Monday, September 12, 2011

በንጉሥ አዋጅ የገቡ ባዕድ አምልኮዎች

በንጉሥ አዋጅ የገቡ ባዕድ አምልኮዎች
ለማርያም ስእልና ለመስቀለኛ እንጨት ያልሰገደ ይገደል[የዘራ ያዕቆብ ሸንጎ ዘደብረ ብርሃን]
የሃይማኖታችን መሠረት የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ ደጋግሞ የሚያስጠነቅቀን ሌሎች አማልክትን እናዳናመልክ ነው። ባዕድ የሚለው ቃል ሌላ፤ ወይም የተለየ የሚል ትርጉም አለው። ሐሳቡ ከእግዚአብሔር ሌላ መመለክ የሚገባው ወይም ሊመለክ የሚችል ምንም ነገር ስሌለ ባዕድ ከተባለ ከእግዚአብሔር ውጭ ከእግዚአብሔር ሌላ ማለት ነው። በዚህ ቃል ውስጥ ማንኛውም ፍጥረት ሰውም ሆነ መላክ እንሥሳም ይጠቃለላል። በእግዚአብሔር የተፈጠረ ሁሉ ምንም ዓይነት ኃይል ይኑረው ያው ፍጡር ነውና ሊመለክ አይችልም።
አማላክት ዓይነታቸው ብዙ ነው፤ ዘርዝረን ልንወስናቸው አንችልም መጽሐፍ ቅዱስ እገሌና እገሌ ሳይል የተቀረጸ ምስልን እና የማንኛውንም ስእል ሁሉንም ጠቅለል አድርጎ እንዲህ ሲል ያስጠነቅቃል።

ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ። በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም ዘጸ 20፥3-5።
በላይ በሰማይ ካለው ማለቱ ጸሐይ ጨረቃና ከዋክብት እንዲሁም መላእክትን ሁሉ የሚያጠቃልል ቃል ነው። በታች በምድር ከለው የሚለው ደግሞ ሰውና እንስሳ ዛፍና ተራራ፣ ውሃና እሳት የመሳሰለው ሁሉ ማለት ነው። ከምድር ምበታች በውሃ ውስጥ ካለው ማለቱ አሳ፣ ጉማሬ አዞ የመሳሰለው የውሃ ውስጥ ተንቀሳቃች ፍጥረት ሁሉ ማለት ነው።
የማናቸውንም ምሳሌ የሚለው ቃል ሊሰመርበት ይገባል፤ ከመላእክት ወይም ከሰው በቀር የሚል አንድምታ እዚህ ውስጥ አልተጨመረም። የማናቸውንም ምሳሌ ካለ የመላእክትንም ሆነ የጻድቃንን ስእል ያጠቃልላል። የተቀረጸውን ምስል የሚለው ቃል ከድንጋይ፣ ከብረት፣ ከወርቅ፣ ከብርና ከእንጨት ተቀርጾ የሚቆም ሐውልት ማለት ነው። የሰውንም ሆነ የመላክን ምስል ከተለያዩ ማዕድናት በባለ ሙያዎች አሠርቶ ማቆም እና ለዚያ ስግደት ማቅረብ አጸያፊ የሆነ የከናናውያን ነውር ነው።
አትስገድላቸው አታምልካቻውም
ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ሰዎችን ለማስተማር፣ ታሪክን በስእልና በሐዋልት ለማስታወስ፣ ተብሎ ስእሎችን እና ሐውልቶችን እንደ መሳሪያ ይጠቀሙ እንደነበር የጥንት የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል። በካታኮንፕ የምድር ቤት ውስጥ እንደዚህ ዓይነት የትምህርት ዘዴዎች ተገኝተዋል። ስደትና መከራ በበዛበት ከአንደኛው መቶ እስከ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች በዋሻና በዱር እየተሰደዱ ይኖሩ ነበር። የክርስቶስን ልደት፣ ታሪክ፣ ሞትና ትንሳኤ፣ የሰማዕታትን ምስክርነት፣ በእሳት ውስጥ እንዴት እንዳለፉ በመጋዝ እንዴት እንደተሰነጠቁ፣ በእምነታቸው ጽናት ድል በመንሳታቸው ያገኙትን አክሊል በስእል እየቀረጹ ያስታውሱትና ይማሩት ነበር። ይህ ታሪክን በስእል የማስተላለፍ ዘዴ እንደጥሩ ሥራ ታይቶ ብዙዎች ይጠቀሙበታል። እነዚያ የጥንት ክርስቲያኖች ትምህርትን በስእል አደረጉ እንጂ በጨርቅ ሸፍነው ግን አይሰግዱለትም ነበር። ወደ ስእልም አይጸልዩም ነበር።
የኪሩቤል ስእል ሰሎሞን ባሰራው ቤተ መቅደስና በራሱ ቤት ግንብ ዙሪያ ተስሎ ነበር። ይህም የእግዚአብሔር ሠራዊት በእስራኤል ሕዝብ ዙሪያ ለጥበቃ መስፈራቸውን ለማመልከት ተብሎ የተደረገ እንጂ በእግዚአብሔር ቦታ እነሱን ተክቶ ለመስገድ ወደ እነርሱም ለመጸለይ አይደለም። ይህም ውስን የሆነ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነው።
በቤቱም ግንብ ሁሉ ዙሪያ በውስጥና በውጭ የኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸ። የቤቱንም ወለል በውስጥና በውጭ በወርቅ ለበጠ። ለቅዱስተ ቅዱሳኑም መግቢያ ከወይራ እንጨት ደጆች ሠራ፤ መድረኩንና መቃኖቹን ደፉንም አምስት ማዕዘን አደረገ። ሁለቱንም ደጆች ከወይራ እንጨት ሠራ፤ የኪሩቤልንና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸባቸው፥ በወርቅም ለበጣቸው፤ ኪሩቤልናና የዘንባባውን ዛፍ በወርቅ ለበጣቸው 1ነገ 6፥29-32
አትስገዱላቸው፣ አታምልኳቸውም ተብሏልና። በእስራኤል የሚታወቀው የኪሩቤል ስእል የሚሰገድለትና የሚመለክ አልነበረም። በጌታ ከታዘዘው ምስጢራዊ የኪሩቤል ስእል ሌላ በቤተ መቅደሱ ውስጥ በጨርቅ የተሸፈነ የሰውና የመላእክት ስእል፣ የሚሰገድለትና የሚመለክ በብሉይ ኪዳን ታሪክ አናገኝም።
በቤተ ክርስቲያን ታሪክም ከጌታና ከሐዋርያቱ ጋር የተያያዙ ትምህርታዊ ስእሎች ትምህርት ሲሰጥባቸው ኖረዋል። ዛሬም በኢትዮጵያ በቤተ ክርስቲያናችን በውስጠኛው ቤት ዙሪያ የጌታን፣ የሐዋርያትን፣ የሰማእታትን፣ ገድል የሚያስታውሱ ስእሎች አሉ የሚያነቡም ሆነ የማያነቡ ሰዎች ሲጎበኛቸው ትምህርት ቀስሞ ይወጣል። የጥንት የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች ታሪክን ለመዘከር ይህን አደረጉ እንጂ ስግደት እና አምልኮ ለነርሱ ለማቅረብ ያደረጉት አይደለም። እነዚህ ስእሎች ጥሩ እንክባካቤ እየተደረገላቸው ቢቆዩ ለሚመጣው ትውልድ የታሪክ መማሪያ ይሆናሉ።
ነገር ግን ምንም ትምህርት ሰጪ ያልሆኑ ባዶ ምስል ብቻ የሆኑ፣ አምልኮና ስግደት የሚደረግላቸው ባዕድ ነገሮች አሁንም አሉ። በዚህ ዘመን ስእሎቹ በመጻህፍትና በቤተ ክርስቲያን ግድግዳ ዙሪያ ለትምህርትነት መሳላቸው ቀርቶ በዱባይና በቻይና ኩባንያዎች በጅምላ እየታተሙ፣ ገብያ ላይ ይውላሉ። መልከ ቀና የሆነችውን ፈረንጅ ማርያም ናት ይሏታል። የጣሊያን ወታደር አለባበስ የለበሰውን ታጣቂ፣ ሚካኤል ነው ይሉታል። አርሴማ የምትባለው ግን ኢትዮጵያዊቱን እትየ መነንን ትመስላለች። ስእሎች ገብያ ላይ ይገኛሉ። ያሁኑ ትውልድ እነዚህን ስእሎች ከገብያ ገዝቶ በምኝታ ቤቱ ወይም በጸሎት ቤቱ በመደርደር በጨርቅ ሸፍኖ ይሰግድላቸዋል፣ ወደ እነርሱም ይጸልያል። ባዕድ አምልኮ በየቤቱ ሆኗል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ በማለት ያስጠነቅቃል።
በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን የተቀረጸ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው ርጉም ይሁን ዘዳ 27፥15።
እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክ ከቶ አላያችሁምና እጅግ ተጠንቀቁ፤
እንዳትረክሱ፥ የተቀረጸውን ምስል የማናቸውንም ነገር ምሳሌ፥ በወንድ ወይም በሴት መልክ የተሠራውን፥ በምድር ላይ ያለውን የእንስሳን ሁሉ ምሳሌ፥ በሰማይም በታች የሚበርረውን የወፍን ሁሉ ምሳሌ፥ በምድርም ላይ የሚሽከረከረውን ሁሉ ምሳሌ፥ ከምድርም በታች በውኃ ውስጥ የሚኖረውን የዓሣን ሁሉ ምሳሌ እንዳታደርጉ፥ ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አንሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር ከሰማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕዛብ ሁሉ የሰጣቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንና የሰማይን ሠራዊት ሁሉ ባየህ ጊዜ፥ ሰግደህላቸው አምልከሃቸውም እንዳትስት ተጠንቀቅ ዘዳ 4፥15-19
መልክ ከቶ አላያችሁም
የእግዚአብሔርንም ሆነ የመላእክትን መልክ ያየ ማንም የለም፤ ይህን ይመስላሉ ብሎ ወስኖ መናገር አይቻልም። መንፈስ የሆነውን አምላክ ይህን ይመስላል ብሎ መስሎ መግለጥ እጅግ ከባድ ድፍረት ነው። እግዚአብሔር መንፈስ ነው፣ የሚሰገድለትም በመንፈስ እና በእውነት ነው። መልኩን አካሉን ለመግለጥ መሞከር ትልቅ ንቀት ነው። ኢየሱስን በሥጋ ስለመጣ ለትምህርታችን በስእል ልንገልጠው እንችላለን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስን በስእል ቀርጾ ለዚያ መስገድ ከቃሉ ውጭ ስለሆነ ባዕድ ነገር ነው።
በሴት ውይም በወንድ መልክ የተሠራውን
የመላእክትም ይሁን የጻዳቃን በሴት ወይም በውንድ መልክ የተሠራን የባለሙያ ውጤት ለጸሎትና ለስግደት ማዋል አይገባም። ለስእል መስገድ እንደሚገባ የሚናገር የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል አንድም ቦታ አናገኝም። የባዕድ አምልኮ አስተማሪዎች ግን የጸጋና የክብር የአምልኮ በሚባል አንድምታ ባዕድ አምልኮን አስፋፍተዋል። ለስ እል የምናቀርበው ስግደታችን የጸጋ ነው ይሉናል። ወደ ስእል የሚጸለየው ጸሎትስ የጸጋ ነው ወይስ የምን? እግዚአብሔር የተናገረውን ቀጥታ በመቀበል እርሱን በመታዘዝ ፈንታ የጸጋ፣ የክብር በሚል ፈሊጥ እውነትን ለመሸፋፈን ይጥራሉ። ያስዝናል።
ለስእል መስገድ እና ወደ ስእል መጸለይ የተጀመረው በዘራ ያዕቆብ ዘመን ነው ከዚያ በፊት የነበረችው በተ ክርስቲያናችን አንዳድ ችግሮች ቢኖሩባትም ንጽሕ አምልኮ ለአማላክችን ታቀርብ ነበር። ወደ ሩቅ ምስራቅ ለጉብኝት ሄዶ ወደ ሀገሩ ሲመለስ የሰማይ ንግስት ተብላ የምትታወቀውን የምሥራቃውያን ሴት ታኦት ምስሏን ይዞ ተመልሷል። ያችን ስእልም ማርያም ናት በማለት ስግደት እንዲደረግላት አዋጅ አዋጣ። አንሰግድም ያሉት ተገደሉ፣ ሌሎች በሚከተለው እርግማን ተረገሙ
ዘኢሰገደ ለስእልኪ አስሪጾ ምማኤ በስጋሁ ወበ ነፍሱ ኢይርከብ ትንሣኤ
ትርጉም -ዝቅ ብሎ ለስእልሽ ያልሰገደ ቢኖር በሥጋውና በነፍሱ ትንሣኤ አያግኝ ማለት ነው። [መልካ ስእል] ይህ እርግማን እስካሁን ድረስ በማንኛውም የቤተ ክርስቲያናችን የጥዋት ጸሎት ሁልጊዜ የሚጸለይ ነው። በክርስቶስ ደም ከርግማን ነጻ የወጣውን የሐዲስ ኪዳን ትውልድ ለሰው ሙያ ካልሰገደ በሥጋውና በነፍሱ ትንሳኤ አያግኝ ብሎ መራገም እብደት ነው።
ወቅድመ ስእላ ስግዱ ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውኡ ቁሙ ወአጽምኡ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምኡ
ትርጉም- ማርያምን በምስጋና ቃል ጥሩ፣ በስሏ ፊት ስገዱ፣ የማርያምን ታምር ትሰሙ ዘንድ ቁሙ ማለት ነው [ሰዓታት]። ለማርያም ስእል መስገድ እንዳለብን የሚናገር የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ግን አናገኝም። ስእሉም የማርያም ስለመሆኑ የሚያረጋግጥልን ምንም መረጃ የለም።
ቀዊምየ ቅድመ ስእልከ ሶበ አወትር ስኢለ በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምአኒ ቃለ
ትርጉም- በስእልህ ፊት ቆሜ ልመናን ባዘወተርሁ ጊዜ እነሆኝ በማለት ፈጥነህ ቃልህን አሰማኝ [መልካ ሚካኤል] ሁልጊዜ የሚካኤል በ12 የሚጸለይ። ይህም የጸጋ ነው? ልመናን ማዘውተር ያለብን በእግዚአብሔር ፊት ወይስ በሚካኤል ስእል ፊት? እስኪ አስረዱን፡ የሚካኤል ስእል የሰው ሥራ አይደለምን? የስእል አምልኮ በቤተ ክርስቲያን እንዲደረግ የተወሰነው በዘራ ያዕቆብ እንደሆነ ታሪክ ይነግረናል። ሐዋርያትም ሆኑ የሃይማኖታችን አምዶች ሦስት መቶ አስራ ስምንቱ አባቶች ጸሎተ ሃይማኖት ተብሎ የሚታወቀውን የእምነት መግለጫ ሲያወጡ ስለ ስእል የተናገሩት የለም። የዘራ ያዕቆብ ትዛዝ የንጉሥ አዋጅ እንጂ ሃይማኖታችን አይደለም፣ ስለዚህ ወደ ጥንታዊት ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ወደ ሆነች ወደ አባቶቻችን እምነት እንመለስ እንላለን።
ብዙ የምንገልጣቸው ነገሮች አሉ። ቤተ ክርስቲያን እራሷን ትመርምር እራሷን ታርም፣ እግዚአብሔርን ይቅርታ ትጠይቅ፣ በጋራ ሆነን ንስሐ እንግባ። አገርና ሕዝብን አንበድል። ትውልድን አንራገም። እውነቱን እናስተምር እንደዚህ ብናደርግ ከጥፋት እንድናለን። ስማችንን እያጠፋችሁ ብታሳድዱን ይብስብን እንደሆነ እንጂ ሌላ ምን ይመጣል? ሚስማር ሲመቱት ይጠብቃል፣ ወርቅ በእሳት ሲገባ ይጠራል፣ አሁን እየሆነ ያለውም ይኸው ነው።
ለእሉ ክሌቱ ፍጡራን ስብሐተ ፈጣሪ ይደልዎሙ እስመ ተአረዩ በክብሮሙ
ትርጉም ለነዚህ ለሁለቱ ፍጡራን ለማርያምና ለመስቀል የፈጣሪ ምስጋና [አምልኮ] ይገባቸዋል በክብር ከፈጣሪ እኩል ሆነዋልና [መስተብቍዕ ዘመስቀል]ይቀጥላል
ዲ ሉሌ ነኝ
Reply
Forward

9 comments:

 1. mekonetsatsel tegebi aydelem

  ReplyDelete
 2. Aba Selama or Dn Lule?
  1) Though your observation is good, you have not dajested the real history of Zerayacob. E.g.
  "ወደ ሩቅ ምስራቅ ለጉብኝት ሄዶ ወደ ሀገሩ ሲመለስ የሰማይ ንግስት ተብላ የምትታወቀውን የምሥራቃውያን ሴት ታኦት ምስሏን ይዞ ተመልሷል። ያችን ስእልም ማርያም ናት በማለት ስግደት እንዲደረግላት አዋጅ አዋጣ። "
  2) when you establish your observations, please go to into the depth of constructive solutions, also. I mean you are trying to do so but it must be with detail and factual solutions.

  ReplyDelete
 3. አብዬ! የኦሪቱ የታቦት ላይ ኪሩብ ዛሬ እኮ በኦርቶዶክሷ ቤ/ክ መቅደስ ውስጥ የለም። እሱን እንሰራለን እንዳይሉ ትተውታል። የሌለውን ለመስራት ግን እሱን በመረጃነት ያቀርቡታል።ዛሬ በየጎዳናው የሚሸጡት ስዕሎች የሰዓሊው ችሎታ የተንጸባረቀባቸው፤ እውቀቱ የፈቀደውን ያህል የሚስለው እንጂ ከህያዋን ዓለም ያገኘው አይደለም። ስዕል መሳይ ታሪካዊ እንጂ ሃይማኖታዊ አይደለም። የሚያረጅ፤ የሚቀደድ፤የማይሰማ የማይናገር (ይሆናል ከተባለም ከአጋንንት እንጂ ከመንፈስ ቅዱስ የማይሆን) «የብርሃንን መልዓክ ሊመስል ራሱን ይለውጣል» እንዳለው ጳውሎስ። ኪሩብ ዛሬ የለም ታዲያ ስዕልን ከየት አመጡት?

  ReplyDelete
 4. What about RAEYE YOHANNES? Doesn't it talk about Virgin Marry??
  We orthodox Tewahido honor, respect, and celebrate the Virgin Marry mentioned in RAEYE YOHANNES. We have nothing to do with your lady from the East who was nmed "nigiste semay"
  ANTE FETIREH AWERAH. EGNA GIN BEMETSEHAF KIDUS BEYOHANNES YETENEGEREN INIKEBELALEN INAMINALEN

  You know what? You are simply ignorant and manipulative!! (KEBATARI!!). By the way how much do you make from protestants?

  ReplyDelete
 5. Yihen hulu gud yawqalu Ye egna ager amagnoch? Yemiyatefuts eyawequ new?

  ReplyDelete
 6. የዮሐንስ ራዕይን የጠቀስከው ሰው ለስዕል ስግደት ይገባል የሚል ጥቅስ የቱ ጋር እንዳለ እባክህን ላንተ የተገለጸልህን ራዕይ ንገረን!! የማርያም ስዕል ራዕየ ዮሐንስ ውስጥ እንዳለ መገለጹን ብፈልግ ባስፈልግ አጣሁ። ራዕይ12 ላይ የተጠቀሰችውን ሴት ማርያም ናት የምትል ከሆነም «...እርሷም ነፍሰጡር ነበረች፤ ልትወልድ ስትል ምጥ ይዟት ተጨንቃ ጮኸች» ሲል ማርያም ክርስቶስን ለመውለድ ምጥና ጭንቅ ይዟት ነበር ማለትህ ነው? ከየት ያገኘኸው ትምህርት ነው? ያልተጻፈ ማንበብ መቼም ልማዳችሁ ነው።(ሎቱ ስብሐት፤ ሰጊድ ወአኮቶት ለባህቲቱ ይደሉ)

  ReplyDelete
 7. ' Dn' Lule, r u Orthodox? I doubt. U r outlouding the suspection that this web portal is prepared by the tehadiso people. Just, go to church, sit and learn. U have not yet started knowing the words of God! May God give u a repenting heart!

  ReplyDelete