Monday, September 19, 2011

ጠባቡ የማህበረ ቅዱሳን አስተሳሰቦች by Berhane Tsegaye on Monday, September 5, 2011 at 4:01am

ካሁን በፊት ስለማኅበረ ቅዱሳን ከውጪ ሰዎች እንጂ ከማኅበሩ ሰዎች ብዙም ሲነገር አልሰማንም፡፡ ቢነገርም የማኅበሩ ሚዲያዎች የማኅበሩን ጽድቅ እንጂ ኀጢአት ሲያወሩ አላየንም፡፡ እንደችግር የሚነሡ ቢኖሩም እንኳ መከራ ደረሰብን ከሚል ያለፈ ትክክለኛ ድካምን የሚገልጽ አስተያየት እንኳ ማንበብ ሳይቻል ቆይቷል፡፡ አሁን ግን ማኅበሩ ወደ ውድቀቱ እየተፋጠነ መሆኑን የሚያሳዩ አንዳን ድ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው፡፡ በአስተያየቶቹ ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን የት ላይ እንዳለ መገመት ይቻላል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የቀረበው የብርሃን ጸጋዬ ጽሑፍ ደጀሰላም ፌስቡክ ላይ የወጣ ነው፤ ያንብቡት::

ቤተ ክርስቲያናችን ብዙ ነፍሳትን ማጥመድ ስትችል በጠባብ አመለካከቶች ምክንያት ብዙዎች እድሉን ባለመጠቀም ይጠፋሉ። ዩንቨርስቲዎች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች እድሚያቸው 18 እስከ 20 ባለው ውስጥ ወደ ዩንቨርስቲዎች ይገባሉ፤ይሄ እድሜ ደግሞ ከላይ ከላይ የሚረገጥበት ጊዜ ነው ከማስተዋል ይልቅ ስሜታዊነት የሚበዛበት ሲሆን እነዚህን ልጅ አይምሮ ያላቸውን ተማሪዎች እንዴት treat ማድረግ እንደሚቻል የታሰበት አይመስልም በግቢ ጉባኤ አስተምሮ ውስጥ ከቤተክርስቲያንዋ አስተምህሮ ጎን ለጎን የልዩነት መንገዶችን እንደ ትልቅ አስተምህሮ በየወቅቱ በመንዛት ማህበረ ቅዱሳን ከሚያስተምረው ትምህርት ውጪ ሌላው በየአውደምህረቱ ያለው አስተምህሮ በጥርጣሬ የሚታይና የተሳሳተ እንደሆነ ስብከቱ የተሀድሶ መዝሙሩ ዘፈን እንደሆነ እየተነገራቸው ይቆዩና ብዙዎቹ break ላይ ወደ ቤተሰብ እና ወደ ቤታቸው ሲመለሱ የሚያነሱት ጥያቄ ሁሉ ስለ ተማሩት ትምህርት ሳይሆን እከሌ መዝሙር እከሌ ዘፈን ጋር ይመሳሰላል ተብለናል እከሌ ተሀድሶ መናፍቅ ነው እያሉ ጥያቄና ክርክሩን ያቀልጡታል።

      ስለተማሩት ትምህርት ሲጠየቁ ብዙ ያወቁት ነገር እንደሌለ መልሳቸው ያስታውቃሉ ብዙዎቹ በትምህርት እያሉ በአመት ወስጥ አንድ ቀን ወይም ሁለት ቀን ግቢ ጉበኤ ይሳተፉና ከዛ በህዋላ የማህበረ ቅዱሳን አባል የመሆን ስሜት ለአፍታ ይሰማቸዋል ተመርቀው ከወጡም በኋላ ስለ ቤተክርስቲያን ሲወራ ሲሰሙ አዎ ግቢ እያለን እያሉ ያወራሉ ስለ መሰረታዊ የቤተክርስቲያንዋ ትምህርት ሲጠየቁ ግን ምንም። አሁን አሁን ሳስበው ማህበሩ የሚፈልገው ይሄን ይመስለኛል።

     እንደሚታወቀው ብዙው የተማረው ሀይል የማህበረ ቅዱሳንነት ስሜት ካደረበት ነገ ባለስልጣን ሆነው በተለያየ የስልጣን ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ማህበሩ የሚገጥመውን ጫና የጋሩታል ይፈርዱለታል ብላችሁ ያሰባችሁ ይመስላል ግን አይደለም እናንተ በደንብ አስተምራችሁ ነፍሱን እንዲያድን ያላደረጋችሁት ባለስልጣን ማህበሩን ያድናል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው። እስቲ አስቡት ዛሬም ሀገራችን ባለባት ድህነት ላይ ስንቶች በስርቆት ሀገሪትዋን ሲመዘብሩ ይኖራሉ ብዙዎቹ ታዲያ በግቢ ጉባኤ ውስጥ ያለፍን ነን የሚሉ ናቸው ምን አለ ባሉ ባልታና በክፍፍል በማይጠቅምም ወሬ በማሪዎች ላይ ከምትነዙ አትስረቅ የምትለዋን የእግዚአብሄርን ህግ በደንብ አስተምራችሁት ቢሆን ኖሮ አገራችሁንም ህዝባችሁንም በታደጋችሁ ነበር ያፈራችሁት ፍሬ ሳይሆን ቲፎዞ ነው።

በተለያዩ ድህረ ገጾች ላይ በሚሰጡ አስያየቶች ላይ ስሜታዊ ያልበሰሉና የማህበርተኝነት ስሜት ብቻ የሚያንጸባርቁ ብዙ ማህበርተኞችን እያየሁ ታዘዝቤአለው ይህም የትህምህርታችው ውጤት ማነስ ነው ተማሪዎቹንም ከማህበርም በላይ አስፍተው ቤተ ክርስቲያንን እንዲያዩ አስተምሩአቸው እናንተ እራሳችሁን የቤተ ክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሰድርጋችሁ በመቁጠር የፈለጋችሁትን ሰው በጣም በወረደ ወንጀል በመወንጀል ግንዛቤው የሌለውን ምእመን ማህበረ ቅዱሳን አለልን ብሎ እነዲዘናጋ አድርጋችሁታል። ፈጽሞ አንድም ቀን ላልዳኑ ሰዎች ስትጨነቁ አይቼ አላውቅም እከሌን ከዚች ቤተ ክርስቲያን ሄዶልኝ አጋፍጬው እንጂ ያልተረዳውን አውቆ ድኖ ተመልሶ የሚባል ነገር እናንተ ጋር የለም የማህበሩ ችግር የቤተ ክርስቲያን ችግር ነው ብሎ በማህበሩ ዙሪያ አስተያየት የሰጡ ሁሉ ለእናንተ ተሀድሶ መናፍቅ ናቸው። ሁልጊዜም የምትደክሙት ከቤተክርስቲያን በላይ ማህበሩን ለማግዘፍ ነው ሲኖዶሱን ጨምሮ ፓትሪያሪኩን ሁሉ በእናንተ መንገድና አስተሳሰብ እንዲመሩ ትሞክራላችሁ።እስቲ በየግቢው ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ሄዳችሁ ሀመር እና ስምአጽድቅ ጋዜጣን በነጻ አድሉና ስንቶቹ እንደሚያነቡት ተከታተሉ ያን ጊዜ አቀራረባችሁ ጀምሮ ለብዞዎች መዳን ምክንያት መሆን እንዳልቻላችሁ ትረዳላችሁ።

በአጠቃላይ በእናንተ አገልግሎት ሰዎችን በሀይማኖት እንዲፀኑ ወተወታችሁ እንጂ በሀይማኖቱ ውስጥ ስላለው እውነት ጮክ ብላችሁ አልነገራችሁትም ለዚህም ነው በሀይማኖት አየኖረ በምግባር መኖር ያልቻለው ለዚህም ነው ኮሽ ባለ ቁጥር በትንሹም በትልቁም የሚደናበረው ለዚህም ነው በዩኒቨርስቲ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ወንዶቹ በሱስ ሴቶቹ sugar dady ሲጠቁ ይህም በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች መገለጫ ሆኖ ሳለ እናንተም ትልቁን ስራ የምንሰራው ግቢ ጉባኤዎች ውስጥ ነው ብላችሁ ትኩራራላችሁ ይህንንም ክፍተት ለመድፈን ውጪ ያለውን ምእመን ጨምሮ በሀይማኖት ውስጥ ያለውንም እውነት ጮክ ብለው የሚናገሩትን አገልጋዮች በየአውደምህረቱ ታሳድዳላችሁ። አሁን ባለው የስብከትና የመዝሙር አገልግሎት ምእመኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲሰበሰብ ምክንያት እንደሆነ ስታውቁ እነ እከሌ ያፈሩት የጉባኤ ደንበኛ እንጂ ቆራቢ አይደለም እያላቹ በጠባብ አመለካከት የተሰበሰበውን ለመበተን ሞከራችሁ ለመሆኑ እናንተ 20 አመት አገልግሎት ውስጥ ስንት ሰው አቆረባችሁ? ለምንስ የተሰበሰበውን ምእመን በዛው አጽንታችሁ ቆራቢ አላደረጋችሁትም? ከቻላችሁ።

 አሁን ባለው የመዝሙር አገልግሎት ላይም ብዙዎቻችሁ በጥላቻና ያለ በቂ ግንዛቤ ያልሆነ አስተያየት እየሰጣችሁ ሰውን ትከፋፍላላችሁ። ለመሆኑ ዘፈንን ትቶ መዘመር ይሻላል ወይንስ ለያሬዳዊ ዜማ እንጨነቃሉ እያሉ መዝፈን መደነስ አይ ያሬዳዊው ዜማ እናውቃለን እሱንም እንዘምራለን የምትሉ ካላችሁ እስቲ በየቦታው ልንሰማው የምንችለው አማራጭ ስጡን። ማህበሩ የሚያሳትመውን የህብረት ዝማሬ ከሆነ እራሳችሁም ደግማችሁ አልሰማችሁትም ይቆየን……………………

23 comments:

 1. Where are Talalak wondmoch ...

  Dejene Shiferaw - (tabote - Tsion)
  Yared G/medihn - (tereteret)
  Dani agalachu (aba giworgis zegascha)

  Kesis Birhanu Gobena better....

  F

  ReplyDelete
 2. ወንድሜ? ማሕበሩ’ኮ እውነተኛ ኦርቶዶክሳዊ ምርመራ አድርጎ የሌሎቹን መዝሙሮች ፈሩን የለቀቀ ሆኖ ስላገኘው ሳይሆን እውነታው ገበያውን ስለተቆጣጠሩለት ነው።
  ሌላው የማሕበሩ ልጆች በስሜት ዕድሜ ላይ ስለሆኑ የማህበሩ ጥማት አድሮባቸው አባል ለመሆን እንጂ ትምህርት አያስተማሯቸውም ባልከው ሐሳብ ተጨማሪ፣ በደጀ ሰላም ብሎግ የሚሰጧቸው አስተያየቶች አርእስቶቹ የስድብ ዓምድ ከሆኑ ከ100 በላይም አስተያየት ይሰጣሉ፤ቁምነገርን የሚፈልጉ ዐምዶች ከሆኑ ግን እነሱ ቁምነገርን ስላልተማሩ የሚሰጧቸው አስተያየቶች በጣም ጥቂት ናቸው ለምሳሌ ማህበሩ በአሁኑ ጊዜ የሐሳብ ማስቀየሻ መንገድ-በደጀሰላም ያወጣው (ተሐድሶ ለማድረግ) አስተያየት ስጡበት ባለው አጀንዳ 39 ብቻ ናቸው ሐሳብ የሰጡበት። ታዲያ ከዚህ ምን ትታዘባላችሁ?

  ReplyDelete
 3. yikoyen alk degmo?ahun ante sew tibalaleh?bewnet haymanotn lmekeyer stnesa bzih tshuf bicha ayidelm fit lfit bagegnh anktkn eshltlh nebr ant beshita?smetawi nachew alk ayidelm?angetkn biqortilh degmo mn endmtl alawkm?ant beshita!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. wendme kante befit yalewn comment aytehiwal?tesadabi nachew alen bizum saykoy hiyaw tesadabi misikir anten agegnen.ayyyyyy mahbere kidusanina teketayochachew!!!!!!!!!

   Delete
 4. legebawe teleke meleiket newe.

  ReplyDelete
 5. grow up mk. you know it is 100% true.

  ReplyDelete
 6. wendmae beewnet yatsnah

  ReplyDelete
 7. I know you may not post it as usual, but I will keep writing. To know what MK is doing, you need to be christian first. Whatever you said on top is not true. How come anybody just create something to make out Mahiber look bad. But I will tell you now this Mahiber was started by God's will so either you or other opposition groups will do whatever you guys like it will live forever. and whenever we have all those hard times we all shine like gold all the time. and may be if you don't know, Mk members are the only good christians you can get at this time. I don't think you take Holy communion at all, but MK members, before they even start serving they will learn how to live a good spiritual life, yeneseha hiwot,...ye Betekiristian tarik, sireat, kenona, dogma..and so on. But you are so silly that you are to brain wash those who are not exposed to know who the real MK is. Don't lie. You said about teaching not to steal. How could you say that when you are lying to people. Lie and stealing and killing is the same sin in the eye of God. they all make you go to hell. Becareful and I know you don't like vergin marry but I will say "Dingil Mariam Libona Tisitih". If you are brave post this.
  thanks
  MK member

  ReplyDelete
  Replies
  1. do u think to be christian u have to be mk?let me tell u the truth to be a christian,u have to be z follower of the only way Jesus.this is the standard of being a christian.now i know u never read bible or u may read iot but not understand it.

   Delete
 8. kezih belay malet neberebh mahberu yebetekrstiann tmhrt endatazaba sengo sileyazeh. yeanten aynet ye berewelede madenageria sira masfecha blachu meyazachun tenkken enawkalen. mechem sytan silemymot slemiferaget teferagetu.

  ReplyDelete
 9. ከኮልፌ መንግስቱ ነኝSeptember 21, 2011 at 2:00 AM

  "angetkn biqortilh degmo mn endmtl alawkm?ant beshita"
  በገዛ እጅህ ማን መሆናችን ገለጥክ፡፡ የፅሁፉንም ትክክለኛነት አረጋገጥክ፡፡ አንገት ከመቁረጥ የተሻለ ዕውቀት ስለማያስጨብጡዋችሁ ታሣፍራላችሁ!! እደጉ እደጉ ጡጦውን ስበሩና አጥንት ሞክሩ፡፡ ለክርስትና የሚጠቅመው እሱ ነው እንጂ አንገት መቁረጥ አይደለም፡፡ ወይ የቲፎዞ መንፈሳዊነት ያሳዝናል፡፡

  ReplyDelete
 10. ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ሾተላይ! ጽንሱ በሰላም ተወልዶ ሊሳም ሲል የሚገድል፡፡ መቼ ነው የሚፈወሰው መቼም በሽታን በሽታ አሞት አያውቅም፡፡ ያሳምማል እንጂ፡፡ ማኅበሩ ቤተ ክርስቲያንን የወላድ መሐን እንዳደረጋት ማሰብ አይፈልግም፡፡ ዘማዊና ጠንቋዮቹ አይቆረቁሩትም፡፡ መልክአ ሳጥናኤል ደጋሚዎቹ ርእሱ አይደሉም፡፡ ወንጌል ተሸካሚዎቹ ግን በዚህ በማኅበረ ሰይጣን እንደጎበጡ ከሚወዱት ሕዝባና ወገን እንደተለዩ እናውቃለን፡፡ ፕሮቴስታንት መቶ ዓመት ለፍቶ ያላገኘውን ባለፉት ሃያ ዓመታት ማኅበረ ቅዱሳን ገፍቶ ሰጥቶታል፡፡ በሽርክና መሥራታቸውን እጠራጠራለሁ፡፡ ምክንያቱም ፕሮቴስታንቱም የሚፈልጉትን ሰው የእኛ ነው እያሉ ለማኅበረ ቅዱሳን ይናገራሉ፡፡ ማኅበሩ ጠብ ቢያልቅበት ከማትሰብከው ከማትቀድሰው ከአንዲት እናት ጋር ትግል ገጥሞ ሲሳደብ እንሰማለን፡፡ መልክአ እጅጋየሁን ደጋሚ መሆኑን እናስተውላለን፡፡ ሕጻን አሮጊት የማይለዩ ያበዱ ውሾች መሆናቸው ያሳዝናል፡፡ ሁሉም አባላቱ ግን በዚህ ሚዛን አይታዩም፡፡ እኔም የማኅበሩ አባል ነኝ፡፡ እውነትን ግን ብንነጋገር መደማመጥ ሳይሆን ስም መለጣጠፍ እንደሚመጣ ስለማውቅ እኔን ከሚመስሉ ሆደ ባሻዎች ጋር አዝኜ እኖራለሁ፡፡ በአባ ሰላማ የጡመራ መድረክ ጭቅጭቅ ልቤ አይረካም፡፡ ዕረፍትን የሚነግረኝ ናፍቆኛል፡፡ ዓይነ ልቡናችንን ያብራልን፡፡ አባቶችን ለወንጌል ጨካኝ ያድርግልን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

  ReplyDelete
 11. «ዲ»ዳንኤል ክብረት/አባባ ተስፋዪ/ስብከቱን ትተህ ዲቃላህን ከየቦታዉ ሰብስበህ ብታሳድግ is better.ወልዶ ካጅ ቅጣፊ።

  ReplyDelete
 12. <<...እኔም የማኅበሩ አባል ነኝ፡፡ እውነትን ግን ብንነጋገር መደማመጥ ሳይሆን ስም መለጣጠፍ እንደሚመጣ ስለማውቅ እኔን ከሚመስሉ ሆደ ባሻዎች ጋር አዝኜ እኖራለሁ፡፡...>>ልቤን ነክቶኛል እግዚአብሔር ይስጥልን! ማኅበሩ ዕድሜ ማረዘሚያ ኪኒን የሚውጥ እንጂ መፈወስን አይፈልግም! አስተያየቱ ጥሩ ነው፡፡

  ReplyDelete
 13. hey try http://www.betepawlos.com/ . it is really interesting. i tought you also like it. if you 'ዕረፍትን የሚነግረኝ ናፍቆኛል' you get something good in their have a nice day.

  ReplyDelete
 14. muzzzzzzzziiiiiiiiiizzzzzzzzz yale bilog

  sirgut aa

  ReplyDelete
 15. ማህበረ ቅዱሳን ማህበረ ቅዱሳን ማህበረ ቅዱሳን ማህበረ ቅዱሳን ማህበረ ቅዱሳን
  ማህበረ ቅዱሳን
  ማህበረ ቅዱሳን
  --------------- ማህበረ ቅዱሳን .........ማህበረ ቅዱሳን
  weyyyyyyyyy beka lela ries yelacihum?
  Siyoum

  ReplyDelete
 16. ከቤተ ጳውሎስ የጡመራ መድረክ ያነበብኩትን ላስነብባችሁ ዕረፍት ለፈለጋችሁ <<...ጌታችን በተያዘ ጊዜ በዚያች ምሽት ብዙዎች ወደ ኋላ ተመልሰዋል፡፡ የሁሉም ሰው ፈተናው አንድ ዓይነት አይደለም፡፡ ይሁዳ ወታደርና ችሎት ፈተናው አይደለም፡፡ አልቅሶ ፍርድ ማሳት ያውቅበታል፡፡ ገንዘብ ግን ትልቅ ፈተናው ነበረ፡፡ ልቡ ለገንዘብ ይርዳል፤ ገንዘብን ለማግኘት አምላኩን ያጣል፡፡ ጴጥሮስ ደግሞ ገንዘብ ፈተናው አይደለም፡፡ ታዲያ በዚያች ሰው ሁሉ እንደ ስንዴ በሚበጠርባት ሌሊት ግማሹ በፍርሃት፣ ግማሹ በገንዘብ ተፈታ፡፡ የክርስቶስን መንፈሳዊ ሀብትነት ላልተረዳ ገንዘብ ፈተና ነው፡፡ እግዚአብሔርንም የማይፈራ፣ የማያስፈራው ያስፈራዋል፡፡ በሰዓታት ጸሎት ላይ፡-

  “ወርቅ ዘተመክዓበ፣ ወመድፍን ዘተረክበ፣ ምናን ዘበዝኃ፣ ወመክሊት ዘረብኃ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ”
  ትርጓሜ፡- “የተከማቸ ወርቅ፣ ተሰውሮ የተገኘ የሀብት ማከማቻ፣ የበዛ ትርፋችን፣ የበረከተ መክሊታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” ይላል፡፡

  የወርቅ ክምችት ዕረፍት ይነሣል፡፡ የክርስቶስ ሀብትነት ግን ያሳርፋል፡፡ የአልማዝ መዝገብ ያስጨንቃል፡፡ የክርስቶስ መክሊትነት ግን ለዘላለም ያጽናናል፡፡ ይሁዳ ከጌታው ጋር ሦስት ዓመት ኖረ፣ ከገንዘብ ጋር ግን አንድ ቀን አልኖረም፡፡ ዕድሜ የሚያረዝመውን ሀብት፣ ዕድሜ በሚያሳጥረው ሀብት ለወጠ፡፡ ያውም ለሚበትነውና ለማይበላው ሀብት ከጌታው ተለየ፡፡ የማያልፈውን ሀብት በሚያልፈው ሀብት የለወጡ፣ የሚያሳርፈውን በሚያሰቅለው ሠላሣ ብር የለወጡ እነ ይሁዳ እንዴት ከሰሩ! አወይ ገበያ አለማወቅ! ወርቅ ሰጥቶ መደብ ይዞ መመለስ፡፡ እውነተኛውን ወርቅ ጥሎ ቅቡን ይዞ መግባት>>
  Tedibabe sanjose

  ReplyDelete
 17. I strongly support Siyoum's ideaI strongly support Siyoum's idea

  ReplyDelete
 18. kezi seytan mahber tselot beentemahiberekidusan

  ReplyDelete
 19. betam ygermal izih Blog lay yale D.Daniel kibret ina mahibere kidusan besteker lela were yelacihum. andigncihun ASTARKUN bitilu ye ager Shimagile inisebesib neber looooooooool sitasazinu!

  ReplyDelete
 20. EGZEABHER SELAM YESTEN.CHRISTEANOCH EBAKACHIEW SELOT ENADEREG
  GETA SELAM ENA FIKER ENDESETEN!!!!!!

  ReplyDelete