Monday, September 5, 2011

የመጻተኞችና የጃንደረቦች መታሰቢያ - - - Read PDF

"ወደ እግዚአብሔርም የተጠጋ መጻተኛ። በእውነት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ይለየኛል አይበል፤ ጃንደረባም። እነሆ፥ እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ አይበል።  እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና።  በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።  ያገለግሉት ዘንድ የእግዚአብሔርንም ስም ይወድዱ ዘንድ ባሪያዎቹም ይሆኑ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የሚጠጉትንም መጻተኞች፥ እንዳያረክሱት ሰንበትን የሚጠብቁትን ቃል ኪዳኔንም የሚይዙትን ሁሉ፥  ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፥ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና የሚቃጠለውን መሥዋዕታቸውንና ሌላ መሥዋዕታቸውን በመሠዊያዬ ላይ እቀበላለሁ" ኢሳ 56፥3-7

  ቅዱሳንን በተገቢው መንገድ ለማክበር ነው በሚል ሽፋን ወደ አምልኮ ባዕድ እየተጓዘች የምትገኘውን ቤተ ክርስቲያናችን፣ ወደ ትክክለኛው አቅጣጫዋ በመመለስ ፈንታ ለተለያዩ የስህተት ትምህርቶች ይህን የትንቢተ ኢሳይያስ ክፍል እንደ ማስረጃ በማቅረብ የእስካሁኑ እንኳ እንዳይበቃ ሌላ ረጅም ዕድሜ እየተጨመረላቸው ይገኛል።
  ለሞቱ ቅዱሳን በመታሰቢያ ስም ብዙ ብዙ ነገሮች እንደተካሄዱና አሁንም እየተካሄዱ እንዳለ ሁሉም ያውቀዋል። ለዚህ እንግዳ ትምህርት ድጋፍ ይሆን ዘንድ የሚጠቀሰው ኢሳ 56፥4-5 የተነገረው ስለመጻተኛ እና ስለጃንደረቦች መሆኑን በቅድሚያ ማወቁ የአንዱን ለሌላ ከመስጠትና በእውነት ስም ቆሞ ሐሰትን ከመናገር ያድናል።
  መጻተኛ ማለት እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ አገሬ የሚለውን ምድር ትቶ በምድረ እሥራኤል የሚኖር እስራኤላዊ ዝርያ የሌለው፣ የሌላ አገር ተወላጅ ሲሆን፣ ጃንደረባ ደግሞ የጾታ መለያ አካሉ የተቆረጠበት ወይም የተጎዳበት እስራኤላዊ ወይም የእስራኤላዊነት መብት የተሰጠው ማለት ነው። ጃንደረባ ሌላም ሁለተኛ ፍቺ እንዳለው ይታወቃል ይኸውም ከፍ ባለ ማዕረግ የሚገኝ ጠባቂ ማለት ነው። [ዘፍ 39፥1፤8፤ አስቴ 1፥10] በዚህ ክፍል የተጠቀሰው ግን በመጀመሪያው ትርጉም የሚገኘውን ጃንደረባ ነው።
  በብሉይ ከዳን ዘመን ስለነዚህ መጻተኞችና ጃንደረቦች የተደነገጉ ሕግጋት ነበሩ። መጻተኛ የሆነ ሰው ለፋሲካ መታሰቢያ በዓል የተዘጋጀውን መብል እንዳይበላ፥ ይከለከል ነበር  "እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን አለ። ይህ የፋሲካ ሕግ ነው፤ ከእርሱ እንግዳ ሰው አይብላ.. መጻተኛና ሞያተኛ ግን ከእርሱ አይብሉ" ዘጸ 12፥43-45
በጋብቻ ከእስራኤል ጋር እንዳይቀላቀል፥ ንጉሥ ሆኖ እንዳይሾም፥ ይከለከል ነበር  "አምላክህ እግዚአብሔር የመረጠውን በላይህ ታነግሣለህ፤ ከወንድሞችህ መካከል የሆነውን በአንተ ላይ ንጉሥ ታነግሣለህ፤ ወንድምህ ያልሆነውን ከሌላ ወገን ሰው በላይህ ንጉሥ ታደርግ ዘንድ አይገባህም" ዘዳ 17፥15
ወደ መቅደስ እንዳይገባ ይከለከል ነበር። "ቍላው የተቀጠቀጠ ብልቱም የተቈረጠ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ" ዘዳ 23፥1
ጃንደረባ ደግሞ እንደ ነውረኛ ተቆጥሮ የተቀደሰን ነገር እንዳያቀርብና ወደ እግዚአብሔር ጉባኤም እንዳይገባ ሕጉ ደንግጓል። [ዘሌ 21፥10 ዘዳ 21፥1]
  ነገር ግን እግዚአብሔር መጻተኞች ወደ እርሱ ለመጠጋት ቢፈልጉ፥ ለእስራኤል የቃል ኪዳኑ ምልክት አድርጎ የሰጠውን ሰንበት ቢያከብሩ፥ እግዚአብሔርን ቢወዱና እርሱን ለማገልገል ራሳቸውን አሳልፈው ቢሰጡት፥ እንዲህ ያሉትን መጻተኞች ሕዝቤ ከሚላቸው ከእስራኤል ወንዶችና ሴቶች ልጆች ለይቶ እንደማያያቸው፥ በጸሎት ቤቱም ደስ እንደሚያሰኛቸውና የሚያቀርቡለትን መሥዋእት እንደሚቀበላቸው ቃል ሲገባ በቃሉ ውስጥ ይነበባል። [ቁ 3፣6-7]
  በተመሳሳይ ሁኔታ ሰለጃንደረቦችም ሰንበቱን ቢጠብቁምና ደስ የሚሰኝበትን ነገር ቢ መርጡ በቤቱና በቅጥሩ ውስጥ ለሕዝቡ ከሰጠው ስምና መታሰቢያ የሚበልጥ የዘላለም ስም እንደሚሰጣቸው ተናግሯል [ቁ 4-5]
  በዚህም ቃል ኪዳን መሠረት በኢየሩሳሌም ዘሩባቤል ባሠራው ቤተ መቅደስ ቅጥር ግቢ ውስጥ በአይሁድና በአሕዛብ መካከል በግድግዳ የተለየ ለጃንደረቦችና ለመጻተኞች መስገጃ ተዘጋጅቶ እንደነበር ታሪክ ያስረዳል። በጌታችን ዘመን ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ሰግዶ የተመለሰው በዚህ ስፍራ ነበር። የሐዋ 8፥፥27 ሐዋርያው ጳውሎስ በኤፌሶን ም 2፥13-16 ላይ "አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል። እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው"  በማለት በምሳሌነት የጠቀሰው በመጻተኞችና በአይሁድ መካከል የነበረውን የልዩነት ግድግዳ ነው። ይህ ግድግዳ በቤተ መቅደሱ ቅጥር ውስጥ ለጃንደረቦችና ለመጻተኞች መታሰቢያ የተሠራ ነበር። አሁን ዋናው የጥል ምክንያት ስለፈረሰ ይህም የልዩነት ግድግዳ ፈርሷል።
  በመሆኑም እግዚአብሔር ለብዙ መጻተኞችና ጃንደረቦች በሕዝቡ መካከልና በቤቱ ውስጥ ዘላለማዊ ስምና መታሰቢያ ሲሰጣቸው እንመለከታለን፤ በምሳሌነት ከመጻተኞች ሩትን ከጃንደረቦች ደግሞ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክን መጥቀስ ይችላል።
  ሩት የገንዛ ምድሯን ሞዓብንና ወገኖቿን ሞአባውያንን ትታ "ሩትም። ወደምትሄጅበት እሄዳለሁና፥ በምታድሪበትም አድራለሁና እንድተውሽ ከአንቺም ዘንድ እንድመለስ አታስቸግሪኝ፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፤ በምትሞችበትም ስፍራ እሞታለሁ፥ በዚያም እቀበራለሁ፤ ከሞት በቀር አንቺንና እኔን አንዳች ቢለየን እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ እንዲሁም ይጨምርብኝ አለች።ኑኃሚንም ከእርስዋ ጋር ለመሄድ እንደ ቈረጠች ባየች ጊዜ እርስዋን ከመናገር ዝም አለች" [ሩት 1፥16-18] በማለት አማቷን ኑኃሚንን ተከትላ ወደ እስራኤል አምላክ በመጠጋቷ እሱ ከሕዝቡ ሳይለያት ተቀብሎ በማክበር የንጉሥ ዳዊትን አያት ኢዮቤድን በመውለድ በክርስቶስ የዘር ሐረግ ውስጥ እስከ መግባት የሚያደርስ ክብር በመስጠት ስሟና ታሪኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲሠፍርና ለዘላለም እንድትታሰብ አደረገ፡[ሩት 4፥13-22፣ ማቴ 1፥5]
ጃንደረባው አቤሜሌክ ወደ እስራኤል አምላክና ወደ ሕዝቡ ተጠግቶ በንጉሡ በሴዴቅያስ ቤተ መንግሥት ያገለግል በነበረበት ጊዜ ለእግዚአብሔር ነቢይ ለኤርምያስ መልካም ነገርን ያደረገ፥ ሕይወቱን ከጥፋት በማዳን የእግዚአብሔርን ሥራ የሠራ የእግዚአብሔር ሰው ነበር። ኢየሩሳሌም በባቢሎናውያን ስትጠፋና ሕዝቡ ተማርኮ ለጉስቁልና እና ለታላቅ ጥፋት ሲዳረግ አቤሜሌክ ግን እግዚአብሔር በኤርምያስ በኩል በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ከጥፋቱ ተሠውሮ ነበር። በወቅቱ የነበሩ ብዙ እሥራኤላውያን ዝክረ ስማቸው እንኳ አስታዋሽ አጥቶ ሲደመሰስ የአቤሜሌክ ስም ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ትልቅ ሥፍራ ተሰጥቶት እየታሰበ ይኖራል። [ኤር 38፥7-13]
  ለመጻተኛዋ ሩትና ለጃንደረባው አቤሜሌክ መታሰቢያና ለዘላለም የማይጠፋ ስም የሰጠው ራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ይህን ለመታሰቢያቸው እንዲሆን ይህን እና ያንን በስማቸው አድርጉላቸው በማለት ማንንም አላዘዘም።
  ደግሞም በመጻተኞች እና በጃንደረቦች ላይ ተደርጎ የነበረው ሕግ የሚሰራው በዚያው በብሉይ ኪዳን ዘመን ብቻ እንጂ በአዲስ ኪዳን እንዳልሆነ ግልጽ ነው። እግዚአብሔር "ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ይባላል"[ኢሳ 56፥7] ባለው መሠረት ምንም ዓይነት የዘር ፥ የቀለምና የአካል ልዩነት ሳይደረግ አይሁዳውያንና አረማውያን በሙሉ የክርስቶስ አካል በሆነችው አንዲት ቤተ ክርስቲያን በማጠቃለል በፊት የነበረውን ልዩነት ጨርሶ ደምስሶታል። [ኤፌ 2፥11-22፤ 3፥1-6፤ ገላ 3፥28]
  ቃሉን በትክክል አንብበው ሳያጤኑ ለመናገር የሚቸኩሉት እና የእግዚአብሔርን ቃል  በትክክለኛው መንገድ ሳይሆን ለግል አመለካከታቸው ደጋፊ እንዲሆን የሚጠቅሱት ወገኖች ይህ የኢሳ 56፥ ክፍል ለቅዱሳን ሁሉና በስማቸው የተለያዩ መታሰቢያዎችን እንድናደርግላቸው የሚናገር ነው ሲሉ ጥቂት እንኳን ቅር አይላቸውም።
  ቃሉ የሚናገርላቸውን ክፍሎች ይዘን በነርሱ አተረጓጎም እንሂድ ቢባል እንኳ ከቃሉ አንጻር እስራኤላዊ ዝርያ ያላቸው ቅዱሳን ለምሳሌ ድንግል ማርያም ቅ/ ጳውሎስ ቅ/ጴጥሮስ በዚህ ውስጥ ተሳታፊነት አይኖራቸውም። እነርሱ መጻተኞች ወይም ጃንደረቦች አይደሉምና። ታዲያ ለእነርሱ ሁሉ እንደተነገረ አድርገው በጅምላ ለምን ይጠቅሳሉ?
  እግዚአብሔር ያዘዘው ስንት ነገር እያለ እሱ ሥሩ ያላለውን እና ራሱ የሚሠራውን እኛ ካልሠራን በሚል አጉል ታዛዥ መስሎ መቅረቡ ራስን ማታለል ነውና በሐሰትና በማስመሰል የእግዚአብሔርን ቃል ተገን አድርጎ ተገቢ ያልሆነ ሥራን ለመሥራት ራስን አሳልፎ ከመስጠት ለአፍታም ቢሆን ቆም ማለትና እግዚአብሔር የሚለውን ሰምቶ መታዘዝ በጌታ ፊት ትክክለኛ ነገር ነው።
የተቀበረ መክሊት ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ
መላከ ሰላም ተሰማ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት

5 comments:

 1. Thank you and may the Lord bless you!

  It is so a wonderful lecture and the truth that has been buried for so many years. I am wondering that hearing this kind of truth from Bete-Kihnet. I know they are very knowledgable, but they are always frightened to speak out what the truth is because of their benefits. Now, I hope that the day of blessing will come to our church. And I believe one day all of us (Mahbere-Kidusan, Tehadso and the unknown party) will sit, learn and worship, together.

  May the Almighty God give us that day!!!

  Abba

  ReplyDelete
 2. zekire Tsadik Yihelu le'alem. " Yetsadik Metasebiya Lezeleamen yinoral" yilal kidus Dawit...se'w mechem be akale siga saymot lezelealem ayinorim. Silezih, yih ye tsadik metasebiya lezelealem yeminorew beyet ne,w? Yemizekre'ws man ne'w? Ebakeh wogene atadenabiren...alem cherkun tilo betekrstiyanun bemichefiribet bezih se'ate Yegnan betekristiyan endeziyaw lemadreg yemitrut mehon alemehonihin mermir.. melake selam negn lalke'w lene tor yeyazih hono new yetesemagn..bamare kuwanquawa melsihin enji sidebihin alisham bel melis.... Ene gin 36 amet sihonegn joroye eskesemaw dires betekristiyanachin kidusanin sitizekir enji sitamelk alsemahum....antem batwash yimeretal

  ReplyDelete
 3. 3rd posting!
  መላከ ሰላም ተሰማ,

  Dinkem melake selam tesema! Melake seitan bibalu yeteshale neber. According to your argument, all the prophesies about Christ disguised in the old testament traditions, sayings and cultures are not applicable to the new testament and Christ. I see that you are breathing the spirit of Satan in all your writings. It is one thing to criticize the "worship" like veneration of the saints, but it is quite another thing to deny their intercession and the remembrance we need to do for them. You are simply useless. Leave alone the saints, even world figures who may have done some good things to humanity are remembered in different forms. You are simply preaching what you have heard from your father, satan.

  ReplyDelete
 4. መላከ ሰላም ተሰማ,

  Dinkem melake selam tesema! Melake seitan bibalu yeteshale neber. According to your argument, all the prophesies about Christ disguised in the old testament traditions, sayings and cultures are not applicable to the new testament and Christ. I see that you are breathing the spirit of Satan in all your writings. It is one thing to criticize the "worship" like veneration of the saints, but it is quite another thing to deny their intercession and the remembrance we need to do for them. You are simply useless. Leave alone the saints, even world figures who may have done some good things to humanity are remembered in different forms. You are simply preaching what you have heard from your father, satan.

  ReplyDelete