Monday, September 26, 2011

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ምን ምን ነገረን? ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኗል) ካለፈው የቀጠለ

5. ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር እየሆነ ነው
በዲያቆን ዳንኤል እይታ ማኅበሩ “በአመራር እጦት ምክንያት፣ ለቤተ ክህነቱ ችግር መፍትሔ ያመጣል ሲባል እርሱ ራሱ የቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር እየሆነ ነው፡፡” በመሠረቱ እንዲህ ዐይነት ራእይ የሰነቀው ራሱ ማኅበሩ ነው እንጂ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ችግሬን ይፈታልኛል ብላ እንዳላቋቋመችው ይታወቃል፡፡ ሌሎች እያሉ ያለው ደግሞ ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያኒቱ መፍትሔ ያመጣል ሳይሆን፣ ከተቋቋመበት ዐላማ ውጪ በሚያደርገው ኢመንፈሳዊ አካሄድና ያራምደዋል በሚባለው ድብቅ ፖለቲካዊ አጀንዳ ቤተ ክርስቲያንን ትልቅ ችግር ላይ ጥሏል ነው፡፡ አቦይ ስብሐት በቅርቡ “ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክህነት ዕዳ ነው” ማለታቸውን ከፍትሕ ጋዜጣ አንብበናል (ፍትሕ፣ ሐምሌ 15/3003 ገጽ 6)፡፡


የማኅበረ ቅዱሳን መሠረታዊ ችግር ቤተ ክርስቲያኒቱን እግዚአብሔር ወዳየላት ግብ ሳይሆን እርሱ ወደሚፈልገው አቅጣጫ ለመውሰድ ማሰቡ ነው፡፡ ዳንኤል እንደሚለው አሁን ያለው አመራር “የማኅበሩ ጉዞ ቤተ ክርስቲያኒቱን የት ለማድረስ እንደ ሆነ ግልጽ ግብ የለውም፡፡” እንዲሁም “ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን የተመሠረተ መሆኑን ዘንግቶታል፡፡” እነዚህ አገላለጾች የማኅበረ ቅዱሳን ራእይ በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ሥር ሆኖ ለቤተ ክርስቲያኒቱ እድገት የበኩሉን ድርሻ ማበርከት ሳይሆን፣ ቤተ ክርስቲያኗን እርሱ ወደሚፈልገው ግብ የማድረስ አካሄድ መሆኑን ይጠቁማሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ሆነ ግብ የማድረስ ሕልምን አንግቦ መንቀሳቀስ ተራ ነገር አይደለም፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሙሉ ለሙሉ የመቆጣጠር ዐላማን የሰነቀ ከፍ ያለ ምኞት ነው፡፡ ዳንኤልን ያበሳጨውም ይህ ሳይፈታ እየተባነነበት ያለው የቀድሞው አመራር ሕልም ይመስላል፡፡

ዳንኤል “ማኅበሩ በተመሠረተባቸው ዓመታት ገና የቤተ ክህነቱን ጠባይ ማወቅ፣ የውስጥ ውሕደትንም መፍጠር፣ ብሎም በቂ የሰው ኀይልም ማፍራት ነበረበትና አይታማም፡፡” ብሏል፡፡ ይህ ሁሉ ዝግጅት ማኅበሩ ያለ መብቱ ለሰነቀውና ከፍ ላለው ቤተ ክርስቲያኒቱን የመቆጣጠርና የመምራት ሕልሙ መንገድ ጠራጊ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህችን ታሪካዊትና ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ሰው እንደሌለባት ቆጥሮ፣ ከጊዜ በኋላ የተነሣ አንድ ማኅበር ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠርና በራሱ መንገድ ለመምራት ማሰቡና መንቀሳቀሱ ትልቅ ችግር ውስጥ ሊከተው እንደሚችል አለ ማሰቡ ነው የማኅበሩ ዋና ድክመት፡፡

6.   ማኅበረ ቅዱሳንና ሊቃነ ጳጳሳቱ
ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተ ክህነት ከሚታወቅባቸው ጠባያቱ መካከል አንዱ በየጊዜው ለሚፈጽማቸው ግድፈቶች፣ ስሕተቶችና ጥፋቶች የሚሰጠውን ማስተካከያ፣ መመሪያና ትእዛዝ አለመቀበል ነው፡፡ ይኸው ጉዳይ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በኩል ዘወትር ቅሬታ እየቀረበበት ነው፡፡ ማኅበሩም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏል፡፡ ይህ ለምን ሆነ ቢባል፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ አካል የሆነው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆኑ አንዳንድ ጳጳሳትን በግሉ ይዟል፡፡ ዳንኤልም የነገረን ይህንኑ ነው፡፡ ማኅበሩ ስትራቴጂክ አመራር የለውም፤ “አቡነ እገሌን አናግሬያቸው ከሚል ያለፈ የመረጃ መሰብሰቢያ መንገድም ሐሳብም የለውም”፣ “አቡነ እገሌን እገሌ አናገራቸው” ከማለት ያለፈ ሥራ እየሠራም አይደለም፡፡

ማኅበሩ አንዳንድ ጳጳሳትን በተለያየ ጥቅማ ጥቅም እንደ ያዘ ይነገራል፤ የተለያዩ መረጃዎችን ይዤባችኋለሁ እያለ በማስፈራራት የዐላማው መፈጸሚያ ያደረጋቸውም አሉ ተብሎ በሰፊው ይወራል፡፡ አንዳንዶቹም ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ይጠቅማል በሚል ቀና ሐሳብ ከጎኑ እንደ ተሰለፉ ይታወቃል፡፡ ሌሎቹም ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር በሚፈጥሩት ግጭት የጠላቴ ጠላት በሚለው ስሌት ሌላ ክፉ ቀን እስኪመጣ የማኅበሩ ደጋፊ ይሆናሉ ይባላል፡፡ ለእርሱ ያላደሩትን ጳጳሳት ግን በደጀ ሰላም ድረ ገጹ ላይ የተለያየ የስም ማጥፋት ዘመቻ ይከፍትባቸዋል፡፡

የማኅበሩ አመራሮች አንድ ችግር ተነሣ በተባለ ቁጥር መዋቅርን ጠብቀው ወደሚመለከተው አካል ሳይሆን የሚሄዱት ወደ አንዳንድ ጳጳሳት ነው፡፡ የእነዚህን ጳጳሳት ሥልጣን ተጠቅመውም የወጣባቸውን ትእዛዝ ያስገለብጣሉ፤ ሌላ ትእዛዝም ያስወጣሉ፡፡ ለምሳሌ፡- በቅርቡ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበሩ የሚያወጣቸውን መጽሔትና ጋዜጣ በሊቃውንት ጉባኤ እንዲያስመረምር የተሰጠውን መመሪያ አሻፈረኝ በማለቱ ጋዜጣውና መጽሔቱ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም እንዳይታተሙ ለማተሚያ ቤቶች ደብዳቤ ይጽፋል፡፡ ማኅበሩም መመሪያውን ተከትሎ በተመደቡለት የሊቃውንት ጉባኤ አባላት ጽሑፎቹን አሳይቶ ከማውጣት ይልቅ፣ በማን አለብኝነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የበላይ ጠባቂ ለተባሉት ሊቀ ጳጳስ ይነግራል፡፡ እርሳቸውም ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልእክቱን አስተላልፈው በዋና ሥራ አስኪያጁ በኩል በተጻፈ ደብዳቤ እግዱ እንዲነሣ ይሆናል፡፡

እዚህ ላይ ልብ ማለት የሚገባው የማደራጃ መምሪያው የበላይ ጠባቂ የተባሉት ሊቀ ጳጳስ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት በ29/9/2003 ዓ.ም. አመልክተዋል፡፡ ያመለከቱት በቃል ይሁን በጽሑፍ ግልጽ አይደለም፡፡ ነገር ግን ማመልከቻቸው ወይም ማሳሰቢያቸው ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የወጣ አይመስልም፡፡ ምክንያቱም ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በእግድ ማንሻ ደብዳቤው ላይ፣ ቀረበልኝ ያለው ማመልከቻ ቀን ብቻ እንጂ የደብዳቤ ቁጥር አልተጠቀሰበትም፡፡ ደብዳቤውና ማሳሰቢያው የሊቀ ጳጳሱ እንጂ የማደራጃ መምሪያው እንዳልሆነ ያስረዳል፡፡ ይህም ማኅበሩ የእዝ ሰንሰለትን ሳይጠብቅ እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ድረስ የተዘረጋ እጅ እንዳለው ያሳያል፡፡ በተሐድሶ እንቅስቃሴ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ እያለ በየአዳራሹ በስውር በጠራቸው ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሮች ላይ እየተገኙ ቡራኬ ሲሰጡ የነበሩትም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ናቸው፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ‘ለአንዳንድ ጳጳሳት አሳይቻለሁ’ በሚል ምክንያት የሚፈልገውን ሁሉ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ወደ ሲኖዶስ አቅርቦ ባላስወሰነበት ሁኔታ ለአንዳንድ ጳጳሳት በግል አሳይቻለሁ የሚለው ጉዳይ፣ የሲኖዶስ ውሳኔ ተደርጎ እንዲወሰድለትም ያላሠለሰ ጥረት ያደርጋል፡፡ በቅርቡ የሰዎችን ትኩረት ለመሳብና ገቢ ለማሰባሰብ በከፈተው የተሐድሶ መናፍቃን ዘመቻ ጉዳይ ላይ ዋና ጸሓፊው ማኅበሩ ጥናት እንዳደረገና የጥናቱን ውጤት ለብፁዓን ጳጳሳትና ለሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ማድረሱን ለዕንቁ መጽሔት ገልጿል (ሰኔ 2003)፡፡ ነገር ግን በየትኛው የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ቀርቦና ውይይት ተደርጎበት ውሳኔ አገኘ? ተብሎ ቢጠየቅ ምላሽ የለውም፡፡ ስለዚህ ወደ ግለሰቦች እንጂ ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ያልቀረበው ጉዳይ የራሱ የማኅበረ ቅዱሳን እንጂ፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ዕውቅና የተሰጠው የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳይ ነው ማለት ግን ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ለዚህም ነው ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዐትና ቀኖና ውጪ የተከፈተው የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲቆም ቅዱስ ፓትርያርኩ በቁጥር ል/ጽ/598/1604/03 በቀን 25/11/2003 ዓ.ም. በጻፉት ደብዳቤ መመሪያ የሰጡት፡፡
   
7.   ማኅበረ ቅዱሳን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስና በአባ ሠረቀ ላይ የያዘው አቋም

“ማኅበሩ አቡነ ጳውሎስን በተመለከተ የተለየ አቋም መያዝ የጀመረው መቼ ነው? እርሳቸው ማኅበሩን ሊያፈርሱ ነው ብሎ መሥጋት ከጀመረ በኋላ፡፡ አባ ሠረቀንም ቢሆን እኮ ዛሬ ዛሬ በእምነት ችግር ይከሳቸዋል እንጂ፣ ከእርሳቸው ጋር ያለው ዋናው ችግሩ ማኅበሩ መነካቱ ነው፡፡ አባ ሠረቀ ማኅበረ ቅዱሳንን ሳይነኩ የፈለጉትን ቢሆኑ ኖሮ አይናገራቸውም ነበር፡፡” ይህ የዳንኤል አነጋገር ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ማንነት፣ አቋምና የወደፊት ራእይ የሚያስተላልፈው ሌላ መልእክት አለ፡፡ በይቅርታ ጽሑፉ ውስጥም በዚህ ነገር ላይ ያለው ዐቋም እንዳልተለወጠ ግልጽ አድርጓል፤ እንዲህ በማለት፡- “በዚያ ጽሑፍ ላይ ስማቸው የተነሡ ግለሰቦች አሉ፡፡ እኔ ለመሞገት የፈለግኩት ማኅበረ ቅዱሳን በእነዚያ ግለሰቦች ላይ የያዘውን አቋም አይደለም፡፡”

በቅድሚያ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ዐላማውን ለማሳካት የተቋቋመ አንድ ማኅበር፣ ሌላ ድብቅ አጀንዳ ከሌለው በቀር በቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች ላይ “አቋም መያዝ” ለምን አስፈለገው? ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮም ሆነ ሥርዐት ተጠያቂዎቹም ሆነ ተጠሪዎቹ እነርሱው አይደሉምን? አቋም መያዝ የሚለው አነጋገርስ ሃይማኖታዊ ነው ወይስ ፖለቲካዊ? … ሌሎችም ብዙ ጥያቄዎች ይነሣሉ፡፡ መቼም “አቋም መያዝ” የሚለው ሐሳብ የሚመነጨው ማኅበሩ ከያዘው የተደበቀ ዐላማ አንጻር መሆኑን መገመት አይከብድም፡፡ ከዚህ ባሻገር ማኅበረ ቅዱሳን ‘ለኦርቶዶክስ ትምህርትም ሆነ ሥርዐት ዋና ተጠሪው እኔ ነኝ፤ እኔ ከምለው ውጪ የሚያስብና የሚናገር ሁሉ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዶግማና ቀኖና ያፈነገጠ ነው’ ብሎ ለመፈረጅ የሚንጠራራ አቅሙን አያውቅ ማኅበር መሆኑን ይጠቁመናል፡፡

እንደ ዳንኤል ጽሑፍ ከሆነ ማኅበረ ቅዱሳን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እና በአባ ሠረቀ ላይ አቋም መያዝ የሚገባው ዛሬ እርሱን ስለ ነካኩት ሳይሆን ቀደም ብሎ ነበር፡፡ አቋም የሚይዘው ከምን አንጻር እንደ ሆነ ግልጽ ባያደርግም፣ አሁን ያለው አመራር አባ ሠረቀን በእምነት ችግር እንደሚከሳቸው ጠቁሟል፡፡ በቅዱስ ፓትርያርኩም ላይ ከዚህ የተለየ አቋም እንደማይኖረው ይገመታል፡፡ ስለዚህ ቀደም ተብሎ ነበር የእምነት ችግር አለባቸው የሚል አቋም መያዝ የነበረበት ማለት ነው፡፡ እርምጃ ለመውሰድ አቋም መያዝ የመጀመሪያ ደረጃ ነው፡፡ ቀስ በቀስ ፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስም ሆኑ አባ ሠረቀ ብርሃን በተሐድሶነት ተፈርጀው ከቤተ ክርስቲያን የሚባረሩበት መንገድ መመቻቸት አለበት የሚል ይመስላል የዳንኤል ሽፍንፍን ሒስ፡፡

መስከረም 12/2002 ዓ.ም. በተደረገው የሰላም ጉባኤ ላይ ማኅበሩ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ያለው አቋም የማያወላውል እንደ ሆነ በቃለ ጉባኤው ላይ ተገልጿል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ደግሞ ግልጽ ያልሆነ አቋም መያዙን ዳንኤል እየነገረን ነው፡፡ በሌላ በኩል ቀደም ብሎ የነበረው አመራር የያዘው አቋም፣ አሁን ያለው አመራር ወቅትን እየጠበቀ ከሚይዘው አቋም ጋር የተለያየ መሆኑ ዳንኤልን ያስከፋው ይመስላል፡፡ ያሁኑ አመራር ካልተነካ አቋም የማይዝና አገር ደኅና የሚል፣ ሲነካ ደግሞ አገር ይያዝልኝ ብሎ የተለያየ ስም እየለጠፈ አቋም ይዣለሁ የሚል ተለዋዋጭ ጠባይ ያለው አመራር ነው ማለት ነው፡፡ በአጠቃላይ ይህ አቋም የመያዝ አካሄድ ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አሳቢ መሆኑን ሳይሆን፣ ማራመድ የሚፈልገው ሌላ ድብቅ አጀንዳ አለው የሚለውን የብዙዎችን እምነት ያጠናክራል፡፡

8.   ማኅበረ ቅዱሳን ኢኮኖሚያዊ ጡንቻውን ማፈርጠም ይፈልጋል
“ሰሞኑን ተሐድሶን በተመለከተ ገለጣ ለባለ ሀብቶች ሲደረግ ባለ ሀብቶች ከአንድ በመመሥረት ላይ ካለ ባንክ ጋር ተባብረው እንዲሠሩ እየተነገራቸው ነው፡፡ ይኼንን ባንክ በተመለከተ አመራሩ የወሰነው ነገር እንደሌለ ዐውቃለሁ፡፡ ውሳኔው የተላለፈው በስውሩ አመራር በመሆኑ፡፡” የሚለው ዳንኤል፣ ማኅበረ ቅዱሳን በኢኮኖሚ ረገድም ጡንቻውን ማፈርጠም እንደሚፈልግ ፍንጭ ይሰጠናል፡፡ ሕጋዊ መንገድን ተከትሎ እስከ ተሠራበት ድረስ ይህ በራሱ ችግር ላይኖረው ይችላል፡፡ ነገር ግን ማኅበሩ ኢኮኖሚያዊ ክንድኑ ማፈርጠም ያስፈለገው ለምንድን ነው? የሚለው ጉዳይ ነው መታለፍ የለበትም፡፡

እንደሚታወቀው ማኅበሩ ሰንቆ የተነሣው ቤተ ክርስቲያኒቱን የመቆጣጠርና የመምራት፣ ድብቅ አጀንዳውንም የመፈጸም ራእይ እንደ ሆነ ይታወቃል፡፡ ለዚህ ተፈጻሚነት ከሚረዱት ነገሮች አንዱና ዋናው ደግሞ ኢኮኖሚያዊ አቅምን ማጎልበት መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ዛሬም ለጠቅላይ ቤተ ክህነትና ለማደራጃ መምሪያው አልታዘዝ የሚለው በአንድ በኩል እጅግ የፈረጠመ ኢኮኖሚያዊ ክንዱን ተማምኖ ይመስላል፡፡ ማኅበሩ የተለያዩ የንግድ ተቋማትን ከፍቶ እየተንቀሳቀሰ ነው፤ ኦዲት አስደርጌያለሁ እያለ ቢያስተባብልም፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ግን ዘወትር ለ19 ዓመታት ኦዲት ያልተደረገ ገንዘብና ንብረት ነው እያንቀሳቀሰ ያለው እያለ ማኅበሩን ይከስሳል፡፡

በቅርቡ እንኳ ይኸው ጉዳይ ከማደራጃ መምሪያው ዐልፎ ማኅበሩና ጠቅላይ ቤተ ክህነት ደብዳቤ እንዲጻጻፉ እስከ ማድረግ ደርሷል፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት በቁጥር 7205/16187/2003 በቀን 30/10/2003 በጻፈው ደብዳቤ ማኅበሩ ሒሳቡን ገለልተኛ በሆኑ ወገኖች ኦዲተር እንዲያስደርግ አዝዞ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ማኅበሩ ትእዛዙን ተቀብሎ የተባለውን ከመፈጸም ይልቅ በቁጥር ማቅሥአመ/30/02/አ/03 በቀን 6/11/2003 ደብዳቤ ጽፎ፣ ሒሳቡን ካሁን ቀደም በውጭ ኦዲተር ማስመርመሩንና የ2003 ዓ.ም. ሒሳብን ኦዲት እንደሚያስደርግ፣ ከዚህ ውጪ “በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ‘የአስተዳደር ማኔጅመንት ኰሚቴ’ የተወሰነውን ውሳኔ ለማስተናገድ አስቸጋሪ መሆኑን” አስታውቋል፡፡ አክሎም ለቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት በሙሉ ኦዲት የመደረግን አስፈላጊነት ጠቅሶና ሽቅብ ወጥቶ፣ “የማኅበረ ቅዱሳንን የገንዘብና የንብረት እንቅስቃሴ ብቻ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያኒቱ በጀት የሚተዳደሩትን የቤተ ክርስቲያኒቱን አካላትና ልዩ ልዩ ድርጅቶችም በተመሳሳይ ሁኔታ በውጭ ኦዲተሮች እንዲመረመሩ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ለመጠቆም እንወዳለን” ሲል ገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ “… ማኅበሩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር የተቋቋመ በመሆኑ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ የሚወጡ ትእዛዞችን ማክበርና መፈጸም የሚገባው ከመሆኑም በላይ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ገለልተኛ በሆኑ ወገኖች ኦዲት እንዲደረግ የማዘዝ ሥልጣን ያለው በመሆኑ የላካችሁት ደብዳቤ አግባብነት የለውም፡፡” በማለት የማኅበሩን ጥያቄ ውድቅ አድርጎ፣ ቀደም ሲል በታዘዘው መሠረት ሒሳቡን በገለልተኛ ወገን እንዲያስመረምር በቁጥር 7655/16187/2003 በቀን 2/12/03 በተጻፈ ደብዳቤ ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡
ማኅበሩ ኦዲት አስደርጌአለሁ እያለ ቢከራከርም፣ በማደራጃ መመሪያው ድረ ገጽ ላይ የወጣው ዘገባ እንዲህ ይላል፡፡ “ቤተ ክርስቲያኒቱ ማኅበሩ በውጪ ኦዲተሮች ኦዲት ማስደረጉን የምትደግፍ ቢሆንም ነገር ግን ማኅበሩ በሥሯ የሚገኝ አካል መሆኑን የሚያረጋግጥ ከሆነ በራሷ ኦዲተሮች ኦዲት እንዲደረግ ማዘዟ ትክክለኛ እና ጤናማ አካሄድ እንደ ሆነ በትከክል ታምናለች፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ማኅበሩ ላለመታዘዝ የሚጠቀምበት ምክንያት እንጂ በውጪ ኦዲተሮች ያስደረገው የአንድ ዓመት ብቻ እንደ ሆነ ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ግን መልሳ መላልሳ የምትጠይቀው 19 ዓመታት ሒሳብ ኦዲት እንዲደረግ እንጂ የሁለት ዓመት ወይም የሦስት ዓመት ብቻ አለመሆኑን በተደጋጋሚ ገልጻለች፡፡ ይሁን እንጂቁስል ያለበት ውሻ እንደልቡ አይጮህምእንደሚባለው 19 ዓመታት ኦዲት የሚሠራ ከሆነ ብዙ ችግር እንደሚገጥመው ከወዲሁ የሚሠጋ ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያኒቱን ትእዛዝ ለመቀበል እጅግ በጣም ተጸይፏል፡፡” (hh://www.eotcss.org, Augest 19,2003 7:45 p.m.)
ለበላይ አካል መታዘዝ ሲገባ በአልታዘዝ ባይነት ጸንቶ ሙግትና ክርክር ማንሣት ከየት የመጣ ነው? መንፈሳዊ ነኝ የሚለውን ማኅበርስ ሌላ ስም አያሰጠውምን? ማኅበሩ የታዘዘውን እንዳይፈጽም የከለከለው ከቶ ምን ይሆን? እንቢተኛና እልከኛ ጠባዩ? ወይስ የሚጠራጠረውና ራሱን ያላጸዳበት ነገር ኖሮ ይሆን? ሒሳቡ ቢመረመር ሊከተል የሚችል ተጠያቂነት እንዳያስከትልበት? ወይስ የማኅበሩ አጠቃላይ ካፒታል እንዳይታወቅ ተፈልጎ? … መልሱን ለአንባቢ መተዉ ሳይሻል አይቀርም፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት ደብዳቤዎች ቀደም ብሎ ማኅበረ ቅዱሳን በቁጥር ማቅሥአ/1050/02/ለ103 በቀን 5/08/2003 ዓ.ም. በጻፈው ደብዳቤ የማኅበሩ ሰብሳቢ የሆኑት ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም ገበያው የባንክ ሒሳቦችን ማንቀሳቀስን ጨምሮ፣ ማንኛውንም ሕጋዊ ጉዳይ ማኅበሩን ወክለው መፈጸምና ውክልናም መስጠት እንዲችሉ የውክልና ደብዳቤ እንዲጻፍላቸው ጠይቆ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የእዝ ሰንሰለትን ያልጠበቀው ደብዳቤ ወደሚመለከተው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የተመራ ሲሆን፣ ማደራጃ መምሪያውም የተጠየቀውንና ከዚህ ቀደም በቁጥር ማቅሥአ/1006/02/03 በቀን 27/07/03 ዓ.ም. የተጻፈለትን ለመፈጸም እንደሚቸገር ገልጿል፡፡ ምክንያቱን ሲያስረዳም፡- “ቤተ ክርስቲያኒቷ ገቢና ወጪአችሁን አሳውቁኝ ስትል፣ ያለውን አጠቃላይ የማኅበረ ቅዱሳንን የሒሳብ መዝገብ አመራሩ በግለሰብ ስም ለማዞር መንቀሳቀስ ጀመረ” በማለት እውነታውን የሚገልጸው ማደራጃ መምሪያው፣ ማኅበረ ቅዱሳን አክሲዮን ቢገዛ እና አጠቃላይ የማኅበሩ ጉዳይ በግለሰብ ፊርማ ቢንቀሳቀስ ያስከትላል የሚለው ችግር፤
“1. በቤተ ክርስቲያኒቷ ስም ማኅበሩ ያካበተው ንብረት ሁሉ የግለሰብ መጫወቻ ይሆናል ብሎ በመስጋቱ ማኅበሩ ቢፈርስም እንኳ ወራሹ በግልጽ በውስጠ ደንቡ ላይ የተገለጸ ስላልሆነ የቤተ ክርስቲያን ንብረት ተበዝብዞ ይቀራል ብሎ በመስጋት፤

“2. አጠቃላይ የማኅበሩ አሠራር ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የእዝ ሰንሰለት ወይም መዋቅር ይወጣል ብሎ በማሰቡ፤
“ከዚህ በፊት ፈጽሞ በውስጠ ደንቡ ያልተካተተ አዲስ ሐሳብ እና አሠራር በመሆኑ እና ይህን መሰል ችግሮችን በውስጡ ያዘለ ስለሆነ በአክሲዮን ጉዳይ ላይ የቀረበውን የማኅበረ ቅዱሳንን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጓል፡፡ ማደራጃ መምሪያውም ይህንን ሁኔታ የሚገልጸው የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ ከመበዝበዝ አኳያ ነው፡፡” ይላል ድረ ገጹ (ዝኒ ከማሁ)፡፡

ሳይጠቀስ የማይታለፈው ማደራጃ መምሪያው በድረ ገጹ ላይ ያስነበበው አስተያየት እንዲህ ይላል፤ “ማኅበረ ቅዱሳን በመንፈሳዊ ማኅበር ስም ተደራጅቶ ለትርፍ የተቋቋመ ማኅበር አለመሆኑን እየገለጸ፣ ነገር ግን ከሀገር ውጪ እስከ ሀገር ውስጥ በብዙ ሚሊዮን የሚያንቀሳቅሰው ገንዘብ በቤተ ክርስቲያኒቷ ስም እስከ ሆነ ድረስ ቤተ ክርስቲያኒቷ ልታውቀው ይገባል ብሎ ማደራጃው በማሳሰብ ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያኒቷ ስም ያግበሰበሰውን ገንዘብ ለማሸሽ የአክስዮን ግዢ መጠየቁና ሁሉም ሒሳብ በአንድ ግለሰብ ፊርማ ብቻ እንዲንቀሳቀስ መፈለጉ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም ሳይሆን ለንግድ ያለውን ፍቅር ያሳያል የሚል አቋም አለው፡፡”
   
9.   ማኅበረ ቅዱሳን እየተዳከመ ነው
ዳንኤል ማኅበረ ቅዱሳን አሁን የሚገኝበትን ሁኔታ ተስፋ በቆረጠ ልብ ነው የገለጸው ማለት ይቻላል፡፡ “ምናልባት የማኅበሩ አሠራርና አመለካከት ጊዜ ያለፈበት /ኤክስፓየር እያደረገ/ ያለም ይመስላል፡፡ ከዚህ በኋላ ማኅበረ ቅዱሳን በዚህ አስተሳሰቡ፣ አካሄዱና አሠራሩ ለውጥ አምጪ ሆኖ መቀጠል አይችልም፤ ቆሟል /ስታክ አድርጓል/፡፡ ምናልባት እንግሊዝኛ ተናጋሪ ቤተ ክህነት ሆኖ ሊቀጥል ይችላል፡፡” በማለት ማኅበሩ ወደ ውድቀት እያመራ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ መስፍን ነጋሽ እንደሚለውም ማኅበረ ቅዱሳን በአሁኑ ሰዓት “የመፍትሔው አካል የመሆን ጉዞን ወደ መጨረሱ በመቃረብ ላይ የሚገኝ፣ በእንግሊዝኛ የችግሩ አካል ለመሆን (ቤተ ክህነቱን ለመቀላቀል) በማዝገም ላይ ያለ ነው፡፡” (አውራምባ ታይምስ ሐምሌ 2003)፡፡ ይህ ተራ ሟርት ሳይሆን፣ በማኅበሩ እንቅስቃሴና አሁን ባለበት ተጨባጭ ሁኔታ የሚለካ ነው፡፡

ማኅበሩ በውድቀት ዋዜማ ላይ መሆኑን ከሚያሳዩት ነገሮች መካከል፡- ዳንኤል እንደ ገለጸው፣ ብቃት ያለው አመራር የሌለው መሆኑ፣ ማእከላት በቢሮ እጥረት እየተቸገሩ መሆናቸውና ከተሟላ ጽሕፈት ቤት ወደ ደሳሳ ጎጆ መሻገራቸው፣ የማኅበሩ ዐይን የሆኑት ሐመርና ስምዐ ጽድቅ መዳከማቸው፣ ዋና ክፍሉ መሪ ማጣቱ፣ ጋዜጠኞች ሲለቁ ሌሎች እንዲተኩ አለመደረጋቸው፣ ቢተኩም ከአቅም በታች የሚጫወቱ መመደባቸው፣ ማዕከላትና የግቢ ጉባኤያት መረሳታቸው፣ በማእከላት የገንዘብ ዕጥረት ማጋጠሙ፣ ለየግቢ ጉባኤያት አስተማሪነት በዝዋይ የካህናት ማሠልጠኛና በሌሎችም ማሠልጠኛዎች ከ500 በላይ መምህራን ቢሠለጥኑም ዐሥር እንኳ አለመገኘታቸው፣ በዋና ማእከል ደረጃ የመምህራን ቁጥር እየተመናመነ መሄዱ፣ በግቢ ጉባኤያት እየታየ ያለው የመምህራን እጥረት ጉባኤያቱን ወደ ግል ሰባክያን እንዲያተኩሩ ማድረጉ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን በየአጋጣሚው ከ40 ሺህ ያላነሱ የተመዘገቡ አባላት አሉኝ እያለ ማንም እንዳይነካው ከሚያስፈራራ ይልቅ፣ ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጣዊ ችግሮቹ የተነሣ ግን “አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም” ቢል ሳይሻለው አይቀርም፡፡ ዳንኤል እንዳቀረበው የመፍትሔ ሐሳብ ማኅበሩ ያለው ዕድል እንደ ገና መነሣት /ተሐድሶ ማድረግ/ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ግን ፀረ እንደ ገና መነሣት /ፀረ ተሐድሶ/ በመሆኑ ስታክ እንዳደረገ መቅረት እንጂ መታደስ ይሆንለታል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ሁለንተናዊ ተሐድሶ አድርጎ በትክክለኛው የወንጌል መንገድ መጓዝና ለቤተ ክርስቲያን ትእዛዝ መገዛት ቢጀምር ግን፣ በዘረጋቸው መዋቅሮቹ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት አያጠራጥርም፡፡

10.  የዳንኤል ስልታዊ “ይቅርታ”
ይቅር ተባብሎና ግንኙነትን አድሶ ጉዞን መቀጠል አስደሳች ነገር ነውና፣ ዲያቆን ዳንኤልን “ቀድሞም ባልዘፈንሽ ኋላም ባላፈርሽ” በሚል ተረት መጎንተል አያስፈልግም፡፡ እርግጥ የእርሱና የማኅበረ ቅዱሳን ውዝግብ በዲያቆን ዳንኤል ስልታዊ ይቅርታ የተደመደመ ይመስላል፤ ይቅርታ በትእምርተ ጥቅስ ውስጥ፤ - ዕንቁ መጽሔት እንደ ጻፈው (ነሐሴ 2003)፡፡

ዳንኤል የተወልን ጽሑፍ ይቅርታውን በጀመረበት የተረት መልእክት መሠረት በብዙዎች ዘንድ ቀሪ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ እርሱ እንዳለውና በጌታ ትንሣኤ ላይ እንደ ተወራው ግን ውሸት ነው ተብሎና እንደ ተራ ወሬ ተቆጥሮ የሚተው “ጊዜያዊ ድል” አይደለም፡፡ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ማንነት፣ አሠራር፣ ራእይና ግብ በቂ ፍንጭ የሰጠ ነው፡፡ በእርሱ እምነት አደባባይ ላይ የዋለው ጽሑፉ፣ ማኅበረ ቅዱሳን ከገጠመው ፈተና እንዲወጣና በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማነሣሣት የተጻፈ ነበር፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ያልታሰበ ውጤት አመጣ፡፡ በዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ እይታ ግን የዳንኤል ጽሑፍ እርሱ ሊቆጣጠረው በማይችል አስገዳጅ ሁኔታ እንዲጽፈውና እንዲሠራጭ ተደርጓል ብሎ ነው የሚያምነው፤ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሆኗል፡፡

ይቅርታዊ ጽሑፉ እጅግ ስልታዊ ነው፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን አመራር እንደ ተወሰነውና እንደ ተጠበቀው ከበደሉ ጽሑፍ ጋር ተመጣጣኝ አይደለም፡፡ ይቅርታ የተጠየቁትም በጽሑፉ በግል ስሜታቸው ተጎዳ የተባሉ ወንድሞች ናቸው እንጂ ማኅበሩ እንደ ማኅበር ወይም አመራሩ ይቅርታ አልተጠየቀም፡፡ በዚህ ላይ ዋና ዋና ጉዳዮች ታልፈዋል፤ ከምንም በላይ ደግሞ ስውር አመራር የለም ሲል አላስተባበለም፡፡

ይቅርታው በሱባኤው ውስጥ መቅረቡም ለዳንኤል የማምለጫ መንገድ የከፈተለት ይመስላል፡፡ “እስኪ መጻጻፉ ይብቃን” ሲልም በስልት አፈግፍጓል፤ ለዚህ ነው ስልታዊ ይቅርታ ማለት ያስፈለገው፡፡

ዳንኤል በመጀመሪያው ጽሑፍ በድሏቸዋል የተባሉትን ወገኖች በአግባቡ ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ፣ የውዝግቡ አካላት ያልነበሩትንና ማኅበሩ “ተሐድሶዎች” የሚላቸውን ወገኖች መንካቱ አስገራሚ ሆኗል፡፡ ተበዳዮች የተባሉትን ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ በጉዳዩ የሌሉበትን “ተሐድሶዎችን” መወረፍ ተበዳዮቹን እንደመካስ ይቆጠራል የተባለ ይመስል እነርሱን በመወረፍ ላይ ነው ያተኮረው፡፡

አይ ማኅበረ ቅዱሳን!!!

20 comments:

 1. guys great job , thank you brothers

  ReplyDelete
 2. Saint Elias has come!!! Everything is going to be straightened out soon!!! Watch and see!!!

  ReplyDelete
 3. ቤተክርስቲያን እንደዚህ አይነት ዓይናማ ጸሐፊያንን አያሳጣት። እንደምንጭ ውሃ ኮለል ያለጽሑፍ። ቢያነቡት የማይሰለች፤ የማይጎረብጥ፤ ሥረነገሩን አብጠርጥሮ የሚያሳይ። ሽሙጥ፤ዘለፋ፤ስላቅና ነቀፋ ብቻ አስተያየት በመስጠት ለተካኑ እርባና የሌለው እውቀት ለተሸከሙ፤ ስፍራ የሚያሳጣ ጽሑፍ። ወንድሜ በእግዚአብሔር ዘንድ አጋጣሚ ብሎ ነገር የለምና በሰዓቱ ከእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ ፈቃዱ ለሆነው ለዚህ ጽሑፍህ ዋጋ ሰጥተህ ቀጥልበት።
  ይደልዎ!!ይደልዎ!!ብለናል።

  ReplyDelete
 4. mone ena wereket yeyazewin ayilekim now we are in 2004

  Solomon

  ReplyDelete
 5. እንደዚህ ዓይነት ጽሑፍ ከነመረጃው እየተጣቀሰ በመቅረቡ በአጭር ጊዜ ባላምነውም ከረዥም ጉዞ በሗላ ለማመን ብቻ ሳይሆን ለግብራዊ-ሰልፍ እንደምገደድ ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ።
  ሌሎች ‘አርቲክል’ አቅራቢዎችም እንደዚህ ሰው ይልመዳችሁ!
  በርታ “በቃሉ”!

  ReplyDelete
 6. thanks god, the spinal chord of tehadiso menafkan is being beaten at every corner of the country by the unreserved effort of mk. now, tahadiso have no base.elelelelelele.LONG LIVE TO OUR CHURCH.

  ReplyDelete
 7. ant men serake yemtekawemewen atawekem tetekeke e/g yerdahe

  ReplyDelete
 8. realy nice touching and accepteable

  ReplyDelete
 9. woregnoch!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 10. ጦራችሁን በማኅበሩ ላይ ያበዛችሁት ለምንድነው አልላችሁም።ለማኅበረ ቅዱሳን ያላችሁን ፍራቻና ጥላቻ ስትገልጡ ለቤተክርስቲያኗ ያላችሁን ርህራሔ የለሽ አቋም ታንጸባርቃላችሁ ። ከወንጌል ነን ብትሉ ያላወቁትን ታሳምኑ ይሆናል።እኛስ አቤቱ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው እንላለን እንጂ አያያዛችሁ አጥፍቶ መጥፋት ይመስላል።

  ReplyDelete
 11. MK IS THE WINNER, TEHADISO THE LOSER

  ReplyDelete
 12. Please correct the web site you posted as (hh://www.eotcss.org, Augest 19,2003 7:45 p.m.)

  to (http://www.eotcssd.org, August 19,2003 7:45 p.m.)

  ReplyDelete
 13. እናንተ በቤተ ክርስቲያን እና በ ማህበረ ቅዱሳን ላይ የተወረወራችሁ ጦሮች ናችሁ ።ዲ /ን ዳንኤል እና ማህበረ ቅዱሳን ግን የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው

  ReplyDelete
 14. I wonder if you guys have anything to say except MK, what's going on? I am very tired every time I see is you posting the same thing or you don't have any good writer that can come up with a new idea?

  ReplyDelete
 15. You guys are bull shit because your articles are cursing.It's not teaching.Please have some one else who knows how to write something else.

  ReplyDelete
 16. Ebakachihu bewnu Danil Kibret sile mahibere kidusan endieh tsefual? Endemayil awkalehu , Enam yesew sim bekentu atagudifu!!!

  ReplyDelete
 17. Enante, yeseytan maderiya. Ayne alachihu atayum , Jero alachihu gin atsemum. Bewnet D/N Daniel Kibret SILE MAHIBERE KIDUSAN yihin ynageraln? yesew sim bekentu atatifu,

  ReplyDelete
 18. ¨SEW LETIRU NEGER SIEQOM SEYTAN AYNUN YAMEWAL¨ Aba Selama man nachew?

  ReplyDelete
 19. Alamnachihum enante seytanoch!!!

  ReplyDelete
 20. If you are real Christians, you will be able to write something that teaches and console people from their earthly sad. You are in a simple position of accusing honest christian. For how long a time you fight our church? Please stop such deeds and stand to serve Christ's church so that you be fateful to have the KINGDOM of GOD.

  ReplyDelete