Monday, October 31, 2011

የ"ሲኖዶስ" የተባለውና ማኅበረ ቅዱሳን በሚፈልገው መንገድ ቀርጾ ብዙ ገንዘብ በማፍሰስ ያስወሰነው ውሳኔ ተቃውሞ እየገጠመውና ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ መከፋፈል እንዳያመራ እያሰጋ መሆኑ በመገለጽ ላይ ነው፡፡ - - - READ PDF

በመንፈስ ቅዱስ ነው የሚመራው እየተባለ ሲነገርለት የኖረውና የቀደሙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም የሚሰጥና እግዚአብሔርን የሚያስከብር ውሳኔ ሲወስኑበት የቆዩት የጳጳሳት ጉባኤ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት 2004 ዓ.ም. ስብሰባው በታሪክ ተጠያቂ የሚያደርገውንና ቤተ ክርስቲያንን ወደ መከፋፈል ሊመራ የሚችል አሰፋሪ ውሳኔ መወሰኑ ብዙዎችን እያሳዘነና እያስቆጣ መምጣቱን ከየስፍራው የደረሱን ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን ልጅ ያለ አድልዎ በትክክለኛው መንገድ የመምራትና የማስተዳደር ኀላፊነት ቢኖርበትም፣ አሁን ያሉት ብዙዎቹ ጳጳሳት ይህን ሁሉን በእኩል አይን ተመልክቶ ትክክለኛ ፍትሕ የመስጠት ግዴታቸውን ባለመወጣትና በገንዘብ ተደልለው እውነትን መሸጣቸው ቤተ ክርስቲያኗን ትልቅ ኪሳራ ላይ የሚጥላትና እነርሱንም በታሪክም ተወቃሽ የሚያደርጋቸው መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

Sunday, October 30, 2011

ደጋፊ እንጂ አባል የሌለው ማህበር ማነው?

ደጋፊ እንጂ አባል የሌለው ማህበር ማነው?

by Dagnu Amde on Friday, October 28, 2011 at 1:39am
  • የማህበረ ቅድሳንን የሐሰት ፖሮፖጋንዳ አድምጠው ለሚነዱ የዋሐን
እንደ እውነቱ ከሆነ የላይ የላይ ዓላማውን ተመልክተው "ማኅበረ ቅዱሳን" ከቅዱሳን መላዕክት፣ ከቅዱሳን ሰማዕታትና ፃድቃን ረድኤት ያሳትፈናል ብለው በምኞት የሚከተሉት ወንድሞችና እህቶች እጅግ፣ እጅግ በጣም ሊታዘንላቸው ይገባል፡፡
 የክርስትና "ሀሁ" እውነትን ከመናገር፣ ለእውነት ከመመሥከር፣ ለእውነት መስዋዕት ከመሆን ይጀምራል፡፡ ነፍሳችን ውስጥ ለእውነት ቅንጣት ታህል ቦታ ካልሰጠን፣ ምንድነው ክርስትናችን? የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን መምጣቱ ስለእውነት አይደለምን? እርሱ ብርሃናችን ነው፤ እውነትም ከእርሱ ዘንድ ነው፤ እውነትም ፍቅር ነው፣ በፍቅሩ እኛን አከበረን፣ ክብርና ምሥጋና እስከ ዘለዓለም ድረስ ለእርሱ ይሁን፡፡

Saturday, October 29, 2011

የአቶ ማንያዘዋል ሲኖዶስ ታሪካዊ ስሕተት ፈጸመ

ገንዘብ ካለእንደሚባለው፣ ማኅበረ ቅዱሳን በገንዘብ የገዛቸውና ነውራቸውን ማስፈራሪያ አድርጎ ሲጠቀምባቸው የነበሩትን ጳጳሳት ተጠቅሞ ዕድሜውን ማራዘም መቻሉና የፈለገውን ማስወሰኑ ተገለጸ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ከትናንት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ሲወዛገብበት በነበረው የማኅበረ ቅዱሳን ህልውና እና የአባ ሠረቀ የማደራጃው መምሪያ ኀላፊነት ጉዳይ ዛሬ በዱላ ቀረሽ ውዝግብ ውሳኔ ያገኘ ይመስላል፡፡ አባ ሠረቀ ከቦታቸው እንዲነሡ፣ ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ እንዳይፈርስና መተዳደሪያ ደንቡ ተሻሽሎ ሥራውን እንዲቀጥል በገንዘብ የገዛቸውና በነፍስ ወከፍ 200 ሺህ ብር የከፈላቸው ሊቃነ ጳጳሳት ማኅበሩ የሰጣቸውን ተልእኮ በሚገባ ተወጥተው ለማኅበረ ቅዱሳን ለወሬ የሚመች ውሳኔ መወሰናቸውን፣ በእውነት ፊት ግን ታሪካዊ ስሕተት መፈጸማቸውንና የቤተ ክርስቲያናችን የመከራ ዘመን እንዲቀጥል መስማማታቸውን ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡

አድማው የባሰ ችግር ያመጣል

አድማው የባሰ ችግር ያመጣል

አጣሪ ኮሚቴውና አባ ማርቆስ ሌሎችም ጳጳሳት ያቀረቡትን እውነተኛ ሪፖርት ለመቀልበስ ሙከራ እየተደረገ ነው። ማህብረ ቅዱሳን በገንዘብ የገዛቸው፣ እንዲሁም በሚያጸይፍ ነገር በነውር ተገኝተው ማህበረ ቅዱሳን መረጃ የያዘባቸው ጳጳሳት፣ ይህን መረጃ ባደባባይ እናወጣዋለን በሚል ማስፈራሪያ ሳይወዱ በግድ የማህበረ ቅዱሳንን አጀንዳ ለማጽፈጸም እየተጣደፉ ነው።

  ነገር ግን ማህበረ ቅዱሳን ደብቄ ይዠዋለሁ የሚለው የጳጳሳቱ መረጃ [ነውር] አፈትልኮ በጃችን ገብቷል። ለማየትም ሆነ ለመስማት የሚዘገነን ነው። ምን አልባት ይህ ማስፈራሪያ መስሎአችሁ እንዳትሳሳቱ፣ መረጃው በጃችን ገብቷል። አድማውን ትታችሁ እውነተኛ መንፈሳዊ ውሳኔ የማትወስኑ ከሆነ ማህበረ ቅዱሳን የደበቀላችሁን እኛ ባደባይ እናሰጣዋለን።

 ጵጵስና እንዲህ መሬት እንደወደቀ ሸክላ ይህን ያህል መውረዱን በማየታችን እጅግ አዝነናል። ነገር ግን ንስሐ ይገባሉ፣ ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፣ በሚል እየጠበቅን ነበር። ኃጢአት የለብንም፣ ፖለቲከኞችም አይደለንም፣ ንጹሕ ቅዱስ ነን፣ እያላችሁ እውነትን የምትቃወሙ ከሆነ ግን እውነቱን እና ማንነታችሁን ለመላው ዓለም እንገልጣለን። አድማ ወይም አመጽ ቤተ ክርስቲያንን አያስተካክላትም። ይታሰብበት!

ሃይማኖቶች ስለፍርድ፦


የትኛውም ሃይማኖት በንድፈ ሃሳብ ደረጃ (theorically) ከሚያመልከው አምላክ ሕግና
ትእዛዝ ከወጣ ቁጣና ቅጣት እንደሚጠብቀው የወል የእምነት ስምምነት አለ። ይህንኑ ቅጣት
አስቀድሞ ለመከላከል በሕይወታቸው ሳሉ ያደርጉ ዘንድ የሰጣቸውን መመሪያ በሚችሉት አቅም
ሁሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ተግባራዊ ለማድረግ ደፋ ቀና ማለታቸውም አይቀሬ ይሆናል።
እንደዚያም ሆኖ ከሞተ በኋላ መልካሙ ሥራው መልካም ዋጋው ሆኖ ስለመከፈሉ ወይም ቁጣን
ስለመቀበሉ ማረጋገጥ አይችሉምና ከአጠገባቸው ለተለየው ሟች በመሪር ልቅሶና በልዩ ልዩ ዓይነት
የሥርዓት አቀባበር ሰውዬውን በመንከባከብ እንዲሁም በማሰማመር የልባቸውን ስሜት በጥሩ
መንፈስ ለመሙላት ይጥራሉ። ምግብና መጠጥ፤ ማብሰያ ቁሳቁስና አልባሳትን ጭምር እዚያ
በጉድጓዱ ከተማ እንዳይቸገር አብረው በመቅበር የችግሩ ልባዊ ተካፋዮች ለመሆን ሁሉን
ያደርጉለታል።

Friday, October 28, 2011

የቅዱስ ሲኖዶስ ምላተ ጉባኤ 4ኛ ቀን 18 አጀንዳ

በ17 አጀንዳ በጳጳሳት ሹመትና በአሜሪካኑ ሲኖዶስ እርቁ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ሰጥቶ ወደ 18ኛው አጀንዳ ትላንት ጥዋት የጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ በሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃና በማህበረ ቅዱሳን ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ክርክርና ውይይት የውሳኔ ኃሳብ ሲቀራቸው ለዛሬ አሳድረውታል፡፡
        ማህበሩ ሊፈርስ ይገባል በማለት የእለቱን አጀንዳ በጠንካራ አቋማቸው የገለፁት አቡነ ማርቆስ አክለውም ማህበረ ቅዱሳንን ከአምስት ጊዜ በላይ እንዳጣራ ኮሚቴ አባል ተደርጌ አውቃለሁ ቅዱስ ሲኖዶሱ የአቋም መለሳለስ አሳይቷል በማለት እስነማስረጃው ለሲኖዶስ አባላቶችን ጉድ እስኪያስብል ያቀረቡት ሪፖርት አባቶችን ከማን ጋር እየሰራን ነው ብለው አንዲያስቡና ማህበሩን እንደገና ሊመለከቱት እድል እንደሰጣቸው ብፁአን አባቶች በድፍረት ቃላት ተናግረዋል ፡፡
      አቡነ ማርቆስ ማህበሩ እንዲታገድና እንዲዘጋ ስጠይቅ ማስረጃ ሳይኖረኝ በጭፍን ጥላቻ አይደለም ብለው ማስረጃቸውንና ምክንያታቸውን ሲተነትኑ ማህበሩ በሶስት ነጥብ የቀለለ ነው
1.  የቀለጠ ሀብታም ነጋዴ ነው
2.  የፖለቲካ ድርጅት ነው
3.  ሐይማኖት የሌላቸው ግለሰቦች መሰባሰቢያና መሸሸጊያ ነው በማለት አብራርተዋል፡፡
       ይሁንና ለቀረቡት ሶስት ምክንያቶች ከብፁአን አባቶች ማስረጃ እንዲቀርብና ቅዱስ

Tuesday, October 25, 2011

የለውጥ ያለህ! - - Read PDF

አምላካችን እግዚአብሔር የለውጥ አምላክ ነው፤ ይህ ማለት ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከስሕተት ወደ ትክክለኛነት፣ ከሐሰት ወደ እውነት እንድንሻገር ይፈልጋል ማለት ነው፣ ብረት ሲዝግ ምንም ነገር መቁረጥ እንደማይችል ሁሉ የሰው አእምሮ ሲደፈን፣ ሐስት እውነት ሲመስል፣ ጨለማና ብርሃን ሲቀላቀሉ እግዚአብሔር ዝም አይልም። ግፍ ሲበዛ፣ ፍትሕ ሲጠፋ፣ ባዕድ አምልኮ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገባ እግዚአብሔር ይቆጣል። ሰይጣን በእንደዚህ ዓይነቱ ድቅድቅ ጨለማ ተሠውሮ ነገሥታቱን መኳንንቱና ፈራጆችን ለክፋት ሲጠቀምባቸው እግዚአብሔር ዝም አይልም። ከፍቅር ይልቅ ጥላቻ፣ ከሰላም ይልቅ ሁከት፣ ከአንድነት ይልቅ መለያየት፣ ሌብነት፣ ዘረኝነት፣ ጭቆና እና ባርነት ለእግዚአብሔር የሚያጸይፉ ርካሽ ነገሮች ናቸው።

ማኅበረ ቅዱሳን ከዐመፅ ተግባሩ ያተረፈው ኪሳራ መሆኑ ተገለጸ - Read PDF

30ኛውን የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤንና ከዚያ ቀጥሎ የሚካሄደውን የጥቅምት 2004 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባን ለግል አጀንዳው ማስፈጸሚያነት ለመጠቀም ቀደም ብሎ ሲዘጋጅ የነበረውና ልዩ ልዩ ስልቶችን ነድፎ ሲንቀሳቀስ የቆየው ማኅበረ ቅዱሳን ያሰበው ሁሉ ሳይደርስ ትክክለኛ ማንነቱ ፈጥኖ እየተገለጠ ልዩ ልዩ ኪሳራዎችን መከናነቡን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡

ጥንተ ተፈጥሮው ከሳሽነት ብቻ የሆነውና ለህልውናው አሥጊ ሆነው ያገኛቸውንናገበያ ዘጊበሚል የፈረጃቸውን ታዋቂ ሰባክያንንና ዘማርያንን በመክሰስ፣ የቅርብ ጊዜ ዲያብሎሳዊ አገልግሎቱን የጀመረው ማኅበረ ቅዱሳን፣ በታሪኩ አጋጥሞት የማያውቀውን ሽንፈት እያስተናገደ እንደሚገኝ ለማኅበሩ የጥፋት ተልእኮናከእኔ በቀር ሁሉም ተሳስቷል፣ መናፍቅ ነውለሚል ቅዠቱ እየተሰጠ ካለው ምላሽ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከዚህ ቀደም የጨለማው ክብደት አላሳይ ብሏቸውና የማኅበሩን ጨለማዊ ሥራ እንደ ጽድቅ ቆጥረዉለት ቀኝ እጃቸውን የሰጡት ሁሉ ዛሬ ፊታቸውን አዙረው ጀርባቸውን እየሰጡት እንደሚገኙ የሰሞኑ ሁኔታ በቂ ምስክር ነው፡፡