Thursday, September 22, 2011

የፈጣሪ ምስጋና ይገባቸዋል

 

"ለእሉ ክሌቱ ፍጡራን ስብሐተ ፈጣሪ ይደልዎሙ እስመ ተአረዩ በክብሮሙ"

ትርጉም "ለነዚህ ለሁለቱ ፍጡራን ለማርያምና ለመስቀል የፈጣሪ ምስጋና [አምልኮ] ይገባቸዋል። በክብር ከፈጣሪ ጋር እኩል ሆነዋልና" [መስተብቍዕ ዘመስቀል]
 አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ደቂቀ እስጢፋኖስን ከገደለና እውነተኛ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምመናን እና መምህራን እመነታቸውን በሰማዕትነት ከፈጸሙ በኋላ። የግል ደብተራዎቹን በማሰባሰብ መስተብቁዕ ዘመስቀል የሚባል ድርሰት ደርሷል። ይህ ድርሰት "ወካዕበ ናስተበቁዖ ለእጸ ቅዱስ መስቀል‚  ትርጉም "ዳግመኛ ቅዱስ የሆነ የእንጨት መስቀልን እንማልደዋለን‚ ብሎ ይጀምራል። ድርሰቱ የመንፈስ ብክለት የደረሰበት ሰው የደረሰው ለመሆኑ ገና ካጀማመሩ ያስታውቃል። መስቀልን እንማልደዋለን ሲል የሚሰማ ሰው አድርጎታል። መስቀል ግኡዝ ፍጥረት ነው፤ ጸሎትና ምልጃን ሊሰማ የሚችል አምላክ አይደለም። ምን አልባት ደራሲው በሰከረበት ቀን ደርሶት
ሊሆን ይችላል እንጂ በአእምሮው ቢሆን ኖሮ እጸ መስቀልን ለመማለድ አይነሳሳም ነበር ብለን እንገምታለን። አሳዛኙ ጉዳይ ግን ዛሬም ምንም እርማት ሳይደረግበት በቤተ ክርስቲያናችን የመስቀል በዓል ሲሆን የሚጸለይ መሆኑ ነው።
  በዚህ ድርሰት ውስጥ ፈጣሪን እና ፍጡራንን እኩል የሚያደርግ ከፍተኛውን ክህደት እናነባለን። "ለነዚህ ለሁለቱ ፍጡራን‚ ይላል ደራሲው "የፈጣሪ ምስጋና‚ ይገባቸዋል ለምን ሲባል "ከፈጣሪ ጋር እኩል ሆነዋል‚ ይለናል። እነዚህ ሁለት ፍጡራን የተባሉት የጌታችን እናት እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ጌታ የተሰቀለበት የእንጨት መስቀል ነው። ሁለቱ ከፈጣሪ ጋር እኩል ሆነዋል ተብሎ በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዘራ ያዕቆብ ሲታወጅ፤ መልካም የሆኑ ኦርቶዶክሳዊ ጥንካሬዎች ሁሉ እየወደቁ መጡ። በዚህ አዋጅ መሠረት በየጸሎቱ ሁሉ እነዚህ ሁለት ፍጡራን ከሥላሴ ጋር በሦስተኛነት ተመለኩ፤ ለስላሴ የሚቀርበው ምስጋና ለሁለቱም መቅረብ ጀመረ። እስከ ዛሬም ድረስ ይህ ሁኔታ አልታረመም።
 እነዚህ ሁለት ፍጡራን ከፈጣሪ ጋር አሁንም እየተመለኩ መሆናቸውን ለማስተዋል አንዳንድ ምሳሌዎችን እንጥቀስ።
ከጸሎተ ሃይማኖት ቀጥለን በምንጸልየው የዘወትር ጸሎት ላይ "እሰግድ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐተ ስግደተ... እሰግድ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ፤ እሰግድ ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ‚ የሚል አለ።
ትርጉም "ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንዲት ስግደት እሰግዳለሁ፤ አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያምም እስግዳለሁ፤ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልም እሰግዳለሁ‚ ማለት ነው። የዘወትር ጸሎት ተብሎ የሚታወቀውን የጸሎት መጽሐፍ ማየት ይቻላል። ስግደት አምልኮ ነው፤ ይህም ለስላሴ ብቻ የሚቀርብ ነው። ነገር ግን በስላሴ ላይ ደርበን የምንሰግድለት አካል መኖሩን አበውም ሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ አላስተማሩንም። እመቤታችንም "ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች‚ በማለት ራሷ ለስላሴ አምልኮ ማቅረቧን ተማርን እንጂ ከፈጣሪ እኩል ሆና ስግደት ለመቀበል ፈቃደኛ መሆኗን አልተማርንም። እመቤታችን በሌላ ድርሰት "መትሕተ ፈጣሪ መልእልተ ፍጡራን‚ "ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ‚ ተብሎ ተነግሮላታል። ዘራ ያዕቆብ ግን ከፈጣሪ እኩል ናት በማለት ያባቶችን ሥነ ትምህርት በንጉሣዊ አዋጁ አጥፍቷል።
 በዚሁ የዘውትር ጸሎት ላይ "ማርያም ሆይ ሰላም እንልሻለን፤ እንሰግድልሻለን፤ ከአዳኝ አውሬ ታድኚን ዘንድ ተማጽነንብሻል፤ ስለ እናትሽ ሰለ ሃና ብለሽ ስለ አባትሽ ስለ ኢያቄም ብለሽ‚ የሚል አምልኮ እናገኛለን። ከአዳኝ አውሬ የሚያድን እግዚአብሔር ነው "እኔ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለ‚ ይላል ቃሉ ኢሳ 43፡11። የምንሰግደው ላክብሮት ነው የሚለው አባባል ውሸት የሚሆነው በዚህኛው ጸሎት ነው። ምክናያቱም "ካዳኝ አውሬ ታድኚን ዘንድ እንሰግድልሻለን‚ የሚለው አባባል አምልኮ እንጂ አክብሮት አለመሆኑ ለማንም ግልጥ ነው። አክብሮት ቢሆን ኖሮ "ስለ እናትሽ ስለ ሃና፣ ስለ አባታሽ ስለ ኢያቄም ብለሽ‚ በማለት ሌላ ሁለተኛ አካል ማቅረብ ለምን አስፈለገ? አይሁድ እግዚአብሔርን ስለ አብርሃም ስለ ይስሐቅ ስለ ያዕቆብ እያሉ ያመለኩበትን አምልኮ መኮረጅ አይደለምን?
 ምግብ ከተመገብን በኋላ እግዚአብሔርን ስለስጦታው ሁልጊዜ እናመስግናለን። በዚህ ምስጋናም ሁለቱ ፍጡራን አብረው ከስላሴ ጋር ሲመለኩ እንመልከት ።
"ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ፤ ስብሐት ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ፤ ስብሐት ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ‚ ትርጉም "ምስጋና ለአብ ምስጋና ለወልድ ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ፤ ምስጋና አምላክን ለወለደች ለመቤታችን ለድንግል ማርያም፤ ምስጋና ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል‚ ማለት ነው።
በመጨረሻው ላይም "ነሐብ ሎቱ ስብሐተ ወአኮቴተ ለእግዚአብሔር ልዑል ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር‚ ትርጉም "ለዑል እግዚአብሔር ለወለደችው ድንግል፤ ለክቡር መስቀሉም አምልኮና ምስግና እናቅርብ‚ ማለት ነው። እግዚአብሔርን፤ ማርያምና መስቀልን የምናመሰግንበት ቃል ምንም ልዩነት የለውም። ይህን ስድብ እመቤታችን ብታውቅ እንዴት ትቆጣ ይሆን? ከፈጣሪዋ ጋር በፈጣሪ የምስጋና ቃል ምስጋና ሲቀርባላት ብትሰማ እንዴት ታፍርብን ይሆን? መስቀልስ መቸም አይሰማ፤ ከስላሴ ጋር የሚቀርብለትን ምስጋና በሄትኛው ጆሮው ይሰማው ይሆን?
 አድህነነ ሕዝበከ "ሕዝብህን አድነን‚ ተብሎ በሚታወቀው የሠርክ ጸሎት ላይ "ወአድህኒነ እምኩሉ ምንዳቤ ወኃዘን‚ "ከችግር እና ከኃዘን ሁሉ አድኚን‚ የሚል ጸሎት አለ። ሕዝብህን አድነን ስንል ጀምረን ዘወር ብለን ምርያምንም አድኚን እንላለን። አዋጁ ሁለቱን ፍጡራን ከፈጣሪ ጋር እኩል ስላደረገ በያንዳዱ ጸሎት ላይ እግዚአብሔርን የምንጠይቀውን ሁሉ ማርያምንም እንጠይቃለን። በዚህ ጸሎት መጨረሻ ላይ
 "ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ፤ ስብሐት ለማርያም እመ አምላክ እግዝእትነ ወመድኃኒትነ፤ ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ እጸ መድኃኒት ኃይልነ ወጸወንነ‚ እንላለን ትርጉም "እናመልከው ዘንድ እኛን ለፈጠረ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል፤ የአምላክ እናት ለሆነች ለመድኃኒታችን ማርያምም ምስጋና ይገባል፤ የመድኃኒት እንጨት ለሆነ፤ መጠጊያና ኃይል ለሆነን ለክርስቶስ መስቀልም ምስጋና ይገባል‚ ማለት ነው። በዚህ ጸሎት ውስጥ ደግሞ እመቤታችን "መድኃኒታችን‚ መስቀሉ "መጠጊያችን‚ ተብለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን መድኃኒታችን እና መጠጊያ የሚለው እግዚብሔርን ብቻ ነው። "ነፍሳችን እግዚአብሔርን ተስፋ ታደርገዋለች፥ ረዳታችንና መጠጊያችን እርሱውና‚ ተብሎ ተጽፏል መዝ 33፡20
ሐዋርያት አባቶቻችን መድኃኒታችን እያሉ የሚጠሩት ጌታችን ኢየሱስ  ክርስቶስን ነው። ታዲያ የኛ ደብተራዎች ከሔት ተምረውት ነው? መድኃኒታችን የሚለውን ቃል ለማርያም የሰጡት? በሌላ ጊዜ ሐዋርያዊ ነን ሲሉ ይደመጣሉ። የሐዋርያትን ትምህርት ግን አይከተሉም።
 በኪዳን ጸሎት ጊዜም ሁለቱ ፍጡራን ከስላሴ ጋር ሲመለኩ "ሰላመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፣ ወፍቅራ ለእግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ፤ ሞገሰ መስቀሉ ወሀብተ ረድኤቱ የሀሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለመ ዓለም አሜን‚ ትርጉም "የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤ የማርያም ፍቅር፤ የመስቀሉ ሞገስና ሀብተ ረድኤቱ ከኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን‚ ማለት ነው።
ሐዋርያው ጳውሎስ "የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር፤ የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን‚ 2ቆሮ 13፡14 ያለው የቡራኬ ቃል ተገልብጦ ማርያምና መስቀል ተተክተዉበታል። በያንዳዱ የአምልኮ ጸሎት ላይ- አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንደኛ፤ ማርያም ሁለተኛ መስቀል ሦስተኛ ሆነው በጋራ በአንድ ምስጋና በማይለያይ ቃል ይመለካሉ። ለእግዚአብሔር አንድ ነገር ካልን ለማርያምም አይቀርም፣ ወደ እግዚአብሔር ከጸለይን ወደ ማርያምም መጸለይ ይግድ ነው አዋጅ ነዋ! አባታችን ሆይ ካልን በኋላ "እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን‚ የሚለውን ጸሎት እንጸልያለን። ይህም እመቤታችን ከፈጣሪ ጋር እኩል ሆናለች የሚለው አዋጅ በታወጀ ማግስት በዘራ ያዕቆብ የተጨመረ ነው።
 በቅርቡ የተመሠረተው ማህበረ ቅዱሳን የተባለው ድርጅት በሚጽፈው ጽሑፍ መደምደሚያ ላይ  እንዲህ ይላል "ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር‚ ትርጉም- ለእግዚአብሔር፣ ለማርያምና ለመስቀል ምስጋን ይገባል‚ ማለት ነው። ለምን ማርያምንና መስቀልን ታመልካላችሁ የሚል አስተዋይ ጠያቂ ሲመጣ "ማርያምንና መስቀልን እናከብራለን እንጂ አናመልክም‚ በማለት የግብዝ መልስ ይሰጣል። በእግዚአብሔር ምስጋና ማርያምንና መስቀልን መጨመር ምን ምንድር ነው? የዘራ ያዕቆብን አዋጅ በተግባር ለመፈጸም አይደለምን?
 እንግዲህ ምን እንላለን? አምልኮአችን የጠራ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ መሆን አለበት፤ የንጉሥ አዋጅ በአዋጅ መሻር ይገባዋል፤ እግዚአብሔርን ለብቻው እናምልከው፤ ዓይኑን በግእዝ ቋንቋ ሸፍነን የምንመራው ሕዝብ እውነቱን አውቆ ወንጀላችንን ያወቀብን ጊዜ ወዮልን። እግዚአብሔርን ከልቡ የሚፈልገውን ወገናችንን እርባና በሌለው ድጋምና ባዕድ አምልኮ ተብትበን ይዘን እንዳይራመድ አድርገነዋል። ልንለቀው ይገባል፣ እግዚአብሔርን አምልኮ በነፍሱና በሥጋው እረፍት ያገኝ ዘንድ ከትከሻው ልንወርድ ይገባናል።
 ቤተ ክርስቲያናችን በነገሥታት አዋጅ ሳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በሐዋርያቱ ቃል መመራት አለባት፤ ቤተ ክርስቲያናችን ሐዋርያዊት እንጂ ንጉሣዊት ሆና መቀጠል የለባትም። የንጉሥ ዘራ ያዕቆብ አዋጅ ተወግዶ የነገሥታት ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ ያወጀው ወንጌል ወደ ቦታው መመለስ አለበት።
ማሳሰቢያ
በአባ ሰላማ ላይ መጻፍ ከጀመርሁ ጀምሮ አንዳድ ለውጦችን እያየሁ ነው። የማናግራቸው ምመናን ቤተ ክርስቲያን ተሃድሶ ማድረግ እንዳለባት አምነዋል ሊቃውንቱና ካህናቱ እጅግ የሚፈልጉት ነው። ጠንካራ ልብ ያለው ግን የማሕበረ ቅዱሳን አባል የሆኑ ጳጳሳት አካባቢ ነው በማህበረ ቅዱሳን አባላት አካባቢ እንኳ ብዙ ለውጥ እያየን ነው። ባሁኑ የጥቅምት ሲኖዶስ መወያያ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ። ነገር ግን እንደተለመደው ተሐድሶን በማውገዝና ስለ ገንዘብ ብቻ የሚደረግ ጉባኤ ከሆነ ግን መጻፌን አላቆምም  በባሰ ሁኔታ እቀጥላለሁ እንጂ ።
ዲ. ሉሌ ነኝ
   

32 comments:

 1. yegeremegn beabatochachn sim dere gets mekfetachu engi menafk mehonachun yasabkbachuwal

  ReplyDelete
 2. በገዛ እጅህ ማን መሆናችን ገለታችሁ፡፡ የንጹሐን ንጽህት ቅድስት ድንግል ማርያምና የመስቀል ክብር ሲናሰ ዓይኑ ደም የሚለብስ ማን እደሆና ስለምናውቅ ብዙ በተወሩ ጊዜ የለፈበት ስልት ነው::

  ReplyDelete
 3. mejemeriawnu tewahdo mech honkina! Geez siletekesk? Tesastehal wondme ,lemasferaratm mokrehal. Atdikem ewnet endehon ewnet new mejemeriawnu tewahdo mech honkina! Geez siletekesk? Tesastehal wondme ,lemasferaratm mokrehal. Atdikem ewnet endehon ewnet new

  ReplyDelete
 4. I am waiting to lough!!! Ben and Anonymous ... Come out and say some thing, oppose this reality.

  F

  ReplyDelete
 5. እርማት የሚፈልጉ ሐሳቦች እንዳሉ በመረዳት 'ለተሐድሶ'ከናንተ ለማበር ስከታተል ነበርሁ ፤ ነገርግን እንደ ፕሮቴስታንት በነጠላ አእምሮ ከመተርጎማችሁ የተነሳ እናንተም በቀለም ያልጠገባችሁ መስሎ ታይቶኛል። ለምሳሌ እንዴት "ለእሉ ክሌቱ ፍጡራን ስብሐተ ፈጣሪ ይደልዎሙ እስመ ተአረዩ በክብሮሙ"= "ለነዚህ ለሁለቱ ፍጡራን ለማርያምና ለመስቀል የፈጣሪ ምስጋና [አምልኮ] ይገባቸዋል። በክብር ከፈጣሪ ጋር እኩል ሆነዋልና"
  በናንተ ዓውደ ምንባብ “ስብሐተ ፈጣሪ ይደልዎሙ”="ለነዚህ ለሁለቱ ፍጡራን ለማርያምና ለመስቀል የፈጣሪ ምስጋና [አምልኮ] ይገባቸዋል፤
  እስመ ተአረዩ በክብሮሙ"= “በክብር ከፈጣሪ ጋር እኩል ሆነዋልና" ተብሎ ተተርጉሞአል።
  እንደዚህ ከሆነ ልክ ክርስቶስ እኔና አብ አንድ ነን ኣንዳለው “እግዚአብሔር= ማርያም፣መስቀል” ማለት ነው። ለምን ቢባል በክብር ከእግዚብሔር አንድ ከሆኑ በግብር አንድ ሆነዋል ማለት ነውና። ይህም ሶስት አማልክት አሉን ያስብላል ማለት ነው።
  ቅሉ ግን ዘርአያዕቆብን መጥላት ሌላ ጉዳይ መተርጎም ደግሞ ሌላ ስለሆነ እስኪ መልሳችሁት እዩት! ወይም የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት እንዴት እንደሚፈቱት ጠይቁ!
  ለምሳሌ አንድ ዐረፍተ ነገር መዘዝ አድርጌ ተናገርኩ እንጂ ሌሎች ከጠቀሳችሗቸውም የግእዙ ዘርፈ ብዙ አገባብና ዘይቤ/ብሂል/ሳትጠብቁ ፈሩን የለቀቀ ትርጉም እንደሰጣችሁት በግሌ ተገንዝብያለሁ።
  እንዴ! እንኳን ሊቃውንቱ ምእመናንም እግዚአብሔር እንጂ ማርያም አዳኝ አለመሆኗ’ኮ ያውቃሉ። ነገርግን ሚስጢሩን አዛብታችሁ ማቅረብ ምን ይመስላል?

  ***ሉሌ ከማለት ፈንታ እናንተ መረጥኹ
  +ተዐረዩ=-ተአረዩ

  ReplyDelete
 6. ይህ ሰይጣናዊ ኣምልኮ መሆኑ መዘንጋት የለብንም።
  ነገር ግን ታዛቢ እንዳለዉ፡ በግእዝ ስትጽፉ በጣም ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
  ዐረየ= ተካከለ እኩል ኮነ ማለት ነው።
  ኣረየ ካላችሁ ግን ለየ፡ ለይቶ ኣወጣ ነው።
  ችግሩ ሓሳቡ እናንተ እንደገለጣችሁ ነው፡ ማርያምንና ግዑዙን መስቀል ከፈጣሪ ጋር እኩል እያመለክን ነው።
  ከዚህ የሚብስ ኃጢኣትና፡ ክህደት ደግሞ የለም። እና ቤተ ክርስቲያኑ ልታስብበት ይገባል።
  ማቅ. የጥፋታቸው ዘመን ሩቅ ኣይሆንም።

  ReplyDelete
 7. Kesh'm yehone blog, ay ke'emnetu ay ke'ewketu: BADO GEREWEYNAY!
  "Te'areyu" does have 2 meanings:
  1. Ekul honu
  2. Temesaselu
  Agebabun temelket, "te'areyu" =Temesaselu.
  Yhm n'ts'ts'ru lehuletu ftretat ersbersachew enji ke'fetari gar aydelem:: Askedmo eko ftretat alachew: Emebetach'n kefetari betach kefturan belay nat, Meskelm bedeme Krstos yetekedese new::
  ... "...Eskemeker dres tewu'achew"e'ewketu: BADO GEREWEYNAY!
  "Te'areyu" does have 2 meanings:
  1. Ekul honu
  2. Temesaselu
  Agebabun temelket, "te'areyu" =Temesaselu.
  Yhm n'ts'ts'ru lehuletu ftretat ersbersachew enji ke'fetari gar aydelem:: Askedmo eko ftretat alachew: Emebetach'n kefetari betach kefturan belay nat, Meskelm bedeme Krstos yetekedese new::
  ... "...Eskemeker dres tewu'achew"

  ReplyDelete
 8. really i were on yr side for the last few months .but yr objective is really not to see a prosperous ,one universal ancient church.rather it is to make this dekama population to protestant .Amazingly ,u are saying that our church before the reign of Zerayacob was with the current protestant teaching that maryam and the rest saints have no value.u ALWAYS SAY ''betekirstianachin" ,which are u refering? I would like to tell u that I DON'T WORRISHOP MARY OR JEsus's cross.nor does i accept the idea that " bedebrelibanos yetekebere yidnal or geta egele letebale kidus yihen yahl tiwuld imrlhalehu alew....minamin minamin.This all are really debteras so that they should be corrected ,i THINK.but this doesn't mean that the core faith of the church is wrong .aamade mistriatn kemtastemir betekirsian beker lela betekirstian yelem.enante gin minim inqua silasie silasie bemalet yesilasen andnet ina sostnet yemtaminu bitmeslum irgitegna negn eyesus amalaj new yemtilu nachihu(tilik ibdet).bezihm silassie yalachihutn tafersalachihu.tinish ewnet alachihu ,wustachihu gin merz new.mahiberekidusan lene mem aydel ,nef sihtetochin yiseral (i know them well).Ashebari,yepolitica budn yemtlut neger gin beftsum wushet new.kezeregninet garm tanesutalachihu .bezih gin kemir aytamum.mk bitefa betekirstian atitefam ,inesu gin yihen yemiasibu yimeslau.simachew hule bebego indinesa yifelgalu(gibzoch nachew).

  ReplyDelete
 9. maneh lule endet new mkn yefeterew zera yakob new ende? Yalgebagn articlocheh bemulu zorew zorew zera yakobenena mkn new yeminekut mades yemtfelegew ensun new ende? Zoro zoro post yemtaregachew articloch behaymanotawi ewket yekesu nachew selez kemetemtem memar yekem bay negn maneh lule endet new mkn yefeterew zera yakob new ende? Yalgebagn articlocheh bemulu zorew zorew zera yakobenena mkn new yeminekut mades yemtfelegew ensun new ende? Zoro zoro post yemtaregachew articloch behaymanotawi ewket yekesu nachew selez kemetemtem memar yekem bay negn

  ReplyDelete
 10. አባ ሰላማ ብሎግ?
  ከላይ አስተያየት ስሰጥ ትክክለኛውን መልስ ለማግኘት ወደ ሊቃውንቱ እንድትሔዱ አቅጣጫን ጠቆምኩ’ንጂ ‘መልስ’ ነው ብዬ የተረዳሁትን አላስቀመጥኩም። ስለ ብሎጋችሁ አጠቃላይ ግምገማ ስሰጥ ግን ስለ ማሕበራትና ግለሰቦች ወዘተ በተመለከተ የምታቀርቡት ሐሳብ እርስበርሳችሁ መልስ ስለምትሰጣጡ ግድ የለም። ‘ትምህርተ ሐይማኖት ነክ ጉዳዮች’ ስታቀርቡ ግን እውን እርማት የሚያስፈልገው ብቻ ለውይይት ብታቀርቡት ግቡን ይመታል፤ ይሁን እንጂ የኔታዎችን ሳትጠይቁ አጣምማችሁ የምታቀርቡ ከሆናችሁ የምትጠባበቁት የሰማይ ዋጋ ማስጎደል ብቻ ሳይሆን ተከታዮቻችሁንም ‘አንትሙ ተአምርዎሙ እምትርጓሜሆሙ ወእምፍሬሆሙ’ ነውና ‘ቴቄል’ ያደርጓችዃል።

  ReplyDelete
 11. so funny 'yetfatachew zemen eruk ayhonm' ye emayen le abaye

  ReplyDelete
 12. የተሳሳተ ትምህርት ማረም እንጂ፡ ምክንያት መስጠት ራሱ ወደ ሌላ ስሕተት መግባት ነው።
  እኛ የምናመልከው፡ እኛን የፈጠረ በቀራንዮ መስቀል ደሙን ኣፍስሶ የታረቀን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።
  ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ ኣምላክ ድንግል በሒልናሃ ወድንግል በሥጋሃ፡ ኣምላክን ለመውለድ የበቃች ቅድስት እናታችን ናት እናከብራታለን እንጂ፡ ኣናመልካትም፡ ኣንሰግድላትንም።
  Anonymous በሚል ስም የጻፈ፡ ሰው ግን በእጅጉ በትርጉም ላይ ተሳስቶኣል።
  ዐረየ = እኩል ሆነ የሚል ትርጉም ብቻ ነው ያለው እንጂ፡ ተመሳሰለ የሚል ትርጉም በማንኛውም የግእዝ ትርጉም የለም።
  መሰለ = የሚለውግ ግስ ራሱ የቻለ ስለ ሆነ ተመሳሰለ ከዚህ ግስ የወጣ ነው።
  ተመሳሰለ ቢባልም፡ እግዚኣብሔርን ያህል የሚመስል ፍጡር ፈጽሞ ኣይኖርም።
  እሱ ቅዱስ ነው እኛ ግን ብቅድስናው ነው የተፈጠርነው፡
  እሱ ምሉእ በኩሉ ወበኩሎሄ፡ ነው እኛ ግን ድሩትና ውሱን ነን፡ እና፡ በእግዚኣብሔር ዙርያ፡ ማንንም ማተካከል፡ ማመሳሰል እንዳንዳፈር፡ ብእጅጉ ጥንቃቄ ኣስፈላጊ ነው።

  ReplyDelete
 13. "ወይም የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት እንዴት እንደሚፈቱት ጠይቁ!"


  የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንታት እኮ እንዲህ የሚጽፉ እና የሚያስጽፉት ተሀድሶች ናቸው:: ሌላ ከየት ሊመጣልህ ነው? ከአጸደ ነፍስ? ሰዎች ይህን ግልጽ እውነት ካላመኑ ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ አያምኑም - ሉቃ 16:31

  ይህኔ አንዱን ኦሪታዊ ጨለማ ደብተራ ይሆናል አንተ ሊቃውንት የምትለው::

  ኦ ነኝ

  ReplyDelete
 14. guys our church should reform now . mk stop and look your self

  ReplyDelete
 15. ማኅበረ ቅዱሳን እነዚህን ችግሮች በደንብ ያውቃል፡፡ ስለፖለቲካ እንጂ ስለነፍስ ግድ እንደሌለው አያችሁ፡፡ ይህ ሁሉ ዘመቻ እያደረገ ያለው ሒሳቡን ኦዲት አድርግ ስለተባለ ነው፡፡ ሒሳብና ሃይማኖት ምን አገናኘው ማኅበሩ ግን የበግ ለምዱ እንዳይገለጥ፣ እኔ ከምወጣበት ቤት ማንም እንዳይኖር እያለ እየተፍጨረጨረ አለ፡፡ በእውነት የአገሬ ሕዝብ በሳል ነው፡፡ ለክተት አወጁ ዝም በማለት አስደንግጦታል፡፡ አባ ጳውሎስም ሆኑ አባ ሰረቀ ሌሎችም በማኅበሩ የተጠሉ አገልጋዮች በምንም ቢጠየቁ የማያሳፍሩ ሊቃውንት ናቸው፡፡ እነርሱ ወጥተው ማን ይግባ ባለቤት ወጥቶ ደባል ይግባ በጋሻውስ እስከዚህ ክፉ ሰው ነው ወይ አሰግድስ ተርቦ ተጠምቶ ያገለገለ አይደለም ወይ እነዚህ ማኅበርተኞች ለዚህች አገር መዓት ሊያመጡ ነው፡፡ እነዚህ ወገኖች አምላክ አላቸው፡፡ ፈራጃቸው ትልቁ ጌታ ነው፡፡

  ReplyDelete
 16. 3rd submission

  Mariaminem hone Meskelen makiberu aykefam... However, it is true that all the venerations at our church have gone beyond what it should be and have at times reached the level of worship. Venerating St Mary, the Cross and the other saints is a well established tradition among all Orthodox Christians. In that case, it is not plausible to state that Emperor ZereYacob introduced those traditions. If he did that at EOTC, who introduced those traditions at the Coptic church, at the Greek Orthodox church, at Russian Orthodox church, at the Catholic church etc...? I hope you would not say ZereYacob...

  It is true that Emperor ZereYacob killed the Deqiqe Estifanos sect and made the said traditions like a cult. It is also true that some of the writings (dersets) at our church are out of touch with the core faith. The solution is not to embrace Protestantism, but to have a well deserved reform that would clean some of the dusts thrown at our Church over the years. Deacon Lule seems to have embraced protestantism, which we need to fight with all our force. We are Orthdox and we will remain so. We just need to focus our energy and attention on Jesus Christ and follow His word.

  Because of the false hopes that Defteras have spread, almost all EOTC followers care less for the word of God while dying for compliance with humanly created rules and customs. For example, if you go to northern Ethiopia, most EOTC followers take murder and superstition as normal while they take working on the a day dedicated to one of the famous saints as a big offence to God. Yetelesene mekabir malet kezihe belay min ale? Getam "tinigine tateralachu neger gen gemelen tewitalachhu" bilo tenagirowal.

  ReplyDelete
 17. ለ ሚ/ር “ኦ” [lulu]
  የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ከምትተች ለምን ከእግራቸው ሥር ቁጭ ብለህ ርቱዕ ቀለማቸውን አትቀጽልም? “ኦ ነኝ” ብለህናል እውነትም ኦ-‘ዜሮ ማይንድ’ ነህ። ለመሆኑ “ይህኔ አንዱን ኦሪታዊ ጨለማ ደብተራ ይሆናል አንተ ሊቃውንት የምትለው::” ስትል “ደብተራ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ ታውቀዋለህ? እኔ እስከማውቀው ድረስ ‘ደብተራ’ ድንኳን እንጂ የሰው ስም ነው ብሎ ያስተማረኝ መምህር የለም። “አይ! ደፍተራ ለማለት ፈልጌ ነው” የሚል ሰንካላ ማስተባብያ ብትፈጠርም እንዳንተ ያልተማሩ ያዳቀሉት እንጂ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች “ደፍተራ” የሚባል ፈጽሞ የለም። ምናልባት የውጭ ቋንቋ ደፍተር/defter/ የሚባል አለ’ንጂ። ታድያ አንተ ፊደልና የቃል ትርጉም ለይተህ ሳታውቅ እንዴት አድሳለሁ ብለህ ወደ ‘ፍካሬ ሚስጢር’ ጥልቅ ልትል ቻልክ? በውኑ ካንተ የማሕበረ ቅዱሳን አባላት አይሻሉም? ቢያንስ እነሱ ገድላትና ድርሳናት ቢያደነቁሯቸውም በከፊል ቢሆንም ያገለግላሉ። እንዳንተ አስመሳይ የሆኑትንና የማሕበሩ ተኩላ-መሪዎችን በመተው ማለቴ ነው።

  ReplyDelete
 18. please read what is written by d.hibret yeshitla on gebrher.com .it is written the real detail of this topic.

  ReplyDelete
 19. Thanks sharing the link Anonymous @ 10:52

  I have read what is written from gebrher.com. I like the fact that he admited that there is a problem in the amharic translation. They question you may need to ask is how much of ye fetari misgana we can give them (for St Mary and to the object) if there is any? Ke amelekowem likafelu neew ?

  ReplyDelete
 20. Anonymous September 25, 2011 10:32 AM

  Brathere fidel sentaki... ብ -ፍ

  tele us yuor likawente betekristians.

  ReplyDelete
 21. This is what written on the bible
  matew 10;2 enanten yemikebel enen yikebelal
  zetseat 7;1 .egziabher musen alew ene leferon amlak adrege shomehalehu
  mez 81(82)1-8 egziabher beamalekt mahber kome ...enegen amalekt nacheu hulachehum yeleul lijoch nachehu,... y
  yoha 10;34 ene amalekt nachhu alku

  ReplyDelete
 22. 2nd koro.5;20 egna bkerestos fanta kerestosen meslen ende kerestos enelemenalen.
  yoha14;13 bene yemiamen ene yemaderegewen yadergal kezihim yebelete yadergal.
  mate 5;14 ene yealem berehan negn.
  yoha9;12 enante yealem berehan nachehu.
  1st koro 6;2 kedusan bealem lay endiferdu atawkumen?
  matew19;28-29 ... enante degmo be12 yesrael neged leteferdu be 12 wenber tikemetalacheu

  ReplyDelete
 23. engedih min enelalen lekidusanu yehin hulu yetsega berehanenetn,yetsega ferajeneten,yetsega amlakeneten setoal.lersu degmo cherenetun genzeb aderege.etsub etsub.menker egziabher belael kidusanihu tebloalena.
  welete tewahido negn

  ReplyDelete
 24. ene gin alem leene ketesekelebet enem lealem ketesekelkubet yegetachen yeeyesus kirestos meskel bekel lela timkihit kene yerak.gelatia;6;14
  mez131(132);7 egrochu bemikomubet sefra enesegdalen. getachen demun yafesesebet ke 6-9 seat egrochu yekomubet meskel new.andem bemahesenwa yeteshekemechew emebetachen nat.
  1sr filipsios.bizuwoch lekrestos meskel telatoch honew yimelalesalu.bizu gize selenesu alhu eyalekesku alhu.

  ReplyDelete
 25. anonymus @11;39
  engedih yemisema joro yalew yesma .letebib andit kal tebekawalech ena tebiban enhun enastewl.yebahriy ena yetsega genzebin eneley,kelay yetezerezerut hasabochh tiyakehin besew sayhon beegziabher hasab yimelesaluna.lehulachen mastewalen yesten,.
  welete tewahido

  ReplyDelete
 26. where is my comment?

  ReplyDelete
 27. tewew lelawen deferete ye ewekete manese selehone enalefewalen
  eshi mariam selematawek enji betawik tikota neber belehal shi mariams selematawik altekotachim tadia yemiyawekew Fetari mariamnena mesekelen kene ekul lemin aderegachehu belo aletekotam esum ayawekim malete new?

  ReplyDelete
 28. አይ አባ ሰላማ!"ከመናፍቅ ትርጓሜ ከጫት ልምላሜ አይጠፋም" እንዲሉ አበው ሆኖ እንጂ አሁን ሊቃውንቱ የአምላክና የድንግል ማርያም የመስቀልና የእግዚአብሔር ደረጃ ይጠፋቸዋል?አንተ "ዲያቆኑ" እንኳን ይገባህል እንኳን ምዕመናን።ይልቅ ትርጓሜውን ተወውና ከዲ. ኅብረት የሺጥላ ትምህርት ሥር ተቀምጠህ ስለእመቤትህና ከቀስት ፊት ስለምታመልጥበት አርማ ደረጃ ተማር።እናመሰግናለን በዚህ ሕጸጽ ምክንያት ሌላ ቁም ነገር ተማርን።ምን አትለኝም?አላዋቂነታችሁንና ተልዕኳችሁን።

  ReplyDelete
 29. Asmesayoch! Orto timeslalachihu gin k'ort'o nachihu.Asmesayoch! Orto timeslalachihu gin k'ort'o nachihu.

  ReplyDelete
 30. ‹‹የፈጣሪ ምስጋና ይገባቸዋል››
  መስተብቁዕ ዘመስቀል በመባል የሚታወቀው የቤተ ክርስቲያናችን የጸሎት መጽሐፍ ‹‹ለእነዚህ ለሁለቱ ፍጥረታት›› ማለትም ለመስቀልና ለእመቤታችን ‹‹ስብሐተ ፈጣሪ ይደልዎሙ›› ይላል፡፡ ይህም ‹‹የፈጣሪ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡›› ማለት ነው፡፡ ለመሆኑ ፍጡርን ‹‹የፈጣሪ ምስጋና›› ማመስገን ተገቢ ነውን?

  እንደሚታወቀው ምስጋና ሁሉ የፈጣሪ ነው፡፡ በአጭሩ እግዚአብሔር የምስጋና ባለቤት ነው፡፡ የእርሱ የሆነውን ነገር ሁሉ ‹‹የእግዚአብሔር ቤት፣ የእግዚአብሔር ሰው፣ የእግዚአብሔር መላእክት … ወዘተ›› እያልን እንደምንገልጽ ሁሉ ምስጋናም የእርሱ የባሕርይ ገንዘብ ነውና ‹‹የፈጣሪ ምስጋና›› እንላለን፡፡

  ሁላችን ቀንና ሌሊት በምንደግመው የአቡነ ዘበሰማያት ጸሎት ውስጥ ይህ ሐቅ ተቀምጧል፡፡ ‹‹እስመ ዚአከ ይእቲ መንግሥት ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም›› ይህም ‹‹መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ምስጋናም ለዘላለሙ አሜን!›› ማለት ነው፡፡ (ማቴ6.13) በዚህ ጥቅስ መሠረት መንግሥተ ሰማያት የማን ናት? ስንባል የፈጣሪ እንደምንለው ሁሉ ምስጋና የማን ነው ስንባልም የፈጣሪ ነዋ! እንላለን ማለት ነው፡፡

  ስለዚህ እውነት ቅዱሳት አዋልድ መጻሕፍትም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተባብረው መስክረዋል፡፡ የቅዳሴና የሰዓታት መጻሕፍት ‹‹ስብሐቲሁ ዘእምኀቤሁ ወውዳሴሁ እምዚአሁ›› ይላሉ፡፡ ይህም ‹‹ክብሩ ከእርሱ የሚገኝ ነው፡፡ ምስጋናውም ከእርሱ ነው›› ማለት ነው፡፡ ምስጋና ከእርሱ የሚገኝ ነውና ‹‹የፈጣሪ ምስጋና›› ይባላል፡፡

  ስለዚህ የጸሎት መጽሐፉ ‹‹የፈጣሪ ምስጋና›› ሲል ከፈጣሪ የተገኘ፣ ገንዘብነቱ የእርሱ የሆነ ምስጋና ማለት ነው፡፡ በተጨማሪም ለቅዱሳን ይቀርብ ዘንድ እርሱ የፈቀደው ምስጋና ማለትም ይሆናል፡፡ በዚህ ጥቅስ ለእመቤታችን ለድንግል ማርያምና ለመስቀል ‹‹የፈጣሪ ምስጋና ይገባቸዋል›› ማለት በተብራራው መሠረት እርሱ የፈቀደውና ገንዘብነቱ የእርሱ የሆነ ማለት ነው እንጂ ለእርሱ የሚቀርበው ዓይነት ምስጋና ይገባቸዋል ማለት አይደለም፡፡ እርሱ አምላክ ነውና የአምልኮ ልዩ ምስጋና ይቀርብለታል፡፡ ለፍጡራን ደግሞ እርሱ የፈቀደውና ከእርሱ የተገኘ የጸጋ ምስጋና ይቀርብላቸዋል፡፡  ፈጣሪ ገንዘቡ ከሆነ ምስጋናው ለቅዱሳንና ለጻድቃን በፈቃዱ እንዲመሰገኑ ይሰጣቸዋል፡፡ እርሱ ለጋስ ጌታ ነውና፡፡ ‹‹ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ›› የሚሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ሐረጋት ይህን የሚያሳዩ ናቸው፡፡ (2ጴጥ1.4) ምስጋና የባሕርይ ገንዘቡ ነው፡፡ የዚህ ጊዜ እነርሱ የሚመሰገኑበት ምስጋና ‹‹የፈጣሪ ምስጋና›› ይባላል፡፡

  እግዚአብሔር በእውነቱ ለቅዱሳን ያልሰጠው ምን አለ? ‹‹ሰላሜን እሰጣችኋለሁ›› ብሎ ሰላሙን ሰጣቸው፡፡ ፍቅሩን ሰጣቸው፡፡ ‹‹ትፈርዳላችሁ›› ብሎ ፍርድን ሰጣቸው፡፡ ታዲያ ምስጋናውን የማይሰጥበት ምን ምክንያት አለ? ቅዱስ ጳውሎስ የገዛ ልጁን ሊሰጠን ያልሳሳው አምላካችን ‹‹ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም›› ያለው ስለዚህ ነው፡፡ (ሮሜ8.32) ከዚህ የተነሣ እግዚአብሔር ለቅዱሳን ምስጋናውን ሰጣቸው ስንል ቅንጣት ታህል አንጠራጠርም፡፡  ቅዱሳን የሚመሰገኑት ምስጋና ‹‹የፈጣሪ ምስጋና›› ካልተባለ ታዲያ የማን ሊባል ነው? የቅዱሳን የራሳቸው ምስጋና ነው እንዳንል ፍጡር ከባሕርይው የሚገኝ ምስጋና የለውም፡፡ ሰይጣናዊና የሐሰት ምስጋናም አስጸያፊ ነውና ለቅዱሳን የሚቀርብ አይደለም፡፡ ይህ ዓይነቱ ምስጋና ጊጉያን (በደለኞች ሰዎች) ለጠንቋዬችና ለአስማተኞች ለራሱም ለሰይጣን የሚያቀርቡት ምስጋና ነው፡፡ ስለዚህ ለቅዱሳን እግዚአብሔር ራሱ ፈቅዶ የሰጣቸውን ‹‹የፈጣሪ ምስጋና›› ለእነርሱ ማቅረብ ተገቢ ነገር ነው፡፡

  አንዳንዶች ግን የቅዱሳንን ምስጋና ለመቃወምና እርሱም ፈቅዶ ያልሰጣቸው አስመስሎ ለመናገር ‹‹እኔ እግዚአብሔር ነኝ ስሜ ይህ ነው ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።›› የሚለውን ጥቅስ ይጠቅሳሉ፡፡ (ኢሳ42.8) ይህ ጥቅስ እግዚአብሔር ለቅዱሳን ምስጋናዬን አልሰጥም የሚል አንድምታ ፈጽሞ የለውም፡፡ ነገር ግን የሚል አስመስሎ መጥቀስ ጥቅሱን በትኩረት አለመመልከትና ክህደትን ሊያሳይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ጥቅሱ በግልጽ የሚለው ‹‹ምስጋናዬንም ለተቀረጸ ምስል አልሰጥም›› ነው፡፡ ታዲያ እኛስ ብንሆን እግዚአብሔር ምስጋናውን ለቅዱሳን ሰጥቷል አልን እንጂ ለተቀረጹ ምስሎች ምስጋናውን ሰጥቷል መች አልን? ይህን ጥቅስ ጠቅሶ ለቅዱሳንም ምስጋና አልተሰጠምና ልናመሰግናቸው አይገባም ብሎ መከራከር ክብር ይግባቸውና ቅዱሳንን ‹‹የተቀረጹ ምስሎች›› ብሎ መስደብ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ጥቅስ እግዚአብሔር ለቅዱሳን ምስጋናውን ሲሰጥ ለተቀረጹ ምስሎችና ለጣዖታት ግን የማይሰጥ መሆኑን የሚያስረዳ መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡  በዲያቆን ኅብረት የሺጥላ

  hibretyes@yahoo.com

  ReplyDelete
 31. can you see hibret yeshitals facebook note for this question please,just read it

  ReplyDelete
 32. ምነው መናፍቃን እንዲህ በቤተክርስትያን ላይ ምቀኛ ኆናችሁ፣እንደቀናችሁ ግልጽ ነው፡፡አይደለም ለእመቤታችን እግዚአብሔር ለመረጣቸው ቅዱሳን ስግደት ይገባል፣ከዚህም አልፎ የጸጋ አማልክት ብሏቸዋል ምን ትሆኑ፡፡ሆዳችሁ አምላካችሁ ሃሳባችሁም ምድራዊ ስለሆነ ሰማያዊውን ሚስጥር ማስተዋል ተስኗችኋል፣ለዚህም ነው አዋቂ ይመስል ቅዱሱን አባት የምትሳደቡት፣ብቻ ልቦና ይስጣችሁ

  ReplyDelete