማር ሕዝቡ እንዲቀበላቸው ይጥራሉ፤ ይህ ብቻ አይደለም እነርሱ የሚደግፏቸው ፖለቲከኞችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ያልደገፈ እንደ ኀጢአተኛ ይፈርጁታል፡፡ የዚች ቤተ ክርስቲያን የወደፊት ዕድገትም ከእነርሱ ማደግና ማነስ ጋር የተያያዘ መሆኑን ለማሳመን ይጥራሉ፡፡ ይህንን የፖለቲካ ዓላማቸውን የማይደግፍ አሊያም የሚነቅፍ ሲገኝም በግልጽም ሆነ በስውር ሊያጠፉት ይነሣሉ፡፡” መቼም ጸሐፊው ስም ባይጠቅሱም፣ እነዚህ የማንነት መገለጫዎች ማኅበረ ቅዱሳንን አይገልጹ ይሆን? 
ይሁን እንጂ የማኅበሩ ዋና ጸሓፊ ዲያቆን ሙሉጌታ “እውነቱን ለመናገር አብዛኞቹ የማኅበረ ቅዱሳን አባሎች የኢሕአዴግ ደጋፊና አባላት ናቸው” ይላል፡፡ ይህም በአንድ በኩል የመንግሥትን ድጋፍ ለማግኘት ታስቦ የቀረበ አነጋገር ይመስላል፡፡ በሌላ በኩል ግን አሁንም ማኅበሩ ከኢሕአዴግም ጋር ይሁን ከደርግ ቅሪቶች ወይም ከተቃዋሚዎች ጋር ከፖለቲካ ንክኪ ያልጸዳ መሆኑን ያሳያል፡፡

የዳንኤል ጽሑፍ “በማኅበሩ ውስጥ የግል ጋዜጦችን ማንበብ በስውር የተከለከለ ነው” ይላል፡፡ ይህም የሚነግረን ተጨማሪ ነገር አለ፡፡ የትምህርት ክፍሉ መደበኛ አገልጋዮች መረጃ ለማግኘት አስፈላጊነቱን አምነው የግል ጋዜጦችን የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው ቢጠይቁ፣ “ጽ/ቤቱ የግል ጋዜጦችን ገዝቶ በቢሮ ማምጣት ማኅበሩን ሊያስመታ ስለሚችል መቅረት አለበት ብሎ ይወስናል፡፡” ጽሕፈት ቤቱን እዚህ ሥጋት ውስጥ የጨመረውና እዚህ ውሳኔ ላይ ያደረሰው ነገር ከቶ ምን ይሆን? ብለን ብንጠይቅ ምላሹን ለማግኘት ብዙ ጥናትና ምርምር አያሻም፡፡ “ምን ያለበት ምን አይችልም” እንደሚባለው ማኅበሩ ካለው የተቃዋሚ ፖለቲካ ንክኪ አንጻር ራሱን ያላጠራበት ነገር ስላለ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በራሱ የሚተማመንና ምንም ንክኪ ከሌለው የግል ጋዜጦችን ፊት ለፊት አይታዩብኝ አይልም፡፡ የትምህርት ክፍሉም የፈለገው መረጃ ከሆነ የግል ጋዜጦችን ብቻ ሳይሆን በመንግሥት በኩል የሚወጡ ጋዜጦችንና ሌሎች መረጃዎችን የሚያገኝበት መንገድ እንዲመቻች መጠየቅ ነበረበት፡፡ ስለዚህ ጥያቄያቸው፣ ሰዎቹ ልባቸው በተቃዋሚዎች ፖለቲካ ታዛ ውስጥ ስላለ የጠየቁት የግል ጋዜጦችን ነው ወደሚል ድምዳሜ ይወስዳል፡፡

ከላይ ከቀረቡት መረጃዎች አንጻር ዳንኤልን ያስቆጣው በማኅበሩ ደንብ መሠረት የማኅበሩ አባል መሆን የሚቻለው በሃይማኖታዊ አቋም እንጂ በፖለቲካዊ አቋም አይደለም የሚለው የማኅበሩ ደንብ በመጣሱ ብቻ ነው ማለት ያስቸግራል፡፡ ቀድሞ በደርግ ርዝራዥነት በኋላም በተቃዋሚ ደጋፊነት ሲታማ የነበረው ማኅበር አሁን በዋና ጸሓፊው በኩል የኢሕአዴግ ደጋፊና አባል ሆነ መባሉ ሳይሆን አይቀርም፡፡

ይቀጥላል

መምህር በቃሉ
ከ5 ኪሎ

13 comments:

 1. For your surprising!

  I have been thinking about, 'why Daniel sent his message to Dejeselam blog if he doesn't know the owner of the blog'?

  Please study it in detail.

  ReplyDelete
 2. መምህር በቃሉ የጽሁፍህ አድናቂ ነኝ። ጽሁፍህ ወዝ አለው። ቃናው የምር እንጂ በእንቶፈንቶ ላይ የቆመ አይደለም። ነገሮችን ያጠናል፤ እንጂ በድምዳሜ አያያቸውም። እየነቀሰና የተሸፈነውን እየገለጠ እንካችሁ፤ አንብቡና ፍርድ ስጡ! እያለ አንባቢን ይጠይቃል። የጽሁፍህን ተቃዋሚዎች የምች ያህል እንደሚመታቸው የሚሰጡት ጸያፍና የንዴት አስተያየቶች በቂ ማረጋገጫዎች ናቸው። ለመሳደብ ክፍት የሆነ ግን ወግ ያለው መልስ መስጠት የማይችል አፋቸውን የሚዘጋ ነው። ሌሎችን ደግሞ የሚያነቃ፤ እንዲያ ጣራ ላይ የሰቀልነው ማኅበር ለካስ የሚበረበር ጉድ አለው እንዲሉ ያደርጋልና በርታ ቀጥልበት።

  ReplyDelete
 3. yedha gulbet begeleba yalkal alu, le ato Bekalu yismamal yedha gulbet begeleba yalkal alu, le ato Bekalu yismamal

  ReplyDelete
 4. weye tehadeso tegebe belachehol, mewedekeyachehu kerbe new gede yelem yehune yetebalew hulu yefetemal endetebale yenantem endezaw new!

  ReplyDelete
 5. sigemere eko eyesusin yemayikebeli mahiberi yepoletica mahiberi engi lela min lihoni yichilali

  ReplyDelete
 6. memihir bekalu kale hiwoti yasemalin!

  ReplyDelete
 7. ስታስጠሉ ይሄ ድረ ገፅ በራሱ የማን ነው የማኅበረ ቅዱሳን አይደለምን
  ምዕመኑ ተሐድሶ ኣለ ብሎ እንዲያምን ሆን ተብሎ የታቀደ ነው
  ደጀ ሰላም፣ኣባ ሰላማ፤ማኅበረ ቅዱሳን ያው ናቹ ለማይሞላው ሆዳቹ፤ለማታገኙት ክብር
  የክርስቲያኖችን ህብረት ትበጠብጣላቹ የይሁዳ ወንድሞች።

  ReplyDelete
 8. sle daniel tkklegnanet meche tenagreh tawkna

  ReplyDelete
 9. የዳንኤል አድናቂዎች ሆይ! ቢያንስ የተጻፈውን በሚመዛዝን ኅሊና አንብቡት እንጂ፡፡ እንዲያው ለመሆኑ ሰውን ከማምለክ የምትወጡት መቼ ይሆን? ሰውን በደፈናው ከምትጸርፉ ሐሳቡን ብትመዝኑ ወደተሻለ ግንዛቤ ትመጡ ነበር፡፡ እናንተ ግን የዳንኤል ተከታዮች ስለሆናችሁ ከዕውር መሪያችሁ ዳንኤል ክብረት ጋር ተያይዛችሁ ወደገደል መግባት የመረጣችሁ ነው የሚመስለው፡፡ እግዚአብሔር ያብርህ አዕይንተ አልባቢክሙ (እግዚአብሔር የልቡናችሁን ዐይኖች ያብራ)

  ReplyDelete
 10. Anegagerhe manenethen selegeltsew Aygermem menm betawera..

  ReplyDelete
 11. በአባቶቻችን ስም የምትነግድ አንተ ማነህ? የማህበሩን ውድቀትስ የምትመኝ፣ በጎ ጎኑን ሳይሆን ደካማ ጎኑን ነቅሰህ የምታወጣ ምንድን ነህ? ለምንስ ማንነትህን ደብቀህ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን ተቆርቋሪ መስለህ ቀረብክ? እውነተኛ ማንነትህንስ ለመግለጥ ምን አሸማቀቀህ? "የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል"፡፡
  ክፍለ ማርቆስ፣ ከደብረ ማርቆስ

  ReplyDelete
 12. እባካችሁ ስለፈጣሪ ብላችሁ እኛን አታወዛግቡን ለእንት ጥቅምና ዝና ስንቱ ክርስቲያን ተወዛገበ፡፡ በቃ ተውን እንደአባቶቻችን በልምድ እንመለለስ ፡፡ በነሱ ውስጥ እኮ ጠንካራ እምነትና ፍቅር ነበር እሱ ብቻ ይበቃናል፡፡ ተውን ተውን ተውን ፡፡

  ReplyDelete