Wednesday, September 7, 2011

የዳንኤ ክብረት ባዕድ ወንጌል --- Read PDF

"የሚያናውጧችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳዳዶች አሉ እንጂ። ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መላክ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን"። ገላ 1፥8።
ማህበረ ቅዱሳን የተባለው ድርጅት ወንጌልን በማጣመም ለወጣቶች አያስተማረ ስንት ዜጎችን እንዳጣመመ እግዚአብሔር ይወቀው፤ ከአጋንንት መንፈስ የሚመጣውን ባዕድ ነገር ያለምንም ፈሪሃ እግዚአብሔር በሕዝብ ላይ በመዝራት የፈጸመው ወንጀል በምድር ባይሆይንም በሰማይ ግን ፍርዱን ያገኛል።
የክርስቶስን ወንጌል በማጣመም የታወቀው ዳንኤል ክብረት የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ራሱ አመለካከት እየተረጎመ ሲያስተምር ምንም ስቅጥጥ አይለውም። ባንድ የስብከት ፕሮግራሙ ላይ “ያዕቆብ በሕልሙ ያየው በመሰላል  አማሳል ያያት እመቤታችን ናት” ይላል።  መጽሐፍ ቅዱስ ግን ከጥንት ደብተራዎችም ሆነ ከዘመኑ ደብተራ ከዳንኤል ክብረት ጋር ፈጽሞ አይስማማም።
"ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ሄደ።  ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ፥ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ፤ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሣ፥ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ። ሕልምም አለመ፤ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር። እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥ እንዲህም አለ። የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፤ ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል፤ እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ። እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና" ዘፍ 28፥10-14።
ያዕቆብ በሕልሙ ያየው መሰላል እመቤታችን ሳትሆን ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለናትናኤል አስረድቷል፤ ሕልሙ ትንቢት ሲሆን ፍጻሜው ግን ክርስቶስ ነው። የጥንት ደንብተራዎች ትርጉም የሐስት ትምህርት መሆኑን የሚያጋልጠው የሚከተለው የጌታ ቃል ነው።  
"ኢየሱስም መልሶ። ከበለስ በታች አየሁህ ስላልሁህ አመንህን? ከዚህ የሚበልጥ ነገር ታያለህ አለው።  እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይ ሲከፈት የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ አለው" ዮሐ 1፥51-52። መላክእት የሚወጡበትና የሚወርዱበት መሰላል የሰው ልጅ ሆኖ የመጣው አምላክችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን እናስተውል።   
ማህበረ ቅዱሳን ለትውልድ ያሰራጫቸው የክህደት ትምህርቶች ስፍር ቁጥር የላቸውም። ነገር ግን ማስተዋል የለም። ምእመናንና የማህበረ ቅዱሳን ጭፍን አባላት እኛ ስለ ማህብረ ቅዱሳን የምንለውን ነገር እንደ ስም አጥፊ እንጂ ትውልዱን ከባዕድ ወንጌል ለማዳን  የምናደርገው ጥረት መሆኑን ሊገነዘቡ አልቻሉም። አሁን አሁን ግን ብዙ ለውጥ እያየን ነው፤ ሕዝቡ ወደ እውነት እየዞረ ነው፤ ወንጌልንም እየፈለገ ነው፤ የሕዝብ የወንጌል ፍላጎት እየጨመራ መምጣቱን በቅርቡ የተረዳው ማህበረ ቅዱሳን ይህን እውነተኛ ጥማት ለማደናቀፍ ተሃድሶ ሊያፈርስህ ነው በማለት ፕርፓጋንዳውን ይነዛል። ቤተ ክርስቲያንን እያፈረሰ ያለው ግን የባዕድ ወንጌል አስተማሪዎች እነዳንኤል ክብረት እና ጓደኞቹ ናቸው። የጥንት ደብተራዎች  በመንፈስ የወለዱት ዳንኤል ክብረት  አንድ መቃርስ የሚባል የጥንት መነኩሴ በኢየሱስ ክርስቶስ መዳኑን ከሞተ በኋላ እንኳ ያላረጋገጠ ሰው ነበር። ሞቶ ወደ ሰማይ ሲሄድ ሰይጣን አሸነፍኸኝ ቢለው ገና በግራ ልሁን በቀኝ አላወቅሁም ሲል መለሰለት ሲል ያስተምራል። የባሰው መጣ። ይህ ሰው ክርስቲያን ሊሆን አይችልም ድኛለሁ ብሎ ካላመነ እንዴት ክርስቲያን ተብሎ ሊጠራ ቻለ? ይህ ገና አልዳናችሁም የሚለውን ጥርጣሬ ለማሰራጨት የታሰበ ነው፤ ወይም ሰው በጌታችን ከተድረገው የቤዛነት ሥራ ይልቅ በራሱ ጥረት እንዲታመን ለማደረግ የተጠነሰሰ የሰይጣን ሥውር ተቃውሞ ነው። ለምሳሌም ያህል በላኤ ሰብእ በጥርኝ ውሃ መዳኑን ይጠቅሳል። እነጳውሎስም ወይም ሰማዕታት በሰይፍ የተገደሉት ገና ስላልዳኑ እንደነበር ለመናገር አላፈረም። ጳውሎስ በመልክቱ ሁሉ አዳነኝ፣ ምህረትን አገኘሁ፣ ጢሞቲዎስንም ሲሰናበት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል እያለ ይናገር የነበረው መዳኑን ሳያረጋግጥ ነውን? አይ ክህደት!
የኢትዮጵያ ሕዝበ ክርስቲያን ማህበረ ቅዱሳን የሚባሉት ሐስተኛ ወንድሞች የእግዚአብሔርን ቃል የሚያጣምሙ መናፍቃን መሆናቸውን አውቆ እንዲጠነቀቅ ስንል እናሳስባለን። ዳንኤል ይህን ባዕድ ወንጌል በጥቅምቱ ሲኖዶስ ቀርቦ መግለጫ እንዲሰጥበትና እርማት እንዲያርግ አለበላዚያ ልጁ ተወግዞ እንዲለይ ስንል እንጠይቃለን።
ነገር ግን ለዚህ ዓለም ከሚመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ::
ከሰባክያነ ወንጌል አንዱ ነኝ
የዳንኤል ክብረትን ባዕድ ወንጌል ከዚህ በታች ያለውን ኦድዮ ያዳምጡና መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ እራስዎን ከመናፍቃን የስሕተት ትምህርቶች ይጠብቁ።
         የዳንኤልን ባዕድ ወንጌል እዚህ ላይ በመጫን ያዳምጡ


27 comments:

 1. Wey zendro, endet sichawetuben norewal gobez

  ....

  Another joke by Yared GM

  ReplyDelete
 2. I am not a fan of Daniel Kibret; I know he has a lot of personality problems and can misbehave very badly. However, his teaching on that is correct. If you read the Kidase Mariam, Aba Hireyacos calls her "the ladder of Jacob." We were condemned and throwm to hell because of of the Original Eve; however, we have been saved and been able to ascend to heaven because of the Second Eve, St. Mary. You don't believe that? If so, you are alien to Christianity.

  You will be suprised that there are many verses in the Bible that simultaneously apply to Christ, His Church, and His Mother. The Bible has andimita tirgume; please go learn the Bible before you open your mouth. Thank you!!

  ReplyDelete
 3. hale loya!!!!!!!!!!!!hal loya!!!!

  ReplyDelete
 4. Anonymous said...
  There are two types of people who are against the teachings of Christ – People who partly believe His teachings (YE AMLIKOT MELK ALACHEW HAILUN GIN KIDEWUTAL YETEBALUT MALET NEW) and those who do not believe in Christ at all (NON-CHRISTIANS). According to our church’s terminology, the first type of people are called ‘Menafikan’.

  Jesus Christ has explicitly taught us to be aware of the Menafikans. He has said “Yebeg lemd lebsew kemimetubachihu tekulawoch tetebeku”. In short what this means is that, they say they are Christians but they are not. When you bring this to the context of this specific training “Orthodox SATIHONU ORTHODOX NEN BILACHIHU SIBEKU….” Muslims and other religion believers never came with a pretext. They never hid who they are. So, the teaching of Christ clearly mentions the wrong doings of people like the organizers of this training. However, according to Jesus Christ, our Lord, we have to keep away from the teachings of both types of people.

  Final remark, It is a pity that you were carried by strange teachings. I personally feel really sorry for you. If you conclude that Milk is Black, it will never be White for you. So, you are the one who closed your eyes to the teachings of Christ. But our eyes were already open and, with the help of God, will remain open.

  Egziabher Betekiristiyanachinin Yitebik!
  Reply
  September 7, 2011 1:24 AM
  Anonymous said...

  ReplyDelete
 5. የሐረሩ ስልጠናና የገብርኄር ሐሩር
  Posted on September 7, 2011 by ገብር ኄር
  በማቴዎስ አጥምዛ (gebrher33@gmail.com)
  ገበየሁ ይስማው ሥልጠናው መካሄዱን አመነ የሠልጣኖች ምልመላ ሂደትን አብራርቷል
  የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ለጉባኤ ከአዲስ አበባ ሳባኪ እንዳይጠራ ወሰነ
  ማኅበረ ቅዱሳን በተሐድሶ ሰራዊትነት የሰለጠነ አባል የለኝም አለ
  ከድሬዳዋ ለተሐድሶ ሰራዊትነት ሥልጠና ወደ ሐረር የተጓዙ በሀሳብ ባለመግባባት ለሦስት ተከፈሉ

  ገበየሁ ይስማው

  በቅርቡ በሐረር ከተማ በሉተራን 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተሐድሶ ሰራዊትነት ዙርያ የተሰጠው ሥልጠና ልዩ ልዩ ውጠየቶችን እያስከተለ እንደሆነ የምስራቅ ኢትዮጵያ የገብር ኄር መንጮች ገለጹ፡፡

  ሐረር

  የሐረር ከተማ እንዳንድ ምዕመናን ግብረ ተሐድሶን በተመለከተ ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው፡፡ እነዚህ ምዕመናን ‹‹በሌሎች አህጉረ ስብከቶች የታገዱ መምህራን ለምን ሐረር ላይ እንዲያስተምሩ ይፈቀድላቸዋል? በከተማው እየተፈጸመ ባለው ግብረ ተሐድሶ ላይ ሀገረ ስብከቱ አፋጣኝ እርምጃ ለምን አይወስድም›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

  የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት አስተዳደር ጉባኤ በሀገረ ስብከቱ እና በሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ያሬድ ሰባሳቢነት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ከመስከረም 1 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ቀን በክብረ በዓላት ወቅት በሀገረ ስብከቱ ልዩ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር አንድም ‹‹መምህር›› ለስብከተ ወንጌል አገልግሎት ከአዲስ አበባ እንዳይጠራ ወስኗል፡፡ በስብሰባው ‹‹ምእመናን መማር ያለባቸው በሀገረ ስብከቱ ከሚገኙ ሊቃውት መሆን አለበት፡፡ እኛ ሊቃውንቱን መድረክ ስለነሳናቸው ነው ሕገ ወጦች አውደ ምህረቱን የተቆጣጠሩት ›› የሚል ሃሳብ ተሰንዝሯል፡፡

  ብጹዕ አቡነ ያሬድም በሀገረ ስብከታቸው እየተፈጸመ ያለውን ግብረ ተሐድሶ በተጠናቀረ መረጃ ለጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል፡፡

  ይህ በእንዲህ እንዳለ የሀዋሳዎችን አሰረ ፍኖት የተከተሉ የሐረር ከተማ ትጉኀን ምእመናን በከተማችው በሀገረ ስብከታቸው እንዲሁም በምስራቅ ኢትዮጵያ ያለው የተሐድሶ ክንፍ ምን እየሠራ እንደሆነ የሚያሳይ በበቂ መረጃዎች የተደራጀ ቪሲዲ ለማሰራጨት ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ዘለግ ላሉ ዓመታት በተሐድሶ ሴራ የተሰቃዩ የሐረር ምእመናንም ቪሲዲው የተንኮለኞችን ሴራ በማጋለጥ እፎይታ እንደሚሰጣቸው ተስፋ አድርገዋል፡፡

  ድሬዳዋ

  ከድሬዳዋ ለተሐድሶ ሰራዊትነት ሥልጠና ወደ ሐረር የተጓዙ ውሉደ ተሐድሶ ድርጊታቸው በመጋለጡ በሀሳብ ባለመግባባት ለሦስት ተከፍለዋል፡፡ በሦስት ሠልጣኞች ሦስት የተለያዩ ሀሳቦች ታይተዋል፡፡ የመጀመሪያው በግልጽ ወደ ሥልጠናው ሲገባ እና ሲወጣ በተቀረጸው የቪዲዮ ምስል እየታየ ለሚጠይቁት ሁሉ ‹‹እኔ ዘመድ ልጠይቅ ወደ ሩቅ ሀገር ሄጄ ነበር የማውቀው ነገር የለም፡፡ ከናካቴውም ሐረርን አላውቃትም ሔጄም አላውቅም›› በማለት ራሱን ከደሙ ንጹህ ለማድረግ ሲሞክር ታይቷል፡፡

  ሁለተኛው ግለሰብ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን በሐሰት አቀናብሮብኝ ነው እንጂ እኔ የማውቀው ጉዳይ የለም ›› በማለት እንደ ኦሪት ኃጢአተኛ በደሉን የሚሸከምለት ፍየል ለመፈለግ ሞክሯል፡፡ አክሎም ‹‹ከዛሬ ስድስት ዓመት በፊት ጀምሬ ሰዎች በእኔ ላይ ማስረጃዎችን እንደሚያሰባስቡ አውቃለሁ ተገኘ የሚባለው ነገር ፍጹም ሐሰት ነው›› በማለት ቀርበው ለጠየቁት ግለሰቦች ሲመልስ ተሰምቷል፡፡‹‹የሥልጠናውን ሂደት የቀረጹት የሚያሳድዱኝም ሸዋዎች ናቸው›› በማለትም ለኑፋቄው የዘረኝነት መከላከያ ጭንብል ሊያጠልቅለት ሞክሯል፡፡

  ከላይ የጠቀስናቸው ሁለቱ ግለሰቦች የአንድ ደብር ‹‹ሰባክያነ ወንጌል›› ሲሆኑ ቀጥለን የምንገልጸው የግብር አጋራቸው ድርጊታቸውን እንዳጋለጠባቸው ይጠረጥራሉ፡፡

  ሥስተኛው ሰው ሁለቱ ወዳጆቹ የከፈቱለትን ቀጭን መውጫ ቀዳዳ በመጠቀም አንድ አካል መረጃ እንዲያጠናቅርለት ልኮት እንጂ አምኖበት ወደ ስልጠናው እንዳልሄደ ቅርብ ለሚላቸው ወዳጆቹ ተናግሯል፡፡ ጨምሮም ያሰባሰበውን መረጃ ለማኅበረ ቅዱሳን መላኩን ገልጿል፡፡

  በሌላ በኩል ከሰልጣኞች መካከል የማኅበረ ቅዱሳን አባል የሆነ አንድ ግለሰብ መኖሩን የተረዱ ምእመናን በማኅበረ ቅዱሳን የድሬዳዋ ማዕከልን ‹‹እንዴት ከእናንተ መካከል እንዲህ ያለ ሰው ይገኛል›› በማለት ጠይቀዋል፡፡ ማዕከሉም እንዲህ አይነት አባል የለንም በማለት አስተ

  ባብሏል፡፡ ለማኅበሩ ቅርበት ያላቸው አስተያየት ሰጪዎች ከስድሳ ሺህ በላይ አባላት ካሉት ማኅበር እንዲህ ያለ መልስ አይጠበቅም፡፡ ማኅበሩ ሁሉንም አባላት የት እንደሚዉሉና እንደሚያድሩ በማያውቅበት ሁኔታ ድፍን ያለ መልስ ከመስጥት ተቆጥቦ የደረሰውን ጥቆማ በመቀበል ጉዳዩን በጥልቀት መርምሮ በመረጃ የተደገፈ ምሁራዊ ውሳኔ መስጠት ይኖርበታል ብለዋል፡፡

  ገብር ኄር ግን የሚመለከታቸው አካላት ጉዳዩን ችላ የሚሉት ከሆነ ከአስተባባሪው ከገበየሁ ይስማው ጀምሮ በሁሉም ላይ ያሉትን ዝርዝር መረጃዎች ለምእመናን የሚያሳውቅ መሆኑን ለመግጽ ይወዳል፡፡

  በተያያዘ ዜና የገብር ኄር ዜና ዘገባ እንደ ሐሩር እሳት ያቃጠለው የአሰበ ተፈሪው ገበየሁ ይስማው ‹‹ሥልጠናው እንደተባለው ኢየሱስን ማለማመድ ሳይሆን ሰባክያነ ወንጌል የዓለም ሃይማኖቶችን አንድ ለማድረግ እንዴት ማስተማር ይገባቸዋል የሚል ነበር›› ብሏል፡፡ የሠልጣኞች ምልምላን

  በተመለከተ ‹‹እኛ ሁሉንም ነው የጠራነው ደፍሮ የመጣውን አሠልጥነናል›› በማለት ገልጿል፡፡ ሴራው በመጋለጡ የተደናገጠው ገበየሁ ‹‹የቀረጹትንም ሆነ ፎቶ ያነሱትን እናውቃቸዋለን በመንግስት ጭምር እየተፈለጉ ነው ለሕግ እናቀርባቸዋለን›› በማለት የሐረር ምእመናን የተሐድሶን ሴራ ለማጋለጥ በሚያደርጉት ጥረት እየደረሰባት ያለውን ውርደት ለመከላከል አልሞት ባይ ተጋዳይነቱን አሳውቋል፡፡

  መረጃው የደረሳቸው የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ መረጃው ጠቃሚ እንደሆነና በሀገረ ስብከታቸው የእርምት እና የጥንቃቄ እርምጃዎችን ለመውሰድ እነደሚገደዱ መናገራቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

  እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን!!!

  Share this:
  Share

  Print

  ReplyDelete
 6. if you don't like Daniel.... that is another point.... if you have some issues with some people in the church... that is another..... but to write this in an insualting manner shows your lack of full knowledge.... buy this book.... http://orthodoxstudybible.com/ and read it..... this is not written by whom you call debteras or daniel...... you will see the same typology there..... The ladder of Jacob is a type of Mother of God and Christ.......
  yemigermegn degimo..... bemesadeb.... bemawigez.... new hulie yemititsifut...

  ReplyDelete
 7. Nathan,

  "አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው" 1 Tim 2:5

  There is no mekakelegna between Heaven and earth. Only Jesus

  ReplyDelete
 8. What is wrong with the writer of this trash?
  Someone from your group has already said what he/she said about the ladder mentioned in the Bible doesn't represent Imebetachin. He/she said a lot of stuff pages after pages. Why are you repeating it again? It is for the mere fact of accusing Dn. Daniel. Isn't it? Dkn. Daniel has been teaching the word of God for years even arround the world. He did preach on different topics the main objective being to help people understand the word of God and live by it. To the contrary your trash I just saw is meant to accuse people. Of course you and Dkn. Daniel can't go together/ are parallel.He is doing some thing constructive while you are full of distruction!!

  ReplyDelete
 9. ሰው እና እግዚአብሔርን ያገናኘ: ያስታረቀ እግዚአብሔር ሆኖ የእግዚአብሔር የፍቅር ልብ ያለው ሰው ሆኖ የሰውን ድካም የሚረዳ: በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል ያለ ጌታ ኢየሱስ ነው "በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤" 1 ጢሞ 2:5

  ሰውም አምላክም የሆነ: ከላይም የሆነ ወደታችም የወረደ መሰላል ጌታ ኢየሱስ ነው "ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው" ዮሐ 3:13

  አባታችን ያእቆብ በፍኖተ ሎዛ ደንጋይ ተንተርሶ ሰማይ ተከፍቶ መላእክት ሲወጡ እና ሲወርዱበት ያየው ጌታ ኢየሱስ ነው(ከልደቱ ጀምሮ) "ሰማይ ሲከፈት የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ አለው።" ዮሐ 1:52

  ዛሬ በደብተራዎች የሀሰት ትምህርት ተጠልፋ ቤተክርስቲያናችን ችላ ያለውችው ሙሽራው ጌታ ኢየሱስ ነው:: ሃሌ ሉያ!!!

  መሰላል ነህ የወርቅ መሰላል ነህ
  ጌታ ኢየሱስ የወርቅ መሰላል ነህ
  ሰው እና አምላክን ያገናኘህ::

  አባታችን ያቆብ በፍኖተ ሎዛ በፍኖተ ሎዛ
  ድንጋይ ተንተርሶ ተኝቶ እንደዋዛ ...

  ኢየሱስ ጌታ ነው::

  F

  ReplyDelete
 10. ዳንኤል መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብቶ አልጨረሰ፣ የአብነት ትምህርት ቤት ገብቶ የአዲሲ ወይም የብሉይ መምህር አልሆነ። ታዲያ እንዴት አድርጎ ነው ተረቱንና እውነቱን ሊለየው የሚችለው። ገና ተምሮ ሳይጨርስ አስተማሪ ስለሆነ ራሱን እንኳ ማሻሻል አልቻለም። ለማንኛውም ጥሩ ጭንቅላት ያለው ወንድማችን ነው። አንድ ቀን ጌታችን እንደ ቅዱስ ፓውሎስ ያበራለት ቀን ያኔ ጥሩ ደቀ መዝሙር ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

  ReplyDelete
 11. ወይ ዳንኤል በአደባባይ ክደትን ጀመረ ማን ዳንኤል ብሎ ስም እንዳወጣለት እኛ ዳንኤልን የምናውቀው ለአምላኩ ሲመሰክር ነው። ት. ዳ. 6፡21-22። ዳንኤል ያልገባው እነ ቅዱስ ጳውሎስ የሞቱት እኮ የአምላካቸውን አዳኝነት ሲመሰክሩ ነው እንጅ እንደ ዳንኤል ክብረት ተረትን ሲያወሩ አይደለም። እንደሚመስለኝ ዳንኤ መጽሐፍ ቅዱሱን ያነበበው አይመስለኝም ምክንያቱም እርሱ የተናገረውን ትረት ቅዱስ ጳውሎስ ውድቅ ያደርገዋል። “እኛ ፍጥረቱ ነንና እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።” ኤፌ. 2፡10 እባክህ ዳንኤል ተረቱን ተወዉና ወንጌልን ስበክ የተረት ጊዜ ካለፈ ቆየ ህዝባችን ነቅቷል እግዚአብሔር ልቦና ይስጥህ።
  ዲ/ን ወንድወሰን

  ReplyDelete
 12. የክህደት አስተያየት ብቻ ለምን ፖስት ታደርጋላችሁ? ታሳዝናላችሁ በጣም
  የድንግል ልጅ ይቅር ይበላችሁ

  ReplyDelete
 13. የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴን አስመልክቶ ቅዱስ ፓትርያሪኩ ከማኅበረ ቅዱሳን አመራር ጋር ውይይት አደረጉ

  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት ከማኅበረ ቅድሳን ሥራ አመራርና አስፈጻሚ ጉባኤያት ተወካዮች ጋር ነሐሴ 15 ቀን 2003 ዓ.ም ስለ ማኅበሩ አገልግሎትና በተለይም የተሐድሶ መናፍቃንን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ውይይት ማድረጋቸውን የማኅበሩ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

  በቅዱስ ፓትርያሪኩ ጽ/ቤት በተካሔደው ውይይት፤ የማኅበሩ አመራር ስለተሐድሶ መናፍቃን እንቅቃሴ አራማጆችና ተቋማት የተዘጋጁ ልዩ ልዩ መጻሕፍት እንዲሁም በምስል ወድምጽ /VCD/ የታገዘ ገለጻና ማብራሪያ ቀርቧል፡፡

  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስም በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ድርጊት ከተመለከቱ በኋላ “ይህ ሁሉ የንብ ሠራዊት እያለ ወረራው ሲካሔድ የት ነበራችሁ?” የሚል የአባትነት ጥያቄያቸውን አቅርበዋል፡፡

  ቅዱስነታቸው፤ ቤተ ክርስቲያንን እና ምእመናንን ከእንዲህ ዓይነቱ ተግባር መጠበቅ የሁሉም ሓላፊነት እንደሆነ ጠቅሰው፤ ከዚህም በላይ መብታችንን በሕግ ሳይቀር ማስከበር እንደሚኖርብን ገልጸዋል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን በልጅነት ድረሻው እያከናወነ ያለው አገልግሎት እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የግለሰቦችን ስም እየጠቀሰ “ተሐድሶ ናቸው” ማለት ግን አግባብ እንዳልሆነና ይህም የቤተ ክርስቲያናችንን አሠራር ጠብቆ መፈጸም እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

  የማኅበሩ አመራር አባላትም፤ በአሁኑ ወቅት እየተከናወነ ያለው ሥራ የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ ምንነት፣ በእንዴት ዓይነት ሁኔታና ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ምእመናን ግንዛቤ አግኝተው ራሳቸውን እንዲጠብቁ፤ እንዲሁም ፕሮቴስታንታዊ የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴን የሚመሩና የሚደግፉ ተቋማትን፣ ስልትና አሠራራቸውን የማሳወቅ ሥራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

  ማኅበረ ቅዱሳን በ1990 ዓ.ም የተሐድሶ መናፍቃንን እንቅስቃሴ የማጋለጥ ሰፊ ሥራ ባከናወነበት ወቅት፤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነው ነገር ግን ፕሮቴስታንታዊ የተሐድሶ ኑፋቄ በምእመኑ ውስጥ በመዝራት ጉልህ ድርሻ የነበራቸው “መነኮሳት” ተወግዘው እንዲለዩ ሲደረግ፤ በቤተ ክርስቲያን ሥርዐትና አሠራር መሠረት ማኅበሩ አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ ለሊቃውንት ጉባኤ አቅርቦ ከዚያም በኋላ በቅዱስ ሲኖዶስ የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጥ ያደረገበት ሁኔታ እንደነበረ፤ የማኅበሩ አመራር አባላት በውይይቱ ላይ አስታውሰው፤ ማኅበሩ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሥርዐትና አሠራር ጠንቅቆ እንደሚያውቅና ይህንኑ ለማስጠበቅ ጠንክሮ እንደሚሠራ ገልጸዋል፡፡ አሁንም ማኅበረ ቅዱሳን እየሠራ ያለው የግለሰቦችን ስም በመጥቀስ “ተሐድሶ” የማለት ሳይሆን፤ ስለ ተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ ምንነትና ስልት ግንዛቤ እንዲኖር በማድረግ ምእመናን ራሳቸውን እንዲጠብቁ የማሳወቅ ሥራ እየተከናወነ እንደሆነ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
  ወደፊትም በዚህ የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴና ሥራ ላይ የተጠመዱ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያኒቷ ውስጥ የሚገኙ አካላትንና ደጋፊዎችን፤ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሥርዐትና አሠራር በመጠበቅ ማኅበረ ቅዱሳን ለሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን አካላትና አባቶች እንደሚያቀርብ በማኅበሩ አመራር አባላት ለቅዱስነታቸው ተገልጿል፡፡

  ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩም፤ በበቂ መረጃ በማስደገፍ ለሚመለከተው የቤተ ክርስቲያን አካል በማቅረብ ሁሉም ነገር በሕግና በሥርዐት መከናወን እንዳለበት አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡
  Share

  ReplyDelete
 14. ይህ እናንተ እንዳላችሁት የዳንኤል ወይም የጥንት ደብተራዎች ትምህርት ሳይሆን የመጽሐፍ ቅዱስና የቤተክርስቲያናችን አስተምሮ ነው:: በእርግጥ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና የናንተ የሉተር እምነት ተከታዮች አስተምሮ በጣም ይለያያል:: ዳንኤል ደግሞ የናንተ እምነት ተከታይ መስሎአችሁ የናንተን ትምህርት እንዲያስተምር ጠብቃችሁ ከነበር በጣም ታሳስታችኋል:: እሱ ያስተማረው የተዋህዶን አስተምሮ ነው በጣም ትክክልም ነው:: አንዳችም ስህተት የለበትም:: ከናንተ ከሉተራን አስተምሮ ስለተለየ ከተደነቃችሁ ደግሞ ዳንኤልን እንዲህ ሰበከ ሳይሆን ማለት ያለባችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንዲህ አስተማረች ነው ማለት ያለባችሁ:: መማር ከፈለጋችሁ ኑና እንንነጋገር::

  Mek

  ReplyDelete
 15. @ Nathan which part of Bible is saying" we have been saved and been able to ascend to heaven because of the Second Eve, St. Mary."I am sure Our Holy Bible Doesn't say Like this before I got saved I believed what you are believing . When I start to read the Bible I didn't get any evidence what I believed and I was asking Church Scholars if they can show me where is the verses like what you quoted but no one is not able to show me those funny verses finally I decided to believe only what the Bible said and now I am being follower of Christ not Merry or Gebereal or Tekelehayimanot just follower of Jesus .READ THE BIBLE AND BE THE FOLLOWER AND THE PREACHER OF CHRIST WHO DIED FOR YOU!

  ReplyDelete
 16. አቶ “እውነት”?
  ለምን ግን ዳንኤል መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብቶ እንዲማር አትመክሩትም? ቢያንስ ያቺ የዓመተ ፊዳ የሆነችው ጥቅስ- ‘ወዮላችሁ’ ወደ አማናዊ-ተስፋ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስ ይለውጣት ነበር!
  እባካችሁ ማንብና ክፍል ውስጥ ገብቶ መማር የሰማይና የምድር ርቀት ስላላቸው ወንድማችን በማታው መርሀግብርም ቢሆን አስተምሩት።

  ReplyDelete
 17. yemitnagerutn ena yemtitsifutin atawukumna yikir yibelachihu.Kidus metsahif lay yetetsafew hulu enante endemitasibut silalhone yihin yilan yihin degimo ayilim kemaletachihu befit kabatoch gar kuch bilachihu temaru.Abatachine kidus Efrem yamesegenat emebetachin endih yetenagerelat endenante asibo sayihone mejemeria kabatochi gare temiro keziam tselio siletegeletselet new.Keketema woten mayimechen bota hunen anid samint enkua lemetseley manchil dekamoch metahif kidus ahun tegeletselin eyalin egziabheren anaskeyim.

  ReplyDelete
 18. tehadiso bemehonachu satafru comment awtu

  ReplyDelete
 19. baed enante weys daniel? daniel yastemarew betekrstian yemtastemrewn new

  ReplyDelete
 20. Alaweyan malet enaneta aydelachuhum

  ReplyDelete
 21. inen yemigermegn inante cigiracihu ke Daniel Kibret gar new. yihe degimo be gilts yemitay silehone lemin isun titacihu iwunetegnawun cigiracihun be gilts atinagerum. indemitayut ye Tewahido Orthodox haimanot teketayoci metitew be inante ina be Daniel mekakel yalewun kebad Tseb mikniyat bemadreg YETEKEDESECEWUN YE ORTHODOX HAIMANOT BEMEKAD LE INANTE AYACEBECIBUM.

  ReplyDelete
 22. እኔን የሚገርመኝ ነገር ቢኖር ... እናንተ ችግራችሁ ከዳንኤል ክብረት ጋር በመሆኑ ትንሽ እንኳን ሳታፍሩ ዳንኤል እንዲህ ብሎ፣ ማህበረ ቅዱሳን እንዲህ ብለው፣ እያላችሁ መጽሐፍ ቅዱስን ለማስተማር መጣራችሁ ነው። ከእግዚአብሔር ቃል አንዱን እንኳን አታከብሩም። ሁሉም ሰው የሚያውቀውን ዘወትር ከአንደበቱ የማይለየውን አዋቂ ፈራጅ ሰጪ ነሺ እሱ አንድዬ መሆኑን ስትገልጹ አላይም። የማነበው ሁል ጊዜ እነ እገሌ እንዲህ ናቸው። የሚል ሀሜት እና ትችት ብቻ ነው።
  እኔ ለምሳሌ የማህበረ ቅዱሳን አባል አይደለሁም ግን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ነኝ! የዳንኤል ክብረት ጽሁፎችን አነባለሁ። የእናንተንም መግቢያ ሀተታ ዜናችሁን ሁሉ አንብቤ አላማችሁን በመገንዘብ እናንተ ፍጹም ሰይጣናዊ እንጂ ቅዱስ አላማ እንደሌላችሁ፣ ማፍረስ እንጂ መገንባትን፣ ማበላሸት እንጂ ማልማትን፣ መበጥበጥ እንጂ ማጥራትን፣ ማሰናከል እንጂ ማቅናትን እንደማትችሉ ስነግራችሁ ከልብ ነው።
  እናንተ ብሎግ ላይ ያለማቋረጥ የሚነበበው እገሌ እኮ እንዲህ አለ (ሀሜት)። እገሌ እንዲህ ነው (ትችት)።
  እናንተ በቅናት መንገድ ላይ የምትጓዙ ናችሁ።
  ቅናት ደግሞ መድሐኒት የለውም ሀኪም ሊያክመው አይችልም።
  ስለዚህ ምንም የማይሳነው ጌታ መድኃኒዓለም ምህረቱን ይላክላችሁ።
  እናቱ ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ታስታርቃችሁ።
  እኔንም እናንተንም ይቅር ይበለን።
  አሜን።

  ReplyDelete
 23. እስቲ መጀመሪያ ምላሳችሁን አድሱ እና ስርዓት ያለው ንግግር ለመናገር ሞክሩ
  መጽሐፍ ቅዱስ አዋቂ ሀይማኖቱን አክባሪ አምላክን ይፈራል እንጂ አፉን ከፍቶ እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ ብሎ እንዳሰኘው አፉ ያመጣለትን ሁሉ ወደ ውጪ አይተፋም
  ከሁሉም በላይ ሁሉም ነገር ለበጎ መሆኑን ያስባል
  ማንኛውም ነገር የሆነው በአንድ አምላክ እንደሆነም ያስታውሳል
  ኃያሉ ጌታ እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ እንደሚችል ያውቃል እናንተ ግን የምትገርሙ አማኞች ናችሁ
  ወሬያችሁ ሁሉ ደብተራ... ዳንኤል ክብረት... እና ማህበረ ቅዱሳን ብቻ ነው
  ታዲያ እናንተ ከእነዚህ ጋር ፀብ አላችሁ እና ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የግድ መፍረስ አለባት???
  የእቃ እቃ ጨዋታ አደረጋችሁት እኮ አንገት የተፈጠረው አዙሮ ለማየት ነው ይላሉ አባቶች ... ልብ ብላችሁ እናንተው የምትጽፉትን አንብቡት እና እራሳችሁን ታዘቡት

  ReplyDelete
 24. Hale luya IYESUS GETA NEW. GETA IYESUS yibarikachihu abaselamawoch aynen aberachuhulign. inem ke widasemaryam ina kidasemaryam andimta lay beye ametu linem yemaygebagn teret siterit noryalehu. Iyesusen resiche Adagnen Getayen zengiche. Abba negn.

  ReplyDelete
 25. weineshet zamdehimanotOctober 10, 2012 at 5:59 AM

  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
  የሚገርመው በማታውቁት ባልተረዳችሁት ሰው ስም አባ ሰላማ ብላችሁ መሰየማችሁ ቅዱስ መጽሐፍን ማንበብ ማለት ዝም ብሎ ተራ ልብወለድ እንደማንበብ አይደለም ማስተዋልና መረዳት ያስፈልጋል እናንት የአስቄዋ ልጀች ለምን አታስተውሉም አንደኛ የማህበረ ቅዱሳንን ስም ለማጥፋት ዲያብሎስ እናንተን መሣሪያ አድርጐ ቢነሳም በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ራስ ራሱን ቀጥቅጦ ከእግራቸው በታች ይጥለዋል እውነትን የሚከተል የሚያፍር መሰላችሁ ሁለተኛ ደግሞ ዲ/ን ዳንኤል እኮ የሚናገረውን የሚሰማ ከማን እንደተማረ የሚያውቅ ሰው ነው 2ኛ ጢሞቲዎስ ምዕራፍ 3 ስለእናንተ የተጻፈውን አንብቡና አስተውሉ ዳሩ እግዚአብሔር ያልተከለው ተክል አይፀድቅም 2ኛ የዮሐንስ መልዕክት ከእኛ ጋር ቢሆኑስ ከእኛ ጋር ፀንተው በኖሩ ዳሩ ከእኛ ጋር ያለመሆናቸውን ለማጠየቅ ወጡ ይላል አሁንም የአጋንንትን ትምህርት እያደመጣችሁ አትጥፉ ከመናፍቃን ጐራ ውጡ አትቅበዝበዙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንስ ብትጠየቅ ሙሉ መልስ ያላት ሙሉ መረጃ ያላት መጽሐፉን በተግባር የምትሰብክ ስንዱ እመቤት ናት ሆዳችሁን አምላክ አታድርጉ ገንዘብን በመውደድ ራሳችሁን ለስቃይ አትዳርጉ አታስመስሉ ለመጨረሻ እስቲ የይሁዳን መልዕክት በጥልቀት የምታስተውሉና የምትረዱ ከሆነ አንብቡ ፡፡
  ጌታችን መድኃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእምሮ ልቡናችሁን ይመልሰው አሜን

  ReplyDelete
 26. dibora elias farisFebruary 9, 2014 at 3:33 AM

  ይህች አለም እንኩዋን ዲ.ን ዳንኤልን ጌታ ኢየሱስንም አልተቀበለችም ይህ ሕዝብ እንደነዱት የሚነዳ ከእንስሳ ያልተሻለ እየሆነ ነው ነገር ግን ዳንኤልን ምንም አልክ ምን he is one of greatest ethiopian son አውርቶ አደልም እዚህ የደረሰው ቀን ከለሌት ሰርቶ እንጂ እንዳንተ ስም እያጠፋ አደለም በአለም ላይ ቤተ.ክ እና ኢትዩ.እያስታወስቀ እንጂ አውርቶ ሕዝብን እንዳንተ ግራ በማጋባት ሳይሆን ተናግሮና ጽፎ አዎንታዊ ተፅእኖ ማሳደር ይሚችል እንጂ ይህን የክህደት ዘርህን እዛው አዳራሽክ ሄደክ ዝራ GOD BLESS HIM!!!

  ReplyDelete