Friday, September 16, 2011

ዋናና ወቅታዊው ጉዳይ


¨c’< ›g“ò
(Ÿ›^Ç ¡/Ÿ}T)
በተለያዩ ጊዜያት አገርን አንዳንዴም ቤተ ክርስቲያንን የሚመለከትና መፍትሔ የሚሻ  አንገብጋቢ ወይም ወቅታዊ ጉዳይ ይነሳል፡፡ በወቅቱ ለሚነሳ ጉዳይ በቅድሚያ ትክክለኛ ግንዛቤ ማግኘት የመፍትሔ ዋና አካል ነው፡፡ የሚቀጥለው በተገኘው ግንዛቤ መሠረት ትክክለኛውን መፍትሔ መስጠት ነው፡፡
የአንድን በሽተኛ ሕመም ሳያውቅ ሐኪም መድኃኒት አያዝም፤ በሽታውን ከሕመሙ ሊፈውስ የሚችለው ሕመሙን ከተረዳ በኋላ ሐኪሙ የሚያዘው መድኃኒት ነው፡፡ በግምት መፍትሔ ይሆናሉ ብሎ አንድ በሽተኛ የሚወስዳቸው መድኃኒቶች ግን በሽተኛውን የባሰ የጤንነት ችግር ውስጥ ከመክተት በቀር ሌላ ፋይዳ የላቸውም፡፡

የወቅታዊ ችግርም መፍትሔ በችግሩ ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ትክክለኛ የወቅታዊው ጉዳይ ግንዛቤ ከሌለ ለችግሩ ተገቢውን መፍትሔ መስጠት ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ትክክለኛ የወቅታዊ ጉዳይ ግንዛቤ ተገኝቶ ተገቢው መፍትሔ ከተሰጠ የሚገኘው ፋይዳ እጅግ ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ወቅታዊው ጉዳይ በፍጹም በቸልታ መታለፍ የለትም፡፡ በቸልታ ከታለፈ ሌሎች ችግሮችን በመውለድ ትውልድን ለተወሳሰቡና ለተባባሱ ችግሮች ይዳርጋል፡፡በቂ ግንዛቤ ያልተያዘበት ተገቢ ትኩረትም ያልተሰጠውና መፍትሔም ያላገኘ ወቅታዊ ጉዳይ ከሁሉም በላይ ለአገር የሚጠቅሙ አዋቂ ሰዎችን ያሳጣል፡፡ያለውና ቀጣዩ ትውልድም ማግኘት የሚችለውን እውቀትና ልምድ ያጣል፤ ተገቢውን ግንዛቤ ባላገኘና ተገቢውም መፍትሔ ላልተሰጣቸው ችግሮች ጣጣ ይዳርጋል፡፡ ስለዚህም በዚህ ባለንበት ወቅት መፍትሔ የሚሻ ወቅታዊው ጉዳይ ምን እንደሆነ በመለየት በቂ ግንዛቤ መጨበጥና መፍትሔውን መፈለግ ግዴታ ነው፡፡ይህ ግንዛቤና መፍትሔ የሚሻ የጊዜው አንገብጋቢ ጉዳይ ምንድነው) የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ነዋ !
 በአሁኑ ጊዜ የቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ የሞቀ ክርክር የሚደረግበት ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳይ እየሆነ መጥቷል፡፡እኔ ተገቢው ግንዛቤና መፍትሔ እንዲገኝ ይችን አጭር ጽሑፍ አቀርባለሁ፡፡ቤተ ክርስቲያን በየጊዜው የተለያዩ ችግሮች አጋጥመዋታል፤ ያጋጥሟታልም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ያጋጠሙዋትን ችግሮች አስተውላ ለችግሮችዋ ተገቢውን መፍትሔ ስትሰጥ መንፈሳዊ ብቃቷና እድገትዋ እንዲሁም ተደማጭነቷ ይጨምራል፡፡ ለዚህ የመጀመሪያዋን የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርገን መመልከት እንችላለን፡፡ ሕግ አጥባቂዎች ወደ አንጾኪያ ወርደው ባስነሱት ሁከት የኢየሩሳሌም ጉባኤ የተነሳውን ክርክር በማዳመጥ ተገቢውን መፍትሔ መስጠት በመቻሉና ውሳኔውንም በደብዳቤ ለአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን በመላኩ አበረታች ነገር እንደተገኘ በግብረ ሐዋርያት ምዕራፍ 15 ቁጥር 31 እና 32 ተጽፎ ይገኛል፡፡ ከዚያም በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለገቡ ኑፋቄዎችና ችግሮች የተለያዩ መልእክቶችን በመጻፍ የቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲጠበቅና የወንጌል ሥራም የበለጠ እንዲስፋፋ ሐዋርያት ተገቢውን ተግባር አከናውነዋል፡፡ በመስቀል ጦርነት ወቅት ደግሞ ቤተ ክርስቲያን በወቅቱ ለተፈጠረው ችግር ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የሚቃረን መፍትሔ ለመስጠት በመሞከርዋ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ኢየሩሳሌምን እንኳ ሳይቀር እስኪይዙ ድረስ ትልቅ ድል አግኝተዋል፡፡ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ቃል÷በጸሎትና በእግዚአብሔር ረድኤት የሚያጋጥሙዋትን ችግሮች ድል እያደረገች ጉዞዋን የምትቀጥል አካል መሆንዋ የታወቀ ነው፡፡ በወቅቱ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ግለትዋ ቀዝቅዞ ስለነበር ያጋጠማትን ወራሪ ጠላት ከላይ በተጠቀሰው መንፈሳዊ መሣሪያ በመዋጋት ፈንታ ተገፋፍታ ወደ ጦርነት ገባች፡፡«ሰይፍን የሚያነሱ በሰይፍ ይጠፋሉ» እያለች ወደ ጦርነት በመግባትዋ በድል ፈንታ ሽንፈት አጋጠማት&ኢየሩሳሌምን'ሰሜን አፍሪካንና ሌሎችንም ይዞታዎችዋን ተነጠቀች፡፡ወደኋላ ሄጄ የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ ማንሳት የፈለግሁት ወቅታዊ ለሆነው የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የጋራ ግንዛቤ ይዘን መፍትሔ እንድንፈልግ ለማሳሰብ ነው፡፡    
በአገራችን ‹‹ተሐድሶ›› የሚለው ሐሳብ ቀደም ብሎ ከ15ኛው ምዕተ ዓመት ጀምሮ ሲነሳ ነበረ!  ዛሬም ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ሆኖ ቀርቧል፡፡አንዳንዶች «በጥናት» ደረስንበት እንደሚሉት ሳይሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሐድሶ ሓሳብ የተነሳው ከውሮጳውያን ተሐድሶም ሠላሳና ዐርባ ዓመታት ቀድሞ እንደሆነ የሚናገሩ ምሁራን አሉ፡፡ እንግዲህ በዚህ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በቂ ግንዛቤ መጨበጥና አግባብ ያለው መፍትሔም መስጠት በቤተ ክርስቲያን ላይ የተጣለና ቸል የማይባል የጊዜው  ግዴታ ሆል፡፡ ብዙዎቹ የቤተ ክርስቲያን ሰዎችና አንዳንድም አለቆች ስለ ተሐድሶ የተVላ ግንዛቤ የሌላቸው መሆኑ እጅግ የከፋ አደጋ ነው፡፡ ተገቢ ያልሆነ የእውር ድንብር ምላሽ ለመስጠት መሞከር ቤተ ክርስቲያንን ትልቅ አደጋ ላይ ይጥላታል፡፡ የተሐድሶን ጽንስ ሓሳብ በጭፍን መቃወም ሆነ መደገፍ አግባብ አይደለም፡፡
ቤተ ክርስቲያን የተሐድሶን ሓሳብ የሚያነሱትን ሁሉ በደፈናው ስም ማጥፋት ማሳደድና ከቤተ ክርስቲያን ማባረር፣ አገልግሎት መከልከልና መድረክ መንፈግ መፍትሔ አይሆናትም፤ ሆኖአትም አያውቅም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ካለፉት ድክመቶችዋ መማር አለባት፡፡ እኔ በዚህ በአጭር ጽሑፍ የቤተ ክርስቲያን አባላት ግንዛቤ ሊጨብጡ ይገባቸዋል በምላቸው ‹‹ሃይማኖት፣ ቤተ ክርስቲያንና ተሐድሶ›› በሚሉት ቃላት ላይ አጭር ሓሳብ ለመስጠት እሞክራለሁ፡፡ተገቢውን መፍትሔ ለመሻት እነዚህ ቃላት የግድ ተገቢውን ግንዛቤ ማግኘት አለባቸው፡፡የእነዚህ መንፈሳዊ ቃላት ግንዛቤ አለማግኘታቸው ከላይ እንደጠቀስኩት ትክክለኛውን መፍትሔ ለመስጠት እንቅፋት ይሆናል፡፡ እነዚህን መንፈሳዊ ቃላት አስመልክቶ ያለው ዋና ችግር ሃይማኖትንና ቤተ ክርስቲያንን አንድ አድርጎ መመልከት ነው፡፡ ሃይማኖትና ቤተ ክርስቲያን ግንኙነት ቢኖራቸውም በፍጹም አንድ አይደሉም፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለሃይማኖት፣ ሃይማኖትም ለቤተ ክርስቲያን ተመሳሳይ አይደሉምና በተለዋዋጭነት አያገለግሉም፡፡ እንግዲህ የሚታየውን የግንዛቤ ችግር ለማስወገድ የሁለቱን ምንነትና ግንኙነት በግልጽ መረዳት ያስፈልጋል፡፡
የክርስትና ሃይማኖት ሰው አውጥቶና አውርዶ የቀመራት ወይም የሚቀምራት ሓሳብ ወይም ፍልስፍና አይደለችም፡፡ የክርስትና ሃይማኖት ከራሱ ከልዑል እግዚአብሔር አንድ ጊዜ የተሰጠች ምንጊዜም የማትለወጥ እውነት ናት፡፡ሃይማኖት ሰው የሚያምንባትና የሚኖርባት እውነት ነች፡፡ይች የክርስትና ሃይማኖት ጌታችንና መድኃኒታችን ያስተማራት÷ ሐዋርያቱ የሰበኳትና የቤተ ክርስቲያን አባቶችም ያስፋፏት÷አደራጅተውም በጽሑፍ ያስተላለፉዋት የእውነት አምድ ናት፡፡ ይችም መንፈሳዊ አባቶች አደራጅተው ያስተላለፍዋት የእውነት አምድ ‹‹ጸሎተ ሃይማኖት›› ተብላ ዋና አእማድ ጉዳዮችን ይዛ ለሰዎች ተላልፋለች፡፡
‹‹ጸሎተ ሃይማኖት›› የትኛውም ክርስቲያን ማመን ያለበትን ወይም የክርስቶስ ተከታይ የሚሆንበትን አእማድ እውነቶች ይዛለች፡፡ እነዚህም እውነቶች የእግዚአብሔር መኖርና የሚታየውንና የማይታየውን ሁሉ መፍጠሩ፣ ዘላለማዊ የሆነው የባሕርይ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታና እውነተኛ አምላክ መሆኑ! እርሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን የሰው ልጆች ለማዳን ከሰማይ መውረዱና በመንፈስ ቅዱስ ግብር ወይም ሥራ ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው መሆኑ! ስለ እኛ ቤዛ ሆኖ በመስቀል ላይ መከራ ተቀብሎ መሞቱ፣ ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱ፣አንዲት ጥምቀት መኖርዋ ፣ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ጋር የሚሰገድለት ጌታና ሕይወት ሰጪ መሆኑና ከሁሉም በላይ የምትሆን አንዲት ቤተ ክርስቲያን መኖዋን እጥር ምጥን ባለ ሁኔታ የሚገልጹ ናቸው፡፡
ይች ከእግዚአብሔር የተሰጠችና በቤተ ክርስቲያን አባቶች በሥርዓት ተደራጅታ የተዘጋጀች ጸሎተ ሃይማኖት የተዘጋጀችበት ዐላማ የግለሰቦችንም ሆነ የሃይማኖት ተቋማትን መንፈሳዊ አቋም ለመመዘንና ውሳኔ ለመስጠት ነው፡፡ አንድ እውነተኛ ክርስቲያን የሚሆነው፣ መሆኑም የሚፈተሸው በጸሎተ ሃይማኖት በተገለጹ አእማድ እውነቶች ነው፡፡ አንድ ምእመን በእነዚህ የጸሎት ሃይማት አእማድ እውነቶች ማመን፣ በእነርሱም እውቀት ማደግና መጽናት በሕይወቱም እነዚህን እውነቶች በተግባር ማሳየት ይኖርበታል፡፡ መናፍቅነት እነዚህን እውነቶች ያለመቀበል፣ በእነርሱም ያለመጽናት ነው፡፡ የጸሎት ሃይማኖትም ዋና ዐላማ እውነተኛውንና ሐሰተኛውን ለመለየት መመዘኛ ሆኖ ማገልገል ነው፡፡እነዚህ የተገለጹት አእማድ እውነቶች እንዴት ነው መመዘኛ ሆነው የሚያገለግሉት) አንዱን ዋና ትምህርት ምሳሌ አድርገን እንመልከት፡፡«ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር የነበረ አንድ የአብ ልጅ( ወልድ ዋሕድ)፡-ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ፡-ከእርሱ(ከአብ)ጋር የሚተካከል፡-ሁሉ በእርሱ የሆነ÷በሰማይ ካለው÷በምድርም ካለው ያለእርሱ ምንም ምን የሆነ የለም፡---» እያለች የክርስቶስን አምላክነት ታስረዳለች ጸሎተ ሃይማኖት፡፡ በዚህ የሃይማኖት መግለጫ መሠረት የክርስቶስን እውነተኛ አምላክነት የሚቀበል እውነተኛ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡በአንጻሩ ደግሞ ይህንን እውነት የማይቀበል አርዮስ እንደተወገዘው መናፍቅ ተብሎ ይወገዛል፡፡እንግዲህበሌሎች አስተምህሮ ላይ ውሳኔ ለመስጠት በእነዚህ አእማድ የሃይማኖት እውነቶች ላይ መደገፍ ግዴታ ነው ማለት ነው፡፡  
እንግዲህ ይህ ክፍል ትክክለኛ ነው÷ ይህ ክፍል ደግሞ ሐሰተኛ ወይም መናፍቅ ነው ለማለት ጸሎተ ሃይማኖት እንደ ቱንቢ ወይም እንደ ማዕዘን ሆኖ ያገለግላል ማለት ነው፡፡ ስለሆነም በስሜት ተነሳስተን የምንጠላውን እገሌ የሚባለው ግለሰብ ወይም ክፍል መናፍቅ ነው፤ የምንደግፈውን ደግሞ ክንፍ ያወጣ መልአክ አድርገን ማሞካሸት አስጸያፊና በእግዚአብሔርም ፊት የሚያስጠይቅ ሥራ ነው፡፡ይህ አስጸያፊ ተግባር ‹‹ብርሃኑን ጨለማ ጨለማውን ብርሃን ለሚሉ ወዮላቸው›› ተብሎ በእግዚአብሔር ቃል ተወግዝዋል፡፡ ከላይ በአጭሩ እንደተመለከትነው ሃይማኖት ሰዎች እንዲያምኑባትና እንዲኖሩባት ከእግዚአብሔር አንድ ጊዜ የተሰጠች የማይጨመርባት ወይም የማይቀነስላት እውነት ነች፡፡ቤተ ክርስቲያን ደግሞ በዋናነት እነዚህን የሃይማኖ እውነቶች ከልባቸው አምነው ክርስቶስን የሚከተሉ ምእመናን ጉባኤ ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ሃይማኖት ሰዎች አምነው የሚድኑበትና መንግሥተ ሰማያት የሚወርሱባት አምላካዊ ድንጋጌ ስትሆን፣ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ይህንን ድንጋጌ በሙሉ ልብ ያመኑ ምእመናን ስብስብ ወይም ጉባኤ ናት፡፡ የሃይማኖትና የቤተ ክርስቲያን ግንኙነት እውነትና እውነትን የተቀበለ ሰው ያለውን ዓይነት ግንኙነት ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ሁለቱ ግንኙነት ያላቸው ቢሆኑም ፍጹም አንድ ዓይነት አይደሉም፡፡

‹‹የሃይማኖትን›› እና ‹‹የቤተ ክርስቲያንን››ልዩነትና ግንኙነት ካለመረዳት ጋር ተያይዞ የሚከሰተው ችግር ደግሞ ‹‹ሃይማኖ አትታደስም››እና ‹‹ቤተ ክርስቲያን አትታደስም›› የሚሉት ሁለት ሓሳቦች መደበላለቅና ሰውን ግራ ማጋባት ነው፡፡ ‹‹ሃይማኖት አትታደስም›› የሚለው ዐረፍተ ነገር እውነት ሲሆን ‹‹ቤተ ክርስቲያን አትታደስም›› የሚለው ዐረፍተ ነገር ግን ስህተት ነው፡፡ በእርግጥ ከላይ እንደተመለከትነው የሃይማኖት ሰጪ እግዚአብሔር በመሆኑ እርሱ በሰጠው ላይ መጨመርም እርሱ ከሰጠው ማጉደልም ወይም የሃይማኖትን ሓሳብ ባልተባለው መንገድ ያለ አውዱ አጣሞ መተርጎምም በእግዚአብሔር ቃል ተከልክሏል፡፡ በዚህ ሓሳብ መሠረት ‹‹ሃይማኖት አትታደስም›› የሚለው አገላለጽ ፍጹም ትክክል ነው፡፡ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት፡፡ቤተ ክርስቲያን ራሳቸው የሆነው ክርስቶስና ምእመናን ኅብረት ማለት ነው፡፡ ክርስቶስን አምነው በደሙ የኃጢአት ሥርየት ያገኙ÷የእግዚአብሔርን የልጅነት ሀብት የተቀበሉ÷ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ እንደ ሚኖር ከክርስቶስ ጋር የተጣበቁና በወንጌል የተሰጠውን እውነት እየፈጸሙ ሚኖሩ ምእመናን ጉባኤ ናት ቤተ ክርስቲያን፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከተቀበለችው እውነት ልትጎድል፣ መንገዷን ልትስት፣ ሃይማኖትን ቸል ልትልና እንዲያውም አልፋ ተርፋ የራሷን ሥርዐትና ወግ ልታቆም ትችላለች፡፡ ይህን ሐቅ መጽሐፍ ቅዱስና የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በብዙ ማስረጃ ግልጽ አድርገው ያብራራሉ÷ያረጋግጣሉም፡፡ ይህ ባይሆን ኖሮ ቤተ ክርስቲያን ንስሓ እንድትገባ በእግዚአብሔር ቃል መታዘዝ ባላስፈለጋትም ነበር፡፡
በዚህ በሁለተኛው ስለ ቤተ ክርስቲያን በተሰጠው ሓሳብ ላይ በመመርኮዝ ስለ ‹‹ቤተ ክርስቲያን መታደስ›› ወይም ስለ ‹‹ተሐድሶ›› በግልጽ መነጋገርና የጭፍን ተቃውሞን ወይም የጭፍን ድጋፍን ችግር ማስቀረትና የጋራ መግባባትንና ግንዛቤን ማግኘት ለችግሩም መፍትሔ መፈለግ ይቻላል፡፡ ይህም ለቤተ ክርስቲያናችን ከምንም በላያ  እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡
አንድ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ወይም በአንድ ዓይነት ስያሜ የምትጠራ ቤተ ክርስቲያን ከሃይማኖት መስመር ልትወጣ የምትችልባቸው አጋጣሚዎች መኖራቸው እርግጥ ነው፡፡ ብዙ ሳንርቅ በሐዋርያት የመጨረሻው ዘመን ላይ የነበሩትን በራእይ ዮሐንስ ምዕራፍ 2 እና ምዕራፍ 3 የተጠቀሱትን አብያተ ክርስቲያናት መጥቀስ እንችላለን፡፡በነዚህ ምዕራፎች የተጠቀሱት ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ክርስቶስ ገንዘቡ ያደረጋቸው ናቸው፡፡ ከነዚህ ሰባት አብያተ ክርስቲያናት አምስቱ ድካም ተገኝቶባቸው ንስሓ እንዲገቡ ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው÷ ሁለቱ ብቻ ናቸው ማበረታቻ የተሰጣቸው፡፡ በሐዋርያት ዘመን የነበሩ አብያተ ክርስቲያናት ሁኔታ እንዲህ ከሆነ ይልቁንስ በብዙ ዘመን ርቀት የሚኙት የኢትዮጵያ ኦርተዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ሌሎችም አብያተ ክርስቲያናት እንዴት የሕይወት ለውጥ ወይም ተሐድሶ አያስፈልጋቸውም)
እንግዲህ የቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ቤተ ክርስቲያን ከሃይማኖት መንገድ የሳተችበትን ወይም የደከመችበትን ሁኔታ በንስሐ አስተካክላ የሕይወት ጉዞዋን በብርታት የምትቀጥልበት የእርማት ድርጊት ማለት ነው፡፡ በአጭሩም የቤተ ክርስቲያን የሕይወት መስተካከል ማለት ነው፡፡ አንዳንዶች የተሐድሶን ሓሳብ አፍራሽ አድርገው እንደሚያቀርቡት ያልነበረ አዲስ ሃይማኖት መመሥረት አይደለም፡፡በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መደረግ ያለበት ተሐድሶ በሕዝቡ መንፈሳዊ ሕይወት ላይ የሚያተኩር መጽሐፍ ቅዱስንና  የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥንታዊ ዶግማ ወይም ትምህርተ ሃይማኖት መሠረት አድርጎ የሚከናወን ነው፡፡
የዚች ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ የሌሎችን ባህል÷አስተምህሮ÷የአምልኮ ሥርዐት መቅዳት ሊሆን አይገባም÷ ወይም አንዳንዶች እንደሚናገሩት ቤተ ክርስቲያኒቱን 'ፕሮቴስታንት' ማድረግ ሊሆን አይችልም፡፡የፕሮቴስታንቱ ክፍል ራሱ በችግር ውስጥ የተዘፈቀና የእግዚአብሔርን እጅ የሚፈልግ ነው፡፡

የአምልኮና የአለባበስ ሥርዐትን÷የዜማና የዜማ መሣሪያዎችን መለወጥ÷ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን መሥራትና ማደስ÷የቤተ ክርስቲያንን ገረገራ አጥር ማጠር÷ አንዳንዶችም እንደሚሉት ዳቦ ቤትና ወፍጮ ቤት ማቋቋም የቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ አይደለም፡፡እነዚህ ፈጽሞ የተሐድሶ ጥያቄዎች አይደሉም፡፡አንዳንዶችም የግብፅን ቤተ ክርስቲያን በመጥቀስ 'አስተዳደራዊ ተሐድሶ' ማድረግ ይገባናል ይላሉ፡፡«አስተዳደራዊ ተሐድሶ ምንድነው)» ሲባሉም ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መጠቀምና የአሠራር ስልት ማሻሻል እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ለመሆኑ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አሠራር የምትጠቀምና የተበላሸ ሕይወት የምትመራ ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ አያስፈልጋትም ማለት ነው) እነዚህ ሁሉ እንደ  እውነቱ ከሆነ በፍጹም የቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ሓሳቦች አይደሉም፡፡ የግብፅ ቤተ ክርስቲያንስ ብትሆን የአስተዳደር ስልት ለውጥን ብቻ ነው ያደረገቺው) በንስሓ ላይ የተመሠረተ የሕይወት ለውጥ አላደረገችም) ደርግ ሥልጣን ሲይዝ ተቋቁሞ የነበረውና እነቄስ ዳኛቸው የነበሩበት « ተሐድሶ ጉባኤ»ም እነዚሁኑ የተሐድሶ ሓሳቦች ይዞ የተነሳ እንጂ ፈጽሞ ትክክለኛው የቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ግንዛቤ የነበረው አልነበረም፡፡የሚያሳዝነው ነገር እነዚህን የተሐድሶ ሓሳቦች ያልሆኑ ጉዳዮች የቤተ ክርስቲያን የበላይ አለቆች ሳይቀሩ ዛሬም ደጋግመው ማንሳታቸው  ነው፡፡
የቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ የእግዚብሔርም እጅ እንዳለበት ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡የቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ሰው አውጥቶና አውርዶ የሚያከናውነው ሓሳብ ሳይሆን የሃይማኖት ሰጪ የሆነው ልዑል እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያንን ንጽሕና ለመጠበቅ የሚያከናውነው ድርጊት እንደሆነ ልብ ማለት መልካም ነው፡፡ይህ በልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ የሚከናወነው ተሐድሶ ሁለት መልክ አለው፡፡ አንደኛው ግለሰባዊ ቆይቶም ማኅበረሰባዊ የሚሆን ከመንፈሳዊ ሕይወት እድገት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በመንፈሳዊ እውቀት የበለፀጉ ሰዎች ሲገኙ በዙሪያቸው ያለማኅበረሰብም ከእነርሱ የእውቀት ማዕድ በመሳተፍ እድገት ያሳያል!በግል የሚታይ የሕይወት ለውጥ ይኖራል፡፡ ይህ የግለሰባዊ ተሐድሶ ለቤተ ክርስቲያን ተሐድሶም መሠረት ሆኖ ያገለግላል፡፡ ሁለተኛው የተሐድሶ መልክ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን የኃጢአት ፍሬ ጎልቶ ሲታይባትና መንፈሳዊ ጉዞዋን በተገቢው መንገድ መቀጠል ሲያዳግታት ኃጢአቷን በንስሓ አስተካክላ በመንፈሳዊ ሕይወትዋና እግዚአብሔር በሰጣት ተልእኮዋ የምትቀጥልበት ተግባር ነው፡፡ አሁን ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳይ የሆነውና እኔም በመግቢያዬ ግንዛቤ ሊያገኝ ይገባዋል ያልኩት የተሐድሶ መልክ ይኸ ነው፡፡
የቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ዐላማ እውነተኛ ንስሓ እንዲመጣና የሕይወት ቅድስና እንዲሰፍን÷የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጌትነትና ቤዛነት የሸፈኑ ነገሮች እንዲወገዱና የክርስቶስም ክብር በቤተ ክርስቲናችን ጎልቶ እንዲታይ÷የክብር ቦታውንና ሥልጣኑን ያጣው መጽሐፍ ቅዱስም ተመልሶ በተገቢው ቦታው እንዲቀመጥ ማድረግ ነው፡፡
 በምድር ላይ ተሐድሶ የማያስፈልጋት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የለችም፤ ራስዋን እየሸነገለች በግብዝነት ሕይወት የምትመላለስ ካልሆነች በቀር የትኛዋም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ያስፈልጋታል፡፡ዛሬ ቤተ ክርስቲያን እየገፈተረች ስለምታስወጣቸው ልጆችዋ በእርጋታ ማሰብ ይገባታል፡፡በቤተ ክርስቲያን ሃይ መባልና መታረም የሚገባቸውን አጉራዘለል ሰዎች ልታርም ይገባታል፡፡ጥፋታቸውን እንዳላየ እያየች ዝም ብትል በታሪክም በእግዚአብሔርም ፊት ያስጠይቃታል፡፡ሌሎች አብያተ ክርስቲያናትም ተሐድሶ እነርሱንም እንደሚመለከት ልብ ይበሉ÷ የሌላውን ጉድፍ በማውጣት ሥራ ተጠምደው የራሳቸውን ግንድ እንዳይረሱት ለማሳሰብ እወዳለሁ ፡፡
ተሐድሶ ቤተ ክርስቲያንን ከጉስቁልና ወደ ብርታት፣ ከሽንፈት ወደ ድል የሚያመጣት እንጂ የሚጎዳት አይደለም፡፡ ራሷን መርምራና ችግርዋን ተረድታ ተሐድሶን ተግባራዊ የምታደርግ ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን አግኝታ ኃይለኛ ትሆናለች! በኃጢአትዋ ምክንያት ከሚመጣባት ከአስከፊው የእግዚአብሔር ፍርድም ታመልጣለች፡፡የቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ የማኅበረሰቡን መጥፎ ገጽታ ይለውጣል ፡፡የሕዝቡ የሥነ ምግባር÷አስተሳሰብ÷ባህል÷ማኅበራዊ ግንኙነት ይለወጣል& ይዳብራል፡፡በጠቅላላው መልካም አገራዊ እሴቶች ላያስገኝ መቻሉ አጠያያቂ አይደለም፡፡

«ቤተ ክርስቲያን ተሳስታለች ትታረም» ማለት የማይሳሳተውንና ሕፀፅ የሌለበትን እግዚአብሔርን «ተሳስተሃል ስህተትህን አርም» እንደ ማለት አድርገው የሚቆጥሩ የዋሃን ብዙዎች ናቸው፡፡ አንዳንዶች ከመንፈሳዊ እውቀት ማነስ፣ አንዳንዶች ደግሞ ኃጢአታቸው እንዳይጋለጥባቸው በመስጋት የተሐድሶ ሓሳብ እንዳይነሳ አጥብቀው ይቃወማሉ፡፡ ለሁለቱም ወገኖች ተሐድሶ እንቅልፍ የሚነሳ ሥጋት ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን በመጽሐፍ ቅዱስ ሚዛን፣ በተቀበለችው ትምህርተ ሃይማኖትና ባሳለፈችው ታሪክ ስትፈተሽ በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ ድክመት ውስጥ መሆንዋን ማንም ሊክድ አይችልም፡፡ ራሱ በቤተ  ክርስቲያን የሚታየው ትርምስ አንድ ማረጋገጫ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን የሚታዩ የተለያዩ ድካሞች «ተሐድሶ! ተሐድሶ! »እያሉ አፍ አውጥተው እየጮሁ ነው፡፡እዚህ ቢዘረዘሩ ጆሮ ጭው የሚያደርጉ በደሎች የሚፈጸሙባት ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ አያስፈልጋት ብሎ መናገር የሚችል ማንም የለም፡፡ረድኤተ እግዚአብሔር የራቃት ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ አያስፈልጋትም  እንዴት ይባላል)
‹‹በቤተ ክርስቲያን የታዩ ድክመቶችና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጩ ነገሮች መወገድ አለባቸው›› የሚሉትን ሁሉ እንደ ቤተ ክርስቲያን ጠላቶ መቁጠርና ማሳደድ፣ ስም ማጥፋት ሌሎችንም ክፉ ክፉ ተገባሮች መፈጸም ቤተ ክርስቲያንን ከችግር ድጥ ወደ ማጥ እንድትገባ በማድረግ ለሌሎች የመግቢያ ቀዳዳዎችን እየከፈተ ሁኔታዎችን ያባብሳል እንጂ ከቶም መፍትሔ ሊሆን አይችልም፡፡ ሊፈነዳ የደረሰን እሳተ ገሞራ ማፈን እንደማይቻል ሁሉ የእግዚአብሔር እጅ ያለበትንም ተሐድሶ ማስቀረት የሚችል ምንም ዓይነት ኃይል የለም፡፡በተለይም በዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምፅአት መዳረሻ ወቅት የቤተ ክርስቲያንን ተሐድሶ ከቶም ሊያስተጓጉል የሚችል ኃይል የለም፤ ተሐድሶ የክርስቶስን ሙሽራ ቤተ ክርስቲያንን ማዘጋጃ መሣሪያ ነውና!

ሓሳቤን ከመደምደሜ በፊት ለኦርቶዶክሳውያን ወገኖቼ ሁሉ ያለኝን ማሳሰቢያ ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንደ ተቋም አባላትም እንደ ግለሰብ ተቆርቋሪዎች የተሐድሶን ሓሳብ በቅጡ ልንገነዘበውና መፍትሔውንም በግልፅ ተረድተን ተገቢውን ነገር ልናከናውን ይገባል፡፡ ጭፍን ተቃውሞ ወይም ጭፍን ድጋፍ መቅረት ይገባዋል፡፡ እንክርዳዱን ለመንቀል ስንዴውንም አብረን እንዳንነቅለው ብርቱ ጥንቃቄ እናድርግ ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን፣ ትምህርተ ሃይማኖትንና የቤተ ክርስቲያንን ታሪክ መመዘኛ በማድረግ ተሐድሶ እናካሂዳለን የሚሉ ክፍሎችን አሰላለፍ በሚገባ ማስተዋልና ተገቢውንም የተሐድሶ ሓሳብ የሚያቀርቡት÷በሌላው ወገን ደግሞ የተፈጠረውን ሁኔታ በመመልከት ምእመናንን ለማፍለስ እንዲሁም ሌላ ጥቅም ለማግኘት የተሰለፉት እነማን እንደሆኑ መለየት አስፈላጊ ነው፡፡ ተሐድሶ እናካሂዳለን የሚሉ ክፍሎችን ሓሳብ ማድመጥና በጽሑፍም ያሰፈሯቸውን አቋማቸውን መረዳት ተገቢውን ተግባር ለማከናወን ይረዳል፡፡ ከሁሉም በላይ መጽሐፍ ቅዱስን ቀጥሎም ስለ ተሐድሶ የተጻፉ መጻሕፍትን ማንበብ ይኖርብናል፡፡ ስለ ተሐድሶ ግንዛቤ ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ይህን ተግባር መፈጸም ይኖርባቸዋል፡፡
ከዚሁ ጎን ለጎንም የቤተ ክርስቲያናችንን ችግር በግልጽ መረዳትና ማመን፣ እንደ ሁኔታውም እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀት ግዴታ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ያሉባትን ችግሮች ሽምጥጥ አድርገን ብንክድና ‹‹ደህና ነች›› ብንል ግመል ሰርቆ አጎንብሶ ነውና ግብዞችና ዋሾዎች እንሆናለን፡፡እኛ የምንሸፋፍናቸውን ችግሮች እግዚአብሔር ወደ ብርሃን በማውጣት በጽድቅ መፍረዱ አይቀርም፡፡ይልቅስ፡-
«አሞኛል፣ አሞኛል፣ አሞኛል በጠና፣
አምላክ ሆይ፣ አድነኝ መድኃኒት ላክና» እያለች ቤተ ክርስቲያን የምትጮኽበትን ጉዳይ  በመመርመር÷ በልዑል እግዚአብሔር ፊት በጾምና በጸሎት መትጋት መፍትሔ  ያስገኛል፡፡ይኽን ምክርም መስማት ተገቢ ነው፡፡
ውስጥሽም ውጭሽም በጣሙን ቆሽሾ
ፀአዳ ነኝ ብትዪ ትባያለሽ ዋሾ፤
ግመል የሰረቀ አያጎነብስም
ንስሓው ይሻላል ከቅጣት አይብስም፡፡

14 comments:

 1. እንግዲህ የቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ቤተ ክርስቲያን ከሃይማኖት መንገድ የሳተችበትን ወይም የደከመችበትን ሁኔታ በንስሐ አስተካክላ የሕይወት ጉዞዋን በብርታት የምትቀጥልበት የእርማት ድርጊት ማለት ነው....የአምልኮና የአለባበስ ሥርዐትን÷የዜማና የዜማ መሣሪያዎችን መለወጥ÷ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን መሥራትና ማደስ÷የቤተ ክርስቲያንን ገረገራ አጥር ማጠር÷ አንዳንዶችም እንደሚሉት ዳቦ ቤትና ወፍጮ ቤት ማቋቋም የቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ አይደለም>የምትለው አንተ ውስጠ መርዝ

  ክርስቶስ በደሙ የዋጃት ቤ/ክርስትያን ምንም ተሀድሶ አያሻትም ይልቅ አንተ የቆሸሸ አእምሮህን አፅድተህ በንስሀ ተመልሰህ የአለሙን ቡትቶ ዘመን አመጣሽ አለማዊ እና የስጋ ፍላጎት የተንፀባረቀበት/የነገሰበት/አስተሳሰብህን ትተሀ እውነተኛ ኦርቶዶክሳዊ ከሆንክ ወደ ቤተ እግዚአብሔር /ወደ እውነተኛዊቱና አማናዊቱ ቤ/ክርስትያን ና::

  ReplyDelete
 2. Do you have any evidence it starts at 15 century?
  one of your friend said ZY brought bad staff to the church. Other friend of you said Tehadiso is when things are gone bad. to renew it. see in every corner you trying to attack but fail with your own words. 15 cen. aba Estefanos does not have any relation with this Tehadiso menga.
  Ben

  ReplyDelete
 3. "ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን? ጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይ ዘንድ አለው? " / 1ኛ ጴጥ 4፥17-18 /
  "ኃጢአተኛውም ካደረጋት ኃጢአት ሁሉ ቢመለስ ትእዛዜንም ሁሉ ቢጠብቅ ፍርድንና ቅን ነገርንም ቢያደርግ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም። የበደለው በደል ሁሉ አይታሰብበትም በሠራው ጽድቅ በሕይወት ይኖራል።" /ትንቢተ ሕዝቅኤል 18፥21-22/

  ReplyDelete
 4. omg ageliglotachun yibark

  ReplyDelete
 5. የቤተክርስቲያን ጠላቶች ግራየገባችሁ ንስሀ ግቡ በንስሀ እራሳችሁ ታደሱና ተመለሱ የተሀድሶ እንቅስቃሴ እኮ በተዋህዶ ልጆች ተመቷል።

  ReplyDelete
 6. እንግዲህ የቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ ቤተ ክርስቲያን ከሃይማኖት መንገድ የሳተችበትን ወይም የደከመችበትን ሁኔታ በንስሐ አስተካክላ የሕይወት ጉዞዋን በብርታት የምትቀጥልበት የእርማት ድርጊት ማለት ነው....የአምልኮና የአለባበስ ሥርዐትን÷የዜማና የዜማ መሣሪያዎችን መለወጥ÷ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን መሥራትና ማደስ÷የቤተ ክርስቲያንን ገረገራ አጥር ማጠር÷ አንዳንዶችም እንደሚሉት ዳቦ ቤትና ወፍጮ ቤት ማቋቋም የቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ አይደለም>የምትለው አንተ ውስጠ መርዝ

  ክርስቶስ በደሙ የዋጃት ቤ/ክርስትያን ምንም ተሀድሶ አያሻትም ይልቅ አንተ የቆሸሸ አእምሮህን አፅድተህ በንስሀ ተመልሰህ የአለሙን ቡትቶ ዘመን አመጣሽ አለማዊ እና የስጋ ፍላጎት የተንፀባረቀበት/የነገሰበት/አስተሳሰብህን ትተሀ እውነተኛ ኦርቶዶክሳዊ ከሆንክ ወደ ቤተ እግዚአብሔር /ወደ እውነተኛዊቱና አማናዊቱ ቤ/ክርስትያን ና::

  ReplyDelete
 7. I may kindly say I am one of those who rationally observe the specific problems of the church which need 'reformation' over them. However, I could not join this team [Aba Selama] the fact that I don't know who those are involved here and still I have been in the journey of analysing their views. Nontheless I would like to give credit to this article and "ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ምን ምን ነገረን?” the reason why for me it seems that the weight of realities become greated than blind thoughts.

  Increase your growing in truth!

  ReplyDelete
 8. the 'wolf in the sheep's fur' religion(established by Jesus ) can NEVER, NEVER,NEVER reformed. reformation is needed for artificial religion (established by Luther and his colleagues)on one hand, and your dirty life decayed by huge sins on the other. you may dream that orthodox church be reformed religiously but your dream REMAINS A DREAM, KEEP ON IT.'orthodox church needs a reform is the third strategy to be used as an instrument to convert it in to protestant, the two strategies used so far become unsuccessful, realizing this , now Luther want to use this third strategy. what makes surprising me is that protestant missionaries would not wake up that this strategy would be foiled. the thadiso's who are hand in hand against the Ethiopian church are those 'the wolf in the sheep's fur as indicated in the bible as they would emerge at the the eve of GOD'S RETURN. HENCE, YOU SHOULD EMERGE OR HAVE BEEN EMERGED AS IT IS A MUST BY THE WORDS OF GOD.

  ReplyDelete
 9. To those who is opposing the Current Reformation Movement in Ethiopia ,You are always in my prayers May the Almighty God Open your eyes to see what Jesus did for your salvation!

  ReplyDelete
 10. አንድ ጥያቄ አለኝ እናንተ ትክክለኛ ነን ባዮች እናውቃለን ባዮች
  የተሐድሶ መንጋዎች እንዴት ስም የአባት ስም ማንነታችሁን የሚገልጽ ፎቶግራፍ የላችሁም???
  ሁል ጊዜ በድብቅ ነው የምትጓዙት ለምን ይሆን??? አላማችሁ ማፍረስ ማጥፋት ማውደም ስለሆነ ይሆን???

  ReplyDelete
 11. የፈጣሪ ቸሩ እግዛብሔርን ህግ ማደስ ስለማይቻል ተሃድሶ የሚባል ዓ/ነገር ለሰዉ ሰራሽ ህግ እንጂ ለፈጣሪ ህግ አይሰራም፡፡

  ReplyDelete
 12. የፈጣሪ ቸሩ እግዛብሔርን ህግ ማደስ ስለማይቻል ተሃድሶ የሚባል ዓ/ነገር ለሰዉ ሰራሽ ህግ እንጂ ለፈጣሪ ህግ አይሰራም፡፡

  ReplyDelete
 13. betkrstyn sitlu algebagnm hintsawnew wyns lela?

  ReplyDelete
 14. bemar yetelewese merz new be tiru agelalets hasabachihun bitasefrum ewnetun meshefen atichilum

  ReplyDelete